Nejashi Printing Press
4.77K subscribers
656 photos
10 videos
6 files
768 links
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
Download Telegram
አዲስ መጽሐፍ ከነጃሺ
***
የመጽሐፉ ሥም ፡ ነፍሲያን ማረቅ
አዘጋጅ ፡ ኢብን አል-ጀውዚ
ትርጉም ፡ ሱለይማን ጠይብ ሐምዛ
የገጽ ብዛት፡ 84

ስለ መጽሐፉ ፡ መጽሐፉ ነፍሲያን በማረቅ እና አጉል ፍላጎቶቿን በማገድብ ወደ ትልቅ ደረጃ ማድረስ ስለሚቻልበት ሁኔታ ይዳስሳል፡፡

ከመጽሐፉ ፡ አላህ ለሰው ልጆች የሚወስነውም ሆነ የሚያመላክተው ነገር ሁሉ ፋይዳው ለእነሱ ነው። አንድም እንደ የምግብ ፍላጎት ዓይነት ጠቃሚ ስሜቶች እንዲኖሯቸው አለዚያም እንደ ቁጣ ኃይል የመሣሠሉትን ክፋቶችን ለመቆጣጠር ነው። የምግብ ፍላጎት ወሰን ሲያልፍ ወደ ስግብግብነት ያመራል። በዚህ ምክንያትም ጎጂ ይሆናል። በተመሳሳይም የሰው ቁጣ ሚዛን ሲስት ጥፋት ማስከተሉ አይቀርም።
የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ በአእምሮ እና በልብ አውታሮች ውስጥ ማስረፅ፣ ማንበር እና ‹ሀዋእ›  (ሥጋዊ ዝንባሌ) ጉዳት እንዳያስከትል መድፈቅ የሚቻልበትን መንገድ መጠቆም ነው። አለፍ ሲልም የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ የሚቃወምን ሥጋዊ ዝንባሌ ፈውሶችን ያመላክታል።
መጽሐፉ በአጫጭር ሰላሳ ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው።

https://nejashibooks.com/

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://t.me/Nejashipp
አስደሣች ዜና ለመጽሐፍ ወዳጆች
****

የሦስተኛውን የሙስሊሞች ኸሊፋ የታላቁን ሰሐባ ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን (ዙን-ኑረይን) ታሪክ የያዘ መጽሐፍ በነጃሺ ማተሚያ ቤት ታትሞ በዛሬው ዕለት በገበያ ላይ ውሏል።

መጽሐፉ 414 ገፆች አሉት።

አዘጋጁ ሸይኽ ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ ሶላቢ ናቸው።
ኡስታዝ አሕመድ ሑሴን ተርጉሞታል ።


መርካቶ ታላቁ አንዋር መስጊድ መግቢያ በር ላይ ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል።

ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ!!

https://nejashibooks.com/

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://t.me/Nejashipp
መላው ሙስሊም ማኅበረሰብ እንኳን ለዒድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሣችሁ።
ዒዱኩም ሙባረክ!
ወኩሉ ዓሚን ወአንቱም ቢኸይር ።

ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር


https://nejashibooks.com/

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://t.me/Nejashipp
የህሊና ዕረፍቶች (ከቁጥር 1- ቁጥር 4)
***

መጽሐፎቹ ውስጥ

* የተለያዩ መሳጭ ጥበባዊ ንግግርች፣
* የታላላቅ ሰዎች አባባሎች፣
* አጫጭርና ውብ የሆኑ ግጥሞች፣
* መረጃዎችና ቆንጆ ሀሳቦች ፣
* ቀልብን የሚያለሰልሱ ምክሮች፣
* አዝናኝ እና አስተማሪ መልእክቶች እና ሌሎችንም
* የማይሰለቹ መጣጥፎችን ያገኙባቸዋል፡፡

ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኟቸዋል።
ፈተናዎች፣ እኛን ከኀጢአት ለማጽዳት የሚከሰቱበት ጊዜ አለ።
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፦
“አንድን ሙስሊም ድካም፣ ህመም፣ ትካዜ፣ ሐዘን፣ ወይም ጉዳት -የእሾህ መውጋት ቢሆንም እንኳን- አይደርስበትም፤ አላህ የተወሰነውን ኀጢአቱን የሚያብስለት ቢሆን እንጂ።” (ቅጽ 7፣ ምዕራፍ 70፣ ቁጥር 545)

