ላንቺ ብቻ
1.6K subscribers
280 photos
11 videos
3 files
151 links
ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb
Download Telegram
#አቢጊያ_ነኝ
ሴትናጥበቧ

👱‍♀አንዲት ኮረዳ ወጣት ከዛች ማዶ ውሃ እየቀዳች በርቀት
የተመለከታት አንድ ወንድ አያት ጠጋ አላትና እስኪ
ንገሪኝ?''አላት!!
#የሴቶች_ተንኮል_ምን_ያህል_ነው? ሲል ጠየቃት

🧑እሷም በከፍተኛ ድምፅ ጩህት አሰማች... ልጁም ደነገጠና ምን
ሆንሽ? በማለት ጠየቃት እሷም እንድህ አለችው... ሊደፍረኝ
ነው ብየ ለሰዎች እነግራለሁ። ሰዎቹም ይገሉሃል አለችው።
እሱም ኢንድህ አለ .. ጥሩና አስተዋይ መስለሽኝ ግራ ያጋባኝን
ነገር ልጠይቅሽ እንጅ ባንች ላይ ክፉ ነገር መስራት አስቤ
አልነበረም አላት እናም ሰዎቹ ከዛ ማዶ ተንደርድረው መጡ....
#በባልዲ ውስጥ የነበረውን ውሃ በሯሷ ላይ
ለቀቀችው።...

⭐️ጩህቷን የሰሙት ሰዎችም ተንደርድረው ሲመጡ
ምን ሆነሽ ነው?ሲሉ ጥይቋት ውሃ ውስጥ ገብቼ ይሄ ልጅ ነው
ያወጣኝ በማለት ለሰዎቹ መልስ ስጠቻቸው
ሰዎቹም ልጁን አመሰገኑትና ወደቤታቸው ተመለሱ....ልጁም
ግራ በመጋባት ለምንድን ነው ይህን ያደረግሽው ሲል
ጠየቃት.
....➡️አየህ? ሴት ልጅ ተንኮሏ ይህ ነው። ሴት ልጅ
ማስገደልም ትችላለች ማስመስገንም ትችላለች አለችው።
እና ሴት ልጅ ስታከብራት ታከብርሃለች.. ስትንቃት ደግሞ
ታስገድልሃለች ሴትን ልጅ አክብራት ሴትን ልጅ ለማክበር
ምክንያት አያስፈልግም ምክንያቱም ከፈጣሪ ልዩ ስጦታ
የተሰጠች ሴት ነች እና።

በነገራችን ላይ የሴት ማለት የአቤል ምትክ ሲሆን ትርጉሙሙም ማስረሻ ወይም ምትክ ማለት ነው። ለዚህም ነው የአቤልን ታናሽ ወንድም ስም "ሴት" ተብሎ የተጠራው።


💪👸 ክብር ለሴት!!

@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
አማክሩኝ

<< እህቶች እስቲ አማክሩኝ

የወንድ ጓደኛ አለኝ። እናም ዕድሜ ከኔ ያንሳል። ሰፊ ልዩነት ሳይሆን 7 or 8 ወር ቢሆን ነው። ይህ ልጅ ፍቅረኛዬ መሆኑ ችግር ያለው ይመስልሻል??

@onlygirlsb

ላይ ሀሳብ ስጡ
ላንቺ ብቻ
አማክሩኝ << እህቶች እስቲ አማክሩኝ የወንድ ጓደኛ አለኝ። እናም ዕድሜ ከኔ ያንሳል። ሰፊ ልዩነት ሳይሆን 7 or 8 ወር ቢሆን ነው። ይህ ልጅ ፍቅረኛዬ መሆኑ ችግር ያለው ይመስልሻል?? @onlygirlsb ላይ ሀሳብ ስጡ
#ምላሾች

1
Awo betame chger alwe....mekneyatume tedare laye betame cheger yametale

2

Abigiya yena wed bezu neger endereda argeshignale amesgenalew ena hasabe setu balshine neger laye bena emnet kehawan kedmo ytftrew adame new selezi yeged esu libeltate yegebale meknyatum eswa mtserawe kesu gera gone new.

