Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
89.3K subscribers
18.2K photos
4.88K videos
284 files
5.89K links
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።

ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!
Download Telegram
ግልፅ ለማድረግ ያክል‼
=================
✍ ከትናንት ጀምሮ በንፅፅር ዳዕዋ ላይ ለተሰማራው ለኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽር የዳዕዋ ሥራው ያግዘው ዘንድ የተሻለ መኪና ብንገዛለት ብለን የኸይር ሥራ እንቅስቃሴ ነበር። ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች «ባለፈ የተሰበሰበው ብር የት ደረሰ?» የሚል ጥያቄና ከዚህ አለፍ ሲልም ነውረኛ ውንጀላወችንና ጥርጣሪዎችን እያነሱ ነበር።

በመጥፎ ጥርጣሬ ላይ ተሰማርተው ብዥታና ውንጀላ ሲያሰራጩ የነበሩ ወንድሞች፤ ቀድሞውንም አቢሲኒያ ባንክ ለተፈጸመው ነገር ይቅርታ መጠየቅ የለበትም ብለው ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች በላይ ሽንጣቸውን ገትረው ሲሟገቱ የነበሩ ናቸው።

ከፊሎች ግን በቀናነት ሊሆን ይችላል ጥያቄውን ያነሱት። በቀናነት ለተነሳ ጥያቄ ተገቢውን ማብራሪያ መስጠት ደግሞ ግድ ነውና ኡስታዙ በዚህ ንግግሩ ላይ ስላለው ነገር ማብራሪያ ሰጥቷል።

ከራሱ አንደበት ለማዳመጥ ኦዲዮውን በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ። (https://t.me/MuradTadesse/33700)

በአጭሩ በጽሑፍ እዚህ ለማስቀመጥ ያክል፦
በባለፈ ተጀምሮ በነበረው ወደ 3 ሚሊዮን ብር ገደማ ተሰብስቦ ነበር። በወቅቱ ታቅዶ የነበረው እስከ ክፍለ ሃገር ድረስ አስቸጋሪ መንገዶችን ለመንቀሳቀስ የሚያመች መኪና ነበር። ያኔ ዋጋው ከ6 እስከ 7 ሚሊዮን ብር ገደማ ነበር። በወቅቱ ይህ የብር መጠን ሳይሞላ ባለበት 3 ሚሊዮን ላይ ቀርቷል።

እርሱ ግን ወንድሞች በተከራዩለት ከታች በምትመለከቷት መኪና እየተንቀሳቀሰ የዳዕዋ ሥራውን እንደቀጠለ ነበር። በመሃል ይህ ብር ዝም ብሎ ከሚቀመጥ ግሽበትም ስላለ ንብረት ላይ ቢሆን ይሻላል በሚል ወንድሞች ጋር በመነጋገር፤ «ለምን ግማሹ ብር ይህቺን መኪና ከኪራይ ይልቅ አይገዛበትም?» በሚል እሳቤ አከራዩን የመኪናዋን ባለቤት አነጋግረው እርሱም ኪራዩን በመቀነስ ጀምሮ ትብብር እያደረገ ነበርና፤ ለሌሎችም ከሚሸጥበት ዋጋ ቀንሶ በ1.4 ሚሊዮን ብር ተስማሙና እስካሁን 1.3 ሚሊዮን ብሩ ተከፍሎታል። መቶ ሺህ ብር ብቻ ይቀራል።

ቀሪው 1.708 ሚሊዮን ብር ግን ከሰው የተሰባሰበ አማና ስለሆነ ሳይነካካ አሁንም በአካውንቱ ላይ ተቀምጧል።

ቀጣይ አላማችን አላህ ብሎ አሁን የጀመርነውን ቻሌንጅ እስከ ጥግ ሳናቋርጥ ከገፋንበት፤ በአካውንቱ ላይ ያለውን ብር፣ አሁን ለጊዜው እየተገለገለባት ያለችዋን መኪናና ወደፊት የሚሰባሰበውን ጨምረን ለዳዕዋ ሥራው አመቺ የሆነውን መኪና ለመግዛት ነው።

በርግጥ ያኔ ከነበረበት 6–7 ሚሊዮን አሁን ላይ የተወሰነ ጭማሬ አለ።

አሁን ላይ ከትናንት ጀምሮ እየገባ ያለውንም ብር እግር በእግር ተከታትለን እናሳውቃችኋለን።

እስካሁን ባለው ግን 3 የባንክ አካውንቶች ተለቀው ስለነበር አዲስ የገባው ብር፤
①) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 526,487 ብር፣
②) በዘምዘም ባንክ፦ 18,145 ብር፣
③) በሂጅራ ባንክ፦ 14,197 ብር ነው።

በድምሩ፦ 558,829 ብር ደርሷል።

አሁን ላይ ከበፊቱ ጋር ግማሽ ገደማ የሚሆነውን ስላሟላን፤ በአላህ ፈቃድ ቀሪውን ግማሽ ተረባርበን ሞልተነው አላህ ካገዘን ከመኪናውም ባሻገር ለዚሁ ለንፅፅር ሥራ የሚውል ተቋም እስከመመስረት ልንሻገር እንችላለን። ቅድሚያ ግን ለጊዜው የተነሳንበት ይህ ነውና እንበርታ።


አላህ ሁላችንንም ለኸይር በር ከፋች፣ ለሸር በር ዘጊ ያድርገን። ሁሌም ካለ አግባብ የመቃረን ሱስ ያውጣን። መሥራት ያልቻለ የሚሠሩትን ባለማደናቀፍ ቢተባበር የት በደረስን ነበር። ሳናስበው በቀልድም ሆነ በተንኮል የሰዎችን ሞራል ጎድተን አላህ ፊት እንዳንጠየቅ እንፍራ። አሁንም ለጋሽ እጆች መዘርጋታቸው ይቀጥል። በአላህ ፈቃድ ሳንሞላ አናቆመውም። የኢስላም ጥሪ ከዚህም በላይ ተቀጣጥሎ ይቀጥላል።


√ የአካውንት ስም፦ Muhammed Khedr Essa
√ የኢትዮጵ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000258086857

√ የዘምዘም ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 000 19768 20101

√ የሂጅራ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000771510001

የምትልኩባቸውን ደረሰኞች ለኸይር ማነሳሻ መላካችሁ ይቀጥል።

t.me/MuradTadesse
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ግልፅ ለማድረግ ያክል‼ ================= ✍ ከትናንት ጀምሮ በንፅፅር ዳዕዋ ላይ ለተሰማራው ለኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽር የዳዕዋ ሥራው ያግዘው ዘንድ የተሻለ መኪና ብንገዛለት ብለን የኸይር ሥራ እንቅስቃሴ ነበር። ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች «ባለፈ የተሰበሰበው ብር የት ደረሰ?» የሚል ጥያቄና ከዚህ አለፍ ሲልም ነውረኛ ውንጀላወችንና ጥርጣሪዎችን እያነሱ ነበር። በመጥፎ ጥርጣሬ ላይ ተሰማርተው…
«ሙሐመድ ኸድርን እስከማውቀው ድረስ ዱንያው ሳይሞላለት የዲኑ ነገር አሳስቦት እየለፋ የሚገኝ ኡስታዝ ነው። ሰዎች ለዲን ሊለፉ ይችላሉ። ነገር ግን የዱንያ ስራቸው ሲቀዘቅዝና ችግሮች ሲበረቱ የቤተሰባቸውን የኑሯቸውን ጉዳይ ለማስተካከል የትኩረት አቅጣጫቸው የተወሰነ መሰረቁ አይቀሬ ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር በኑሮው ይህ ነው የሚባል ትልቅ ገቢ የሌለውና ልጁን ለማስተማር ሳይቀር የተቸገረበት ሁኔታ እንደነበረ መረጃው አለኝ!! ሆኖም ሁላችንም እንደምንታዘበው ዲኑን ከመኻደምና ኢስላምን ከመስበክ ከድሮ ጀምሮ ደከመኝ ብሎ አያውቅም። በቴሌግራም ዳዕዋ ይሰራል። በርካቶችን ያሰልማል። የቴሌግራም ግሩፑ ሲስፋፋ በሪፖርት ያዘጉበታል፣ እሱ ግን እንዳዲስ ይጀምራል፣ በዩትዩብ ሰዎችን ያሰልማል። ይታገላል እንጂ አይሰለችም። አሁን ደግሞ በአካል መሬት ላይ ወርዶ የመንገድ ዳር ዳዕዋውን ወጥሮ ይዟል።

እንደሱ አይነት ጠንካራ አይበገሬ ሰዎቻችን ጥቂቶች ናቸው እና እኛም ልንኻድማቸው መሰልቸት የለብንም። በርቱ አህባቦቼ እንደግፈው!!

﴿ وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلٗا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ ﴾[ فصلت: 33]
"ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔም ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ንግግሩ ያማረ ማነው? (ማንን)" (ፉሲላት፡ 33)

ኡስታዝ መሐመድ ኸድር
የአካውንት ቁጥሩ 
CBE= 1000258086857
Zamzam Bank=0001976820101
Hijra Bank=1000771510001Âť

Š: Huda Multimedia
«ሳኡዲ አረቢያ ነጻ የፍልስጤም ሀገር ሳይመሰረት ከእስራኤል ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንደማታደርግ ገለጸች

ጥር 29/2016
ሳኡዲ አረቢያ ነጻ የፍልስጤም ሀገር ሳይመሰረት ከእስራኤል ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንደማታደርግ ገለጸች።
ሳኡዲ አረቢያ በ1967 ስምምነት መሰረት ነጻ የፍልስጤም ሀገር ካልተመሰረት እና እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ወረራ ካላቆመች ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደማይኖራት ለአሜሪካ ተናግራለች።
በትናንትናው እለት የኃይትሀውስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ክርቢይ የባይደን አስተዳደር ሳኡዲ አረቢያ እና እስራኤል ግንኙነት የማደስ ንግግር ለመጀመር ፈቃደኛ ናቸው ብለው ነበር።
ነገርግን ሳኡዲ አረቢያ በፍልስጤም ጉዳይ ያላትን ጥብቅ አቋም የሚያሳይ መግለጫ አውጥታለች።
ሁለቱ የገልፍ ጎረቤቶቿ አረብ ኢምሬትስ እና ባህሬን በፈረንጆቹ በ2020 ግንኙነት ከጀመሩ በኋላ የሳኡዲ እና የእስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመር ጉዳይ ንግግር ሲደረግበት ቆይቷል።
የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ሳኡዲ አረቢያ በአሜሪካ የሚደገፈውን ግንኙነት የማደስ ሂደት ውሃ ቸልሳበታለች ተብሏል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሁለት ቀናት በፊት ለአምስተኛ ጊዜ ባደረጉት የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው ሳኡዲ አረቢያን ጎብኝተው ተመልሰዋል።
ብሊንከን አሜሪካ የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ቆሞ፣ የእስራኤል-ሳኡዲ አረቢያ ግንኙነት የማደስ እና የፍልስጤም ሀገር ምስረታ ሂደቶች እንዲፋጠኑ እንደምትፈልግ ተናግረዋል።» ጀይሉ ቲቪ
ዛሬ በጣም ካስደሰቱኝ ነገሮች አንዱ የፌዴራል መጅሊሱን ፕሬዝዳንት ጨምሮ ሌሎችም ልዑካን ወደ ትግራይ ክልል ማቅናታቸው ነው።

ይህ ብዙ ትርጉም አለው። በፖለቲከኞችና በዘረኞች ቁማር ሳቢያ ተበጣጥሶ የነበረውን ኢስላማዊ ወንድማማችነት ዳግም ለመዘርጋት መደላድል ነው።

ምንም እንኳ በብዙ ትምክህተኞች ሳቢያ የበርካታ የትግራይ፣ የወሎ፣ የአፋርና የሌሎችም አካባቢዎች ንጹሐን ህይዎታቸውን ቢያጡም፣ ለአካል ጉዳተኝነት ቢዳረጉም፣ ለስነ ልቦና ቀውስና ለስደት ቢዳረጉም… ያለፈውን መመለስ ስለማይቻል ቀሪ ጊዜን ከቂም በጸዳ መልኩ ከምንም በላይ የኢስላምን የመተሳሰር ገመድ አስበልጦ ለጋራ ዲን በጋራ መሥራትን የሚያክል የለም።

አላህ መልካም ጅማሮ አድርጎት የበለጠ የተሻለ ተስፋ የምናይበት ያድርገው። ባለፈው ቀውስ ሳቢያ እስካሁን ድረስ ለረሃብና አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን መልሶ ማቋቋምና ማገዝ መዘንጋት የለበትም።

||
t.me/MuradTadesse
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ⓵④③④]👌


#ቁርኣን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ⓵④③③]👌


#ቁርኣን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሁንም ላይ የሙስሊሞችን ድምፅ አፍነው ዘመኑን የማይመጥን ዘግናኝ ጭቆና የሚፈፅሙ አካላት አሉ።

በቤኒሻንጉል ክልል ለ40 ዓመታት የሙስሊሙ ይዞታና ንብረት የነበረውን መስጅድና መድረሳን ያካተተ ይዞታ ሸንሽኖ ለቤተክርስትያንነት እና ለግለሰቦች መኖርያነት መሰጠቱን እየሰማን ነው።


ጉድ'ኮ ነው!
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ግልፅ ለማድረግ ያክል‼ ================= ✍ ከትናንት ጀምሮ በንፅፅር ዳዕዋ ላይ ለተሰማራው ለኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽር የዳዕዋ ሥራው ያግዘው ዘንድ የተሻለ መኪና ብንገዛለት ብለን የኸይር ሥራ እንቅስቃሴ ነበር። ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች «ባለፈ የተሰበሰበው ብር የት ደረሰ?» የሚል ጥያቄና ከዚህ አለፍ ሲልም ነውረኛ ውንጀላወችንና ጥርጣሪዎችን እያነሱ ነበር። በመጥፎ ጥርጣሬ ላይ ተሰማርተው…
የኸይር ሥራ ዘመቻችን እንደቀጠለ ነው‼
===========================
✍ በንፅፅር የዳዕዋ እንቅስቃሴ ላይ ለተሰማራው ለኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽር የዳዕዋ ሥራ አጋዥ ይሆነው ዘንድ የጀመርነው መኪና የመግዛት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአላህ ፈቃድ ሞንታሪቦውን ለመያዝ አመች የሆነ መኪና ባለመኖሩ ሳቢያ ቤት ውስጥ የተቀመጠውን ሞንታሪቦና ጀኔሬተርም መያዝ የሚችልና በክፍለ ሃገርም በአስቸጋሪ መንገዶች ጭምር እየተንቀሳቀሱ የኢስላምን አስተምህሮ ለማድረስ አመቺ የሆነ መጓጓዣ ማመቻቸት አለብን።

ይህን የምናደርገው ያለው ተጨባጭ ስለሚያስገድድ እንጂ ለግለሰቡ ምቾት አይደለም።
በስንት የጥመት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሳይቀሩ ከዚህ በባሰ መልኩ እየተደገፉ፤ እኛ ሐቅ ላይ ሆነን በዚህ መስክ ለተሰማሩ ኡስታዞች የዳዕዋ ሥራቸውን ብናግዝ ምንም ነውር የለውም።

በኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽር ዳዕዋ ሳቢያ ብዙዎች በአካልና በሶሻል ሚዲያ ጭምር ሂዳያ አግኝተዋል! እኛ በዚህ እንቅስቃሴ ላይ አላህ ከሰጠን ላይ ቀንሰን አሻራችንን ብናሳርፍ ከምንዳው ተቋዳሽ እንሆናለን። 
መቼም ለአንድ ሰው የሂዳያ ሰበብ መሆን ምንዳው ምን ያክል እንደሆነ አልነግራችሁም።

አላህ ከሰጣችሁ ላይ በመስጠት የኢስላምን ጥሪ በማስፋፋት ላይ ሁሉም አላህ ባገራለት ልክ ይሳተፍ። አሁንም ተሳትፏችን ይቀጥል፤ በየጊዜው የደረሰበትን አሳውቃችኋለሁ። በአላህ ፈቃድ የተፈለገው የብር መጠን ሞልቶ የታቀደው መኪና ተገዝቶ እስከምናይ ድረስ ያለውን ነገር መረጃውን አደርሳችኋለሁ። ኢንሻ አላህ እናሳካዋለንም።


√ የአካውንት ስም፦ Muhammed Khedr Essa
√ የኢትዮጵ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000258086857

√ የዘምዘም ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 000 19768 20101

√ የሂጅራ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000771510001

የምትልኩባቸውን ደረሰኞች ለኸይር ማነሳሻ በኮመንት ወይም በውስጥ መስመር @Murad_Tadesse ላይ መላካችሁ ይቀጥል።
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም በጉንችሬ ከተማ ሰላም መስጅድ‼ =================================== ✍ በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ ሰላም መስጅድ የፊታችን እሁድ ማለትም የካቲት 03 /2016 ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።   እነዚህና ሌሎችም ዱዓቶች የሚገኙበት ልዩ የዳእዋ ፕሮግራም፦ ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር…
እሁድ → እግሮች ሁሉ ወደ ጉንችሬ ያመራሉ‼
===============================
✍ በአላህ ፈቃድ የፊታችን እሁድ የካቲት 3, 2016 E.C. ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የጉራጌ ዞኗ ጉንችሬ ከተማ ደምቃ ትውላለች። ላለፉት አመታት በኩፋሩም በጙላቱም ተፅዕኖ ስር ወድቃ የነበረችው ውቢቷ ጉንችሬ፤ ትክክለኛው የዳዕዋ ጮራ ዳግም ይፈነጥቅባታል። በዕለቱ ከአዲስ አበባ በሚሄዱ ታላላቅ ዳዒዎች ከሚዳሰሱ የሙሐደራ ርዕሶች መካከል፦

①) የቢድዓህ አደጋዎች፣
②) የሲሕር መዘዞቹ እና መፍትሄው፣
③) ተውሒድ የነብያት ጥሪ፣
④) በሱንና ላይ መፅናት… እና ሌሎችም ወሳኝ ወሳኝ ርዕሶች ይዳሰሳሉ።



√ የእለቱ ተጋባዥ ዱዐቶች፦

ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ
ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ
ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
ዶክተር ዐብዱ ኸይሬ
ኡስታዝ ዐብዱል ካፊ ሙሐመድ
ኡስታዝ ዐብዱ-ር'ረሕማን ዐባስ


√ የፕሮግራሙ ቦታ፦ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ ከሃይስኩል ጀርባ መነኻሪያ አካባቢ ሰላም መስጅድ ውስጥ


ይህ አጓጊ የሆነ ፕሮግራም ላይ ቤተሰብዎንና ወዳጅ ዘመድዎን በመያዝ በጊዜ ይገኙ።

√ ለሴት እህቶቻችን በቂና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል።

እናንተም በዚህ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በክብር የተጋበዛችሁ ስለሆነ፤ ከወዲሁ ቀጠሯችሁን በማስተካከል በሰዓቱ ተገኙ።


✔ ለጉዞው ቅልጥፍና ይመች ዘንድ ለመሄድ ያሰባችሁ ሰዎች ወደ እነዚህ የዳዕዋው አስተባባሪዎች ጋር በመደወል እስከ ነገ ጁሙዓህ ድረስ እንድታሳውቁ አሳስበዋል።

🔹ቤተል፣ ዓለም ባንክ እና ዙሪያው አስተባባሪዎች

ዐብዱልጀሊል ፋሪስ  0937775792
ዐብዱልሀዲ ሙሐመድ  0947540222
አሕመድኑር አይታ  0911106306

🔹ኮካ, አብነት መርካቶ
ሬድዋን  0909113696
መኑር ዲኖ  0911082208
ዐብዱሰላም ኸይሩ 0913842798
ኢብራሂም   0921776328

🔹ፉሪ ኬንተሪ
ሙባረክ ኑሩ  0911921980
ዐብዱልጀባር  0911895313
ሙሐመድ ዑመር 0919411289
ኢብራሂም ኸሊል 0912420191
አብራሂም ዐረብ 0911830951

🔹ወለቴ
መኑር ዐባስ 0920969361
ሬድዋን ዑመር 0919225578

🔹ቦሌ ገርጂ
ሰኢድ ሙሐመድ  0913786613
ሱፊያን ለማ  0922976870
ዐብዱልጘፋር  0910122537

🔹አጠና ተራ
ዐብዱልፈታሕ በህሩ 0961065933
ከማል አወል  0919225568



♠
የላ! ጉዞ ወደ ጉንችሬ!
||
t.me/MuradTadesse
ሰሞኑን ምን እየተካሄደ ነው⁉️
===================
✍ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች "ፋኖ" ነን የሚሉ ቡድኖች የአማራ ክልልን ህዝብ ነፃ እናወጣለን በሚል ሽፋን የክልሉን ሙስሊም ማኅበረሰብ እያሰቃዩት ይገኛል።
በባህር ዳር ከተማና አካባቢዋ ብዙዎች እየታገቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር እየተጠየቁ ቆይተዋል። በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች ተመሳሳይ ነገር እየተስተዋለ ነው።

ከነዚህ ቡድኖች ባሻገር በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ የአሕባሽ ቡድኖች ከነዚህ ፋኖ ነን ከሚሉና አንዳንድ ሆድ አድ አደር የመንግስት አመራሮች ጋር በመሆን «ውሃብያ» የሚሉትን ሙስሊም ማኅበረሰብ እያሰቃዩ ይገኛሉ። በዳውንት ወረዳ የወረዳው አመራሮች ከነዚህ ጽንፈኞች ጋር በማበር በህጋዊ መንገድ የተመረጠውን መጅሊስ በመፈንቀል ህዝበ ሙስሊሙን ደም ሊያቃቡት ጫፍ ደርሰዋል።

እንደ ጃዊ ባሉ የክልሉ አካባቢዎች ከታች የምትመለከቱት አይነት አደገኛና መርዘኛ መልዕክት እየተሰራጨ ነው። ከዚህ መልዕክት ቀጥሎ የሚፈጠረውን በላእ አላህ ይወቅ።

በቤኒሻንጉል ክልል 43 አመታት ገደማ የቆየ መስጅድና መድረሳ መሬቱ እየተሸረሸረ ለቤተ ክርስቲያንና ለግለሰቦች መኖሪያ ይሆን ዘንድ መሰጠቱን ሰምተናል። ይህ ጉዳይ በቪድዮም ቀርቧል።https://t.me/MuradTadesse/33710
★
ከተወሰኑ ወራቶች ወዲህ ትንሽ ተንፈስ ብለን ነበር። አሁን ደግሞ በማናውቀው ጉዳይ ምን በላእ አምጥተው ሊያንጫጩን ይሆን? ምንስ እየተደገሰልን ይሆን? አላህ በየቦታው ያሉ ንጹሐን ወገኖቻችንን ይጠብቅልን።
የአማራ ክልል መጅሊስ ከፌዴራሉ መጅሊስ፣ ከክልሉ አማራርና በየደረጃው ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገረ የክልሉን ሙስሊም ማኅበረሰብ ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል። ደምፃቸው ታፍኖ ሲሰቃዩ ዝምታን መምረጥ የለብንም።
||
t.me/MuradTadesse