️ ንስር አማራ🦅
55.9K subscribers
13.5K photos
868 videos
50 files
4.39K links
የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
💚💛❤️

እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2
@NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅

ንስር አማራ🦅
#የግፉአን_ድምፅ
t.me/NISIREamhra
Download Telegram
🔥#ዘመቻ_አንድነት_ወሎ_ቤተ_አማራ_ግንባር‼️

ተጠናክሮ በቀጠለው ዘመቻ አንድነት አሳምነው ክፍለጦር ታልቅ ጀብዱ በመፈፀም
ድል ተጎናፀፉ::

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ ትናትና ሚያዚያ 23/2017 ዓ.ም ጉባላፍቶ ወረዳ ሃራ ከተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ላስቴ ቢቲሞ በር ረሽን አጅበው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ሆድ አደር ሚሊሻዎች ላይ በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት 11 በመደምሰስና ቀሪዉን በማቁሰል ታላቅ
ድል ተጎናፅፈዋል::

ጠላት ይሄንን የበጋ ወራት በምድርም በሰማይም ብለን ፋኖን ማዳከም አለብን ካልሆነ ግን ወደ ዉጊያውን ክረምት ከወሰዱት ይደመሱሱናል በሚል ገምግሞ እውር ድንብሩን በመሄድ ለብ ለብ ብሎ ሰልጥኖ የመጣ በርካታ ሰራዊቱን በደፈጣ እያስጨረሰው ይገኛል:: ለዚህም በጥይት ብቻ ሳይሆን ገደል ገብቶ እያለቀ እንደሆነ የሰሞኑ የወልድያ ዙሪያ ዉጊያ ይመሰክራል::

በብልፅግና ካድሬ ፕሮፓጋንዳ እና ለሆዱ ሲል ከትዳሩ እና ከግብርና ሞያው እየተነቀለ እየመጣ እየተማገደ እያለቀ ላለው ባንዳም ያለምንም መሰላቸት በፍፁም ትግስት ይደረግ የነበረው ሰላማዊ ጥሪ አሁንም እንደተጠበቀ ሲሆን ይህንን ተላልፎ ወገኑ ላይ የሚደረገዉን ዘር ማጥፋት ተባባሪና ተሳታፊ ሆኖ የተገኘው ግን ዛሬም ቀዳሚ የጥቃት ኢላማችን ሆኖ እንደሚቀጥል ለማሳሰብ እንወዳለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ በዘመቻ አንድነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ዘመቻ አንድነት!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
©የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ)

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#በደፈጣ_ጠላት_ተደመሰሰ‼️

ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር !

የቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ 1ኛ መብረቅ ሻለቃ ከዳንግላ አዲስ ቅዳም በፓትሮል ሲጎዝ የነበረን ጠላት ጉንድሪ ላይ ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ ሲሆን  ከ 15 በላይ ጠላት ወደ ላይኛዉ ተሸኝቶል በዘሪሁን _13 ታርጌት ተደርጎ ጠላት ዶጋ አመድ ሁኗል ፓትሮሏ በአንብስትቹ ከጥቅም ዉጭ በመሆኗ በptr ተጎትታ ተወስዳለች

ንስሮቹ የቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ አናብስቶች ጠላትን ከተማ ድረስ በመግባት በተጋጋሚ እያደባዩት ሲሆን በአፋጎ ሳይንቲስቶች የተመረተዉ ዘሪሁን_13 ትን በመጠቀም ተደጋጋሚ ጠላትን እየወቁት ይገኛሉ

©ፋኖ ይበልጣል የዉነቱ ጀግናዉ  (እሳቱ) የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥 የአባ እረፍርፍ የሻለቃ አንሙት ልጆች እጅን በአፍ እሚያስጭን ጀብድ ፈፀሙ‼️

   የምድር ድሮን በመባል የሚታወቀው የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ ሻለቃ ሁለት (መብረቁ) ሻለቃ በዛሬው እለት ማለትም በቀን 24/08/2017 ዓ.ም በይልማና ዴንሳ ወረዳ እና በአዴት ከተማ አስተዳደር ትብብር የዞንና የክልል አመራሮች  በአዴት ከተማ ላይ ስብሰባ ለማድረግ በስብሰባ አዳራሽ መግባት በጀመሩበት ሰዓት ከጠዋቱ 2:00 ሰአት እስከ እረፋድ 4:00 ሰዓት የጀግናው የሻለቃ አንሙት ልጆች አዴትን ዙሪያዋን በመክበብ
#በዘሪሁን13 የፈጠራ ውጤት እና በዲሽቃ አመራርን ያነጣጠረ ጥቃት መሀል ከተማ የመሰብሰቢያ አዳራሽንና የአስተዳደር ህንፃን በመደብደብ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ተችሏል።

   እሚገርመው ጥቃቱ በሚፈፀም ሰሀት የአብይን ተላላኪ አመራሮችን አጅቦ የመጣው የአገዛዙ ዙፍን አስጠባቂ ሀይልና ከፍተኛ የብልፅግና አመራሮች ቦርጫቸውን ታቅፈው እርስ በርሱ እየተጠላለፉ እግሬ አውጭኝ ብለው ፈርጥጠዋል። ቀኑንም የመሸበትና የከሸፈው የብልፅግና ውሎ ብለነዋል። አሁንም በአማራ ህዝብ ደም በሚቀልድና የህዝባችን የመከራ ዘመን በሚያራዝም ሀይል ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን።

  
ድል የጭቁኖች ጋሻና ጉልበት ለሆነው ፋኖ!
    ክብር ለተሰው ሰማዕታት!!!💪💪💪

©አማረ ጌታቸው የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለጦር የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት
 
          ጎጃም አዴት!

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#የታፈሱ_ወጣቶች_በአናብስቱ_ነፃ_ወጡ‼️

የዛሬ የውጊያ ውሎ
የአማራ ፋኖ በሸዋ በአፄ ይኩኑ አምላክ ስር የምትገኘው ብሩኬ ደምሴ ብርጌድ በዛሬው ዕለት ከግሼ እራቤል ወጣቶችን አፍሶ በግዳጅ ወደ ስልጠና ለመውሰድ ከግሼ ራቤል ተነስቶ ወደ ወረኢሉ ለማሻገር አስቦ ወጣቶቹን በቅጥቅጥ ጭኖ በድሻቃና በብሬን አጅቦ
#ዋየት_ጅረት ላይ ሲደርስ እንቢ አልገዛም ሻለቅ በዘመቻ መሪው ኮማንዶ ታደሰ ተስፋዬ እየተመራች ተወርውራ በመድረስ የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ነኝ በሚለው ጥምር ጦር ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር ወጣቶቹን ያለምንም ጉዳት #ሙሉ_በሙሉ አስለቅቃለች(ነፃ አውጣለች)።

በዚህ ወቅት ጥምር ጦር የተባለው እግሬ አውጭኝ ብሎ ሊፈረጥጥ ችሏል ሲሉ ከንስር አማራ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፋኖ መ/ር ከበደ ወርቁ የብሩኬ ደምሴ ብርጌድ የፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ገልፀዋል‼️


#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
️ ንስር አማራ🦅
Photo
🔥ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜ/ጀ/ል ውባንተ አባተ ኮር(1ኛ ኮር) ጉና ክፍለጦር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ‼️

በጀመርነው የህልውና ትግል 22 ወራትን እያስቆጠርን ቢሆንም አለምን ያስደመሙ አያሌ ሁነቶችንና፤በርካታ ድሎችን ብናስመዘግብም ትግል ነውና ብዙ ፈተናዎችንም አስተናግደንበታል። ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲሉ የሞቀ ቤታቸውንና ኑሯቸውን ትተው በዱር በገደሉ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው አይተኬ የሆነውን ውድ ህይዎታቸውን ገብረውበታል። የአማራ እናቶች ያፈራቻቸው ጀግና አርበኞች በደማቸው ደማቅ ታሪክ እየፃፋ ካለፉ በርካታ አርበኞች መካከል እነ አርበኛ ውባንተ አባተ፣ አሌክስ አባተ ፣ፋኖ ባየው መልካሙ፣ እነ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌ፣ እነ አርበኛ ቴዲ ... ወዘተ የመሳሰሉ እልፍ ጀግኖችን ያጣን ቢሆንም በደማቻው የለኮሱት የትግላችን ሻማ ወደኋላ ላይመለስ ከትናንት በበለጠና በተፋጠነ መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ጀግንነትን ከአባቶቻቸው የወረሱት የገብርየና የቴዎድሮስን ግብር የተላበሱት ውጊያ ሲገባ ሳቅ ሳቅ የሚላቸው አባል ሳይወጣ የማይሸሹት የእስቴዴንሳ ብርጌድ አባል የሆኑት እነዚያ  የጦሩ ገበሬዎች ዝምተኛውና አመለ ሸጋው የትናንቱ የአማራው ልዩሀይል አባል የዛሬው ፋኖ መሪ ያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሻለቃ ሁለት መሪ የነበረው
#ሻለቃ_ፍቃዴ_አለባቸውና የሻለቃ አንድ ዘመቻ መሪ የነበረው #ዘመቻ_አበበ_አንለይ ለቀጠናዊ ትስስር አባይን በመሻገር ወደ ጎጃም ሞጣ ወረዳ ልዩ ስሙ አይጠፋዘር ወደሚባል ቦታ በተጓዘበት ከግሪሳውና የአንድ ወገን ስርአት አስጠባቂ  ሰራዊት ጋር ባደረጉት 3ቀን የፈጀ እልህ አስጨራሽ መደበኛ ውጊያ ከአጋር ፋኖ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ከ150 በላይ ሙት እና ከ70 በላይ ቁስለኛ በመጣል 3 ዙ 23 በማቃጠል በቀን 19/08/2017 ዓ.ም ውድ ህይዎታቸውን ለአማራ ህዝብ ሰውተው አልፈዋል።
ለተሰውት ታጋይ ሰማዕታት ፍቃዴ አለባቸው እና አበበ አንለይ ነፍሳችሁን ልዑል እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ያሳርፍልን። ለሰማዕታቱ ቤተሰቦችና የትግል አጋሮች በጉና ክፍለጦር ስም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጂ ዘመዶቹም  መፅናናትን እንመኛለን።

በስተመጨረሻም ውድ የጉና ክፍለጦር አባላትና የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ አመራርና አባላት ሀዘናቹ ሀዘናችን ስለሆነ ያጣናቸው ታጋይ መሪዎችን ከእንግዲህ የማናገኛቸው ስለሆነ ሰራዊቱን በማፅናናት የጀመርነውን ትግል ከግብ ለማድረስ ማሰልጠንና ማደራጀት የግድ ስለሆነ እንደነ ፍቃዴ ያሉ ጀግኖችን እንድትፈጥሩ መልዕክታችን ነው።

                ታጋይ ይሞታል ትግል ይቀጥላል
©ጉና ክፍለጦር

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
️ ንስር አማራ🦅
Photo
🔥#ጦርነት‼️

ጦርነት 'በሁለት ተጣራሪ ሀሳብ ባላቸው' ግን ደግሞ 'ተመጣጣኝ የትጥቅና ሰው ሀይል ቁመና ባላቸው' ሀይሎች የሚፈጠር ግጭት ነው። የተለያየ የጦርነት ስልት ወይም ተቃውሞ አለ። የህልዉና አጣብቂኝ የገባ ህዝብ ሲኖርህ ደግሞ የቁመናህ ልኬታን መስፈርት ሳታደርግ እስከመጨረሻው ህቅታ ትገጥማለህ። የአማራ ህዝብ አሁን የገጠመው ይሄው ነው። በጓንዴ ቁመህ ጠብቀኝ መሳሪያና ባይራክታር ድሮን፣ በክላሽንኮቭና su27 ሚግ፣ በሮኬትና F-1 ቦምብ መካከል ባለ ልዩነት ውስጥ ቁመን ጠላትን የገጠምነው የተጋረጠብን ችግር የመኖርና አለመኖር አጣብቂኝ ስለሆነ ነው።

ፋኖ እስካሁን እየተጠቀመበት ያለው ስልት አንድ አይነት ነው። እሱም የሽምቅ (ጎሬላ) ውጊያ ይባላል። ይህ ስልት ሁለት አላማ አለው፦
፩ኛ መንግስት መር የዘር ጭፍጨፋን መክቶ ለድርድር ማቅረብ ወይም
፪ኛ ፋሽሽታዊ ስርዓትን ገርስሶ ስልጣን መያዝ ነው።

በሽምቅ(ጎሬላ) ውጊያ ውስጥ “ህዝባዊነት” ሊከበርም ሊታፈርም የሚገባ ቀይ መስመር ነው። በቀጠናችን ውስጥ ከሽምቅም ከፍ ያለ መደበኛ ዉጊያወች ሲደረጉ የቆዩት ህዝቡ ለነፃነቱ የፈጠረው ትግል ስለሆነ ነው። የትግል አጀንዳና ሀሳባችን ባለቤቱ ህዝብ ነው። በዚህ ህልውናን የማስቀጠል ትግል ውስጥ ‘ፋኖ’ የአማራ ህዝብ በሚያደርገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ድጋፍ ሰጭ አካል ነው።

የሆነው ሁኖ ይህ የያዝነው የትግል ስልት ፋኖን የት ድረስ ያስኬደዋል? “ግለሰባዊ ዝና፣ ስውር የጠላት እጆች፣ ስልጣንና ቁሳዊ ፍላጎት” በተለያዩ ጭምብሎች እየተሸፈኑም ቢሆን ተጋድሏችንና የትግል ስልቱን ለማወክ እየሞከሩ ነው። በማወቅ አስልተው፣ ባለማወቅም ተታለው ከዚህ ዝብርቅርቅ ጎራ የተሰለፉም ለመሰለፍ የሚዳዱም አሉ። ይህ ለህዝባችን ከጠላትነት በላይ ጠላትነት ነው። ይታሰብበት!

ቁጭም ብድግም ብለን የምንታገልለትን ህዝብ ማገልገል ግዴታችን እንጅ ወገንን በግልምጫም በቁንጥጫም ማሳቀቅ መቆም አለበት።

አንድ ያልሆነ ፋኖ የህዝብን ጥያቄ አይመልስም። በህዝባዊ ጥያቄና ትግል መነገድም መቆም አለበት።

በታሪክ፣ በፖለቲካ፣ በውትድርናና በማህበራዊ ዘርፍ በልካቸው ማውራት የሚችል ስብስብ ሀይል {stock} ውስጣችን ላይ አለን። ከዚህ ላይ “አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ” የሚለው መፈክራችን ገቢራዊነትን ይፈልጋል። የትግል ሜዳው ሃቅን እንጅ ቲፎዞን የሚፈልግ አሰላለፍን መያዝ የለበትም።

አንዳንድ ወንድሞች ያለ ፍላጎታቸው (ሳይወዱ በግዳቸው) የሚታገሉ (ይቅርታ የምናታግላቸው) አሉ። በህፃንነቱ ትምህርት ቤት ሂድ ተብሎ አልሄድም ያለን ህፃን “ቤተሰብ ለመጣዒ ዕጣ ፋንታው አስቦ… አስገድዶ ትምህርት ቤት የመላክን ያክል” የህፃንነት ባህሪይ ያጠቃቸው መሪ ነን ባዮች ከውስጥም ከውጭም በተቀናጀ የሚዲያ ስም ማጥፋት ዘመቻ መሪዎች ላይ መክፈት አስነዋሪ ተግባር ነው።

ትግል በባህሪው ፌርማታ አለው። ሲያቅተን የፈለግንበት ቦታ የመውረድም የማረፍም መብት የተጠበቀ ነው። በድብቅ አጀንዳ የህዝብን ትግል ክዶ ራስን ለቶክሲዶ ሱፍ ቀድሞ በማጨት ብዙ ዋጋ የተከፈለበትን
ድል አሳልፎ ለመስጠት መሞከር፣ ከዚህም ከዚያም ግጭትን በመጥመቅ ለድርድር ሸብረክ የሚል ደካማ ሀይል ለማፍራት መሳተፍ… ትግሉን የተሸከሙ አባላችንን አቅም ካለማወቅ የመነጨም ቂልነት ነው።

ግራም ተነፈሰ ቀኝ ግን...
አንድ አማራ አንድ ፋኖ!
ሁሌም እንደምንመካከረው፦ “Focus on the high impact activities” Brothers!

አይዞን!

©ኢንጅነር ማንችሎት እሱባለው
የአማራ ፋኖ በጎጃም ወታደራዊ አማካሪ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#አስቸኳይ_መረጃ_ሼር_ይደረግ!

አገዛዙ እስትንፋሱን ለማራዘም
#ለወታደርነት ያፈሳቸውን ህፃናት ከጋይንት 4ባስ፣ ከክምር ድንጋይ ወረዳ 6ባስ በመጫን ወደ ደብረታቦር ከተማ አምጥተዋቸዋል።

ስለዚህ ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ ከደብርታቦር በሗላ ያሉ መንገዶች ይጠበቁ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ማስልጠኛ ካንፕ ስለሚወሰዱ የታፈሱ አማራዎችን እናድን‼️

ይሰማል ፋኖ
ይሰማል አማራ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥በቡሬ ንፁሃን  አባት እና ልጅ በፋሽስቱ አገዛዝ ተረሸኑ‼️

የቡሬ ከተማ የፋሽስቱ አገዛዝ  ንፁሀንን መረሸኑን ቀጥሏል በቀን 24 / 08 / 2017 ዓም ከምሽቱ 5:00 ሰዓት ገደማ ከቤት በማስወጣት አባት እና ልጅን ቡሬ ከተማ ፈረስ ወጋ ከመኖሪያ ቤቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽኗቸዋል።

➣ ዘላለም ከበደ የቡሬ ዙሪያ ወረዳ የወረዳ የተፈጥሮ ሀብት ባለሙያ ሲሆን ከምንም አይነት ፖለቲካ ፍፁም ገለልተኛ የከተማችን ነዋሪ ነው።

➦ ዘላለም ከበደ ዕድሜ 41
➦ ልጅ              ዕድሜ 15

ይህ አገዛዝ ቀን ቀን መሰብሰቢያ አደራሽ እየሰበሰበ ቢደሰኩርም ደም ግብሩ የሆነው ሰው በላ ስርዓት ግን የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈው ይገኛል።

♦️ የቡሬ ከተማ ወጣት በእየ ተራ ከማለቅህ በፊት ወደ ጀግናው የቡሬ ዳሞት ብርጌድ በአፋጣኝ ተቀላቀል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#አፋሕድ_ከአገዛዙ_የባሰ_ጠላት_ነው‼️
አፋሕድ ከአገዛዙ በትናትናው ዕለት ፋኖን ይወጋ ዘንድ 1 አይሱዙ
#ተተኳሽ ተበርክቶለታል‼️

ራሱን መከላከያ ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን ከደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ከወገል ጤና 1 አይሱዙ መኪና ተተኳሽና መሳሪያ በመጫን ታች ጉርቢት አፋፍ ድረስ ደጋው ክፍለ ድረስ አጅቦ በመውሰድ
#ጨጎማ ላይ በኮረኔል ፋንታው ሙሃቤ የሚመራው የዳውነት ፋኖ በይፋ ህዝቡ እያዬ አስረክቧል ፣የእስክንድር ሚሊሾቾም ተቀብለው ወስደዋል ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች አረጋግጠዋል።

ምንጮቻችን አያይዘውም አፋሕድ ከአገዛዙ ጋር አብሮ ይሰራል የሚለው በህዝቡ እንዳይረጋገጥ ለማድረግ የውሸት የተኩስ ልውውጥ በማድረግ መኪናው ወደ
#ጨጎማ_መገንጠያ_ዋድላ መስመር እንዲንቀሳቀስ ተደርጓ የኮረኔል ጦር መልሶ #ጨጎማ ላይ ተተኳሹን ተረክበዋል ግን ህዝባቸንንን መሸዎድ አይቻልም ህዝቡ አፋሕድ በፋኖ ስም የሚንቀሳቀስ የአብይ ሚሊሻ አንደሆነ በአይናቸው አይተው አረጋግጠዋል ሲሉ በአግራሞት አረጋግጠዋል።

በእስክንድር ነጋ የሚመራው አፋሕድ በጠላትነት ፈርጆን ሊያጠፋን በምድርና በሰማይ የጥይት አረር ከሚያዘንብብን አብይ አህመድ በላይ ጠላት ነው። ምክንያቱም አማራን ነፃ አወጣለሁ በማለት በፋኖነት ስም እየማለ ተግባሩ ግን ከጠላት ስንቅና ትጥቅ እየተቀበለ
#ድምፅ_አልባ ግድያ እየፈፀመብን ነው‼️

ይህ ተተኳሽ አፋሕድና አገዛዙ በጋራ ፋኖ ላይ ለሚከፍቱት ውጊያ የቀረበ ስለሆነ የጎንደርና ወሎ መገናኛ ቀጠናና አጎራባች ፋኖዎች ዝግጁ እንድትሆኑ ንስር አማራ ታስጠነቅቃለች‼️

የአፋሕድን ገመና በይበልጥ መሬት ላይ ካለው
#ከጨጎማ ህዝብ ማረጋገጥ ይቻላል‼️

#መረጃው_ሼርርርር_ይደረግ‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#አርበኛ_አበበ_ፈንታው‼️

አርበኛ አበበ ፈንታው ሁሌም ከፊቱ ላይ እልህ፣ ወኔ ፣ጀግንነት የሚነበብበት ፣ በትግል የጉዞ ሂደቱ በተሳሳተና በፀረ አማራ መንገድ ተገኝቶ የማያቅ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ 💪

አርበኛ አበበ ፈንታው የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሲሆን አንደበቱ ማራኪ፣ ቃላቶቹ ቁጥብ ፣ ንግግሩ የፕሮፓጋንዳ ጋጋታ የለለበት የመርህ ሰው ፣ የህዝብ ግንኙነት የውሀ ልክ ብንለው ያንስበታል። እነዚህ ውስን ቃሎች የመግለፅ አቅም ባይኖራቸውም አርበኛው በጥቂቱ ይህንን ይመስላል🙏

#በዚህ_ቀጥል_አርበኛው‼️
#እናከብርሀለን🙏

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ናሁሰናይ_ብርጌድ💪

      የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በዋና እሙሀይ የምትመራው ናሁሰናይ አንዳርጌ ብርጌድ ዛሬ ሚያዚያ 25/2017 ዓ/ም  ከአምባ ጊወርጊስ ወደ ገደብየ በኦራል ሲንቀሳቀስ የነበረ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሀይል ልዩ ቦታው ወርቀደቦ ላይ ከቀኑ 6 ሰአት ላይ በተወሰደ ኦፕሬሽን ሹፌሩ ተመትቶ የጠላት መኪና እግሩን ወደ ላይ ሰቅሎ በመገልበጡ አንድም ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ የነበሩት 27 በሙሉ ወደ ላይኛው ቤት ተሸኝተዋል ።

   ጠላት አስከሬን ለማንሳት ከገደብየ እና ከአምባ ጊወርጊስ ከተሞች በርካታ ሀይል ይዞ ቢመጣም የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ ወይም ከወደቁ በኃላ መፈራገጥ አጉል ጀርባ መምለጥ ሁኖበት ለሶስት  ሰዓት ከፍተኛ ምት ገጥሞት ምንም ሳይፈይድ ለድጋፍ የመጡ ሌሎች ሀይሎች ከፍተኛ ሰባዊ  እና ቁሳዊ  ኪሳራ አስተናግደው ተጨማሪ አንድ ኦራል እና ሁለት ፒካፕ መኪኖች ተመትተው ባሉበት ቁመው ቀርተዋል። አገዛዙ ዛሬም እንደ ትናንቱ የሽንፈት ጽዋን ተጎጭቶ በሀፍረት ተመልሷል።

      ናሁሰናይ አንዳርጌ ብርጌድ ከዳባት እስከ አምባወርጊስ ከተማ ከሌሎች የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አባላት ጋር በመሆን በተደጋጋሚ ኦፕሬሽን በመስራት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የምትታወቅ እና የምንኮራባት ጠንካራ ብርጌዳችን  ናት።

ለአዲስ ስኬት እንበቃለን፣ ምቹ ሀገር እንገነባለን::
              
                         አንድነት ኃይል ነው      
            
©አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥በዘመቻ አንድነት ወሎ ቤተ-አማራ ተከዜ ክፍለ ጦር ድል አስመዘገበ‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ተጠናክሮ በቀጠለው የህልውና ትግል በላስታ አሳምነው ኮር ስር በአርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ የሚመራው ተከዜ ክፍለ ጦር የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ላይ
ድል ተቀዳጀ።

ሚያዚያ 24/2017 ዓ.ም አመሻሽ  10:00 ሰዓት አካባቢ መነሻውን ግዳን ወረዳ ሙጃ ማርያም አድርጎ ዴንሳ ከተማ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን አፈሳ ለማካሄድ አስቦ የተንቀሳቀሰውን የጠላት ጦር በንቃት ሲከታተሉት የነበሩት ተከዜዎቹ ሻለቃ አንድና ልዩ ዘመቻ ፋኖዎች ዴንሳ ከተማ ዙሪያውን በማተት ለጠላት የእሳት ረመጥ ሆነው በጥይት አረር ሲቆሉት አምሽተው አይበገሬዎቹ ዴንሳ ከተማን ሳያስነኩ ጠላት አንድ ፖትሮል መኪና ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደነበረበት ሙጃ ማርያም ተመልሷል። በዚህ አውደ ውጊያም በጠላት ሰራዊት በኩል አንድ ከፍተኛ አመራር እንደተሰዋና በዚህም የተበሳጨው የአገዛዙ ጦር ሙጃ ማርያም ላይ የሚገኙ ወጣቶችን አፈሳ እያካሄደ ይገኛል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ በዘመቻ አንድነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ላስታ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን ገልጿል።


    ድላችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ)

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ከበባው_ተቀልብሶ_ጠላት_ተለብልቧል💪

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር የሰሜን ብርቅዬ ክ/ጦር በአርበኛ ደሳለኝ ፈንቴ የሚመራ በኪንፋዝ በገላ አጠላ ላይ ጠላት ሌሊቱን ተጉዞ ዙሪያውን አፈና ያደረገባቸው ቢሆንም ከበባውን በመስበር በትንሽ መሰዋትነት የጠላትን ሃይል ረፍርፈውት ከበባውን ሰብረው መውጣት ችለዋል።

የንስሮቹ አይን አይስትም!!ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮርሰሜን ብርቅየ ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ከበባውን ቀልብሶ ወደማጥቃት ተሸጋግሯል።

©የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ለሀቀኞች_የአማራ_ፋኖ_ስራ_አስፈፃሚዎች‼️

ብአዴን የሰፈር፣የመንደር ልጅ፣ ቤተሰባዊነት ፣ እንዲሁም በጥቅም ሰንሰለት በመተሳሰር አማራነትን በሆዱ ሸጦ ለበርካታ አመታት በዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ዘግናኝ ግፍ አስፈፅሞብናል‼️

አሁን ላይም በአማራ ፋኖ አደረጃጄቶች አቅም ሳይሆን ትውውቅ ፣ ጀግንነት ሳይሆን ቲፎዞ(አጨብጫቢ) ፣ ሀቀኝነት ሳይሆን ምላስ፣ ጭንቅላት ሳይሆን ሆድ ያላቸው ሰዎች ማይገባቸው ሰዎች ሀላፊነት ላይ ተቀምጠው ህዝቡን፣ ጦሩንና ትግላችንን ዋጋ እያስከፈሉትና እየጎዱት ይገኛሉ። ትውልዱ እየታገለ ያለው እኛም ሌት ከቀን የምንለፈልፈው
#የጠገበውንና_የአረጀውን_ብአዴን አውርደን #የራበውና_አዲስ_ብአዴን ለማንገስ አይደለም‼️

ታጋዩንና ህዝቡን ከሚያማርሩ ነገሮች ግምባር ቀደሙ ነገር የአመራሮች አፀያፊ ስራ መሆኑን አስረግጠን እንናገራለን‼️

ስለሆነም ለአማራነት በሀቅ ቆመው የአካልና የህይወት መስዎትነት የከፈሉ የፋኖ አባላትና አመራሮች እንዲሁም የህዝባችን ደም (መስዋትነት) የሚያራክሱ ከታችኛው መዋቅር እስከ ዕዝ ድረስ በሀላፊነት የተሰገሰጉ ግለሰቦችን በመመርመር የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን‼️

ክብር ለትግሉ ሰማዕታት‼️


#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ባህርዳር💪

መኮድና አየር ሀይል ላይ ጥቃት ተፈፅሟል!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር የጣናው መብረቅ ብርጌድ በዛሬው እለት ከሌሊቱ 9:30-11:ዐዐ ሰዓት ድረስ በተደጋጋሚ ከባድ መሳሪያ ጥቃት አድርሷል። በካምፑ ላይ ከፍተኛ ቁሳዊ ጉዳት ማድረስ ተችሏል፣ጠላት በብስጭት በመድፍ ዙሪያውን ተራራ ሲደበድብ አርፍዷል።

[የአማራ ፋኖ በጎጃም]

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#የጠላት_እንቅስቃሴ_ሸዋ‼️

አሁን ዙ~23 ከጉንደ መስቀል ወደ ሜታ መስመር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
️ ንስር አማራ🦅
Photo
🔥#የተሸነፈዉ_ቡድን_ተቋማትን_አወደመ‼️

በሰሜን አቸፈር ወረዳ ሳንክራ ት/ት ቤት ላይ የብልፅግና ወታደር ነን ባዮች ካምፕ አድርገዉ በነበሩበት ሰዓት ትምህርት ቤቶችን መገልገያ የነበሩ፦

✔️ወንበሮችን
✔️መፃሃፍቶችን
✔️መስታዉቶችን በማረጋገፍ
✔️አጥሮችን አፍርሶ

ከፈረጠጠ በኋላ ወደ በረሃ(ዳርፉር) ከገባ በኋላ አማራ በኢኮኖሚ እንዲደቅ የፈለገዉ አዉዳሚዉ የሸኔ ስብስብ በሳንክራ የፈፀመዉን ተግባር በዳርፉርም ፋኖ የህዝብ ልጅ አስከብሮት የነበረዉን የት/ት ቤትና የመብራቱን ተቋም አማራ ጠሉ ብል*ግና አዉድሞታል።

✔️ የመብራት ገመዶችን መበጣጠስ
✔️የቀበሌዉን መገልገያ ተቋሞች ማዉደም
✔️የግለሰብ ቤት ገብቶ ፍሪጅ መስበርና የእህል ሚዛኖችን ጭኖ መዉሰድ

እና ሌሎችንም በማዉደም ጫንቃ ላይ ተሰባስቦ ግለሰቦች ቤት እየገባ ዝርፊያዉን ቀጥሎበታል።

እራሱን የተመታዉ እባብ ህዝቡን በመዝረፍና ተቋሙን በማዉደም አፃፋዉን የመለሰ መስሎት ጥፉቱን ቀጥሎበታል።

   ፋኖ በህዝቡና በፈጣሪ ሃይል ያሸንፋል
ብልፅግናም ብቻዉን ቀርቶ ይሸነፋል !!

አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!

