Good News
እሪ በከንቱ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ የገቡ ወጣቶችን ከደራሽ ጎርፍ መታደግ ተቻለ
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 10 እሪ በከንቱ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ ያገለገሉ ፕላስቲክ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለመልቀም ወንዝ ዉስጥ የገቡ የ18 እና የ19 ዓመት ወጣቶች በድንገት የደራሽ ጎርፍ ሰለባ ሆነዋል።ወጣቶቹ ራሳቸውን ለማዳን ከተንጠለጠሉበት ቁጥቋጦ ላይ በህይወት ማትረፍ መቻሉን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
ወጣቶቹ ህይወታቸዉ አደጋ ላይ ቢወድቅም እድለኛ ሆነዉ በወንዙ ዉስጥ በነበረ ቁጥቋጦ ላይ ተንጠልጥለው መቆየት ቢችሉም ጎርፉ ከፍተኛ በመሆኑ ለ25 ደቂቃ በጠየቀ የነፍስ አድን ትግል ማትረፍ ተችሏል።
የኮሚሽኑ ዋናተኞች በዋና ገብተዉ ህይወታቸዉን ማትረፍ ችለዋል ።በአዲስ አበባ የተለያዩ በወንዞች ዉስጥ በመግባት የገለገሉ ቁሳቁሶችን በመሰብሰብና በመሸጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በዚህ በክረምት ጊዜ በወንዝ አካባቢ ያለ እንቅስቃሴዎችን እንዲያቆሙ ኮሚሽኑ አሳስባል
በተመሳሳይ ታዳጊዎችና ህጻናት ጎርፍ ያመጣቸዉን ቁሳቁሶች ለማዉጣት ወንዝ ዉስጥ ለመግባት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙና ወላጆችም ልጆቻቸዉን መጠበቅ ያስፈልጋልም ብለዋል።
ከትላንት ወዲያ እሁድ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ ስድስት ጎርፍ ያመጣዉን ኳስ ለማዉጣት በወንዝ ዉስጥ የገቡ የ9 እና የ14 ዓመት ታዳጊዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ግራክ አቴንስ ከተማ አቆርጦት የነበረው በረራ ዳግም መጀመሩን አስታውቋል::
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን ወደ ግሪክ አቴንስ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ከ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚቀጥል ሲገልፅ ደስታ ይሰማዋል። በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን ወይም በድረ ገፃችን ተጠቅመው ትኬትዎን ይግዙ ። መልካም በረራ !
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
https://www.ethiopianairlines.com/et
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

አሜሪካ በኦሮሚያ ክልል የተገደሉ የአማራ ብሔር ተወላጆች ጉዳይ እንደሚያሳስባት አስታወቀች፡፡
የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በምዕራብ ወለጋ በተገደሉ ንጹሃን የአማራ ብሔር ተወላጆች ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በጥቃቱ ህይወታቸው ላለፈ ዜጎች ሀዘኑን የገለጸው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኢትዮጵያውያን ችግሮችን ለማስወገድ ከግጭት ይልቅ ሰላማዊ ንግግርን እንዲያስቀድሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ልዩነትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባም ነው ዋሸንግተን ያሳሰበችው፡፡ ሁሉንም ያሳተፈ፤ ለሁሉም ተጎጂዎች የሚሆን ፍትህና ተጠያቂነት ያለበት ብሔራዊ ዕርቅ እንዲደረግም ነው አሜሪካ ጥሪ ያደረገችው።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም ስለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ሁኔታ በተለይም ባለፉት ቀናት ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ ስለተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ መወያየታቸው ተገልጿል።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴም በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ይህን ድርጊት አውግዟል፡፡
ፕሬዚዳንቷ እንዳሉትም፥ በየትም ቦታ የዜጎች ሕይወት ውድነቱና ክብሩ መሸርሸር የለበትም፡፡
“ሞትን ከተለማመድነው ከግድያ በኃላ ከማውገዝና የሃዘን መግለጫ ከማውጣት አዙሪት አናልፍም፤ ከዚያ በላይ መሄድ ይኖርብናልም” ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።