Natnael Mekonnen
169K subscribers
30.2K photos
3.09K videos
28 files
6.55K links
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Download Telegram
#Ethiopia : በኢትዮጲያ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 169 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,805 ደርሷል፡፡

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-

~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ5,798 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 168 ኢትዮጲያዉያን እና 1 የአሜሪካ ዜጋ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

~111ዱ ወንዶች ሲሆኑ 58ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።እድሜያቸዉ ከ1 እስከ 78 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።

~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 138 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣11 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣5 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣6 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 4 ሰዎች በደ/ብ/ብ/ህ ክልል፣1 ሰዉ ከሀረሪ ክልል

ተጨማሪ መረጃ ፦

~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 131,368 ደርሷል።

~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 12 ሰዎች አገግመዋል።(10 ከአማራ፣2 ቤንሻንጉል ክልሎች)

~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 262 ደርሰዋል።

~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ 18 ታማሚዎች አሉ ፡፡(+2)

~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 1522 ናቸው።

~ የ 19 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

የሟች ሁኔታ፦

~ የ35 ዓመት ሴት ኢትዮጺያዊት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተካሄደ ምርመራ ሊረጋገጥ ችሏል፡፡
#Ethiopia : ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደቡብ ሐረሪና ኦሮሚያ ክልል የተደረጉ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መረጃዎች

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግሥት 182 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል አራት (4) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 20 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን (ሀዋሳ ዙሪያ) ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 2 - የ25 ዓመት የሲዳማ ዞን (በንሳ ወረዳ) ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 3 - የ25 ዓመት የሲዳማ ዞን (በንሳ ወረዳ) ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 4 - የ20 ዓመት የሲዳማ ዞን (በንሳ ወረዳ) ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ሶስቱ (3) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ግለሰቦች በይርጋለም ለይቶ ማቆያ ፤ አንደኛው (1) ሀዋሳ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው ሰላሳ አንድ (31) የላቦራቶሪ ምርመራ ነው አንድ (1) ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው፡፡

ዛሬ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከጅቡቲ የተመለሰ የአቦከር ነዋሪ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አሳውቋል።

በአጠቃላይ በሐረሪ ክልል ደረጃ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አስራ ሶስት (13) ደርሷል

ባለፉት 24 ሰዓት በኦሮሚያ ክልል የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 887 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው አስራ አንድ (11) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 103 ደርሰዋል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ47 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰበታ ከተማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 2 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ከተማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 3 - የ21 ዓመት ኢትዮጵያዊት የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

ታማሚ 4 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሸዋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

ታማሚ 5 - የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊ የምዕራብ ሸዋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።

ታማሚ 6 - የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዳማ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 7 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 8 - የ12 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዳማ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 9 - የ10 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 10 - የ5 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዳማ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላት።

ሌላኛዋ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዟ የተረጋገጠው አንዲት የ35 ዓመት ሴት ስትሆን ህይወቷ ካለፈ በኃላ በተደረገ 'የአስክሬን ምርመራ' ነው ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠው። የመኖሪያ አድራሻዋ #በመጣራት ላይ ይገኛል።
#Ethiopia : በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,343 ደርሰዋል! በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ግንቦት 28/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 1,343 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 138 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 7 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው የተቀሩት 129 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት (138) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 20 ሰዎች
• ልደታ - 8 ሰዎች
• ጉለሌ - 19 ሰዎች
• ቦሌ - 23 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 12 ሰዎች
• የካ - 24 ሰዎች
• ቂርቆስ - 6 ሰዎች
• አራዳ - 4 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 8 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 9
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 5 ሰዎች

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,343 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 375 ሰዎች
• ልደታ - 188 ሰዎች
• ጉለሌ - 176 ሰዎች
• ቦሌ - 143 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 128 ሰዎች
• የካ - 73 ሰዎች
• ቂርቆስ - 57 ሰዎች
• አራዳ - 55 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 51 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 38
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 59 ሰዎች
በትግራይ ክልል ወልቃይት ኦራሪት ተቃውሞውን አስተባብራችኋል የተባሉ 340 ሰዎች መታሰራቸውን አረና ገለፀ።

