NB tutorial service
2.83K subscribers
46 photos
34 files
56 links
Welcome🤚 Get access to educational books, exam questions, study tips, and learning resources all in one place. Our channel is dedicated to helping students and young learners improve their knowledge, prepare for exams, and succeed in their studies.
Download Telegram
Channel photo removed
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ይሰጣል። - ትምህርት ሚኒስቴር

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልፀዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የመልቀቂያ ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ ሲሰጥ እንደነበር፣ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም መድረክ ላይ የተገኙት ሚኒስትሩ አስታወሰዋል፡፡

ዘንድሮ ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የተለያዩ ግብዓቶች ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን፤ በፈተና ጣቢያዎች በቂ የኢንተርኔት አቅርቦት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ይሠራል ብለዋል።

ክልሎች በቂ ኮምፒዩተር፣ ኔትዎርክ እና አማራጭ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር በትኩረት እንዲዘጋጁ ያሳሰቡት ሚኒስትሩ፤ ለተማሪዎች በቂ ስልጠና መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በ2017 ዓ.ም ለመልቀቂያ ፈተናው ከተቀመጡ 585,882 ተማሪዎች መካከል 23% ያህሉ ፈተናውን በኦንላይን የወሰዱ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

@nbtutorialservice
👍1817👌4
🗓 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል !

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ መጋቢት 15 ቀን 2018 ከቀኑ 11 ሰዓት 30 እንደሚጠናቀቅ፣ ያልተመዘገበ እንደማይፈተን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስቧል።

በጀት ከተመደበ፣ ፈተና አስፈጻሚዎች ከተሰማሩ በኋላ አዲስ ተመዝጋቢ ቢቀርብ ለማስተናገድ እንደሚቸገሩ አስረድተዋል። ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። 

ተመዝጋቢዎች ከ9 እስከ 11 የተማሩበት ውጤት ሊኖራቸው እና አሁን ላይ 12ኛ ክፍል እየተማሩ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል። ድጋሚ ለሚፈተኑ ደግሞ 750 ብር ክፍያ በመፈጸም ከዚህ በፊት የተፈተኑበትን አድሚሽን ካርድ ማስገባት፣ https://register.eaes.et ላይ መመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ይህም 150 ብሩ ለምዝገባ፣ ለእያንዳንዱ ስድስት ፈተና 100 ብር ተደርጎ ተሰልቶ፣ ተፈታኞች " ቢያንስ ኮስት ሸር " እንዲያደርጉ እና  " ከፍዬ ነው " በሚል ለፈተናው ትኩረት እንዲሰጡ ታስቦ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል።

ተፈታኞች በመረጡበት የፈተና ማእከል መፈተን እንደሚችሉ ያስረዱት እሸቱ (ዶ/ር)፣ " ለምሳሌ አምና አርባምንጭ የተፈተነ ተማሪ፣ ዘንድሮ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ከሆነ ለመፈተን አርባምንጭ መሄድ ሳይጠበቅበት አዲስ አበባ ካሉ ትምህርት ቤት አንዱን መርጦ የግል ተፈታኝ ሆኖ ይፈተናል " ብለዋል።

የዜናው ምንጭ: ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@nbtutorialservice
@nbtutorialservice
20👍3
ዛሬ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸውን የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎች በድጋሚ አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1,ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች በተፈጥሮ ሳይንስ
እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ፊዝክስ ሲሆኑ

በማህበራዊ ሳይንስ
እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

2,ፈተናው በየትምህርት ዓይነቱ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል። የዝግጅት አግባቡም 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት (Common Contents) ላይ ያተኩራል። ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን ይሆናል።

ዛሬ አዲስ የተነገረው ነገር የ Economics ትምህርት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን መሆኑን ነው፡፡

ምንጭ፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@nbtutorialservice
@nbtutorialservice
8
የ 2018 ዓ.ም ኢንትራንስ ፈተና 100% online በ 6 ዙር ለመስጠት ታቅዷል፡፡ ፈተናው ከመሰጠቱ በፊት ቢያንስ (በግምት)2 ወር ተማሪዎች የሚለማመዱት Mock Exam እደሚኖር አሳውቀዋል፡፡

ምንጭ: ትምህርት ሚኒስቴር እና የፈተናዎች አገልግሎት
14
የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በሌላ በኩል፦

- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም

- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም

- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም

- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም

@NB_tutorialservice
10👍2
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 24 ቀን እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ይሰጣል።

በዘንድሮው ሀገር ፈተና 564,219 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

🔴 የተፈጥሮ ሳይንስ ፦ 306,964 ተማሪዎች፤

🔴 የማህበራዊ ሳይንስ ፦ 257,255 ተማሪዎች

ለፈተናው 667 ማዕከላት እንደተዘጋጁ ተገልጿል።

ፈተናው በዋናነት በበይነ መረብ (Online) የሚሰጥ ሲሆን በተለያዩ አስገዳጅና ልዩ ምክንያቶች ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተማሪዎች ብቻ በወረቀት ይፈተናሉ።
10🫡3
🔴የሬሜዲል ፈተና መስጫ ቀን ተራዘመ

ከግንቦት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ/ም ሊሰጥ ፕሮግራም ወጥቶለት የነበረው የሬሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ) ፈተና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲሰጥ ተራዝሟል።

ምንጭ: የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5😁1
🔴ዘንድሮ ኢንትራን ፈተናን የምትወስዱ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የቀራችሁ 1 ወር ከ9 ቀን ነዉ ።

እናም በዚህ ስዓት በዉስጣችሁ የተለያዪ የፍርሀት ስሜት እንዲሁም የተደበላለቁ ስሜቶች ሊሰሟችሁ ይችላሉ ፤

ነገር ግን ይህንን ስሜታችሁን መቅበር ያለባችሁ በቀራችሁ ጊዜ የምትችሉትን ያህል ክለሳ በማድረግ እንዲሁም በዋናነት የተለያዮ አመታት የኢንትራንስ ጥያቄዎችን በመስራት ነዉ ፤

ይህንን ስታደርጉ የፍርሀት ስሜታችሁ እየቀነሰ ጥያቄዎቹን የመስራት አቅማችሁ ደግሞ እየጨመረ ይመጣል።

ስለዚህ አሁን የትኛዉም ደረጃ ያህል ያጠናችሁ ተማሪዎች የምትችሉትን ያህል ክለሳ አድርጉ። በዋናነት ግን የተለያዮ አመታት የኢንትራንስ ጥያቄዎችን በመስራት ላይ ጊዜያችሁን አሳልፉ፤ ከዚያ Confidence እየጨመራችሁ ፍርሀታችሁን ማሸነፍ ትችላላችሁ💪

@nbtutorialservice
🥰133
ለ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ልምምድ ያድርጉ!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

ተፈታኞች በተደለደላችሁበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ያለውን ሊንክ በመጠቀም፣ User Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Password በሚለው ላይ 1234 በማስገባት፤ በኮምፒውተር፣ በላፕቶፕ፣ በታብሌት፣ በስልክ እና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሳሪያዎች ማንኛውንም አይነት የኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም መለማመመድ ትችላላችሁ ተብሏል።

@nbtutorialservice
9👍4
🔴 የዘንድሮው የኢንትራንስ ፈተና ሰኔ 24 የሚጀመር ሲሆን ፈተናዉን የሚጀምሩት የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ናቸዉ።

👉በዚህም መሠረት ዛሬ ከ2:30 ጀምሮ የተለያዩ የEnglish Entrance Exam Question ስለምንለቅላችሁ ሁላችሁም ጠብቁን 🙌
🙏4🔥21
NB tutorial service pinned «🔴 የዘንድሮው የኢንትራንስ ፈተና ሰኔ 24 የሚጀመር ሲሆን ፈተናዉን የሚጀምሩት የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ናቸዉ። 👉በዚህም መሠረት ዛሬ ከ2:30 ጀምሮ የተለያዩ የEnglish Entrance Exam Question ስለምንለቅላችሁ ሁላችሁም ጠብቁን 🙌»