ረመዷን ቁርአን በብዛት የሚነበብበት ወር ነው። ቁርአን ዝምብሎ ብዙ ለመጨረስ ብቻ በጥድፊያ ማንበብ ከቁርአን ተጠቃሚነትን ያሳጣል። በቁርኣን ተጠቃሚ ለመሆን ከሚያስችሉን መንገዶች መካከል ጥቂቶቹን እነሆ፦
1- ቁርኣንን ማንበብ ከመጀመር በፊት፡
አላህ ይህን ቁርኣን እንድንጠቀመው ልቦናችንን ይከፍትልን ዘንድ በተማጽኖ ሆነን ዱዓእ ማድረግ ያስፈልገናል። አላህ በቁርኣን እንድናስተነትንና በርሱ ልባችን እንዲነካ እንዲያግዘን ደጋግመን እንጠይቀዋለን። ይህ ዱዓእ ትልቅ ሚና ያው ሲሆን፣ ለልቦና ቁርኣንን እንዲቀበል ጥሩ መነሳሳት ይፈጥራል።
2- ቁርኣንን አብዝቶ ማንበብ፡
ከቁርኣን ጋር ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ ማንበብ ሌላኛው በቁርኣን እንድንጠቀም የሚያስችለን ነው። ቁርኣንን የምናነብበት ቦታ በተቻለው መጠን እርጋታ ያለበት ቦታ ቢሆን በላጭ ነው። ረብሻና ጫጫታ ካለባቸው ቦታዎች ርቆ ማንበብ ለአዕምሮ ምቹ ነው። ከመቅራታችን በፊት ደግሞ ዉዱእ ማድረግና ጥርስን መፋቅ (ሲዋክ) መርሳት የለብንም።
3- ቁርኣንን ውብት ባለው ድምፅ ማንበብ፡
ቁርኣንን አሳምሮ ማንበብ ትልቅ ድርሻ አለው። ለውስጣችን ደግሞ ስሜት ይሰጣል። ግንዛቤንና ማስተንተንን በመፍጠር ረገድ ሚናው ከፍ ያለ ነው። ይህን ጊዜ በውስጣችን ላይ ከመረዳትና በርሱ ከመገሰጽ ጋር ኢማን ይመጣል።
4- በተረጋጋና በሐዘን ስሜት ላይ ሆኖ ማንበብ፡
ቁርኣንን በምናነብበት ጊዜ ሕግጋቱን ጠብቀንና ቆም ብለን ማስተንተን ባለብን ቦታ እየቆምን፣ ማዘን ባለብን ቦታ እያዘንን መሆን አለበት። በሐዘን (ልብን በሚሰብር ቅላጼና ስሜት) ላይ ሆነን በልባችን ላይ ተጽእኖው እንዲያርፍ ማድረግ አለብን።
5- የአንቀጾችን ጥቅል ግንዛቤ መረዳት መቻል፡
የአዕምሮ ሥራ ቁርኣን ስናነብ መረዳትና መገንዘብ ነው። የእያንዳንዱ አንቀጽ ጥቅል መልዕክት ለማወቅ ከሞከርን ንባባችን እንዳይቋረጥ ይረዳዋል። ይህ ማለት እያንዳንዱን የቁርኣን አንቀጽ ቃል በቃል ትርጉማቸውን ከጀርባቸው ያዘለውን ነገር ማወቅ ማለት አይደለም። ጥቅል የአንቀጹን ትርጉም ወይም ከአንቀጹ ጋር የተያያዙ መልዕክቶችን ከተረዳን በቂ ነው። ይህን ማድረግ በመጀመራችን በአጭር ጊዜ ደረጃችን ወደ ከፍተኛው ቁርኣንን ማስተንተን እንዲሁም በርሱ ተጽዕኖ ውስጥ የምንጓዝበት መንገድና ስሜት ላይ ያደርሰናል።
6- ከቁርኣን ጋር ጥሩ ግንኙነት ለማድረግ መታገል፡
ቁርኣን ልክ አንተ ላይ እንደወረደ፣ አንተን እንደሚያናግር ሆነ በሕይወትህ ላይ ልፋትና ተግባርህ ሁሉ ከርሱ እንዲቀዳ መታገል፣ አንቀጾቹ የሚጠይቁበት ቦታ ስትደርስ እንደሚያናግርህ ማሰብ፣ ዱዓእ በሚያደርግበት ጊዜ አሚን ማለትን ያካትታል።
ውስጥህን የሚያነቁ አንቀጾችን ደጋግሞ ማንበብ፡ ልቦና ላይ ተጽእኗቸው ከፍተኛ የሆኑ አንቀጾችን ደጋግሞ ማንብብ ለልቦና ብርሃን ሲሆን በውስጥም ኢማንን ይቀሰቅሳል።
7- ከጎንህ አጫጭር የቁርኣን ትርጉም (ተፍሲር) ቢኖር መልካም ነው፡
ቁርኣንን በምናነብበት ጊዜ ትርጉሙን በቀላሉ ለማወቅ በምንቸገርበት ጊዜ የቁርኣን ትርጉሞችንና ማብራሪያዎችን ብንይዝ ይመረጣል። ነገር ግን ቁርኣንን አንብበን ከጨረስን በኋላ ወደ ትርጉም መሄዱ በላጭ ነው። ቁርኣኑ እየተነበበ ከድባቡ ሳይወጣ ቃላትን መፈለግና ወዲያው መመለስ የሚቻልበት አጋጣሚ ካለ ግን ቢደረግ ችግር የለውም።
ምንጭ ፡ ጥቂት የረመዷ ቀናት መጽሐፍ
ዐብዱረዛቅ ነጋሽ እንደተረጎመው
https://nejashibooks.com/
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://t.me/Nejashipp

ረመዷን የቁርኣን ወር
***
ደጋጎቹ ቀደምት አባቶቻችን (ሥራቸውን አላህ ይውደድላቸውና!) በረመዷን ወር ውስጥ ቁርአን መቅራት ያበዙ ነበር፡፡ ሶላት ውስጥ ሆነውም ሆነ ከሶላት ውጪ ቁርአን ያነብቡ ነበር፡ (አላህ ይዘንላቸውና!)
