️ ንስር አማራ🦅
56K subscribers
13.5K photos
868 videos
50 files
4.39K links
የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
💚💛❤️

እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2
@NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅

ንስር አማራ🦅
#የግፉአን_ድምፅ
t.me/NISIREamhra
Download Telegram
🔥#አፋሕድ_ከአገዛዙ_የባሰ_ጠላት_ነው‼️
አፋሕድ ከአገዛዙ በትናትናው ዕለት ፋኖን ይወጋ ዘንድ 1 አይሱዙ
#ተተኳሽ ተበርክቶለታል‼️

ራሱን መከላከያ ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን ከደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ከወገል ጤና 1 አይሱዙ መኪና ተተኳሽና መሳሪያ በመጫን ታች ጉርቢት አፋፍ ድረስ ደጋው ክፍለ ድረስ አጅቦ በመውሰድ
#ጨጎማ ላይ በኮረኔል ፋንታው ሙሃቤ የሚመራው የዳውነት ፋኖ በይፋ ህዝቡ እያዬ አስረክቧል ፣የእስክንድር ሚሊሾቾም ተቀብለው ወስደዋል ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች አረጋግጠዋል።

ምንጮቻችን አያይዘውም አፋሕድ ከአገዛዙ ጋር አብሮ ይሰራል የሚለው በህዝቡ እንዳይረጋገጥ ለማድረግ የውሸት የተኩስ ልውውጥ በማድረግ መኪናው ወደ
#ጨጎማ_መገንጠያ_ዋድላ መስመር እንዲንቀሳቀስ ተደርጓ የኮረኔል ጦር መልሶ #ጨጎማ ላይ ተተኳሹን ተረክበዋል ግን ህዝባቸንንን መሸዎድ አይቻልም ህዝቡ አፋሕድ በፋኖ ስም የሚንቀሳቀስ የአብይ ሚሊሻ አንደሆነ በአይናቸው አይተው አረጋግጠዋል ሲሉ በአግራሞት አረጋግጠዋል።

በእስክንድር ነጋ የሚመራው አፋሕድ በጠላትነት ፈርጆን ሊያጠፋን በምድርና በሰማይ የጥይት አረር ከሚያዘንብብን አብይ አህመድ በላይ ጠላት ነው። ምክንያቱም አማራን ነፃ አወጣለሁ በማለት በፋኖነት ስም እየማለ ተግባሩ ግን ከጠላት ስንቅና ትጥቅ እየተቀበለ
#ድምፅ_አልባ ግድያ እየፈፀመብን ነው‼️

ይህ ተተኳሽ አፋሕድና አገዛዙ በጋራ ፋኖ ላይ ለሚከፍቱት ውጊያ የቀረበ ስለሆነ የጎንደርና ወሎ መገናኛ ቀጠናና አጎራባች ፋኖዎች ዝግጁ እንድትሆኑ ንስር አማራ ታስጠነቅቃለች‼️

የአፋሕድን ገመና በይበልጥ መሬት ላይ ካለው
#ከጨጎማ ህዝብ ማረጋገጥ ይቻላል‼️

#መረጃው_ሼርርርር_ይደረግ‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#አርበኛ_አበበ_ፈንታው‼️

አርበኛ አበበ ፈንታው ሁሌም ከፊቱ ላይ እልህ፣ ወኔ ፣ጀግንነት የሚነበብበት ፣ በትግል የጉዞ ሂደቱ በተሳሳተና በፀረ አማራ መንገድ ተገኝቶ የማያቅ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ 💪

አርበኛ አበበ ፈንታው የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሲሆን አንደበቱ ማራኪ፣ ቃላቶቹ ቁጥብ ፣ ንግግሩ የፕሮፓጋንዳ ጋጋታ የለለበት የመርህ ሰው ፣ የህዝብ ግንኙነት የውሀ ልክ ብንለው ያንስበታል። እነዚህ ውስን ቃሎች የመግለፅ አቅም ባይኖራቸውም አርበኛው በጥቂቱ ይህንን ይመስላል🙏

#በዚህ_ቀጥል_አርበኛው‼️
#እናከብርሀለን🙏

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ናሁሰናይ_ብርጌድ💪

      የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በዋና እሙሀይ የምትመራው ናሁሰናይ አንዳርጌ ብርጌድ ዛሬ ሚያዚያ 25/2017 ዓ/ም  ከአምባ ጊወርጊስ ወደ ገደብየ በኦራል ሲንቀሳቀስ የነበረ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሀይል ልዩ ቦታው ወርቀደቦ ላይ ከቀኑ 6 ሰአት ላይ በተወሰደ ኦፕሬሽን ሹፌሩ ተመትቶ የጠላት መኪና እግሩን ወደ ላይ ሰቅሎ በመገልበጡ አንድም ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ የነበሩት 27 በሙሉ ወደ ላይኛው ቤት ተሸኝተዋል ።