©የአፋጎ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ብርጌድ የህ/ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ አበበአምላኬ(ማንከቻዉ)

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
️ ንስር አማራ🦅
Photo
🔥#ከአማራ_ፋኖ_በጎጃም_የተሰጠ_መግለጫ‼️
       ሚያዝያ 26/2017 ዓ.ም

የአብይ አህመድ አሸባሪ ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ በአሁኑ ሰዓት ሁሉን አቀፍ ወንጀሎችን እየፈጸመ ይገኛል።

የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ያለው አብይ አህመድ የአማራ ገበሬ ጠላት ወደያዛቸው ከተሞች ገበያ ውሎ ለመመለስ በሄደበት በማገት እና ሚሊሻ ብለው ወደሚጠሩት አደረጃጀት በግድ በማስገባት እንዲሁም ወጣቱን የእለት ጉርሱን ለመሸፈን የቀን ስራ ከሚሰራበት ቦታ በማገት አድማ ብተና እና መከላከያ ወደሚሉት የግለሰቦች ሰራዊት በማስገባት አማራውን- በአማራው ማታኮስ በሚል ስር የሰደደ የጥላቻ አጀንዳ የተጠመደው ወራሪ ሐይል ሰለባ ሁነው የሚገኙ ወጣቶች አሉ።

አብይ አህመድ የአማራን ርዕስቱን መንጠቅ ፣ ትጥቁን ማስፈታት የሚለው አጀንዳ የመጀመሪያ የመተግበሪያ መቅድሙ በማድረግ የጀመረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በህዝባችን ላይ የስነልቦና ጫና ለመፍጠር በክልል እና ዞን ከተሞቻችን የሚኖሩ ማህበረሰባችንን በማስገደድ መሳሪያ ገዝተው ገቢ እንዲያደርጉ ተደርገዋል።

መንግስታዊ አሸባሪው የአብይ አህመድ ቡድን የአማራን ህዝብ የኢኮኖሚ ተመጽዋች እንዲሆን ፣ አርሶአደራችን በገንዘቡ የአፈር ማዳበሪያ ገዝቶ ምርት እንዳያመርት  የማዳበሪያ የሽያጭ ተመን ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ በመጨመር እንዲሁም ገንዘቡን ወስዶ መግደያ መሳሪያ ለመግዛት በእቅድ እየሰራ ይገኛል ።

አብይ አህመድ እና ጭፍሮቹ በአሁኑ ሰዓት አከርካሪያቸው የተመታ በመሆኑን በዓለም  አደባባይ በፍርድ ገመድ እየተጎተቱ  የሚቆሙበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን አየገለጽን:-

ማዳበሪያን በተመለከተ :-
ከአመት ዓመት አርሶ እና አለስልሶ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚመግበውን የአማራ ገበሬ በሐይል በመውረር ከላይ በድሮን እና በጀት ፤ ከምድር በታንክ እና በእግረኛ በየቤቱ እየገባ መጨፍጨፉ ሳያንስ የኢኮኖሚ አሻጥር ውስጥ በማስገባት ማዳበሪያ በመከልከል እና እጅግ በተጋነነ ዋጋ ለሽያጭ በማቅረብ በህዝባችን ላይ የኢኮኖሚ ጦርነት አውጇል ።

በዚህም :-
1.1/ የአፈር ማዳበሪያ ለሽያጭ ያቀረበበት ዋጋ የአማራን ገበሬ የሐገር የጀርባ አጥንት የካደ ብቻ ሳይሆን ህልውናውን ለማጥፋት በተጋነነ ዋጋ ለመሸጥ እየተዘጋጀ በመሆኑ መላው አርሶ አደራችን አሁን በቀረበበት ዋጋ ማለትም በ 8,000 ( ስምንት ሺህ ) ብር እንዳትገዙ እናሳስባለን ።

1.2/ የህልውና አደጋ ገጥሞት ራሱን ከወራሪ ጠላት እየተከላከለ በሚገኘው የአማራ ገበሬ ላይ የገንዘብ ትርፍ ለማግኘት ከወንበዴው ስርዓት ተመሳጥራችሁ በህገ ወጥ መንገድ የአፈር ማዳበሪያ ከዝናችሁ በተጋነነ ዋጋ ለመሸጥ የተዘጋጃችሁ ነጋዴዎች በትክክለኛው ተመን የማትሸጡ ከሆነ ድርጅቶችን የአማራ ፋኖ በጎጃም ማዳበሪያውን ለማህበረሰቡ እንደሚያከፋፍል እና እናንተም ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን ።

1.3/ ለመላው የጎጃም ማህበረሰባችን :- በህገወጥ መንገድ ማዳበሪያ ከዝነው የሚገኙ ነጋዴዎችን በአካባቢያችሁ ለሚንቀሳቀሱ ብርጌዶች እና ሻለቆች እንድትጠቁሙ እንጠይቃለን ።

2/ከአሁን በፊት የውትድርና ሙያ ስልጠና ወስዳችሁ ማለትም በእግረኛ ፣ በኮማንዶ፣ በሜካናይዝድ እና በሌሎች ወታደራዊ ዘርፎች የሰለጠናችሁ እና በፋኖ አደረጃጀት ያልተካተታችሁ ወገኖቻችን በሙሉ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የድርጅታችን ብርጌድ /ክ/ጦር በመሄድ እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን። በዚያውም በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና መከራ እያዩ እንዳላዩ መሆን የጨፍጫፊውን ስርዓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።

3/የአብይ አህመድ የግል ሰራዊት በመሆን በሚዎረዎርላችሁ ሽርፍራፊ ገንዘብ ቤተሰባችሁን እና ህዝባችንን እየገደላችሁ ያላችሁ የሚሊሻ አባላት በሙሉ ወደኛ እንድትመጡ እና ቤተሰባችሁን በሰላም እንድታስተዳድሩ የምረት ጥሪ እናደርጋለን።

4/ ከስራ ገበታችሁ በአብይ ቅልብተኛ ወታደሮች ታግታችሁ በግዳጅ የአድማ ብተና አባላት ፣ የመከላከያ አባላት የተደረጋችሁ ወጣቶች በሙሉ የያዛችሁትን የጦር መሳሪያ በመያዝ ወደ ድርጅታችን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን።

5/ ከሌላ ክልል ተገዳችሁ ወደ መከላከያ ሰራዊት/የአብይ ጦር /የገባችሁ ግለሰቦች ድርጅታችን ውስጥ ተቀላቅላችሁ ከመታገል ባለፈ ወደ ቤተሰቦቻችሁ ለመሄድ ለምትፈልጉ ድርጅታችን ባወጣው የመሳሪያ የክፍያ ተመን መሰረት እየተከፈላችሁ የምትሄዱ መሆኑን እንገልጻለን።

6/ በምናደርገው የህልውና ተጋድሎ ውስጥ የግል ጦር መሳሪያ ታጣቂዎች ታላቅ ተጋድሎ እያደረጋችሁ የምትገኙ መሆኑ ይታዎቃል።ነገር ግን  በድርጅታችን ባለው የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ ተጠርንፎ ለመታገል ሁኔታዎች ያልፈቀዱላችሁ የግል ታጣቂዎች ለድርጅታችን በውሰት እንድታስረክቡ ስንል እናሳስባለን።
በውሰት የሰጣችሁበትን  መታዎቂያ መጣል ወይም ለሶስተኛ ወገን አሳልፍ መስጠት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

7/ በህዝባችን ላይ እየተደረገ ያለውን   ይፋዊ የኢኮኖሚ ጦርነት ለመከላከል ማንኛውም የእህል ነጋዴ ላልተዎሰነ ጊዜ ከቦታ ቦታ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ
©የአማራ ፋኖ በጎጃም

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#መረጃ‼️
አሁን ከቀኑ 10:10  ከተለያዩ ቦታ የመጡ እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች በፖሊስ ታጅበው ወደ ማንጎ መናፈሻ ህዳር 11 የህዝብ ላይበራሪ አካባቢ ገብተዋል።

የንስር አማራ ምንጫችን አያይዘው አንዳንዶችን ለመስማት ሞክሬ ነበር አብዛኞቹ ዘመቻ ምናምን ሲሉ ነበር።አንዱ እንዲያውም በቅርቡ ይኖራል ሲል ሰምቸዋለሁ።

የደህንነት አባሎች ፋኖን ለመሰለል የሚላኩ ሊሆኑ ስለሚችሉ አስቸኳይ ለፋኖዎች አድርሱልኝ 3 የታጠቀ የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ አጅበዋቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል መረጃው ይሰራጭ‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ከህዝባችን_ጋር‼️  #ኑዉ_ዝብሊ‼️

"አዊና አሚኺሪ ንካማ እምፕልካ እምልካ ቻኻ ዜርካ ኪፂስታያሱ ኽምቢስ ጌዉስኝፅኝስ ኳያንኩሳ እንኳኽና። እንስ ዙርሜ አይኝስ እንቶጂ ዴሬትየን። እምፕላ ፄፃፋዳ ላኝሾ ሴንቴክኝስ ካላዉ ዝኩኒ ይንታማ ሞኬርስ።"

|"አገዉ አማራ እያሉ አንዳንድ ወፍ ዘራሾች ባልተቀጣ አፋቸዉ ለልዩነት እንደሚጮኹ ሰምተናል። ለእነዚህ መልስ ለመስጠት እናንተ አትድከሙ። አንድ የፀጉር ዘለላ ለሁለት መሰንጠቅ የሚሆንለት ካለ መጦ ይሞክረን።"|

ዛሬ ከህዝባችን ጋር በአንድነት ስንመክር አንድ አባት ከተናገሩት የተወሰደ!

ዛሬ በቀን 26/08/2017 ዓ/ም ከህዝባችን ጋር ትኩረት ሰጥተን በሰፊዉ የተመካከርንባቸዉ ሀሳቦች፦
በአስተዳደር ሁኔታዎች ፣ በአፈር ማዳበሪያ ጉዳይ ፣ አሸባሪዉ  ፀረ አማራ የብልፅግና ቡድን በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለዉ የጥፋት ተግባር እና እየነዛ ያለዉ የአገዉ አማራ ልዩነት ትርክት ምን ይመስላል በሚለዉ ሲሆን በቂ ዉይይት ተደርጎባቸዉ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጦባቸዋል።

ዉይይቱን የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር ፫ኛ ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ዋና ሰብሳቢ ፋኖ ሙሉነህ አዳሙ፣

👉የብርጌዷ ጽ/ቤት ሀላፊ ፋኖ ዮሐንስ ተረፈ፣
👉የብርጌዷ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር  ሀላፊ ፋኖ ገብረማርያም በየነ እና
👉የብርጌዷ ም/ ዘመቻ መሪ ሀምሳ አለቃ ማስተዋል ታደለ

👉ከብርጌዷ ሻለቃ ፪ አመራሮች ከእነ ፋኖ ዘመን ይሁን ጋር በመሆን ቀበሌዎችን ተከፋፍለው መርተዉታል።

አዲስ ትዉልድ፣
አዲስ አስተሳሰብ፣
አዲስ ተስፋ!

©ፋኖ ተሻገር አደመ ከ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ህ/ግንኙነት

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra