ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
#አቢጊያ_ነኝ

አዲስ ሰው ተዋውቀሽ ካፌ/ሬስቶራነት ውጥ አብረሽው ገብተሻል? እናም የልጁን/የሰውዬውን ጥሩ ሰው መሆን አለመሆን ማወቅ ትፈልጊያለሽ? እንግዲያውስ ለአስተናጋጁ የሚሰጠውን ትህትና እና ንቀት ብቻ ተመልከቺ፡ በቂ ፍንጭ ታገኚያለሽ፡፡
🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
💁‍♀ስለ Eye Glass እናውራ

👓🕶👓🕶👩‍🏫🕶👓🕶👓🕶

ሶስት አይነት መነፅር ተጠቃሚዎች አሉ፤ Active users, Passive users እና semi-active users የሚባሉ ማለት ነው፡፡ በአማርኛ አዘውታሪዎች፣ ከፊል አዘውታሪዎች እና አልፎ አልፎ ተጠቃሚዎች እንደማለት ነው፡፡
አዘውታሪዎች የሚባለው ብዙውን ጊዜ በሃኪም ወይም በአዋቂ ትዕዛዝ ከእንቅልፍ ሰዓት ባለው ጊዜ ሁሉ መነፅርን የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች መነጽሩ በቃ አንዱ የመልካቸው ገፅታ ይሆናል ማለት ነው፡፡ መነፅሮቹ ለ long sighted ወይም short sighted የሚታዘዙ አይነቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ከፊል ተጠቃሚዎች የሚባሉት ደግሞ ለምሳሌ ኮምፒውተር ለመጠቀም እና ወረቀቶችን ለማንበብ በሚፈልጉበት ጊዜ ሁሉ መነፅር የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ እነዚህ መነፅሮች የብርሃን መቀነሻ እና ማጉያ አይነት ስራ ያላቸው መነፅሮች ናቸው፡፡
አልፎ አልፎ ለመድረክ (ፕረዘንቴሽን) ፕሮቶኮል፣ ለፀሃይ ለስራ ደህንነት አልያም ለፋሸን ሊጠቀሙት ይችላሉ፡፡
እንደሚመስለኝ እህቴ አዘውታሪዎች ከሚባሉት ተርታ ነች፡፡ እስኪ መነፅር ስለሚያሳድረው የስነልቦና ለውጥ እንመልከት፡፡
ትዝ ይለኛል የሆነ ጊዜ የሳይኮሎጂ መምህራችን ክፍል ውስጥ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ጠንከር ያለ የክርክር ርዕስ ከፍቶ እንደነበር ትዝ ይልኛል፡፡ በወቅቱ እኔ ስከራከር የነበረው መነፅር በባለመነፅሩ ላይ አሉተዊ ተፅዕኖ ያሳድራል የሚል ነበር፡፡ ክርክሬን በማስረጃ አስደግፌ ተማሪዎቹን በሚገባ ማሳመኔ ማሳመኔ ትዝ ይለኛል፡፡ ነገር ግን ያን መምህራችን መጨረሻ ላይ የነገረን ነገር ስለ መነፅር የነበረኝን አመለካከት ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ተቀየረ፡፡ እስካሁን ድረስም ይህን አመለካከቴን ትክክል መሆኑን በየዕለቱ ማረጋገጥ ችያለው፡፡

በቅድሚያ መነፅር በማድረግ ውስጥ ምናልናት ሊድርሱ የሚችሉ ተፅኖዎችን እንለይ፡፡ መነፅር ስታደርጊ ከወትሮው በተለየ ይበለጥ ጭምት( Gentle woman) ያርግሻል፡፡ ማለትም ሳታደርጊ ከነበረው ጊዜ ያነሰ ቅልጥፍና እና ነፃነት ነው የሚኖርሽ፡፡ እናም መነፅር ስታደርጊ ዋና ትኩተርሽ ወደፊት ብቻ ስለሚሆን ከጎንሽ እና ከጀርባሽ ላለው ነገር አነስተኛ ትኩረት( Attention ) ነው የሚኖርሽ፡፡
ሌላው አሁን የምነግርሽ ነገር አሉተዊ ይሁን ወንታዊ ተፅዕኖ ይሁን አላውቅም ብቻ እውነታው ወንዶች ሳይኮሎጂካሊ መነፅር የሚያደርጉ ሴቶችን ላማናገር ለመተዋወቅ ለመቃለድ ያላቸው ድፍረት ያንሳል፡፡ ልብ በሉ ፍላጎታቸው ጨምሮ ድፍረታቸው ያንሳል ማለት ነው፡፡ እኔ ይህ እንኳ ጠቃሚ መስሎ ነው የሚታየኝ፡፡

