ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
ከትላንቱ የቀጠለ

3⃣ ሴቲቱ የሌላ ሰው ሚስት እኮ ነች!
ለማለት የፈለግሁት ያኔ አብሬአቸው ስወጣ የነበሩ ሴቶች አብዛኞቹ ዛሬ የሌሎች ወንዶች ሚስቶች ሆነዋል፡፡

🔹 ታዲያ ዛሬ በነዚያ ወንዶች እግር ራሴን አኑሬ ሳስበው ምነው ባላደረግሁት ማለትም አብሬአቸው ባልወጣሁ ኖሮ ብዬ እቆጫለሁ፡፡ራሴን በራሴ ምታው ምታው ይለኛል፡፡ግን ምን ዋጋ አለው አንዴ ሆኖ አልፎአል❗️🤷‍♂

♦️በሌላ ጎኑ ሳየው ደግሞ እኔም ሳገባ ሚስቴ ከሌላ ሰው ጋር ትወጣ የነበረችና ያም ሰው የፈለገውን አድርጎባት እንደተለያት እያሰብኩ መኖሩን በጭራሽ አልፈልገውም፡፡

አንተስ ብትሆን ሚስትህ አንድ ወቅት ከሌላ ወንድ ጋር እንደነበረች ማሰብ የሚቀልህ ይመስልሐል

👉አያቸሁ በራስ ሲመጣ እንዴት ከባድ እንደሆነ!

👉ነገሩን ገፋ አድርገን ስናየው ደግሞ ሌላም ገጽታ አለው፡፡ ሴቲቱ የአንድ ወላጅ ልጅም እኮ ነች፡፡

የእኔ ሴት ልጅ ብትሆን ኖሮስ? እህቴስ ብትሆንስ እንደእኔ ዓይነቱ ወንድ መጠቀሚያው አድርጎአት ቢተዋት እንደ ቀላል ነገር ሊቆጠር ይገባልን

እንግዲህ ዛሬ ሴቶችን በሌላ ዓይን ማየት ጀምሬአለሁ፤ አንድ ሌላ ሰው የወደፊት ሚስት፣የሌላ ሰው ልጅ ወይንም እህት እንደሆኑ አድርገን ማሰብ እንድናከብራቸውና እንድንጠነቀቅላቸው ሊረዳን እንደሚችል ተምሬአለሁ፡፡

4⃣ ወሲብ አሪፍ የተባሉትን ግንኙነቶቼን እንኳ ሳይቀር ገድሎብኛል፡፡
ኮሌጅ ሳለሁ አንዲት የልብ ወዳጅ ነበረችኝ፡፡የምኞቴን ዓይነት ሴት ነበር ያገኘሁት! ከርሷ ጋር የማሳልፋቸው ጊዜያት ሁሉ እጅግ ጣፋጮች ነበሩ፡፡ በቃ ተግባባን ነው የምላችሁ፡፡

🔸ግን ታዲያ ጥቂት ቆየንና በእኔ አነሳሽነት ወሲብን መለማመድ ጀመርን፡፡
ብዙም ሳይቆይ የመገናኘታችን ምክንያቱ ወሲብ ብቻ መሆን ጀመረ፡፡

🔴እርሷን በይበልጥ ለመቀራረብና ለማወቅ የነበረኝ ጉጉት ሁሉ ጠፋ፡፡

🔹ታዲያ በመቀራረብ ፈንታ መራራቅ ጀመርን፡፡ ያን ድንቅ ህብረታችንን ወሲብ ገደለው!

💢ሰዎች ከሰዎች ጋራ በተለያዩ ደረጃዎች ማለትም በስሜት፣ በአእምሮ፣ በአካልና በመንፈስ ህብረትን ያደርጋሉ፡፡

🔹ታዲያ እኔና ጓደኛዬ በአካል በሚሆነው ግንኙነታችን ላይ ብቻ ትኩረትን ስናደርግ ሌሎቹ የግንኙነት መስመሮቻችን ተቃጠሉብን፡፡

👉ያን ድርጊት ሳንለማመድ ታግሰን ብንቆይ ኖሮ ርግጠኛ ነኝ ዛሬም አብረን በሆንን ነበር፡፡

ይህ ሁኔታ እጅግ ብዙ ዎች ላይ ሲከሰት ታዝቤአለሁ፡፡ ይህ ለምን ይሆናል ምክንያቱን ቀጥዬ አቀርበዋለሁ፡፡

5⃣ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ሌሎችንም የግንኙነት መስመሮች ያበላሻል❗️

ከአንዲት ሴት ጋር ወሲብን በፈጸምኩ ጊዜ ሁሉ ሁለት ነገሮች እንደሚሆኑብኝ ታዝቤአለሁ፡፡እንዴት እንደሚከሰቱ አለማስተዋሌ እንጂ ያልተከሰቱባቸው ጊዜያት ነበሩ ለማለት አልደፍርም፡፡

ያልኳችሁ ሁለቱ ነገሮች
👉አንደኛው ለሴቲቱ ያለኝ ክብር መቀነሱ ( ባልፈልገውም እንኳ ማለቴ ነው) ሲሆን
👉ሁለተኛው ደግሞ ሴቲቱ በእኔ እምነት ማጣቷ ነው(እርሷም ሳትፈልገው ማለት ነው)❗️

💢ይህ ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ መሆኑን ወይንም መከሰቱን ብቻ ነው የማውቀው፡፡ምናልባትም ስንፈጠር እንደዚያ ተደርገን ተሰርተን እንደሆነ ብዬም አስባለሁ፡፡

💢 አንድ ነገር ግን ርግጠኛ ነኝ፤ የእኔ ብቻ ገጠመኝ አይደለም፡፡ በሌሎች ሰዎች ህይወትም ደግሞ ደግሞ ሲከሰት ዐይቻለሁኝ፡፡

💢ብዙዎች ከፈጸሙት ቅድመ ጋብቻ ወሲብ የተነሳ የዛሬ ትዳራቸው ለብዙ ቀውስ እንደተዳረገ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡ አለመተማመንንና አለመከባበርን ይዘው ነው ወደትዳር ህይወት የሚገቡት!
እንግዲህ መተማመንና መከባበር ደግሞለአንድ ትዳር ህልውናና ጤንነት ወሳኝ ነገሮች እንደሆኑ ልብ ይሏል!

አንድ በቅርብ የተጋቡ ባልና ሚስትን አውቃለሁ፤ በወር ከአንድ ጊዜ ያነሰ የወሲብ ህብረት ነው ያላቸው፡፡ እርሱ አያከብራትም፤ይህን በደንብ ታውቃለች፡፡እርሷም አታምነውም፡፡ስለዚህ ራሷን ለርሱ መስጠትን በፍጹም አትፈልግም፡፡

👉ይህ አሳዛኝ ክስተት ቢሆንም ከምንገምተው በላይ አውነትና በጣምም የተለመደ ነው፡፡

👉ይሁንና ማንም ስለዚህ ጉዳይ በአደባባይ በግልጽ አይናገርምም ሆነ አያስተምርም፡፡ ቲቪ ላይ የምናያቸው ቅድመጋብቻ ፈጻሚ ጥንዶችም ስለዚህ ምንም የሚሉት ነገር የለም፡፡

💢 በቃ ምን አለፋችሁ ሁሉ ሰው እንዳለ እያወቀ ሊናገረው የማይፈልገው እውነት ቢኖር ይሄ ነው፡፡

........ ይቀጥላል

#Share #Share #Share



@onlyfemaleb
#ላንቺ ብቻ ክብደት ለመቀነስ የሚረዱ የስፖርት አይነቶችን እናሳያችኋለን
#ላንቺ ብቻ
ክፍል ሶስት

6⃣ እስከ ጋብቻ ታግሶ መቆየት በትዳር ውስጥ የተሳካና ጣፋጭ ወሲባዊ ህይወትን እንድንለማመድ ይረዳናል ፡፡

ለምን ትሉ ይሆናል፡፡ መልሱ አጭርና ግልጽ ነው፡፡

👉እኔ ለርሷ ያለኝን አክብሮት እርሷም በእኔ ያላትን እምነት እንደጠበቅን ወደ ትዳር ስለምንገባ ነው፡፡

💢አንድ የተማርኩት ነገር ቢኖር ሴት ልጅ ወንዱን ካላመነችው መላው እኔነቷን ልትሰጠው አትፈልግም ፤ ከእርሱ ጋር መሆንም ደስታን አይሰጣትም፡፡

👉 ውስጠ ምስጢሩ እንዲህ ነው፡፡ሴቶች ወሲብን ተጠቅመው ፍቅርን ለማግኘት ስለሚሞክሩና ወንዶችም በፍቅር አሳብበው ወሲብን ስለሚያገኙ ከዚህ የተሳሳተ መሠረት ላይ ቆመው ወሲብን ይፈጽማሉ፡፡

💢 ሴቲቱ ጓደኛዋን ላለማጣት ስትል ድርጊቱን መፈጸሟን ትቀጥላለች፡፡

💢 ወንዱም ከጓደኝነታቸው ይልቅ ወሲቡን ስለሚፈልገው ህብረታቸው ይቀጥልና ልክ ጋብቻው ተሳክቶ ከተፈጸመ በኋላ ሴቲቱም የምትፈልገው ሰው እጁዋ መግባቱን ስታረጋግጥ እርሱን ለማግኘት ስትል ትፈጽም የነበረውን ወሲብ ችላ ማለት ትጀምራለች፡፡

👉 እንዲያውም ከጋብቻ በፊት ወሲብ እናድርግ ብሎ እርሷን በመገፋፋቱ በልቧ ጥላቻና ቂምን መቋጠሯ ስለማይቀር ስለወሲብ ማሰብ እንኳ አትፈልግም፡፡

ወንዱም ቢሆን ወሲብን ለራሱ ርካታ እንጂ ከርሷ ጋር ፍጹም አንድ ለመሆን ሲል ስለማያደርገው (ይህንን ስሜቱን እርሷ በደንብ ታውቅበታለች) የተበላሸ የወሲብ ህይወት መኖርን ይያያዙታል፡፡

ይህን ሁሉ ፈጥሬ የማወራችሁ አይምሰላችሁ፡፡አይደለም❗️

ዛሬ ከኮሌጅ ህይወት ወጥቻለሁ፡፡ በዙሪያዬ ብዙዎች ሲያገቡ እያየሁ ነው፡፡ ታዲያ ይህን ያልኩዋችሁን ሁሌም በብዙዎች ትዳር እየታዘብኩ አለሁ፡፡

📌መፍትሔው ታዲያ ምንድነው ትሉ ይሆናል፤ መልሴ
👉 ‹‹ መጠበቅ፣ መጠበቅ አሁንም እስከጋብቻ ድረስ ታግሶ መጠበቅ!!!›› የሚል አጭርና ግልጽ መልስ ነው፡፡

🔵 ታግሶ የጠበቀ ወንድ ለሚስቱ ያለው ክብር ከፍተኛ ይሆናል፤ ሚስቲቱም እንዲሁ!

🔸 ስለዚህ አንዳቸው ላንዳቸው ያላቸው ፍቅር ትኩስና ከፍተኛ ስለሚሆን የወሲብ ህይወታቸውም ጣፋጭና የተሳካ ይሆናል፡፡

...... ይቀጥላል

#share #share

💢💢 @onlyfemaleb 💢💢


💢💢 @onlyfemaleb 💢
@onlyfemaleb
©
#ርዕሰ_መምህር፦ "ለአንድ ልጅ ጉርድ ፎቶግራፍ ስንት ታስከፍላላችሁ?"
#ፎቶ_አንሺ፦ "ለአንድ ፎቶግራፍ 20 ብር ያስከፍሎታል ጌታዬ"
#ርዕሰ_መምህሩ፦ "ይህማ አይሆንም፤ ባይሆን የልጆቹ ብዛት 500 ስለሆነ፣ ልንከፍልህ የምንችለው በአንድ ልጅ- 10 ብር ብቻ ነው"
#ፎቶ_አንሺው፦ "ይሁን እሺ!፤ ብዙ ከሆኑ፣ ለአንድ ልጅ 10 ብር ያስማማናል"።
••●◉
#ርዕሰ_መምህር፦ "መምህር፥ ሂድና ለተማሪዎቹ በነገው ዕለት ለፎቶግራፍ ክፍያ የሚውል፥ እያንዳንዳቸው 25 ብር እንዲያመጡ ንገራቸው!"
የክፍል መምህሩ፦ "እሺ!፤ ያሉኝን አሳውቃቸዋለሁ"።
••●◉
#መምህር፦ "መልካም ቀን ተማሪዎች!፤ ነገ ወደ ትምህርት ቤት ስትመጡ ለፎቶግራፍ ክፍያ የሚሆን 30 ብር ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ!"።
••●◉
#ተማሪ፦ "እማዬ፥ ለፎቶግራፍ ክፍያ የሚሆን 40 ብር ነገ ይዛችሁ ካልመጣችሁ- ትምህርት ቤት አትገቡም ተብለናል "።
••●◉
#እናት፦ "አባት፥ ልጅህ፣ ለፎቶግራፍ ክፍያ የሚሆን 50 ብር ነገ ይዘህ ና ተብሎአል"
#አባትም፦ "ወይ ጉድ! እኛ በቃ በዚች አገር ላይ መኖር አልቻልንም ማለት ነው?፤ ይህ መንግስት በየጊዜው ዋጋ ከመጨመር ሌላ ሥራ የለውም እንዴ?!፤ ሌላው ቢቀር እንዴት በትምህርት ወጪ ላይ እንዲህ ይደረጋል?!፤ ቀድሞም ብለን ነበር ለነገሩ፥ "ይሔ ጠቅላይ ሚኒስቴር አይረባም!"።
••●◉ #ልብ_በል
• ስርቆት የሚጀምረው ከቤት ነው፥ ለቤትህ ታማኝ ካልሆንሽ በውጪ ታማኝ ልትሆኝ አትችይም።

@Onlyfemaleb
7_DAY_CHALLENGE___7_MINUTE_WORKO.mp4
30.4 MB
ክብደት ለመቀነስ የሚጠቅሙ 7 የስፖርት አይነቶች

@onlyfemaleb
ላንቺ ብቻ

ማንኛውም ጥያቄ እና ሀሳብ

@OnlyGirlsB

መጠየቅ ትቺያለሽ

መብትሽ ነው የፈለግሽውን መጠየቅ
ላንቺ ብቻ

የቀጠለ

ክፍል አራት

7⃣ ከሌሎች ሴቶች ጋራ ወሲብን አለመፈጸም ማለት በትዳር ውስጥ የተሳካና ጣፋጭ የወሲብ ህይወትን መኖር ማለት ነው፡፡

👉ወሲብ ምስጢራዊ ነገር ነው፡፡ አልፎ አልፎ የሚደረግ ነገር እንኳ ቢሆን በሰዎች ህይወት ውስጥ ጥልቅ የሆነ ውስጣዊ መተሳሰርን የሚፈጥር ነገር ነው፡፡

💢 ታዲያ ችግሩ እዚህ ጋ ነው፤ ከሌሎች ሴቶች ጋር ብዙ ውስጣዊ መተሳሰርን ፈጥሬ ካለፍኩ ከወደፊቱዋ ሚስቴ ጋራ የጠበቀ መተሳሰር እንዳይኖረኝ እንቅፋትን ፈጥሮብኝ ያልፋል ፡፡

🔸 ልክ እንደ ስኮች ቴፕ ፕላስተር ማለት ነው፡፡ ስኮች ቴፕን ደጋግማችሁ የተጠቀማችሁበት ጊዜ የማጣበቅ ሐይሉ እያነሰ ሄዶ በስተመጨረሻ ከምንም ነገር ጋር መጣበቅ ያቅተዋል፡፡

📌 ከጋብቻ በፊት ከሌሎች ሴቶች ጋራ መጣበቅ ከጀመርኩ ከወደፊቷ ሚስቴ ጋራ እንደሚገባኝ መጣበቅ ይሣነኛል ፤ በርሷም ሊኖረኝ የሚገባኝ ደስታ ይቀንሳል ፤ የሚገባትንም ፍቅር መስጠት እቸገራለሁ፡፡

👉 ይሁንና ዛሬ ታማኝ ሆኜ የማሳልፋት እያንዳንዲቷ ቀን ለነገዋ ሚስቴ ተገቢ ፍቅርና አክብሮትን እድሰጣት የሚያስችለኝን ግኝኙነት እንድፈጥር ይረዳኛል፡፡
የሚገርም ነው❗️

ማህበረሰባችን ምንዝርናን ማለትም በጋብቻ ውስጥ ያለ ዝሙትን አወግዛለሁ ይላል፡፡ በሌላ ጎን ግን ቅድመጋብቻ ወሲባዊ ግንኙነቶችን ሲኮንን አይታይም፡፡

🔹የጊዜን ስሌት ስናወጣው ቅድመጋብቻ ወሲብ እኮ ያው ምንዝርና ማለት ነው፡፡

🔴ምንዝርና የትዳር ህብረትን ምን ያህል እንደሚጎዳ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡

🔴ቅድመጋብቻ ወሲብ የሚያመጣው ቀውስ ግን ከዚህ ያልተናነሰ ነው፡፡

🔸 በጋብቻ ውስጥ ሊኖር የሚገባውን መተሳሰርና መጣበቅ እጅጉን ይጎዳል!

8⃣ ከአንዲት ሴት ጋራ በወሲብ መጣጣም አለመጣጣማችንን ለማወቅ የግድ አብረን መተኛት አያስፈልገንም‼️

🗝 👉ወሲብ ትዳርን ለማሟላት የተፈጠረልን ወይንም የተሠጠን ነገር እንጂ የትዳር የመጨረሻው ግብ አይደለም‼️እኔ የተማርኩት ነገር ይህንንም ነው፡፡

👉 ልክ ኬክ ከተጋገረ በኋላ በስተመጨረሻ ለማሳመርና ለማጣፈጥ ብለን እንደምናለብሰው ዓይነት ክሬም ወሲብም ሌሎች የግንኙነታችን ክፍሎች ሁሉ በሚገባ የሚሰሩ ከሆነ ወሲብም ለትዳራችን ልዩ ማጣፈጫ ይሆነናል ማለት ነው፡፡

📌 ሌሎች የግንኙነታችን ክፍሎች የሰመሩ ከሆኑ የወሲብ ህይወታችንም የተሳካ ይሆናል፡፡

🔑ለዚህም ነው ጥሩ የወሲብ ህይወት እንዳለኝ ለማወቅ ከወደፊቷ ሚስቴ ጋራ አብሬ በመተኛት መፈተሽ የሌለብኝ❗️

💢 በሌሎች የግንኙነት መስመሮች የተሳካልን ከሆንን በወሲብም ጉዳይ እንዲሁ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡

👉 ሌላም ያስተዋልኩት አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ወሲብን የግንኙነቶቻችን መሰረትና መለኪያ አድርገን የምንወስደው ከሆነ የተሳካ የወሲብ ሕይወት እንዳይኖረን እንቅፋት ይሆናል፡፡

📌እንግዲህ አስቡበት❗️
የፈጸምነውን ወሲብ ለግንኙነታችን ጤናማነት መለኪያ እያደረግን ሁሌም በመነጽር የምንፈትሸው ከሆነ ወዳቂ መሆናችን የማይቀር ነው፡፡

💯ለምን ቢባል እንድንደሰትበት የተሰጠንን ነገር በገዛ እጃችን መታሰሪያችን ስለምናደርገው ነው፡፡

💢 ይሁንና በሌሎች የግኝኙኘታችን መስመሮች ላይ ተግተን ከሰራንና ወሲብንም ዋና ጉዳይ ካላደረግነው ጣፋጭ የሆነ የወሲብ ህይወት እንዲኖረን የሚያስችለን መሥመር ውስጥ ገባን ማለት ነው፡፡

♦️ ስለዚህ የምንፈጽመውን ወሲብ ሁሌም አሪፍና አስደናቂ የማድረግ ግዴታ ውስጥ አንገባም ማለት ነው፤ ምክንያቱም ሁሌም አስደናቂ መሆን አይችልምና

..........ይቀጥላል


💢💢 @onlyfemaleb 💢💢
💢💢 @onlyfemaleb 💢💢
#ሰላም አንቺ ውድ እና የተከበርሽ
ላንቺ ብቻ የፍቅር_ግንኙነትን_ረጅም_ጊዜ_ለማቆየት_ሚረዱ_ነጥቦች
#አንደኛውና ዋነኛው ነገር
#ኩርፊያን ማቆም ነው ትንሽዋ
ነገር ምትገነው በኩርፊያ ም/ክ ነው በምንም ነገር
ከማኩረፍም ሆነ ከመበሳጨት በፊት ተነጋገሩ።
☞ሁለተኛው ነገር ምንም ነገር #አትመዝኚ/ን ለምን
አይደውልም ለምን ቴክስት አይፅፍም …………… #ለምን
ሚለውን ነገር ባጠቃላይ ከአይምሮዋቹ አሶጡት ምንም ነገር
አትመዝኑ ሁሉም የሆነበት የራሱ ም/ክ አለ።
#ሶስተኛው እና ግን ቀዳሚዊ ነገር ለሁሉም ነገር #አትቸኩሉ
በአንዴው ስለ አንድ ሰው ማንነት ሳታውቁ አበድንልህ
ሞትንልህ አትበሉ በስተመጨረሻ ስለ አፍቃሪያቹ ስሰሙ
መጨረሻው መዘዙ ለናተው ነው።
#ለወሲብ አትቸኩሉ ከስጋዊ እርካታ በፊት ልባዊ ፍቅራቹን
ማጠንከር አለባቹ #ወሲብ አስቀድማቹ ኃላ ፍቅራቹን ረስታቹ
ሁሌም ለስጋዊ እርካታቹ ብቻ መገናኘት ትጀምራላቹ
በመጨረሻም ግንኙነታቹ ይፈርሳል።
ሌላው ደሞ ሁሌም እንደምለው #ትኩረት #ትኩረት #ትኩረት ትኩረት አስፈላጊው ነገር ነው ለአጋራቹ #ትኩረት እና
#ጊዜ ስጡ።
☞ካለሱ ወይም ካለስዋ መኖር አልችልም ብላቹ አስቡ
ባሰባቹ ቁጥር ለአፍቃሪያቹ ትልቅ ቦታ እየሰጣቹት ትመጣላቹ
#ቅናትን አጥፉ
#ወሬ አትስሙ
#በሆዳቹ_ቂም ከመያዛቹ በፊት መነጋገር ልመዱ
☞ይሄ ቢሄድ ያይመጣል ምትሉትን ሁሉ ከሀሳባቹ አውጡ
#ጉልቻ_ቢቀያየር_ወጥ_አያጣፍጥም ዝም ብላቹ 10ፍቅረኛ
ከመያዝ ይልቅ ለህይወታቹ ሚያስፈልገውን ሰው መርጣቹ
#መስዋት ብትከፍሉለት ይሻላል።
#እህቴ መለያየትን እንደመፍትሄ አትውሰጂ
መለያየት መፍትሄ አይደለም ፍቅር እንደ ህፃን ልጅ ነው
በትግስትና በእንክብካቤ ነው ማደግ ያለበት ትግስት ይኑራቹ
ያለፈውን አታስታውሱ ባለፈ ሚዛን አትመዝኑ።
#share #share #share #share #share #share

@onlyfemaleb

ለማንኛውም ጥያቄ

@OnlyGirlsB
#ስለ_ጤናሽ

መረጃ ማንኛውም መረጃ ታገኝበታለሽ
ላንቺ ብቻ

I hope my '' husband '' has this reaction when he sees me on weeding day

@onlyfemaleb

#join & #share