#Ethiopia : በትግራይ በተቃውሞው ተሳትፋችኋል የተባሉ ታፍነው እየተወሰዱ በመሆኑ ወጣቱ በፍራቻ ወደ በረሀ ወርዷል ብሏል አረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፡፡የትግራይ ህዝብ ከገበሬ እስከ ተማረው ፤ ፍትህ ሲጎድልበት ጭቆና ሲያይልበት በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን መግለፅ መቀጠሉን የገለፀው አረና 11 ሺህ ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን ባሰማባት ኦራሪት ወልቃይት የአካባቢውን ምክትል አስተዳዳሪ ጨምሮ ተቃውሞውን መርታችኋል፣አስተባብራችኋል የተባሉ 340 ሰዎች ታፍነው ተወስደው ታስረዋል ብሏል፡፡የአረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አምዶም ገብረስላሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገተናገሩት የትግራይ ህዝብ በቅቶታል ብለዋል፡፡

በተለይ በዋጅራት፣ በማይሀንሰን ፣ ኦራሪት ወልቃይት፣ በሌሎች አካባቢዎችም የተስተዋሉት ታቃውሞዎችና ቁጣዎች የትግራይ ህዝብ በደሉ ከሚሸከመው በላይ እንደሆነበት ማሳያዎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።የተዘጋው መንገድ የተከፈተው አሁን ላይም የተረጋጋ የሚመስለው ህወሀት ለተቃውሞዎቹ በሀይልና በጠመንጃ በሰጠው ምላሽ ነው ብለዋል አቶ አምዶም፡፡በተለይ በ ኦራሪት ወልቃይት፣ በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል፣ ቆስለዋል፣ ሌሊት የመኖርያ ቤታቸው በር እየተሰበረበረ እየተወሰዱ ነው ያሉ ሲሆን ወጣቱ በፍራቻ ከመኖርያ ቤቱ ሸሽቶ በረሀ ነው ያለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ግፍ የዳረጋቸው ለመብታቸው መታገል መጀመራቸው ነው ያሉት አቶ አምዶም በትግራይ የለውጥ ፍላጎቶቹ ንረዋል፤ አረና ህወሀት እንደሚለው ይሄን የታቀውሞ ሰልፍ ባይጠራም ፤ የህዝቡ ጥያቁ ጥያቄያችን ስለሆነ እስከመጨረሻው ከህዝቡ ጎን ነን ብለዋል፡፡ህወሀት ምርጫ እንደማያሸንፈን ያውቀዋል ያሉት አቶ አምዶም ለዛ ነው አሁን በኮሮና ግርግር ህዝብ በነፃነት ወጥቶ በማይመርጥበት ሁኔታ አሸነፍኩ ለማለት ምርጫው ይደረግ እያለ ያለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ህዝቡ ህወሀትን አንቅሮ እንደተፋው እናውቃለን፣ እኛ ሳንሆን ራሱ ህወሀት ያውቀዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልልን አስተያየት ለማካተት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

Via Ethio FM
#Ethiopia : ዛሬ በ28/9/2012 ዓ/ም በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ስድስት (6) ሰዎች ሁሉም ወንድ ሲሆኑ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ናቸው፤የእድሜ ክልላቸው ከ25 እስከ 38 ዓመት ውስጥ ይገኛል። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።

አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት

• ምዕ/ጎንደር - 87 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 3 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 3 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው

እስካሁን ድረስ በአማራ ክልል 2,557 የላንራቶሪ ምርመራ ተደርጓል ፤ አንድ መቶ ስምንት (108) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
Good news

#Ethiopia : በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በለይቶ ማቆያ የነበሩ የሆስፒታሉ ሰራተኞች በሙሉ ከኮቪድ-19 #ነጻ መሆናቸው ሁለት ጊዜ በምርመራ ተረጋግጦ ዛሬ ግንቦት 28/2012 ዓ.ም ከለይቶ ማቆያ ወጥተዋል - #GondarUniversity
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጸብ የመፍጠር ዓላማ የላትም”- ጠ/ሚ/ር ሀምዶክ

#Ethiopia : የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ ከሱዳን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ሀገራቸው ከጎረቤት ኢትዮጵያ ጋር ጸብ የመፍጠር ዓላማ የላትም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ የተለየ የድንበር ችግር ጉዳይ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ቀደም ሲልም በተለያዩ ጊዜያት የነበረ ነው ብለዋል፡፡ ሱዳን ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት ጋር የድንበር ችግሮች ሲያጋጥሟት እንደነበርም አውስተዋል፡፡

“ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት በባህል ፣ በታሪክ እና በመልክአ ምድር እና በመልካም ጉርብትና የተሳሰረ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ እናም “በመካከላችን የሚፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችሉ ስልቶች አሉን” ብለዋል፡፡ ከሰሞኑ የተፈጠረው ክስተትም በዚህ መንገድ እንደሚፈታ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ ገልጸዋል፡፡

#AlAin
ስለ ሀገር አንድነት ማቀንቀን አሀዳዊ የሚያሰኝ ከሆነ ልሁን

#Ethiopia : አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መተዳድር ዛሬ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ የተናገሩት::
በዩናይትድ ኪንግደም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ40 ሺ በለጠ

#Coronavirus ባለፉት 24 ሰዓት በዩናይትድ ኪንግደም የ357 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 40,261 መድረሱ ሪፖርት ተደርጓል፡፡በዩናይትድ ኪንግደም አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 283,311 መድረሱን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል፡፡
#Coronavirus ግብፅ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 1,348 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የአርባ (40) ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 31,115 ደርሰዋል። በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1,116 ከፍ ብሏል።
"የህወሓት ታጣቂዎች ከኦነግ ሸኔ ጋር ተደባልቀው አየተንቀሳቀሱ ነው" - የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት

#Ethiopia : በርከት ያሉ የህወሓት ታጣቂዎች ከኦነግ ሸኔ ጋር ተደባልቀው አየተንቀሳቀሱ ነው ሲል የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ወንጅሏል። የክልሉ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር ግርማ ገላን ለመገናኛ ብዙሃን እንዳሉት ከሥልጠና ቦታ ጠፍተው የመጡ ወጣቶችም ማን እንዳስለጠናቸው እና ተልዕኮ እንደሰጣቸው በግልፅ ይናገራሉ ብለዋል። #VOA
#Coronavirus አጫጭር አለም አቀፍ መረጃዎች

በኢንዶኔዥያ ጃካርታ የሚገኘዉ መስጊድ ከሁለት ወር በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአርብ የጸሎት ስነስርዓት ተካሄደበት በደቡብ እስያ ግዙፏ ከተማ ጃካርታ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ መስጊድ መሄድ መከልከሉን ተከትሎ ላለፉት ሁለት ወራት የሀይማኖት ስፍራዎች ዝግ ተደርገዉ ቆይተዋል፡፡በዛሬዉ እለት በጋራ መስገድ ተፈቅዷል፡፡በጃካርታ ከተማ 7,766 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸዉ ሲረጋገጥ የ523 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በሜክሲኮ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አላደረግህ በሚል ታስሮ የነበረዉ ወጣት ህይወቱ ማለፉ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱ ተነግሯል:: ጆቫኒ ሎፔዝ የተባለ በግንባታ ሙያ ላይ የተሰማራ ወጣት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አላደረግህ በሚል በቁጥጥር ስር ሲዉል በፖሊስ የሀይል እርምጃ ተወስዶበታል፡፡የተወሰደበት የሀይል እርምጃ ለሞት ያበቃዉ መሆኑን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጣን በሜክሲኮ ፈጥሯል፡፡

የፊት እና የአፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረገ ከማህበራዊ ርቀት እና የአይን ጥበቃ
መከላከያዎች ጋር ተደምሮ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ከ85 በመቶ በላይ እንደሚገታው
በአለምአቀፍ የጤና ድርጀት አስተባባሪነት የተሰራ አንድ ጥናት ጠቁሟል፡፡ The Lancet በሚባል አለምአቀፍ ጆርናል ላይ የታተመው ይህ ጥናት ከዚህ በፊት በጉዳዩ ዙሪያ በተለያዩ አካላት የተሰሩ 44 የምርምር ውጤቶችን በመተንተን የተከናወነ ሲሆን ፤ ከ16 ሃገራት በተወጣጡ 25,000 ሰዎች ላይም ትኩረቱን በማድረግ ሰፊ ምልከታዎችን ያደረገ ጥናት ነው፡፡

በአሜሪካ ቢዝነሶች እንቅስቃሴ እየጀመሩ በመሆናቸው እና የሰራተኛ ቅጥር በመጀመሩ የሥራ አጦች ቁጥር በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር ከነበረው 14.7 በመቶ ወደ 13.3 በመቶ ዝቅ ብሏል

የአልባሳት ምርቶች አቅራቢዉ GAP በኮሮና ቫይረስ ቀዉስ የተነሳ በርካታ ሱቆቹ በመዘጋታቸዉ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ 932 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ኪሳራ ደረሰበት፡፡ GAP ባለፈዉ ዓመት በተመሳሳይ ጊዜ የ227 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ትርፍ አግኝቶ ነበር፡፡

የዩጋንዳ ጠ/ሚ የሆኑት ሩገንዳ ከእርሳቸዉ ጋር የቅርብ ንኪኪ የነበራቸዉ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸዉን ተከትሎ ራሳቸዉን አገለሉ፡፡በዩጋንዳ ለ79 ባለስልጣናት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ሁሉም ነጻ ሆነዋል፡፡

