Muhammed Computer Technology (MCT)
37.3K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
​​​​✳️ Arduino Programming
◽️ Banzi በ2005 (እ.ፈ.አ) የተጀመረው Arduino (ሲነበብ አርድዊኖ) የኤሌክትሮኒክስ ፕሮጀክቶች ለመስራት የምንገለገልበት የቴክኖሎጂ ውጤት ነው!

◽️ አርድዊኖ ፕሮግራማብል (Program ከጻፍን በኋላ ምንጭንበት) ሰርኪውት ቦርድና (Circuit Board) IDE (Integrated Development Environment, ኮድ ወይም ፕሮግራም ምንጽፍበት ሶፍትዌር) ያካትታል!

◽️ C/C++ የፕሮግራም መጻፍያ ቋንቋ (programming language) ላይብረሪዎች በመጠቀም ስራውን ሚከውነው አርድዊኖ, ኮምፒተራችንን በመጠቀም IDEው ላይ የጻፍነውን ኮድ በUSB ኬብል በመጠቀም ሰርኲት ቦርዱ ላይ መጫን ይኖርብናል!

◽️ የአርድዊኖ ቦርድ ማይክሮኮንትሮለር (microcontrollers) ስር የሚካተት ሲሆን ከማይክሮፕሮሰሰርስ (microprocessors, እንደነ Raspberry_Pi, የአርድዊኖ ዓይነት ፕሮግራማብል ቦርድ) ካሉት የሚለየው የራሱ Firmwareና Operating System ስለሌለው ነው!

◽️ አርድዊኖ በምንጽፈው ኮድ ተመስርቶ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ለምሳሌ የሰዎችና ስፒከሮች ድምጽ (Voice Sensor), የመብራትና የጸሀይ ብርሃን (Light sensor), የሰዎች እንቅስቃሴ (Movement Sensor) ወይም ጽህፎች (Text Inputs) እንደ ግብአት በመጠቀም ሌላ ውጤት (Output) መፍጠር ይችላል!

◽️ የአርድዊኖ ፕሮግራም ለመጻፍ/ለመጠቀም የአርድዊኖ ሰርኲት ቦርድ (ምስሉ ላይ ያለው ለምሳሌ, አርድዊኖ ኡኖ, $39 ይሸጣል) መግዛትና
አርድዊኖ IDE (በነጻ ይገኛል) ሊኖረን ይገባል!

