ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
#አቢጊያ_ነኝ

እንዴት ናቹልኝ የኔ ውዶች ከዚህ ቀን በኋላ #online የማማከሪያ ሰዓት ዘውትር ሰኞ እስከ እሁድ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት
ምን አልባት ስራ አዳሪ በምሆንበት ቀን ላልኖር እችላለው።
ከ online ውጪ ማለትም text ባየሁ ቁጥር ለመመለስ በማንኛው ሰዓት እናንተን ለመርዳት እና ለማገዝ ተዘጋጅቻለው።
#ቤተሰብ
#ትምህርት_እና_ስራ
#ፍቅር
#ጤንነት
#ጓደኝነት
#ሴትነት
#ወሲብ
#እንዲሁም ማንኛውንም ሀሳብ መመካከር እንችላለን መጪው ጊዜ የእኔ እና የአንቺ ነው።
ሚስጥር ጠባቂነቴ እስከ አሁን ባማከርኳቸው እህቶቼ ታይቷል ተመስግኛለው።
#እስካሁንም እጅግ በርካታ ሴቶችን online አማክሬአለው

#አንቺስ??

💯 አንድ % ሚስጥራቹ ይጠበቃል

@onlygirlsb

ላይ ማንኛውንም ሀሳብ ማንሳት መብታቹ ነው።

#share #share
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#የጨጓራ_በሽታ_ቀላል_መፍትሔዎች

#1. ቆስጣ እና ካሮት - የቆስጣ ጁስ እና የካሮት ጁስን በመደባለቅ መጠጣት
#2. ኬክ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለመጠቀም
#3. ዝንጅብል -አነስተኛ የዝንጅብል ክፍል ወስዶ ከምግብ በፊት መውሰድ የምግብ ልመትን ያፋጥናል በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያን ያክማል፡፡
4. እርጎ -በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሠት የጨጓራ ህመም ተመራጭ ነው፡፡
5. ድንች - ግማሽ ብርጭቆ የድንች ጁስን በቀን 3 ጊዜ ምግብ ከመመገብ 15 ደቂቃ በፊት መጠጣት
6. ውሃ - በቀን ከ8-10ብርጭቆ ውሃ መጠጣት
7. በፆም ወቅት ፍሬሽ የሆኑ የፍራፍሬ ጁሶችን መጠቀም ለምሳሌ ወይን ብርቱካን አፕል ፓፓያ…
8. ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ አለመመገብ ምክንያቱም ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ የምግብ ልመትን ስለሚያዘገይ ትንሽ ትንሽ ምግብ ሠአትን ጠብቆ መመገብ
9. ሁል ጊዜ በባዶ ሆድ የሞቀ ውሃ መጠጣት
10. በአንድ ገበታ ላይ የተለያዩ ምግቦችን አደባልቀው አለመመገብ
11. ከመተኛቶ 2 ሠዓት በፊት እራት መመገብ
12. በቫይታሚን ቢ12 እና አይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
13. ስጋና የስጋ ተዋፅዎ መቀነስ በተለይ ለእራት አለመጠቀም
14. አልኮል ሲጃራና ጫትን አለመጠቀም
15. ቡናና ሻይ መቀነስ
16. በሀኪም ያልታዘዙ መድሀኒቶች አለመውሰድ
17. ቅመማ ቅመም መቀነስ
18. ከዛሬ ጀምረው ይተግብሩት፣

@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

Happy New year

#2020
​​#ስለ_ጤናሽ

➡️ለጥርስ ህመም የመጀመሪያ ህመም እርዳታ

አንቺ ሊተገብሪያቸው የምትቺይው ምክሮች:-

ሞቅ ባለ ውሀ አፍሽን መጉመጥምጥ

በጥርስ መጎርጎሪያ በጥርስሽ መካከል የቀሩ የምግብ ትራፊዎችን ማውጣት

ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት መውሰድ

ወደ ጥርስ ህክምና መሄድ ያለብሽ...