ዮርዳኖስ ከሁለት ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬዉ እለት መስጊዶችን ከፈተች።765 የቫይረሱ ተጠቂዎች በሀገሪቱ ሲገኙ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ባንግላዲሽ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚል በማረሚያ ቤት ዉስጥ የነበሩ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ታራሚዎችን ከእስር ለቀቀች፡፡ከነዚህ መካከል ከ300 በላይ የሚሆኑት ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር መቀላቀላቸዉን ዩኒሴፍ አስታዉቋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ 6ቶን የህክምና ቁሳቁስ ለእንግሊዝ ድጋፍ ማድረጓ ተሰማ፡፡ኢምሬትስ ከእንግሊዝ ጋር የደህንነትና የመከላከያ ግንኙነቷን ማቆሟን ይፋ ማድረጓ ይታወሳል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በአእምሮ መረበሽ በርካታ ሰዎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን የዩናይትድ ኪንግደም ብሄራዊ ስታትስቲክስ ቢሮ አስታዉቋል፡፡በወረርሽኙ ወቅት በአእምሮ መረበሽ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ካለፉት አምስት ዓመታት አንጻር በአማካይ 50በመቶ ጨምሯል፡፡

በኢራቅ ባለፉት 24 ሰዓት 1006 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ተነገረ፡፡በመላዉ ኢራቅ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9,846 ሲደርስ የ285 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ፈረንሳይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር መቻሏን አሳውቃለች።

በዩናይትድ ኪንግደም በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ40,000 በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት 357 ሰዎች ሞተዋል።

የኡጋንዳው ጠቅላይ ሚንስትር ሩሃካና ሩጉንዳ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ራሳቸውን አግልለው ተቀምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸውን ያገለሉት ከሳቸው ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ነው

ባለፉት 24 ሰዓት በኬንያ ተጨማሪ 134 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል ፤ 51 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 2,474 ፣ ሞት 79፣ ያገገሙ 643 ናቸው።

በኬንያ የኮቪድ-19 ህክምና የሚሰጥባቸው የለይቶ ማቆያ ማከሚያ ማዕከላት መሙላታቸውን ተከትሎ ለህሙማኑ ህክምና በቤት እንዲሰጥ መወሰኑን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል -

በጅቡቲ 69 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 22 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 4,123 በቫይረሱ ተይዘዋል ፤ 1,707 አገግመዋል፣ 26 ሰዎች ህይወት አልፏል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በለውጡ ማግስት የተናገሩት ታሪካዊና አስደናቂ ንግግር::
#Ethiopia : የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

Mayor Office of Addis Ababa በዚህም መሰረት፣

1. በሊዝ የተያዙና ከአሁን ቀደም አግባብ ባለው አካል የይዞታ ማረጋገጫ በሊዝ ሥራአት እንዲሥተናገዱ በተወሠነላቸውና በቀጥታ በሊዝ በተያዙ የመኖረያ ይዞታዎች ላይ
በአልሚዎች ተይዘው የሊዝ ክፍያ ፍሬ ግብር እንዲከፍሉ ነገር ግን ወለድና ቅጣት እንዲነሳላቸው፤

2. መሬት አግባብ ባለው የሊዝ ሥራአት ወስደው በወቅቱ ግንባታ ያልጀመሩና ያላጠናቀቁ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች እንዲሁም ተቋማት የግንባታ ፈቃዳቸውን ያለቅጣት እንዲያድሱና ተጨማሪ የኣንድ ዓመት የማራዘሚያ ጊዜ እንዲሰጣቸው፤

3. በሪልስቴት ከተያዙት ውጪ የመኖሪያ ይዞታዎች ወለድና መቀጫ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳላቸው፤

4. ለቢዝነሥ በተለይም በሆቴልና ቱሪዝም ይዞታዎች መቀጫን ሙሉለሙሉ ወለድ ደግሞ 30% እንዲቀር የተወሰነ ሲሆን ውሣኔው የከተማ አሥተዳደሩን እሥከ አንድ ቢልየን ብር ገቢ የሚያሣጣ ቢሆንም የተቀዛቀዘውን የከተማችን ኢኮኖሚ በተለይም የኮንሥትራክሽን ዘርፋን በማነቃቃት ረገድ ከሚኖረው ሚና ባሻገር ውዝፍ ገቢዎች እንዲሠበሠቡ የሚያሥችልና ከ50 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ወቅታዊ ውሣኔ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡በክስ ሂደት ላይ ያሉ አልሚዎችም ከቅጣቱና ከወለድ ክፍያ 30 በመቶ ተነስቶላቸው እንዲከፍሉ ተወስኗል።