◽️ በአርድዊኖ ከተሰሩ ስራዎች ለመጥቀስ ያክል የጣት አሻራ, የርቀት መለክያ እቃዎችና የህጻናት ማጫዎቻ ሮቦት አሻንጉሊቶች ይገኙበታል
።
ውድ የቻናሌ ተከታታዮች የት ሆነው ነው የሚከታተሉኝ?
Anonymous Poll
28%
አዲስአበባ
9%
ባህርዳር
2%
አዳማ
4%
ሀዋሳ
6%
ጎንደር
1%
አሶሳ
2%
ድሬዳዋ
8%
ደሴ
5%
ደ/ማርቆስ
36%
ሌላ
Microsoft የሰራቸው Operating ሲስተሞችና የተሰሩበት ዓመት በፈረንጆቹ
📍Windows 1.0 (1985)
📍Windows 2.0 (1987)
📍Windows 3.x (1990, 1992)
📍Windows 95 (1995)
📍Windows 98 (1998)
📍Windows ME (2000)
📍Windows XP (2001)
📍Windows Vista (2006)
📍Windows 7 (2009)
📍Windows 8 (2012)
📍Windows 8.1 (2013)
📍Windows 10 (2015)
📍Windows 10X (2020) (only for Tablets)
# የዌብሳይት_ጥቆማ
=============
የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ
#5 የነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ድህረገፆች
(ብዙ መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ ሼር ያድርጉት)
1) Stanford Engineering Everywhere(SEE)
ይህ ድረገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው። ድረገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።
2) MIT Open እና Courseware
የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው # የድረገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች
# የኢንተርኔት ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው። ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።
3) GitHub.com
በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድህረገጽ ነው። እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድህረገጽ ዓይነት ነው።
4) W3 Schools
ይህ ድህረገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፡ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት ይሰጣል።
በተጨማሪም # በድረገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።
5) Codecademy
አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድህረገጽ ነው። በተለይ # ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።
ብዙ # መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ # ሼር ያድርጉት..
#ኦርጅናል Samsung smart ሞባይሎችን በቀላሉ ማወቅ ይፈልጋሉ?
መጀመሪያ *#06# ብለዉ ሲደውሉ የ IMEI ቁጥሩ ለምሣሌ 351532046393715 እዚህ ላይ ከመጀመሪያ ይቁጠሩ ''04" በ 7ና8ኛ ድጅት ይገኛል
ስለዚህ 7&8 ከሆነ የchina low quality ነው
🛑 80 or 08 የጀርመን fair quality.
🛑 10 or 01 የfinland good quality.
🛑◽00 ከሆነ original factory በጣም አሪፍ quality.
🛑 13 Azerbaijan ከሆነ በጣም መጥፎ (bad) quality.
🛑 03 or 04china ግን ጥሩ ከ 00,01 ያነሰ ነው።
🛑 ልብ ይበሉ 05 China ,Brazil,USA, Finland ሊሆን ይችላል።
🛑 06 China, mexico, Brazil ሊሆን ይችላል ።
✅ The numbers 05 or 50 indicates that your galaxy smartphone is manufactured either in
Brazil, USA or Finland
✅ The numbers 08 or 80 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in
Germany Or China
✅ The numbers 01 or 10 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in
Finland
✅ The numbers are 02 or 20 indicates that your galaxy smartphone is assembled in UAE or India
✅ The numbers 03 or 30 indicates that your phone is made in China or South Korea
✅ The numbers 04 or 40 indicates that your phone is made in China or UK
✅ The numbers 06 or 60 indicates that your galaxy smartphone is manufactured either in
Hong Kong, China, Mexico or France
✅ The numbers 00 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in the Original Factory
✅ The numbers 13 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Azerbaijan
✅ The numbers 07 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Germany
✅ The numbers 20 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Germany
✅ The numbers 70 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Finland
✅ The numbers 91 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Finland
✅ The numbers 41 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in the UK
✅ The numbers 44 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in the UK
✅ The numbers 18 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Singapore
✅ The numbers 67 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in the US
✅ The numbers 71 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Malaysia
✅ The numbers 81 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in China
👍1
ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ምንድነው?
ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ምንድነው?በኮምፒዩተር ኢንዳስትሪ እንደፋሽን ቦግ ብልጭ የሚሉ ቴክኖሎጂዎች በየግዜው ይከሰታሉ። ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ከዚህ አንጻር ተጠቃሽ የሚባል ቴክኖሎጂ ነው። ቃሉን በቀጥታ ወደ አማርኛ ከተረጎምነው “ዳመና ላይ ማስላት” ማለት ሲሆን ይህ ዓይነት ትርጉም መስጠት አንገታችንን ቀና አድርገን ዳመና ፍለጋ መዞር እና ግራ መጋባት ልያስከትል ይችላል።
በአጭሩ ሲገለጽ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ የኮምፒተር አገልግሎቶች፤ ማለትም ሰርቨሮች፣ የውሂብ ማጠራቀምያዎች፣ አውታረመረቦች፣ ሶፍትዌሮች እና ሌሎች አገልግሎቶችን ኢንተርኔት (ክላውድ) ተጠቅሞ የሚያቀርብልን ቴክኖሎጂ ነው። ይህ ማለት ውሂብ ወይም ዳታ የምናስቀምጠው በኮምፒተራችን ሳይሆን፤ ሌሎች ድርጅቶች በሚቆጣጠሩት ኮምፒዩተር ነው ማለት ነው። ያስቀመጥነውን ውሂብ ማግኘት ስንፈልግ፣ ኢንተርኔትን ተጠቅመን ወደ የግላችን ኮምፕዩተር መገልበጥ ወይም እዛው ክላውድ ላይ እያለ በ ማሰሻ(browser) ከፍተን ማየት እንችላለን። ይሁን እና ክላውድ ኮምፒዩቲንግ ውሂብ ማከማቻ ጎተራዎች ብቻ አይደለም በ አገልግሎት መልክ የሚያቀርብልን፤ ማንኛውም ኮምፒተራችን ላይ ማድረግ የምንችለውን ተግባር በተሻለ ፍጥነት እና ዋጋ ማከናወን የሚይስችለን ቴክኖሎጂ ነው።
ከክላውድ ኮምፕዩቲንግ መምጣት በፊት፤ ሶፍትዌር የሚያመርቱ እና የሚጠቀሙ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ብዙ ዓይነት ሶፍትዌር እና ሃርድዌር ገዝተው ይጠቀሙ ነበር። ይህ ውድ እና ውስብስብ ከመሆኑም በላይ፤ ለአጭር ግዜ ብቻ መጠቀም የምንፈልገውን ሃርድዌር ከመግዛት ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረም። በዚህም ምክንያት ወደ ገበያ ለመግባት የሚፈልጉ ድርጅቶች ከጅምሩ ብዙ ወጪ ማውጣት ግድ ይላቸው ነበር። ድርጅቶች ከጅምሩ ምን ያክል የውሂብ ማጠራቀምያ (storage)፣ የማስያ ጉልበት(processing power) ወዘተ…. እንደምያስፈልጋቸው በቀላሉ መገመት አይችሉም።
ድርጅታቸው ከሚፈልገው በላይ ጉልበት ያላቸው ሃርድዌር ከገዙ ለ አላስፈላጊ ወጪ ይጋረጣሉ፤ ካሳነሱት ደግሞ ሲስተማቸው ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ይታገላል። ይህንን ዓይነት ችግር ለመፍታት ክላውድ ኮምፒዩቲንግ ወሳኝ ቴክኖሎቹ ሁኖ ብቅ ካለ ሰነባብቷል።
እንደ አማዞን፤ ማይክሮሶፍት እና ጉግል የመሳሰሉ ድርጅቶች ብዙ ክፍተኛ አቅም ያላቸውን ኮምፒተሮችን አዘጋጅተው ለድርጅቶች እና ግለሰቦች ያከራያሉ። ለምሳሌ አንድ ሰው 100 ኮምፒተሮችን ተጠቅሞ ውስብስብ የሆነ የ ኮምፒተር ሲሙሌሽን መስራት ቢፈልግ፤ 100 ኮምፒተሮችን መግዛት አይጠበቅበትም ማለት ነው። ከ አማዞን እነዛን ኮምፒተሮች ተከራይቶ ተገቢውን ሶፍትዌር ኮምፒተሮቹ ላይ በርቀት(ኢንተርኔት ተጠቅሞ) ይጭናል። የፈለገውን ስራ አከናውኖ የተገኘውን ውጤት ወደ ራሱ ኮምፒተር መውስድ ይችላል። ይህ ሰውዬ እንደዚህ በማድረጉ ብዙ ነገር አትርፏል።
አንደኛ ስራው መጀመርያ እንዳሰበው በ 100 ኮምፒተሮች ብቻ የማይከናወን ከሆነ በቀላሉ ተጨማሪ ኮምፒተሮችን ማሰማራት ይችላል። ለዚህም ነው ክላውድ ኮምፒዩቲንግ ተለጣጭ (elastic) ባህሪ አለው የሚባለው።
ሁለተኛ ሰውዬው የሚከፍለው ብር ልክ እንደ ውሃ እና ኤሌክትሪክ፤ በተጠቀመበት መጠን ነው፤ እነዛን 100 ኮምፒተሮች ለ አንድ ሰዓት ብቻ ከተጠቀመ፣ የሚከፍለው በዛ ልክ ብቻ ነው።
ስለ ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ጥቅም እና ምንነት አንድን ምሳሌ በማንሳት አውርተናል። ይሁን እና ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ሳናውቀው በብዙ መልኩ እንጠቀምበታለን። የሞባይላችን ውሂብ መጠባበቅያ(backup) ስናስቀምጥ፤ ኢሜል ስንጠቀም ወዘተ… ውሂባችን ክላውድ ላይ እይተቀመጠ ነው። ለዛም ነው ስልካችን ቢጠፋም አስፈላጊውን ቅጽ በመሙላት የጠፉብንን ውሂቦች የምናገኘው። ፌስቡክ ደግሞ ካየነው ሙሉ በሙሉ ክላውድ መሰረት ያደረገ አፕሊኬሽን ነው፤ ምክንያቱም ኢንተርኔት እስካለን ድረስ ማንኛውንም ፌስቡክ ላይ ያደረግነውን እንቅስቃሴ በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነን ማየት ስለምንችል።
በተለምዶ ኮምፒተራችን ላይ ጭነን የምንጠቀምባቸው ሶፍትዌሮች በብዛት ወደ ክላውድ እየተዘዋወሩ ነው። ለምሳሌ አብዛኞቻችን ከምንጠቀምበት የ ከማይክሮሶፍት ኦፊስ ምርት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ግን ሙል በሙሉ ክላውድ ላይ የተመሰረተ ጉግል ዶክስ የሚባል ምርት በ ጉግል ለተጠቃሚዎች ቀርቧል።
⚫️ ዩቲዩብ (You Tube)

◽️ቻድ ሀርሊ፣ ስቲቭ ቻን፣ እና ጃዉድ ካሪም በተሰኙ ሶስት ግለተሰቦች ቪዲዮን በድረ-ገጽ ለብዙሃን ለማሳየት ታስቦ የተሠራዉ ዩቲዩብ ለጥቅም የዋለዉ በ2005 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ነበር። በተፈጠረ በዓመቱ የጉግል ኩባንያ ዩቲዩብን በመግዛት የኢንተርኔት ዘርፉን ተቆጣጠረበት። የመጀመሪያዉ የዩቲዩብ ቪድዮ የተጫነዉ በ2005 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ጃዉድ ካሪም በተባለ ከዩቲዩብ መስራቾች አንዱ በሆነዉ ግለሰብ ነበር። ይህ ቪድዮ ከተጫነበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ በመቶ ሚሊዮኖች፣ የሚቆጠሩ ቪድዮዎች ተጭነዋል። ዩቲዩብን ተወዳጅና ስኬታማ ያደረገዉ በየትኛዉም የዓለም ክፍል የሚገኝ ማንኛዉም ሰዉ ቪዲዮዉን በቀላሉ እና በፍጥነት በመላዉ ዓለም እንዲታይ ማስቻሉ ነዉ። ይህ ደግሞ ግለሰቦች ፍጹም ኖሯቸዉ የማያዉቀዉን በዓለም አቀፍ ደረጃ በቢሊየኖች የመታየት ሃይልን አጎናጽፏቸዋል። በርካቶች የተለያየ ችሎታቸዉን አሳይተዉ ታዋቂና ባለጸጋ ለመሆንም በቅተዋል።

. ከ1.5 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚ ያለዉ ዩቲዩብ በየወሩ በአጠቃላይ ቢደመር ከ3.25 ቢሊዮን ሰዓት በላይ ርዝመት ያለዉን ቪድዮ ለእይታ ያቀርባል። ጉግል ሰዎች በሚጭኗቸዉ በእነዚሁ ቪድዮዎች ላይ ማስታወቂያን በማሳየት ከዩቲዩብ ብቻ በየዓመቱ ከ4 ቢሊዮን ዶላር (የ2016 ዓ.ም. መረጃ) በላይ ገቢ በየዓመቱ ያገኛል። ቪድዮዎቻቸዉን በዩቲዩብ የሚለቁ ግለሰቦችም ቪድዮዎቻቸዉ በታዩ ቁጥር ተያይዘዉ ከሚታዩት ማስታወቂያዎች ላይ ገንዘብን ያፍሳል።
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።
🖥 የዘመናዊ ኮምፒዉተር አፈጣጠርና እድገት አጭር ታሪክ