አንድ ታላቅ ገጣሚ እንዳለውም፦
“አንድ ሰው ምንጣፍ ሲደበድብ ውጥኑ ምንጣፉ አይደለም። ምንጣፉ ውስጥ ያለው አቧራ እንጂ።”

አንጥረኛ ወርቅን የሚቀጠቅጠው ሊያጠፋው አይደለም። ሊያፀዳው ነው።
አላህም ምእመናንን ለማጽዳት ልክ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን በፈተና እንደሚያፀዳቸው በቁርኣን ነግሮናል።
ወርቅ በእሳት ሲለበለብ ጉድፎቹ ይወገዱለታል።
የአማኝ ልብ በፈተና እንዲያልፍ ሲደረግም የቀልብ ላይ እድፎች ይወገዳሉ።

የባዶነት ስሜት መንስኤው እና ፈውስ
በያስሚን ሙጃሂድ
ትርጉም - ሱለይማን ጠይብ።


https://t.me/Nejashipp

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/
የሚያጎለብቱ ፈተናዎች
*,
ፍጥረትን ስናጠና የአላህን ሱንና (መንገድ) የተመለከቱ በርካታ እውነታዎችን እናገኛለን። ለምሳሌ፣ አጥንታችን ሲሰበርና መልሶ ሲድን፣ አጥንቱ ተሰብሮ የዳነበት ጥግን ቦታ ላይ የበለጠ ጠንካራ ይሆናል። ዓለማዊ ፈተናዎቻችንም ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። ከታላላቅ የሱና ምሁራን አንዱ የሆኑት አል-ዒዝ ኢብን ዐብዱሰላም “ፈተናዎችና 17 ፋይዳዎቻቸው” የሚሰኝ ዕውቅ ድርሰት አላቸው።

በዚህ ሥራቸው ሸይኹ፣ ፈተናዎች የአላህን የኃያልነት (ሁሉን ቻይነት) ልክ እንድንረዳ እንደሚያደርጉ አብራርተዋል። ብዙውን ጊዜ የሕይወታችን መሪዎች ራሳችን እንደሆንን እናስባለን። ሕይወታችንን ራሳችን የምንሾፍር ይመስለናል። ሁሉን ነገር የማበጀት እና ሰባራን ሁሉ የመጠገንን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት እንጥራለን። ይህ ደግሞ መከራ ውስጥ ይከተናል። ዘና ማለት አንችልም። እንቅልፍ ካይናችን ይሸሻል።

ብዙዎች፣ ሁኔታዎች ላይ ሥልጣን አለን ብለው በማሰባቸው ምክንያት ውስጣዊ ሰላምን አያገኙም። በሕይወታችን ላይ የተለገሥነውን ውሳኔ የማሳለፍ ክህሎት ትክክለኛ ሥልጣን አድርገን እንቆጥረዋለን። ፈተናዎችና መከራዎች ደግሞ አላህ በእኛ ላይ የማይገሠሥ ሥልጣን ያለው መሆኑን እንድናስታውስ ያስገድዱናል። አላህ አል-ቀሃር (አስገዳጅ) እና አል-ዐዚዝ (አሸናፊ) ነው።

እናም ይህ ዕውቀት ወደሚያድነንንና ድህነታችንን በማስታወስ አላህን እንድንከጅል ወደሚያደርገን ግንዛቤ ይመራናል። ከአላህ ፊት መልካም የማርገድ ስሜት ውስጣችን ያሰርፃል። “በአላህ ቢሆን እንጂ ኃይልም ሆነ ብልሃት የለም፣” የሚለውን ወርቃማ መርህ በገቢር ያስተምረናል። ሰዎችን ሁሉ ወይም ሁሉንም ነገር የምናድን እኛ አለመሆናችንን ይዘክረናል።
የምናስተካክለው እኛ እንዳልሆንን፣ ኃላፊነትም እንዳልተጣለብን ያስገነዝበናል። ይህ ኃላፊነት የአላህ መሆኑን ጭምር።