ኢማም አዝ-ዙህሪ ይህ ታላቅ ወር በቀረበ ጊዜ፡- “ቁርአን የሚነበብበት፣ የሚያበሉበትና የሚያጠጡበት ወር መጣ፡፡” እያሉ ይቀበሉት ነበር፡፡
ማሊክ ኢብን አነስ የረመዷን ወር የገባ ጊዜ ሐዲስ ማንበባቸውንና ከዕውቀት ማዕዶች ላይ መገኘታቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ፊታቸውን ወደ ቁርአን ብቻ ያዞሩ ነበር፡፡
ቀታዳህ (አላህ ይዘንላቸውና!) በአዘቦቱ በየሰባት ሌሊቶች፣ በረመዷን ውስጥ ደግሞ በየሦስት ሌሊቶች፣ እንዲሁም በመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት ውስጥ ደግሞ በእያንዳንዷ ሌሊት ሙሉ ቁርአንን አንብበው ይጨርሱ ነበር፡፡
ኢብራሂም አን-ነኸዒይ (አላህ ይዘንላቸውና!) በረመዷን ወር ውስጥ በየሦስት ሌሊቱ፣ በመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት ደግሞ በየሁለት ሌሊቱ ሙሉ ቁርአንን አንብበው ይጨርሱ ነበር፡፡
አል-አስወድ (አላህ ይዘንላቸውና!) የረመዷን ወር ሲገባ፣ በየሁለት ሌሊቱ ቁርአንን አንብበው በመጨረስ ሙሉ ወሩን ያጠናቅቁ ነበር፡፡
ከቁርአን ጋ አብሮ የመኖሩ ጉዳይ ግን በንባብ ብቻ የሚሆን አይደለም፡፡ የተቀረውን ዓለም ረስቶ፣ ነፍስን ከመለኮታዊው መጽሐፍ ጋር ብቻ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ እኔ የት ላይ ነኝ? ብሎ በጥልቀት ከነማን ጋር ነኝ? ብሎ ወደ ውስጥ መመልከትን ይፈልጋል፡፡
ሃሳቡን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ የአል-አህነፍ ቢን ቀይስን ሁኔታ እንደ ምሳሌ ወስደን እንመልከት፡-
አንድ ቀን፣ አል-አሕነፍ ኢብን ቀይስ ተቀምጠው እያለ ድንገት አንድ የቁርአን አንቀፅ ትዝ አላቸው፡-
لقد انزلنا اليكم كتابا فيه ذكركم افلا تعقلون
الأنبياء: ١٠
"ክብራችሁ በውስጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደናንተ በርግጥ አወረድን። አታውቁምን ?" (አል-አንቢያእ፡ 10)
ከላይ የተጠቀሰው አንቀፅ በአዕምሯቸው ውል ያለ ጊዜ፣ የቁርአን ገፆችን ገልጬ እራሴን መፈለግ አለብኝ፣ እኔ ማን እንደሆንኩና እነማንን እንደምመስል ማወቅ ይኖርብኛል አሉ፣ ከዚያም ሌላውን ነገር ሁሉ ወዲያ ጣሉና ተጠቃለው ገቡ፡፡ በታላቅ ተመስጦ ማንበብ ጀመሩ፡፡ በንባባቸውም የሚኖሩበትን ዘመን ትተውና እጅግ እርቀው ወደ ኋለኛው ዘመን በመመለስ ፍለጋና ንፅፅሩን ተያያዙት፡፡

ትላልቅ ታሪኮችን ሰፊ ምርምር በማድረግ አደራጅተው በመፃፍ የሚታወቁት ሸይኽ ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ አስ-ሶላቢ በዚህ በተከበረው ወርሀ ረመዷን የ25 የአላህ ነቢያትና መልእክተኞችን ታሪክ የያዘ ትልቅ ጥራዝ 18 ቅጽ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ህትመቱ አልቆ መረከባቸውን ገልፃዋል፡፡
የመፃሕፍቱ ሕትመት የተከናወነው ደማስቆ በሚገኘው ዳር ኢብኑ ከሢር ነው፡፡
በመፃሕፍቱ ከፍጥረት መጀመር ጀምሮ የአላህ ነቢያቶች የአደም ዐ.ሰ. ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ኢብራሂም፣ ሉጥ፣ ኢስማዒል፣ ኢስሐቅ፣ የዕቁብ፣ ዩሱፍ፣ ሹዐይብ፣ ሃሩን፣ ሙሳ፣ ዳውድ፣ ሱለይማን፣ አዩብ፣ ዩኑስ፣ ኢድሪስ፣ ዙልኪፍል፣ ኢልያስ፣ አል-የሰዕ፣ ዘከርያ፣ የሕያ፣ ዒሳ እና የመጨረሻው ነቢይ የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ታሪኮች የተካተቱበት ነው፡፡ እነኚህ ሀያ አምስቱ የአላህ ነቢያት ቁርኣን ውስጥ ሥማቸው ተጠቅሷል፡፡
