Natnael Mekonnen
169K subscribers
30.2K photos
3.09K videos
28 files
6.55K links
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Download Telegram
☝️☝️☝️
ቴሌግራም ዋትስአፕን በመብለጥ በሩሲያ ቀዳሚ መልእክት መላላኪያ ሆነ

በሩሲያ የዋትስአፕ ድርሻ ከ48 በመቶ ወደ 32 በመቶ ዝቅ ብሏል። የሩሲያ ባለስልጣናት ቴልግራም እያበረታቱ ሲሆን እንደ ኢንስታግራምና ፌስቡክ ያሉ አገልግሎቶችን እያገዱ ነው።
https://am.al-ain.com/article/telegram-booms-in-russia
በነገው እለት በመላው አዲስ አበባ የህዝብ ውይይት ይደረጋል ተባለ!

ነገ ረቡዕ 14/07/14 ዓ.ም በመላው አዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ወረዳዎች ፤በክ/ከተማ እንዲሁም በከተማ ደረጃ የህዝብ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡በውይይቱ በየደረጃው ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎችና ሃሳቦች ይደመጣሉ ብሏል የከተማ አስተዳደሩ።
# በባለሙያ እና በመሳሪያ የተደራጀ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ
# የብሬስ ህክምና ለማስጀመር ነፃ የማማከር አገልግሎት እና የአከፋፈል መንገድ
# ለተማሪዎች ልዮ ቅናሽ( መታወቂያ መያዝ እንዳይረሱ )
#ሁሉንም ህክምና በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰጣለን
ቁጥር 1- 4ኪሎ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ ላይ
ቁጥር 2- ኮተቤ 02 ጆሲ ሙል ላይ
👉ለበለጠ መረጃ  በ0911-42-42-42
0970-51-71-51 ይደውሉልን
በቲሊግራም - https://t.me/shalomdentalclinic
Face book- @shalomdentalclinic
ጊዜ ይሄዳል! እኛስ አብረን እየሄድን ነው?

ስለተቀመጥክ ቆሞ አይጠብቅህም! ስኬታማ ለመሆን የጊዜ አጠቃቀማችንን አብረን እናዳብር 🏃🏾
Join our telegram

https://t.me/+kpVVJnBHB5ZhZjI0
🎁 አዳዲስ ስማርት ስልኮችን በቅናሽ ዋጋ ከሙሉ አክሰሰሪ ጋር እንዲሁም ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር ከ HABMART :: 📲 0913849228

👉 Iphone 11 dual sim (128gb ) ..39,000br
Iphone X 256gb … 26000br
S10 5g 256/ 8gb ram …. 23,999br
S9+ 64gb/4gb ram ....16,500br
Note 9 128gb /6gb ram... 19,500br
A51 5g 128/ 8 …. 18000br
A90 5g 128 / 6 … 16500br
A42 5g 128 / 6 … 17000br
A22 5g 128/ 6 … 16500br

A12=128/4=11000 birr
M12=64/4=10000birr
A22,5g=128/6=15000birr
A32=128/6=17300birr
M32=128/6=14700 birr
M32,5G=128/6=16000 birr

Mo3core=32/2=8400birr
A02=32/2=8900birr
A02=32/3=9000birr
A52=128/8=23,500br
A12=128/6=14200br
M12=128/6=13700br
A03s=64/4=11300br

ሌሎችም አሉን ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን 📲 0913849228

📍ቦሌ መድሃኒአለም Selam city mall, 3rd floor
ልደታ AIA የገበያ ማዕከል , ground floor
አምስት ከባድ የብሬን ጦር መሳሪያዎችን ከደሴ ወደ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን በሕገወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ከነ መሳሪያው በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

ግለሰቡ የተያዘው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል እንደሆነ ተነግሯል።

መነሻውን አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ያደረገ ሕገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ግለሰብ ሰሌዳ ቁጥሩ አአ ኮድ2 B23782 በሆነ ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ ላይ አምስት ከባድ ብሬን በድብቅ በመጫን መዳረሻውን ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን በማድረግ በመጓዝ ላይ እያለ በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የመረጃ ኦፊሰሮች በግለሰቡ ላይ ከመነሻው ክትትል በማድረግ አዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በተለምዶ ካራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲደርስ ለአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ጥቆማ በመስጠት ከነጦር መሳሪያው እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል።
ሩሲያና ዩክሬን የምርኮኛ ልውውጥ አደረጉ

