✍️✍️✍️
የተግባር ሕይወት.....!!!!
❤❤❤
#በእኛ ሚዛን አብደዋል ወይም የአዕምሮ ህመምተኞች ናቸው ብለን ከምንመድባቸው ሰዎች መካከል ነው። ምሽት ላይ ሰብሰብ ብለን እራታችን እየበላን ሳለ ድንገት ወደእኛ መጣ። እራታችንም ስለደረሰ "ና እንብላ" አልነው። እሱም ሳያቅማማ አብሮን ተመገበ።
ከጀርባው አዝሎት ከሚዞረው ከአሮጌው ሻንጣው ውስጥ ምን እንዳለው አስከፈትነው እና ተመለከትነው። ከልብስ ውጭ ኹለት መጻሕፍት ተመለከትን። 'ክርስቲያናዊ ሕይወትና ትምሕርተ ሃይማኖት' እንዲሁም 'ክርስቲያናዊ ሥነምግባር' የሚሉ ግሩማን መጻሕፍት ናቸው።
❤❤❤
#እጅግ በጣም ተገረምሁ፤ በመጻሕፍቱ ስላለው ቁምነገር ጠየቅኩት። እጅግ የሚደንቅ ምላሾችን ሰጠን። እንዴት እንደ አነበበው ጠየኩት። ማንበብ ለእሱ ቀላሉ ነበር፤ጭራሽ እሱ ከማንበብ አልፎ አውቆት በተግባር ሕይወት እየኖረው ነው፤ሌላ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል። እኛ ግን ዝቅተኛው ላይ መድበነው ነበር።
ወደል ወደል አይኖችን ይዘን የምናይ እውራን ሆነናል።
#ብዙ አንብበናል ግን በተግባር ተመዝነን ቀለን የተገኘን ሰዎች ነን።
እስከ ማዕዜኑ???
#ጌታ ሆይ የተግባር ክርስቲያን አድርገን!!!
#ግሩም ግብርከ መድኃኔዓለም!!!
👏👏👏
ቸር ጊዜ!!!

"ተመጽውቶ መጽዋች..."
❤❤❤
#በሙሉዓለም የባሕል ማዕከል ቁልቁል ወደ መስቀል አደባባይ ቀስ ብየ በእርጋታ ከእራሴ ጋር ብቻ እየተነጋገርኩ እየተጓዝኩኝ ነበር።
#ድንገት አንድ ሰው ፈጠን ብሎ አለፈኝ፤ የእጅ የአካል ጉዳት ያለበት ነው፤ አዳፋና ያረጀ ብርድልብስ ነገር ለብሷል፤ በደህናው እጅ ደግሞ በፌስታል የሆነ ነገር አንጠልጥሏል።
ያንጠለጠለው ነገር ትርፍራፊ ምግብ(በተለምዶ ቡሌ) እንደሆነ አላጣሁትም።በመንገዴ አቅጣጫ ስለሆነ ተከተልኩት።
#መስቀል አደባባይ ጫፍ እየሩሳሌም ሎጅ ሲደርስ ቆም ብሎ ሰዎችን ይፈልጋል። በእድሜ ከእሱ ቀደም የሚሉ አንድ አይነስውር ተመጽዋች ዛፏ ስር ቁጭ ብለዋል።
❤❤❤
"ደህና ዋልክ አያ ይርጋ? " አላቸው።
"እግዜር ...ይመስገን. ..ደህና፤ ታምራት ነህ?" አሉት ደከም ባለ ድምጽ።
" አዎ እኔ ነኘ...እነ በላይ የት ሄዱ?" ሲል ጠየቀ።
" ኧረ እንጃ እረፋድ ላይ እንደሄዱ ድምጻቸውን አልሰማሁም " መለሱለት።
"ውሏችሁ እንዴት ነበር? ምጽዋት አገኛችሁ ወይስ?" ጠየቃቸው።
"ይመስገነው አንድየ... አንዲት ደግ ሰው ቆሎ ሰጥታኝ በላሁ፤ ይሄው አስቀምጨላችሁ ነበር ብላ እስኪ..." አኮፍዳቸውን ወደእሱ አቅጣጫ ገፋ አደረጉለት።
"እናቴ ባታ ድረሽልኝ😯...በአመቷ በዓታ ቆሎ?...እኔማ ዝክሩ ሰፈር ሂጀ ፋሲካ ሆኖልኝ አይደል የዋለ አያ ይርጋ...የረጠበ ነገር አልተቋደሱም ማለት ነው እስካሁን? " በመገረም ተናገረ።
"ይሄስ በእሱ ቸርነት አይደል የተገኘ ታምራት...አንዲት እናት ከጠላይቱም አቅምሳኛለች..." በማመስገን ተናገሩ።
"በሉ በሉ ለመጭው እሱ ያውቃል... ልጀ እና ባለቤቴ አልተንቀሳቀሱም አልበሉም ብየ ነበር እየፈጠንኩ የመጣሁት...ይያዙ ይብሉ፤ ብዙ ነው ያመጣሁት..." በፌስታል የያዘውን ትርፍራፊ አቀረበላቸው።
"ኧረ እኔ ቆሎው አጥግቦኛል ለልጅህና ለሚስትህ ይሁን..." አሉና ተግደረደሩ።
"አይይ አያ ይርጋ ኑሯችን ያውቁታል፤ ለነገ ደግሞ ዛሬ ያበላን አምላክ ያውቃል! " አለና እንዲበሉ ገፋፋቸው።
አይነስውሩ ተመጽዋችም....
"ፈቃዱ ከሆነ ከምጽዋት ያውጣህ!...ሌላም ከሆነ ደግሞ ለምነህ አትጣ!... ታምራት..." ብለውም መረቁት እና በስመ ሥላሴ ባርከው መመገብ ጀመሩ።
#ይሄ መዓድ ቅዱስ እግዚአብሔር ያለበት መዓድ እንደሆነ ያስታውቃል። በእጦት ውስጥ መተሳሰብን ያሳየ ነውና። እኛ በቅንጦት ውስጥም ሆነን መተሳሰብ ርቆናል። አዎ የትርፍራፊው (የቡሌው) መዓድ ላይ እሱ አለበት።
❤❤❤
#እኔም መተሳሰባቸው እየደነቀኝ መድኅኔዓለምን አመስግኘ፤
'ግሩም ግብርከ'
እያልኩትጉዞየን ቀጠልኩ።
#ተመጽውቶ መጽዋች ይሉታል ይሄ ነው!!!
✍️በነገራችን ፎቶ(ምስል) የማንሳት እድሉ ነበረኝ፤ ግን ያለፈቃድ ማንሳት አልፈለኩምና ተውኩት።
👉ቅዱስ አምላክ ካለን ላይ የምናካፍል ያድርገን።

'...መቅለሌ ቢቀልልኝ፤
የቅዱሳን ጥላ ቢያርፍብኝ
....ቁራሽ አካፈልኩኝ....።'
❤❤❤
#ከገብያ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የግራ መስመሬን ይዠ፤ ይሄን የኛውን የብዙዎቻችንን የዓለማውያንን ሀሳብ እያወጣሁ፣ እያወረድኩ እየተጓዝኩኝ ነበር።
"ተመዘን ተመዘን...ጋሼ ተመዘን..." የሚል ድምጽ ይሰማኛል።
ዞር ብየ ድምጹን ወደሰማሁበት ተመለከትኩ፤ የሆነ ደስ የሚል ብላቴና ከእናቱ በጣም ትንሽ ራቅ ብሎ ትንሽየ ሚዛን ይዞ ተቀምጧል፤ ከጥጉ እናቱ ትለምናለች።
"ተመዘን ጋሼ ሚዛን ተመዘን..." አለኝ ድጋሜ አንጋጦ እየተመለከተኝ።
"ቤቢ ..ተመዝኘ ቀልየ ተገኘሁ ቤቢየ..." አልኩት።
"እ...ጋሽየ...ለእኔ ተመዘንልኝ..." አለኝ በሚያሳዝን የሕጻን አንደበቱ ለሦስተኛ ጊዜ በተማጽኖ።
❤❤❤
#ያልኩት ነገር አልገባውም፤ እንዲገባውም አይጠበቅም። እሱ አላማውና ሀሳቡ እኔ ሚዛኗ ላይ ወጥቼ ከዛ የምሰፍርለት ትንሿ ዲናር ናት፤ ከዛም የዕለት ጉርሱ።
#በቅጽበት አሰብኩ፤ እራሴ ባመጣሁት ቃል ይሄ ነገር ከላይ እንደሆነ አመንኩኝ።
ከዛም ለጥቄ ደግሞ....
'.....መቅለሌ ቢቀልልኝ፤
የቅዱሳኑ ጥላ ቢያርፍብኝ...'
ብየ ለቤቢ ደጋግሜ ተመዘንኩለት።
👉ስጡ... ይሰጣችሁማል።
-ተመዝኖ ከመቅለል በምሕረቱ ይጠብቀን!

❤2
👉"ባልና ሚስት እንደ እጅና ዓይን ሊሆኑ ይገባል፤ እጅ ሲጎዳ ዓይን ሊያለቅስ ዓይን ሲያለቅስም እጅ እንባን ሊያብስ ይገባል። "
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
❤1
✍️✍️✍️
"እንደ ተርታ ሰው...!!!"
❤❤❤
#አንድ የቤተክርስቲያን የዜማ ሊቅ ናቸው፤ ድንገት መንገድ ላይ ተገናኘን፤ ጠንከር ያለ ሰላምታ ተለዋወጥን። በጊዜው እኔ መነጽር ደረቴ ላይ አድርጌ፤የማንችስተር ዩናይትድ መለያ ለብሸ፤ ኮፍያ ደግሞ አናቴ ላይ ጣል አድርጌ ነበር።
"ኧረ ኧረ ኧረ እንደተርታ ሰው እንዲሁ..." አሉኝ ሊቁ ፈገግ ብለው ግን በቁምነገር እየተናገሩ።
❤❤❤
#ለካ የሆነ የሆነ ጊዜ ላይ መድረክ አካባቢ ወጣ ገባ ስል አይተውኝ ኑሯል። ከዚያስ ከሊቃውንት ወገን መድበውኝ እርፍ።
'ወይ አለመተዋወቅ'🤔 በጣም ገረመኝ።
ንግግራቸውን በብዙ እይታዎች ብገነዘበውም ይሄኛው ግን ከበደኝ። የሀገሬ ሰው "ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ!" የሚል ግሩም ብሂል አለው።
#የተማሩት ዝም ሲሉ በማንመጥነው መድረክ በድፍረት እየቆምን ውኒጥ ውኒጥ እያልን አስቸገርን። ከዛስ ተርታ ሆነን ሳለ በሰዎች ዘንድ ነቀፌታ እንደሌለው ትልቅ የጭብጨባ ግንብ ገንብተን ግን ደግሞ በንፋስ ወዳቂዎች ሆንን።
#ጌታ ሆይ ከዚህ ሁሉ ጠብቀን፣ ቆጥበን!!!

የእኛን ሳንፈጅ፣
በሰዎች መፍረድ።
እስከ መቼ....???🤔
❤❤❤
#ተወዳጆች ኦርቶዶክሳውያን ሆይ....
👉ያው ሰሞኑን ዘመነ ጥምቀት፣አስተርዮ ስለሆነ አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ተወልዶ፤ ተጠምቆ እስከ ሞት ድረስ ለወደደን አምላካችን እና ለተከተሉት ቅዱሳኑ ሁሉ በአለው አቅም፤ በአለው ጸጋ ሁሉ ሲዘመር ሲያወድስ ሰንብቷል።
#ታዲያ አንድ የማውቀው ወጣት(ወደ ቤተክርስቲያን ቀረብ ያለና የሚያገለግል ነው) በዚያም በዚያም በቡድን በቡድን ሆነው ሲዘምሩ የነበሩ ወጣቶችን ሲመለከት ቀይቶ እንዲህ ሲል ሰማሁት።
"ይህ ዱርየ ሁላ ይዘምራል...አሁን ደህና ሰው እኮ ይመስላሉ...አስመሳይ ሁሉ..." ሲል ሰማሁት።
ቀረብ አልኩትና "ና " ብየ ወደ አንዱ የዘማርያን ቡድን ወሰድኩትና "እኔ ምልህ እስኪ ዱርየ ናቸው ያልከኝን አሳየኝ " ብየ አፋጠጥኩት።
"አንተ ደሞ ምን ይሄ ሁሉም የዱርየ ጥርቅም አይደል እንዴ...." ሲል መለሰልኝ።
❤❤❤
#የሚገርማችሁ ወስጄ ካሳየሁት የዘማርያን ቡድን ውስጥ ደግሞ በአይኔ በብረቱ ያየኋቸው፣ የማውቃቸው #አንድ ወንድም እና #ሦስት እህቶች በየጊዜው ንሥሓ የሚገቡ፤ የጌታችን ቅዱስ ሥጋ ክቡር ደም የሚቀበሉ (የሚቆርቡ) ናቸው።
ከዛም ለጥቄ "ወንድሜ እስኪ ንገረኝ አንተ ትቆርባለህን? " ብየ ጠየኩት።
" ኧረ አልቆረብኩም፤ ንሥሓ ግን በየጊዜው እገባለሁ" አለኝ።
"ከእነዚህ ዱርየ ከምትላቸው ዘማርያን ወጣቶች መካከል የሚቆርቡ እንዳሉ እነግርሃለው፣ አሳይሃለው፤ ሰዎችን ሳናውቅ አንፍረድ።" አልኩት።
"የምርህን ነው?...አምንሃለው እስኪ ዮሐንስን በለኝ " አለኝ በምወደው ቅዱስ ሐዋርያ ሊያስምለኝ እጁን እየዘረጋ።
እኔም በቅዱስ #ዮሐንስ ስም የማውቀውን፣ ያየሁትን እውነት ነገርኩት።
ከዛም "እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ፤ በተናገርኩትና በፈረጅኩት ንሥሓ እገባለሁ፤ እኔም አምላኬ ይርዳኝና በዚህ ዓመት ሥጋወደሙ ለመቀበል እዘጋጃለሁ..." አለኝ።
እኔም "ቅዱስ አምላክ ይፍቀድልህ፣ ያሳካልህ።" ብየ በኅጥያተኛ አንደበቴ መረቅሁት።
❤❤❤
#ወንድሜ ባይገርምህ በእለተ ሐሙስ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቀን ከነዚያ ዘማርያን ቡድን ውስጥ የነበረ አንድ ወንድማችን በቅርብ ከምትገኘው ገዳም ጎራ ብሎ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሊቀበል ዝግጅቱን ጨርሷል።
#አምላከ ቅዱሳን ይጠብቀው፣ ያዝልቅለትም።
👉ግን እስከመቼ ነው የምንፈርደው🤔?
በሰዎች ከመፍረድ ይልቅ እንደ ነቢዩ ዮናስ "እኔ ነኝ ኃጢአተኛ" ማለት አይሻልምን?
#ሁላችንም ለዚህ ቅዱስ ተግባር ያብቃን!!!

ቸር ናችሁ ተወዳጆች በገናውያን!!!
👇👇👇💚💛❤👇👇👇
#እነሆ የበረከት ጉዞ🚎🚌
ወደ እመ ምዑዝ #ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እና ቅድስት ኪዳነምሕረት ገዳም፦
❤❤❤
#እናታችን ቅድስት ፍቅርተክርስቶስ ታላቅ ተጋዳይ ሰማዕትና ጻድቅ የቅድስት ኪዳነምሕረትን ቤተክርስቲያን #በአንድ ቀን ውስጥ በሰንሰል፣በስሚዛና በአይጥ ሀረግ የሰራች ቅድስት ናት።
#እናታችን ቅድስት ፍቅርተክርስቶስ የተሰጣት ቃልኪዳን፦
-በጸሎትሽ የተማጸነ ባለጤና ይሁን
-ስምሽን የጠራ የከበረ ይሁን
-በቀናች ሃይማኖት ሁኖ የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ፣ያጻፈ፣የሰማ፣ያሰማ ፤ቀዝቃዛ ውሃ በስምሽ የሰጠ ኃጢአቱ ይሰረይለታል።
-ልምረው ያላወጋጀሁትን ወደ ደጅሽ አላስጠጋውም።
-ለቤተክርስቲያንሽ መባ የሰጠ
-የተላከ
-ቤተመቅደስሽን መጥቶ የተሳለመ እስከ 12 ትውልድ የምሕረት ቃልኪዳን እሰጠዋለሁ ተብላ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን ተሰጥቷታል።
❤❤❤
እናታችን ቅድስት ፍቅርተክርስቶስ
📇ታሕሳስ 16- ቤተመቅደሷን የሰራችበት
📆ታሕሳስ 29- ልደቷ
📅የካቲት 29- እረፍቷ ይከበራል።
#ስለዛም
ክቡራን ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ሂደን ይህን በዓል አብረን እንድናከብር በገናውያንን እና መላው ኦርቶዶክሳውያንን መንፈሳዊ ጥሪ አቅርበውልናል።
#ይህን ጥሪ በመቀበል #የካቲት 29 በገዳሟ በቦታው ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ተጉዘን ለማክበር ዝግጅት ላይ እንገኛለን።
#ተወዳጅ ኦርቶዶክሳውያን በገናውያን ሆይ የምትችሉ ሁሉ በዚህ ድንቅ የበረከት ቦታ በመገኘት በረከት እንድናገኝ ይሁን።
❤❤❤
👉የትኬት ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ 3000 ብር
👉መነሻ ቀን ቅዳሜ- 28/06/2018 ዓ.ም
👉በዓል ንግስ በገዳሙ እሑድ- 29/06/2018 ዓ.ም
👉መመለሻ ቀን ሰኞ- 30/06/2018 ዓ.ም
☎️📞ለበለጠ መረጃ፦
-0918747372
-0924125454
-0918719540
💚💛❤
ቸር ጊዜ👏

ስማችን ከብዶ......
ግብራችን ወርዶ.....እንዲሁ አለን🤔🤔🤔
❤❤❤
#በጃንሆይ ጊዜ ነው አሉ ጣሊያን በአጼ ሚኒሊክ ጊዜ ወረራዋን ስትፈጽም በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቀምሳ ተዋርዳ ተመልሳ ነበር፤ ከዚያም ከ40 ዓመት በኋላ ለመበቀል በካቶሊክ ጳጳሷ መድፏን አስባርካ ሀገራችን ወረረች።
#ይህ ወረራ በሀገራችን የሰሜኑ ክፍል ተጀምሮ ወደ ሌሎች ክፍሎች ቀጥሏል። ታድያ ይገርማችኋል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲዋጓቸው ከነበሩት ጀግኖች መካከል አሉላ አባነጋ አንዱ ነበሩ። አሉላ አባነጋ የነበሩበትን ቀጠና ጣሊያኖች ተቆጣጠሩትና በአካባቢው መኖር ጀመሩ።
❤❤❤
#ጣሊያኖች ተንኮለኞች ናቸውና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ለማናደድ የጣሊያኑ ጀኔራል ውሻውን አሉላ ብሎ ሰይሞ ይጠራዋል። በዚህ የበሸቀችው የአካባቢው ተወላጅ የሆነች ምግብ በማብሰል ከጣሊያኖች የተቀጠረች ሰው አንድ ቀን ለዚያ በጀግናው ስም ለተሰየመ ውሻ መርዝ ሰጠችውና በልቶ ሞተ።
#ከዚያም ጣሊያኖች ተበሳጭተው መጡና፦
"ምን ነካው? ማን ገደለው ውሻችንን...?" ብለው ቀወጡት።
እሷም "ስሙ ከብዶት ሞተ...!!!" ብላ መለሰችላቸው።
#ዛሬስ ስንቶቻችን ስማችን ከብዶን ይሆን?
#በነገራችን ላይ መጠሪያ ስሞቻችን በተመለከተ ወደፊት በሰፊው እመለስበታለሁ።
❤❤❤
#ጌታ ሆይ...
ስማችን ከብዶ.....
ግብራችን ወርዶ....ከማየት ጠበቀን!!!
-'ስሙ ከብዶት ሞተ'...ከመባል አቅበን!!!

❤2🔥1
✍️✍️✍️
ሰላም እንዴት ናችሁ!!
❤❤❤
#ተወዳጁና ተናፍቂው የ3 ቀናት የቅዱሱ ሐይቅ(Holy Lake) የጣና ገዳማት ጉዞ ቅዱስ እግዚአብሔር ፈቅዶ እነሆ ደረሰ።
#የምትችሉ ኑ አብረን እንጓዝ፤ አካባቢያችን እንወቅ፤ ቅዱሳን መካናትን እንሳለም።
❤❤❤
#በዚህ ቅዱስ ሐይቅ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ገዳማት ደጋፊ የሌላቸው አሉ። ስለሆነም ተሳትፋችሁ በረከት ማግኘት የምትፈልጉ፦
-እጣን
-ዘቢብ
-ጧፍ
-ሻማ
#እንደተለመደው መሳተፍ የምትፈልጉ የቻላችሁትን ገዝታችሁ፤ የመጽሐፍ ስማችሁን ጽፋችሁ ብትሰጡን የምናደርስ መሆኑን ለመግለጥ እወዳለሁ።
ለበለጠ መረጃ፦
0927688782 -ሙሴ
ብላችሁ ልታገኙኝ ትችላላችሁ።

❤1👏1
ይች ሴት ትናፍቀኛለች"
እጅግ ትናፍቀኛለች... ያቺ በእግዚአብሔር ጥላ ስር የበቀለች፣ በቤተ መቅደስ ቅጥር የለመለመች፣ በዝምታዋ ውስጥ ሺህ ቃላትን የምትናገር፣ በፈገግታዋ ውስጥ የሰላምን ወንዝ የምታፈስ። እሷን ሳስባት... ፊቴ ላይ የሚመጣው ምስል እንደ ርብቃ ለጥሙ ጥም የሚሆን የውኃ ማሰሮ ይዛ፣ ትህትናን ተከናንባ ወደ ልቤ ጉድጓድ የምትመጣውን ያቺን እንቁ ነው፡፡ በስደት እንደጸናችው እንደ ሩት፣ 'አምላክሽ አምላኬ ነው'' ብላ በታማኝነት የጸናችውን ያቺን ቅን ሴት። እርጋታዋ የቤቴ ምሰሶ፣ ጸሎቷ ደግሞ የቤቴ ጣራ ነው፡፡ አለባበሷ... ሥጋን ለመግለጥ ሳይሆን ነፍስን ለማድመቅ የተሰፋ። ያ በነጭ ነጠላዋ ውስጥ የሚታየው ክብሯ፣ እንደ ደመና ግርማን ያጎናጽፋታል። ፋሽን የማይለውጠው፣ ጊዜ የማይሽረው የቅድስና ግርማ አላት፡፡ እሷን ያየ የፈጣሪን ጥበብ ያያል፤ እሷን ያየ የሞራልን ልዕልና ይረዳል።
"ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።" (ምሳሌ 31፥30)
ጸሎቷ... እንደ ሐና የልብ ጩኸት የሆነ፣ ከከንፈር በላይ ምስጢርን ለፈጣሪ የምታወጋበት። በእምነት ወደ መቅደስ ስትገሰግስ፣ በጠዋት ኪዳን፣ በሠርክ ማኅሌት የምትታይ የቤተ መቅደስ ርግበ-ሰላም። ስሟን ስጠራው የምግባር ሽታ ይሸተኛል፤ ትህትናዋን ሳስበው ኩራቴ ይቀልጣል። ትናፍቀኛለች... ይህቺ ዓለም በጫጫታ በደፈረሰችበት ዘመን፣ እንደ ጥልቁ ኩሬ የረጋችው ያቺ ኦርቶዶክሳዊት ወይዘሪት። በእምነት የታጠረች፣ በሥነ-ምግባር የታነጸች፣ በወንጌል የታሸች። የእሷ ማንነት እንደ ሣራ "ጌታዬ" ብላ ለትዳሯ የምትገዛ፣ እንደ ሊድያ ቤቷን ለበረከት የምትከፍት፣ እንደ ማርያም እና ማርታ ቃሉን ለመስማትና ለማገልገል የምትተጋ ናት፡፡ አዎ! እሷን መናፈቅ ማለት... እግዚአብሔርን መፍራትን መናፈቅ ነው፡፡ እሷን መናፈቅ ማለት... ሰላምን መናፈቅ ነው፡፡
ያቺን ሴት—የጽዮን ልጅ የሆነችውን፣ የቅዱሳን እናቶችን ፈለግ የምትከተለውን—በጣም፣ እጅግ በጣም ትናፍቀኛለች!
#ያልተኖረ_ህልም
#ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹

👍1
በመጽሐፍ ቅዱስ ስማቸው የተጠቀሰ ሀገራትና የዛሬ ስያሜያቸው።
እስያ (መካከለኛው ምስራቅ)
✍️1. እስራኤል - አሁኗ እስራኤል ፦ ከ2,500 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️2. ባቢሎን - አሁኗ ኢራቅ ፦ ከ280 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️3. ፋርስ - አሁኗ ኢራን ፦ ከ30 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️4. ሶርያ - አሁኗ ሶርያ ፦ ከ70 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️5. ዮርዳኖስ - አሁኗ ዮርዳኖስ ፦ ከ70 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️6. አሦር - አሁኗ ሰሜን ኢራቅ ፦ ከ150 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️7. ሜዶን - አሁኗ ሰሜን ኢራን ፦ ከ25 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️8. ሳባ - አሁኗ የመን ፦ ከ10 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️9. ዐረብ - አሁኗ ሳዑዲ አረቢያ ፦ ከ10 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️10. ኤላም - አሁኗ ደቡብ ኢራን ፦ ከ10 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️11. ህንድ - አሁኗ ህንድ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️12. ገላትያ - አሁኗ መካከለኛ ቱርክ ፦ 10 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️13. ኤፌሶን - አሁኗ ቱርክ ፦ ከ15 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️14. ቂልቅያ - አሁኗ ደቡብ ቱርክ ፦ 15 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️15. ፍርግያ - አሁኗ ቱርክ ፦ 9 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️16. ቢታንያ - አሁኗ ሰሜን ቱርክ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️17. ጳንጦስ - አሁኗ ሰሜን ቱርክ ፦ 5 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️18. ልድያ - አሁኗ ምዕራብ ቱርክ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️19. አርሜንያ - አሁኗ አርሜንያ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
🌍 አፍሪካ
✍️20. ግብፅ - አሁኗ ግብፅ ፦ ከ600 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️21. ኢትዮጵያ (ኩሽ) - አሁኗ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ፦ ከ40 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️22. ሊቢያ - አሁኗ ሊቢያ ፦ 6 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️23. ፑጥ - አሁኗ ሰሜን አፍሪካ ፦ 7 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️24. ቀሬና - አሁኗ ምስራቃዊ ሊቢያ ፦ 10 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️25. ሲኒም - (አንዳንዶች ቻይና ይሏታል) ፦ 1 ጊዜ ተጠቅሳለች።
🌍 አውሮፓ
✍️26. ሮሜ - አሁኗ ጣሊያን ፦ ከ20 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️27. ግሪክ - አሁኗ ግሪክ ፦ ከ15 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️28. መቄዶንያ - አሁኗ ሰሜን ግሪክ ፦ ከ20 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️29. አካይያ - አሁኗ ደቡብ ግሪክ ፦ 10 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️30. ስፓንያ - አሁኗ ስፔን ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️31. ቆሮንቶስ - አሁኗ ግሪክ ፦ ከ10 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️32. ተሰሎንቄ - አሁኗ ግሪክ ፦ 7 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️33. ቀርጤስ - አሁኗ ግሪክ ፦ ከ10 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️34. ቆጵሮስ - አሁኗ ቆጵሮስ ፦ ከ10 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️35. ታርሴስ - አሁኗ ስፔን ፦ ከ20 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️36. ኢሊሪቆን - አሁኗ አልባኒያ ፦ 1 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️37. ዳልማጥያ - አሁኗ ክሮኤሺያ ፦ 1 ጊዜ ተጠቅሳለች።
🌍 እስያ (መካከለኛው ምስራቅና አናቶሊያ)
✍️38. ከለዳውያን - አሁኗ ደቡብ ኢራቅ ፦ ከ80 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️39. ሊቃኦንያ - አሁኗ መካከለኛ ቱርክ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️40. ቢታንያ - አሁኗ ሰሜን ምዕራብ ቱርክ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️41. ሚስያ - አሁኗ ሰሜን ምዕራብ ቱርክ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️42. ካጰዶቅያ - አሁኗ መካከለኛ ቱርክ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️43. ደድያም - አሁኗ ሰሜን ምዕራብ ሳዑዲ አረቢያ ፦ 11 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️44. አሞሬዎን - ጥንታዊ የከነዓን ነገድ ፦ ከ80 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️45. ኬጤዎን - ጥንታዊ የሶርያና ቱርክ ግዛት ፦ ከ60 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።ኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ፦ ከ35 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።
✍️47. ጌርጌሴዎን - ጥንታዊ የከነዓን ነገድ ፦ 7 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️48. ፒሲድያ - አሁኗ ደቡብ ቱርክ ፦ 2 ጊዜ ተጠቅሳለች።
🌍 አውሮፓ
✍️49. ማልታ - አሁኗ ማልታ (ደሴት) ፦ 1 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️50. ሲራኩስ - አሁኗ ሲሲሊ (ጣሊያን) ፦ 1 ጊዜ ተጠቅሳለች።
✍️46. ኢያቡሴዎን - የጥንቷ

#ትውልደ_መምህራን_ይትባረኩ✅
የመምህራን ልጆች መምህራን ናቸው፣
በሊቅነት ግርማ በጥዑም ቃላቸው❗
በአባትነት ሞገስ ሰው የሚያከብራቸው።
የሃይማኖት ተክል ጉንቱ የሀገር ዋርካ ፣
ፍሬያችኁ እልፍ ነው በሥራ ሚለካ❗
#አባት_እና_ልጅ
➊ ክቡር የኔታ #ሊቀ_ምሁራን_ዓለሙ እና መምህረ መምህራን የኔታ #በጽሐ_ዓለሙ
➋ ክቡር አባ መልአክ እና የኔታ ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ
➌ ክቡር የኔታ #ሊቀ_ሊቃውንት_ያሬድ ሽፈራው እና መጋቤ አእላፍ #ቅዱስ_ያሬድ
➍ ክቡር ነፍሰ ኄር #መጋቤ_ሐዲስ_ድምፀ_አንበርብር እና ሊቀ ጉባዔ #ጌታሁን_ድምፀ_አንበርብር
✅ለሊቃውንት አባቶቻችንና መምህራኖቻችን የአገልግሎት ዘመናቸው ይባርክልን ፣በዕድም በጤናና ያቆይልን ፣ በረከታቸውም ትድረሰን አሜን❗

❤4
✍️✍️✍️
#ተወዳጆች ቅኑዓን ሆይ ታዛዦች ከሆንን
እስኪ ሁላችንም ....
1ኛ. ለሌሎች እናጋራው(share) እናድርገው!!!
2ኛ. ፕሮፋይል ፒክቸር(PP) እናድርገው!!!
3ኛ. ስቶሪ(Story) እናድርገው!!!
4ኛ. የዚህ ሳምንት ጃሌንጅ (ቢያንስ 4 ሰዎች ማምጣት) እናድርገው!!!

እንዲህ ባለች ሴት ይባርክህ።
ስኬትህን እንደ ራሷ ስኬት በምትቆጥር፣ በትንሽ እርምጃህ እንኳን በምትደሰት፣ መንገድህ ሲከብድ "አትበሳጭ፣ እኔ ከጎንህ ነኝ" ብላ በምትቆምልህ ሴት ይባርክህ።
ቀኑ ክፉ ሲሆን "ይህም ያልፋል" ብላ ተስፋ በምትሰጥህ፣ ስትወድቅ "ተነስ፣ አንተ ይህን ማድረግ ትችላለህ" ብላ በምታበረታታህ ሴት ይባርክህ።
"የእከሌ ባል እንዲህ ነው፣ የእከሌ ሰው እንዲያ ነው" ብላ በማነጻጸር ፈንታ፣ ያለህን አቅም አይታ በምታምንብህ፣ ህልምህን በምታከብር፣ ጥረትህን በምታደንቅ ሴት ይባርክህ።
አንቺንም እንዲሁ በአንቺ መኖር የሚያመሰግን፣ ክብርሽን የሚጠብቅ፣ እንባሽን የሚያብስ፣ ፈገግታሽን የሚያበዛ፣ "ከጎንሽ ነኝ" ብሎ በቃሉም በተግባሩም የሚያሳይ ሰው ይባርክሽ።
ውበትሽ ሲቀየር፣ ዘመን ሲያልፍ፣ ሁኔታዎች ሲለዋወጡ እንኳን ፍቅሩ የማይቀየር፤ ዛሬ እንደወደደሽ ነገም እንዲሁ የሚወድሽ፣ በምክንያት ሳይሆን በልቡ የሚያከብርሽ ሰው ይባርክሽ።
እንዲህ ያለ ፍቅር ይባርካችሁ።
ስህተት ሲፈጠር "ማን ጥፋተኛ ነው?" ብሎ የማይጠይቅ፣ "እንዴት እናስተካክለው?" ብሎ የሚጀምር፤ ኩራትን ከፍቅር በታች የሚያደርግ፣ ይቅርታን ከክርክር በላይ የሚመርጥ ፍቅር ይባርካችሁ።✨🤍

#እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ።
#ይቺን የፍልሰታን ጾም አስመልክቶ የቤተክርስቲያናችን አገልግሎት በሌሊትም በቀንም የጎላ እንደሆነ ይታወቃል።
#ስለዛም በተለይ ወደ ገጠር አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ብዙ ነገር ያስፈልጋቸዋል።
👉ለምሳሌ፦
-ሻማ
-ጧፍ
-እጣን
-ዘቢብ
.......እንዲሁም ሌሎች ንዋያተ ቅድሳት
የምትችሉ ገዝታችሁ ብትልኩ በረከት ታገኛላችሁ።
👉የሚያስፈልጋቸው አብያተ ክርስቲያናት ለመጠቆም ያክል፦
-ጎንባት ቅዱስ ጊዮርጊስ
-ሮቢት በዓታ
-ዘንዘልማ ቅዱስ ጊዮርጊስ
-ይባብ ቅዱስ ያሬድ
-ዘጌመስመር አርባዕቱ እንስሳ ኪሩቤል
-ይነሳ ኢየሱስ
-ማይሐጹራ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ
......እንዲሁም ሌሎች ብዙ አሉ።
ለሌሎችም አድርሱት የሚችሉ ሁሉ ይላኩ፤ ይሳተፉ፤ ያድርሱ።

👉#ለደብረታቦር ፬ቱ ጉባኤያት ቤተመጽሐፍት መጻሕፍትን እያሰባሰብን ስለሆነ ማንኛውም ሳይንሳዊ፣ፍልስፍናዊና ሃይማኖታዊ መጽሐፍት ድጋፍ ማድረግ ከፈለጋችሁ እንድታመጡልን ስል ጥሪየን አቀርባለሁ።
0927688782 -ደውሉልኝ ወይም በውስጥ ጻፉልኝ!!!