ይህ ግንዛቤ ሕይወታችንን መታደግ የሚችል ነው። ከሰዎች ጋር ያሉንን ግንኙነቶች ማረቅ ይችላል። የሰው ልጅ ልቦና የዓለምን ክብደት እንዲሸከም አልተበጀም። ይህን ክብደት መሸከም የሚችል አላህ ብቻ ነው። ይህን ጭነት ለሰማይና ለምድር ባለቤት እስካላስረከብን ድረስም ይህን ከንቱ ክህሎታችንን በሚያፈርስ ጫና ሥር ስንሰቃይ መኖራችን አይቀርም።

https://t.me/Nejashipp

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/
በየዕለቱ እንድንሰግድ የታዘዝናቸው የአምስት ጊዜያት ሰላቶች፣ የልባችን ኦክሲጅን (እስትንፋስ) ናቸው።

ሰላት የተውን ጊዜ መተንፈስም ያቅተናል። አካላዊው ልባችን ያለ ኦክሲጅን መኖር እንደማይችለው ሁሉ፣ መንፈሳዊው ልባችንም ያለ ዚክር (በተለይም ያለ ሰላት) ሕያው ሊሆን አይችልም።

የሰላት መድኃኒት በታወቁ (ተለይተው በተወሰኑ) ሰዓቶች እንዲወሰድ በአላህ የታዘዘው ያለ ምክንያት አይደለም። ልክ አንድ ሐኪም እንደሚያዘው መድኃኒት፣ የሰላትን ክፍለ ጊዜ ጠብቀን መስገድ አለብን። ምክንያቱም ሐኪሙ (አላህ) ያን ያደረገበት እርሱ ብቻ የሚያውቀው ምክንያት አለው።
ለአላህ ከዶክተር ጋር የማይነፃፀር እጅግ የላቀ መገለጫ እንዳለው ሳይዘነጋ።

የፈጅር ሰላት፣ ፀሐይ ከመውጣቷ ጥቂት ቀደም ብሎ እንዲሰገድ ሲወስን ያን ያደረገበትን ምክንያት ያውቃል። ሐኪም ያዘዘልንን ሕይወት አድን መድኃኒት በየዕለቱ የተወሰነውን እየተውን ብንወስድ ምን ይከሰታል? በቀን አምስቴ እንድንወስድ የታዘዝነውን መድኃኒት፣ ማታ ከመኝታ በፊት አምስቱንም ብንወስድ ምን ይፈጠራል? መቼም መድኃኒቱ በታዘዘው ሰዓት መወሰድ የሚኖርበት እኛን በሕይወት እና በጤና ለማቆየት እንደሆነ አይጠፋንም።

የባዶነት ስሜት
ያስሚን ሙጃሂድ

ትርጉም ፡ ሱለይማን ጠይብ

https://t.me/Nejashipp
https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://t.me/NejashiPP/1575
አዲስ አበባ ውስጥ በሞተረኛ
ወደተለያዩ የአገሪቱ ከተሞችና የውጭ አገራት በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ይዘዙን

ስልክ

+251945858585
የሐጅ ግዴታነት በቁርኣን እና በነቢያዊ መልእክት (ሐዲሥ) የጸና ነው። ስለዚህ ማንኛውም አካላዊም ሆነ ቁሳዊ አቅሙ የተሟላለት ወንድ ይሁን ሴት ሙስሊም፣ በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ሐጅ ማድረግ ይኖርበታል።

ሐጅ እየደረሠ ነው።

ውድ አንባቢያን! ይህ መጽሐፍ በሐጅ እና ዑምራ ዙርያ የተዘጋጀ ድንቅ መጽሐፍ ነው።
የመጽሐፉ ዋና ዓላማ በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሐጅ እና ዑምራ ለሚጓዙ ምእመናን በሥርዓቱ ዙርያ የእስልምናን አስተምህሮ በትክክል አውቀው መተግበር ይችሉ ዘንድ መረጃ መስጠት ነው።

መጽሐፉ ምንም እንኳ አጠር ያለ ቢሆንም በጉዳዩ ዙርያ ጠቃሚ መረጃዎችን ይዟል።

ግለሰቦች፣
በሐጅና ዑምራ ዙርያ የሚሠሩ ተቋማትና ኤጀንሲዎች መጽሐፉን ይጠቀሙበት ዘንድ እንመክራለን።

https://t.me/Nejashipp

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/
ከ “አርዓያ ቁጥር አንድ” መጽሐፍ የተወሰደ
****
ይህ መጽሐፍ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) የተግባቦት መንገዶች ይዳስሳል፡፡ መጽሐፉ ቀጥር አንድ እና ሁለት አለው፡፡

አዘጋጁ ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር ነው፡፡
አንብቡት ትጠቀሙበታላችሁ፡፡
***
ከመጽሐፉ ፡-

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከሁሉም በላይ በዱዓ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። እንደሰው ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ ያደርጋሉ። ከዚያም ነገረ ጉዳያቸውን በአላህ ላይ ይተዋሉ። በሁሉም ነገር ላይ የመጨረሻውን ስኬት አላህን አጥብቀው ይለምናሉ። ከርሱ ፍቃድ ውጭ የሕይወትን ሚዛን መጠበቅና ለስኬት መብቃት እንደማይቻል ያስተምራሉ። ትልቁን የሕይወት ስዕል በሚይዙና አጠቃላይነት ባላቸው የዱዓ ቃላት ላይ ያተኩራሉ። ለአብነት የሚከተሉትን እንመልከት፤-

* ‹‹አላህ ሆይ! ፍቅርህን አንተን የሚወዱ ሰዎችንም ፍቅር ወደ ፍቅርህ የሚያደርሰኝንም በጎ ተግባር እለምነሃለሁ። አላህ ሆይ! ፍቅርህን ከነፍሴ ከቤተሰቤና ከቀዝቃዛ ውሃ ይበልጥ ለእኔ ተወዳጅ አድርግልኝ።›› (ቲርሚዚ የዘገቡት)

* ‹‹አላህ ሆይ! ከማይጠቅም ዕውቀት አንተን፣ አንተን ከማይፈራ ልቦና ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌለው ዱዓ በአንተ እጠበቃለሁ።›› (ሙስሊም የዘገቡት)

*‹‹ዱዓ (ማድረግ) አምልኮት ነው።›› (አቡ ዳዉድና ቲርሚዚ)

* ‹‹አላህ ያልለመነውን ሰው በርሱ ላይ ይቆጣበታል።›› (ቲርሚዚ የዘገቡት)

ሰው የቱንም ያህል ቢያውቅ፣ የቱንም ያህል ቢጥር፣ የቱንም ዓይነት ደረጃ ላይ ቢደርስ፣ሁሌም ቢሆን የሚቀሩት ነገሮች አሉት። የሚያንሰው ዕውቀት፣ ያላገኘው አጋጣሚ፣ ያላሸነፋቸውና የሚታገሉት ስሜቶች ያሉበት ነው። በሌላ አባባል ሰው ውስን ነው። የሚሆነውን ለመሆን የፈጣሪውን እርዳታ ዘወትር መጠየቅ አለበት። በዱዓ ወደ ተመዛዘነ ሕይወት መቅረብ ይችላል።

ከአባባሎች
***
* ‹‹ጥልቅ የልብ ምኞት በዱዓ መልስ ያገኛል።›› (የሰዕድ ጥበቦች ገ/157)

* ‹‹ዱዓ በድርጊት ሊደገፍ ይገባል። አለዚያ ባዶውን ይቀራል።›› (የሰዕድ ጥበቦች /ገ/157)

* ‹‹ጭንቀትና ግራ መጋባት ወደ ዱዓ መሩኝ። ዱዓ ግራ መጋባትንና ጭንቀትን አስወግድልኝ።›› (የሰዕድ ጥበቦች /ገ/157)

https://t.me/Nejashipp

https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/
ከኢሕያእ ዑሉሚዲን ገፆች
አዘጋጅ ፡ ኢማም አል-ገዛሊ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ ABX (PhD)
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል ።

በትዕዛዝ አዲስ አበባ ውስጥ በሞተረኛ
ክልሎች እና ውጭ አገር በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን ።

ስልክ - +251945858585