የምርኮኛ ልውውጡ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የመጀመርያው ነው ተብሎለታል። በልውውጡ ሩሲያ ዘጠኝ ወታደሮቿ እንዳስመለሰች ገልጻለች።
https://am.al-ain.com/article/first-prisoner-exchange-between-russia-and-ukraine
እርግጥ ነው በኦሮሚያ ክልል በተለይ ኦነግ/ሸኔ የሚንቀሳቀስበት አካባቢ ብሔራቸው አማራ የሆኑ ተለይተው ቢገደሉም በአካባቢው ያሉ የኦሮሞ ተወላጆችንም ስቃይ እንግልት ሞትና ዝርፊያን ልናዳምጥ ልንረዳ ይገባል:: የኦሮሞ ህዝብ ኦነግ/ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች የሚደርስበትን ግፍ ያድምጡ:: https://natnaelmekonnen.com/breaking-news-video-of-chefe-oromia-members-asking-shimeles-abdissa/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia : ዛሬ ምሽቱን ‹‹ የልማት ጋሬጣ›› በሚል ርእስ በከተማችን አዲስ አበባ በመሬት ዙርያ ሲካሄድ የቆየውን ቅርምትና ዝርፊያ የሚያሳይ ዶክመንታሪ ከታች በተዘረዘሩት ቴለቪዥን ጣቢያዎች ይቀርባል!! ይከታተሉ!

👉 በአዲስ ቴሌቪዥን ፤- 2፡30
👉 በኢቢሲ ፡- 3፡00
👉 በፋና፡- 3፡00
👉 እንዲሁም በዋልታ ፡- 3፡00 ይጠብቁ።
መልካም ቆይታ….
በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ይዞታ በሌላቸው ግለሰቦች ስም ከ65 ሚሊየን ብር በላይ ተገቢ ያልሆነ የካሳ ክፍያ ወስደዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 3 ተከሳሾች ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዟል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው ዛሬ ትእዛዙን የሰጠው።

ትዛዙ የተላለፈባቸው የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ገረመው ግዛቸውን ጨምሮ የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽህፈት ቤት የካሳ ይዞታ ማረጋገጥና ማጽደቅ ዘርፍ ሰራተኞች የነበሩ 21 ተከሳሾች ናቸው።

በ1ኛ ተከሳሽ አማካኝነት በቦሌ አራብሳ አካባቢ በውሃና ፍሳሽ ተቋም ለሚሰራ ውሃ ማጣሪያ ፕሮጀክት ስራ ይዞታ ከሌላቸው ግለሰቦች ጋር በዘመድና በጥቅም በመተሳሰር የመሬት ይዞታ እንዳላቸው ተደርጎ ስም ዝርዝር መግባቱ በችሎቱ ተጠቅሷል፡፡
የማዕድን ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሚገኘውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ኔዘርላንድስ ስዌል እና አሶሼት ኢንክ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር በዛሬው እለት ተፈርሟል።ኩባንያው በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ 3 ሺህ 500 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የተሰሩ የፍለጋ እና የጥናት ውጤቶችን መነሻ በማድረግ በአካባቢው ያለውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መጠን የማሳወቅና ኢኮኖሚያዊ ግምገማን የሚያሳይ ጥናት ያካሂዳል ተብሏል።

በስምምነት ስነስርአቱ ላይ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰን የኩባንያው ተወካዮች እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በሰዓት ከ6 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚምዘገዘገው ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል

ሩሲያ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል የተጠቀመች የዓለማችን የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች። ለመሆኑ ሃይፐርሶኒክ የተባለው የጦር ማሳሪያ ከሌሎች ምን የተለየ ያደርገዋል?
https://am.al-ain.com/article/hypersonic-missiles
ኢዜማ “ለውጡ በጠበቅነው ልክ አልሄደም”ሲል መንግስትን ተቸ

ብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እሰራለሁ ብሏል። ከመንግስት ጋር መስራት የማንኛውም “ጤነኛ ፓርቲ ባህሪ መሆን አለበት”-የኢዜማ ሊቀመንር የሽዋስ አሰፋ።
https://am.al-ain.com/article/ezema-says-the-change-the-government-embarked-on-fails-to-keep-going-in-tempo-as-expected
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 42 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን ተያዘ!

የኢትዮጰያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሸቱ 2፡30 ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡

ሦስት የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች መነሻቸውን ብራዝል-ሳኦፖሎ በማድረግ በኢትዮጵያ በኩል ወደተለያዩ ሀገራት 1,895 ጥቅል ፍሬ (42 ኪሎ ግራም) የሚመዝን ኮኬይን በቦርሳ ይዘው ለማለፍ ሲሞክሩ የኢትዮጰያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላችውን የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ አደጋኛ ዕፅ ቁጥጥር ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር አዲሱ ባለኒ ገልፀዋል፡፡

ኢንስፔክተሩ አያይዘውም ግለሰቦቹ በአየር መንገዱ ጣቢያ ውስጥ ግርግር በመፍጠር እና ከሰራተኞች ጋር በመጋጨት ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርጉም በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ መነሻዋን ብራዝል ሳኦፖሎ መዳረሻዋን ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል ዱባይ ለማድረግ 1049 ጥቅል ፍሬ (21 ኪሎ ግራም ከ380 ግራም) የሚመዝን ኮኬይን ይዛ የተገኘች ብራዝላዊት የኢትዮጰያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋል መቻሏን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ 15 ቀን ውስጥ 2044 ጥቅል ፍሬ (63 ኪሎ ግራም ከ380 ግራም) ኮኬይን መያዙን ከኢትዮጰያ ፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