Muhammed Computer Technology (MCT)
37.5K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
GEOGRAPHY Grade 11 Text Book ከላይ ያለውን በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ!
English Grade 1 Text Book ከላይ ያለውን በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ!
👍2
ቢዝነስ ፕላን👆👆
Business Grade 1 Text Book ከላይ ያለውን በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ!
ከይቅርታ ጋር የምለቅቃቸውን መጽሀፎችን በሌላ የቴሌግራም ቻናል በመክፈት እራሱን የቻለ መፅሐፎችን የሚጫኑበት ቻናል ለመክፈት አሰብኩ ምክንያቴ ደግሞ ይህ ቻናል በጽሁም የሚለቀቁ መረጃዎችን ቢለቀቁበት የተሻለ መሰለኝ ስለዚህ አዲስ ቴሌግራም ቻናል ይከፈት? ሀሳባችሁን ከታች ባሉት ምርጫዎች ይግለጹልኝ
Anonymous Poll
89%
አዎ ይከፈት
11%
አይከፈት
እንዴት የ ማንኛዉንም windows computer administrator password ማለፍ እንችላለን?
▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃

Requirements:
—> ማንኛዉም የwindows operating system የተጫነበት cd ወይም usb
Eg. Windows7 os or windows 8 os

Let’s begin………..
—> computrሩን ከ cd ወይም ከusb ማስነሳት(boot from cd or usb)
—> ልክ boot አርጎ ከተነሳ በኋላ shift+F10 መጫን ከዛ command promote ይከፈታል
ምናልባት command promote ካልከፈተ shift+fn+F10 ሞክሩት
⚠️ማሳሰቢያ ከዚህ በታች " " ወይም የ quotation ምልክት ስትጽፉ ማድረግ የለባችሁም።
—> Type “cd c:” without quotation ኢንተርን ይጫኑ
—>Type “dir” enter ይጫኑ

--> Windows የሚለው ዝርዝር እስከሚመጣ ድረስ ፊደሉን እየቀያየሩ መሞከር
Eg. “D:” hit enter then “dir” hit enter then check “windows”
“E:” hit enter then “dir” hit enter then check “windows”
—> ከዛ በ ስእሉ ላይ የሚታየዉን በትክክል ይጻፉ
—> “cd windows/system32” hit enter

--> Type “rename osk.exe osk.old” hit enter
—> Type “rename cmd.exe osk.exe” hit enter

--> አሁን 75% ሚሆነዉን ስራ ጨርሰናል ከዚ ቀጥሎ computerun restart ማድረግ
—> ከስር በግራ በኩል የሚታየዉን icon መጫን
—>On-Screen Keyboard የሚለዉን መምረጥ

-->command promote display ሲሆን ስእሉ ላይ ያለዉን command ማስገባት
—> Type ”net user” hit enter
—> Type ”net user help *” hit enter —---- help ማለት የ computeru ስም ነው

-->ከዛ ምትፈልጉትን password ማስገባት
—> Password እንድይኖረው ከፈለጋቹ ደሞ hit enter ሁለቴ

--> አሁን Passwordu ተከይሯል ማለት ነው
—> የከየራቺሁትን Password አስግብታቹ login ማረግ

ለጓደኛዎ #share ማድረጎን አይርሱ።
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
👍2
Cisco Packet Tracer በሲስኮ ሲስተም የተፈጠረ አውታረ መረብ/የኔትወርክ መሳሪያ ነው፡፡ ለኔትወርክ ሰርቲፊኬቶች ስልጠና የሚጠቅም ሶፍትዌር በመሆኑ በPacket Tracer ተማሪዎች ያልተገደበ የቁጥር መሳሪያዎችን አውታረመረብ/ የኔትወርክ እቃዎችን ልክ እንደ እውነተኛ ዲቫይሶቹ በመሆኑ የሙከራ ስልጠናዎችን እና ችግሮችን ለመማር ያስችላቸዋል፡፡
የመሳሪያው ዓላማ የተማሪዎችን የኔትዎርክ መሰረታዊ መርሆችን ለመማር ልዩ ክህሎቶችን ለማዳበር የተሰራ ሲሆን እንደ ራውተር ፣ስዊች እና የተለያዩ የኔትወርክ ዲቫይሶችን የያዘ ነው፡፡
Cisco Packet Tracer የተለያዩ ስሪት ያለው ሲሆን 7.3 አሁን ያለው ነው ለዊንዶ፣ ላይኑክስ እና ማክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች እንደፍላጎታችሁ መጫን ትችላላችሁ። ጎግል ላይ Cisco Packet Tracer version 7.3 ብላችሁ ሰርች በማድረግና በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ።
ቴሌግራም አካውንት # Delete ካደረኩት ምን ይፈጠራል?

➡️# Join (Subscribe) ያደረጋችሁት ቻናል፣ ግሩፖች ላይ በሙሉ ትወጣላችሁ።

➡️እናንተ # Create ያደረጋችሁት ግሩፕ፣ ቻናል ካለ አይደለትም ግን ባለቤት አልባ ይሆናል፤ # አድሚን ያደረጋችሁት ሰው ቢኖርም ጥቅም የለውም። ‼️

➡️መጀመሪያ ወደሌላ አካውንት # Transfer ማድረግ ይመከራል።

➡️# Block ያደረጋችሁ ወይም ያደረጋችሁት ሰው ካለ # Unblock ይሆናል።

➡️ከማንኛውም ሰው ጋር የተላላካችሁት/ ያወራችሁት ነገር በሙሉ ይጠፋል።‼️

💯እዚ ቻናል ላይ የሚለቀቅ ማንኛውም ነገር እውነተኛ ነው የሚያቁን ያውቁናል ስለሚያቁን ይተማመኑብናል።
የBIOSና CIMOS ልዩነት ምንድን ነው?
#BIOS_VS_CMOS
👉ብዙውን ጊዜ ባዮስ(BIOS) እና CMOS ተመሳሳይ ነገር ተደርገው ይታሰባሉ:: ነገር ግን ሁለቱም የተለያዩ የኮምፒውተር #ሃርድዌር ክፍሎች ሲሆኑ ሁለቱም አብረው በመሆን በተገቢ ሁኔታ ኮምፒውተር እንዲሰራ ያደርጋሉ፡፡

👉 #ባዮስ(BIOS) በmotherboard ላይ የሚገኝ የኮምፒውተር ቺፕ(ፕሮግራም የተጫነበት) ሲሆን ይህ የባዮስ ቺፕ ኮምፒውተር በትክክል እንዲሰራ ያግዛል:: እንዲሁም በኮምፒውተር ውስጥ ሌሎች ክፍሎች የሚቆጣጠሩ ልዩ ፕሮግራም ይዟል:: እነዚህ ሌሎች ክፍሎች የዳታ ማስቀመጫ #ሃርድ_ዲስክ#የቪዲዮ_ካርዶች#የድምፅ_ካርዶች#የአውታረ_መረብ ካርዶች(Network_cards)፣ #ፍሎፒ_ዲስክ#ዩኤስቢ(USB) እና ሌሎች ይገኙበታል::
ባዮስ ባይኖር የተለያዩ የኮምፒውተር ክፍሎች
መስተጋብር መፍጠር ወይም በትክክል አይሰሩም ነበር፡፡

👉 #CMOS ሌላው በmotherboard ላይ የምናገኘው አንዱ የኮምፒውተር ቺፕ ሲሆን ስለ ኮምፒውተር ክፍሎች በባዩስ ላይ ያደረግነውን ለውጦች ቅንብር #መረጃ_የሚያከማች(store information) ነው። በተጨማሪ የኮምፒውተሩን ሲስተም #ቀን_እና_ሰአት ይይዛል።
ይሁን እንጂ ለCMOS ቺፕ የሚሆነውን ሃይል ሲሞስ ባትሪ CR2032 ይጠቀማል፡፡ ይሄ የCMOS ባትሪ ለCMOS ቺፕ የማያቋርጥ ኃይል ይሰጠዋል. የሲሞስ ባትሪ CR2032 የምንለው ትንሽ ጠፍጣፋ ክብ ሲሆን የባዩስን #ሴቲንግ(ቅንብር) ለውጥ ለማጥፍት ስንፈልግ በቀላሉ ባትሪውን በመንቀል ወደ ዲፎልቱ እንዲመለስ እናደርጋለን፡፡
👍1
Civics Grade 8 Text Book ከላይ ያለውን በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ!
📚 C++ Programming
❗️PART ONE
📝 Course Title: C++ Programming
Content :👇🏻
📚 Introduction to Programming
📚 C++ Over View
📚 Facts

📚Introduction to Programming:
ሰላም ሙሀመድ ነኝ የዛሬው ትምህርታችን C++ ነው!

በአለማችን ላይ እንደ Wikipedia, 700 programming languages በላይ የፕሮግራምንግ ቋንቋዎች አሉ።
Programming ምን ማለት ነው?🤔
የሰው ልጆች በቋንቋ እንደሚግባባው ሁሉ የሰው ልጅ ከኮምፒውተር ጋር ለመግባባት (የተለያዩ ትዕዛዝ ለመስጠት) ለብዙ አመታት ለተመራማሪዎች የራስ ምታት ነበር. ምክንያቱም ኮምፒውተሮች የሚያውቁት 👉 0101001 (binary numbers) ነው እኛ ደግሞ ይሄንን መረዳት አንችልም 🤷‍♂!! ስለዚህ ሁለታችንን የሚያግባባን high level programming ቋንቋዎች ተፈጠሩ። በመሆኑም እኔ ለምሳሌ cout<<"hi" ብዬ ብፅፍ ኮምፓይለሩ (compiler) ለኮምፒዩተሬ ዘደ 101010 ቀይሮ ይግረዋል ። 🤝

📚C++ Overview
1⃣ C++ (ሲ ፕላስ ፕላስ) is general purpose programming language.
ማለትም ከቪዲዮ ጌም እስከ ኮምፒውተር እና የሞባይል አፕሊኬሽን፣ ከሙዚቃ ማቀነባበሪያ አፓች እስከ የተወሳሰቡ የAI ሶፍትዌሮች ሁሉንም መስራት ያስችላል

2⃣ C++ is Object Oriented
ይህ በ programming ውስጥ እጅግ በጣም ወሳኝ Concept ነው (የምሬን ነው) ወደፊት በሰፊው እናያለን።
ግን በአጭሩ ለማብራራት ያህል (ለምሳሌ ነው)
OOP (Object Oriented programming) ውስጥ ነገሮችን ልክ እንደ እውነተኛ Object ነው የምናስመስለው ። እንበልና በ C++ ውስጥ አንድ ስለ 20 መኪኖች የቀለም አይነትና ፍጥነት የምናገር ኮድ ለመፃፍ ለሁሉም መኪኖች የተለያዬ ኮድ አንፅፍም! በቃ አንድ "car" ምባል class በመፍጠር color የምባል variable , speed () የምባል function በውስጡ በመጨመር ef
class Car {
public :
public:
void speed();
string color;
}
ይሄንኑ class ለብዙ object(ያው በዚህ ኮድ የኛ object መኪናው ነው) መጠቀም ችላለው።
Car car1;
Car car2;
Car car20; ...... እያልኩ ማለት ነው
ወደፊት ይገባችኋል ግን በጣም ወሳኝ ነው 😊

3⃣ C++ is case sensitive !
ማለትም በቀላሉ ለማስረዳት....
በC++ ዉስጥ "MUHAMMED" , "muhammed", "MuHAmmeD" ሶስቱም በጣም የተለያዩ ቃላት ናቸው specially Variable አርገን ስንጠቀም። ስለዚህ በ C++ ዉስጥ አንድ Variable "name " ብዬ ቢፈጥር..... ይሄን Var መጠቀም ምችለው ልክ እንደፃፍኩት ሁሉንም Small letter ማድረግ አለብኝ👉🏾 ("name")

📚 ለጠቅላላ እውቀት 😊
C++ የተፈጠረው በ Bjarne Stroustrup የተባለ ግለሰብ በ 1979 ነበር ።
C++ የተፈጠረው "C" ከምባል programming ነው።
ስለዝህ "C" የ "C++" አባት ነው....እናቱስ ?🤔😁
Content :👇🏻
📚 Environment SetUp
📚 Basic Syntax
📚 Comments In C++
📚 Variable & Data Type
1⃣ Environment Setup
ያው አጫጫኑ ብዙ አይነት መንገድ አለ። ከፈለጋቹ Code::Block ሶፎትዌር በመጫን በቀላሉ መስራት ትችላላቹ።
በዚህ ሊንክ ገብታችሁ https://quincy-2005.software.informer.com/1.3/ DOWNLOAD Free 18.4 MB ነው ሶፍትዌሯ
በመቀጠል Quincy ወይም ያወረዳቹትን በመክፈት file ምለው ዉስጥ new በማለት ወይም በቀላሉ (Ctr+n) በመጫን መክፈት ትችላላችሁ።
2⃣ Hello World
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በመጀመሪያ የ C++ ኮዶች የመጀመሪያው መስመር ላይ headers (ከላይ ለምፃፍ) tag አላቸው ። ይህም ለኮምፓይሌሩ (compiler C++ በኮምፒውተር ላይ እንድሰራ የምያደርግ) የምንጠቀማቸዉን የተለያዩ መረጃዎች ይሰጠዋል። ለምሳሌ
#include <iostream>

በዝህች ኮድ ውስጥ hashtag (#) የምያመለክተው የcompiler preprocessorለመጥራት ስሆን '#include ' ደግሞ ኮምፓይለሩ '<iostream>' header እድያካትት (to include ) ይነግረዋል።
Note :
iostream is the header file which contains all the functions of program like cout, cin etc. and #include tells the preprocessor to include these header file in the program.

በዚህም መሰረት የተለያዩ Modues (library ) መጠቀም ስንፈልግ ከኮዳችን አናት (header) ላይ ይህችን እንፅፋለን ሁሌ!
ለምሳሌ C++ ላይ Maths ለመጠቀም
#include <math.h> 🤷‍♂ እንጠቀማለን።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
📖በመቀጠል main() የምባል function ሁሌም ያስፈልገናል
በምንስፈው ኮድ ውስጥ ብዘ አይነት የተለያዩ function ስለሚንስፅፍ ኮምፓይለሩ ሁሌም ስራዉን ከ 'main()' function ይጀምራል።
ለምሳሌ

#include<iostream>
int main()
{
//put your code here
}
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
📖Cout<<
ይህ Syntax በውስጡ የምንፅፈው ነገር በኮምፒውተር ላይ display እንድሆን ያደርጋል ። ወይም ኮምፓይለሩ ያስገባነውን process አርጎ እድያሳየን ያደርጋል።
ለምሳሌ

#include<iostream>
int main()
{
cout<< "Hello world "
}

ከላይ አስተውላችሁ ከተመለከታችሁ cout<< ሚለውን syntax ወደ ውስጥ ስፔስ አድርጌ ከቃሉ በፊት እና ኋላ ይሄን ምልክት ( " " )ፅፌዋለው ይህም የፃፍኩት ቃል (string) መሆኑን ለማመልከት ነው። ቁጥር ወይም በፊት define ያረኩት variable ብሆን አልጠቀምም
📖 Using namespace std
ይህ የመጀመርያ C++ version ላይ አልነበረም just ለኮምፓይለሩ namespace እንድጠቀም መናገር አለብን።
ስለዚህ ሁሌም ኮዳችን አናት(head) ላይ ይህችን አትርሱ
using namespace std;

።(ይህ በፅሁፍ ሲሆን ስለማይታይ ከታች ባስቀመጥኩት ፎቶ ላይ መመልከት ትችላላችሁ።)
ከዚህ በመቀጠል ፋይላችንን ሴቭ እናደርጋለን እሱን ለማድረግም በቀስታችን file ሚለውን በመንካት ከዚያም save as ሚለውን በመጫን ወይም ኮንትሮል S (ctrl s) በመንካት የሚመጣው ዊንዶ ላይ ስሙን የፈለጋችሁትን ከሰጣችሁ ቡሀላ .cpp ብላችሁ ቀጥላችሁ ፃፉ ይህም

Yourfilename.cpp

ይህንን ሴቭ አድርጋችሁ ቅድም Quincy ለይ ከሆናቹ (Ctr + Alt + N ) በማድረግ ወይም ሌላ ከሆነ run በመንካት አስጀምሩት። ወይም የሚሮጥ ሰው አይነት አይከን አለ እሱን መጫን አለብን።
👍2
ማጠቃለያ

#include<iostream>
using namespace std;
int main()
{
cout<< "Hello world "
}

Result (out put):
------------------------------
Hello world
---------------------------------
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
3⃣ Comments
በprogramming ውስጥ ኮድ ስንፅፍ comment መጠቀም በጣም የተለመደና ጥሩ ልምድ ነው።
ኮምፓይለሩ ኮዳችንን run ስያደርግ በኮሜንት መልክ የተፃፈውን ይተወዋል....
ኮዳችንን ኮመንት ማድረግ!
••••••••••••••••••••••••••
ኮመንት ማድረግ ማለት ኮዳችንን ለሚያነቡ ሰዎች ስለ ኮዳችን ቀላል ማብራርያን ወይም መረጃን የምንሰጥበት መንገድ ነው:: ይህ ኮመንት የተንዛዛ መሆንም የለበትም በቀላሉ ማስተላለፍ የፈለግነውን መልእክት በአጭሩ መግለፅ አለብን::

ኮዳችንን ኮመንት ማድረግ ጠቀሜታው ኮዳችንን ለሚያነቡ ሌሎች ሰዎች ብቻ ሳይሆን እኛም ተመልሰን ከጊዝያት ቡሀላ ኮዳችንን እንዳንረሳው እና በቀላሉ እንድናስታውስ ያግዘናል::

ማስታወሻ:-
ፕሮግራማችንን በከፈትነው ጊዜ ኮመንት ያደረግነው ነገር ለተጠቃሚዎች አይታይም::

ከምስሉ እንደምትረዱት ኮመንት እንደተፃፈ የምታውቁት ኮዱን ከከፈታችሁ ብቻ ነው::

ማሳሰብያ:-
የተለያዩ ሰዎች እንዲያዩ ማይፈለጉ ነገሮችን በኮመንት ውስጥ መፃፍ አይመከርም::
ለምሳሌ: ፓስወርዶች ወይንም ክሬዲት ካርድ ቁጥሮች የመሳሰሉትን ከመፃፍ ይቆጠቡ
••••••••••••••••••••••••••••••••

Example Comments

#include<iostream>
using namespace std;
int main()
{
// this is comment
cout<<"Hello world "
// put your comment here
}

Output
Hello World
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••


እስካሁን የተነጋገርነውን አደረጋችሁ? ውጤቱንም አገኛችሁ? እንኳን ደስ አላችሁ የመጀመርያችሁን C++ ኮድ ሰርታችኋል💪። በሚቀጥሉት ክፍሎች በዚ ትምህርቶች ስላሉ ተከታተሉን ፔጁን ላይክ እና ሼር በማድረግ ይተባበሩን። በሌላ ክፍል እስክንገናኝ ሰላም ቆዩን።

Next On This Channel:
💚 Standard Input Output
💛 Variables
❤️ If & else + functions
🧡 Data Structure stay tuned

ይቀጥላል
1
C++ ምንድን ነው? ከላይ ያልርውን ፓስት ይመልከቱ! 👆👆👆
C++ TUTORIAL 👆👆👆
👍1
በቃሌ መሰረትና በቴሌግራም ቻናል አባላቶች ምርጫ መሰረት የመጽሐፎችን፣ ጋይዶችን፣ ሪሰርቾችን፣ ሪፈረንሶችን፣ ወርክሽቶችን፣ ልብወለዶች በፒዲኤፍ(PDF)አፕልኬሽኖችን ለመጫን የሚያስችል እራሱን የቻለ የቴሌግራም ቻናል Ethiopian Digital Library የሚል ቻናል ከፍቻለሁ። ስለዚህ ወደዚህ ቻናል እንድትቀላቀሉ ግብዣየ ነው።
👇👇👇👇👇ይጫኑ👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
What is C Programming Language?
ሲ (የኮምፒዩተር ፕሮግራሚግ ቋንቋ) ምንድን ነው?
ሲ የኮምፑተር ፕሮግራሚንግ ቋንቋ (የተለመደ አጠራሩ ሲ )
የኮምፒውትር ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ሲሆን ለ ዪኒክስ የሲስተም አሰሪ ተብሎ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ በደኒስ ሪቺ (Dennis Ritchie) ተሰርቶ ቀረበ። ከዚያ ወዲህ በአብዛኛው የኮምፒዩተር የሲስተም አሰሪ ተስፋፍቶ በአለም በስፋት ከሚያገለግሉ ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች አንዱ ነው።
ሲ ሌሎች ታዋቂ ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ገጽታ ላይ ታላቅ ሚና ተጫውቶዋል። በተለይም ሲ++ ለሲ ማሻሻያ ተብሎ የታቀደ ቋንቋ ነው። የተመጠነና ብቃት ያለው ኮድ ለማውጣት የተመቻቸ ቋንቋ ሆኖ ሲታወቅ፣ የሲስተም አሰሪ ሶፍትዌሮችን ለመስራት የተለመደ ቋንቋ ሆኖ ሳለ ሌሎች ሶፍትዌሮችንም ለመጻፍ በስፋት ያገለግላል።
የC ቋንቋ
The language was formalized in 1988 by the American National Standard Institute (ANSI).
የ UNIX OS ሙሉ በሙሉ በሲ ፕሮግራሚግ ቋንቋ የተጻፈ ነው።
Cross-platform ሲሆን በማንኛውም ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማለትም በWindows, Unix/Linux and Mac የሚሰራ የፕሮግራሚንግ አይነት ነው።
አሁን ላይ ያሉ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች የሲ ፕሮግራሚንግ ቋንቋን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የC programming የአጻጻፍ ቅርጽ ወስደዋል ለምሳሌ C++ን ጨምሮ C# , Unix's C shell , D, Go , Java , JavaScript (including
transpilers), Julia, Limbo , LPC, Objective-C , Perl, PHP , Python , Rust , Swift , Verilog.
ስለዚህ C ፕሮግራሚንግ አሁን ላይ ላሉ የአለማችን ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች መሰረት የጣልና የፕሮግራሚንግ አቢዮት እንዲፈነዳ ያደረገ ነው።
C በAmerican National Standard Institute (ANSI) ህጋዊነቱንና የፕሮግራሚንግ መስፈርቱን ያሟላበት በ1988 ነበር።
ሲ መጀመሪያ ላይ ለስርዓት ልማት ሥራ (system development) በተለይም ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ለሚያካሂዱ ፕሮግራሞች ጥቅም ላይ ውሏል ፡፡
አንድ የ C ፕሮግራም ከ 3 መስመሮች እስከ ሚሊዮኖች መስመሮች መጻፍ ይቻላል።
በC programing የተጻፈ ፕሮግራም save ስናደርግ
የጽሑፍ ፋይሎችን ከቅጥያ ጋር መጻፍ አለበት ".c"; ለምሳሌ, hello.c ብለን ማስቀመጥ ይኖርብናል ማለት ነው።
ለ C የፕሮግራም ቋንቋ ለምስራት ከፈለጉ በኮምፒተርዎ ላይ የሚከተሉትን ሁለት የሶፍትዌር መሳሪያዎች ያስፈልጉዎታል
1 Text Editor and
2 The C Compiler.
Text Editor ፕሮግራማችንን ለመጻፍ የሚጠቅመን ነው Examples Windows Notepad, OS Edit command, Brief, Epsilon, EMACS, and vim or vi.
A C program የሚከተሉትን ያካትታል−
Preprocessor Commands
Functions
Variables
Statements & Expressions
Comments
ቀላል የC ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ፕሮግራም እንደሚከተለው አቅርቤላችኋለሁ።
#include <stdio.h>
int main () {
/* my first program in C */
printf ( "Hello, World! \n" );
return 0 ;
}
ከላይ ያለውን ፕሮግራም መግለጫ
የፕሮግራሙ የመጀመሪያ መስመር #include<stdio.h> የቅድመ-ፕሮሰሰር ትእዛዝ ነው ፣ ይህም ወደ ትክክለኛ ማጠናቀር ከመሄዱ በፊት ለ C ኮምፓይለር የ stdio.h ፋይልን እንዲያካትት ይነግረዋል፡፡
ቀጣዩ መስመር int maim () የፕሮግራሙ አፈፃፀም የሚጀመርበት ዋና ተግባር ነው ፡፡
የሚቀጥለው መስመር ኮሜንት ሱባል /*...*/ በኮምፓይለሩ እንዳይነበብ /*ውስጥ*/ ምንም ብንጽፍ ኮምፓይለሩ አያንብበውም እናም በፕሮግራሙ ውስጥ ተጨማሪ አስተያየቶችን እንድንጨምር ይረዳናል፡፡ ስለዚህ እንደዚህ ያሉ መስመሮች በፕሮግራሙ ውስጥ አስተያየቶች(Comment) ተብለው ይጠራሉ ፡፡
የሚቀጥለው መስመር printf (...) “Hello world” የሚል መልእክት ወደ እስክሪናችን የሚያወልን ወይም የሚያሳየን ነው፡፡
የሚቀጥለው መስመር return 0; የmain () ተግባሩን ያጠናቅቃል እና values ወደ 0 ይመልሳል።
በተጨማሪም ለማንበብ
👇
https://www.tutorialspoint.com/cprogramming/index.htm
👇 https://en.m.wikipedia.org/wiki/C_(programming_language)
በPDF ቴሌግራም ላይ እጭናለሁ።
አስተያየት ካላችሁ ኮሜንት ላይ ወይም በ
ወደ ቴሌግራም ቻናሌ ለመግባት ከፈለጋችሁ https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ወደ Ethiopian Digital Library ለመግባት ከፈለጋችሁ https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary