STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) ️
35.2K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
AASTU የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቋ

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የ2015 ዓ.ም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስገባው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገሪቷ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለሁለተኛ ጊዜ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲተ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 25-28/2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው አጠናቀዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በወጣላቸው ቅደም ተከተል መሰረት በዩኒቨርሲቲያችን ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን ሁላችሁም በሰላም ከቤተሰቦቻችሁ ጋር እንድትገናኙ መልካም ምኞቱን ያስተላልፋል፡፡

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲያችን እና በመላ ሀገሪቱ ፈተናውን ለወሰዱ ሁሉ መልካም ውጤት እንዲገጥማቸው ይመኛል፡፡
በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው በሁለት ዙር 17,721 (8833 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን እንዲሁም 8893 የተፈጥሮ ሳይንስ) ተማሪዎችን ተቀብሎ ማጠቃለያ ፈተናውን እንዲወስዱ አስችሏል፡፡
በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው በፈተና ሂደቱ ተሳታፊ ለሆኑ አካላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናውን በታላቅ አክብሮት ይድረስልኝ ብሏል፡፡

ዘገባው የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙኑት ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ነው፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆነ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው  ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ወስኗል።

ውሳኔው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ መፈጸም እንደሚያስችላቸው የታመነበት በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቅስ እንዲችል፣ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ እንዲወጣ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ስርዓትን በቀዳሚነት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንደሚሆን ይጠበቃል።

© ትምህርት ሚኒስቴር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲቲዩት
ለሁሉም አዲስና ነባር የክረምት ተማሪዎች

ለነባር የክረምት ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመረው ነሐሴ 08/2015 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን ለአዲስ የክረምት ተማሪዎች ደግሞ ምዝገባ የሚከናወነው ነሐሴ 08 እና 09/2015 መሆኑን እናሳስባለን።ስለዚህ ሁሉም የክረምት ተማሪዎች ነሐሴ 04 እና 05/2015 ወደ ግቢ መግባት ይጠበቅባቹሃል።

ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለአዳሪ ት/ቤት ትምህርት ዕድል ፈላጊዎች

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2015 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈትናችሁ

📝 በእቴጌ መነን የሴቶች 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት

📝 በገላን የወንዶች 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት

📝 በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ቀዳማዊ ምኒሊክ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ

መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች ለተጨማሪ መረጃ ከላይ የተያያዙትን ፎቶዎች መመልከት ችላላችሁ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
"ፈተናው ከስርቆትና ከኩረጃ ነጻ ሆኖ ተጠናቋል" ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከማንኛውም ፈተና ስርቆትና ኩረጃ ነጻ በሆነ መልኩ ተጠናቋል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን እና ተማሪዎችም ፈተናውን በሰላማዊና በተረጋጋ ሁኔታ መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

በአጠቃላይ 840 ሺ 859 የማህበራዊ ሳይንስና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በ2 ሺ 785 የፈተና ጣቢያዎች ተፈትነዋል።

ከሀምሌ 19 እስከ ሀምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር በተሰጠው ፈተና ከ30ሺ 438 የሚበልጡ ፈተና አስፈጻሚዎች መሰማራታቸውንም አመላክተዋል፡፡

በህግ ጥላ ስር ላሉ 515 ተፈታኞችና በኢትዮጵያ ለሚማሩና በውጭ አገር ለሚኖሩ ተፈታኞች ከነሀሴ 23 እስከ 26 ድረስ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጣቸው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ መምህሩ ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስፈታኝነት ተመድበው ባቀኑበት ጎንደር ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርጓል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት መምህር የነበሩት ታደሰ አበበ ገብረሀና (ረ/ፕ/ር) ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈታኝነት ተመድበው በሔዱበት ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም ህይወታቸው ማለፉን ተቋሙ አመልክቷል።

በ38 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት መምህር ታደሰ አበበ፤ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 2009 - 2013 ዓ.ም በእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍል በመምህርነትና በኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን ከየካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ምክትል ዲን በመሆን እያገለገሉ ነበር፡፡

መምህር ታደሰ አበበ ባለትዳርና የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
"የመኝታም ሆነ የምግብ አገልግሎት አይቋረጥም" ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ በዩኒቨርሲቲው ለተመደቡ ተማሪዎች የመኝታ እና የአልጋ አገልግሎት እንዳማያቋርጥ አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው በአማራ ክልል ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች ስልክ ካለመያዛቸው አንፃር እና ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት የሚቸገሩ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው የመኝታም ሆነ የአልጋ አገልግሎት ለተማሪዎቹ እንደማያቋርጥ ያስታወቀው።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈታኝ መምህር ሕይወቱ ማለፉ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
በቅድሚያ ለ 2015 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች 🎓  እንኳን ደስ አላቹ እያልን ለተመራቂዎች ፣ ለልደት ፣ ለ Anniversary እና ለማንኛውም ዝግጅት  ምርጥ ስጦታ ከዚህ በፊት ያልተለመደ ማንኛውንም አይነት ፎቶ ወይም ምስል ባማረ ሁኔታ እንጨት ላይ በ#MDF Colour ስራዎቻችን  በተመጣጣኝ ዋጋ በሚፈልጉት Size ለወዳጅ ዘመድዎ ያበርክቱ  🛒🛍


ይዘዙን ያሉበት ቦታ በነፃ  እናደርሳለን!

Contact:   📩 @Henak_21
                  📞 0924848164

#ለተጨማሪ የስጦታ አማራጮች ከታች ያለውን Link በመንካት ይጎብኙ👇👇

@Habesha_Gift