ዶ/ር ዐሊ ሶላቢ ከዚህ ቀደም ያዘጋጇቸው ግዙፍ መፃሕፍት ማለትም የነቢዩ ሙሐመድ የሕይወት ታሪክ የያዘው ለዓለማት እዝነት፣ እንዲሁም የአስ-ስዲቅ አቡክር እና የአል-ፋሩቅ ዑመርን ሙሉ የሕይወት ታሪኮች የያዙ መፃሕፍት በኡስታዝ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል) በነጃሺ ማተሚያ መታተማቸው ይታወሳል፡፡
ማተሚያ ቤታችን የዙን-ኑረይን ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ በቅርቡ በገበያ ላይ ያውላል፡፡
https://nejashibooks.com/
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://t.me/Nejashipp
የመፃሕፍቱ ሕትመት የተከናወነው ደማስቆ በሚገኘው ዳር ኢብኑ ከሢር ነው፡፡
በመፃሕፍቱ ከፍጥረት መጀመር ጀምሮ የአላህ ነቢያቶች የአደም ዐ.ሰ. ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ኢብራሂም፣ ሉጥ፣ ኢስማዒል፣ ኢስሐቅ፣ የዕቁብ፣ ዩሱፍ፣ ሹዐይብ፣ ሃሩን፣ ሙሳ፣ ዳውድ፣ ሱለይማን፣ አዩብ፣ ዩኑስ፣ ኢድሪስ፣ ዙልኪፍል፣ ኢልያስ፣ አል-የሰዕ፣ ዘከርያ፣ የሕያ፣ ዒሳ እና የመጨረሻው ነቢይ የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ታሪኮች የተካተቱበት ነው፡፡ እነኚህ ሀያ አምስቱ የአላህ ነቢያት ቁርኣን ውስጥ ሥማቸው ተጠቅሷል፡፡
ዶ/ር ዐሊ ሶላቢ ከዚህ ቀደም ያዘጋጇቸው ግዙፍ መፃሕፍት ማለትም የነቢዩ ሙሐመድ የሕይወት ታሪክ የያዘው ለዓለማት እዝነት፣ እንዲሁም የአስ-ስዲቅ አቡክር እና የአል-ፋሩቅ ዑመርን ሙሉ የሕይወት ታሪኮች የያዙ መፃሕፍት በኡስታዝ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል) በነጃሺ ማተሚያ መታተማቸው ይታወሳል፡፡
ማተሚያ ቤታችን የዙን-ኑረይን ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ በቅርቡ በገበያ ላይ ያውላል፡፡
https://nejashibooks.com/
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://t.me/Nejashipp
የረመዳን ዕድሎች
1- የመፆም ዕድል
*
በረመዷን ወር ውስጥ የሚገኙት ኢማናዊ ዕድሎች በርካታና ምቹ ናቸው፡፡ ብልህ ሰው እነኚህን አላህን የሚገዛባቸውን አጋጣሚዎች፣ በረከት የሚዘንብባቸውን ባለመልካም መዓዛ ወቅቶች በአግባቡ ይጠቀማል፡፡
አቡ-ዘር (ረ.ዐ.) እንዲህ ይሉ ነበር፡-
“ሰዎች ሆይ! በእውነት ልምከራችሁ፡፡ ለመቃብሮች የብቸኝነት ኑሮ፣ በሌሊት ጨለማ ውስጥ ስገዱ፡፡ ለትንሳኤው ቀን መጨናነቅ፣ ዱንያ ውስጥ እያላችሁ ፁሙ፡፡ ያን የጭንቅ ቀን ፈርታችሁ መፅውቱ፡፡”
አል-አስወድ ኢብን የዚድ ፆም ያበዛ ነበር፡፡ አንድ ዓይኑ እስክትጠፋ ድረስ ያዘወትር ነበር፡፡ “አካልህን ለምን ይህን ያህል ታስቃያለህ?” ተብሎ በተጠየቀ ቁጥር “ዘላለማዊ ረፍቱን ፈልጌ” በማለት ይመልስ ነበር፡፡
ዓሚር ኢብን አብዲ ቀይስ ይህችን ዓለም ተለይተው የሚጓዙባት የመጨረሻዋ ሰዓት የቀረበች ጊዜ አለቀሱ፡፡ “ምን አስለቀሰዎት?” ተባሉ፡፡ እንዲህ የሚል መልስ ሰጡ፡- “ያለቀስኩት ሞትን ፈርቼ አይደለም፣ ለመኖር ጓጉቼም አይደለም፡፡ ነገር ግን በአላህ መንገድ በሚደረግ ጉዞ ላይ ከሚኖረው ጥማት፣ ከቀዝቃዛው ወቅት የሌሊት ሶላት መለየቴ ነው የሚያስለቅሰኝ፡፡”
አንድ የአላህ ወዳጅም እንዲሁ፣ ከሞት አፋፍ ላይ የደረሱ ጊዜ በኃይለኛ ፍርሃት ተዋጡ፣ ተንሰቅስቀው አለቀሱ፡፡ ይህን ሁኔታቸውን የተመለከቱ ሰዎች ለምን? ብለው ሲጠይቋቸው እንዲህ በማለት ተናገሩ፡- “ፆመኞች ለአላህ ብለው ሲፆሙ ከነሱ ውስጥ ባለመሆኔ ሰጋጆች ለአላህ ብለው ሲሰግዱ ከነሱ ውስጥ ባለመሆኔ፣ አወዳሾች ለአላህ ብለው አምላካቸውን ሲያወድሱ ከነሱ ውስጥ ባለመሆኔ፣ እንጂ በሌላ ነገር አይደለም ያለቀስኩት፡፡ ይኸው ነው የሚያስለቅሰኝ፡፡”
በረመዷን ወር ውስጥ የሚገኘው የመፆም ዕድል በሌላ በምንም ነገር ሊለወጥ የማይችል እድል ነው፡፡ ከረመዷን ውጭ ሌሎች በርካታ የፆም ዓይነቶች ወይም የመፆሚያ አጋጣሚዎች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ ነገር ግን ልቡ በኢማን የተሞላና በእርግጠኝነት የተዋበ ሰው ካልሆነ በስተቀር ሌላው ሰው አይሳካለትም፡፡ ተሳክቶለት ቢፆምም አያሳምረውም፡፡ የረመዷን ፆም ግን ግዴታ ነውና ሁሉም ይፆመዋል፡፡ ይህ ማለት ግን እያንዳንዱ ሰው አስተካክሎና አሟልቶ ይፆመዋል ማለት አይደለም፡፡ አንዱ ግለሰብ ከሌላው ግለሰብ በልባዊነቱ ይለያያል፡፡ በዚህ ምክንያትም ነው፣ ምንዳው ከኔ ብቻ ነው በማለት አላህ ወደ ራሱ ያስጠጋው፡፡

በድር - በኢስላም ታሪክ ታላቁና የመጀመርያው ድል
***
ረመዷን ሙስሊሞች በመንፈሳዊነት በከፍተኛ ደረጃ የሚነቃቁበት ወር ነው፡፡ ከትእግስት እስከ ተስፋ ከቁርጠኝነት እስከ ፅናት አቋማቸው ከፍ ይላል፡፡ መልካም ነገር ሁሉ ይገራላቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ረመዷን የድል ወር ነው ተብሎ የሚታሰበው፡፡ በርካታ ድሎችና ስኬቶች የተገኙበት ወር በመሆኑ ፡፡
ከነኚህ ድሎች መካከልም በሁለተኛው ዓመተ ሂጅራ ረመዷን 17 ቀን ከመዲና 150 ኪሜ ርቀት አካባቢ በድር በተባለው ቦታ ላይ የዋለው የታላቁ የበድር ጦርነት ይታወሳል፡፡ በዚህ ጦርነት ላይ በቁጥር 314 የሚሆኑ በወጉ ያልታጠቁ ሙስሊሞች በሚገባ ከታጠቀውና በእግረኛ እና ፈረሠኛ ከተደራጀው 1ሺህ የሚሆን የቁረይሽ ጦር ጋር ገጥመው አሸንፈዋል፡፡
የበድር ጦርነት ለሙስሊሞች መንሠራራት ትልቅ የመስፈንጠሪያ ክስተት ሆኖ አገልግሏል፡፡ ከዚያ በኋላ የሙስሊሞች ወኔ በእጅጉ ከፍ አለ፡፡ በአላህ ላይ ያላቸው እምነትም ይበልጥ ተጠናከረ፡፡ በድሉ ሞራልም ሙስሊሞች በሚገባ እየተደራጁ መጡ፡፡ በዙርያቸው ባሉ ጠላቶችም ሊፈሩ ቻሉ፡፡
በድር ሐሰትና እውነት፣ እምነትና ክህደት ፍንት ብሎ የተለየበት ቀን በመሆኑ የውም አል-ፉርቃን /የመለያ ቀን በመባል ይታወቃል፡፡
በድር የመጀመርያዎቹ በቁጥር ጥቂት የሆኑ ሙስሊሞች በጥቂት ሰውና የመሣርያ አቅም በሁሉም ዘርፍ እጅጉ በሚበልጣቸው ጠላት ላይ ከፍተኛ ድል የተቀዳጁበት በመሆኑ ሁሌም እንደተወሳ ይኖራል፡፡

ከረመዳን ዕድሎች
2- አላህ ፊት የመቆም ዕድል
***
ይህ ዕድል፣ እውነተኛ አማኝ እንጂ ሌላው ሰው ልብ የማይለው፣ ቀልቡና መንፈሱ በኢማን ፈገግታ የፈኩለት ሰው ቢሆን እንጂ ሌላው ሥራዬ ብሎ የማይጠብቀው ትልቅ ዕድል ነው፡፡ እውነተኛ ደስታና ሰላም ምንጭ ነው፡፡ የኢማን ጥፍጥና፣ አላህን የመገዛት ጣዕም፣ ተለይቶ የሚታወቅበት አጋጣሚ ነው፡፡ ከአላህ ጋር ያለ ግንኙነት ይቀጠልበታል፣ ይታደስበታል፡፡ ወደ አላህ ይቃረቡበታል፡፡
ጉዳዮች የሚገሩበት፣ ችግሮች የሚቀረፉበት፣ ፈተናዎች የሚመለሱበት... ደጃፍ ነው፡፡ እንዲሁም ስህተቶች የሚታበሱበት፣ ኃጢያቶች የሚደመሰሱበት፣ ወንጀሎች ይቅር የሚባሉበት... አጋጣሚ ነው፡፡