🔘1950ዎቹ - በ "ቫኪዩም ቲዩብ" ብቻ ይሰሩ የነበሩት ኮምፒዉተሮች መጠናቸዉ የአንድ ቤት መጠን እስኪያክል ድረስ እጅግ ግዙፍ የነበሩ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ እጅግ ቀርፍፍ ነበሩ። በወቅቱ እነዚህን ኮምፒዉተሮች በብቸኝነት ይጠቀምባቸዉ የነበረዉ የአሜሪካ ሚሊቴሪ ተቋም ሲሆን ዋጋቸዉም የትም የሌለ ነበር።

🔘1960ዎቹ - በትራንዚስተሮች መፈጠር የተነሳ ቀርፍፍዉን የ"ቫኪዩም ቲዩብን" አሰራርን በመቀየር የኮምፒዉተሮች የአካል መጠን መቀነስ ሲቻል ብቃታቸዉንም ማሻሻል ተቻለ። በዚህ ወቅት ነበር ሜይንፍሬም (mainframe) የተባሉ ፈጣንና ወድ ኮምፒዉተሮች ተፈጥረዉ ከማሊቴሪና የመንግስት ተቋም አልፎ ለግል ድርጅቶች ጥቅም መዋል የጀመሩት።

🔘1970ዎቹ - በመቶዎች የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮችን ያካተተ ኢንቴግሬትድ ሰርኪዩት "Intergrated Circute Board" አንድ ክፍልን ሊሞላ የሚችል መጠን ያለዉን የሜይንፍሬም ኮምፒዉተር አሳንሶ በጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ ኮምፒዉተር "Desktop" እንዲፈጠር አስቻለ።

🔘1980ዎቹ - በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮች እጅግ በጣም ትኝሽ መጠን ባለዉ የኮምፒዉተር ቺፕ ዉስጥ ህያዉ መሆን የኮምፒዉተር በጣም አንሶ በአንዲት ቦርሳ ዉስጥ የሚገባና ከድርጅት አልፎ ለግል ጥቅም መዋል የሚችልበት "Personal Computer (PC)" ዘመን ተወለደ። ኮምፒዉተሮች ጠረጴዛ ላይ ከመቀመጥ አልፈዉ ጭን ላይ የሚቀመጡበትን መጠን ይዘዉ "laptop" በሚል ስያሜ ብቅ አለ።

🔘1990ዎቹ - የኢንተርንት መወለድ ኮምፒዉተሮች እርስ በእርሳቸዉ እና በሌላ ቦታ ከሚገኝ ከፍተኛ አቅምና የመረጃ ብዛት ያለዉ የኮምፒዉተር ስብስብ "datacenter" ጋር ተገናኝተዉ ከዚህ ቀደም በራሳቸዉ አቅም ብቻ ከሚሰጡት አገልግሎት እጅግ የላቀ ጥቅምን በፍጥነት መስጠት እንዲችሉ አደረገ።

🔘2000ዎቹ - ለእጃችን መዳፍ እንኳን የማይሞሉ፣ ነገር ግን ብቃታቸዉ ከአንድ መጠኑ ከፍ ካለና ምርጥ ከሚባል ኮምፒዉተር ያልተናነሰ ተግባር ማከናወን የሚችሉ እንደ ረቀቀ ስልክ (Smartphone) ያሉ ተንቀሳቃሽ ቁሶች (mobile devices) በስራ ላይ ዋሉ። ከስልኮችም አልፈዉ ታብሌቶቻችን፣ ሰዓቶቻችን፣ የቤት ቁሶቻችን፣ መኪናዎቻችን እና ልብሶቻችን ሳይቀሩ የኮምፒዉቲንግ ብቃት እየተካተተላቸዉ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ ይህ ዘመን አብሮን ባለ ኮምፒዉተር ላይ ብቻ ከመደገፍ ይልቅ እንደ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ (Cloud computing) እና የመሴሰሉት የተራቀቁ በኢንተርኔት ተገናኝተዉ መሰራት የሚችሉ እና ከእኛ ርቀዉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተበታትነዉ በሚገኙ እጆግ ፈጣን ኮምፒዉተሮች አማካኝነት በርካታ ተግባር ማከናወን ተቻለ። ቀደም ሲል እንደተጠቀሰዉ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ ማለት የኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች ሶፍትዌርኝ፣ ሃርድዌርን፣ መረጃን አና የተለያዩ ዲጂታል አሠራሮችን በራሳቸዉ ኮምፒዉተር ላይ ከመጫን ይልቅ ካሉበት ሰርቨሮች በኢንተርኔት አማካኝነት በየትኛዉም ጊዜና ቦታ ልክ መቦራትና ዉሃ ቤታችን ድረስ እንደሚመጣዉ ከአገለግሎት ሰጪዎች ላይ በሚፈልጉት መጠን መጠቀም የሚያስችል አሠራር ነዉ።

ይህ ሁሉ ፈጽሞ የበቃ በማይመስልበት ሁኔታ የኮምፒዉተር እድገትና ፍጥነት ሩጫዉን ቀጥሏል። ከላይ የተጠቀሰዉን አስደናቂ የኮምፒዉተር የለዉጥ እድገት ህያዉ ያደረገልን የMoore's Law ወደ ፍጻሜ እየመጣ ያለ ይመስላል።
ምክንያቱም የትራንዚስተሮች እጅግ አናሳ በሆነ መጠንና በጣም በተጠቀጠቀ ሁኔታ በአነስተኛ ቦታ ላይ እንዲያርፉ የሚደረግበት የቺፕ አሠራር የመጨረሻ ገደቡና ጥጉ ላይ እየደረሰ ስለመጣ ነዉ። አንድን ትራንዚስተር ምንም ያህል እናሳንሰዉ ብንል ከአቶሚክ መጠን በታች ልናደርገዉ አንችልም። ይህ ሂደት ወደ ፍጻሜዉ እየተቃረበ የመምጤቱን ጉዴይ ባለሞያዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና አምራቾችም ይስማሙበታል። የትንቢቱ ባለቤት ጎርደን ሙር እራሱ በ2015 ዓ.ም. በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ከ50 ዓመታት በፊት የተነበየዉ Moore's Law ማክተማያዉ እየተቃረበ እንደመጣ ጠቁሟል።

ኮምፒዉተር እስከዛሬ በዚህ አይነት የረቀቀ የእድገት ሂደት ዉስጥ ካለፈ፣ "ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?" የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮ ይመጣል።

🤷‍♂ "ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?"

በእርግጥ ቀጣዩቹ ኮምፒዉተሮች ምን አይነት ይሆኑ ይሆን? የወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች በጨረር፣ በኳንተም የፊዚክስ ህግ እና በሰዉነታችን ዉስጥ በሚገኙ በዲኤንኤ አማካኝነት የሚሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም በማንኛዉም ቁስ ላይ ተለጥፈዉ የሚገኙ፣ ወይም ደግሞ የራሳችን ኮምፒዉተር ሳያስፈልገን በሌላ ቦታ ተቀምጠዉ በኢንተርኔት አማካኝነት ያላቸዉን አቅም ሙሉ በሙሉ ከፈለግነዉ ቦታ ሆነን መጠቀም የምንችልባቸዉ አይነቶችም ሊሆኑ ይችላሉ።

የፋይበር ኦፕቲክስ "Finer-optic" ወይንም በጨረር አማካኝነት መረጃን ከአንድ ኮምፒዉተር ወደ ሌላዉ በፈጣን ሁኔታ በማስተላለፉ አሰራር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በፋይበር ኦፕታክስ የሚተላለፉ መረጃዎች በኤሌትሪክ ሽቦ ዉስጥ ከሚተላለፉት ፍጥነታቸዉ በእጅጉ የተሻለ ሲሆን፣ በተጨማሪም እንደ ኤሌክትሮማግኔቲክ ያሉ የተለያዩ ጣልቃ ገብ ግብዓቶች አሠራሩን አያደናቅፉትም ። ታድያ ለምን ከኤሌትሪክ ትራንዚስተር ይልቅ በጨረር የሚሰራ ኮምፒዉተር መስራት አይቻልም? ይህን ማድረግ ከተቻለ የኮምፒዉተሮችን የዉስጥ የመረጃ አቀማመር አቅም እጅጉን እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል። ምንም እንኳን ተመራማሪዎች በዚህ ዙርያ ተስፋ ሰጪ የሙከራ ስራዎች ቢያከናዉኑም መጠኑ ያነሰና በብዛት ተመርቶ በኮምፒዉተሮች ዉስጥ ሊገጠም የሚችልን በጨረር የሚሠሩ ቺፕ ህያዉ ለማድረግ ሙሉ ስኬትን እስከአሁን አላገኙም።

በጨረር አማካኝነት የሚሰሩ ኮምፒዉተሮችን ለመፍጠር በሚደረገዉ ምርምር የኢትዮጵያዉ ዶክተር ሰለሞን አስፍ እጅ አለበት። ዶክተር ሰለሞን የበርካታ ፈጠራ ስራዎች ባለቤት ሲሆን በዋናነት የሚታወቅበት የፈጠራ ስራዉ በተለመደዉ አሠራር በኤሌትሪክ ከሚሰሩ ትራንዚስተሮች ይልቅ ኮምፒዉተሮች በብርሃን ጨረር (optical pulse) አማካኝነት መረጃን ለማስላት የሚችሉበትን ሙከራ ያደረገበት የምርምር ስራዉ ነዉ። ይህ ግኝት ለወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች አሁን ካሉት ማሽኖች እስከ አንድ ሺህ እጥፍ ፍጥነት እንደሚሰጣቸዉ ሲጠበቅ፣ የኤሌክትሪክ ፍጆታንም በእጅጉ ይቆጥባል ተብሏል። የዶክተር ሰለሞን ዋና ግኝት ፎቶዲቴክተር (photodetector) የሚባሉትና የብርሃን ጨረር መልዕክትን (optical signals) አጉልተዉ የሚያስተላልፉ ቁሶች (በሞያዊ አጠራራቸዉ "amplifiers") እንዴት አድርገዉ መልዕክትን ለማይክሮፕሮሰሰሮች በሚገባ መንገድ በማስተላለፍ ጨረር መልዕክቶችን ወደ ኤሌክትሪክ መልዕክት (electrical signals) በመቀየር ለኮምፒዉተር አሰራር ጥቅም እንዲዉሉ ማድረግ ነዉ።
የሞባይል ባትሪን እድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች
አንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የሚጎረብጡ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችንን ከሚጎረብጡ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሞባይል ባትሪ ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ፣ በዚህ ዙሪያ ለሳይቴክ ደንበኞች መላ የሚሆን ነገር አናቀርብላቸውም ብለን አሰብን… ምን ትላላችሁ?
ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ የተሰሩት ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) ሲሆን ይሄም ባትሪ በአግባቡ ካለመጠቀም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ ይደክማል፤ ያረጃል፡፡ ይሄም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡ የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው ሲሆን ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ የሚያስግሩባቸውን ምክንያች እና ባትሪን በተሻለ መጠቀም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች እንደሚከተለው እንጠቁማችኋለን፡፡
የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡-
1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም
ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡
2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡
3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር
በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት
ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ
የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
ፕሮጀክት ቀረፃ
******************
******************
አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

1⃣ ማውጫ (Table of contents)
ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡
ማውጫ ሁሉንም ምዕራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

2⃣ አጭር መግለጫ (Executive Summary)
ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው የሚገቡ ሃሳቦች

✅ ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር
✅ ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ
✅ ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ
✅የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ
✅ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም
✅ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡

3⃣መግቢያ (Back Ground)
ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-
✅ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ
✅ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው
✅ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡

4⃣ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale)
ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡

5⃣የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective)
ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡
ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡

6⃣የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description):-

✅ የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ
✅ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ
✅የፕሮጀክቱ ቀጣይነት
✅የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት
✅ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ አለበት፡፡

7⃣የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization):-

✅ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ
✅የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር
✅የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡

8⃣የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮች ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries):-

✅ተጠቃሚዎች (Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡
✅ያገባኛል ባዮች (stakeholders):-
የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (Primary stake holders)፡-

በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡

9⃣የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation):-

የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው በማን፤ እንዴት፤ መቸና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡

1⃣0⃣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption):-

✅ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡

✅ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡

1⃣1⃣ ክትትና ግምገማ (Monitoring and Evaluation):
ይህ ርዕስ የሚይዛቸው፡-

✅የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት እንደሚቀርብ
✅ የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት
✅ የግምገማ ዕቅድን
✅ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ

1⃣2⃣ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት (sustainability):
ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡
👍2😁1
ብዙዎቻችን የ Google እና የGmail አካዉንት ልዩነት ግራ🤔 ያጋባናል?

ከዚህ በመቀጠል ልዬነታቸዉን አናያለን።

ጎግል #አካዉንት Google Account ምድነዉ?

✅ ጎግል አካዉንት ማለት ጎግል የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች ለምሳሌ እንደ Gmail, Google+,Google hangouts ,Google drive እንድናገኝ የሚያደርገን ነዉ።

✅ዋናዉ የጓግል አገልግሎት #Service Gmail ነዉ።
አንድ ሰዉ የ Gmail አካዉንት ለመክፈት መጀመሪያ የ Google አካዉንት መክፈት አለበት።

✅ጎግል አካዉንት ለመክፈት የሚያስፈልገን #User name እና #Phone number ነዉ።

✅ጎግል አካዉንት ሌላ ተጨማሪ አገልግሎት ይሰጠናል።

ለምሳሌ

✅Google+ ማለት #internet ላይ መሠረት ያደረገ ማሀበራዊ ኔቶርክ ነዉ።

✅Google hangouts የመገናኛ ዘዴ ነዉ። የ Messaging ,Video chat,SMS እና VOIP #features ይይዛል።

✅Play Store የተለያዩ አፕልኬሽኖችን ለስልካችን እንድናወርድ ይረዳናል።

✅አንዳንድ የ Google አገልግሎቶች ለመጠቀም የ Google አካዉንት አይጠይቁም ለምሳሌ #Google book እና Google map።

Gmail አካዉንት ምንድነዉ?

✅Email #digital መልእክቶችን በ #Internet ላይ በጥቂት ሰከንዶች ዉስጥ መላላኪያ መንገድ ነዉ።

✅እኛ email እንድንልክ እና አንድንቀበል የሚያደርጉ የተለያዪ የ email አገልግሎት አቅራቢዎች(Service Provier) አሉ ።

✅በዛዉ Gmail አገልግሎት ሰጭዉ ሲሆን email ደግሞ የሚሰጠዉ አገልግሎት ነዉ።

✅Gmail የ#Google አገልግሎት አቅራቢ (Service Provider) ነዉ።

✅አንድ ተጠቃሚ #desktop computer, laptop, smart phone, tablet በመጠቀም ወደ Gmail አካዉንቱ #log in ማድረግ ይችላል።

✅የሚጠቀምበት #device internet connection ሊኖረዉ ግድ ይላል።

✅የተለያዩ email client አሉ ለምሳሌ #Hotmail , #Yahoo ነገር ግን በጣም ታዋቂዉ Gmail ነዉ።

Gmail ብዙ ጥቅሞች አሉት።

✅አንድ #User ለብዙ ተቀባዮች(recepants ) መልእክት መላክ ይችላል።

✅#Text, attach document,insert image and link ማድረግ ይችላል።

✅ከዚህ በተጨማራ ትላልቅ ፋይሎችን #Google drive ላይ #upload ያደርጋል። #Spam filterin ይሰጣል።virus protection እና email reminder አገልግሎት
ይሰጣል።
ስለተከታተላችሁን እናመሠግናለን🙏
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንዴት ናችሁ? 👆👆👆
አሁን ደግሞ ይዤላችሁ የመጣሁት እኛን ትምህርት ቤታችንን፣ ወረዳችንን፣ ዞናችንን፣ ክልላችንን፣ እንዲሁም ሀገራችንን ሊጠቅም የሚችል ምርጥ የፈጠራ ስራ ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ። ስራውም ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ የግልም ሆነ ለመንግስት ትምህርትቤቶች የሚጠቅም ከዚህ በፊት የነበረን የወረቀት የተማሪዎችን የመረጃ አያያዝ ወደ ኮምፒውተራይዝድ Online system(Students Information Management System) ይዤላችሁ ምርጥቻለሁ። ስለሆነም ከጥቅሙ ስነሳ
✅ የትምህርት ቤቶች የመረጃ አያያዝ በጣም ዘመናዊ የሚያደርግ።
✅ የሀብት፣ የጉልበት እንዲሁም የጊዜን ብክነት ሙሉበሙሉ በሚባል ደረጃ የሚቀንስ።
✅ ለመምህራን፣ ለተማሪዎች፣ የመረጃ አያያዝ ባለሙያዎች ስራንና መረጃ አያያዝን ቀላልና ቀልጣፋ የሚያደርግ።
✅ ሌላም ሌላም ዘርፈ ብዙ ስራዎችንና ጫናወችን የሚቀንስ።
◄◄◄ የሚሰራቸው ስራዎች▻▻▻
✅ የመረጃ ሲስተሙ ለብዙ አመታት መረጃን መያዝ የሚችል ነው። የአንድ አመትን ውጤት ብቻ ይዞ የሚያቆም አይደለም።
✅ ሲስተሙ እያንዳንዱ የሚመለከተው ተጠቃሚ(Users) ለምሳሌ መምህራን ር/መምህራን የመረጃ ባለሙያዎች በአንድ ላይ እንደማንኛውም ለምሳሌ እንደ ፌስቡክ username and password በማስገባት መጠቀም ይችላሉ።
✅ ሲስተሙ ብዙ ተጠቃሚዎችን ማስጠቀም ይችላል
✅ መምህርንን ተማሪዎችን በአንድ ላይ መዝግቦ ይይዛል።
✅ የመረጃ ስርአቱ በትምህርት ቤቱ ህጋዊ ባለሙያ በአንድ ቦታ ቁጭ ብሎ መቆጣጠር የሚያስችል።
✅ የሚመለከተው አካል ለምሳሌ የትምህርት ቤት ር/ መምህሩ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያለውን የተማሪዎችን ውጤት ያለበትን ሁኔታ ማየትና መከታተል የሚያስችል።
ለምሳሌ ምን ያክል ተማሪ የማለፊያ ውጤት፣ ወደሚቀጥለው ክፍል መዘዋወር ያልቻሉት ምን ያክል ናቸው እንዲሁም ሌሎች ተግባራቶችን ማየትና መሰራት ያለበትን ስራ እንዲያይ ይረዳዋል።
✅ መምህራን ወቅታዊ ውጤት በማስገባት ብቻ ሲስተሙ ለምሳሌ transfer sheet, Roster, student result sheet, ሌሎችንም ያካተተ ሲሆን automatically ሲስተሙ የሚሰራቸው ስራዎች ለምሳሌ የውጤት ድምር፣ አማካይ ውጤት፣ ደረጃን እንዲሁም ሌሎችን መስራት ይችላል።
✅ ለተማሪዎች በ1 ደቂቃ ውስጥ ለምሳሌ የተማሪውን transcript, result sheet በወረቀት ከተፈለገ print በማድረግ አገልግሎት ማግኜት ይቻላል።
✅ የተማሪዎች ማንኛውንም ውጤት አስተማሪው የራሱን ተማሪዎችን ውጤት መሙላት የሚያስችል።
✅ ተማሪዎች የራሳቸውን ውጤት ቀን በቀን ምን ያክል እንደሰሩ መከታተል የሚያስችል።
✅ ተማሪዎች ውጤታቸውን በማየት ማስተካከል ያለባቸው የትምህርት አይነት ጠንክረው በማንበብ እንዲሁም በአለበት እንዲቀጥሉ ማድረግ የሚያስችል።
🛑 ከላይ እንደምሳሌ ጻፍኳቸው እንጁ በጣም ብዙ ስራዎችን መስራት የሚችል ነው። በጣም ለተጠቃሚዎች ቀላል፣ ምቹ፣ ግራ የማያጋባ ነው።
🛑 እናም ይህንን ሲስተም ለመጠቀም የሚገልግ ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤት መጠቀሚ የሚገልግ ካለ በ☎️ 0929273364 ብትደውሉልኝ ወይም በፊስቡክ ፔጄ inbox(መልእክት) ብትልኩልኝ ለማስጠቀም ዝግጁ ነኝ።
ከላይ በምስሉ የምትመለከቱት sample snapshot ነው።
#ሼር በማድረግ አበረታቱኝ!
#ኮሜንት
#like
#አስተያየት ካለ ጻፉልኝ
ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ ልታገኙኝ ትችላላችሁ
👇
https://t.me/ma2323me
👍3
እንዴት ኢሜል #Email አካውንት እንከፍታለን?
✅እንደነገርኳችሁ Email account ለመክፈት መጀመሪያ Google Account መክፈት አለብን።

✅Gmail website ሲገቡ ወደ Google sign up page ይወሰዶታል።

✅መሰረታዊ መረጃዎች name, birth date, gender,እና location እንድታስገቡ ይጠዪቃችኋል።

✅ለሚከቱትፍ email address ስም መስጠት ዪጠበቅባችኋል።

አካዉንቱን ለመክፈት ከታች ያሉትን እስቴፖች ዪከተኩ።

👇👇👇👇👇👇
1⃣የሚወዱtን አሳሽ #browser (Google Chrome, Opera mini, Firefox ,PHX browser ወይም ሌላ) ይክፈቱና www.gmail.com ብለው ይጻፉ

2⃣ከዛ #Create Account የሚለውን ዪጫኑ

3⃣ #Sign Up form ሲመጣላችሁ የሚጠዪቃችሁን #information (First Name ,Last Name, Username እና Password) አስገብታችሁ #Next የሚለውን ተጫኑ

4⃣ከዛ የስልክ ቁጥራችሁን አስገቡ እና አካውንታችሁን #Verify አድርጉ።

👉ስልክ ቁጥራችሁን አስገብታችሁ #Next የሚለውን ስትጫኑ ስልክ ቁጥራችሁ ላይ የማረጋግጫ ኮድ (Verification Code ) በ SMS Google ይልክላች ሗል

5⃣ የተላከላችሁን የማረጋገጫ ኮድ ያሲገቡ እና #Verify የሚልውን ዪጫኑ

6⃣ከዛ #Personal Information ማስገቢያ #form ዪመጣላችኋል ከዛ #Name, Birth day እና Gender አስገብታችሁ #Next የሚለውን ይጫኑ።

7⃣ Privacy and Terms የሚል ሲመጣ I agree የሚልውን ዪጫኑ

8⃣አሁን በሚገባ አካውንታችሁን ፈጥራችኋል🤷‍♀።

አስኪ #Share እና #Like በማድረግ አበረታቱን💪።

ያወቁትን ማሳወቅ መልካምነት ነዉ።
ለጓደኞቻችሁ #Share ↪️ አድርጉ
ስለተከታተሉን እናመሠግናለን🙏
👍3
🔴 ጉግል ተርጓሚ (Google Translate) አማርኛ

ጉግል የፍለጋን ስራ ከማስተናገድ ባለፈ እንደ ኢሜይል አገሌግሎትና ሌሎችንም በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ከእነዚህ አገልግሎቶችም አንዱ ትርጉም ነዉ። የበርካታ አገራትን ቋንቋ በትርጉም ሲያስተናግድ የቆየዉና ጉግል ተርጓሚ (Google Translate) በመባል የሚታወቀዉ የድረ-ገጽ አገልግሎት በቅርቡ ደግሞ የአማርኛ ቋንቋንም አካቷል። ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ወይንም ደግሞ ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ መተርጎም የሚችለዉ አሠራር በአሁኑ ሰዓት የሚሰጣቸዉ ትርጉሞች ጥሩ ጅማሬ ቢሆኑም ገና ብዙ ክፍተቶች ያሉበት እንደሆነ ይታያል። ነገሩን ከበድ ያደረገዉ ደግሞ በእንግሊዝኛና በአማርኛ መካከል በጎንዮሽ የሚሄዱ እና አቻ የሆኑ አዉዳዊ የዓ/ነገር ክምችቶች ገና በመረጃ ቋታቸዉ ወይም "ዳታቤዛቸዉ" ዉስጥ በብዛት አለመኖሩ ነዉ።

በመጠኑ ለማብራራት ያህል፣ የጉግል ትራንስሌት ሶፍትዌር የሚሰራዉ "statistical machine translation" በሚባል ሎጂክ ሲሆን፣ ጉግል በሁለት ቋንቋ መካከል ያሉ የጎን ለጎን የቃላት ክምችቶችን በዳታቤዙ ወስጥ ያጠራቅም እና ልዩ በሆነ የሶፍትዌር ኮድ አማካኝነት ተመሳሳይ ትርጉምን የማግኘት መላምትን ያካሄዳል። ይህ አሠራር "parallel data" ወይንም የጎን ለጎን የዓ/ነገር ትርጉም እኩሌታ መረጃ ላላቸዉ ቋንቋዎች በተሻለ መንገድ ይሠራል። ለምሳሌ፦ English-Spanish በጥሩ ሁኔታ የሚሰራ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ አማርኛን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ቋንቋዎች በጉግል ትራንስሌት ላይ ገና ጅማሬ ላይ ያሉና ገና በርካታ ትክክለኛ ያልሆነ ትርጉም ሊያስገኙ ይችላሉ። ይህ የጉግል ሶፍትዌር ትርጉም አሠራር መዝገበ-ቃላትን ብቻ ከመጠቀም ባለፈ በሳል እንዲሆን የሰዋሰዉና የዓ/ነገር አዉድንም አካቶ መያዝ ይኖርበታል።

በ2016 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. መገባደጃ ላይ ጉግል ይፍ ያደረገዉ የተሻሻለ መተርጎሚያ አሠራር ከሰዉ ተርጓሚ በጣም የተቀራረበ ብቃት እንዳለዉ ኩባንያዉ ገልጾ ነበር። የሰዉ-ሠራሽ ክህሎት ቴክኖሎጂን የሚጠቀመዉ ይህ አዲስ አሠራር "Google Machine Neural Translation" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የትርጉም ስህተትን 80 በመቶ እንደሚቀንስ ተነግሮለታል።
ሊንኩን ከፈለጋችሁ👇
https://translate.google.com
❤1