ከጥርስ ህመሙ ጋር ትኩሳት ካለ

ህመሙ ከአንድ ቀን እና ከዚያ በላይ ከቀጠለ

በአተነፋፈስሽ ላይ ወይም ምግብ ስትውጪ ከተቸገርሽ

የእንፌክሽን ምልክቶች ካለ ለምሳሌ እብጠት ካለ፤ ምግብ ሲመገቡ ህመም ካለ፤ የድድ መቅላት ወይም ሽታ ያለው ፈሳሽ ካለዎት ሀኪም አማክሪ የኔ እህት።

#share #share
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#ስለ_ጤናሽ

ለፀጉራችን ምን ዓይነት እንክብካቤ ማድረግ እንችላለን?

1. ፀጉራችንን በየሳምንቱ የመታጠብ ልምድ ማዳበር ይኖርብናል፤ ይህን የማድረግ ጥቅሙ በፀጉራችን ላይ የተጠራቀመውን የፀጉር ቅባቶችን ከላብ ጋር አንድ ላይ በመሆን ፀጉራችንን እንዳያቆሽሹ እና ለፎሮፎር እንዳንጋለጥ ይረዳናል፡፡

2. ኮንዲሽነር (conditioner) መጠቀም፡- የዚም ጥቅም የሚሆነው ፀጉራችንን ካለምንም ችግር ማበጠር እንድንችል ያደርገናል በተጨማሪም ለፀጉራችን ልስላሴ ይሠጠዋል፡፡ ኮንዲሽነር ስንጠቀም በፀጉራችን ጫፍ ላይ በመጀመር ወደሌላው ማዳረስ ይቻላል፡፡

3. ፀጉራችንን ከድርቀት ለመከላከል እንዲሁም የፀጉርን ወዝና ልስላሴ ለመጠበቅ የተለያዩ ገበያ ላይ ያሉ ትሪትመንት ቅባቶችን በወር ከአንድ እስከ ሁለት ጊዜ መጠቀም ጥቅሙ የበዛ ነው፡፡

4. ፀጉር ቤት ወይም ቤት ሆነ ፀጉራችንን በእሳት/ፔስትራ ከመሰራታችን በፊት heat protector products መጠቀም ፀጉራችንን ከጉዳት ይከላከለዋል፡፡

5. ፀጉራችንን ራሳችን ቤት ውስጥ የምንሠራ ከሆነ (ተኩስ) ፀጉራችንን በሳምንት ከአንድ ጊዜ በላይ ለእሳት/ፔስትራ ማጋለጥ የለብንም፡፡

6. ሹሩባ በምንሠራበትም ጊዜ ፀጉራችን መጥበቅ የለበትም፡፡ ፀጉራችን በሚጠብቅበት ጊዜ ፀጉር ስለሚጎዳ ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል፡፡

ሴትነት ሳይንስ ነው፡ ስለዚህ በጥበብ እንኑረው።
@onlyfemaleb
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Kidu via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
@Sellers and buyer
@ዱባይ ገበያ
@ available on hand
contact @Elu_jo
https://t.me/joinchat/AAAAAEPylbBjUwNq9_KGHQ
በዓል እንዴት እያለፈ ነወ?

@onlygirlsb

ንገሩኝ እስኪ
#አቢጊያ_ነኝ

#የዳሌ መስፋት በወሊድ ጊዜ በጣም #ምጥ እንደሚቀንስ እና በእርግዝና ጊዜ ደግሞ ለልጁ እንደሚጠቅም ታውቂያለሽ??

#share

💅 join join

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#የዳሌ መስፋት በወሊድ ጊዜ በጣም #ምጥ እንደሚቀንስ እና በእርግዝና ጊዜ ደግሞ ለልጁ እንደሚጠቅም ታውቂያለሽ??

#share

💅 join join

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
ስታይልሽ እንዴት አይነት ነው?

🎀ሚኒስከርት ይመችሻል?

🎀ሱሪ ነው ምታዘወትሪው?

🎀ብራስሌት ደስ ይልሻል?

🎀የራስሽ ምርጫ የሆኑ ጌጣጌጦች አሉሽ?
ለማንኛውም ምርጧ ሴት የሚያምርባትን የምታውቀዋ ናት። ስለዚህ አንዲት ጠንካራ ሴት እንደምታደርገው ለውጫዊ አስተያየት ደንታ ሳይኖርሽ ራስሽን መግለፅ አለብሽ።

እመኚኝ፡ መጪው ጊዜ አሪፍ ነው።

#share @onlyfemaleb
#ጤናሽ

ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ጠቃሚ የሆኑ 5 የምግብ አይነቶች

በአለማችን 350 ሚልዮን ሰዎች በጭንቀትና በድብርት እንደሚጠቁ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡ የተለያዩ ቫይታሚን፣ ንጥረ ነገሮችን (Minerals)፣ ጤናማ የቅባት አይነት የያዙ ምግቦች እንዲሁም ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርጉ (Antioxidants) ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ያግዛሉ ይላል #የሜዲካል_ዴይሊ_ዘገባ፡፡

ከዚህ በታች የተጠቀሱት የምግብ አይነቶች ከጭንቀትና ድብርትን ከማስወገድ ባሻገር ለጤናማ አእምሮ ስርዓትም አጋዥ ናቸው፡፡

1⃣ የዕህል ምግቦች

ሴሮቶኒን (Serotonin) የተሰኘው ንጥረ ነገር ንቁ እንዲንሆንና ዘና እንድንል የሚያደርግ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ሜላቶኒን ደግሞ ጤናማ የእንቅልፍ ስርዓት አንዲኖረን ያደርጋል፡፡ የዕህል ምግቦች ሴሮቶኒን እና ሜላቶኒን በአግባቡ በሰውነታችን ውስጥ እንዲኖር በማድረግ ጭንቀትና ድብርትን ለመቀነስ ድርሻቸውን ይወጣሉ፡፡

2⃣ ኮሮሪማ

ኮሮሪማ ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርግ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የተሰኘ (Antioxidants) በውስጡ ይገኛል፡፡ በተለይም ኮሮሪማን በጥሬው መመገብ ከጭንቀትና ድብርት በፍጥነት ለመውጣት እንደሚያግዝ ዘገባው ያስረዳል፡፡

3⃣ እንጆሪ 🍓

እንጆሪን መመገብ እራስን እስከማጥፋት ድረስ የሚያደርሰውን የጭንቀትና የድብርት አይነት ጭምር ለማስወገድ ጠቃሚ መሆኑን በቅርቡ የተደረገ ጥናት ያትታል፡፡ እንጆሪ ሰውነታችን ያጠራቀመውን ምግብ በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያደርጉ (Antioxidants) ጨምሮ በቫይታሚን ሲ የበለጸገ በመሆኑ ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ተመራጭ ምግብ መሆኑን ዘገባው ገልጿል፡፡

4⃣ እርጎ 🥤 እና እንቁላል 🥚

እርጎና እንቁላል ጭንቀትና ድብርትን ማስወገድ የሚችሉ ምጣኔያቸውን የጠበቁ የፕሮቲንና የካርቦሃይድሬት ምጣኔ ያካተቱ የምግብ አይነት ናቸው፡፡ እርጎና እንቁላል የደም ስኳር መጠን ሚዛኑን ጠብቆ እንዲሄድም በማድረግም ጭምር ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ ሚናቸውን ይወጣሉ፡፡

5⃣ ጥቁር ቸኮሌት 🍫

ጥቁር ቸኮሌት ዶፓማይን (Dopamine) የተሰኘ አይምሮዋች የደስታ ስሜት እንዲሰማው የሚያደርግ ንጥረ ነገር አካቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የደስታ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርገውን እንዶሮፊንስም (Endorphins) ጭምር በውሰጡ ይገኛል፡፡ ጥቁር ቸኮሌት ከተጠቀሱት በተጨማሪ የሰውነታችንን የኮሊስትሮል መጠን የመቀነስ ሚናም ሲለሚጫወት ጭንቀትና ድብርትን የማስወገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የሜዲካል ዴይሊ ዘገባ ያስረዳል፡፡

♨️ ለሌሎች ሼር ያድርጉ❗️
@onlyfemaleb
BOSS COLLECTION
High quality products
Contact @janajan1
Call 0921273990
https://t.me/BOSS_COLLECTION
#አቢጊያ_ነኝ
👩🏽‍🦰👱🏽‍♀️የፀጉር መርገፍ👱🏽‍♀️👩🏽‍🦰

የፀጉር መርገፍ በጭንቅላታችን ላይ ያለን ፀጉር ብቻ ሳይሆን ሌላ አካላቶቻችን ላይ ያለን ፀጉር ያጠቃልላል፡፡

ለዛሬ የፀጉር መርገፍ መንስኤዎችን እና የፀጉር መርገፍን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገራለን፡፡

#መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

👉🏾 በዘር፡- ሴቶች ላይ የፀጉር መሸሽ እና መሳሳት
👉🏾 ሰውነታችንን በሚያጠቁ በሽታዎች፡- የታይሮይድ ህመሞች፣ የካንሰር ህመሞች
👉🏾 መድሃኒቶች፡- የካንሰር ህክምናዎች
እጅግ በጣም የሚያጠብቅ ሹሩባ
👉🏾 የአእምሮ ጭንቀት
👉🏾 ለፀጉር እድገት የምንጠቀማቸው ግብአቶች

ስለመንስዔው ማወቅ የፀጉር መርገፍን እንዴት መከላከል እንዳለብን ለማወቅ እጅግ ይረዳናል፡፡

🗒 #ፀጉራችን ከመርገፉ በፊት የምናያቸው ምልክቶች...🗒

-የፀጉር መሳሳት
-በአንዳንድ የፀጉራችን ክፍል ውስጥ ባዶ የሆኑ ቦታዎች መኖር
-ፀጉራችንን በምናበጥርበት ወይም በምንታጠብበት ጊዜ የሚታይ የፀጉር መርገፍ

የፀጉር #መርገፍን ለመከላከል ወይንም ለመቀነስ ማድረግ ያሉብን ነገሮች

-ለፀጉር የምንጠቀማቸው ግብአቶች ከተፈጥሮ የተሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ
-ሹሩባ በምንሰራበት ወቅት ላላ አድርጎ መሰራት
-ጭንቀታችንን ለቅርብ ለምንለው ሰው ማውራት
-በበሽታዎችና በመድሃኒቶች የሚመጡ የፀጉር መርገፎችን ከሃኪማችን ጋር በመነጋገር ማስተካከያዎችን ማድረግ
-እንደ ፊታችን ሁሉ ፀጉራችንንም መንከባከብ

ፀጉራችንን እንዴት #መንከባከብ ይኖርብናል?

👉🏾 #ማንኛውም ነገር ለማደግ ግብአት እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለፀጉርም ግብአት ያስፈልጋል፡፡ ፀጉራችንን በንፅህና መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚመቸንን ሻምፖ እና ኮንዲሽነር በመሞከር ፀጉራችን ላይ የሚመጣውን ለውጥ ማስተዋል፤ የምንጠቀማቸው ግብአቶች ሰልፌት የሌላቸው መሆኑን በእቃው ላይ የሚፃፈውን ንጥረ ነገር ማየት ይኖርብናል፡፡

👉🏾 #ለፀጉራችን የሚስማማንን ቅባት መለየት፤ ፀጉር ከሰው ሰው ስለሚለይ እኛም ለፀጉራችንን የሚስማማንን ፀጉር በምናየው ለውጥ መወሰን ይኖርብናል፡፡
ለፀጉራችን ቢያንስ በ2 ሳምንት አንድ ጊዜ የተለየ እንክብካቤ ማድረግ ማለትም አቮካዶ፣ እርጎ፣ ቅቤን ፀጉር ላይ በመቀባት መንከባከብ ይኖርብናል።

@onlyfemaleb

#join #join #join

በቀጣይም ብዙ የጤና መረጃዎችን እነግርሻለው።