Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ሲም ካርድን ይተካል የተባለው #ኢ_ሲም ምንድን ነው…?
እንደ ኦ.ኢ.ኤም፣ አፕል እና ጎግል ያሉ የስማርት ስልክ አምራቾች ደግሞ በአዳዲስ ምርቶቻቸው ላይ ኢ ሲም ማካተት መጀመራቸው ተሰምቷል። “ኢ ሲም ምንድን ነው”..? ካላችሁ ኢ ሲም ልክ እንደ መደበኛው ሲም ካርድ በስማርት ስልካችን ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለን ነው። ነገር ግን ኢ ሲም በቀጥታ በስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ የሚገጠም እንጂ እንደ ከዚህ በፊቱ አይነት ማስገቢያ የሚፈልግ እንዳልሆነ ተነግሯል። ኢ ሲምን አጠቃቀም አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው ሲም ካርድ ጋር ሲነጻጸር ቀላል እንደሆነም ነው የተነገረው። እንዲሁም ኢ ሲም አንድ ጊዜ የስማርት ስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ ከተገጠመ በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ እንደሚሆንም ነው የተጠቆመው። ከዚህ በተጨማሪም ኢ ሲም የስማርት ስልክ አምራቾች በጣም ጠፍጣፋ ስልክ ለማምረት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ እንደሆነም ነው የተገለፀው። በአሁኑ ወቅትም አንድ አንድ የስማርት ስልክ አምራቾች በስልኮቻቸው ላይ ከመደበኛው ሲም ካርድ በተጨማሪ ኢ ሲምን እንደ አማራጭ እያቀረቡ እንደሆነም ተነግሯል። አሁን በገበያ ላይ የዋሉ እና ኢ ሲምን የሚቀበሉ ስማርት ስልኮችም ጎግል ፒክስል 2፣ ጎግል ፒክስል 2 XL፣ ጎግል ፒክስል 3፣ ጎግል ፒክስል 3 XL፣ ጎግል ፒክስል 3a፣ ጎግል ፒክስል 3a XL፣ አይፎን XS፣ አይፎን XS Max፣ አይፎን XR፣ አይፓድ ፕሮ እና ኳልኮም ስናፕድራጎን 850 ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ዊንዶውስ 10 ኮምፒውተሮች ይገኙበታል።
ሼር ማድረግዎን አይርሱ፤፤ መልካም ቀን ይሁንልዎ
Like እና Share ማድረግ አይርሱ!
====================
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍41
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ሲም ካርድን ይተካል የተባለው #ኢ_ሲም ምንድን ነው…? እንደ ኦ.ኢ.ኤም፣ አፕል እና ጎግል ያሉ የስማርት ስልክ አምራቾች ደግሞ በአዳዲስ ምርቶቻቸው ላይ ኢ ሲም ማካተት መጀመራቸው ተሰምቷል። “ኢ ሲም ምንድን ነው”..? ካላችሁ ኢ ሲም ልክ እንደ መደበኛው ሲም ካርድ በስማርት ስልካችን ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለን ነው። ነገር ግን ኢ ሲም በቀጥታ በስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ የሚገጠም እንጂ እንደ…»
እንዴት የኮምፕይተራችንን ፍጥነት መጨመር እንችላለን
የ ኮምፒዩተራቹ operating system window 10 ነው? በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል? እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን።
. Power option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ
.Disable unwanted start up programs
ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል
Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን)
ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ። እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።
.Defragment and optimize drive
Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ
. Delete unnecessary temporary file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።
. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ
Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ
እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት
. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ
ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን
በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ
. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R)
regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user
Control panel
Mouse
Mouse hover time
valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ
Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር
. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ
Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ
Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ
በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ
ሼር ማድረግዎን አይርሱ፤፤ መልካም ቀን ይሁንልዎ
Like እና Share ማድረግ አይርሱ!
====================
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍71
በታሪክ ሳተላይት ቴቪ ወደ ገበያ የወጣው እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው ። ሁሉም ነገር ግዙፍ፤ ከባድና ውድ ነበር። እድል ገጥምዎት እቃውን ሁሉ ቢገዙ እንኳን መገጣጠሙ ሌላ ስራ ነበር።
ሳተላይት ቴቪ ከብሮድካስት ቴቪ በተለምዶ አንቴና ቴቪ ከምንለው ጋር በብዙ ተመሳሳይ ነው። ሁለቱም ገመድ አልባ በሆነ መንገድ የሬዲዮ ሲግናልን በመጠቀም የቴሌቪዥን ስርጭትን ለተጠቃሚ የማቅረብ ዘዴ ነው። የሳተላይት ቴቪ ከ ብሮድካስት ቴቪ የተሻለ ቴክኖሎጂ የሆነበት ምክንያት እጅግ በበለጠ ከፍታ ላይ ባሉ ሳተላይቶች ሰፊ የምድርን አካል በእይታ ውስጥ በመክተቱ ነው። ይህም በቀላሉ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ጥራት እንዲደርስ ያደርገዋል።
ዛሬ የሳተላይት ቴሌቪዥን ተጠቃሚዎች ጣቢያዎቻቸውን የሚያገኙት በቀጥታ ስርጭት ሳተላይቶች Direct Broadcast Satellites - DBS አቅራቢዎች bein , Sky , DirecTv , Dish Network በመሳሰሉት ነው።
እንዴት ይሰራል? 4ቱ ክፍሎች
በምቹ ሶፋችን ላይ ቁጭ ብለን የሪሞታችንን ቁልፎች በመጫን በቀላሉ እየቀያየርን የምንመለከታቸው ፕሮግራሞች እንዴት ውስብስብ ሂደቶችን እንደሚደርሱን እንመልከት!
ምንጭ የሆኑ የዝግጅት ጣቢያዎች ክፍል
እነዚህ እንደ HBO ,ESPN ,CNN የመሳሰሉት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ናቸው። ተወዳጅ የሆኑ የቴሌቪዥን ዝግጅቶችን እያዘጋጁ መሬትን በመሬት ፍጥነት እኩል እየዞሩ ወዳሉት ሳተላይቶች ይልካሉ። እንደ ABC ,CBS ,FOX ,Nbc ያሉ ሃገራዊ ጣቢያዎች ስርጭታቸውን በቅጥታ ወደ ሳተላይቶች አይልኩም። ይልቁንም ከፍተኛ ጥራት ያለውን እና እጅግ ብዙ Gb ሲግናላችውን በምንም አይነት የለውጥ ሂደት Compression ሳያልፍ በፋይበር ኦፕቲክ ኬብሎች ወደ ማሰራጫ ጣቢያዎች ይልካሉ። ይህ ሲሆን ደግሞ እነዚህ ሲግናሎች እጅግ የተወሳሰበ ሳይንሳዊ ሂደቶችን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል ::
ማሰራጫ ጣቢያ
ይህ ክፍል የተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ወደ ሳተላይት የላኩትን ሲግናል በምቀበል ወደ ዲጅታል ሲግናል በመቀየር ወደ ሌላ ሳተላይት በድጋሚ ይልካል።
ዲሽ
አሁን ሁላችንም ወደምናውቀው ምዕራፍ ደርሰናል። ይህ ክፍል በየቤታችን ጣሪያ ላይ እና በየብሎኮቻችን ግድግዳ ላይ የምናገኛቸው ከማሰራጫ ጣቢያዎች የተለያዩ ሂደቶችን ያለፉ የሳተላይት ሲግናሎችን የሚቀበሉ ሰሀኖች ናቸው።
የዲሽ ሰሀኖች ሁለት ዋና ክፍሎች አሏቸው
የሬዲዮ ጨረሮችን እንዲቀበል ምቹ ተደርጎ የተሰራ Parabolic Surface ሩብ ክብ የሆነ የብረት ሰሀን። እና
Low Noise Block - LNB የራዲዬ ጨረሮችን የማጉላት እና አላስፈላጊ ጨረሮችን የማጥራት ስራ የሚሰራው ክፍል ነው።
መቀበያ ረሲቨር
ከLNB የሚመጣውን ሲግናል ወደ ምስል እንዲቀየር አድርጎ ወደ ቴሌቪዥናችን የሚልከው ክፍል ነው።
ረሲቨር ሁለት ዋና ዋና ስራዎች ይከውናል።
በIT ባለሙያዎች ኮድ የተደረጉ የተቆለፉ ሲግናሎችን ውስጡ ባለው ቺፕ አማካኝነት መክፈት።
የተከፈቱትን ዲጂታል ሲግናሎች MPEG-2 እና MPEG-4 ወደ አናሎግ በመቀየር ወደ ቴሌቪዥን መላክ።