   ጠላት አስከሬን ለማንሳት ከገደብየ እና ከአምባ ጊወርጊስ ከተሞች በርካታ ሀይል ይዞ ቢመጣም የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ ወይም ከወደቁ በኃላ መፈራገጥ አጉል ጀርባ መምለጥ ሁኖበት ለሶስት  ሰዓት ከፍተኛ ምት ገጥሞት ምንም ሳይፈይድ ለድጋፍ የመጡ ሌሎች ሀይሎች ከፍተኛ ሰባዊ  እና ቁሳዊ  ኪሳራ አስተናግደው ተጨማሪ አንድ ኦራል እና ሁለት ፒካፕ መኪኖች ተመትተው ባሉበት ቁመው ቀርተዋል። አገዛዙ ዛሬም እንደ ትናንቱ የሽንፈት ጽዋን ተጎጭቶ በሀፍረት ተመልሷል።

      ናሁሰናይ አንዳርጌ ብርጌድ ከዳባት እስከ አምባወርጊስ ከተማ ከሌሎች የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አባላት ጋር በመሆን በተደጋጋሚ ኦፕሬሽን በመስራት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የምትታወቅ እና የምንኮራባት ጠንካራ ብርጌዳችን  ናት።

ለአዲስ ስኬት እንበቃለን፣ ምቹ ሀገር እንገነባለን::
              
                         አንድነት ኃይል ነው      
            
©አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥በዘመቻ አንድነት ወሎ ቤተ-አማራ ተከዜ ክፍለ ጦር ድል አስመዘገበ‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ተጠናክሮ በቀጠለው የህልውና ትግል በላስታ አሳምነው ኮር ስር በአርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ የሚመራው ተከዜ ክፍለ ጦር የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ላይ
ድል ተቀዳጀ።

ሚያዚያ 24/2017 ዓ.ም አመሻሽ  10:00 ሰዓት አካባቢ መነሻውን ግዳን ወረዳ ሙጃ ማርያም አድርጎ ዴንሳ ከተማ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን አፈሳ ለማካሄድ አስቦ የተንቀሳቀሰውን የጠላት ጦር በንቃት ሲከታተሉት የነበሩት ተከዜዎቹ ሻለቃ አንድና ልዩ ዘመቻ ፋኖዎች ዴንሳ ከተማ ዙሪያውን በማተት ለጠላት የእሳት ረመጥ ሆነው በጥይት አረር ሲቆሉት አምሽተው አይበገሬዎቹ ዴንሳ ከተማን ሳያስነኩ ጠላት አንድ ፖትሮል መኪና ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደነበረበት ሙጃ ማርያም ተመልሷል። በዚህ አውደ ውጊያም በጠላት ሰራዊት በኩል አንድ ከፍተኛ አመራር እንደተሰዋና በዚህም የተበሳጨው የአገዛዙ ጦር ሙጃ ማርያም ላይ የሚገኙ ወጣቶችን አፈሳ እያካሄደ ይገኛል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ በዘመቻ አንድነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ላስታ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን ገልጿል።


    ድላችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ)

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ከበባው_ተቀልብሶ_ጠላት_ተለብልቧል💪

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር የሰሜን ብርቅዬ ክ/ጦር በአርበኛ ደሳለኝ ፈንቴ የሚመራ በኪንፋዝ በገላ አጠላ ላይ ጠላት ሌሊቱን ተጉዞ ዙሪያውን አፈና ያደረገባቸው ቢሆንም ከበባውን በመስበር በትንሽ መሰዋትነት የጠላትን ሃይል ረፍርፈውት ከበባውን ሰብረው መውጣት ችለዋል።

የንስሮቹ አይን አይስትም!!ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮርሰሜን ብርቅየ ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ከበባውን ቀልብሶ ወደማጥቃት ተሸጋግሯል።

©የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ለሀቀኞች_የአማራ_ፋኖ_ስራ_አስፈፃሚዎች‼️

ብአዴን የሰፈር፣የመንደር ልጅ፣ ቤተሰባዊነት ፣ እንዲሁም በጥቅም ሰንሰለት በመተሳሰር አማራነትን በሆዱ ሸጦ ለበርካታ አመታት በዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ዘግናኝ ግፍ አስፈፅሞብናል‼️

አሁን ላይም በአማራ ፋኖ አደረጃጄቶች አቅም ሳይሆን ትውውቅ ፣ ጀግንነት ሳይሆን ቲፎዞ(አጨብጫቢ) ፣ ሀቀኝነት ሳይሆን ምላስ፣ ጭንቅላት ሳይሆን ሆድ ያላቸው ሰዎች ማይገባቸው ሰዎች ሀላፊነት ላይ ተቀምጠው ህዝቡን፣ ጦሩንና ትግላችንን ዋጋ እያስከፈሉትና እየጎዱት ይገኛሉ። ትውልዱ እየታገለ ያለው እኛም ሌት ከቀን የምንለፈልፈው
#የጠገበውንና_የአረጀውን_ብአዴን አውርደን #የራበውና_አዲስ_ብአዴን ለማንገስ አይደለም‼️

ታጋዩንና ህዝቡን ከሚያማርሩ ነገሮች ግምባር ቀደሙ ነገር የአመራሮች አፀያፊ ስራ መሆኑን አስረግጠን እንናገራለን‼️

ስለሆነም ለአማራነት በሀቅ ቆመው የአካልና የህይወት መስዎትነት የከፈሉ የፋኖ አባላትና አመራሮች እንዲሁም የህዝባችን ደም (መስዋትነት) የሚያራክሱ ከታችኛው መዋቅር እስከ ዕዝ ድረስ በሀላፊነት የተሰገሰጉ ግለሰቦችን በመመርመር የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን‼️

ክብር ለትግሉ ሰማዕታት‼️


#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

25/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ባህርዳር💪

መኮድና አየር ሀይል ላይ ጥቃት ተፈፅሟል!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር የጣናው መብረቅ ብርጌድ በዛሬው እለት ከሌሊቱ 9:30-11:ዐዐ ሰዓት ድረስ በተደጋጋሚ ከባድ መሳሪያ ጥቃት አድርሷል። በካምፑ ላይ ከፍተኛ ቁሳዊ ጉዳት ማድረስ ተችሏል፣ጠላት በብስጭት በመድፍ ዙሪያውን ተራራ ሲደበድብ አርፍዷል።

[የአማራ ፋኖ በጎጃም]

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#የጠላት_እንቅስቃሴ_ሸዋ‼️

አሁን ዙ~23 ከጉንደ መስቀል ወደ ሜታ መስመር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
️ ንስር አማራ🦅
Photo
🔥#የተሸነፈዉ_ቡድን_ተቋማትን_አወደመ‼️

በሰሜን አቸፈር ወረዳ ሳንክራ ት/ት ቤት ላይ የብልፅግና ወታደር ነን ባዮች ካምፕ አድርገዉ በነበሩበት ሰዓት ትምህርት ቤቶችን መገልገያ የነበሩ፦

✔️ወንበሮችን
✔️መፃሃፍቶችን
✔️መስታዉቶችን በማረጋገፍ
✔️አጥሮችን አፍርሶ

ከፈረጠጠ በኋላ ወደ በረሃ(ዳርፉር) ከገባ በኋላ አማራ በኢኮኖሚ እንዲደቅ የፈለገዉ አዉዳሚዉ የሸኔ ስብስብ በሳንክራ የፈፀመዉን ተግባር በዳርፉርም ፋኖ የህዝብ ልጅ አስከብሮት የነበረዉን የት/ት ቤትና የመብራቱን ተቋም አማራ ጠሉ ብል*ግና አዉድሞታል።

✔️ የመብራት ገመዶችን መበጣጠስ
✔️የቀበሌዉን መገልገያ ተቋሞች ማዉደም
✔️የግለሰብ ቤት ገብቶ ፍሪጅ መስበርና የእህል ሚዛኖችን ጭኖ መዉሰድ

እና ሌሎችንም በማዉደም ጫንቃ ላይ ተሰባስቦ ግለሰቦች ቤት እየገባ ዝርፊያዉን ቀጥሎበታል።

እራሱን የተመታዉ እባብ ህዝቡን በመዝረፍና ተቋሙን በማዉደም አፃፋዉን የመለሰ መስሎት ጥፉቱን ቀጥሎበታል።

   ፋኖ በህዝቡና በፈጣሪ ሃይል ያሸንፋል
ብልፅግናም ብቻዉን ቀርቶ ይሸነፋል !!

አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!

©የአፋጎ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ብርጌድ የህ/ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ አበበአምላኬ(ማንከቻዉ)

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
️ ንስር አማራ🦅
Photo
🔥#ከአማራ_ፋኖ_በጎጃም_የተሰጠ_መግለጫ‼️
       ሚያዝያ 26/2017 ዓ.ም

የአብይ አህመድ አሸባሪ ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ በአሁኑ ሰዓት ሁሉን አቀፍ ወንጀሎችን እየፈጸመ ይገኛል።

የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ያለው አብይ አህመድ የአማራ ገበሬ ጠላት ወደያዛቸው ከተሞች ገበያ ውሎ ለመመለስ በሄደበት በማገት እና ሚሊሻ ብለው ወደሚጠሩት አደረጃጀት በግድ በማስገባት እንዲሁም ወጣቱን የእለት ጉርሱን ለመሸፈን የቀን ስራ ከሚሰራበት ቦታ በማገት አድማ ብተና እና መከላከያ ወደሚሉት የግለሰቦች ሰራዊት በማስገባት አማራውን- በአማራው ማታኮስ በሚል ስር የሰደደ የጥላቻ አጀንዳ የተጠመደው ወራሪ ሐይል ሰለባ ሁነው የሚገኙ ወጣቶች አሉ።

አብይ አህመድ የአማራን ርዕስቱን መንጠቅ ፣ ትጥቁን ማስፈታት የሚለው አጀንዳ የመጀመሪያ የመተግበሪያ መቅድሙ በማድረግ የጀመረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በህዝባችን ላይ የስነልቦና ጫና ለመፍጠር በክልል እና ዞን ከተሞቻችን የሚኖሩ ማህበረሰባችንን በማስገደድ መሳሪያ ገዝተው ገቢ እንዲያደርጉ ተደርገዋል።

መንግስታዊ አሸባሪው የአብይ አህመድ ቡድን የአማራን ህዝብ የኢኮኖሚ ተመጽዋች እንዲሆን ፣ አርሶአደራችን በገንዘቡ የአፈር ማዳበሪያ ገዝቶ ምርት እንዳያመርት  የማዳበሪያ የሽያጭ ተመን ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ በመጨመር እንዲሁም ገንዘቡን ወስዶ መግደያ መሳሪያ ለመግዛት በእቅድ እየሰራ ይገኛል ።

አብይ አህመድ እና ጭፍሮቹ በአሁኑ ሰዓት አከርካሪያቸው የተመታ በመሆኑን በዓለም  አደባባይ በፍርድ ገመድ እየተጎተቱ  የሚቆሙበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን አየገለጽን:-

ማዳበሪያን በተመለከተ :-
ከአመት ዓመት አርሶ እና አለስልሶ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚመግበውን የአማራ ገበሬ በሐይል በመውረር ከላይ በድሮን እና በጀት ፤ ከምድር በታንክ እና በእግረኛ በየቤቱ እየገባ መጨፍጨፉ ሳያንስ የኢኮኖሚ አሻጥር ውስጥ በማስገባት ማዳበሪያ በመከልከል እና እጅግ በተጋነነ ዋጋ ለሽያጭ በማቅረብ በህዝባችን ላይ የኢኮኖሚ ጦርነት አውጇል ።

በዚህም :-
1.1/ የአፈር ማዳበሪያ ለሽያጭ ያቀረበበት ዋጋ የአማራን ገበሬ የሐገር የጀርባ አጥንት የካደ ብቻ ሳይሆን ህልውናውን ለማጥፋት በተጋነነ ዋጋ ለመሸጥ እየተዘጋጀ በመሆኑ መላው አርሶ አደራችን አሁን በቀረበበት ዋጋ ማለትም በ 8,000 ( ስምንት ሺህ ) ብር እንዳትገዙ እናሳስባለን ።

1.2/ የህልውና አደጋ ገጥሞት ራሱን ከወራሪ ጠላት እየተከላከለ በሚገኘው የአማራ ገበሬ ላይ የገንዘብ ትርፍ ለማግኘት ከወንበዴው ስርዓት ተመሳጥራችሁ በህገ ወጥ መንገድ የአፈር ማዳበሪያ ከዝናችሁ በተጋነነ ዋጋ ለመሸጥ የተዘጋጃችሁ ነጋዴዎች በትክክለኛው ተመን የማትሸጡ ከሆነ ድርጅቶችን የአማራ ፋኖ በጎጃም ማዳበሪያውን ለማህበረሰቡ እንደሚያከፋፍል እና እናንተም ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን ።

1.3/ ለመላው የጎጃም ማህበረሰባችን :- በህገወጥ መንገድ ማዳበሪያ ከዝነው የሚገኙ ነጋዴዎችን በአካባቢያችሁ ለሚንቀሳቀሱ ብርጌዶች እና ሻለቆች እንድትጠቁሙ እንጠይቃለን ።

2/ከአሁን በፊት የውትድርና ሙያ ስልጠና ወስዳችሁ ማለትም በእግረኛ ፣ በኮማንዶ፣ በሜካናይዝድ እና በሌሎች ወታደራዊ ዘርፎች የሰለጠናችሁ እና በፋኖ አደረጃጀት ያልተካተታችሁ ወገኖቻችን በሙሉ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የድርጅታችን ብርጌድ /ክ/ጦር በመሄድ እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን። በዚያውም በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና መከራ እያዩ እንዳላዩ መሆን የጨፍጫፊውን ስርዓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።

3/የአብይ አህመድ የግል ሰራዊት በመሆን በሚዎረዎርላችሁ ሽርፍራፊ ገንዘብ ቤተሰባችሁን እና ህዝባችንን እየገደላችሁ ያላችሁ የሚሊሻ አባላት በሙሉ ወደኛ እንድትመጡ እና ቤተሰባችሁን በሰላም እንድታስተዳድሩ የምረት ጥሪ እናደርጋለን።

4/ ከስራ ገበታችሁ በአብይ ቅልብተኛ ወታደሮች ታግታችሁ በግዳጅ የአድማ ብተና አባላት ፣ የመከላከያ አባላት የተደረጋችሁ ወጣቶች በሙሉ የያዛችሁትን የጦር መሳሪያ በመያዝ ወደ ድርጅታችን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን።

5/ ከሌላ ክልል ተገዳችሁ ወደ መከላከያ ሰራዊት/የአብይ ጦር /የገባችሁ ግለሰቦች ድርጅታችን ውስጥ ተቀላቅላችሁ ከመታገል ባለፈ ወደ ቤተሰቦቻችሁ ለመሄድ ለምትፈልጉ ድርጅታችን ባወጣው የመሳሪያ የክፍያ ተመን መሰረት እየተከፈላችሁ የምትሄዱ መሆኑን እንገልጻለን።

6/ በምናደርገው የህልውና ተጋድሎ ውስጥ የግል ጦር መሳሪያ ታጣቂዎች ታላቅ ተጋድሎ እያደረጋችሁ የምትገኙ መሆኑ ይታዎቃል።ነገር ግን  በድርጅታችን ባለው የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ ተጠርንፎ ለመታገል ሁኔታዎች ያልፈቀዱላችሁ የግል ታጣቂዎች ለድርጅታችን በውሰት እንድታስረክቡ ስንል እናሳስባለን።
በውሰት የሰጣችሁበትን  መታዎቂያ መጣል ወይም ለሶስተኛ ወገን አሳልፍ መስጠት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

7/ በህዝባችን ላይ እየተደረገ ያለውን   ይፋዊ የኢኮኖሚ ጦርነት ለመከላከል ማንኛውም የእህል ነጋዴ ላልተዎሰነ ጊዜ ከቦታ ቦታ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ
©የአማራ ፋኖ በጎጃም

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#መረጃ‼️
አሁን ከቀኑ 10:10  ከተለያዩ ቦታ የመጡ እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች በፖሊስ ታጅበው ወደ ማንጎ መናፈሻ ህዳር 11 የህዝብ ላይበራሪ አካባቢ ገብተዋል።

የንስር አማራ ምንጫችን አያይዘው አንዳንዶችን ለመስማት ሞክሬ ነበር አብዛኞቹ ዘመቻ ምናምን ሲሉ ነበር።አንዱ እንዲያውም በቅርቡ ይኖራል ሲል ሰምቸዋለሁ።

የደህንነት አባሎች ፋኖን ለመሰለል የሚላኩ ሊሆኑ ስለሚችሉ አስቸኳይ ለፋኖዎች አድርሱልኝ 3 የታጠቀ የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ አጅበዋቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል መረጃው ይሰራጭ‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ከህዝባችን_ጋር‼️  #ኑዉ_ዝብሊ‼️

"አዊና አሚኺሪ ንካማ እምፕልካ እምልካ ቻኻ ዜርካ ኪፂስታያሱ ኽምቢስ ጌዉስኝፅኝስ ኳያንኩሳ እንኳኽና። እንስ ዙርሜ አይኝስ እንቶጂ ዴሬትየን። እምፕላ ፄፃፋዳ ላኝሾ ሴንቴክኝስ ካላዉ ዝኩኒ ይንታማ ሞኬርስ።"

|"አገዉ አማራ እያሉ አንዳንድ ወፍ ዘራሾች ባልተቀጣ አፋቸዉ ለልዩነት እንደሚጮኹ ሰምተናል። ለእነዚህ መልስ ለመስጠት እናንተ አትድከሙ። አንድ የፀጉር ዘለላ ለሁለት መሰንጠቅ የሚሆንለት ካለ መጦ ይሞክረን።"|

ዛሬ ከህዝባችን ጋር በአንድነት ስንመክር አንድ አባት ከተናገሩት የተወሰደ!

ዛሬ በቀን 26/08/2017 ዓ/ም ከህዝባችን ጋር ትኩረት ሰጥተን በሰፊዉ የተመካከርንባቸዉ ሀሳቦች፦
በአስተዳደር ሁኔታዎች ፣ በአፈር ማዳበሪያ ጉዳይ ፣ አሸባሪዉ  ፀረ አማራ የብልፅግና ቡድን በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለዉ የጥፋት ተግባር እና እየነዛ ያለዉ የአገዉ አማራ ልዩነት ትርክት ምን ይመስላል በሚለዉ ሲሆን በቂ ዉይይት ተደርጎባቸዉ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጦባቸዋል።

ዉይይቱን የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር ፫ኛ ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ዋና ሰብሳቢ ፋኖ ሙሉነህ አዳሙ፣

👉የብርጌዷ ጽ/ቤት ሀላፊ ፋኖ ዮሐንስ ተረፈ፣
👉የብርጌዷ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር  ሀላፊ ፋኖ ገብረማርያም በየነ እና
👉የብርጌዷ ም/ ዘመቻ መሪ ሀምሳ አለቃ ማስተዋል ታደለ

👉ከብርጌዷ ሻለቃ ፪ አመራሮች ከእነ ፋኖ ዘመን ይሁን ጋር በመሆን ቀበሌዎችን ተከፋፍለው መርተዉታል።

አዲስ ትዉልድ፣
አዲስ አስተሳሰብ፣
አዲስ ተስፋ!

©ፋኖ ተሻገር አደመ ከ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ህ/ግንኙነት

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ዘመቻ_አንድነት_ጎንደር_ግንባር‼️
    
በዘመቻ አንድነት ጎንደር ግንባር ከ100 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ተደምስሷል።

🔸የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጎቤ ክ/ጦር በሻለቃ እሸቴ አሸብር የሚመራው የደጀን ብርጌድ፣ በሻለቃ ብርሃኑ ሙላውና ሻለቃ ደሳለኝ ተቀባ የሚመሩ ሻለቆች በጥምረት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ቦታው ሙሴባምብ፣ደበዝ እና ኩርቢ በተባሉ ቦታዎች በልዩ ወታደራዊ ስልት ጠላትን በመሳበሰና ቆራርጦ በመክበብ ጠላትን ያፈራረሰ ወታደራዊ
ድል ተገኝቷል።
በሶስት ቦታ በተደረገ አውደ ውጊያ ከ48 በላይ ሙት፣22 ቁስለኛ እንዲሁም 25 እጅ የሰጠ ምርኮኛ ሁኗል።
01 ብሬን፣02 አርባ ጎራሽ ክላሽ፣55 ክላሽና በርካታ ተተኳሽ ጥይትና የእጅ ቦምብ ከጠላት ተማርኳል።በዚህም የታች አርማጭሆ ወረዳ የፀጥታ መዋቅር ሙሉ በሙሉ ፈርሷል።

🔸 በጠገዴ ወረዳ የጎቤ ክ/ጦር ዋግሹም ብርጌድ በቀጠናው የነበረውን የጠላት ቅጥረኛ ሀይል በማጥቃት ከ24 ሙት፣ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ቁስለኛ ሲሆን 45 እጅ የሰጠ ምርኮኛ ሁኗል።አካባቢውን ከግፈኛው አገዛዝ በማፅዳት ነፃ ማውጣትም ተችሏል።

🔸 የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የራስ አሞራው (3ኛ) ኮር የአያሌው ብሩ ክ/ጦር በሰሜናዊ ጎንደር ቀጠና ወቅን አካባቢ በደፈጣ በወሰደው ኦፕሬሽን ሁለት የጠላት ወታደራዊ ተሽከርካሪ ከጫነው ወራሪ ሀይል ጋር ሙሉ በሙሉ ተ*ደ*ም*ስ*ሷ*ል።

    የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በሁሉም የጎንደር ማዕዘናት አካሎ ማጥቃቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

          ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
   © የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር (አፋአጎ)
              

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

27/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#መረጃ_ከግዮን_ሰማይ_ስር‼️
በግዮን ብርጌድ ከ20 በላይ ጠላት ተደመሰሰ‼️

በዛሬው ዕለት ሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ ከተማ ድንጋይ ገበጣ ከተባለ ቦታ ላይ መሽጎ የነበረውን ጠላት የጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ግዮን ብርጌድ መብረቁ ሻለቃ ተጠግታ በማደር ጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመሰንዘር ከ20 በላይ የጠላትን ሀይል መደምሰስ ችላለች።

ይህ አሸባሪ ሀይል ቅዳሜ  ከተለያዩ የገጠር ክፍሎች ለገበያ የሚሄዱ ባለትዳር ሴቶችን እየመረጠ በማስቀረትና በመድፈር  አስነዋሪ ስራ ሲሰራ ሰንብቷል፤ በዚህ ነውረኛ ስራው የተናደዱት አይበገሬዎቹ የግዮን ልጆች መብረቁ ሻለቃ ወደ ጠላት ምሽግ ተጠግታ በማደር ጠላትን መጫ አሳጥተው እናቴ ጥሪኝ ሲያሰኙት አርፍደዋል።

ጠላት የወደቀውን አስከሬን በሁለት ፓትሮል ጭኖ የወሰደ ሲሆን በዚህ ሽንፈትን የተከናነበው ይህ አሸባሪ ሀይል የአፈር ማዳበሪያ ለማምጣት ከገጠር ወደ  ከተማ ሲጓዙ የነበሩ አባ የስጋት ተሰማ እድሜ 78 ፣ ምህረት በለጠ እድሜ 76 እና አታላይ ጥላሁን እድሜ 40 የአሊቦ ቀበሌ ተወላጅ 3 ንጹሀንን ገድሏል።

ድል ለተገፋው ለአማራ ህዝብ ድል ፋኖ!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ

©የቻለ አድማሱ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለጦር የግዮን ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት


#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

27/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#ብልፅግና_ያጠመደው_ፈንጅ_ራሱን_ላይ_ፈነዳ

ዛሬ 27/8/2017
#የቲሊሊ ማህበረተሰብ እና መምህራንን ሰብስቦ የውሸት ናዳውን ሲነዛ ፋኖ ያወደመው ተቋም እያለ አራሱ ያወደመውን ቪዲዮ ሲያሳይ ቆይቶ ወደ ህዝብ አስተያይት ሲወርድ ከወርቁ የቲሊሊ ህዝብ ፈንጅ የሆነ ምላሸ ተከትሎታል ። ከእነዚህ ምላሾች ውስጥ ባጭሩ:

1ኛ.ፋኖ የወደመው ተቋም ምትሉን ፋኖ ድሮን፣መድፍ፣ ሞርታር ወይስ Rpg አለው ይሄን ሁሉ ተቋም አወደመ ምትሉን በእናንተ እውር ድንብርነት በሚወረወር ከባድ መሳሪያ እንጅ፡

2ኛ ፋኖ ቀረፅ ይቀርፃል ትላላችሁ፣ እናንተስ ምትቀርፁ ወጉን መንግስት የሚል ስም ይዛችሁ በቀል ይዟችሁ ነው ወይስ ደሞዝ ቸግሯችሁ የመንግሥት ካዝና በተከታታይ ጦርነት ወድሞ፡

3ኛ ፋኖዎችን መልሷቸው ምትሉትን እንዲህ እንደምታስቡት ቀላል ሀይል ከሆነ እንደ ተማሪዎቹ ስም ዝርዝራቸውን ስጡንና ቀስቅሰን እናምጣቸዋ፡

4ኛ.በደሞዝ አታንገራግሩን ከዚህ በኋላ ማንንም ሁነን መኖር እንችላለን።

5ኛ.ፅንፈኛው አብይና ብልፅግና እንጅ ፋኖዎቹ ተገፍተው የወጡ የህዝብ ልጆች ናቸው ፋኖ ብላችሁ ጥሩ።በማለት በግድ የሰበሰቧቸው ሆድ አደር ካድሬና ዙፋን አስጠባቂውን ደንቆሮ ሰራዊት አዋርደውት ወጠዋል ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዎል‼️

#ክብር_ለቲሊሊ_ህዝብ🙏

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

27/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
ሀዲስ አለማየሁ 7ኛ ክፍለጦር
ከ2:00 ስዓት እሰከ 12:00 ስዓት የተደረገ መደበኛ ውጊያ

የአማራ ፋኖበጎጃም የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ከፍለ ጦር ሁሉም ብርጌዶች ውጊያ ውለዋል።ጠላት በቀጠናው ከፍተኛ ሀይል ከከባድ መሳሪያ ጋር ያሰማራ ሲሆን ነበልባሉ ፋኖ መውጫ መግቢያ ሲያሳጠው ውሏል።
-አዋበል መብረቁ ብርጌድ ሉማሜ ላይ ተዋግቷል
-ተድላ ጓሉ ብርጌድ የጎራ እና የምስጥና ላይ ተዋግቷል
-የቦቅላ አባይ ብርጌድ :ጥቁር አንበሳ እና ተድላ ጓሉ ብርጌድ አምበር ላይ የተዋጉ ሲሆን የባሶ ሊበኑ አብራጂት ብርጌድ ኮርክ እና የላምገጂ  ላይ ጠላትን ቁም ስቅል ሲያሳየው ውሏል። በዘፈቀደ የሚተኩሰው የአብይ ሰራዊት ከ22 በላይ መድፍ የተኮሰው ሲሆን የማህበረሰቡን በግ:ፈረስ እና የቀንድ ከብቶችን የገደለ ሲሆን የንፁሃንን ቤት አፍርሷል። የጨነቀው የጠላት ሀይል ቢኤም: ዙሪያ 23 :መድፍ እና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን ከየትኖራ በማንቀሳቀስ ሲጠቀም ቢውልም ፋኖ ለቁጥር የሚያዳግት አስከሬን እና ቁስለኛ አሸክሞታል።
በነበረው ውጊያ  5 የጠላት ቃኝ እና መሐንዲሶች በዘሪሁን 13 ሙሉ ለሙሉ ተደምስሰዋል።
ይኸን ውጊያ 100 አለቃ አበበ ሰውመሆን የአፋጎ ዘመቻ መምሪያና 100 አለቃ ገረመው አጋዢ (አበጀ በለው) የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር ዋና ጦር አዛዥ በበላይነት መርተውታል።
ፋኖ መ/ር እንደሰው ታምሩ የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር ህ/ግንኙነት ሀላፊ


#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

28/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥"#ሁሉም_በዝግ_ይጠናቀቃል"‼️

"የአማራ ፋኖ አንድ ድርጅት የማዋለድ ታሪካዊ ውይይት ጠላት ብልፅግና እና አህፋድ አንዴ ሱዳን ፣ ትግራይ ፣ ኤርትራ ፣ ሞላሌ ፣ ሰላሌ ቢሉ ቢቅበዘበዙ መረጃው ድፍን ድርግም ዝም ጭጭ ያለ ነገር ሁኖባቸው ተቅበዝብዘዋል።

የእኛ ሰፈር ጉዶች ደግሞ ዘመነ ፣ ተፈራ ፣ ዋርካው ፣ ሃብቴ ፣ ዝናቡ ፣ ሳሚ ፣ ደሳለኝ ፣ ድርሳን ሚስተር X ሚስተር Y ብለው የወሬ ፊኛቸው አብጦ ሊፈነዳ ነው።

አትልፉ ፈፅሞ ፈፅሞ አንድም የተቋም አመራር ፣ የክ/ጦር አመራር የሚዲያ ግሪሳ ውይይቱ የት ቦታ እንዳለ የተሰብሳቢ ብዛት የተነሱ ሀሳቦች የሚያውቁት መረጃ የለም። ራሳችሁን ተገማች ከማድረግ ተቆጠቡ።

ውይይቱን ከተሰብሳቢዎች ውጭ አጃቢዎቻቸው እንኳን መስማት ፈፅሞ አይችሉም።

የአንድነት ብስራቱን በጉጉት እየጠበቅን ነው!
በዬ እምነታችን ፍፃሜው እንዲያምር እንፀልይ‼️"

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

28/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥ወጣት እያፈሰ ወደ ጦርነት የሚማግደው የብልፅግና አገዛዝ አሁን ደንሞ የባንክ ጥበቃዎችን በግዴታ ለወታደርነት ስጡኝ እያለ ባንኮችን እየጠየቀ ነው‼️

ጉዳዩ- ከተቋማችሁ ጥበቃዎች አንድ ሰው መልምላችሁ እንድትልኩልን ስለማሳወቅ፣

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው የመ/ከ/አስ/ሚዕ/ቤት ከአለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ለ6 ወር ያህል ተጠርንፎ የሚቆይ ለተቋሙ አጋዥ የሚሆን የጥበቃ ባለሙያ መልምላችሁ በዛሬው እለት እንድታሳውቅን ስንል ሀገራዊ ግድታችሁን እንድትወጡ እያልነ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት መልምላችሁ የማታሳውቁን ከሆነ በእኛ በኩል አስገድደን የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን‼️

©የመራዊ ከተማ አስተዳድር ሚሊሻ ፅ/ቤት

ይላል ፋኖማ እውነትም ከብዶታል ቀጣይ የቤት ሰራተኛቹህን ስጡኝ ይላል።

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

28/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥#በታሪክ_ይመዝገብ
ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች::

አበበ ሙላቱ (አበበ ፂሞ) የተባለው ግለሰብ ESAN ቴሌቪዥን ላይ ከደረጀ ሐብተወልድ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ከአፋህድ ውጭ ያሉትን የአማራ ፋኖዎች እንደመስሳቸዋለን። በተለይ የፖለቲካ የስበት ማዕከል ከሆነው ሸዋ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአማራ ፋኖ በሸዋ ፋኖዎችን እንደመስሳቸዋለን ብሏል።
ልክ እናስገባቸዋለን ሲል ዝቷል።

ይህን ለማድረግ ደግሞ ስራ ጀምረናል እያለ እየዛተ ነው።

በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአፋሕድ ቡድን ከአገዛዙ ስንቅና ትጥቅ እየተበረከተለት፣ ከምድር ሀይል እስከ አየር ሀይል ሽፋን እየተሰጠው አማራን ብለው በወጡ የአማራ ፋኖዎች ላይ ጥቃት መክፈቱ ቀጥሏል፣ አድል ቀንቷቸው ቢያሸንፉ ግን
#በመጨረሻ ጋላቢዎች ብቻ ሲቀሩ ተጋላቢ ፈረሶች (ታችኛው ተዋጊ) ይበላሉ( ይጠፋሉ)‼️

አፋሕድ ላይ ያላችሁ ወጣቶች ንቁ‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

28/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra
🔥ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር አፄ ፋሲል ክፍለጦር የተሰጠ ወቅታዊ ማሳሰቢያ‼️

በደቡባዊ ጎንደር ከወረታ ከተማ፤ እስከ ጉማራና፤ አለም በር ድረስ በአፄ  ፋሲል ክፍለጦር አመራር ስም ማለትም ሻለቃ ዝናው ነኝ እያሉ ለባለሃብቶቹ  እየደወሉ ገንዝብ የሚቀበሉና፤ የሚጠይቁ እንዳሉ ደርሰንበታል።እነዚህ የተደራጁ ሌቦች ሕዝባችን እያሰቃዩ እና ገንዘብ የሚቀበሉ ዘራፊዎች ናቸው ።

ፀረ ሕዝብ የሆነው አገዛዙ እንዳሰማራቸው በሕዝባችን በደረሰን ጥቆማ መሰረት የተወሰኑትን በቁጥጥር ስር ማዋልvችለናል ።አፄ ፋሲል ክፍለጦር እስከ ዘረፉት ንብረታቸው በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።

መንግስት አደራጅቷቸው የሚዘርፉ ሌቦችን ስታዩ ለአፄ ፋሲል ክፍለጦር አመራርና አባል ጥቆማ  በመስጠት እንዳትተባበሩን እንጠይቃለን ።

©አርበኛ ዝናው አያናው የአፋአጎ ሜካናይዝድ አሀድ መምሪያ አላፊ እና የአፄ ፋሲል ክፍለጦር ዋና አዛዥ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

28/08/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra