Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
86.6K subscribers
17.6K photos
4.54K videos
281 files
5.69K links
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።

ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመስጅድ ላይ ቸርች ግንባታ
=====================
ጎንደር ውስጥ ከ800 በላይ አመታት ያስቆጠረ የሙስሊሞች ሐሪማ ቤተ ክርስቲያን ተገነባበት ሲባል ሰምተው አዝማች ለመያዝ አስበው ነው መሰል፤ የሐዋሳ ጽን'ፈኞች ከመስጅድ አጠገብ የግለሰብ ቤት ተከራይተው ሲረብሹ ከርመው ሙስሊሙ ቢያመለክትም የሚያስቆማቸው የመንግስት አካል ጠፍቶ ጭራሽ ዛሬ መጥተው የመስጅዱን መግቢያና መውጫ አጥረው ቸርች ለመገንባት ረብሻ ፈጥረዋል።

ህዝበ ሙስሊሙም ጉዳዩን ለማስቆም ወደ ጸጥታ አካላት ቢደውሉም ወዲያውኑ አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ይህ መስጅድ ከ13 አመታት በፊት 2003 ላይ ህጋዊ ፈቃድ ተሰጥቶት የተገነባ ነው።

በተለይም በዚህና በሐድያ አካባቢ ያሉ የመንግስት አካላት ሙስሊሞች ላይ ያላችሁን አመለካከት ብታስተካክሉ ይሻላል።


ቪድዮ፦ ጽንፈኞቹ ቦታውን ሲያጥሩና ህዝበ ሙስሊሙ ሲያስቆማቸው የሚያሳይ

||
t.me/MuradTadesse
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
በመስጅድ ላይ ቸርች ግንባታ ===================== ጎንደር ውስጥ ከ800 በላይ አመታት ያስቆጠረ የሙስሊሞች ሐሪማ ቤተ ክርስቲያን ተገነባበት ሲባል ሰምተው አዝማች ለመያዝ አስበው ነው መሰል፤ የሐዋሳ ጽን'ፈኞች ከመስጅድ አጠገብ የግለሰብ ቤት ተከራይተው ሲረብሹ ከርመው ሙስሊሙ ቢያመለክትም የሚያስቆማቸው የመንግስት አካል ጠፍቶ ጭራሽ ዛሬ መጥተው የመስጅዱን መግቢያና መውጫ አጥረው ቸርች…
ወደየት እያመራን ይሆን⁉️
=================
የነ ሮበርትስ (Oral Roberts) የብልፅግና ወንጌል (The Prosperity Gospel (PG)) ወደየት ይወስደን ይሆን?
||
እነሆ በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ከተማ በሚገኘው ኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ በተማሪዎችና በመምህራን እንዲሁም ከጀርባ በመንግስት አካላት ድጋፍ ባለው መልኩ ባለ 32 ገፅ የፕሮቴስታንት እምነትን የሚሰብክ፣ እስልምናን የሚያንቋሽሽ፣ ውዱን ነቢይ ﷺ የሚሳደብ መርዘኛ ጽሑፍ ታትሞ በተማሪዎች ዘንድ እየተሰራጨ እንደሆነና ሙስሊም ተማሪዎች በግደታ ጭምር እምነታቸውን እንዲቀይሩ እስከማስገደድ ድረስ የዘለቀ ጽንፈኝነት መከሰቱን እየሰማን ነው።

ይሄ ነገር በየቦታው ትንኮሳው በዛና ወደየት ልናመራ ይሆን? ምንድን ነው መፍትሄው? መጅሊስ በዚህ ጉዳይ ከምሁራን ጋር ቁጭ ብሎ በሩን ዘግቶ ተነጋግሮ አንድ ቆፍጠን ያለ አቋም መያዝ የለበትም ትላላችሁ?

አላህ ከሴራቸው ይጠብቀን! በተለይ የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ በዚህ ጉዳይ ያለውን ነገር በአስቸኳይ አናግሮ ጉዳዩን ለህዝብ ማሳወቅ ይጠበቅበታል።


||
t.me/MuradTadesse
በመንግስትና በኃይማኖቶች መካከል ስላለውና ስለሚኖረው ግንኙነት በስፋት የሚዳስሰው ባለ 160+ ገፅ ረቂቅ አዋጅ በሶፍት ኮፒ (PDF) ደርሶኛል።

ላንብበውና በቴሌግራም ቻነሌ (https://t.me/MuradTadesse) ላይ እለቀዋለሁ። እናንተም አንብባችሁ ከመፅደቁ በፊት መስተካከል ያለበትን ሃሳብ ከወዲሁ እንዲስተካከል ማድረግ አለብን። አይደለም ዛሬ ትናንትም በዚያ አፋኝ ስርዓት ወቅት ይህንን ኡማ ማስቆም አልተቻለም፤ ወደፊትም አይቻልም።
①) 🕋 ሐጅ እና ዑምራ

🎙 በኡስታዝ ሰልሰቢል ሐጂ ዙመካን

🔗 https://youtu.be/fQICqKHLJbk


②) የሐጅ ግቦች

በኡስታዝ ተውፊቅ በደዊ
https://youtu.be/QnW0niD2j0I?si=3KLxYEODTthulCGw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ⓵⑥②①]👌


#ቁርኣን

القرآن الكريم راحة نفسية
 

ከታች የምትመለከቱት ልጅ

ስም : ዐብዱልዋሲዕ ሚስባሕ
     የጠፋው አሸዋ ሜዳ ጅብሪል መስጂድ አካባቢ በቀን  17/08/2016 አስር ላይ   ሐሙስ ነው የጠፋው፡፡
የዛን ቀን የለበሰው አረንጓዴ ቱታ ነው፡፡
ከጠፋ ሳምንቱ፡
የአዕምሮ ህመምተኛ ነው፡፡

   

ያየ ሰው ካለ በዚ ስልክ ይሳውቀን፡፡

  0936364343
0910848775
በነገራችን ላይ… ለተቋሞቻችሁ ወይም ለግላችሁ ብቁ ሠራተኞችን ማግኘት ስትፈልጉ ሐላል የሥራ ማስታወቂያ #በነፃ ለማስለቀቅ ከፈለጋችሁ፤ ይህን የቴሌግራም ቻነል https://t.me/HalalDigitalNetwork ተቀላቀሉ።

ሥራ ፈላጊዎች ወይም ማሻሻል የምትፈልጉም ተቀላቀሉ።
Secularism .pdf
65.3 MB
የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ጥናት
===================

የመንግስት እና ሃይማኖት ግንኙነት በኢትዮጵያ፤ ትናንት ዛሬ እና ነገ

አዘጋጅ፦ የፌዴራል የፍትሕና የህግ ኢንስቲትዩት

የሶፍት ኮፒ (PDF) መገኛ ሊንክ፦ https://t.me/MuradTadesse/35708


እያንዳንዷን መስመር ምን ታሲዛለች፣ ምን ትርጉም አላት፣ ምን ተፈልጎባት ነው ብላችሁ በጥንቃቄና በጥሞና አንብቡት። በተለይም ከኡማው ጥቅምና ጉዳት አንፃር!
||
t.me/MuradTadesse
x.com/MuradTadesse
fb.com/MuradTadesse
ummalife.com/MuradTadesse
tiktok.com/@MuradTadesse
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
Photo
በካንሰር በሽታ ለታመመው የራያው ወንድማችን አሚር 3.3+ ሚሊዮን ብር ተሰባስቦለታል። በአላህ ፈቃድ በቅርቡ ወደ ሃገረ ቱርክ አቅንቶ ሕክምናውን የሚከታተል ይሆናል። ከምንም በላይ መልካም ዱዓችሁን ይሻልና በመልካም ዱዓችሁ አስታውሱት። ገንዘብ በማዋጣት ረገድ አነሰ በዛ ሳትሉ ስትረባረቡ የነበራችሁ ወንድምና እህቶች፣ እናቶችና አባቶች በሙሉ፤ አላህ የበለጠ ይተካችሁ፣ እናንተንም፣ ቤተሰባችሁንም፣ ወዳጅ ዘመዳችሁንም አላህ ከመሰል ህመምና ከመጥፎ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ።

ባረከ-ል'ሏሁ ፊኩም!
ደግሞ ለአላህ ብዬ እወዳችኋለሁስ፤ በተለይ በኸይር ሥራ ላይ ያላችሁ የነቃ ተሳትፎ ደስ ይላል፤ ለብዙዎች ጭንቀትና ስቃይ መገላገል ሰበብ ሆናችኋል። ኢኽላሱን ሰጥቶ ሶደቃችሁን አላህ ለዚያ ጭንቅ ቀን መሰተሪያ ጥላ ያድርግላችሁ።
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
Secularism .pdf
የሃይማኖት ጉዳዮችን በሚመለከት እየተረቀቀ ባለው አዋጅ ላይ ቅሬታ ቀረበ

(ሪፓርተር ጋዜጣ )

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና የወንጌል አማኞች ካውንስል በተናጠል ለሰላም ሚኒስቴር በላኩት ደብዳቤ፣ አዲስ በመረቀቅ ላይ ያለው የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ ላይ ያላቸውን ቅሬታ አሰሙ፡፡

የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና የወንጌል አማኞች ካውንስል ረቂቅ አዋጁ ባይደርሳቸውም፣ ከዚህ ቀደም የአዋጁን መንፈስ በቃል በተረዱት መሠረት ሊካተቱ ይገባቸዋል ያሏቸውን ምክረ ሐሳቦች፣ አስተያየቶችና ቅሬታዎች ለሰላም ሚኒስቴር መላካቸውን ሪፖርተር የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡

የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሚያዝያ 28 ቀን 2016 E.C. ለሰላም ሚኒስቴር በላከውና ሪፖርተር የተመለከተው ምክረ ሐሳብ፣ ረቂቅ አዋጁ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በዘመናት ትግል ለማረጋገጥ እየሞከሩ ያሉትንና በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የዜጎች እኩልነትና የሃይማኖት ነፃነት መብቶችን የሚጥስ፣ ሙስሊሞች በዓለም አቀፍ ሕግ የተቀመጠላቸውን የሃይማኖት ነፃነትና ሰብዓዊ መብቶች የሚገረስስ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብሏል፡፡

‹‹መንግሥት፣ የመንግሥትን ከሃይማኖት የመለያየትና የዜጎችን ሃይማኖታዊ ነፃነትና እኩልነት መብት መርሆዎች ዝርዝር ለመደንገግ የጀመረውን እንቅስቃሴ እናደንቃለን፡፡ ሆኖም ለረቂቁ ግብዓት የሚሆኑ ውይይቶች እንደሚኖሩ በመጠበቅ ላይ ባለንበት ወቅት መጀመሩን ባላወቅነው ረቂቅ ላይ ለመወያየት ሚያዝያ 3 ቀን 2016 E.C. በሰላም ሚኒስቴር መጋበዛችን ቅሬታ ፈጥሮብናል፤›› ብሏል፡፡

ምክር ቤቱ የረቂቁን ቅጂ አለማግኘቱን አስታውቆ፣ ይህ ባልሆነበት አስተያየቱን መጠየቁ ለሚያቀርበው ግብዓት ተገቢውን ትኩረት እንዳልተሰጠና ለይስሙላ መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ በማለት ገልጿል፡፡ ምክር ቤቱ አስተያየቱን በጽሑፍ እስኪሰጥ ሳይጠበቅ የፍትሕ ሚኒስቴር ባልደረቦች ከቀናት በኋላ ወደ ክልል ከተሞች ለውይይት ማቅረብ እንደሚጀምሩ መግለጻቸውንም ጠቁሟል፡፡ በተያዘው የግንቦት ወር አጋማሽ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ፍትሕ ሚኒስቴር ረቂቁን ለማቅረብ ማቀዱን ገልጿል፡፡

ረቂቁ የሃይማኖቶችንና የሃይማኖት ተከታዮችን እኩልነት እንዳይረጋገጥ የሚያደርግ፣ የእስልምና መሠረታዊ አስተምህሮዎችን ከግምት ያላስገባ፣ ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ከሃይማኖቱና ከዜግነት ተሳትፎው እንዲመርጥ የሚያስገድድ፣ ለመንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ያልተገባ ተቆጣጣሪነት የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ ምክር ቤቱ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

ረቂቁ የያዛቸውን ዝርዝር ጉዳዮች በሚመለከትም ሃይማኖታዊ ምልክቶችን እንደ የቤተ እምነቱ አስገዳጅ ሕግጋቶች ልዩ ሁኔታዎችን መደንገግ ሲገባው ሃይማኖታዊ መገለጫዎችን ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ቤትና ከሥራ ገበታ የሚያስወግዱ ድንጋጌዎችን መያዙ፣ እንዲሁም የሙስሊም ሴቶችን ሰብዓዊ መብት በግልጽና በጥቅሉ የሚጥስ መሆኑን እንደተመለከተ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በትምህርት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ የጋራ አምልኮ ተግባራትን መከልከል፣ ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ከእምነቱና ከሥራው ወይም ከእምነቱና ከትምህርቱ እንዲመርጥ የሚያስገድድ መሆኑ፣ እንዲሁም አምልኮን ከተፈቀደለት ቦታ ውጪ ማከናወን መከልከሉ፣ የእምነት ነፃነት መብቶች አተገባበር ላይ ጫና የሚያሳድር መሆኑን ገልጿል፡፡

የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ሐሳብ የሚጋራ ደብዳቤ ዓርብ ግንቦት 2 ቀን 2016 E.C. ለሰላም ሚኒስቴር የላከው ደግሞ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ነው፡፡ ካውንስሉ ረቂቅ አዋጁ አባላቱን በተመለከተ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1208/2012 የሚቃረን መሆኑን ገልጾ፣ ሕገ መንግሥታዊ የሆኑ የእምነትና የሃይማኖት ነፃነት መብትና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን የሚመለከት በመሆኑ፣ ረቂቁን ለማየት እንዲሰጠው ቢጠይቅም እንዳልተሰጠው አስረድቷል፡፡

ረቂቁ በቤት ውስጥ የሚደረግን አምልኮና የአደባባይ ስብከትን የሚከለክል መሆኑን ካውንስሉ ከሰላም ሚኒስቴርና ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በነበረው ውይይት ወቅት በተደረገለት ገለጻ መረዳቱን በመግለጽ፣ ይህም በቀጥታ የወንጌል አማኞችን የሚነካና ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የሌለው መሆኑን አስታውቋል፡፡

በሕገ መንግሥቱ መሠረት ዜጎች የአምልኮ ሥርዓት ለመፈጸም በመንግሥት አካል የግድ መመዝገብ የማያስፈልጋቸው ቢሆንም፣ በረቂቁ ውስጥ ግን የነፃነቱ ሰጪና ነሺ የምዝገባው መኖር አድርጎ ማስቀመጡ ትክልል አለመሆኑን፣ እንዲሁም ከመፅደቁ በፊትም ካውንስሉ እንዲስተካከሉ በደብዳቤ የጠየቃቸው ጉዳዮች እንዲስተካከሉ አሳስቧል፡፡

የሁለቱን የእምነት ተቋማት ምክረ ሐሳብ፣ አስተያየትና ቅሬታ አስመልክቶ የሰላም ሚኒስቴር ምላሽና አስተያየት ለማካተት የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡
Audio
11 ምላሾች በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ || NesihaTv
ወንድማችን አስቸኳይ ድጋፋችሁን ይሻል
============================
(እንደተለመደው ላስቸግራችሁ፤ ሙስሊም ከኸይር ነገር አይጠግብምና ሰሞኑን ስለደጋገምኩባችሁ እንዳትሰላቹ። ጉሮሮው ላይ በተፈጠረ አሰቃቂው የካንሰር በሽታ ለሚሰቃየው ወንድማችን እንድረስለት!)
||
በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ወንድማችን ዐብደ-ል'ሏህ በድሩ ይባላል። ወንድም ዐብደ-ል'ሏህ የዛሬን አያደርገውና የአላህ ውሳኔ ሆኖ ዛሬ ላይ ከአላህ በታች የእኛን እርዳታ ቢሻም፤ ትናንት ግን በወሎ፣ በአፋር፣ በባሌ፣ በሲዳማና በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉና ለተቸገሩ ወገኖቻችን በራሱ መኪና ጭምር እየተንቀሳቀሰ ድጋፍ ከሚያደርጉት መካከል ነበር።

አሁን ላይ የነበረበት ቶንሲል ጉሮሮው ላይ ወደ ካንሰር በሽታ ተቀይሮበት ታሟል። ወደ ሃገረ ቱርክ በማምራት በተደጋጋሚ የጨረር ሕክምናን ጨምሮ በርካታ ሕክምናዎችን ሞክሯል።
እህቱ እንደነገረችኝ ከሆነ እስካሁን ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ጨርሰዋል። ዐብደ-ል'ሏህ ከራሱ ንብረት አልፎ የቤተሰቡን፣ የወዳጆቹን ሳይቀር ተጠቅሟል።

ይህን ያደረገው ወደ ህዝብ ፊት ላለመምጣት በራሱና በቤተሰቡ አቅም እዛው ከጨረሰ ለመሞከር ነበር። ግን የአላህ ውሳኔ ሆነና አልቻለም። አሁን ላይ ዶክተሮቹ በሰጡት ተስፋ መሠረት በአላህ ፈቃድ ከ90% በላይ የመዳን እድል አለው። ነገር ግን በመሃል ገንዘቡን ሲያሟጥጥ የተወሰነ ሕክምናው ተስተጓጉሎ ስለነበር አሁን ላይ ፈጥኖ አዲሱን ሕክምና ማግኘት አለበት።

ወንድማችን አሁን ላይ ህመሙ ጉሮሮውን ስለዘጋው ምግብ የሚወስደው በጎድን በቱቦ መልክ ነው። አስቡት! በሽታው አሰቃቂው ካንሰር! የታመመበት ቦታ ጉሮሮው! አላሁ-ል-ሙስተዓን! አስባችሁታል ስቃዩን!

ወንድማችን አሁን ላይ አዲሱን ሕክምና ለመጀመር 5 ሚሊዮን ብር ያስፈልግሃል ብለውታልና ሁላችንም ተረባርበን እንሙላለት። ዐብደ-ል'ሏህና ቤተሰቡ ወደኛ ከመምጣታቸው በፊት የሚችሉትን ሁሉ አድርገው ነበር። ግን ዛሬ ላይ እገዛችሁን ይሻሉ። በአላህ ፈቃድ እናንተም አታሳፍሯቸውም።

በሽታው ካንሰር ስለሆነ መታከም ወደማይችል የከፋ ደረጃ ሳይሸጋገርበት ፈጥነን እናሳክመው። ጊዜ የማይሰጥ ዘግናኝ በሽታ ስለሆነ እንጂ ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስላስቸገርኳችሁ አሁን ላይ ባሳረፍኳችሁ ነበር። ግን ስቃዩ ለዐብደ-ል'ሏህ አላረፈለትምና ምንዳ የሚያስገኝ ሶደቃ ስለሆነ ሚስኪኖችን ሲረዳ ለነበረው ዐብደ-ል'ሏህ ስቃይ መወገድ ሰበብ እንሁነው፤ አላህም ከዚያች ጭንቅ ቀን ያወጣናል ኢንሻ አላህ። ገንዘብ እንደሆነ እንደምታዩት ነው። አላህ ይጠብቀንና ነገ ማንኛችን ምን ላይ ወድቀን ምን እንደምንሆን አናውቅምና ዛሬ ላይ ከገንዘባችን አነሰ በዛ ሳንል ወደ አኺራችን በሶደቃ መልክ እናሳልፍ።

የዐብደ-ል'ሏህ ሁለት ህፃናት ልጆቹና ባለቤቱ የአባታቸውንና የባለቤቷን መዳን አላህ እናንተን ሰበብ እንዲያደርግላቸው በገንዘባችሁና በዱዓችሁ እንድታግዟቸው ጠይቀዋል።


በባለቤቱ እና በስሙ በተከፈቱት የባንክ አማራጮች ድጋፍ በማድረግ እናግዘው።

የአካውንት ስም፦ ፋጡማ ነስሩ ሐሰን
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000307233968 
አዋሽ ባንክ፦       014251336744800
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል፦ 1338403800001
አቢሲኒያ፦  186746977
ዘምዘም ባንክ፦  0040743420101
ንብ ባንክ፦ 7000057909922
ዳሽን ባንክ፦  2907571242711

የአካውንት ስም፦ ዐብደ-ል'ሏህ  በድሩ
ሂጅራ ባንክ፥ 1000643150001


ለኸይር ማነሳሻ ስለሚጠቅም የምትሰድቁበትን ደረሰኝ ኮመንት ላይ ወይም በውስጥ መስመር t.me/Murad_Tadesse ላይ ላኩልኝ።


አነሰ በዛ ሳትሉ ወንድማችንን ተረባርበን እናሳክመው፤ የቻለ በገንዘቡ፣ ይህን ያልቻለ መልዕክቱን በማሰራጨትና በመልካም ዱዓው አይርሳው።


||
t.me/MuradTadesse
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ወንድማችን አስቸኳይ ድጋፋችሁን ይሻል ============================ (እንደተለመደው ላስቸግራችሁ፤ ሙስሊም ከኸይር ነገር አይጠግብምና ሰሞኑን ስለደጋገምኩባችሁ እንዳትሰላቹ። ጉሮሮው ላይ በተፈጠረ አሰቃቂው የካንሰር በሽታ ለሚሰቃየው ወንድማችን እንድረስለት!) || በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ወንድማችን ዐብደ-ል'ሏህ በድሩ ይባላል። ወንድም ዐብደ-ል'ሏህ የዛሬን አያደርገውና የአላህ ውሳኔ…
ከዚህ ሁሉ ወንድምና እህት፣ አባትና እናት መካከል 2 ሺህ ብር የሚያዋጣ 2 ሺህ ሰው ይጠፋል ወይ?



የዚህ ወንድማችን ነገር ሳስበው ይበልጥ ያሳዝናል።
አስቡት! ስሙ ሲጠራ ራሱ የሚሰቀጥጠን የካንሰር ህመም ነው እያሰቃየው የሚገኘው። ያውም ሌላ የሰውነት ክፍሉ ላይ ሳይሆን ጉሮሮው ላይ። ምግብ እንኳ መመገብ ዘግቶት በጎኑ በተደረገለት ቱቦ በኩል ነው ምግብ ወደ ሰውነቱ የሚገባው።

ይህ ወንድም እኛን አሳክሙኝ ከማለቱ በፊት እንኳን የራሱን በዙሪያው ያሉ ሰዎችን ገንዘብ ተጠቅሟል። ግን ሊበቃው ስላልቻለ የሰው ፊት ማየት ግድ ሆኖበታል። ከሁለት ህፃናት ልጆቹና ባለቤቱ ጋር ሰቃዩን እየገፋ ነው።

የወንድማችን ህመሙ ከዚህ ወደከፋ ደረጃ ሳይሸጋገርበት እንተባበርና ፈጥንን እናሳክመው።


ሐቂቃ ቀናነት ካለ'ኮ ከሚያስፈልገው 5 ሚሊዮን ብር መካከል የጎደለው 4 ሚሊዮን ገደማውን እዚህ እኔ ቻነል ላይ ካላችሁት 85,000+ ውስጥ 20 ሺህ የምትሆኑት በነቂስ 200 ብር ብቻ ብታዋጡ የሚሸፈን ነበር። ወይም 2000 የምትሆኑት በነፍስ ወከፍ 2000 ብር ብታዋጡ ይሞላለታል።

እስኪ አሁን ይተግበር! ስልካችሁን ወጣ አድርጉት! ወንድማችን ትናንት መኪናውን ይዞ የተቸገረን ሲረዳ የነበረ ነው። የኛንስ ነገ ማን ያውቃል?

እስኪ የ2000ውን ቻሌንጅ "ሀ" ብሎ የሰደቃ በሩን የሚከፍተው ጀግና ማነው? ከዚህም በላይ ከዚህም በታች አላህ ያገራልንን ያክል በማዋጣት እናሳክመው።


የአካውንት ስም፦ ፋጡማ ነስሩ ሐሰን
CBE፦ 1000307233968 
አዋሽ ፦   014251336744800
BOA፦  186746977
ዘምዘም፦  0040743420101

ዐብደ-ል'ሏህ  በድሩ
ሂጅራ፥ 1000643150001


ለማነሳሻ ስለሚጠቅም ደረሰኙን ኮመንት ላይ ወይም በውስጥ መስመር t.me/Murad_Tadesse ላይ ላኩልኝ።
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ወንድማችን አስቸኳይ ድጋፋችሁን ይሻል ============================ (እንደተለመደው ላስቸግራችሁ፤ ሙስሊም ከኸይር ነገር አይጠግብምና ሰሞኑን ስለደጋገምኩባችሁ እንዳትሰላቹ። ጉሮሮው ላይ በተፈጠረ አሰቃቂው የካንሰር በሽታ ለሚሰቃየው ወንድማችን እንድረስለት!) || በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ወንድማችን ዐብደ-ል'ሏህ በድሩ ይባላል። ወንድም ዐብደ-ል'ሏህ የዛሬን አያደርገውና የአላህ ውሳኔ…
«…የግቢ ተማሪ ነኝ፤ የአቅሜን ነው የረዳሁት፣ አላህ ዐፊያ ያድርገው!»

የአንድት እህት መልዕክት ነው! አላህ ይቀበላት! ውጤቷንም A+፣ ጸባይዋንም A+፣ ትዳሯንም A+… ያድርግላት።

ከዚህች እህት በላይ አቅም ያለው ሌላ ወንድምና እህት ጠፍቶ ነው? ከርሷ የተሻለ አካውንቱ ላይ ባላንድ ያለ ታጥቶ ነው። አይመስለኝም! ነፍስያን የማሸነፍና ያለማሸነፍ ጉዳይ እንዳይሆን፤ ጀግኖች ወንድማችንን እናሳክመው። የኛም ነገ አይታወቅምና በዱንያም ሆነ በአኺራህ ከማንም በላይ የሶደቃ ጥቅም ለኛው ነውና በርቱ ጓዶች!


በባለቤቱ እና በስሙ በተከፈቱት የባንክ አማራጮች ድጋፍ በማድረግ እናግዘው።

የአካውንት ስም፦ ፋጡማ ነስሩ ሐሰን
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000307233968 
አዋሽ ባንክ፦       014251336744800
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል፦ 1338403800001
አቢሲኒያ፦  186746977
ዘምዘም ባንክ፦  0040743420101
ንብ ባንክ፦ 7000057909922
ዳሽን ባንክ፦  2907571242711

የአካውንት ስም፦ ዐብደ-ል'ሏህ  በድሩ
ሂጅራ ባንክ፥ 1000643150001


ለኸይር ማነሳሻ ስለሚጠቅም የምትሰድቁበትን ደረሰኝ ኮመንት ላይ ወይም በውስጥ መስመር t.me/Murad_Tadesse ላይ ላኩልኝ።


አነሰ በዛ ሳትሉ ወንድማችንን ተረባርበን እናሳክመው፤ የቻለ በገንዘቡ፣ ይህን ያልቻለ መልዕክቱን በማሰራጨትና በመልካም ዱዓው አይርሳው።