3
Anchi tanashinetu redemptions belibonash niket kaladerebish choir yelewim,,gn chigiru egna setoch ekoyawechachin( wendochin) beastesaseb enbeltalen maletim besal nen kenesu ga sininetsatser. So libishin aymiroshin masamen alebish. Yihe neger gn hulum lay ayseram keedmeyachew belay besalina asteway wendoch silalu, libachun medemametu aykefam
tanashinetu tesemtosh
#ምላሾች
4
አዎን ፤ በሚገባ ፍቅረኛሽ ሊሆን ይችላል ፤ ስለ እድሜ ከተነሳ አይቀር ሁል ጊዜ ወንዶች ከሴቶች መብለጥ አለባቸው ተብሎ ይነገራል ( according to biblical background ) እኔም እቀበለዋለው ፤ በጥንዶቹ የሰመረ የፍቅር ሕይወት ውስጥ ወንድ ስልጣን ፣ሃላፊነት እና ፍቅር በወንድ አባወራነቱ 😁 በኩል መገለጥ ስላለበት ፤ ከዚህ አንጻር እድሜው መብለጡ በተፈጥሮ ብስለትን ያጎናጽፈዋል በሚል ነው ። ነገር ግን እድሜ በልጦ ያለመብሰል በተቃራኒም እድሜ አንሶ እጅግ መብሰል ሊኖር ይችላልና ሁል ጊዜ የወንድ ከሴቲቱ በእድሜ መብለጥ መልካም ነው ወይም ስኬታማ ሕይወትን ይፈጥራል ማለት ያስቸግራል ፤ ይህንን ከግምት ውስጥ ብናስገባ መልካም ነው ። ሁል ጊዜ ተቃራኒ ጾታዎች ወደ #relationship ለመግባት ትልቁን ተቀዳሚ ሚና መጫወት ያለበት ግን በሁለቱ መካከል ያለ የፍቅር አንድነት ሊሆን ይገባዋል ። ፍቅር ለእኔ እንደሚገባኝ ያለ እውቀት የሆነ መነዳት አይደለም ፤ ለምሳሌ ሚስት የበሰለ አመለካከት አላት እንበል ባል ግን ከሷ ያነሰ ብስለት ቢኖረው ፤ የብስለታቸው ሁኔታ ብቻ ካጣመራቸው ፤ ሄዶ ሄዶ የሆነ ያለመግባባት ሲመጣ ግንኙነታቸው ሊበላሽ ይችላል ፤ ነገር ግን ጥንዶቹን አንድ ያደረገ ሃያል የፍቅር ጥምረት ካለ ፤ የተሻለው አካል ( የበሰለው ( ወንዱ ወይም ሴቷ ) በፍቅር ምክንያት በእውቀት የሆነ እይታ ስለሚመራ አንዱ የተሻለ እንዲሆንለት የራሱን ጥረት ያደርጋል ። ከላይ ባነሳነው ምሳሌ እውነተኛ ፍቅር በመካከላቸው ኖሮ ሴቲቱ ከወንዱ የተሻለ የበሰለች ከሆነ ፤ ፍቅረኛዋን ትወደዋለችና መጽሐፍ ገዝታ ልትሰጠው ትችላለች ወይም በአጭሩ አንዱ አንዱ ላይ በጎ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው ፤ እንዲህ ነው እንግዲህ ፍቅር ። ስለዚህ እህቴ የተሻለውን ነገር ተመልከቺ እላለሁ ።

ቻናላችሁን እከታተላለሁ ፤ በርቱ ፥ ቻናላችሁ አስተማሪ ነው ፤ ከዚህም በላይ ብትሰሩበት ደግሞ ተወዳጅ እና አስተማሪ ይሆናል ።
5

Ay lewumi fikira ...wonawu lesu yaleshi fikri nw esumi bihoni wuda ..takiyaleshi egna sefer be 2 amet yemitbelitewu Bali neberat ahun arijitewoli endat endemiyamiru bitay so chiger yelewum
5
I think yemiwodesh kehone malete lanchi ewnetegna feker menorun karegagetsh problemu altayegnem

6
ስንት የአለማችን famous ሰዎች አሉ እድሜ ያልገደባቸው።

7
የዕድሜ ጉዳይ አብዛኞቹ አስተያየት እንደሰጡት እንደቀልድ የሚታይ ነገር አይደለም። በዚህ በዕድሜ case ብቻ በህይወቴ ትልቅ ቦታ የምሰጠውን ሰው ርቄያለሁ፡ እጅግም ተፈትኜበታለሁ። ትዳር ላይ ሲገባ ደግሞ ኢፌክቱ በግልፅ መውጣትና መታየት ይጀምራል።

ስለዚህ አማክሩኝ ያለችው ልጅ ለሚመጣው የሳይኮሎጂ ጣጣ መዘጋጀት አለባት

@onlyfemaleb
8

Fev be wer kehone chigr yelewm almost z same new indene gn yemagebaw bale be 5 amet bibeltegh indet des indemilgh

9
Enam set lij ke wendu lij be edme meblet yalebat aymeslegnm
Ene ahun tanashen guadegna lemareg yemr ychenkegnal yehone responsibility neger ysemagnal so bzum mebelalet yelebachewm

10
ወንድ ልጅን ሁሌ ከሴት ልጅ አስበልጦ የማየት ችግር ይመስኛል። በዕድሜ፡ በደሞዝ፡ በዕውቀት ደረጃ ማግባት የሚፈልጉት እንዲበልጥ ይፈለጋል ወንዶች ደግሞ በተቃራኒው ነው የሚፈልጉት። እንኪ አሁን ደግሞ እኛ መብለጥ እንልመድ። ስለዚህ የእህቴ ጥያቄ ችግር የሌለው ይመስለኛል።

11
Age cigr yelewn gn wend kef sil arif ymeslgal gn wanaw fkl nw be 1 amet dres bebltew cgr ylewm bye asebalew

@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ
#ላንቺ_እና_ለእኔ
የጨጓራ በሽታ ቀላል መፍትሔዎች

1. ቆስጣ እና ካሮት - የቆስጣ ጁስ እና የካሮት ጁስን በመደባለቅ መጠጣት

2. ኬክ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለመጠቀም

3. ዝንጅብል -አነስተኛ የዝንጅብል ክፍል ወስዶ ከምግብ በፊት መውሰድ የምግብ ልመትን ያፋጥናል በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያን ያክማል፡፡

4. እርጎ -በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሠት የጨጓራ ህመም ተመራጭ ነው፡፡

5. ድንች - ግማሽ ብርጭቆ የድንች ጁስን በቀን 3 ጊዜ ምግብ ከመመገብ 15 ደቂቃ በፊት መጠጣት

6. ውሃ - በቀን ከ8-10ብርጭቆ ውሃ መጠጣት

7. በፆም ወቅት ፍሬሽ የሆኑ የፍራፍሬ ጁሶችን መጠቀም ለምሳሌ ወይን ብርቱካን አፕል ፓፓያ…

8. ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ አለመመገብ ምክንያቱም ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ የምግብ ልመትን ስለሚያዘገይ ትንሽ ትንሽ ምግብ ሠአትን ጠብቆ መመገብ

9. ሁል ጊዜ በባዶ ሆድ የሞቀ ውሃ መጠጣት

10. በአንድ ገበታ ላይ የተለያዩ ምግቦችን አደባልቀው አለመመገብ

11. ከመተኛቶ 2 ሠዓት በፊት እራት መመገብ

12. በቫይታሚን ቢ12 እና አይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ

13. ስጋና የስጋ ተዋፅዎ መቀነስ በተለይ ለእራት አለመጠቀም

14. አልኮል ሲጃራና ጫትን አለመጠቀም

15. ቡናና ሻይ መቀነስ

16. በሀኪም ያልታዘዙ መድሀኒቶች አለመውሰድ

17. ቅመማ ቅመም መቀነስ

18. ከዛሬ ጀምረሽ ተግብሪው፣ ለሌሎችም ሼር አድርጊው ✔️
ላንቺ ብቻ
አማክሩኝ << እህቶች እስቲ አማክሩኝ የወንድ ጓደኛ አለኝ። እናም ዕድሜ ከኔ ያንሳል። ሰፊ ልዩነት ሳይሆን 7 or 8 ወር ቢሆን ነው። ይህ ልጅ ፍቅረኛዬ መሆኑ ችግር ያለው ይመስልሻል?? @onlygirlsb ላይ ሀሳብ ስጡ
#አቢጊያ_ነኝ
…ሁላችሁም የየራሳችሁን ሀሳብ ሰጥታችሁናል። እኔ ደግሞ በእህቴም ጥያቄ ላይ ተመስርቼ የራሴን ምክር/ሀሳብ ልስጥ።

