Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
87K subscribers
17.9K photos
4.68K videos
283 files
5.76K links
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።

ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!
Download Telegram
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ተኝቶ የማያድረው አሚር ወንድም አሚር ጀማል ታፋው ላይ በወጣበት አሰቃቂው የካንሰር በሽታ የተነሳ ተኝቶ አያድርም። ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ እምባውን ሲያነባ ያድራል። ያቺ ከጎኑ የማትጠፋው ሚስኪን እናቱም የምታሳክምበት በቂ ገንዘብ ስለሌላት ያላት አማራጭ አብራ እንቅልፏን አጥታ ማልቀስ ነውና ስታነባ ታድራለች። ታዲያ ይህቺ ኡማ እንዲህ አይነቱን በስቃይ ውስጥ ያሉ ባሮቹን ማሳከሚያ በመቻል ሰበብ ማድረስ…
2.982 ሚሊዮን ብር ደርሰናል
======================
በአሰቃቂው የካንሰር በሽታ ታሞ እንቅልፉን በስቃይ ለሚያጣው ወንድማችን አሚር ጀማል ለሕክምናው የሚያስፈልገው የ3 ሚሊዮን ብር ወጪ ሊሞላ ጫፍ ደርሷል። አሁን ላይ 2.982 ሚሊዮን ብር ደርሰናል። አል-ሐምዱ ሊላህ! ወንድማችን ዐፊያው ተመልሶለትና ስቃዩ አብቅቶ የበለጠ የምንደሰት ያድርገን። እነዚያ አብረው እንቅልፋቸውን አጥተው ከልጃቸው ጋር ሲያለቅሱ የሚያድሩ ሚስኪን እናቱ ዓይኖችም እምባቸው ይታበስ።

ለዚህ ሁሉ ካላችሁ ላይ ቀንሳችሁ ከ20 ብር ጀምሮ እስከ 20 ሺህ ብር፣ አለፍ ሲልም እስከ 100 ሺህ ብር ድረስ በነቂስ ስታዋጡ የነበራችሁ ወንድምና እህቶች አላህ ይቀበላችሁ፤ ኢኽላሱንም ይወፍቃችሁ። ፖስት ላይ እንዳይበዛ ብዬ እንጂ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የተሳተፋችሁበት ከ300 በላይ ደረሰኝ አለ። አላህ እናንተንም፣ ቤተሰባችሁንም፣ ወዳጅ ዘመዳችሁንም ከዱንያም ሆነ ከአኺራህ ስቃይ ይጠብቅላችሁ።

ወንድም አሚር ለሕክምና ብቻ የተጠየቀው 3 ሚሊዮን ብር ይሁን እንጂ፤ ለትራንስፖርት፣ ለሆቴልና ለምግብ የሚጠበቅበት ወጪ ሲደመር ትንሽ ከፍ ይላል። ምናልባትም አንድ እናቱ ስለሆነች ያለችው አብሮት የሚሄድ አስታማሚ ወጭም ግድ ይሆንበታልና አሁንም እስከመጨረሻው ትብብራችሁ አይለየው። የጎደለውን እንደተለመደው ተረባርበን እንሙላለት።

ግሩም ናችሁ! አላህ ሐጃችሁን ያውቃልና በሚጠቅማችሁ መልኩ ይፈፅምላችሁ።

ቡሪክቱም!

በሉ! ሌሎቻችሁም ተሳተፉና የወንድማችንን ስቃይ በአላህ ፈቃድ እንዲያከትም እናድርገው።

√ CBE፦

1000598161953

√ የአካውንት ስም፦ Seada Emame Hasen
√ አቢሲኒያ ባንክ፦

53776469

√ የአካውንት ስም፦ Seada Ahmed

ደረሰኝ  ኮመንት ላይ @Murad_Tadesse ላይ ላኩልኝ።
አፋልጉን
========
ይህቺ ታዳጊ ስሟ ሰሚራ ነሰሩ ይባላል። ትናንት ከመሳለሚያ አካባቢ ዐሱር ወቅት ላይ ነው የጠፋችው።

ማንኛውም መረጃ ያላችሁ በዚህ ስልክ ቁጥር አሳውቁን። 0932379635//0922501026
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የህዝበ ሙስሊሙን ወቅታዊ ቁጣ ለማብረድ ብለው በዘዴ ለጊዜው አሰርን ብለው ካልለቀቁት፤ ዛሬ ገቢ ተደርጓል። ይሄ ልጅ ትንሽ አፍልቶ ነበር። የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ አሁንም ሌሎቹንም ገቢ ማስደረግ አለበት። በቂና ተመጣጣኝ እርምጃ ሳይወሰድባቸው ዝም ብለው ለሽፋን አስገብተው የሚያስወጧቸው ከሆነ ግን፤ ህዝበ ሙስሊሙ ራሱን በራሱ የማስከበር ሙሉ መብት አለው።

||
t.me/MuradTadesse
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Where is UNICEF?
Where is the International law?
Where is the Geneva Convention?
Where are the Human Rights Organizations?
Where is the Universal Declaration of Human Rights?
Where is the United Nations I spit on?
Where are the 57 Islamic countries? The 2 billion Islamic world?
«አንድ እንጀራ ለአራት ፥ አንድ ዋንጫ ለሰባት
እኔ አልጓተትም፣
የአላህ አገር ሰፊ ፥ እሄዳለሁ የትም።»
Forwarded from STEM with Murad 🇪🇹
ኒቃቢስቶች ይችላሉ
================
ኒቃቢስት ሆኖ ፕሮግራመር/ ኮደር/ ደቨሎፐር… መሆን ይቻላል። እንዳውም ሐላል የሆነው ቴክኖሎጂ ይበልጥ ለሙስሊም ሴቶች ሸሪዓውን የጠበቀ ገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ።

ምክንያቱም ሴት ልጅ በቤቷ እንድትረጋ ሸሪዓው አዟታል። ኢኽቲላጥ ባለበት የሥራ ቦታ ላይ ኑሮን ለማሸነፍ በሚል ከምትጋፈጥ፤ በቤቷ ውስጥ ረግታ ከየትኛውም ሰው በላይ ተከፋይ መሆን ትችላለች።
ስትፈልግ remotely freelancer ሆና መሥራት ትችላለች፣ ሲያሻት ከከስተመር ኦርደሮችን እየተቀበለች በሃገር ውስጥም ከቤቷ ሆና መሥራት ትችላለች።

ከተቃራኒ ጾታ ጋር ንክኪ ሳይኖረው የተሻለ ሐላል ገቢ ማግኘት ትችላለች። በዚህ መልክ ለመሥራት ደግሞ እንደዚህ የቴክኖሎጂ መስክ የተሻለ የለም።

የሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ዜጋ የሆነችው ኒቃቢስቲቷ እህት ጀዋሂር "My Child" የተሰኘ አፕ ሠርታ አበርክታለች። አፑ የሚንተባተቡ (stuttering) ልጆችን የመናገር ክህሎት ለማዳበር የሚያግዝ ነው።
እህታችን የአሜሪካው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው የአፕል አመታዊ የተማሪዎች የስዊፍት ውድድር (Apple's Swift Student Challenge) አሸናፊ ሆናለች።

Jawaher Shaman from Saudi Arabia 🇸🇦  created her app My Child to help children with speech conditions.

Love Niqabi Coders❤️!

ዝርዝሩን ከአፕል ድረ ገፅ ዜና ላይ አንብቡ።
Link

||
t.me/STEMwithMurad