Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
89.3K subscribers
18.2K photos
4.87K videos
284 files
5.89K links
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።

ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢላሃና🤲🤲🤲

የበዳይዎች ሌሊት ረዘመ
طال ليل الظالمين!

እድሚያቸውን አሳጥርልን!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ⓵①⑧①]👌


#ቁርኣን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፈለስጢን ከወንዙ እስከ ባሕሩ ድረስ ነፃ ትሆናለች።
Palestine🇵🇸 will be free from the River to the Sea.


ሰንዓን የመን፣ ቶኪዮ ጃፓን፣ ባርሴሎና ስፔን፣ ባጝዳድ ኢራቅ፣ ቶሮንቶ ካናዳ፣ ሲድኔይ አውስትራሊያ፣ ኳላ ሉምፐር ማሌዢያ፣ ቪና አውስትራሊያ፣ ኒው ዮርክ አሜሪካ፣ ለንደን እንግሊዝ፣ አቴንስ ግሪክ…


The whole world stands with Palestine except the Zionists and their relatives.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አማን ጆርዳን፣ ማድሪድ ስፔን፣ ሲዖል ደቡብ ኮሪያ፣ ትሪፖሊ ሊብያ፣ ኢስላማባድ ፓኪስታን፣ ሳንቲያጎ ቺሊ፣ ቱኒስ ቱንዚያ…!
Audio
🔹رسالة إلى شعب الفلسطين

لفضلية الشيخ دكتور عثمان الخميس

ዶክተር ዑሥማን አል-ኸሚስ
لا حول ولا قوة الا بالله
لا حول ولا قوة الا بالله

والله لم يعُد القلب يحتمِل رُؤية المناظر 💧💧

قلبي بَـكى، ايه والله القلب بَكى قبل العين
تصلنا المقاطع و نراها فقط خِلال الجهاز، اذًا كيف بالذين عاشوا تلك اللحظات و فقدوا الأهالي و الأحباب و من أصبحوا بلا مأوى
حَزينة جدًا على كُل ما يحصل لأخواننا المسلمين وليس بـ اليد غير الدّعاء
• أوصي جميع الإخوة و الأخوات بالدّعاء للأمة الإسلامية🌧️
لعلّ دعوة أحدكم تُصيب و يستجيب الله

الله يزيدهم صَبر و همّة و ثبات
و يبشرهم بالنّصر على الأعداء

حسبي الله ونعم الوكيل على أعداء الإسلام💧💧

#لك_الله_يا_غزة

🌸🌧
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የእስራኤል ሚሳኤል መቃወሚያዎቹ ያልቻሉት የሐማሱ አልዘዋሪ ሚሳኤል!
تصاویری از پهباد انتحاری گردان‌های قسام موسوم به "زواری" که برای اولین بار در نبرد طوفان الاقصی به خدمت گرفته شده و در ایجاد پوشش برای نفوذ مبارزان این گردان به داخل اراضی اشغالی مشارکت داشت.
ስለ ፈለስጢን ምን አዲስ አለ⁉️
=====================
ስለ ፈለስጢን ጉዳይ በተወሰነ መልኩ መጻፌን እያቆምኩ የመጣሁት አካሄዱ ደስ ስላላለኝ ነው። ልክ የዛሬ ሳምንት ጽዮ'ናዊያኑ በጋዛ ነበልባሎች የሚገባቸውን ሲያገኙ ተደስተን ነበር። እስከ ተከታታይ 3 ቀናት ድረስም ጥሩ ነገር ነበር። ግን ቀስ በቀስ ጽዮ'ናዊያኑ እዝነትና ርኅራሄ በሌለበትና ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ተጠቅመው በጋዛ ሰማይ ላይ በየቀኑ የሚያርከፈክፉት ቦምብ ህፃነትና ሴቶችን፣ ቤታቸው በሰላም የተቀመጡ ያልታጠቁ ንጹሐንን መቅጠፉ ቀጠለና የፈለስጢናዊያን ሟቾች ቁጥር እጅጉኑ እያሻቀበ መጣ። ከትናንት በፊት ጀምሮ የፈለስጢናዊያን ሟቾች ቁጥር ከጽዮ'ናዊያኑ መብለጥ ጀመረ። በተለይ ትናንትና ከትናንት በፊት ደግሞ በብዙ የፍጥነት መጠን ጨመረ።

እስካሁን በይፋ በተለቀቀው መረጃ መሠረት 1900 ፈለስጢናዊያን ህይዎታቸውን አጥተዋል። ከመካከላቸው 614 ጨቅላ ህፃናትና 370 ሴቶች የሚገኙ ሲሆን 7696 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል። በትናንትናው ዕለት በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 20 ህፃናትን ጨምሮ 256 ፈለስጢናዊያን ሲገ'ደሉ 1788 የሚሆኑት ቆስለዋል። አጠቃላይ ከ420 ሺህ ያላነሰ ፈለስጢናዊ ተፈናቅሏል። በአይሁዳውያኑ በኩል 1500 የሚሆኑት የተገ'ደሉ ሲሆን ወደ 3400 ገደማ የሚሆኑ ቆስለዋል። የእነርሱ ሟቾች የእሳት ናቸው፤ የእኛዎቹን አላህ በጀነት ያበሽርልን።

የጦርነቱ አድማስ ከጋዛ ሰርጥ አልፎ ወደ በርካታ የዌስት ባንክና እየሩሳለም አካባቢዎች ተሸጋግሯል። ከሐማስ ጋር ተያያዥነት አላቸው የተባሉ አካላትን ሁሉ ማፈኑ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

እስራኤል ከአሜሪካ የተላከላት ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በእጇ የገባ ሲሆን የምድር ውጊያ ለመጀመርም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ጦሯን በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ አስፍራለች። ነገር ግን የእስራኤል ጦር ስነ ልቦናና ዝግጁነት ያላስተማመነውና ጋዛ ሰርጥ ውስጥ ከገባ በኋላ ምን እንደሚያጋጥመው መገመት ስላልቻለ አሜሪካ ለጊዜው የምድር ውጊያውን ገታ አድርጊውና በአየር ድብደባው ካዳከምሽ በኋላ ትቀጥያለሽ ብላታለች።

እስራኤል የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎችን በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ደቡብ ጋዛ ለቃችሁ ውጡ የሚል መልዕክት በአየር ላይ በትናለች፣ በድምፅም አስተላልፋለች። አንዳንዶች እውነት መስሏቸው ትናንት ከቤታቸው እንደወጡ በአየር ላይ በጣለችው ቦምብ ወደ 70 የሚሆኑትን ስትገ'ድል፤ ከ200 በላይ የሚሆኑትን አቁስላለች። ከነዚህ በተጨማሪ በሊባኒስ ድንበር ከሒዝቡልሏህ ጋር በገጠመችው ጦርነት ድንበር ላይ ጋዜጠኞችን በቦምብ ደብድባለች። ግን ማንም ጠየቂ የላትም። ገዳ'ዩ ሌላ ቢሆን ኖሮ ሲለፈልፉ የሚገኙት እነ አሜሪካ አስገ'ዳይ ስለሆኑ ማን ይቃወማታል?

እስራኤል ይህን ጦርነት ለመቋቋም ብላ ከተቀናቃኝ ቡድን መሪው ጋር በህብረት የጥምር መንግስት የመሠረተች ሲሆን፤ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጋር በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ4 ጊዜ በላይ ከተደረገው የስልክ ወሬ ባሻገር ቢሊንከንና የአሜሪካ ጦር መሪ በአካል እስራኤል ውስጥ ተፈኝተው ፈለስጢናውያንን ለመግ'ደል የሚያስፈልጋትን ሁሉ እንደሚያሟሉላት ቃል በተደጋጋሚ ቃል ገብተውላታል።
(የቢሊንከንን ጥልቅ ስሜት የተሞላበት ንግግር ስሙና ታዘቡ። የተመታችው ራሷ አሜሪካ ነው የሚመስለው። https://t.me/MuradTadesse/32206)

አሜሪካ በአካል ከላከችው የዘመናዊ ጦር ድጋፍ ባሻገር ሌላ ሃገር ፈለስጢናውያንን እንዳያግዝ ለማስፈራራት ግዙፉን የባህር ኃይሏን ወደ አካባቢው አስጠግታለች። ከርሷ ባሻገር እንግሊዝም ሁለት የጦር መርከቦችን አንቀሳቅሳለች። ጀርመንም እስራኤል ለዚህ የዘር ማጽ'ዳት ወንጀሏ ያግዟት ዘንድ ልጠቀምባቸው ያለቻትን ዘመናዊ ድሮኖች እሰጣለሁ ብላለች።

የአሜሪካው ቢሊንከን ከእስራኤል ጉብኝቱ ባሻገር ወደ ዓረብ ሃገራት በማምራት ሐማስን በማውገዝ መግለጫ እንዲሰጡ ለማድረግና ፈለስጢናውያንን እንዳያግዙ ጫና ለማድረግና ሼም ለማሲያዝ ሞክሯል። ሳዑዲ ዓረቢያ ሐማስን ታወግዝ ዘንድ በይፋ የቀረበላትን ጥሪ እንደማትቀበል ገልጻ የፈለስጢናውያንን መብት እስከሚከበርና መሬታቸው እስከሚመለስ፣ ምስራቅ እየሩሳለምን ዋና ከተማቸው አድርገው ሃገራቸውን እስኪገነቡ ድረስ አጋርነቷን እንደምትቀጥልና በጋዛ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ከበባና ጭፍ'ጨፋ እንደምትቃወም አሳውቃለች። ኳታርና ግብፅም መፍትሄው ጦርነትን አቁሞ መደራደር እንደሆነ ገልጸዋል። ግብፅ ግን ስደተኞች እንዳይገቡባት ነው መሰል የራፋን ማቋረጫ ዘግታለች።

ቱርክን ጨምሮ የዐረብ ሃገራት ጦርነቱ ቆሞ ድርድር ይደረግ ከማለት ውጭ አለፍ ያለ ነገር እስካሁን አላሳዩም። የጋዛ ህዝብም ከመብራት፣ ከመድኃኒት አቅርቦት፣ ከምግብ፣ ከውሃና ከነዳጅ ታግቶ ቀናትን እየፈጀ ነው። በየቀኑ በሚጎርፈው የሟቾችና ቁስለኞች ብዛት የጋዛ ሆስፒታሎች የሞሉ ሲሆን ነዳጅ ሊያቆምባቸው ስለሆነ ቁስለኞችን ማከም ስለማይችሉ በጋዛ ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይፈጠር ተሰግቷል።

እስራኤል እስካሁን በጋዛ ላይ 4 ሺህ ቶን የሚመዝኑ 6 ሺህ ቦምቦችን መጣሏን አሳውቃለች። ይህም አሜሪካ አይኤስአይኤስን ለማጥፋት ከተጠቀመችው የበዛ ነው። ይህ እስራኤል በ1 ሳምንት ያዘነበችው ቦምብ አሜሪካ በአፍጋኒስታን 1 አመት ስትቆይ ከተጠቀመችው ይበልጣል። አስቡት! የጋዛን ጽናት!

የእስራኤል አላማ አንድ ነው። ጋዛ በየጊዜው እየተተናኮሰ ከሚያሰጋኝ፤ ባለፈ ሳምንት የጀመረኝ እርሱ ስለሆነ ተበዳይ ነኝ በሚል ሽፋን እነ አሜሪካም ከጎኔ ስለሆኑ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ሐማስን ከምድረ ገፅ በማጥፋት ሰላሜን ማግኘት አለብኝ ነው። ወዳጇ አሜሪካም እያለች ያለችው የተከፈለው ዋጋ ተከፍሎ ሐማስ ለወዳጄ እስራኤል ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ መቀበር አለበት ነው።

እስራኤልም ይህን ሁሉ ቦምብ እያዘነበች ያለችው የጋዛን ወታደራዊ መሠረት ለመምታት በማሰብና የፈለስጢናዊ ሟቾች ቁጥር ከእርሷ አንሶ ስለነበር መሸነፍ ስለሆነባት ለማስበለጥ ነበር።
ከአሁን አሁን የጋዛን መሠረት አገኘሁት እያለች የጠረጠረችውን ቦታ ሁሉ በቦምብ እያወደመች ነው። በሚያሳዝን መልኩ በርካታ ውብ ህንፃዎች ከአፈር ጋር ተቀላቅለዋል። መስጅድና የትኛውም መሠረተ ልማት አልቀራትም። አሁን ደግሞ ጭራሽ የአልአዋድ ሆስፒታልን ልመታ ስለሆነ ቁስለኞቹን ቶሎ ያውጣ ብላለች። ሐማስ ሮኬት የሚተኩሰው ከዚያ መስሏታል መሰል።


የአሜሪካውም ሲአይኤ፣ የራሷም ወናፉ ሞሳድ እስካሁን ያልተገለጠላቸው ጘይብ የሆነባቸው ሚስጥር «ሐማስ ሮኬት እያስወነጨፈ ያለው ከየት ሆኖ ነው?» የሚለው ነው። የአሜሪካውም ደህንነት ያለው ለኛም አልገባንም ነው። አሁንም አይግባችሁ አቦ!

የሚገርመው ደግሞ ሐማስ ከሚያስወነጭፋቸው ሚሳኤሎች መካከል «አል-ዘዋሪ» የተሰኘውን ሚሳኤል በአኩሬሲያቸው የተመሰከረላቸው የእስራኤሎቹ የተተኮሰን ሚሳኤል መቃወሚያ አይረን ዶሞች መቋቋም ያልቻሉት መሆኑ ነው።
(ራሱ ሐማስ የለቀቀውን ሚሳኤሉን በዚህ ቪድዮ ማየት ትችላላችሁ። https://t.me/MuradTadesse/32238)

ቢጨንቃቸው የአሜሪካው ወታደራዊ ቴክኒካል ክፍል ለነዚህ አሉ ለተባሉ ስመጥር መቃወሚያዎች ናቸው ለተባለላቸው ሚሳኤል ኢንተርሴፕተሮች ጥገና አደረገ። ግን አሁንም አልዘዋሪ ሲላክባቸው አይረንነታቸው ወደ ፕላስቲክነት መቀየሩ አልቀረም። እንዳውም አንዱ የአሜሪካ ባለስልጣን ግራ ቢገባው አይኤሶችን ስንዋጋ ፊታቸው ላይ ሰይጣን ነገር አለ፤ ሐማስ ደግሞ ከነዚያ የባሰ ሰይጣን ነገር ያለበት ነው ብሏል። መንፈስ ነው የሆኑባቸው።
ያኔ እስራኤል አቅሟ በደንብ ሳይጠገን በ6 ቀኑ የዐረብ እስራኤል ጦርነት ጊዜ ከ3 ሃገራት ጋር ገጥማ ነበር። ዛሬ ግን በአንድት ጠባብ ሰርጥ ውስጥ የሚገኝ ቡድን ይሄው ከነዚያ ሁሉ አጋሮቿና ከዚያ ሁሉ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዋ ጋር በጽናት አንድ ሳምንትን ቀጥ አድርጎ ይዟታል። አሁንም ቢሆን በጋዛ ሰርጥ ዙሪያና በዋና ከተማዋ ቴል አቪቭ ጭምር ሚሳኤል ማስወንጨፉን አላቆመም። ትናንት ማታም ዋና ከተማዋ ላይ የሚገኝ ህንፃንና ተሽከርካሪዎችን አመድ አድርጎባታል። እርሷ ግን «ቆይ የት ሆኖ ነው የሚያስወነጭፈው? እንደት እስካሁን በዛች ጠባብ ከተማ ላይ ካረፈ ከ6 ሺህ ቦምብ መካከል አንዱ እንኳ በድንገት አይመታውም?» ብላ ዛሬም አዳሯን ድብደባዋን አጠናክራ ቀጥላለች።

የሚያሳዝነው በዳይና ወራ'ሪ ለሆነችው እስራኤል ይሄ ሁሉ ስመ ዲሞክራሲ ኃያላን አጋር ከጎኗ ሲቆም፤ ተበዳይና ተወራሪ ለሆኑት ፈለስጢናዊያን ከሚስኪኖች ዱዓእ ውጭ ከጎናቸው በግልፅ የሚቆምና የጦር ድጋፍ የሚያደርግ አንድ አንኳ ሃገር መጥፋቱ! የወታደር ድጋፍ ማድረግና መዋጋቱ ቀርቶ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ቢያገኙ የጽዮ'ናዊቷ እድሜዋ ባልረዘመ ነበር። ሰው ለበዳይ ሲያግዝ ሼም ያልያዘውን ለተበዳይ ማገዝ እንደት ሼም ያሲዛል! ሃብት እንደሁ እድሜ ለነዳጅ አለ! ምን ጎድሎ!

ያም ሆነ ይህ የህፃናትና የሴቶች እንዲሁም የንጹሐን ሞት ከልብ ያሳዝናል። ሌላው'ማ ቢገድ'ልም ቢመለትም አንደየውኑ አውቆ ገብቶበታል። ደግሞም ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከሕክምናና መሰል አገልግሎቶች መታፈናቸው ያሳዝናል። ጦርነቱ ምነው ባልተጀመረም አንልም፤ አንደዜ ተጀምሯልና! ባይጀመርም በየአመቱ ሞትና ቁስለኛ ፈለስጢን ላይ የተለመደ ነው። የዑለማዎች ብይን እንዳለ ሆኖ አንዳንዴ ሞት ላልቀረ ነገር ገድ'ሎ መሞት ሳይሻል አይቀርም። ቀስ በቀስ ግን ጋዛዊያንን በሐመስ ሽፋን አፈናቅለው ግዛታቸውን ባላስፋፉና ወደ ጎረቤት ሃገራትም ባልተሻገሩ። ግን እስከየትም ቢስፋፉ በቀኑ መጨረሻ ወቅት መሸነፋቸው 100% አይቀሬ ነው። የአላህና መልዕክተኛው ቃል ኪዳን ስለሆነ።

ያ እነርሱ የሚሸነፉበት የውርደት ጊዜ ለኛ ትውልድ ክብር የሚገባው ከሆነ ይሸነፋሉ። አሊያ ግን ይህ የነርሱ መሸነፍ ክብር የሚገባው ሌላ ተተኪ ትውልድ ሲመጣ ያነ ጊዚያቸው ማክተሙ አይቀርም። ኢንሻ አላህ!

አሁን ላይ እኛ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ያለን ብቸኛው ጥቅም ከልብ መልካም ዱዓእ ማድረግ፣ የጽዮ'ናዊያንና አጋሮቿ እድሜ እንዳይረዝም፣ የጋዛዊያን የጨለማ ሌሊት እንዳይረዝም ከልብ ዱዓእ እናድርግ።


እንደ ጥቅል ደግሞ የሚያሳዝነው የኛዎቹ ሞት መብዛትና መቼ ነው የሚያቆመው የሚለው እንጂ እስራኤልን በዚህ ጦርነት በምንም መልኩ መጠገን የማትችለው፣ አይደለም በጠላቶቿ በወዳጆቿ ዘንድ ጭምር ከጉራና ከስም ውጭ ከነ ስለላ ድርጅቷ ወናፍ (ስም ብቻ፣ ባዶ) መሆኗ ታይቷል። ዛሬ ላይ ባያሸንፏት እንኳ ለሌላ ጊዜ ተናቦና ተጠናክሮ ለያዛት አካል አንድ ቀን የማትፈጅ ጭብጥ መሆኗ ታይቷል። ሐማስ ውርደትን ከነ ካባው ነው ያለበሳት። ያንን ስሟን ለማስመለስ አሜሪካን ሌት ከቀን እየለመነች ብትታገልም አንደዜ ስላለፈ ማስመለስ አልቻለችም። የዛሬ ሳምንት ልክ ሐማስ እንደጀመራት ወዲያው በቁጥጥር ስር ታውለዋለች ተብሎ ቢታሰብም አልሆነም። ግን እንቀጠለ ነው።


የጋዛ ህንፃዎችም በአላህ ፈቃድ ይገነባሉ፣ የእስራኤላዊያን ዱንያዊ ውርደት ግን በምንም አይገነባም፣ በአኺራህም ይዋረዳሉ። ኢንሻ አላህ! አላህ ሟቾቻችንን የጀነት ያድርጋቸው፤ በህይዎት ያሉትን በቃችሁ ይበላቸው፣ የታመሙትን ቶሎ መሻርን ይወፍቃቸው፣ በጠላቶቻቸው ላይ ድልን ያቀዳጃቸው።

||
t.me/MuradTadesse