ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
ላንቺ ብቻ
#አቢጊያ_ነኝ ሰላም ሰላም 🙏🙏 ምላሽ በ @onlygirlsb @ስጪ እሺ አንድ እህታችን የጠየቀችው ጥያቄ ላይ ተመስርቼ ሀሳቦቼን ልጀምር፡- - << 1 አንዲት ሴት ማንስትሬሽን ላይ ሁና sex ብታደርግ ጉዳቱ ምንድን ነው? 2 አሁንም ማንስትሬሽን ከጨርሰች በሆላ ወይ በ1 ቀን ወይም በ2 ቀን ልዩነት sex ብታደርግ እርግዝና ይፈጠራል? #share #ምላሽ @onlygirlsb
#አቢጊያ_ነኝ
ለጥያቄዎቹ ቀጥታ ምላሽ ከመስጠት ስለ ወር አበባ ሙሉ መረጃ ከዛን ጥያቄውን ይመልሳል እራሱ።
እስኪ በየተራ የወር አበባ አራት
ክፍሎችን እንመልከት ። የወር አበባ አንዲት
ሴት በ28 ቀናት ውስጥ የምታየው የደም
ፍሰት ተፈጥሮ ነው ። በዚህ ቀን ውስጥ
የወር አበባ ዑደት ሲከሰት ስስ
የሆነውውስጣዊ የማህፀን ክፍልና የደም ስር
ደም በብልት በኩል ያፈሳሉ ።
በዚህም ፍሰት ውስጥ ከ10ML እስከ
80ML ደም ሊፈስ ይችላል ። ይህም
የተለመደ ነፃና ጤናማ ፍሰት ነው ።
በዚህም ወቅት የተለያዩ እመሞች ይከሰታሉ ።
ከዚህም አንዱ የሆድ መሸማቀቅ እንዲሁም
እመም ይኖራል ። ምክንያቱም ደግሞ
ማህፀንና የሆድ ጡንቻ ተቆራኝተው ደም
ስለሚያስወጡ ነው ። ይህም ከ1-5 ቀን
ሊወስድ ይችላል ።
#share

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
ሁለተኛው የወር አበባ ዑደት ወቅት ደግሞ
Follicular phase ይባላል ከ1-13 ቀን
ባለው ውስጥ የሚከናወን ነው ። ይህም
ወቅት ጥቃቅን ቀዳዳዎች ያሉት ወንፊት
መሰል የማህፀን ውስጥ እንቁላል
የሚፈጠርበት አካል ለዝግጅት የሚነቃቃበት
ወቅት ነው ።
ደም እየፈሰሰ እንዴት ? ካላችሁ እንዲህ ነው

እድገትን የሚቆጣጠረው ሆርሞን አመንጪው
ጭንቅላት ላይ የሚገኘው Pitutary Gland
ሆርሞን በማመንጨት እንቁላል በሚያድግበት
በዚህ ክፍል ውስጥ ማነቃቃትን ይፈጥራል ።
በዚህ ኢደት ውስጥም ፔሬድ ከቆመ በኋላ
በዚህ ቀረጢት መሰል ክፍል ውስጥ እንቁላል
መዘጋጀት ይጀምራል ። ይህም ኢደት
እንቁላል እስኪጠነክር ድረስ 13 ቀናትን
ይወስዳል ። ይህ ዑደት የመዘጋጂያ ወራት
ነው ። በዚህ መሃል እርግዝና ሊፈጠር
ይችላል ።
ጥያቄ ካላችሁ ጻፉልኝ
@onlygirlsb
ለሌሎችም አድርሱ

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

ይህ ሦስተኛው የወር አበባ ዑደት ቀን ደግሞ
(Ovulation phase ) እንቁላል ከተዘጋጀ
ፔሬድ ከኤደ ከ13ተኛው ቀን በኋላ የበሰለው
እንቁላል የሚገኝበት 14ተኛው ቀን ነው ።
በዚህ ቀን ውስጥ እንቁላል አመንጪው
የማህፀን ክፍል እንቁላሎችን መልቀቅ
የሚጀምርበት ቀን ነው ።
pitutary gland /ሆርሞን አመንጪው
አካል እንቁላል እንዲለቀቁ ያደርጋል ።
በዚህ ወቅት የወንድ ስፐርምና የተዘጋጀው /
mature የሆነው የሴቷ እንቁላል ወደ
ማህፀን አልፈው ተገናኝተው ፅንሰት
ከተፈጠረ በማህፀን ውስጥ ይፀናል ወይንም
እርግዝና ይፈጠራል ማለት ነው ። ይህ ወሳኝ
የሆነ ብቸኛው ቀን ነው ። አያስከፍልም ! አያሳፍርም ! ሌላው ይድረሰው እራስ ወዳድ ወይ አይናፋር አትሁኑ
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
ይህ ደግሞ የመጨረሻውና #አራተኛው የወር
አበባ ዑደት ቀን ነው ። Luteal phase
ይባላል ። በዚህ ቀን ውስጥ እንቁላል
አመንጪው አካል ቀጣይ የወር አበባ ቀን
ከመምጣቱ በፊት እንቁላል ይለቃል በዚህ
ጊዜ ውስጣዊው የማህፀን ክፍል ይወፍራል
። ምናልባትም እርግዝና ሊፈጠር ይችላል ።
ግን የወንድን ስፐርም በሚገባ ያላገኘው
እንቁላል በመበላሸት ቀጣይ የወር አበባ ቀን
ኢደቱን ይጀምራል ።

@onlyfemaleb
#Join በሉ ለሌሎች እንዲደርስ
ይሄን አንብበሽ ጥያቄው ካልተመለሰ በውስጥ መስመር አውሩኝ
#አቢጊያ_ነኝ

#የወር_አበባ ቀረ ማለት እርግዝና ተፈጥሯል ማለት ብቻ አይደለም ። የወር አበባ በተለያዩ ምክንያቶች ሊቀር ይችላል ፤ ከእነዚህም ውስጥ ፦
#ጭንቀት
#የውፍረት መቀነስ ወይንም መጨመር
#የሆርሞን እጥረት
#የእርግዝና መከላከያ መድሐኒቶች
#የማህፀን ችግር ካለ
የወር አበባ 3-4 ሳምንትሊቀር ይችላል ።

ብዙ ለማወቅ #join_join

#share #share #share

@onlyfemaleb

@onlyfemaleb

@onlyfemaleb
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዉዶቼ #share በማድረግ ቁጥራችን ይብዛ።

@onlyfemaleb
በዚህ ሳምንት ብዙ ስለ ወር አበባ እናወራለን።

@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

ሞዴስን ለእረዥም ሰዓት መጠቀም አደጋ አለው !።








ጥናቶች እንዳመላከቱት የፍሰት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ ሞዴስን በየ አራት ሰዓት ውስጥ እያዩ መቀየርና ከዛ በላይ አለመጠቀም ። ፍሰቱ አነስተኛ ከሆነ ደግሞ እስከ ስምንት ሰዓት ውስጥ ፍሰቱን እያያችሁ መጠቀም እንዳለባችሁ ይመክራሉ ።





ከነዚህ ሰዓቶች በላይ መጠቀም ግን የብልት መመረዝ ሊያስከትልባችሁ ይችላል ።



በተጨማሪም ለባክቴሪያ መመረት ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር ለአንጀት ችግር ይዳርጋቹሃል ። ይህም አሳሳቢ ለሆነ የጤና ችግር ሊዳርጋችሁ ይችላል ።

ስለዚህም ሞዴስን በአግባቡ እየቀየራችሁ ልትጠቀሙ ይገባል ።

#share #like #comment

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
*የጡት ላይ ለውጥ *
ልክ እንደሰውነት መጠን መቀያየር የጡት መጠንም መቀነስና መጨመር ይኖራል ። ይህን ለውጥ እንደቀላል ሊታይ የማይገባው ጉዳይ ነው ። ምክንያቱም ብዙዎችን በስውር እያጠቃ ያለው የጡት ካንሰር በነዚህ ምክንይቶች ውስጥ መኖሩ ነው ።

ይህንን ጉዳይ በመዘንጋት በጡት ላይና አካባቢው የህመም ስሜት ከተከሰተ ነገሩን ስር ወደመስደድ ይወስደዋል ። ስለዚህም ከወትሮው ለየት ያሉ ነገሮች ከገጠሜችሁ ልትታዩት ይገባል ። አንዳንድ ሴቶች በሰውነታቸው ላይ የሚከሰቱትን ምልክቶችና ለውጦች በጥንቃቄ ሲከታተሉ ይስተዋላል ። ይህን ሁሉም ሴት ሊያደርገው የሚገባ ጥንቃቄ ነው ።
ለምሳሌ ፦
❖ የጡት መሰርጎድ
❖ ከጡት ጫፍ የሚወጣ ያልተጠበቀ ፈሳሽ
❖ የጡት ማቃጠልና የመደንዘዝ ስሜት መሰማት
❖ የጡት መቅላትና መጥቆር
❖ ወደሌላ የሰውነት ክፍል የማይሻገር የጡት አካባቢ ብቻ እመም ሲኖር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ።

በተጨማሪም በአሜሪካን በካንሰር ማህበረሰብ የጡት እብጠት ፥ የቆዳ መቆጣተ እንዲሀ የጡት ቆዳ መወጠር ሲኖር የጡት ካንሰር መኖሩን ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል ።

አንዳንድ ጊዜ የወር አበባ ከመምጣቱ በፊት የጡት ላይ እመም ቢኖርም የሚከሰተው በሆርሞን ለውጥ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ጤናማና የተለመደ ነው ። ከዚህ በተለየ መልኩ ግን ከላይ የጠቀስናቸውን መሰል ምልክቶች ካስተዋላችሁ የእክምና እይታና እርዳታ ያስፈልገዋል ። ስለዚ ዶክተር ጋር ቀርቦ ለማማከር ጥያቄ ውስጥ የማይገባ አማራጭ ነው ።
👍 @onlyfemaleb
share share sgare share
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
#አቢጊያ_ነኝ

ሰሞኑን ከወትሮው በተለየ የፕሮግራም መዘግየት እንደተፈጠረ ይገባኛል።

ለዚህ የራሱ ምክንያት ያለው ቢሆንም በተለይ እስከ ጥቅምት 5 ድረስ ዩንቨርሲቲ በሚገቡና ዩንቨርስቲ ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች የተለያዩ የምክርና የማዘጋጀት ስራ ስራ ስለምሰራ መደበኛ ፕሮግራሞችን ከጥቅምት 7 ጀምሮ እንደሚቀጥሉ ቃል ልገባላችሁ እፈልጋለሁ።

ለሁሉም አይነት ሃሳብ
@onlygirlsb

#join #join
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
በቅድምያ ግን በPeriod'ና በእርግዝና ጉዳይ የተጠየቀውን ጥያቄ በዝርዝር ላስረዳ፡ በዚሁ እናንተም እውቀታችሁን ትገመግማላችሁ።

"በቀን አቆጣጠር መሰረት እርግዝናን እንዴት መከላከል ይቻላል??
***********************
የቀን አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ የርግዝና መከላከያ መንገድ፡ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የማያስከትል ሲሆን፡
እርግዝናን ለመከላከል ውጤታማ የሚሆነው ግን ጊዜውን ጠብቆ ለሚመጣ የወር አበባ ብቻ ነው፡ በዚህ መሰረት በአንድ የወር አበባ ሳይክል ውስጥ ያሉትን ቀናቶች ዕርገዝና የመፈጠር ዕድልን እንደሚከተለው እንመልከት፦

➊ ከ1ኛው እስከ 7ኛው ቀን ያለው ጊዜ ከ95_100% #ዕርግዝና_አይፈጠርም💪


➋ ከ8ኛው እስከ 10 ኛው ቀን ያለው ጊዜ ከ40_60% #ዕርግዝና_ይፈጠራል🤔


➌ ከ11ኛው እስከ 16ኛው ቀን ያለው ጊዜ ከ80_100% #ዕርግዝና_ይፈጠራል🤷‍♀


➍ ከ17ኛው እስከ 19ኛው ቀን ያለው ጊዜ ከ40_60%
#ዕርግዝና_ሊፈጠር ይችላል😟


➎ ከ20ኛው እስከ 26ኛው ቀን ያለው ጊዜ ከ95_100% #ዕርግዝና_አይፈጠርም

➏ከ27ኛው እስከ 32ኛው ቀን ያለው ጊዜ የወር አበባ የሚታይበት ይሆናል፡ #ዕርግዝናም_አይፈጠርም👍

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
sharing is caring !!!

«የከንፈር ድርቀት ማጥፊያ ተፈጥሮአዊ ዘዴዎች»
የከንፈር መሰነጣጠቅ ዋና ዋና ምክንያቶች የቫይታሚን እጥረት፣ አለርጂ፣ ድርቀት፣ ማጨስ፣ የፀሃይ ጨረር እና ከባድ የአየር ንብረት ናቸው፡፡ በገበያ ላይ ብዙ የሚሸጡ የከንፈር መንከባከቢያዎች ቢኖሩም ተፈጥሮአዊ ዘዴዎች ግን የተሻሉ ናቸው፡፡

1. ስኳር - ሁለት የሻይ ማንኪያ ስኳርን ከአንድ የሻይ ማንኪያ ማር ጋር መደባለቅ፡፡ ከንፈር ላይ በመቀባትም ለተወሰነ ደቂቃ ማቆየት ከዛም በጣት ማሸት፡፡ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ፡፡

2. ማር- ማር በጣም ጥሩ ከንፈርን አለስላሽ ነው፡፡ ከዛም በተጨማሪም የመፈወስ እና ባክቴሪያዎችን ማስወገድ ንጥረነገር አለው፡፡-ተፈጥሮአዊ ማርን ከንፈርን መቀባት

3. የጽጌረዳ አበባ- አንድ እፍኝ የፅጌረዳ አበባን ማጠብ፣ፅጌረዳውን ከወተት ጋር ለተወሰነ ደቂቃ ማሸት - የተቦካውን የጽጌረዳ አበባ በቀን ለ 2 ወይም ለ 3 ጊዜ መቀባት፡፡
መልካም ጤንነት
@onlyfemaleb