ሶላት የተቂዮች (አላህን በቅን ፈሪዎች) ያይን ማረፊያ፣ የተውሒድ ባለቤቶች የልብ መርጊያ ናት፡፡
በሶላት ጭንቀቶች ይወገዳሉ፡፡ ሸክሞች ይቀላሉ፡፡ ትካዜዎች ይርቃሉ፡፡ ኃጢያቶች ይታበሳሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን ከታላቁ ጌታው ፊት የቆመው ሰው፣ ራሱን አስተናንሶ፣ ባክብሮታዊ ፍርሃት ተሞልቶ፣ አንገቱን ሰብሮ፣ ሁለመናውን አረጋግቶ፣ አዕምሮውን ሰብስቦ፣ ልቡን ጥዶ፣ የጌታውን ፀጋና ምህረት ተስፋ አድርጎና የወዲያኛውን ዓለም ከልቡ አስቦ ከቆመ ብቻ ነው፡፡
ሶላት የነፍስ ማረፊያ፣ የቀልብ መርጊያ ናት፡፡ ለዚህ ነበር መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) “የዓይን ማረፊያዬ በሶላት ውስጥ ተደረገችልኝ፡፡” ያሉት (ቡኻሪና ሙስሊም)
እንዲህም ይሉ ነበር፡- “አንተ ቢላል! (እባክህን) በሶላት አሳርፈን፡፡” (ቲርሚዚና አን-ነሳኢይ)
ግዴታ ከተደረገው ሶላት በተጨማሪ ሌሎች ሶላቶችን በፈቃደኝነት መስገድ፣ ማዘውተርና ማብዛት፣ ወደ ዓለማት ጌታ ያቃርባል፣ ውዴታውን ያስጨምራል፣ ፍቅሩን ያስተርፋል፣ የቅርብ ወዳጅነቱን ያስገኛል፡፡
ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሶላትን እንዲያ የማፍቀራቸውና የማብዛታቸው አንዱ ምክንያት ይኸው ነበር፡፡ በያንዳንዷ ሌሊት አስራ አንድ ምናልባትም አስራ ሦስት ረከዓዎችን ይሰግዱ ነበር፡፡ ከግዴታዊ ሶላቶች በፊትና በኋላ የሚገኙ ጥብቅ ሱናዎችን በምንም ሁኔታ አይተውዋቸውም ነበር፡፡
የዱሐ (የረፋድ ሠዓት) ሶላት አራት ረከዓ ወይም ከዚያ በላይ ይሰግዱ ነበር።
ሌሊት በሚሰግዱበት ጊዜ ረከዓዎችን ያስረዝሟቸው ነበር፡፡
የግዴታዊ ሶላት አሥራ ሰባት ረከዓዎችን ጨምሮ፣ በየቀኑ ወይም በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ከአርባ (40) ረከዓዎች በላይ መስገድ ዘወትራዊ ተግባራቸው ነበር ።
ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ)፡- “የሌሊት ሶላትን አደራ፣ ከናንተ በፊት የነበሩ ደጋግ ሰዎች ዘወትራዊ ተግባር ነው፡፡” በማለት ተከታዮቻቸውን በአፅንኦት መክረው አልፈዋል።
ሰህል ኢብን ሰዕድ (ረ.ዐ) ባስተላለፈው ሐዲሥ “ጅብሪል ወደኔ መጣና “አንተ ሙሐመድ! የፈለግከውን ያህል ኑር፣ በእርግጥ ትሞታለህ፡፡ አንድን ሰው የፈለግከውን ያህል ውደደው፣ በእርግጥ ትለየዋለህ፡፡ የፈለግከውን ሥራ፣ በእርግጥ ዋጋው ይከፈልሃል፡፡ ልብ በል! የሙእሚን ግርማ ሞገሱ በሌሊት መቆሙ ነው፣ ልዕልናው ደግሞ ከሰዎች ምንም አለመፈለጉ ነው፡፡” አለኝ ብለዋል።
አላህ ይዘንላቸውና! ወህብ ኢብን ሙነበህ እንዲህ ይሉ ነበር፡- “በሌሊት ሶላት የተናቀ ይከበርበታል፣ የተዋረደ ልዕልና ያገኝበታል፡፡ የቀን ፆም፣ ከግለሰቡ ላይ ሥጋዊ ስሜቶችን ይቆርጣል፡፡ ሙእሚን ጀነት ውስጥ እንጅ እረፍት የለውም፡፡”
ኢብን ዐባስ (ረ.ዐ.) በበኩላቸው፣ ነገ በፍርዱ ቀን የሚቆምበት ጊዜ እንዲያጥርለት የሚፈልግ ሰው፣ ዛሬ ዱንያ ላይ ሳለ ያን ጊዜ ፈርቶና የጌታውን እዝነትና ፀጋ ተስፋ አድርጎ በሌሊቶቿ ውስጥ ሲቆም፣ ሲጎነበስና ሱጁድ ሲያደርግ አላህ ይየው ብለዋል።
በረመዷን ወር ውስጥ ከሚገኙ ዕድሎች ሁሉ በላይ ትልቁና ወርቃማው ዕድል ግን፣ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በከፍተኛ ትጋት ልናነጋት በሚገባን፣ “ለይለት አል-ቀድር” የሚል ስያሜ በተሰጣት ልዩ ሌሊት ውስጥ ከአላህ ፊት የመቆም እድል ነው፡፡

ውድ ደንበኞቻችን
ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ መርካቶ አንዋር መስጊድ መግቢያ በር ላይ የሚገኘው መክተባችን ወሩን ሙሉ ክፍት ነው።

Telegram
Nejashi Printing Press
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
አዲስ መጽሐፍ ከነጃሺ
***
የመጽሐፉ ሥም ፡ ነፍሲያን ማረቅ
አዘጋጅ ፡ ኢብን አል-ጀውዚ
ትርጉም ፡ ሱለይማን ጠይብ ሐምዛ
የገጽ ብዛት፡ 84
ስለ መጽሐፉ ፡ መጽሐፉ ነፍሲያን በማረቅ እና አጉል ፍላጎቶቿን በማገድብ ወደ ትልቅ ደረጃ ማድረስ ስለሚቻልበት ሁኔታ ይዳስሳል፡፡
ከመጽሐፉ ፡ አላህ ለሰው ልጆች የሚወስነውም ሆነ የሚያመላክተው ነገር ሁሉ ፋይዳው ለእነሱ ነው። አንድም እንደ የምግብ ፍላጎት ዓይነት ጠቃሚ ስሜቶች እንዲኖሯቸው አለዚያም እንደ ቁጣ ኃይል የመሣሠሉትን ክፋቶችን ለመቆጣጠር ነው። የምግብ ፍላጎት ወሰን ሲያልፍ ወደ ስግብግብነት ያመራል። በዚህ ምክንያትም ጎጂ ይሆናል። በተመሳሳይም የሰው ቁጣ ሚዛን ሲስት ጥፋት ማስከተሉ አይቀርም።
የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ በአእምሮ እና በልብ አውታሮች ውስጥ ማስረፅ፣ ማንበር እና ‹ሀዋእ› (ሥጋዊ ዝንባሌ) ጉዳት እንዳያስከትል መድፈቅ የሚቻልበትን መንገድ መጠቆም ነው። አለፍ ሲልም የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ የሚቃወምን ሥጋዊ ዝንባሌ ፈውሶችን ያመላክታል።
መጽሐፉ በአጫጭር ሰላሳ ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው።
https://nejashibooks.com/
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://t.me/Nejashipp
***
የመጽሐፉ ሥም ፡ ነፍሲያን ማረቅ
አዘጋጅ ፡ ኢብን አል-ጀውዚ
ትርጉም ፡ ሱለይማን ጠይብ ሐምዛ
የገጽ ብዛት፡ 84
ስለ መጽሐፉ ፡ መጽሐፉ ነፍሲያን በማረቅ እና አጉል ፍላጎቶቿን በማገድብ ወደ ትልቅ ደረጃ ማድረስ ስለሚቻልበት ሁኔታ ይዳስሳል፡፡
ከመጽሐፉ ፡ አላህ ለሰው ልጆች የሚወስነውም ሆነ የሚያመላክተው ነገር ሁሉ ፋይዳው ለእነሱ ነው። አንድም እንደ የምግብ ፍላጎት ዓይነት ጠቃሚ ስሜቶች እንዲኖሯቸው አለዚያም እንደ ቁጣ ኃይል የመሣሠሉትን ክፋቶችን ለመቆጣጠር ነው። የምግብ ፍላጎት ወሰን ሲያልፍ ወደ ስግብግብነት ያመራል። በዚህ ምክንያትም ጎጂ ይሆናል። በተመሳሳይም የሰው ቁጣ ሚዛን ሲስት ጥፋት ማስከተሉ አይቀርም።
የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ በአእምሮ እና በልብ አውታሮች ውስጥ ማስረፅ፣ ማንበር እና ‹ሀዋእ› (ሥጋዊ ዝንባሌ) ጉዳት እንዳያስከትል መድፈቅ የሚቻልበትን መንገድ መጠቆም ነው። አለፍ ሲልም የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ የሚቃወምን ሥጋዊ ዝንባሌ ፈውሶችን ያመላክታል።
መጽሐፉ በአጫጭር ሰላሳ ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው።
https://nejashibooks.com/
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://t.me/Nejashipp
አስደሣች ዜና ለመጽሐፍ ወዳጆች
****
የሦስተኛውን የሙስሊሞች ኸሊፋ የታላቁን ሰሐባ ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን (ዙን-ኑረይን) ታሪክ የያዘ መጽሐፍ በነጃሺ ማተሚያ ቤት ታትሞ በዛሬው ዕለት በገበያ ላይ ውሏል።
መጽሐፉ 414 ገፆች አሉት።
አዘጋጁ ሸይኽ ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ ሶላቢ ናቸው።
ኡስታዝ አሕመድ ሑሴን ተርጉሞታል ።
መርካቶ ታላቁ አንዋር መስጊድ መግቢያ በር ላይ ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል።
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ!!

መላው ሙስሊም ማኅበረሰብ እንኳን ለዒድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሣችሁ።
ዒዱኩም ሙባረክ!
ወኩሉ ዓሚን ወአንቱም ቢኸይር ።
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
https://nejashibooks.com/
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://t.me/Nejashipp
ዒዱኩም ሙባረክ!
ወኩሉ ዓሚን ወአንቱም ቢኸይር ።
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
https://nejashibooks.com/
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://t.me/Nejashipp
የህሊና ዕረፍቶች (ከቁጥር 1- ቁጥር 4)
***
መጽሐፎቹ ውስጥ
* የተለያዩ መሳጭ ጥበባዊ ንግግርች፣
* የታላላቅ ሰዎች አባባሎች፣
* አጫጭርና ውብ የሆኑ ግጥሞች፣
* መረጃዎችና ቆንጆ ሀሳቦች ፣
* ቀልብን የሚያለሰልሱ ምክሮች፣
* አዝናኝ እና አስተማሪ መልእክቶች እና ሌሎችንም
* የማይሰለቹ መጣጥፎችን ያገኙባቸዋል፡፡
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኟቸዋል።
***
መጽሐፎቹ ውስጥ
* የተለያዩ መሳጭ ጥበባዊ ንግግርች፣
* የታላላቅ ሰዎች አባባሎች፣
* አጫጭርና ውብ የሆኑ ግጥሞች፣
* መረጃዎችና ቆንጆ ሀሳቦች ፣
* ቀልብን የሚያለሰልሱ ምክሮች፣
* አዝናኝ እና አስተማሪ መልእክቶች እና ሌሎችንም
* የማይሰለቹ መጣጥፎችን ያገኙባቸዋል፡፡
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኟቸዋል።
ፈተናዎች፣ እኛን ከኀጢአት ለማጽዳት የሚከሰቱበት ጊዜ አለ።
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፦
“አንድን ሙስሊም ድካም፣ ህመም፣ ትካዜ፣ ሐዘን፣ ወይም ጉዳት -የእሾህ መውጋት ቢሆንም እንኳን- አይደርስበትም፤ አላህ የተወሰነውን ኀጢአቱን የሚያብስለት ቢሆን እንጂ።” (ቅጽ 7፣ ምዕራፍ 70፣ ቁጥር 545)
አንድ ታላቅ ገጣሚ እንዳለውም፦
“አንድ ሰው ምንጣፍ ሲደበድብ ውጥኑ ምንጣፉ አይደለም። ምንጣፉ ውስጥ ያለው አቧራ እንጂ።”
አንጥረኛ ወርቅን የሚቀጠቅጠው ሊያጠፋው አይደለም። ሊያፀዳው ነው።
አላህም ምእመናንን ለማጽዳት ልክ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን በፈተና እንደሚያፀዳቸው በቁርኣን ነግሮናል።
ወርቅ በእሳት ሲለበለብ ጉድፎቹ ይወገዱለታል።
የአማኝ ልብ በፈተና እንዲያልፍ ሲደረግም የቀልብ ላይ እድፎች ይወገዳሉ።
የባዶነት ስሜት መንስኤው እና ፈውስ
በያስሚን ሙጃሂድ
ትርጉም - ሱለይማን ጠይብ።
https://t.me/Nejashipp
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://nejashibooks.com/
