NGCS PARENTS GRADE 9-12
2.78K subscribers
948 photos
39 videos
334 files
70 links
Download Telegram
Forwarded from nardos Kebede
Photo from Nardos
Forwarded from nardos Kebede
Photo from Nardos
❤1
Forwarded from nardos Kebede
Photo from Nardos
Forwarded from Kido
❤2
Forwarded from Kido
❤29🥰1🤓1
Forwarded from NGCS PARENTS GRADE 1-8
ቀን ሐሙስ መስከረም 21/2019 ዓ.ም

በዘንድሮ 2019 ዓ.ም የ 8ኛ እና 6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና (ሚኒስትሪ) ተፈታኝ ልጅ ላላችሁ ወላጆች እንዲሁም አሳዳጊዎች በሙሉ ልጆቻችሁ ወደ ሚኒስትሪ መፈተኛ ጣቢያቸው የሚገቡበት አድሚሽን ካርድ ላይ የሚቀመጠውን ፎቶግራፍ ማስነሻና አድሚሽን ካርድ ዝግጅት እና ህትመት ወጪ ላይ የሚውል በ ተፈታኝ ተማሪዎች ቁጥር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ሰኞ መስከረም 25/2019 ዓ.ም በየክፍላቸው እየሄድን ስለምንሰበስብ ከላይ የገለፅነውን የገንዘብ መጠን (ሁለት መቶ ብር) በልጆቻችሁ በኩል እንድትልኩልን እያሳሰብን ከዚሁ ጎን ለጎን እስከ አሁን ለልጆቻችሁ የትምህርት ቤቱን መታወቂያ ካርድ ያላወጣችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች ይህንን በቶሎ ከወዲሁ እንድታስፈፅሙ እናሳስባለን። ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ በፈተና ቀናቶች የትምህርት ቤት መታወቂያ እና የፈተና ጣቢያ መግቢያ ካርድ ይዘው መንቀሳቀስ ስላለባቸው ነው።

ትምህርት ቤቱ
❤6🔥1
Forwarded from NGCS PARENTS GRADE 1-8
ቀን:-እሁድ መስከረም 24/2019 ዓ.ም

የዘንድሮን 2019 ዓ.ም 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና(ሚኒስትሪ) ተፈታኝ ልጅ ላላችሁ ወላጆች እንዲሁም አሳዳጊዎች በሙሉ ነገ ሰኞ መስከረም 25/2019 ዓ.ም በአድሚሽን ካርዳቸው ላይ የሚውል ፎቶግራፍ ማስነሻና ማሳተሚያ የሚሆን 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በየክፍላቸው አየሄድን ስለምንሰበስብ በልጆቻችሁ በኩል እንድትልኩልን በአክብሮት እናሳስባለን ። የትምህርት ቤቱን መታወቂያ ካርድ እስከአሁን ያላወጣችሁላቸው ከሆነ ከቢሮ እንድታወጡ እናሳስባለን ።

ትምህርት ቤቱ
❤6
28/9/2019

ለ 6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ወላጆች /አሳዳጊዎች ፡፡
ቅዳሜ መስከረም 30/1/2019 ከጠዋቱ 2 : 00 እስከ 3 : 00 ሰዓት በተማሪዎች ትምህርት ዙሪያ እና የተማሪዎች አገር አቀፍ ክልላዊ ፈተና የሚደረግ ወይይት እንዲገኙ እያሳሰብን ሁሉም ወላጅ በስብሰባው ላይ ተገኝቶ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደር ጥሪ እናደርጋለን በስብሰባው ካልተገኙ በተገኙት ተሰብሳቢ ውሳኔ የሚጠቃለል መሆኑ እናሳስባለን ፡፡

ት/ቤቱ
❤2
ቀን:-ዓርብ መስከረም 29/2019ዓ.ም

ለዘንድሮ 2019 ዓ.ም የ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና (ማትሪክ) ተፈታኝ ልጅ ላላችሁ ወላጆች እንዲሁም አሳዳጊዎች በሙሉ ። የግል ተማሪዎች እንደሁልጊዜው ሁሉ የመፈተኛ ማኑዋሉ ባስቀመጠው መሠረት ለመመዝገቢያ 150.00(አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ለፈተናዎቹ በየትምህርት ዓይነቱ ( የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሚወስዷቸው ስድስት የትምህርት ዓይነቶች ስለሆኑ) ለአንድ ትምህርት 100.00 (አንድ መቶ ብር) በድምሩ 750.00(ሰባት መቶ ሃምሳ ብር የሚከፈል መሆኑን እየገለፅን እያንዳንዱ አስፈታኝ የግል ትምህርት ቤት ከተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰበስበውን ብር ለአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በአካውንታቸው ገቢ በማድረግ ተፈታኝ ተማሪዎቹን በኦንላይን ማስመዝገብ ስላለበት ነገሮችን ከወዲሁ ዝግጁ አድርገን ለመጠበቅ ይረዳን ዘንድ ከመጪው ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ጀምሮ 750.00 ብሩን ስለምንሰበስብ በልጆቻችሁ በኩል እንድትልኩልን ስንል በተጨማሪም እስከአሁን የፋይዳ መታወቂያ ካርድ ኮፒውን
የ 8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ውጤት ሰርቲፊኬት
እንዲሁም ከቀድሞ ትምህርት ቤታችሁ ትራንስክሪፕት ያላመጣችሁ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንድታመጡ እናሳስባለን ።

ትምህርት ቤቱ
❤11
ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም
ለዘንድሮ 2019ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና (ማትሪክ) ለምትወስዱ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

* በትራንስሪፕታችሁ እና በጂፒኤ ሰነዶቻችሁ ላይ የሚያርፉ በቅርብ ጊዜ በትምህርት ቤቱ ዩኒፎርም የተነሳችኋቸው ሁለት ባለቀለም ጉርድ ፎቶግራፎች ከነገ ጀምሮ ለቢሮ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

* የፋይዳ መታወቂያ ካርዳችሁን ፎቶ ኮፒ እስከ አሁን ያላመጣችሁ በቶሎ እንድታመጡ

* ለአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተሰብስቦ በጥቅል ገቢ የሚደረገውን የመመዝገቢያ(150.00ብር) እና ለ 6 ትምህርቶች መፈተኛ 6*100 (600 ብር) በድምሩ 750.00 ብር ከነገ ጀምሮ ስለምንሰበስብ ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ።

* ትራንስክሪፕት ከቀድሞ ትምህርት ቤቶቻችሁ እንዲሁም የ ሚኒስትሪ ውጤት ሰርቲፊኬት እስከ አሁን ያላመጣችሁ እንድታመጡ እናሳስባለን።


ትምህርት ቤቱ
❤7
ልደታ ማርያም የልጃገረዶች ት/ቤት
9/2/2019
ውድ የ9ኛ–12ኛ ክፍል ተማሪዎች፣
ነገ በሚካሄደው የፎቶ ፕሮግራም ላይ ሁሉም ተማሪዎች መገኘት እንዳለባቸው እናሳውቃለን። ስለዚህ ሁሉም ተማሪዎች በትክክለኛው የትምህርት ቤት ዩኒፎርም በንጹህና በሥርዓት ተዘጋጅታችሁ መምጣት አለባችሁ።

የሁሉም ተማሪዎች መገኘት ግዴታ ነው።
👍13👎8❤1
18/2/2019

ውድ ወላጆችና አሳዳጊዎች፣
ከ ልደታ ማርያም ካቶሊክ ትምህርት ቤት ሰላምታ ይድረሳችሁ!
የ4ኛ፣ 5ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆችና አሳዳጊዎች በልዩ የወላጅነት ሴሚናር ላይ እንድትሳተፉ በደስታ እንጋብዛችኋለን። የዚህ ሴሚናር ዓላማ በወላጆችና በልጆቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ነው።
ሴሚናሩ ልጆቻችንን በተሻለ ሁኔታ መረዳት፣ ባህሪያቸውን በአግባቡ መምራት፣ ስሜታዊና ትምህርታዊ እድገታቸውን መደገፍ እንዲሁም ኃላፊነት የሚሰማቸውና በራሳቸው የሚተማመኑ ግለሰቦች ሆነው እንዲያድጉ ስለሚያስችሉ ጉዳዮች ያተኩራል። በተጨማሪም ውጤታማ የወላጅነት አስተዳደግ ዘዴዎችን እና የልጆቻችንን ስኬት ለመደገፍ ከትምህርት ቤቱ ጋር በትብብር መሥራት ስለሚቻልባቸው መንገዶች ጠቃሚ ግንዛቤ ይሰጣል።
• ቀን፦ 21/2/2019
• ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
• ተሳታፊዎች፦ የ4ኛ፣ 5ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆችና አሳዳጊዎች
• ቦታ፦ ልደታ ማርያም ካቶሊክ ትምህርት ቤት የስብሰባ አዳራሽ
ለሁልጊዜው ትብብራችሁና ድጋፋችሁ ከልብ እናመሰግናለን። በሴሚናሩ ላይ በመገኘት ለልጆቻችን የተሻለ እድገትና ስኬት በጋራ እንድንሠራ እንጋብዛችኋለን።
ከአክብሮት ጋር፣
የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተረስ
ሲስተር ሜሪ ሺና (Sr. M. Sheena)
❤2