ዛሬ ③ ፕሮግራሞችን በሳይንስ ሙዚየም ታድሜ ነበር።
ከጠዋቱ ክፍለ ጊዜ፤ መንግስት ለስታርታፖች አዲስ ያዘጋጀው አዋጅ ከመፅደቁ በፊት ከህዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መደረግ ስላለበት በርሱ ላይ ሃሳቦች ተነስተዋል፣ የፓነል ዲስከሽንም ነበረው።
ቴክኖሎጂንና፣ ፈጠራንና የማምረትን አቅም ለማፋጠንና ለማገዝ የተቋቋመው የፓን አፍሪካ ቲምቡክቶ (Timbuktoo ManuTech Hub) በይፋ ተበስሯል። ስታርታአፕ ያላችሁ ምዝገባ እስለ ደሴምበር 25 ስላለ ተመዝገቡ።
ከሰአት ደግሞ ዓለም አቀፍ የአንተርፕረነሮች ሳምንትን ዝግጅት ታድሚያለሁ። ቆንጆ ቆንጆ ሃሳቦች ተነስተዋል። እንዲህ አይነት መድረኮች ለብዙ ነገር ስለሚጠቅሟችሁ ቴክ ላይ ያላችሁ ወይም ሌላ ዘርፍ ላይ የሚመለከታችሁ ኢቨንት ሲኖር ብትታደሙ ታተርፋላችሁ።
ችግሩ የኛ ሰው በዚህ ረገድ ሲበዛ ሰነፍ ነን!
ዝርዝር ነገር ከታች ባያያዝኩት የሊንክድኢን ፖስቴ ላይ አለ፤ ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።
https://www.linkedin.com/posts/murad-tadesse-a0a919160_innovation-entrepreneurship-startups-activity-7266149221399990272-odBp?utm_source=share&utm_medium=member_android

Linkedin
Sign Up | LinkedIn
500 million+ members | Manage your professional identity. Build and engage with your professional network. Access knowledge, insights and opportunities.
ጭራሽ የነርሱን እምነት መዝሙር በግዴታ እያስዘመሯቸው ነው⁉️
==========================================
✍ ሙስሊም ባስገነባው ተቋም ላይ ሙስሊም ዓይነ ስውራን ሶላት መስገድና ኢስላማዊ አለባበሳቸውን በነፃነት መልበስ አልቻሉም ሲባል ዝም አልን። እምነታችን ይበልጣል ያሉ ዓይነ ስውራን እህትና ወንድሞች ቢጮኹ አልሰማቸው ስንልና አጋዥ ሲያጡ ተቋሙን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል።
እዛው ሆነው ጫናዎችን ተቋቁመው ትምህርታቸውን ለመማር የወሰኑ እህት ወንድሞች አሁን ደግሞ ወደ ሌላ ከባድ ጫና ተዳርገዋል።
ይሄውም የሌላ እምነት መዝሙር በግዴታ እንዲዘምሩ እየተደረጉ ነው።
በአጭሩ ተቋሙ የማክ'ፈሪያና የሚሸነሪ ተቋም እየሆነ ነው ማለት ይቻላል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ምንም ማድረግ ያልቻለ መጅሊስና ኡማ መኖሩ ያሳዝናል፣ ያሳፍራል፣ ያበሳጫል።
በነገራችን የዚህ ጭቆና ፈፃሚዎች የተቋሙንና የህዝቡን ስነ ልቦና ቀስ በቀስ ካዳመጡ በኋላ ነው ወደዚህ ያመሩት። መጀመሪያ ሶላት ከለከሉ፣ መጅሊሱም ሆነ ህዝቡ ምንም አላመጣ። ከዚያም በግድ መዝሙር ማስዘመር ጀመሩ ተባለ፤ አሁንም ምንም የምናመጣ አይመስልም። ከዚያ ቀጣይ በግድ አከ'ፈሯቸው ብንባል እንኳ ምንም ላንል እንችላለን።
||
t.me/MuradTadesse

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ጭራሽ የነርሱን እምነት መዝሙር በግዴታ እያስዘመሯቸው ነው⁉️ ========================================== ✍ ሙስሊም ባስገነባው ተቋም ላይ ሙስሊም ዓይነ ስውራን ሶላት መስገድና ኢስላማዊ አለባበሳቸውን በነፃነት መልበስ አልቻሉም ሲባል ዝም አልን። እምነታችን ይበልጣል ያሉ ዓይነ ስውራን እህትና ወንድሞች ቢጮኹ አልሰማቸው ስንልና አጋዥ ሲያጡ ተቋሙን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። እዛው…
ቆይ ግን ምን ታስቦ ነው?
ቢያንስ እንደት ግልፅ የሆነ የመረጃ ፍሰት አይኖርም?
ቀጣይ ምን ዜና እስከምንሰማ ነው የምንጠብቀው?
በነዚህ ዓይነ ስውራን ጉዳይ አላህ አይጠይቀንም ወይ?
ጭራሽ በእንቶ ፋንቶ ትሬንድ ተጠምደናል። ይህ ደብዳቤ የተላከልኝ ችግሩ ከተከሰተ ጀምሮ ለሚመለከታቸው የመጅሊስ ተቋማት በአካል ጭምር በመገኘት በተደጋጋሚ ሲያመለክት ከነበረው ዐብደ-ል'ሏህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም ተቋም ነው።

«እንደ አሲዱ ብዛት ፥ እንዴ'ኔ አንድ መሆን፣
እንዴት እሆን ነበር ፥ አላህ ተኔ ባይሆን።»
[አሲድ → ምቀኛ፣ ተኔ → ከእኔ]
ያ'ገራችን ገጣሚዎች'ኮ ቅኒያቸው👌
እንዴት እሆን ነበር ፥ አላህ ተኔ ባይሆን።»
[አሲድ → ምቀኛ፣ ተኔ → ከእኔ]
ያ'ገራችን ገጣሚዎች'ኮ ቅኒያቸው👌
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምዕራባዊያን ኢስላምን ከሚኮንኑበት ነገር አንዱ ስለሆነው እስከ 4 የማግባት ጉዳይ፤ ምላሹን ከራሳቸው ከእህቶች አንደበት አዳምጡ!
አንዳንድ ሰዎች የሰው ድግስ ላይ ስትሄዱ ለምንድ ነው አግበስብሳችሁ ምግብ የምታነሱት? ገና ለገና እናንተ ስላልፋችሁበት የጸብ ይመስል ከምራችሁ ታነሳላችሁ! በልታችሁ ብትጨርሱት'ኮ ችግር አልነበረውም። ከአቅማችሁ በላይ ስላነሳችሁ ከመጠን በላይ ለማስተረፍ ትገደዳላችሁ። ወይ ብዙ መብላት ከፈለጋችሁ ሆዳችሁን አስርቡትና ኑ! እስክትጠግቡ ብሉ፤ ግን እባካችሁ አታባክኑ። የቂም አነሳስ አታድርጉት እንጂ!
ከጠናባችሁ ቴክአወይ አድርጉልን በሉን¡
ከጠናባችሁ ቴክአወይ አድርጉልን በሉን¡
2,3,4 ማግባት በእህቶች ዘንድ እንዲፈራና እንዲጠላ ያደረገው የብዙ ወንዶች ተግባር ነው።
መልኳ እስኪቀዬር ድረስ አብራው ወጥታ ወርዳ ከችግር ለመላቀቁ ሰበብ የሆነችውን የመጀመሪያ ሚስቱን፤ ከወለደችና ከተጎሳቆለች በኋላ እርሷን ከነ ልጆቿ አስታቅፎ አዲስ ካገባት ወጣት ጋ፤ ዛሬ አለፈለትና ጊዜውን ያሳልፋል። በቃ! expired እንዳደረገ መጠቃቀሚያ እቃ ነው የሚያያት።
ታዲያ የዚህችን አይነት እህት እጣ ፈንታ እያዩ፤ እንደት ነው ሌሎች ሴቶች ይህን ጉዳይ እሺ ብለው ወደው የሚቀበሉት። ተፈጥሯዊው የመቅናት መንፈስ እንዳለ ሆኖ፤ ይህ ተግባር የጥላቻ ዙሩን ያከረዋል። ለማንኛውም መስፈርቱን የማታሟሉ ወንድሞች ሃብት ስላላችሁ ብቻ አታግቡ። መስፈርት ሲባል ሃብት አንዱ እንጂ ሁሉ ነገር አይደለም።

አሁን ደግሞ እስኪ ወደ ቢዝነስ፦
①) ከሶፍትዌር ማበልፀግ በተጨማሪ ለመኖሪያ ቤታችሁ፣ ለሥራ ቦታችሁ፣ ለድርጅቶች፣ ለንግድ ማዕከሎች፣ ለሆቴሎች፣ ለት/ቤች… ወዘተ የደህንነት ካሜራ (ሴኩሪቲ ካሜራ) የሚሠራላችሁ ከፈለጋችሁ፣
②) የኢንተርኔት ዝርጋታ ከፈለጋችሁና ሙሉ የኔትወርኪንግ ሥራ ካሻችሁ፣ የኮምፒዩተር ጥገናም ሆነ የLAN ሥራ ካስፈለጋችሁ… አዲስ አበባና አዳማ ላይ ብቻ ያላችሁ በውስጥ t.me/Murad_Tadesse ላይ አናግሩኝ። ወይም በኢሜይል contact@muradtadesse.com ላይ ጻፉ። በተቋም ደረጃም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ስለሚሠራላችሁ ፈታ ብላችሁ ሃሳባችሁንና የሚሠራላችሁን ነገር በዝርዝር ጻፉ። መልዕክት ስለሚበዛ ሰላምታ ብቻ ጽፋችሁ መልስ ከመጠበቅ ሰላምታውንም ፍላጎታችሁንም አንድ ላይ በዝርዝር አስፍሩት።
(ካሜራ ካለ ሠራተኛን የትም ቦታ ሆኖ በአካል መገኘት ሳይጠበቅባችሁ መቆጣጠር ትችላላችሁ። ሠራተኛውም ሳያለምጥ ቆፍጠን ብሎ ይሠራል፣ ለሌባም ጥሩ መድኃኒት ነው!)
*
③) በአክሲዮን መስክ በልዩ ልዩ ዘርፎች የተደራጃችሁ ቢዝነሶች የአመራር ምርጫን ጨምሮ አጀንዳዎችን በአክሲዮን ድርሻ መጠን ሼር ሆልደሮችን ስታስመርጡ ሁሉም በአካል ካልተገኙላችሁ ወይም ተገኝተው ራሱ አሠራሩ አድካሚና የፍትሕ መጓደል ቅሬታ የሚነሳበት ከሆነ፤ ጽድት ያለ ሥራችሁን የሚያዘምን ሲስተም እሠራላችኋለሁ። ጸዴ ዌብሳይትና አፕ የምትፈልጉም ኑ!
(ባይሆን በክፍያ ነው እሺ¡ ቢዝነስ ላይ እያላችሁ ሶደቃ ይመስል በነፃ መስሏችሁ የምትመጡ እረፉ፤ ለሃብታም መሰደቅ ወንጀል አይሆንብኝም ወይ¡)

በርግጥም ትልቅ ዱዓእ!
ለሌሎች የምንሰጠውን ምክር ለነፍሳችን ብንተገብረው ኖሮ የት በደረስን ነበር። «አላህን ፍሩ!» ብሎ መካሪ ለነፍሱ አላህን ፈርቶ ሲገኝ ደስ ይል ነበር።
«አላህን መለመን ያለብን ለሰዎች የምንመክረውን አይነት ስብዕና እንዲሰጠን ነው።» አለ ወንድም አንዋር!

በነገራችን ላይ… እኛ ሃገር ላይ ደፋር ሆኖ ሰው ዘንድ የሚታወቀውና ሽፋን የሚያገኘው አዋቂ ሳይሆን ታዋቂ ነው። በእንቶ ፋንቶው ሁሉ ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚታወቅና ተከታታይ ያለው ሰው የመንግስትም ሆነ የአንዳንድ ኢስላማዊ የሚባሉ ሚዲያዎች ሽፋን እየተሰጠው፤ እንዲህ አይነት ምሁራን ወጣ ወጣ ባለማለታቸው ብቻ ህዝቡ ዘንድ ብዙም አይታወቁም። በዘርፉ ባሉ አዋቂዎች ዘንድ ግን ይሄው ትልቅ ቦታ አላቸው።
ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ የጂማ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር ቃል ኪዳን ሐሰን አባተ አንዱ ነው። በአካል ባላውቀውም የሆነ ጊዜ ፖስቼው አንዳንድ ጂማ ዩኒቨርስቲ የሚያውቁትና ያስተማራቸው ወንድምና እህቶች በዲኑም በትምህርቱም በውስጥ መጥተው በጎ አስተያየት ሲሰጡ ታዝቢያለሁ።
ፕሮፌሰሩ ፈታ ብሎ ቀለል ያለ ህይዎት መምራት የሚመቸውና የማወቁን ያክል ልታይ ልታይ የማይል ይመስላል። በርግጥ ያወቀ ሰው ስለሚሰክን ለዛም ይሆናል። ግን የሃገራችን ሚዲያዎችና ተቋማት እንዲህ መታወቅ የሚገባቸውን ምሁራን ወደፊት አምጥተው የሚገባቸውን ክብር ቢሰጧቸው፣ የሚያስፈልጓቸውን ፋሲሊቲዎች በማሟላት የምርምር ምህዳራቸውን የበለጠ እንዲያሰፉትና ማኅበረሰቡን እንዲጠቅሙ እድሉን ቢያመቻቹላቸው የተሻለ ነበር።
ፕሮፌሰር ቃልኪዳን ሐሰን የ2024 የስታንፎርድ እና ኤልሲቨር (Elsevier) የአለማችን Top 2% ሳይንቲስቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ተካቷል። በርግጥ ከአሁን በፊትም በዚሁ ደረጃ ውስጥ ነበር። በርታ!
የሪሰርች ሥራ አድካሚ ቢሆንም ወጥረህ ይዘኸዋል፤ ማሻ አላህ!

ባንኮች ከወለድ ነፃ አገልግሎት ላይ ስናስተላልፍም ሆነ ዝም ብለው የአገልግሎት ክፍያ እያሉ የሚቆርጡትን በቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ ማስቆም ግድ ይላል። ምክንያቱም እኛ ወለድ ብለን ስለማንወስድባቸው፤ እነርሱም የአገልግሎት ብለው ሊቆርጡብን አይገባም። አሊያ ቢዝነስ እስከ ሆነ ድረስ የማይቆርጡብንን ባንኮች ማጠናከር አለብን።