ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
Forwarded from Kidu via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
@Sellers and buyer
@ዱባይ ገበያ
@ available on hand
contact @Elu_jo
https://t.me/joinchat/AAAAAEPylbBjUwNq9_KGHQ
በዓል እንዴት እያለፈ ነወ?

@onlygirlsb

ንገሩኝ እስኪ
#አቢጊያ_ነኝ

#የዳሌ መስፋት በወሊድ ጊዜ በጣም #ምጥ እንደሚቀንስ እና በእርግዝና ጊዜ ደግሞ ለልጁ እንደሚጠቅም ታውቂያለሽ??

#share

💅 join join

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#የዳሌ መስፋት በወሊድ ጊዜ በጣም #ምጥ እንደሚቀንስ እና በእርግዝና ጊዜ ደግሞ ለልጁ እንደሚጠቅም ታውቂያለሽ??

#share

💅 join join

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
ስታይልሽ እንዴት አይነት ነው?

🎀ሚኒስከርት ይመችሻል?

🎀ሱሪ ነው ምታዘወትሪው?

🎀ብራስሌት ደስ ይልሻል?

🎀የራስሽ ምርጫ የሆኑ ጌጣጌጦች አሉሽ?
ለማንኛውም ምርጧ ሴት የሚያምርባትን የምታውቀዋ ናት። ስለዚህ አንዲት ጠንካራ ሴት እንደምታደርገው ለውጫዊ አስተያየት ደንታ ሳይኖርሽ ራስሽን መግለፅ አለብሽ።

እመኚኝ፡ መጪው ጊዜ አሪፍ ነው።

#share @onlyfemaleb
#ጤናሽ

ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ጠቃሚ የሆኑ 5 የምግብ አይነቶች

በአለማችን 350 ሚልዮን ሰዎች በጭንቀትና በድብርት እንደሚጠቁ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡ የተለያዩ ቫይታሚን፣ ንጥረ ነገሮችን (Minerals)፣ ጤናማ የቅባት አይነት የያዙ ምግቦች እንዲሁም ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርጉ (Antioxidants) ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ያግዛሉ ይላል #የሜዲካል_ዴይሊ_ዘገባ፡፡

ከዚህ በታች የተጠቀሱት የምግብ አይነቶች ከጭንቀትና ድብርትን ከማስወገድ ባሻገር ለጤናማ አእምሮ ስርዓትም አጋዥ ናቸው፡፡

1⃣ የዕህል ምግቦች

ሴሮቶኒን (Serotonin) የተሰኘው ንጥረ ነገር ንቁ እንዲንሆንና ዘና እንድንል የሚያደርግ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ሜላቶኒን ደግሞ ጤናማ የእንቅልፍ ስርዓት አንዲኖረን ያደርጋል፡፡ የዕህል ምግቦች ሴሮቶኒን እና ሜላቶኒን በአግባቡ በሰውነታችን ውስጥ እንዲኖር በማድረግ ጭንቀትና ድብርትን ለመቀነስ ድርሻቸውን ይወጣሉ፡፡

2⃣ ኮሮሪማ

ኮሮሪማ ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርግ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የተሰኘ (Antioxidants) በውስጡ ይገኛል፡፡ በተለይም ኮሮሪማን በጥሬው መመገብ ከጭንቀትና ድብርት በፍጥነት ለመውጣት እንደሚያግዝ ዘገባው ያስረዳል፡፡

3⃣ እንጆሪ 🍓

እንጆሪን መመገብ እራስን እስከማጥፋት ድረስ የሚያደርሰውን የጭንቀትና የድብርት አይነት ጭምር ለማስወገድ ጠቃሚ መሆኑን በቅርቡ የተደረገ ጥናት ያትታል፡፡ እንጆሪ ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርጉ (Antioxidants) ጨምሮ በቫይታሚን ሲ የበለጸገ በመሆኑ ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ተመራጭ ምግብ መሆኑን ዘገባው ገልጿል፡፡

4⃣ እርጎ 🥤 እና እንቁላል 🥚

እርጎና እንቁላል ጭንቀትና ድብርትን ማስወገድ የሚችሉ ምጣኔያቸውን የጠበቁ የፕሮቲንና የካርቦሃይድሬት ምጣኔ ያካተቱ የምግብ አይነት ናቸው፡፡ እርጎና እንቁላል የደም ስኳር መጠን ሚዛኑን ጠብቆ እንዲሄድም በማድረግም ጭምር ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ሚናቸውን ይወጣሉ፡፡

5⃣ ጥቁር ቸኮሌት 🍫

ጥቁር ቸኮሌት ዶፓማይን (Dopamine) የተሰኘ አይምሮዋች የደስታ ስሜት እንዲሰማው የሚያደርግ ንጥረ ነገር አካቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የደስታ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርገውን እንዶሮፊንስም (Endorphins) ጭምር በውሰጡ ይገኛል፡፡ ጥቁር ቸኮሌት ከተጠቀሱት በተጨማሪ የሰውነታችንን የኮሊስትሮል መጠን የመቀነስ ሚናም ሲለሚጫወት ጭንቀትና ድብርትን የማስወገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የሜዲካል ዴይሊ ዘገባ ያስረዳል፡፡

♨️ ለሌሎች ሼር ያድርጉ❗️
@onlyfemaleb
BOSS COLLECTION
High quality products
Contact @janajan1
Call 0921273990
https://t.me/BOSS_COLLECTION
#አቢጊያ_ነኝ
👩🏽‍🦰👱🏽‍♀️የፀጉር መርገፍ👱🏽‍♀️👩🏽‍🦰

የፀጉር መርገፍ በጭንቅላታችን ላይ ያለን ፀጉር ብቻ ሳይሆን ሌላ አካላቶቻችን ላይ ያለን ፀጉር ያጠቃልላል፡፡

ለዛሬ የፀጉር መርገፍ መንስኤዎችን እና የፀጉር መርገፍን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገራለን፡፡

#መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

👉🏾 በዘር፡- ሴቶች ላይ የፀጉር መሸሽ እና መሳሳት
👉🏾 ሰውነታችንን በሚያጠቁ በሽታዎች፡- የታይሮይድ ህመሞች፣ የካንሰር ህመሞች
👉🏾 መድሃኒቶች፡- የካንሰር ህክምናዎች
እጅግ በጣም የሚያጠብቅ ሹሩባ
👉🏾 የአእምሮ ጭንቀት
👉🏾 ለፀጉር እድገት የምንጠቀማቸው ግብአቶች

ስለመንስዔው ማወቅ የፀጉር መርገፍን እንዴት መከላከል እንዳለብን ለማወቅ እጅግ ይረዳናል፡፡

🗒 #ፀጉራችን ከመርገፉ በፊት የምናያቸው ምልክቶች...🗒

-የፀጉር መሳሳት
-በአንዳንድ የፀጉራችን ክፍል ውስጥ ባዶ የሆኑ ቦታዎች መኖር
-ፀጉራችንን በምናበጥርበት ወይም በምንታጠብበት ጊዜ የሚታይ የፀጉር መርገፍ

የፀጉር #መርገፍን ለመከላከል ወይንም ለመቀነስ ማድረግ ያሉብን ነገሮች

-ለፀጉር የምንጠቀማቸው ግብአቶች ከተፈጥሮ የተሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ
-ሹሩባ በምንሰራበት ወቅት ላላ አድርጎ መሰራት
-ጭንቀታችንን ለቅርብ ለምንለው ሰው ማውራት
-በበሽታዎችና በመድሃኒቶች የሚመጡ የፀጉር መርገፎችን ከሃኪማችን ጋር በመነጋገር ማስተካከያዎችን ማድረግ
-እንደ ፊታችን ሁሉ ፀጉራችንንም መንከባከብ

ፀጉራችንን እንዴት #መንከባከብ ይኖርብናል?

👉🏾 #ማንኛውም ነገር ለማደግ ግብአት እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለፀጉርም ግብአት ያስፈልጋል፡፡ ፀጉራችንን በንፅህና መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚመቸንን ሻምፖ እና ኮንዲሽነር በመሞከር ፀጉራችን ላይ የሚመጣውን ለውጥ ማስተዋል፤ የምንጠቀማቸው ግብአቶች ሰልፌት የሌላቸው መሆኑን በእቃው ላይ የሚፃፈውን ንጥረ ነገር ማየት ይኖርብናል፡፡

👉🏾 #ለፀጉራችን የሚስማማንን ቅባት መለየት፤ ፀጉር ከሰው ሰው ስለሚለይ እኛም ለፀጉራችንን የሚስማማንን ፀጉር በምናየው ለውጥ መወሰን ይኖርብናል፡፡
ለፀጉራችን ቢያንስ በ2 ሳምንት አንድ ጊዜ የተለየ እንክብካቤ ማድረግ ማለትም አቮካዶ፣ እርጎ፣ ቅቤን ፀጉር ላይ በመቀባት መንከባከብ ይኖርብናል።

@onlyfemaleb

#join #join #join

በቀጣይም ብዙ የጤና መረጃዎችን እነግርሻለው።
ላንቺ ብቻ
Photo
#አቢጊያ_ነኝ

#የቆዳ_ሸንተረርን_ማጥፋት_ይችላል ?
ሁሉም ሰው የቆዳ ሸንተረር ቢጠፋልኝ ብሎ ያስባል። ቆዳ ላይ የሚፈጠር ሸንተረር ጤና ላይ የሚፈጥረው ችግር ባይኖርም ለእይታ አይስብም።
የቆዳ ሸንተረር ሙሉ በሙሉ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ነገር ግን ከግዜ በኋላ ትልቀቱ እየቀነሰ ይመጣል።

#መንስኤዎች
ሸንተረር የሚፈጠረው ቆዳችን በፍጥነት በሚያድግበት ግዜ ነው። ሰውነት በሚያድግበት ፍጥነት ቆዳ አብሮ መለጠጥ ሲያቅተው ሸንተረር ይፈጠራል። እነዚህ ሸንተረሮች በህክምናው ቋንቋ ስትሪያ(stria) ተብለው ይጠራሉ።
ኮላጅን ቆዳ ተላጣጭ እንዲሆን የሚረዳ ፕሮቲን ነው። ቆዳ በቂ ኮላጅን ከሌለው በሚለጠጥበት ግዜ ሸንተረር ይፈጠራል።
የሚከተሉት ምክንያቶች የሸንተረር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፦
#በፍጥነት ክብደት መጨመር
#እርግዝና
#ሰውነትን ማጎልመስ
#ከፍተኛ የሰውነት ስቴሮይድ
#ሸንተረር በዘርም የሚተላለፍ ክስተት ነው።

#ማን_ላይ_ይከሰታል ?
ሸንተረር ይበልጥ በሴቶች ላይ ይፈጠራል። በተለይ በእርግዝና ግዜ። በልጅ ምክንያት ሆድ ሲለጠጥ ሸንተረር ሊወጣ ይችላል።
ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ ክብደት ስትቀንስ ሸንተረሩ አብሮ ሊቀንስላት ይችላል።
ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ጭማሪ የሚያመጡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ሸንተረር ሊፈጠርባቸው ይችላል። በልጅነት እድሜም ልጆች በፍጥነት በሚያድጉበት ግዜ ሸንተረር ሊፈጠርባቸው ይችላል።
ሸንተረር በሚከተሉት የሰውነት አካላት ላይ ሊፈጠር ይችላል፦
#እጅ
#ጀርባ
#ጡት
#መቀመጫ
#ዳሌ
#ትከሻ
#ሆድ
#መፍትሄዎች
ሸንተረርን ያጠፋሉ ተብለው የሚሸጡ በርካታ ክሬሞች እና መድሃኒቶች አሉ። ውጤታማነታቸው ግን አጠያያቂ ነው።
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#የእከክ_በሽታ_መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች
እከክ በአይን የማይታዩ “ሳርኮፕተስ” በሚባሉ ተዋስያን አማካኘነት የሚመጣ የቆዳ በሽታ ነው፡፡
ይህ የቆዳ በሽታ በበሽታው ከያዘው ጋር በጋራ ልብስ መልበስ፤በጋራ በመተኛትና እንዲሁም በንኪኪ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ሊተላለፍ የሚችል በሽታ ነው፡፡
የበሽታው ምልክቶች
-በከፍተኛ ሁኔታ የማሳከክና በቆዳ ላይ ሽፍታን ማሳየት
-ማሳከኩም በተለይ ማታ ላይ ያይላል
-የበሽታው ነብሳት በቆዳችን ውስጥ ለመራባት በሚመቻቸው ትንሽ መስመር ውስጥ እንቁላል በመጣል ይራባሉ፡፡
በመሆኑም እንቁላሉ ወደ ላይኛው ቆዳ ላይ በመውጣት ትናንሽ መግል የያዘ ሽፍታ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
የሚያሳክኩት የሰውነታችን ክፍሎችም፡-
 ብብት
 በየመገጣጠሚያ አካላት
 በክርን
 ተረከዝ
 ጡት እና
 በመራቢያ አካላትና ጉልበት አካላ አካባቢ ነው፡፡
በህጻናት ላይ ደግሞ
 በጸጉር ቆዳ፤በፊት ላይ፤አንገት፤እጅና እግር አከባቢ በከፍተኛ ይከሰታል፡፡
የእከክ በሽታን ባለመታከም ምክንያት ሊደርሱ የሚችሉ በሽታዎች
 እከክን ባለመታከም ሌሎች በተለያዩ ባክቴሪያዎች የሚመጡ ለቆዳ በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል
 በተጨማሪም የበሽታ መከላከል አቅማቸው አናሳ/ የወረደ ሰዎች፤ ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ እና ካንሰር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ በአስከፊ ሁኔታ ሙሉ የሰውነት ቆዳን ሊያዳርስ ይችላል፡፡
#በሽታውን ለመከላከል
• ከቤተሰብ ውስጥ ቀድሞ የተያዘውን ሰው ቶሎ ማሳከም
• ልብስ በጋራ/ተቀባብሎ አለመልበስ
• በበሽታው የተያዘ ሰው ታክሞ እስከሚድን ድረስ የአካል ንክኪ አለማድረግ
• የእከክ በሽታ ከታከምን በቀላሉ ሊያድን ቢችልም በሃኪም የተሰጡን መድሓንቶችና ተያያዥ ምክሮች በአግባቡ መጠቀም/ ስራ ላይ መዋል ይገባል፡፡

@onlyfemaleb

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
ስለ #ብልት መታጠን መረጃ
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
#የማህፀን_ውስጥ_እጢ

የማህፀን ዕጢ የምንለው የካንሰርነት ባሕርይ የሌለው የማሕፀን ውስጥ ዐዥባጭ
ሲሆን በአብዛኛው የሚከሰተው በወጣትነት ዕድሜ ላይ ነው፡፡ የማህፀን ውስጥ ዕጢ
ወደ ማኅፀን ካንሰርነት የመለወጥ ዕድሉ እጅግ በጣም አናሳ ነው፡፡
የማሕፀን ዕጢ ከማሕፀን ግድግዳ ጡንቻዎች የሚነሳ ሲሆን የሴሎች ጤናማ ባልሆነ
ሆኑታ ሲከፈሉ የሚመጣ ሆኔታ ነው፡፡ ይህ የማሕፀን ዕጢ በፍጥነት የሚያድግ ወይንም
በዝግታ የሚያድግ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ተመልሶ በራሱ ሊጠፈም
ይችላል፡፡
የማሕፀን ዕጢ በሴቶች ላይ እጅግ የተለመደ በመሆኑ ምክንያት ከ4 ሴቶች ሦስቱ
በሕይወት ዘመናቸው የማሕፀን ዕጢ እንደሚኖራቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን
ምልክት ስለማያሳዩ እንዳላቸውም የማወቅ ዕድል የላቸውም፡፡ በአብዛኛው የሚገኘው
በድንገት በሚደረግ ምርመራ ነው፡፡
የማሕፀን ዕጢ ምልክቶች
የማኅፀን ዕጢ በአብዛኛው ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳይ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች
ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች እንዚህ ናቸው፡፡
• ከፍተኛ የሆነ የወር አበባ መብዛት
• ከሰባት ቀናት በላይ የሚቆይ የወር አበባ ማየት
• ማሕፀን አካባቢ ግፊት መሰማት ወይንም ሕመም
• ቶሎ ቶሎ የውሃ ሽንት መምጣት
• የሆድ ድርቀት
• የጀርባ እና የዕግር ሕመም ስሜት
• አልፎ አልፎ ከፍተኛ የሆነ ሕመም (አጣዳፊ) የሚያስከትል ሲሆን ይህም የሚሆነው
የደም ዝውውር በሚቀንስ ጊዜ/በሚቋረጥ ጊዜ ነው፡፡
የማሕፀን ዕጢ ለምን ይከሰታል
ይህ ነው የሚባል ዕርግጥ ምክንያት የሌለው ቢሆንም ጥናቶች የሚያመለክቷቸው
ከሆርሞኖች እና የጀኔቲክ ሁኑታዎች ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው ነው፡፤
ለማሕፀን ዕጢ ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁኔታዎች
• ከዘር፡- እናት ወይንም እሕት የማሕፀን ዕጢ ወደ ዘር ካላቸው ተጋላጭነትን
ይጨምራል፡፡
• ጥቁር ዘር፡- ጥቁር ሴቶች በአብዛኘው ተጋላጭነታቸው ይጨምራል፡፡
• በልጅነት የወር አበባን ያዩ ከሆነ እና አመጋገብ ናቸው፡፡
የማኅፀን ዕጢ ለከፋ የጤና ችግር የሚዳርግ ባይሆንም የደም ማነስ እና ምቾት
ማጣትን ግን ሊያስከትል ይችላል፡፡
የማሕፀን ዕጢ እና እርግዝና
የማሕፀን ዕጢ በአብዛኛው እርግዝናን የማይቃረን ቢሆንም አንዳንዴ ዕጢው
በሚገኝበት ቦታምክንያት በጥቂት ሰዎች ላይ እርግዝናን እንዳይፈጠር መንስዔ
ይሆናል፡፡ ይህ በመሆን ጊዜ ሐኪምን በማማከር ከእርግዝና በፊት መደረግ ያለባቸውን
ቅድመ ሆኔታዎች ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?
• የማያቋርጥ የማሕፀን አካባቢ ሕመም ካለ
• ከፍተኛ ሕመም ያላቸውና በብዛት የሚያስቸግሩ የወር አበባ ጊዜያት
• ከወር አበባ ፅዳት ውጪ የደም መፍሰስ
• በግብረ ስጋ ግኝኑነት ጊዜ የሕመም ስሜት ከተሰማዎተግ
• የሆድ ዕብጠት ካለዎዘ
• የውኃ ሽንትን ማስወገድ መቸገር
እጅግ ከፍተኛ የሆነ ድንገተኛ የማኅፀን አካባቢ ሕመም ካለዎትና ከፍተኛ የደም መፍሰስ
የሚኖር ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
Forwarded from Najwa
Najwa Henna design
💐You think it, I ink it
Henna is the expression of beauty without wordsLet me make you glow on special day for
Wedding👰
Nikah💍
Parties 💃
Birthdays 🎂
Holliday's....for more information you can contact me by this no 0923776030
@NajwaNasir
https://t.me/hennabynajwa