🌸ወደ ጠቃሚ ጎኖቹ እንምጣ፡፡
ልብ በሉ ሲጀመር ፅሁፌ አላማው የመነፅርን ጠቃሚነት እና አወንታዊ ጎኖቹን( Posetive side) ማጉላት ነው፡፡ እናም ወደ እውነታው እንምጣ፡፡
በቅርቡ በተሰራ ጥናት 44% ሰዎች የውሃ (colorless ) መነፅር የሚጠቀሙ ሰዎች Intelligente ናቸው ብለው ያስባሉ፡፡
በስራው አለም ደግሞ 36% ሰዎች መነፅር የሚደርግ ሰራተኛ Professional መስሎ እንደሚታያቸው ተናግረዋል፡፡
40% ሰዎች ደግሞ መነፅር አድርጎ ወደ ስራ እና class መሄድ Formality [ ፋሽን የመከተል ስሜት ] እንደሚያሰማቸው ተረጋግጧል፡፡

እኔም ያስተዋልኩት ነገር ነው፡፡ ችምችም ያሉ ቅንድቦች እና Clear lence መነፅሮች ጋራ በተመልካቹ ላይ ሳይፈልጉ የአክብሮት ስነልቦናዊ ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ ደስ አይልም?🤓 የስራ ቦታ ብዙ ጊዜ ፊልሞች ላይ የምናስተውላቸው አለቆች ስራ አስኪያጆች እንዲሁም መሪዎች መነፅር ሲያዘወትሩ የምናስተውላቸው ጥቃቅን ፅሁፍ ስራ ስለሚበዛባቸው ብቻ አይደለም ይሄ የተለመደ የስነልቦና Trick ስለሆነ ነው፡፡
እውነቴን ነው ምላችሁ ስለ መነፅር አውርቼ አልጠግብም፡፡ በድጋሚ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ እንድመለስ ተስፋ አለኝ፡፡

💁‍♀በተረፈ እህቴ ከተለያዩ ፕሮግራሞች አንጻር ለጠየቀችው፡ መነፅር ላንች ምቾት ባይሰጥም ተመልካችሽ ላይ ምንም ጥሩ ያልሆነ ስሜት አይሰጥም፡፡ ልብሶች ላልሺው ደግሞ ነጭ ግላስ/መነፅር ከሆነ ከማንኛውም ልብስ ጋር ተቀራራቢ የሆነ mach ነው ያለው፡፡ Sun glasses የሚባሉት የፀሃይ መነፅሮች ካልሆኑ በስተቀር ይህ መነፅር ይህ ነው የሚባል ልዩ የአልባስ አይነት የለም፡፡
ስለዚህ ፀጉርሽ ላይ ትኩረት አድርጊ እና ዘና ብለሽ ወደተጠራሽበት ቦታ በክብር ሂጂ፡፡

👸ሴትነት ትልቅ ሳይንስ ነው!! በአግባቡ እንላበሰው፡ መልካም ቀን፡🌝💛


💄#Share
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
+
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎍🎍🎍🎍🎍🎍🎍🎍🎍🎍
1. ሁላችንም ለማንም ለመናገር አፍረን ይሆናል። ግን እውነታው ሁሌም የግራው ጡታችን ከቀኙ በትንሹ በለጥ ይላል።

2. ለመሆኑ የሽፍታና ፊት ላይ የሚወጡ ኢንፌክሽኖች ዋነኛ ምንጭ የትራስ ጨርቅ አንደሆነ ስንቶቻችን እናውቃለን? /የትራስ ጨርቅን በሳምንት ሁለቴ በማጠብ( በመቀየር) ብቻ ከ 60% በላይ በሆነ መጠን የፊት ኢንፌሽኖችን መቀነስ እንችላለን።
🎍🎍🎍🎍🎍🎍🎍🎍🎍🎍

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
#ውበት_እና_እኛ
*****************
ውበትን በተመለከተ አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎች

👉ለቅንድብ፡- ማታ ከመተኛቶት በፊት ቫዝሊን በማስካራ መቀቢያ ጥቂት በመንከር ቅንድቦን እን ሽፋሽፍቶን በማስካራ መቀቢያ ማበጠር እና ቫዝሊኑን በድንብ እንዲቀባ ማድረግ ወይም ቫዝሊኑን በእጅም መቀባት ይቻላል ይህን በየቀኑ በመጠቀም ቅንድቦ እንዲበዛ ማድረግ ይችላሉ፡፡

👉ለጠቆረ አንገት፡- 3 ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ ከ2 ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ጋር ማዋሀድ ከዛም አንገት ላይ አዳርሶ መቀባት በመቀጠልም ለ20 ደቂቃ አቆይቶ በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ ተመራጭ መፍትሄ ነው፡፡