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «በታሪክ ሳተላይት ቴቪ ወደ ገበያ የወጣው እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው ። ሁሉም ነገር ግዙፍ፤ ከባድና ውድ ነበር። እድል ገጥምዎት እቃውን ሁሉ ቢገዙ እንኳን መገጣጠሙ ሌላ ስራ ነበር። ሳተላይት ቴቪ ከብሮድካስት ቴቪ በተለምዶ አንቴና ቴቪ ከምንለው ጋር በብዙ ተመሳሳይ ነው። ሁለቱም ገመድ አልባ በሆነ መንገድ የሬዲዮ ሲግናልን በመጠቀም የቴሌቪዥን ስርጭትን ለተጠቃሚ የማቅረብ ዘዴ ነው። የሳተላይት…»
የተለያዩ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች ሎጎዎች ትርጉም
1. Apple
የ computer science አባት ተብሎ የሚጠራው Alen Turing በ ሁለተኛው የ አለም ጦርነት ወቅት enigma code በመባል የሚታወቀውን የ German military command የሚስጥር ኮድ በመስበር ሚሊየኖችን ከሞት ለመታደግ ችሏል ነገር ግን ለደህንነት ስጋት ነው ተብሎ ስለታሰበ በ cyanide የተለወሰ apple በመስጠት አንዴ ከመጉመጡ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በዚህም ምክንያት Apple ካምፓኒ እሱን ለመዘከር ሎጎው አድርጎታል።
2. Amazon
የ online መገበያያ የሆነው አማዞን ሎጎ አይታቹት ከሆነ ከ A ተነስቶ እስከ Z ድረስ የሚሄድ ቀስት አለው። ይሄም የሚያሳየው ምንም ነገር አማዞን ላይ ተፈልጎ እንደማይታጣ ሲሆን ፤ Amazonየሚለው ስም ደሞ ከ አለማችን ትልቁ
ደን እና ወንዝ ከሆነው ከብራዚሉ Amazon የተወሰደ ሲሆን የድርጅቱን ግዝፈት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው።
3. Nike known as " SWOOSH "
የ ራይት ምልክት በ ግሪክ አፈታሪክ ውስጥ የ እንቅስቃሴ ፣ የመብረር ፣ የ ድል እና የፍጥነት ምልክትን ነው። የተወሰኑት እንደሚያስቡት የ check mark ምልክት አይደለም። ናይክም ይሄን ለመግለጽ ነው ምልክቱ ያደረገው።
4. Facebook
የፌስቡክ ምልክት small capital " f " ነው። ይሄም ፌስቡክ የሚለውን የሚገልጽ መሆኑን ብዙዎቹ ያምናሉ ነገር ግን ከዚህ በተጨማሪም ሰው አጎንብሶ ሲጠቀም ያሳያል የሚል መላምንትም አለ። ሰማያዊ የሆነው ደሞ የ fb ፈጣሪ የሆነው zuckerberg color blindness ስለሆነ ነው።
5. IBM
የተለያዩ የ electronics ምርቶችን የሚያመርተው international business machine IBM ሎጎው ላይ ያለው ነጫጭ ወደ ጎን የተሰመሩ መስመሮች የሚያመለክተው ከምንም በፊት እኩልነት ይቅደም የሚለውን ነው።
6 እናንተስ የምታውቋቸውን ድረጅቶች አርማ ትርጉም ኮሜንት ላይ ጻፉልኝ
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍2
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «የተለያዩ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች ሎጎዎች ትርጉም 1. Apple የ computer science አባት ተብሎ የሚጠራው Alen Turing በ ሁለተኛው የ አለም ጦርነት ወቅት enigma code በመባል የሚታወቀውን የ German military command የሚስጥር ኮድ በመስበር ሚሊየኖችን ከሞት ለመታደግ ችሏል ነገር ግን ለደህንነት ስጋት ነው ተብሎ ስለታሰበ በ cyanide የተለወሰ apple በመስጠት አንዴ…»
#ኦርጅናል Samsung smart ሞባይሎችን በቀላሉ ማወቅ ይፈልጋሉ
መጀመሪያ *#06# ብለዉ ሲደውሉ የ IMEI ቁጥሩ ለምሣሌ
351532046393715 እዚህ ላይ ከመጀመሪያ ይቁጠሩ
''04" በ 7ና8ኛ ድጅት ይገኛል ስለዚህ
7&8 ከሆነ የchina low quality ነው
80 or 08 የጀርመን fair quality.
10 or 01 የfinland good quality.
00 ከሆነ original factory በጣም አሪፍ quality.
13 Azerbaijan ከሆነ በጣም መጥፎ (bad) quality.
03 or 04china ግን ጥሩ ከ 00,01 ያነሰ ነው።
ልብ ይበሉ 05 China ,Brazil,USA, Finland ሊሆን ይችላል።
06 China, mexico, Brazil ሊሆን ይችላል ።
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍2
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «#ኦርጅናል Samsung smart ሞባይሎችን በቀላሉ ማወቅ ይፈልጋሉ መጀመሪያ *#06# ብለዉ ሲደውሉ የ IMEI ቁጥሩ ለምሣሌ 351532046393715 እዚህ ላይ ከመጀመሪያ ይቁጠሩ ''04" በ 7ና8ኛ ድጅት ይገኛል ስለዚህ 7&8 ከሆነ የchina low quality ነው 80 or 08 የጀርመን fair quality. 10 or 01 የfinland good quality. 00 ከሆነ original factory…»
የራም ማስታወሻን ለመዘርጋት የሚያገለግሉ መስመሮች በሁለት ዋና ክፍሎች እንከፍላቸዋለን፡፡
1. ተቀያያሪ ራም (Dynamic RAM)
2. የማይቀያየር ራም (Static RAM)
1. ተቀያያሪ ራም (Dynamic RAM)
በካፓሲተር ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ነው
በየጊዜው የማስታወስ ሀይሉን ካፓሲተሩን በመሙላት የሚያገለግል ነው
ፍጥነቱ ዝግ ያለ ሲሆን የሚፈልገውን የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ግን አነስተኛ ነው
ብዙ መጠን መረጃን የማቀፍ ችሎታ አለው
የያዘውን መረጃ በተደጋጋሚ በኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያስታውስ ይደረጋል፡፡ አልበለዚያ መረጃው ይጠፋል
በብዙ ኮምፒተሮች ውስጥ እንደ ዋና ማስታወሻ ክፍል ይጠቀሙበታል፡፡
2. የማይቀያየር ራም (Static RAM)
መረጃውን የኤሌክትሪክ ሀይል እስካለ ድረስ ያለምንም ችግር በፍጥነት መረጃን የመመዝገብ ችሎታ አለው
በትራሲስተር ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ኤሌክትሪክ በተደጋጋሚ በመስጠት ይዘቱን እንዲያስታውስ ማድረግ አያስፈልግም፡፡
የሚጠቀመው የሀይል መጠን ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ሙቀት ያመነጫሉ
በአብዛኛውን ጊዜ ፍጥነት በሚያስፈልጋቸው ኮምፒተሮች ላይ እንጠቀምበታለን
መረጃን ለመመዝገብ የሚያስፈልገው የማስታወሻ የመያዝ መጠኑ አነስተኛ ነው፡፡
ROM (Read Only Memory)፡- ይህ የሚሞሪ ዓይነት ከስሙ መረዳት እንደምንችለው መረጃዎችን ለማንበብ ብቻ ይገለግላል፡፡ እዚህ ሚሞሪ ላይ ያሉትን መረጃዎች መጻፍ ወይም መቀየር አይቻልም፡፡ መረጃዎችን ግን ለዘለቄታው ያስቀምጣሉ፡፡
ROM የምንለው የማስታወሻ አካል ወይም ሜሞሪ ተለዋዋጭ ያልሆነ መመሪያዎችን ለሁል ጊዜ የሚይዝ ነው፡፡ ኤሌክትሪክ ኃይል ቢቋረጥም ሆነ ባይቋረጥ የያዘውን መረጃ የማያተን ነው፡፡ ROM ኮምፒተሩ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን በላዩ ላይ የተሰሩትን የተለያዩ ትዕዛዞችን እንዲያነብ እንጂ እንዲፃፍበት የማይፈቅድ እና ኮምፒተሩ በተደጋጋሚ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን የሚጠቀምበት መመሪያዎችን የሚይዝ የሜሞሪ ዓይነት ነው፡፡ ተጠቃሚው በውስጡ ያሉትን መረጃዎች ለማንበብ ይችላል እንጂ የመለወጥ ወይም በላዩ ሌላ ተጨማሪ መረጃ መፃፍ አይችልም፡፡ ስለዚህም በሮም ላይ ያሉ መረጃዎች በዋናነት እንዲያገለግሉ ተደርገው ኮምፒተሩ በፋብሪካው በተሰራበት ወቅት የተፃፈ መመሪያዎችን የያዘ ማስታወሻ ወይም ሜሞሪ ሲሆን በኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋት የያዘውን መረጃ አያጠፋም፡፡ ROM የምንለው ማስታወሻ ዋና ዋና ትዕዛዞችን የያዘ መመሪያ የምናስቀምጥበት ስፍራ ነው፡፡ እነዚህንም መሠረታዊ መነሻ ሀሳብንና ውጤቱን ማቀናጃ (Basic input output system (BIOS) መመሪያዎችን ኮምፒተሩ ስራ በሚጀምርበት ጊዜ መጀመሪያ ሊያገኘው የሚፈልገው መነሻ ሀሳብ ነው፡፡ እነዚህ መሰረታዊ መመሪያዎች በዋናነት በኤሌክትሪክ መረጃ መዝገብ ተመስግበው ይቀመጣሉ፡፡ ለምሳሌ አንድን በስርዓት የተዘጋጀ መጽሀፍ ብንገዛ እናነበዋለን እንጂ ያለደራሲው ፍቃድ የማሻሻል እና የመፃፍ መብት የለንም፡፡
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር