Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
How to create log in form in HTML&CSS:
ይሞክሩት ሙሀመድ አሚን
<!DOCTYPE html>
<html>
<head>
<title>LOG IN</title>
<style>
/*css*/
body {
}
div{
border:solid black;
border-radius:10px;
background-color:black;
text-align:center;
filter:opacity(85%);
height:80px;
overflow:auto;
margin-left:100px;
margin-right:100px;
-webkit-transition:margin 2s ,height 2s;
transition:margin 2s ,height 2s;
}
div:hover{
margin-left:20px;
margin-right:20px;
height:250px;
}
div ,h1{
color:white;
}
# l {
color:green;
}
# i {
color:green;
}
div input{
border:solid white 1px;
border-radius:10px;
margin-top:20px;
padding-left:10px;
color:white;
background-color:black;
-webkit-transition:background-color 2s;
transition:background-color 2s;
}
div input:hover{
background-color:green;
}
div button{
border:solid black 1px;
border-radius:5px;
width:50px;
height:30px;
margin-top:20px;
background-color:white;
-webkit-transition:background-color 1s;
transition:background-color 1s;
}
div button:hover{
background-color:green;
}
</style>
</head>
<body>
<div>
<h1>
<span id="l">L</span>OG
<span id="i">I</span>N
</h1>
<br />
<input type="email" placeholder="example@email.com"/>
<br />
<input type="password" placeholder="pass word"/>
<br />
<button>log in</button>
</div>
</body>
</html>
#የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ
አረብ መጋቢት 18 እስከ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት ድረስ
እንደምን አመሻችሄ ክቡራን የሰው ልጆች ፣ በአለማችን ከ200 ሀገራትና ግዛቶችን ያዳረሰው የወቅቱ የሰው ልጆች ፈተና የሆነው የኮሮና ቫይረስ 587,990 ሰዎችን ለክፎ 26,909 ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳርጓል
እንዲሁም 2,841 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
132,440 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል
428,641 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል
────────────
በጣልያን ቫይረሱ አሁንም የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +919 ሰዎች ሲሞቱባት ተጨማሪ +5,909 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
───────────────
────────────
ስፔንም በቫይረሱ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 2ኛዋ ሀገር ነች +569 ሰዎች ሲሞቱባት +6,273 አዳዲስ ኬዞችንም አስተናግዳለች።
───────────────
በጠቅላላ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
1ኛ 9,134 ጣልያን
2ኛ 4,934 ስፔን
3ኛ 3,292 ቻይና
4ኛ 2,378 ኢራን
5ኛ 1,995 ፈረንሳይ
6ኛ 1,518 አሜሪካ
──────────────
በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
1ኛ 99,116 ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ
2ኛ 86,498 ጣልያን
3ኛ 81,340 ቻይና
4ኛ 64,059 ስፔን
5ኛ 50,178 ጀርመን
6ኛ 32,964 ፈረንሳይ
7ኛ 32,332 ኢራን
───────────────
የኮሮና ቫይረስን በጋራ እና በግል እንከላከል
የእጃችንን ንፅህና በአግባቡ እንጠብቅ
ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ አንገኝ
ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀት እንጠብቅ!
መልካም አዳር ይሁንላችሁ!
ምንጭ
https://www.worldometers.info/coronavirus/
ሊንኩን በመጫን የሁሉንም ሀገር በኮሮና ቫይረስ የተጠቁትን ሀገሮች ምን ያህሎ ሰው እንደሞተ ለማወቅ ትችላላቹሁ በየቀኑ ግን ቁጥሩ እየጨመረ ነው ፡፡
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
# የኮኮሮና_ቫይረስ_ስርጭት_ወቅታዊ_መረጃ
√ እሑድ መጋቢት 20 እስከ ጠዋቱ 04:00 ድረስ
በመላው አለም በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሞቱት ሰዎች ቁጥር 30 ሽህ አልፏል። ጠቅላላ የቫይረሱ ኬዝም 664,621 ደርሷል
30,889 ሰዎች እስካሁን በቫይረሱ ሞተዋል
142,368 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል
491,361 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል
466,131 ሰዎች በመካከለኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ
25,230 ሰዎች ደግሞ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው
በአሜሪካ የኬሮና ቫይረስ ጉድ እያፈላ ነው። ጠቅላላ ያስተናገደችው ኬዝ 123,776 የደረሰ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም 2,229 ሆኗል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ በአሜሪካ የተመዘገበው +19,452 አዳዲስ ኬዝ የትኛውም ሀገር ላይ ታይቶ አይታወቅም። የሞቱት 525 ሰዎችም በአንድ ቀን ለሀገሪቱ ሪከርድ ሆኗል።
በኒውዮርክ ብቻ ባለፉት 24 ሰዓት 277 ሰው የሞተ ሲሆን 7,137 እዲስ ኬዝም ተገኝቷል። አሜሪካ ካላት ጠቅላላ ኬዝም 53,393 የሚሆኑት ከኒውዮርክ ናቸው።
ጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 889 ሰው ሞቶባት 5,974 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች። ጠቅላላ ሟቾችም 10,023 ሆኗል
ስፔንም ባለፉት 24 ሰዓት 844 ሰው ሞቶባት 7,516 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች። ጠቅላላ ሟቾችም 5,982 ሆኗል
ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 4ኛዋ ሀገር ነች። 319 ሟችና 4,611 አዳዱስ ኬዝ አስተናግዳለች
──────────
√ የመረጃ ምንጫችን:- ስፒዶሜትር ድህረ ገፅ ነው
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች ተገኙ
******
በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡
ምንጭ EBC
👍1
# በኢትዮጵያ_የኮሮና_ቫይረስ_ኬዝ_19_ደርሷል
በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡
#ታማሚ 1
የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን መጋቢት 8፣ 2012 ከብራሰልስ ቤልጅየም እንዲሁም መጋቢት 10፣2012 ዓ.ም ወደ ካሜሮን የጉዞ ታሪክ የነበራት ሲሆን ግለሰቧ የበሽታው ምልክት ስለታየባት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ አድርጋለች፡፡ ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በመጋቢት 19፣2012 ዓ.ም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል፡፡
# ታማሚ 2 እና 3
የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር፡፡ ግለሰቦቹ በመጋቢት 19፣2020 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 በመጠቀም ማግኘት ይቻላል።
ምንጭ:- ጤና ሚኒስትር
ሊንኩን በመጫን የሁሉንም ሀገር በኮሮና ቫይረስ የተጠቁትን ሀገሮች ለማወቅ ትችላላቹሁ በየቀኑ ግን ቁጥሩ እየጨመረ ነው ፡፡
https://www.worldometers.info/coronavirus/
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ተገኙ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ተገኙ።
በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ግለሰቦች የ38 ዓመት ወንድ እና የ35 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።
ሁለቱም ግለሰቦች በተለያዩ ቀናት ወደ ዱባይ የጉዞ ታሪክ የነበራቸው ሲሆን የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ምንጭ FBC
#የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ
እሁድ መጋቢት 20 እስከ ከምሽቱ 1:45 ሰዓት ድረስ
እንደምን አመሻችሁ ክቡራን የሰው ልጆች ፣ በአለማችን ከ200 ሀገራትና ግዛቶችን ያዳረሰው የወቅቱ የሰው ልጆች ፈተና የሆነው የኮሮና ቫይረስ 702,368 ሰዎችን ለክፎ 33,178 ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳርጓል
እንዲሁም 2,321 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
149,215 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል
519,975 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል
────────────
በጣልያን ቫይረሱ አሁንም የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +756 ሰዎች ሲሞቱባት ተጨማሪ +5,217 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
───────────────
────────────
ስፔንም በቫይረሱ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 2ኛዋ ሀገር ነች +624 ሰዎች ሲሞቱባት +5,564 አዳዲስ ኬዞችንም አስተናግዳለች።
───────────────
በጠቅላላ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
1ኛ 10,779 ጣልያን
2ኛ 6,606 ስፔን
3ኛ 3,300 ቻይና
4ኛ 2,640 ኢራን
5ኛ 2,329 አሜሪካ
──────────────
በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
1ኛ 131,403 ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ
2ኛ 97,689 ጣልያን
3ኛ 81,439 ቻይና
4ኛ 78,799 ስፔን
5ኛ 60,659 ጀርመን
6ኛ 38,309 ኢራን
───────────────
የኮሮና ቫይረስን በጋራ እና በግል እንከላከል
የእጃችንን ንፅህና በአግባቡ እንጠብቅ
ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ አንገኝ
ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀት እንጠብቅ!
መልካም አዳር ይሁንላችሁ!
#የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ
ሰኞ መጋቢት 21 እስከ ጠዋቱ 01:30 ሰዓት ድረስ
ውድ የሀገሬ ልጆች በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ ፣ ባለፉት 24 ሰዓት የኮሮና ቫይረስ በመላው አለም 3,110 ሰዎችን የገደለ ሲሆን 58,865 አዲስ ተጠቂዎችም ሪፖርት ተደርገዋል
───────────
ስፔን ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት ቀዳሚዋ ሀገር ነች 821 ሰዎች ሲሞቱባት +6,875 አዳዲስ ኬዞችንም አስተናግዳለች።
────────────
በጣልያን ቫይረሱ አሁንም የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +756 ሰዎች ሲሞቱባት ተጨማሪ +5,217 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
────────
ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በርካታ ሰው የሞተባት 3ኛ ሀገር ነች። 292 ሰዎች ሲሞቱባት ++2,599 አዲስ ኬዝም አስተናግዳለች።
────────
አሜሪካ በ24 ሰዓት ውስጥ በርካታ ኬዝ ያስተናገደች ሀገር መሆኗን ቀጥላለሽ (+18,469) እንዲሁም 264 ሟቾች እንዳሉባትም ሪፖርት አድርጋለች
─────────
ኔዘርላንድ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው ካጡት ውስጥ ነች 132 ሰዎች ሲሞትባት +1,104 አዳዲስ ኬዝ አስተናግዳለች።
────────────
በኢራን ባለፉት 24 የሞቱባት ሰዎች 123 ሲሆኑ +2,901 አዳዲስ ተጠቂዎችንም አስተናግዳለች።
────────────
በብሪታኒያ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 209
ሰው የሞተ ሲሆን +2,433 ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘዋል።
────────
ቻይና ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 5 ሰዎች የሞቱባት ሲሆን +45 አዳዲስ ኬዝ እንዳለባትም ሪፖርት አድርጋለች።
──────────────
ደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +93 አዳዲስ ኬዝና 1 ሞት ያስተናገደች ሲሆን በጠቅላላው 1,280 ኬዝ በማስተናገድም ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ነች።
────────────
ግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት +33 አዳዲስ ኬዝ እና 4 ተጨማሪ ሟች የተገኘባት ሲሆን በጠቅላላው 40 ሞት አስተናግዳ በአፍሪካ በርካታ ሰው የሞተባት ሀገርም ሆናለች።
────────────
አልጄሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ 2 ተጨማሪ ሰው ሞቶባት +57 አዳዲስ ኬዞችንም አግኝታለች ። አጠቃላይ 31 ሰው ሞቶባታል።
───────────
ሞሮኮ በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ +77 የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያገኘችና 1 ተጨማሪ የሞት ሪፖርትም አላት። ጠቅላላ 26 ሰው ሞቶባታል
────────────
በሀገራችን ትላንት ብቻ 5 አዲስ ታማሚ የተገኘ ሲሆን በሀገራችን ያለው ጠቅላላ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ 21 ደርሶ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 2ቱ አገግመው 2 ጃፓናዊ ታማሚዎችም ወደ ሀገራቸው ሄደዋል።
ካሜሮን 4 ሰው ሞቶባት 48 አዲስ ኬዝም አስተናግዳለች
ዲ.ሪ. ኮንጎ በ24 ሰዓት 16 አዲስ ኬዝና 2 ሟች አለባት
አንጎላ በ24 ሰዓት 2 አዲስ ኬዝና 2 ሟች አለባት
ቡርኪናፋሶ 1 ሰው ሞቶባት 15 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች
ቱኒዚያ በ24 ሰዓት 34 አዲስ ኬዝ እስተናግዳለች
ኮትዲቯር በ24 ሰዓት 64 አዲስ ኬዝና 1 ሟች አለባት
ሞሪቲየስ 1 ሰው ሞቶባት 5 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች
────────────
ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ሞት ያስተናገዱ ሀገራት
+821 ስፔን
+756 ጣልያን
+292 ፈረንሳይ
+264 ዩናይትድ ስቴትስ
+209 ብሪታኒያ
ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
+18,469 ዩናይትድ ስቴትስ
+6,875 ስፔን
+5,217 ጣልያን
+4,740 ጀርመን
+2,901 ኢራን
+3,809 ፈረንሳይ
────────────
በጠቅላላ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
10,779 ጣልያን
6,803 ስፔን
3,304 ቻይና
2,640 ኢራን
2,606 ፈረንሳይ
በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
142,178 ዩናይትድ ስቴትስ
97,689 ጣልያን
81,470 ቻይና
80,110 ስፔን
62,435 ጀርመን
አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 33,980 ሺህ ሆኗል
ጠቅላላ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ 722,347 ደርሷል
ጠቅላላ ከቫይረሱ ያገገሙትም 151,766 ሆነዋል
አሁን ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች 536,601 ናቸው
በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙት 509,920 ሆነዋል
በአሳሳቢ ደረጃ የሚገኙትም 26,681 ሰዎች ናቸው
────────────
√ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በጋራ እንከላከል።
# በቅድመ_ጥንቃቄ_እና_በፀሎት_እንበርታ
√ መረጃ አይናቅም ስለዚህ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ
√ ቁጥራዊ መረጃዎቹን ያገኘሁት :- ስፒዶሜትር ዌብሳይት ላይ ነው
───
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህምድ ይፋ አድርገዋል።
በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ_19) በሽታ የተያዙ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን ለማሳወቅ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ባደረገው ተጨማሪ ስልሳ ስድስት (66) የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች በማረጋገጡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሶስት (23) ደርሷል፡፡
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ግለሰቦች በአማራ ክልል ባህር ዳር ነዋሪ የሆኑ የ37 ዓመት ሴትና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ የሆኑ የ32 ወንድ ዓመት ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ ዕለት አስቀድሞ አንደኛዋ ታማሚ መጋቢት 10 ከዱባይ እንዲሁም ሁለተኛው ታማሚ መጋቢት 12 ከአሜሪካ የገቡ ናቸው፡፡ ሁለቱም ታማሚዎች የበሽታው ምልክት በማሳየታቸው በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዘቸው ተረጋግጧል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚዎቹ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ሰዎች የመለየትና ክትትል ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ሁለቱም ታማሚዎች በአማራ ክልል የለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ አስራ ዘጠኝ (19) ታማሚዎች ሲኖሩ አንድ ታማሚ በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ሁለት ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ሲሆን ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡ ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገበር እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
መጋቢት 21 ፣ 2012 ዓ.ም
👍1
# በኢትዮጵያ_የኮሮና_ቫይረስ_ኬዝ_ሙሉ_መረጃ
የወቅቱ የአለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው መጋቢት 03-2012 ሲሆን ዛሬ ላይ በ19ኛ ቀኑ የተጠቂዎች ቁጥር 23 ደርሷል።
እስኪ በሀገራችን የተገኘው 23ቱን ኬዞች እናስታውሳቸው
መጋቢት 3-2012 የመጀመሪያው ታማሚ
1. የ48 አመት ጃፓናዊ የካቲት 25 ከቡርኪናፋሶ የመጣ
መጋቢት 05-2012 ላይ የተገኘባቸው
2 የ44 አመት ጃፓናዊ
3 47 አመት ጃፓናዊ
4 42 አመት ኢትዮጵያዊ
ከመጀመሪያው ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ያላቸውና ሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ
መጋቢት 07-2012 የተገኘበት
5. የ34 አመት ኢትዮጵያዊ መጋቢት 04 ከዱባይ የገባ
መጋቢት 08-2012 የተገኘባት
6. የ59 አመት እንግሊዛዊት የካቲት 23 ከዱባይ የገባች
መጋቢት 10-2012 ላይ የተገኘባቸው
7. የ44 አመት ጃፓናዊ ከመጀመሪያው ታማሚ ጋር የተነካካ
8. የ85 አመት ኢትዮጵያዊት የካቲት 23 ከውጭ የመጡ
9. የ39 አመት ሆስትሪያዊ መጋቢት 6 የገባ
መጋቢት 13-2012 ላይ የተገኘባቸው
10. የ28 አመት ኢትዮጵያዊ ከቤልጅየም መጋቢት 5 ገባ
11. የ43 አመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ መጋቢት 10 ገባ
መጋቢት 14-2012 ላይ የተገኘበት
12- የ34 አመት ኢትዮጵያዊ መጋቢት 04 ከዱባይ የገባ
መጋቢት 18-2012 ላይ የተገኘባቸው
13- የ72 ዓመት ሞሪሸሳዊ መጋቢት 5 ከኮንጎ ብራዛቪል የመጡ
14- የ61 ዓመት የአዳማ ከተማ ኢትዮጵያዊ ይፕትም ያልተጓዙ
15- የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት መጋቢት 12 ከእስራኤል ተመላሽ
16- የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት የውጭ ጉዞ ያላደረገች
መጋቢት 20-2012 ላይ የተገኘባቸው
17- የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ መጋቢት 10 ከካሜሮን የመጣ
18- የ14 አመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ከተማ ነዋሪ
19- የ48 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ከተማ ነዋሪ
20- የ38 ዓመት ወንድ የዱባይ የጉዞ ታሪክ የነበረው
21- የ35 ዓመት ሴት የዱባይ የጉዞ ታሪክ የነበራት
መጋቢት 21-2012 ላይ የተገኘባቸው
22- የ37 ዓመት ሴት የባህር ዳር ነዋሪ ከዱባይ ተመላሽ
23- የ32 ዓመት ወንድ በአዊ ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ ከአሜሪካ ተመላሽ
√ ጠቃሚ መረጃ ስለሆነ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «# በኢትዮጵያ_የኮሮና_ቫይረስ_ኬዝ_ሙሉ_መረጃ የወቅቱ የአለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው መጋቢት 03-2012 ሲሆን ዛሬ ላይ በ19ኛ ቀኑ የተጠቂዎች ቁጥር 23 ደርሷል። እስኪ በሀገራችን የተገኘው 23ቱን ኬዞች እናስታውሳቸው መጋቢት 3-2012 የመጀመሪያው ታማሚ 1. የ48 አመት ጃፓናዊ የካቲት 25 ከቡርኪናፋሶ የመጣ መጋቢት 05-2012 ላይ…»
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምላሽ አሰጣጥን (የኮቪድ-19) አስመልክቶ የተዘጋጀ ዕለታዊ መግለጫ
-------------------
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህ መረጃ እስከ ተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ በአጠቃላይ 1013 የላቦራቶሪ ምርመራ ያደረገ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 66 የላብራቶሪ ምርመራ አካሄዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት (3) ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጧል፡፡ በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ አምስት (25) ደርሷል፡፡
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሁለት ግለሰቦች የ30 ዓመትና የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ በመጋቢት 15 ፣2012 ዓ.ም ወደ ሀገር የገቡ ሲሆን በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን የበሽታውን ምልክት ታይቶባቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ሶስተኛዋ ታማሚ የ60 ዓመት እድሜ ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 6፣2012 ዓ.ም ከፈረንሳይ የተመለሱና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሶስቱም ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ አንድ (21) ታማሚዎች ሲኖሩ ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ሁለት ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡ ነገይቻላን ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገበር እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል::
የጁምዐ እና የጀመዐ ሰላትን አስመልክቶ የዑለማ ምክር ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ:–
★★★★★★★★★★★★★★★
ወረርሽኙ ዛሬ ከደረሰበት ደረጃና ከስርጭቱ ፍጥነት እንዲሁም ከአስቸጋሪነቱ እና ከገዳይነቱ አንፃር የጁምዐ እና የጀመዐ ሰላት ለመተውና ለማስቆም የሚያስገደድ ሸሪዐዊ ምክንያት በመሆኑ ፈታዋ ከተሰጠበት ከዛሬ መጋቢት 22 ቀን 2012 ጀምሮ በሽታው በሰው ልጆች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት መቆሙ በጤና ባለሙያዎች እስከሚረጋገጥበት ጊዜ ድረስ የጁምዐ እና የጀመዐ ሰላት ታግዶ እንዲቆይ የኡለማ ምክር ቤት ወስኗል።
#የኮኮሮና_ቫይረስ_ስርጭት_ወቅታዊ_መረጃ
√ ማክሰኞ መጋቢት 22 ምሽት 02:00 ላይ
በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሟቾቹ ቁጥር 40 ሺህ ያለፈ ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 824,559 ደርሰዋል። በአሜሪካ ብቻ የተጠቂዎች ቁጥር 175 ሺህ አልፏል ፣ በእንግሊዝ በአንድ ቀን ሪከርድ የሆነ በርካታ ሰው ሞቶባታል
በጣልያን ዛሬም የ837 ሰው ሕይወት ተቀጭቷል
ስፔን ዛሬ 553 ሰው ሞቶ 6461አዲስ ኬዝም ተገኝቷል
በብሪታኒያ ዛሬ 381 ሰው ሞቶ 3,009 ኬዝም ተገኝቷል
አሜሪካ ዛሬ ብቻ እስካሁን 283 ሰው ሲሞትባት 11,881 አዲስ ኬዥም አስተናግዳለች ነጠቅላላው 175,669 ኬዝና 3,424 ሞት አስተናግዳለች።
በኢራን 141 ሰው ሲሞት +3,110 አዲስ ኬዝ ተገኝቷል
ኔዘርላንድ ዛሬ +175 ሰው ሞቶባት 845 እዲስ ኬዝም አላት
በቤልጅየም ዛሬ 192 ሰው ሞቶ 876 አዲስ ኬዝም ተመዝግቧል
በሳውዲ አረቢያ ዛሬ 110 አዲስ ኬዝና 2 ሞት የተመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ የቫይረሱ ኬዝ 1,563 ሲሆን 10 ሞትም ተገኝቶባታል
በእስራኤል ዛሬ 136 አዲስ ኬዝና 1 ሞት የተመዘገበ ሲሆን በጠቅላላ በሀገሪቱ 4,831 ኬዝና የ17 ሰዎች ሕይወት ደግሞ ተቀጥፏል።
በአረብ ኢምሬትስ ዛሬ 53 ኬዝና 1 ሞት ተገኝቷል
አልጄሪያ ዛሬ ብቻ 9 ሰው ሲሞትባት 132 ተጨማሪ ኬዝም አላት
ማይናማር ፣ ታንዛኒያ ማዮቴ እና ቤላሩስ ለሀገራቸው የመጀመሪያ የሆነ የሞት ሪፓርት አድርገዋል
በሀገራችን ዛሬ 3 ኬዝ ተገኝቶ ጠቅላላ የተጠቂዎች ቁጥር ወደ 25 ከፍ ሲል 2ቱ ማገገማቸውም ጤና ሚኒስትር አሳውቋል።
824,559 ጠቅላላ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ
40,673 ጠቅላላ እስካሁን የሟቾች ቁጥር
174,359 እስካሁን አገግመው የወጡ
609,527 አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው
578,617 መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ (95%)
30,910 አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ (5%)
* መረጃዎቹ እየመረጥን ያቀረብነው እንጂ የሁሉንም ሀገራት አለመሆኑን እንድታውቁልን እንዲሁም ይህ የዛሬ ወቅታዊ እንጂ የ24 ሰዓት ውጤት አይደለም።
────────────