👉ለፊት፡- ማዲያት እና አፍንጫዎት አካባቢ የሚወጣ ጥቁር ጠቃጠቆ አለቦት? እንግዲያውስ 3 ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ፣ 1 ማንኪያ የቀረፋ ዱቄት እንዲሁም 1 ማንኪያ እርድ በማዋሀድ ፊቶን ቀብተው ከ10-15 ደቂቃ አቆይተው መታጠብ፡፡

👉ለአይን፡- ለአይን ውበት እና ጤንነት ኪያር ጠቃሚ ነው፡፡ 1 ኪያር በክብ ስላይስ አድርጎ በመቁረጥ ኪያሩን አይኖትን ከድነው ከላይ ማስቀመጥ ከዛም ከ15-20 ደቂቃ ያህል በጀርባ ተኝቶ እረፍት ማድረግ፡፡

👉ለጥርስ ንጣት፡- የአንድ ሙዝ ልጣጭ የውስጠኛውን ክፍል በመጠቀም ጥርሶትን በልጣጩ ለ2 ደቂቃ ማሸት ከዚያ በመደበኛ የጥርስ ሳሙናና ብሩሽ ጥርሶትን በማጽዳት ማንጣት ይችላሉ፡፡



××××××××××××××××××××××××××××××××××××

🕯❤️ከተባበርን ለውጥ

እናመጣለን❤️🕯

🌹ፍቅር ያሸንፋል!🌹
ሁሉም መልካም ይሆናል!🙏



┄┄┄┉┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┉┄┄┄
@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

💁‍♀ #ስለ_ብብት_መጥቆር!

ብዙዎቻችን ብዙዎቻችን አንዳንድ ግዜ የሆነ ነገር ሲያስጨንቀን ጭንቀታችን የኛ ብቻ ስለሚመስለን በአለም ላይ ከዛ ጉዳይ ጋር deal እያደረገች ያለች ብቸኛዋ ሴት አድርገን እንመለከት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሃሳቦቻችንን እንደዚህ በጋራ አምጥተን ማውራት ስንጀምር ችግራችን ገና መፍትሄ ሳያገኝ የኛ ጥያቄ የኛ ችግር የሌሎቹም መሆኑን ስንረዳ መረገጋት እንጀምራለን፡፡ በዚህም የበርካታ ሴቶች ስሜት እንደዚህ መሆኑን ካስተዋልኩ ቆይቻለው፡፡
ለዚህም ነው የበርካቶች ሃሳብ የመሰለኝን የውስጥ ጥያቄዎች መልሼ ቻናሉ ላይ መወያያ እነዲሆኑ የማደርገው፡፡ በእያንዳንዱ አርዕስቶች ፖስቶች ቁጥር በርካታ ስሜታዊ መልእክቶች ሲደርሱኝ በስራዬ ርክት እላለሁ፡፡
አሁንም ቢሆን የናንተ ብቻ ጭንቀት እና እጣ-ፈንታ የመሰላችሁን ነገር መተንፈሳችሁን አታቁሙ፡፡
ወደርዕሳችን እንመለስ፡ የብብትን ጥቁረት እንዴት ማስወገድ እንደምንችል እንይ፡-
ብዙ ጊዜ በተለይ በዚህ በበጋ ወቅት ቀለል ያለ ፓክ-አውት ወይም ሌላ ጃፖኒ ሰይዝ እጅሄ ያለው ልብስ ለብሰሽ ከቤት ወጣ ማለት ያምርሽና እጅሽን ከፍ ስታደርጊ ብብትሽ ውስጥ እንዳይታይ የምትፈልጊው ገፅታ ይኖር ይሆናል፡፡ ዘመናዊ ልጅ ከሆንሽ ብብትሽ እንደሃፍረተ-ስጋ የምትደብቂው ሚስጥር ሳይሆን በነፃት ራስሽን የምትገልጪው ሰውነትሽ ነው፡፡
#አንደኛ

አንዱ ዘዴ ከዚህ በፊት የተጠቀሰው ነው፤ በድጋሜ ለመናገር ያህል
2 ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ ከ 1 ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ጋር ማዋሀድ ከዛም ብብትን በሚገባ መቀባት በመቀጠልም ለ20 ደቂቃ አቆይቶ በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ ተመራጭ መፍትሄ ነው፡፡

#ሁለተኛው በፍፁም የማትገምቱት ነገር ነው፡ ድንች!🥔🥔
አሰራሩ፡
አንድ አነስ ያለ ድንች ታዘጋጂአለሽ፡፡ ከዛ በጣም በስሱ ትከትፊውና ጎድጎድ ያለ ሰሀን ውስጥ ውሃ እስኪያወጣ ትጨምቂዋለሽ( ትጨፈጭፊዋለሽ) ፡፡ ከዚያ ውሃውን (ጭማቂውን) ብብትሽ ውስጥ ትቀቢዋለሽ፡፡ አንድ 15 ደቂቃ አቆይሽ ቀዝቀዝ ባለ ውሃ ታጥበሽ አድርቂው፡፡ በተቻለሽ መጠን ጥዋትና ማታ ይህን ማድረግ ብትጀምሪ በስምንት ቀን ውስጥ ግልፅ ለውጥ ማየት ትችያለሽ፡፡
🍄ልብ በይ ፡ ከሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር እንጂ ተመሳሳይ ጥቅም ያለቸው ሌሎች ዘዴዎች አሉ፡፡

#Share

@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#ፍቅረኝነት
#ጋብቻ

🏯በፅኑ መሠረት ላይ ያልተመሰረት ህንፃ በብርቱ ንፋስ እንደሚዋድቅ፤ ጋብቻም እንዲሁ በጽኑ #መርሆዎች ላይ ያልተመሰረተ ከሆነ የህይወት ተግዳሮቶች በገጠሙት ጊዜ መቋቋም መቻሉ የሚያጠራጥር ነው።

እስኪ ደስተኛና ስኬታማ ጋብቻ የሚመሰረትባቸውን #አስር የመርህ አለቶች እንይ!

1. ❤️ #ፍቅር
2. #እውነት
3. 👍 #መተማመን
4. 💞 #መስጠት
5. 💚 #መከባበር
6. 💝 #መታዘዝ
7. 🤴 #እውቀት
8. 💑 #ታማኝነት
9. 💗 #ትዕግስት
10. 💵 #አስተማማኝ_ኢኮኖሚ

#ሴቶች_ብቻ_ተቀላቀሉ
#share
#Join

@onlyfemaleb
ለምክር ፈላጊ ክፍት ነው።

@onlygirlsb
ብርቱ ሴቶች!

በ2019 (2012 ) ክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ወ/ሮ ፍሬወይኒ መብርሀቱ ብርቱ ሴቶች ብሎ አለም ዕውቅና ሰጥቶልናል፡፡ እኛም ሴት ማለት ሀገር ነችና ክብሩ የሀገር ነው ብለናል፡፡
#ሴትልጅጥንካሬናት!
#ጾታዊጥቃትንእቃወማለሁ!
@onlyfemaleb
#ፍቅርና_ጋብቻ

“ፍቅር ምንድን ነው?” ሲል ተማሪው ለመምህሩ ጥያቄ አቀረበ፡፡

“ለጥያቄህ መልስ ለመስጠት በቅድሚያ በአንድ የስንዴ ማሳ ሂድና ትልቁን ስንዴ መርጠህ ይዘህ ናና መልሱን እነግርሃለሁ፡፡

#ነገር ግን ልብ አድርግ የአሰራር ሕጉ የሚፈቅደው በስንዴው ማሳ አንድ ጊዜ ብቻ በማለፍ የስንዴውን ዛላ ይዘህ ትመለሰላህ እንጅ በማሳው ውስጥ መመላለስ አይቻልም አለው” መምህሩ፡፡

#ተማሪው እንደተባለው ወደ ስንዴው ማሳ ገባና የመጀመሪያውን ሽና (መደዳ) ይዞ ሲጓዝ አንድ ትልቅ የስንዴ ዛላ አገኘ ነገር ግን ይሄን አድንቆ ሌላ ከዚህ የላቀ ትልቅ ይኖራል በማለት ፍለጋውን ቀጠለ እንዳሰበውም ከበፊቱ የተሻለ ትልቅ አገኘ፡፡
#ምን አልባትም እስካሁን ካየሁት የበለጠው እየጠበቀኝ ይሆናል በማለት ፍለጋውን ቀጠለው፡፡ #የስንዴውን ማሳ ከግማሽ በላይ ካደረሰ በኋላ ከዚህ በፊት ካገኛቸው የስንዴ ዛላዎች የበለጠ እንደማይኖር ተረዳና ቀደም ብሎ አግኝቶት በነበረውና ባመለጠው ትልቅ የስንዴ ዛላ እየተቆጨ ባዶ እጁን ወደ መምህሩ በተመለሰ ጊዜ “ፍቅር ማለት እሱ ነው፡፡

#የተሻ ፍለጋው አልገታ ብሎህ ፍለጋውን ቀጠልክ ነገር ግን የተሻለውን እንዳጣህ ዘግይተህ ተገነዘብክ” አለው መምህሩ፡፡

“ታዲያ ጋብቻ ማለትስ ምንድን ነው?” ሲል ሁለተኛ ጥያቄውን አቀረበ
መምህሩም “አሁንም ጥያቄህን ለመመለስ ባንድ የማሽላ ማሳ ሂድና ትልቅ ነው ያልከውን ማሽላ ይዘህ ተመለስ፡፡ #ታዲያ አሁንም እንደበፊቱ የአሰራር ሕጉ የሚፈቅድልህ አንድ ጊዜ ማለፍ እንጅ ተመልሶ መፈለግና ማንሳት አይቻልም” አለው፡፡ #ተማሪው ወደ ማሽላው ማሳ በደረሰ ጊዜ ከበፊት ስህተቱ ተምሮ ስህተቱን ላለመድገም ከማሳው ግማሽ እንደደረሰ አንድ በቂ ነው ብሎ ያሰበውን መካከለኛ ማሽላ ይዞ ወደ መምህሩ ተመለሰ፡፡ #መምህሩም “አሁን ጥሩውን ፈልገህና የተሻለ ነው ብለህ ያሰብከውንና ምርጡንም እንዳገኘህ አምነህ በእምነት ይዘህ መጠሀል ይህ ማለት ጋብቻ ነው” በማለት ጥያቄዎቹን መለሱለት፡፡

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
ስለ ቀይ ስር የማናውቃቸው አስገራሚ የጤና ሲሳዮች

ለብዙዎቻችን ቀይ ስር ከገበታ ማድመቂያነት የዘለለ የምግብ ንጥረ ነገር ያለው አይመስለንም፡፡ ተፈጥሮ ከቸረችው ቀይ ቀለም ተነስቶ ስያሜውን ያገኘው ቀይ ስር ለብዙዎች የምግብ ንጥረ ነገር ያለው አይመስላቸውም፡፡ በአገራችህ እንኳን ያለውን እውነታ ያየን እንደሆነ በየአይነት አዘን ሌሎቹን ምግቦች ጥርግ አድርገን በልተን ስንጨርስ ቀይስርን ገፋ አድርገን እንተዋለን፡፡ ለመሆኑ እንዲህ በአገራችን ገበታ የሚገፋው ቀይ ስር በሳይንስ ምን ያህል የተረጋገጠ የጤና ጠቀሜታ ይኖረው ይሁን ስንል ሳይንሳዊ ጥናቶችንና መረጃዎችን አገላበጥን እናም እነዚህን ታአምራዊ የቀይስር የጤና ሲሳዮች አገኘን፡፡ እናም አካፈልናችሁ፡፤

1. ብዙ የምግብ ንጥረ ነገር አነስተኛ ካሎሪስ እና ቅባት አለው፡- ቀይ ስር በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀገ ሲሆን ፕሮቲን፣ አነስተኛ ካሎሪስና ቅባት፣ ፋይበር፣ ቫታሚን ሲ፣ ፎሌት፣ ቫታሚን ቢ6፣ ማግኒዚየም፣ ፖታሲየም፣ ፎስፎረስ፣ ማንጋኒዝና ብረትን ይዟል፡፡

2. የደም ግፊትን ይቀንሳል፡- ቀይ ስር ከፍተኛ መጠን ናይትሬትስ የሚባል ንጥረ ነገር ስላለው በአለም አቀፍ ደረጃ ለሞት የሚዳርጉትን የልብ ድካምና የልብ መስነፍን ጨምሮ ስትሮክን የሚያመጣን የደም ግፊት መጠን ለመቀነስ የደም ቧንቧዎችን ግድግዳ ያሰፋል፡፡

3. የአትሌትክስ ውጤታማነትን ይጨምራል፡- ቀይ ስር መብላት የኦክስጂን የመጠቀም አቅምን ያሳድጋል እንዲሁም የድካም ስሜትን ይቀንሳል፡፡ አትሌቶች ለስልጠና ወይም ለውድድር ከመግባታቸው በፊት ለብርታት እንዲሆናቸው ከ2-3 ሰዓት ቀደም ብለው ቀይ ስር እንዲመገቡ ይመከራል፡፡

4. የብግንነትን ወይም የማቃጠል ስሜትን ይቀንሳል፡- ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት፣የልብና ጉበት በሽታ እንዲሁም የካንሰር በሽታ ከግብግነት ወይም ከማቃጠል ጋር ይያያዛል ይሁንና ቀይ ስር ቀይ ቀለም እንዲኖረው የሚያደርገው ቤታሌንስ የተሰኘው ንጥረ ነገር ይህን ብግነት ይከላከላል፡፡