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፦
“አንድን ሙስሊም ድካም፣ ህመም፣ ትካዜ፣ ሐዘን፣ ወይም ጉዳት -የእሾህ መውጋት ቢሆንም እንኳን- አይደርስበትም፤ አላህ የተወሰነውን ኀጢአቱን የሚያብስለት ቢሆን እንጂ።” (ቅጽ 7፣ ምዕራፍ 70፣ ቁጥር 545)
አንድ ታላቅ ገጣሚ እንዳለውም፦
“አንድ ሰው ምንጣፍ ሲደበድብ ውጥኑ ምንጣፉ አይደለም። ምንጣፉ ውስጥ ያለው አቧራ እንጂ።”
አንጥረኛ ወርቅን የሚቀጠቅጠው ሊያጠፋው አይደለም። ሊያፀዳው ነው።
አላህም ምእመናንን ለማጽዳት ልክ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን በፈተና እንደሚያፀዳቸው በቁርኣን ነግሮናል።
ወርቅ በእሳት ሲለበለብ ጉድፎቹ ይወገዱለታል።
የአማኝ ልብ በፈተና እንዲያልፍ ሲደረግም የቀልብ ላይ እድፎች ይወገዳሉ።
የባዶነት ስሜት መንስኤው እና ፈውስ
በያስሚን ሙጃሂድ
ትርጉም - ሱለይማን ጠይብ።
https://t.me/Nejashipp
https://www.tiktok.com/@nejashibooks
https://nejashibooks.com/
የሚያጎለብቱ ፈተናዎች
*,
ፍጥረትን ስናጠና የአላህን ሱንና (መንገድ) የተመለከቱ በርካታ እውነታዎችን እናገኛለን። ለምሳሌ፣ አጥንታችን ሲሰበርና መልሶ ሲድን፣ አጥንቱ ተሰብሮ የዳነበት ጥግን ቦታ ላይ የበለጠ ጠንካራ ይሆናል። ዓለማዊ ፈተናዎቻችንም ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። ከታላላቅ የሱና ምሁራን አንዱ የሆኑት አል-ዒዝ ኢብን ዐብዱሰላም “ፈተናዎችና 17 ፋይዳዎቻቸው” የሚሰኝ ዕውቅ ድርሰት አላቸው።
በዚህ ሥራቸው ሸይኹ፣ ፈተናዎች የአላህን የኃያልነት (ሁሉን ቻይነት) ልክ እንድንረዳ እንደሚያደርጉ አብራርተዋል። ብዙውን ጊዜ የሕይወታችን መሪዎች ራሳችን እንደሆንን እናስባለን። ሕይወታችንን ራሳችን የምንሾፍር ይመስለናል። ሁሉን ነገር የማበጀት እና ሰባራን ሁሉ የመጠገንን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት እንጥራለን። ይህ ደግሞ መከራ ውስጥ ይከተናል። ዘና ማለት አንችልም። እንቅልፍ ካይናችን ይሸሻል።
ብዙዎች፣ ሁኔታዎች ላይ ሥልጣን አለን ብለው በማሰባቸው ምክንያት ውስጣዊ ሰላምን አያገኙም። በሕይወታችን ላይ የተለገሥነውን ውሳኔ የማሳለፍ ክህሎት ትክክለኛ ሥልጣን አድርገን እንቆጥረዋለን። ፈተናዎችና መከራዎች ደግሞ አላህ በእኛ ላይ የማይገሠሥ ሥልጣን ያለው መሆኑን እንድናስታውስ ያስገድዱናል። አላህ አል-ቀሃር (አስገዳጅ) እና አል-ዐዚዝ (አሸናፊ) ነው።
እናም ይህ ዕውቀት ወደሚያድነንንና ድህነታችንን በማስታወስ አላህን እንድንከጅል ወደሚያደርገን ግንዛቤ ይመራናል። ከአላህ ፊት መልካም የማርገድ ስሜት ውስጣችን ያሰርፃል። “በአላህ ቢሆን እንጂ ኃይልም ሆነ ብልሃት የለም፣” የሚለውን ወርቃማ መርህ በገቢር ያስተምረናል። ሰዎችን ሁሉ ወይም ሁሉንም ነገር የምናድን እኛ አለመሆናችንን ይዘክረናል።
የምናስተካክለው እኛ እንዳልሆንን፣ ኃላፊነትም እንዳልተጣለብን ያስገነዝበናል። ይህ ኃላፊነት የአላህ መሆኑን ጭምር።
ይህ ግንዛቤ ሕይወታችንን መታደግ የሚችል ነው። ከሰዎች ጋር ያሉንን ግንኙነቶች ማረቅ ይችላል። የሰው ልጅ ልቦና የዓለምን ክብደት እንዲሸከም አልተበጀም። ይህን ክብደት መሸከም የሚችል አላህ ብቻ ነው። ይህን ጭነት ለሰማይና ለምድር ባለቤት እስካላስረከብን ድረስም ይህን ከንቱ ክህሎታችንን በሚያፈርስ ጫና ሥር ስንሰቃይ መኖራችን አይቀርም።