ብዙዎቻችሁ ጠቃቅሳችሁ ያለፋችሁት ነገር ነው። ሴት ልጅለ እድሜ Sensetive ናት!!
እያንዳንዱ አመት ለሴት ልጅ ትርጉም አለው። ለዚህ ነው ከወንድ ልጅ ይልቅ እኛ ሴቶች ለልደታችን ቀን ትልቅ ትርጉም የምንሰጠው።
ሲጀመር ሴት ልጅ ገና ከህፃንነቷ ነው ፈጣን አካላዊ ለውጦችና እድገቶችን ማሳየት የምትጀምረው። በኢ -መፍልኤ ፆታዊ ለውጦችም ቢሆን ሴት በጊዜ ነው ለውጦችን ማምጣት የምትጀምረው።
ሳይንስ እንደሚለው አንዳንዴም በምቹ ነሮ እና ጤና ላይ ያለች ሴት ከ 9 አመቷ የወስ አበባ ማየት ልትጀምር ትችላለች።

እናም ከአዋቂነት አንፃር ስናነፃፅር የወንድ ልጅ እውቀት የሚበስለው በመኖር ውስጥ ሲሆን የሴት ልጅ ግን ይበልጥ በተፈጥሮ የሚገኝ ነው ። ለዚህም ነው ሴት ልጅ በዕድሜ እኩያዋ ከሆነ ወንድ ጋር ሲነፃፀር የተሻለ EQ(Emotional Quetient) የማመዛዘን ብቃት የሚላበሱት።

ስለዚህ ሁለቱን ልዩነቶችን ለማመጣጠን በግንኙነቶች በተለይም በትዳር ጥምረት ጊዜ የወንዱ ዕድሜ ቢያንስ ቢያንስ በ2 እና ከዚያ በላይ ዓመት ቢበልጥ ተብሎ በስነልቦና ባለሙያዎች የሚመከረው።
ብዙ እህቶቼ "ፍቅር ካለ…" የሚል ነገር በተደጋጋሚ አንስታችኋል። በርግጥ እናንተም እንዳላችሁት አንዳንዴ Exeptional መገጣጠም ሊፈጠር ይችል ይሆናል። ነገር ግን ይሄው የዕድሜ ልዩነት በግልፅ ሊለይ የማይችል ለውጦችንና አነስተኛ የሚመስሉ ጭቅጭቆችን ይዞ ሲመጣ ይስተዋላል። ይህ ግን በይበልጥ ከተማና ከተማ ቀመስ ትዳሮችን ብቻ ነው የሚመለከተው።

ወደ እህታችን ጥያቄ ከመጣን ግን ልጁ የኔ እጣፋንታ ነው፡ ልዩ ስጦታዬ ነው፡ ፍቅራችንም ዘለቄታ እንዳለሁ ውስጤ ይነግረኛል የምትዪከሆነ/ከተሰማሽ ይህን የወራት ልዪነት: ከቁብ አለመቁጠር ትችላላችሁ። ነገር ግን በጥቂቱ እንኳን ጥርጣሬ ከተሰማሽ በግንኙነትሽ ላይ በድጋሜ እንድታስቢበት እላለሁ። ህይወት ቀልድ አይደለችም፡ ተጨማሪ ነገሮችን በውስጥ መስመር እናወራለን።

💄ንግስቶች ከያንዳንዱ ፅሁፍ ቁምነገሩን በልባችሁ መውሰድ እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ ማጋራት አትርሱ።

መጪው ጊዜ የእኛ ነው💪👸

@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

በፎሮፎር ተቸግረው
ፎረፎር ለማጥፋት የሚረዱ 4 ዘዴዎች
እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች ፎረፎር እንደሚያሰቃያቸው እንገነዘባለን:: ፎረፎር በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ይከሰታል። በተለይም በጸጉር ቆዳችን ላይ የሚገኙ ነጭ የደም ህዋሳቶች ሲሞቱ ነው ፎረፎር የሚከሰተው።
ፎረፎር ፀጉር እንዲያልቅና እንዲበጣጠስ ከማድረጉም በላይ የጸጉር ውበትንና ቆዳን ይጎዳል። ይሁን እንጂ በተለያዩ መንገዶች ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።
1. እርጎ እና በርበሬ
በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው እርሾ በአንዳንድ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ መጉረብረብ እና መንተብተብ ይፈጥራል። ለዚህም እንደ እርጎ ያሉ ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን የሚይዙ የምግብ አይነቶችን መጠቀም አይነተኛ መፍትሄ ነው።
ሁለት ማንኪያ የደቀቀ በርበሬ እና 1 ኩባያ እርጎ በመደባለቅ ፀጉራችን የሚበቅልበትን ቆዳ መቀባት እና ከአንድ ሰዓት በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይነገራል።
2. እሬት (ኦሊ ቬራ)
እሬት ፎረፎርን ለመከላከል በተለይም በኢትዮጵያ ለበርካታ ዘመናት ስንጠቀምበት ኖረናል።
በፎረፎር የተገጎዳ ቆዳን እሬት መቀባት የሞቱ ህዋሳቶችን ከማስወገዱም ባሻገር ለፀጉር እድገት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ይታመናል።
3. አፕል
አፕል ለፀጉር እድገት የሚረዳው ፕሮሳይኒዲን ቢ - 2 የተባለ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር የያዘ መሆኑን ተከትሎ ጤናማ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል።
ሁለት ማንኪያ የአፕል ጭማቂ ከሁለት ማንኪያ ውሃ ጋር በመቀላቀል መቀባት፤ ከዚያም ከ15 ደቂቃ በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ብሎም የፀጉር እድገትን ለማፋጠን ይረዳል።
4. ዝንጅብል
ዝንጅብል ለሰውነት መጉረብረብ ወይም መመረዝ የሚያጋልጡ ነገሮችን የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮች ይዟል። ስለሆነም ዝንጅብልን በመላጥና በማድቀቅ ከሰሊጥ ዘይት ጋር በመደባለቅና የፀጉር ቆዳን በመቀባት ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።
#አቢጊያ_ነኝ 💓:

💄ዘመናዊ ሴት ከሆንሽ💁‍♀

🏵Periodሽ መች እንደሚመጣ ቀድመሽ ማወቅ፤

🏵የውሸት እና የእውነት ፈገግታ መቻል፤

🏵የወንዶችን አለም መጋፈጥ መቻል፤

🏵ሴት መሆን ከባድ መሆኑን ማወቅ መቻል፤

🏵ረዥም ጆሮ_ጌጥ እና አጭር ጆሮጌጥ መቼ እንደሚደረገ ማወቅ ፤

🏵ሱሬ ወይም አጭር ቀሚስ መች እንደሚያምርብሽ፤

🏵ውሀ ቻፒስቲክ ወይም Color ቻፒስቲክ መች መጠቀም እንዳለብሽ………እነዚህን ሁሉ ማወቅ አለብሽ!!

ስለዚህ ሴት መሆን ራሱ ሰፊ ሳይንስ መሆኑን አምነሽ ራስሽን ከምን ግዜውም በላይ ለመጠበቅ ተነሺ፡ ያኔ ምርጧን አንቺነትሽን ታገኚዋለሽ።

@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

#የጡት_ካንሰር_ህመም_ ምልክቶች
ጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በወጣት ሴቶች ላይም የመከሰት እድል አለው፡፡
የጡት ካንሰር መነሻ መንስኤዎች በእርግጠኝነት የሚታወቁ ባይሆንም የተካሄዱ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ ለህመሙ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎችን በከፊል እንደሚከተሉት ቀርበዋል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም መንስኤዎች
1. እድሜ
በጡት ካንሰር የመጠቃት እድል በእያንዳንዱ 10 ዓመት የህይወት ዘመን በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
2. በዘር
ይህ የካንሰር አይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን በካንስር ህመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት ፣ እህት ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
3. ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ህመም የነበረባቸው
4. ልጅ ያልወለዱ ሴቶች ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን እድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች
5. ጡት ያለማጥባት
6. ደረታቸው ለብዙ ግዜ ለጨረር የተጋለጡ ሴቶች
7. ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር
8. ሲጋራ ማጨስ
የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች
1. በጡት ላይ እና በጡት አካባቢ የሚወጣ እባጭ
አብዘኛውን ግዜ የጡት ካንሰር ህመም ምልክት የሚሆነው ህመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ አብዛኛውን ግዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር አይነት ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
2. የጡት መጠን እና ቅርጽ መለያየት
አንዱን ጡት ከሌላኛው ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት
4.የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ
ይህ አይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት (ቀድሞ የነበረ) ወይም ተፈጥሮአዊ የሆነውን የጡት ጫፍ መገልበጥ አያካትትም
5. የህመም ስሜት
አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል ፡፡ ነገር ግን የጡት አካባቢ ህመም በአብዛኛው የካንሰር ህመም ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም የሚሰራጭባቸው ቦታዎችን የሚከተል የህመም ምልክት ሊኖረው ይችላል፡፡ ቀድሞ የሚሰራጨው ወደ ብብታችን ስር በሚገኘው(Lymph node ) በተላበው አካባቢ ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊስከትል ይችላል፡፡
የጡት ካንስር ቅድሚያ ካልተደረሰበት እና ህክምና ካላገኘ ወደ ጉበታችን እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተበራከተ ያለ የህመም አይት ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማናኛውም አይነት የህመሙ ምልክቶች የታዩት ሠው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በቶሎ መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል፡፡
ታድያ እንደዚህ አይነት እንብበሽ ለሌሎች ሼር አለማድረግ ራስ ወደጅነት ነው።
የኔ ውድ ለሴቶች ብቻ #share አድርጊው እሺ

@onlyfemaleb
@onlyfemaleb
🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝
#አቢጊያ_ነኝ
ሰላም ሰላም 🙏🙏

ምላሽ በ @onlygirlsb
@ስጪ

እሺ አንድ እህታችን የጠየቀችው ጥያቄ ላይ ተመስርቼ ሀሳቦቼን ልጀምር፡- -

<<

1 አንዲት ሴት ማንስትሬሽን ላይ ሁና sex ብታደርግ ጉዳቱ ምንድን ነው?

2 አሁንም ማንስትሬሽን ከጨርሰች በሆላ ወይ በ1 ቀን ወይም በ2 ቀን ልዩነት sex ብታደርግ እርግዝና ይፈጠራል?

#share
#ምላሽ
@onlygirlsb
4⃣4⃣4⃣
#አቢጊያ_ነኝ
# ለሴቶች # በጣም #ጠቃሚ #መረጃ
***********************************
# ጡት_ማስያዣን_እንደለበሱ
# መተኛት_የሚያስከትላቸው_በርካታ_ጉዳቶች
1. #የደም ዝውውር እንዲገታ ያደርጋል!
አንዳንድ የመሰርሰር ባህሪ ያላቸው ጡት ማስያዣዎች የጡት ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ በማድረግ የነርቭ እንቅስቃሴን ይገታሉ። የስፖርት ታይት የጡት ማስያዣዎችን እንደለበሱ መተኛትም የጡት ህዋሳትን እንደሚጎዳ
ይነገራል።
2. #የቆዳ መጉረብረብ ወይም መቆጣትን ያስከትላል!
የጡት ማስያዣ ማንገቻዎች እና አቃፊ ብረቶች ከቆዳ ጋር ሲጣበቁ ቆዳን የማድማት እና የማሳበጥ ባህሪ አላቸው። ይሁን እንጂ በእንቅልፍ ስአት ይህን የህመም ስሜት ላንረዳው እንችላለን።
3. #ምቾት ያሳጣል!
ምቾት ማጣትም ጡት ማስያዣን እንደለበሱ ከመተኛት የሚመጣ ችግር ነው። ጡት ማስያዣው የሚፈጥራቸው የህመም ስሜቶች ጥልቅ እንቅልፍ እንዳይወስደንም ያደርጋል።
4. #ቆዳ ያጠቁራል!
የጡት ማስያዣ መቆለፊያዎች እና ማንገቻ ገመዶች በቀጥታ ከቆዳ ጋር ሲጣበቁ ቆዳን የማበለዝ እና የማጥቆር ሀይል አላቸው።
5. #ፈንገስ እንዲፈጠር ያደርጋል!
እርጥበታማ እና ሞቃታማ ስፍራዎች ለፈንገስ መፈጠር ምቹ መሆናቸው ይታወቃል። የጡት ማስያዣን እንደለበሱ መተኛትም የጡት ፈንገስ እንዲፈጠር የሚያደርግ ሲሆን፥ ችግሩ በተለይም በበጋ ወራት ይባባሳል። በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው እና ሌሎች ምክንያቶች ጡት ማስያዣን ለብሶ መተኛትን እርም ሊያስብሉ እንደሚችሉ ጥርጥር የለውም።

#share እያደረግን ለሁሉም ሴቶች ይድረስ።

@onlyfemaleb
#አቢጊያ_ነኝ

ኦፕሬሽን መውለድ ጥቅሙና ጉዳቱ
ህጻናት ይህችን ዓለም በሁለት መንገድ ይቀላቀላሉ፡- በምጥ ወይም ደግሞ በኦፕሬሽን (surgical delivery by Caesarean section)፡፡ በአሁን ወቅት የህክምና አማራጭ ያላቸው እናቶች አምጦ ከመውለድ ይልቅ በኦፕሬሽን መውለድን እንደተሻለ አማራጭ ሲወስዱት ይታያል፡፡ አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎችም በሁለቱም መንገድ መውለድ ያለውን ጠቀሜታና የጎንዮሽ ጉዳት አስረድተው ውሳኔውን ለእናቶች ከመተው ይልቅ በኦፕሬሽን እንዲወልዱ እናቶችን ሲገፋፉ ይታያል፡፡ ለመሆኑ በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መፈቀድ አለበት? ያለው ጥቅምና ጉዳቱስ ምንድን ነው?
በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መወሰን አለበት?
1. አምጦ መውለዱ ለእናትየው ወይም ደግሞ ለህፃኑ ህይወት አደጋ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ሲታመንበት
2. ጽንሱ በጣም የፋፋ/የወፈረ/ ከሆነ እና የእናትየው ማህጸን ጠባብ ከሆነ
3. የጽንሱ አቀማመጥ በትክክል ካልሆነ ማለትም በእርግዝና የመጨረሻዎች ቀናት ጭንቅላቱ ወደታች ካልመጣ
4. በምጥ ወቅት ጽንሱ በቂ ኦክስጅን ካላገኘና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመው
5. መንታና ከዚያ በላይ ጽንስ ሲኖር
6. የተራዘመ ምጥ ሲኖር እና
7. እናትየው ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባት፤ የስኳር በሽተኛ ከሆነች፡ የHIV ቫይረስ ካለባት
ጥቅሙ፡-
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እናቶችን እና የጽንስን ህይወት ይታደጋል፡፡ እናቶች በምጥ ወቅት ሊሰማቸው የሚችለውን የተራዘመ ስቃይ ያስቀራል።
ጉዳቱ፡-
1. ጽንሱን ለማውጣት የሚቀደደው የሰውነት ከፍል ለመዳን ጊዜ ይወስዳል፤ በሰውነት ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳም በቀላሉ የሚድን አይደለም።
2. የእናቶችን የሆስፒታል ቆይታ ያራዝማል፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በፍጥነት አገግመው ልጆቻቸውን ለማጥባትም ሆነ ለመንከባከብ ይቸገራሉ።
3. የመጀመሪያ ልጃቸውን በኦፕሬሽን የወለዱ እናቶች ቀጣይ ልጆችን በተመሳሳይ ሂደት እንዲወልዱ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህም በማህጸን ግድግዳ ላይ ተደጋጋሚ ጠባሳዎች ያስከትላል፤ ቁስሉ በቶሎ ካልዳነ ደግሞ የማህጸን ግድግዳ ከሌላ የሰውነት ከፍል ጋር ሊጣበቅ ይችላል።
4. በምጥ ከሚወልዱ እናቶች ይልቅ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች ለከፍተኛ ደም መፍሰስና እንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በምጥ ከሚወልዱ እናቶች የመሞት ዕድላቸው ሶስት አጥፍ የሰፋ ነው።
5. በኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ የሽንትና የሰገራ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሊጎዱ ይችላሉ
****ስለዚህ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር እናቶች አምጠው መውለድን ቢመርጡ ይመከራል፡፡ አምጠው የሚወልዱ እናቶችም የተሻለ የመንፈስ እርካታ እንዳለቸው ይናገራሉ፡፡
# ካነበባችሁ በኋላ #ሼር ማድረግ #አይርሱ
@onlyfemaleb