5. የምግብ የመፈጨት ሂደትን ጤናማ ያደርጋል፡- ቀይ ስር ፋይበር ስላላው ጤናማ የምግብ መፈጨት ሄደትን ያሻሽላል፡፡

6. የአእምሮ ጤናን ያሻሽላል፡- ቀይ ስር ናይትሬትስ የተሰኘ ንጥረ ነገር ስለያዘ ወደ አንጎላችን የሚሄደውን የደም ፍሰት በመጨመር በእርጅና ምክንያት የሚከሰተውን የመጃጀት በሽታ ይቀንሳል፡፡

7. ካንሰርን ይከላከላል፡- ካንሰር ማለት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የሕዋሳት (የሴል) ዕድገት ነው፡፡ ስለሆነም ቀይ ስር ውስጥ ቀለም የሚፈጥረው ንጥረ ነገር የካንሰር ሴል ዕድገትን ይቀንሳል፡፡

8. ክብደትን ይቀንሳል፡- ቀይ ስር ከፍተኛ ውሃና ዝቅተኛ ካሎሪ ስላላው የሰውነት ክብደትን ይቀንሳል፡፡

9. ጣፋጭና በተለያየ አይነት አቀራረብ ለምግብነት ይውላል፡- ቀይ ስር ከአትክልት ጋር፣ በጭማቂ መልክ እንዲሁም በእኛ አገር ባይለመድም የቀይ ስር ቅጠል እንደ ጎመን ተቀቅሎ ይበላል።

ምንጭ:- ዶ.ቤዛ አያሌው
@onlyfemaleb

⚡️ለሌሎች ሼር ያድርጉ!
Forwarded from Soliyana Fa
ከቤተሠብዎ,ከፍቅር አጋርዎ ጋር ተመሳሳይ ልብስ……,የprogram ቀሚሶች,የልጆች አልባሳት,humanhair,ቦርሳዎች,ሠአቶች(የጥንዶች), የስጦታ እቃዎች…………………ሁሉንም በአንድ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ ከታች ያለውን link ተጭነው ይምረጡ👇👇👇👇👇👇
t.me/Cherstinfashion
👆👆👆👆👆👗👠👜
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢጊያ_ነኝ
#ጓደኛሽ_ሸንቃጣ_የሆነችባቸው_20 ሚስጥሮች
👯👯👯👯👯👯👯👯👯👯
1. #የሚጠጣ ውሃ ከእጃችሁ አትጡ
በማንኛውም ጊዜ ውሃችሁን ከቦርሳችሁ አውጥታችሁ መጎንጨት፣ ከጠማችሁም ጥማችሁን እስክትቆርጡ ድረስ መጠጣት ጥሩ ነው፡፡ ውሃ ብዙ አማራጭ ያለው መጠጥ ነው፡፡ ባዶውን ከጉሮሯችሁ አልወርድ ብሎ ያስቸግራችሁ እንደሆነ ሎሚ ወይም የሎሚ ጁስ ደባልቃችሁ ልትጠጡ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርበት የምታገኙት ከሆነ ቫይታሚን ውሃ መጠጣትም ሌላኛው አማራጭ ነው፡፡ ንፁህ እና ኩልል ያለ ውሃን የመሰለ ነገር የለም፡፡
Nice ethiopian women body
2. #የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንደ አንድ አስደሳች ድርጊት እንጂ እንደ አንድ መወጣት ያለባችሁ እለታዊ ግዴታ አትመልከቱት፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰውነታችሁ እና ህይወታችሁ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አዎንታዊ ለውጥ አስቡት፡፡ ቀጥሎ ምን መብላት እንደሚጠበቅባችሁ ከመጨነቅ ይልቅ ቀጥሎ ምን አይነት እንቅስቃሴ ልታደርጉ እንደምትችሉ አስቡ፡፡
3. #የተመጣጠነ ምግብ ብሉ፡፡
አንዳንድ ምግቦች ምንም እንኳ ከስብ ነፃ ሆነው በአንፃሩ የፕሮቲን ይዘታቸው ከፍ ያለ ቢሆንም ዋና የካሎሪ ምንጭ ስለሚሆኑ ክብደት እንድትጨምሩ ሊያደርጓችሁ ይችላሉ፡፡ የምትመገቡት የቱንም ያህል የተመጣጠነ ምግብ ቢሆንም ዞሮ ዞሮ ተጨማሪ ካሎሪ ማለት ተጨማሪ ክብደት መሆኑን አትዘንጉ፡፡
4. #የካፌይን አጠቃቀማችሁን ገደብ አበጁለት፡፡
ከሲጋራ በተዘዋዋሪ ከሚመጣ ጢስ እንኳን ቢሆን ራሳችሁን አርቁ፡፡
5. #የአጭር ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እቅድ ላይ ትኩረት አድርጉ፡፡
ዋናው ትኩረታችሁ መሆን ያለበት የለት ተዕለት ግባችሁን ዳር ማድረስ መሆን መቻል አለበት፡፡
6. #በቀን ውስጥ በትክክል ምን ያክል እንደምትመገቡ ለመለየት የሚያስችላችሁን ዝርዝር መረጃ አነስተኛ ደብተር ወይ ማስታወሻ ላይ መዝግባችሁ ያዙ፡፡ በየካፌው የምትመገቡት ቺፕስ፣ ልጆቻችሁ መክሰስ ሲበሉ አብራችሁ የምትጎራርሱትን ነገር ሁሉ አካቶ መመዝገቡ አስፈላጊ ነው፡፡
7. #አልፎ አልፎ ለምሳሌ በሳምንት አንድ ቀን እንዳሻችሁ ሁኑ (ሺ ዓመት አይኖር)፡፡ ይሁን እንጂ ሳምንት ሙሉ ወይም አንድ የዓመት ረፍት ጊዜ ሙሉ እንዳይሆን ጥንቃቄ አድርጉ፡፡
8. #በዙሪያችሁ የሚገኙ ሌሎች ሰዎችም ጤናቸው የተጠበቀ እንዲሆን የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ አብሯችሁ ስፖርት የሚሰራ ጓደኛ ቢኖራችሁ መልካም ነው፡፡ ሌሎች በቅርበት የምታውቋቸውን ሰዎችም ስፖርት እንዲሰሩ አበረታቷቸው፡፡ ጠዋት ተነስቶ የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ዱብ ዱብ ማለት የሚወድ ጎረቤት ካላችሁ እናንተም መቀላቀል ትችሉ እንደሆነ ጠይቁ፡፡
9. #መሰልቸት እንዳይገጥማችሁ በየጊዜው የምትሰሩትን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ቀያይሩ፡፡ ኤሮቢክስ፣ ብስክሌት መንዳት፣ ዋና መዋኘት፣ ዳንስ፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወዘተ እንደየሁኔታው እየለዋወጣችሁ ልትሰሯቸው የምትችሏቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ናቸው፡፡
10. #በጤና፣ የአካል ብቃት ወዘተ… ዙሪያ መረጃ የሚሰጡ መጽሔቶች እና ጋዜጦችን ‹‹ሰብስክራይብ›› በማድረግ ቢሯችሁ አሊያም ደግሞ ቤታችሁ ድረስ እንዲመጣላችሁ አድርጉ፡፡
11. #አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ ንብረቶች ላይ ገንዘባችሁን አውጡ፤ ለስፖርት ምቹ የሆነ ጫማ፣ ቱታ፣ ሙዚቃ ማዳመጫ ኤምፒስሪ ወዘተ፡፡
12. #አንዳንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነቶችን አዘውትራችሁ ለምሳሌ ለስድስት ወይም ለሰባት ቀናት መደዳውን በተከታታይ አንዳንዴም ጠዋትና ማታም ጭምር ለመስራት አቅዱ፡፡
13. #ሰውነታችሁን ከሌሎች ሰውነት ጋር አታነጻጽሩ፡፡ በምትኩ የራሳችሁ ምርጥ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡
14. #አመጋገባችሁ ያልተመጣጠነ ከሆነ የተመጣጠነ ለማድረግ ጥረት አድርጉ፡፡ በየዓለቱ ቫይታሚን እና ሚኒራል እየወሰዳችሁ መሆኑን አረጋግጡ፡፡
15. #የአካል ብቃት እንቅስቃሴያችሁን ደረጃ እና ክብደት በየጊዜው ለማሻሻል ስራ ስሩ፡፡
16. #ዝም ብላችሁ ከጊዜ ለጊዜ እና አጋጣሚ ውሳኔውን ከመተው ይልቅ አንድ ቀን ቀደም ብላችሁ በማግስቱ የምትሰሩትን የእንቅስቃሴ አይነት አቅዱ፡፡ ከኩባንያ መሪዎች እስከ ቤት እመቤቶች እና የሀገር መሪዎች ድረስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ እናንተም ጊዜ የምታጡበት ምክንያት የለም፡፡
17. #ክብደት መቀነስ ከሚለው ክልል ወጥታችሁ ሁለገብ አካላዊ ብቃት መፍጠር ወደሚለው ሽግግር አድርጉ፡፡ ስኬታችሁን ልብሳችሁ ምን ያህል ልክክ እንደሚልባችሁ በመመልከት ወስኑ፡፡
18. #ያለማቋረጥ ልትከተሉ የምትችሉት የአመጋገብ ልምድ ይኑራችሁ፡፡ የቱንም ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የምታደርጉ ቢሆንም የ‹‹ካሎሪ›› ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን እስከ አዘወተራችሁ ድረስ ሸንቀጥቀጥ ለማለት ፈተና ይገጥማችኋል፡፡
19. #በቂ እንቅልፍ ተኙ፡፡ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች በጊዜ የመተኛት እና እጅግ ጥሩ እንቅልፍ የማግኘት ልማድ አላቸው፡፡
20. #የአልኮል መጠጥ አወሳሰዳችሁን በተለያዩ የበዓላት እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ወቅት ብቻ ወስኑ፡፡
.....................................................
Join

Share

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

በዚህ የ#በጋ ወቅት መረሳት የሌለባቸው ነገሮች 🤗🤗🤗

1. ሁሌም #ውሃ መጠጣት አለብን ይሄ ቆዳ ደረቅ አንዳይሆን ይረዳዋል::ከዛም በተጨማሪ ሰውነታችንን ቶሎ ቶሎ ሎሽን መቀባት ቆዳ እንዳይደርቅ እና ነጭ እንዳይሆን ይረዳዋል እኔ እና መሰሎቼ ምንጠቀመውን በጣም ቆንጆ #hydrating mask እና ሎሽን ልጠቁማችሁ
👉#perfect cosmetics peel-off mask
👉#glysolid body lotion
👉#hand cream alovera+ avocado- for your hands

2. ቆዳችን ላይ ያሉትን #dead skin ለሱ ተብለው በተዘጋጁ #scrubs ወይም ቤታችን ውስጥ በቀላሉ በሚዘጋጁ የፊት #mask ቶሎ ቶሎ ማስወጣት/ማስወገድ ያስፈልጋል::

3.ሁልጊዜ የፀሀይ መከላከያ(#sun screen) መጠቀም የቆዳችንን በፀሀይ የመጎዳት አቅም ይቀንሰዋል:: ለሁሉም የቆዳ አይነት የሚስማማ እኔ ለራሴ ምጠቀመውን ላጋራቹ ትወዱታላቹ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
👉#skin aqua sunscreen, light textured and non greasy, for normal to oily skin

4. ስለ ቆዳ ብቻ እያወራን ከንፈራችንን ረሳነሳው 🙊🙊🙊🙊,,, #ከንፈራችንን ቢያንስ በየ ሁለት ሰዓቱ ሚያለሰልስ ቻፒስቲክ መቀባት ቆንጆ ነው
ጥቆማ 😊😊😊
👉# Nivea sun protect chapstick
👉# carmex moisturizing lip balm

5. በቫይታሚን እና omega-3 የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር የሰውነት ፀሃይን የመከላከል አቅም ያሳድጋል

በመጨረሻማ እንደ ኮፍያ እና መነፅር የመሳሰሉ ነገሮችን መጠቀም ለቆዳችን ተጨማሪ ሽፋን ይሰጥልናል::

Join

Share

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

እንዴት ናቹልኝ የኔ ውዶች ከዚህ ቀን በኋላ #online የማማከሪያ ሰዓት ዘውትር ሰኞ እስከ እሁድ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት
ምን አልባት ስራ አዳሪ በምሆንበት ቀን ላልኖር እችላለው።
ከ online ውጪ ማለትም text ባየሁ ቁጥር ለመመለስ በማንኛው ሰዓት እናንተን ለመርዳት እና ለማገዝ ተዘጋጅቻለው።
#ቤተሰብ
#ትምህርት_እና_ስራ
#ፍቅር
#ጤንነት
#ጓደኝነት
#ሴትነት
#ወሲብ
#እንዲሁም ማንኛውንም ሀሳብ መመካከር እንችላለን መጪው ጊዜ የእኔ እና የአንቺ ነው።
ሚስጥር ጠባቂነቴ እስከ አሁን ባማከርኳቸው እህቶቼ ታይቷል ተመስግኛለው።
#እስካሁንም እጅግ በርካታ ሴቶችን online አማክሬአለው

#አንቺስ??

💯 አንድ % ሚስጥራቹ ይጠበቃል

@onlygirlsb

ላይ ማንኛውንም ሀሳብ ማንሳት መብታቹ ነው።

#share #share
@onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ pinned «#አቢጊያ_ነኝ እንዴት ናቹልኝ የኔ ውዶች ከዚህ ቀን በኋላ #online የማማከሪያ ሰዓት ዘውትር ሰኞ እስከ እሁድ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ምን አልባት ስራ አዳሪ በምሆንበት ቀን ላልኖር እችላለው። ከ online ውጪ ማለትም text ባየሁ ቁጥር ለመመለስ በማንኛው ሰዓት እናንተን ለመርዳት እና ለማገዝ ተዘጋጅቻለው። #ቤተሰብ #ትምህርት_እና_ስራ #ፍቅር #ጤንነት #ጓደኝነት #ሴትነት #ወሲብ…»