Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
# BREAKING
መጋቢት 3/2012 ዓ/ም የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በሀገራችን ከተገኘ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት (16) ደርሷል፡፡
መጠንቀቅ ይኖርብናል ዘመዶች። ያአሏህ ምህረትህን ለግሰን!
ምንጭ ፋና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ውሳኔዎች አስተላለፉ
*****
የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ እያደረሰ ያለውን ፈታኝ ሁኔታ ኢትዮጵያ ለመቋቋም እንዲቻላት የሚከተሉት መመሪያዎች እና ተጨማሪ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ውሳኔ አስተላለፉ።
* ጡረታ የወጡ እንዲሁም በትምህርት ላይ ያሉ የጤና ባለሞያዎች ለብሄራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ
* ከዛሬ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ የሚደርሱ እና ለይቶ ለመከላከያ በተዘጋጁት ሆቴሎች ለመቆየት አቅም የሌላቸው መንገደኞች ወደ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተዘዋውረው ለ15 ቀናት እንዲቆዩ የወጣው መመሪያ ተግባራዊ እንዲያደርጉ
* ከዛሬ አንስቶ ለተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንዲቆዩ
* በገበያ ስፍራዎች እና በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ተፈፃሚ እንዲደረግ፤ በፌዴራል መንግሥት አስከፊ ብሔራዊ አደጋ በሚከሰት ጊዜ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች እንዲቋረጡ የማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ መብት አለው። ሆኖም በሕገ-መንግሥቱ የተደነገጉት እርምጃዎች ተግባራዊ ከመደረጋቸው በፊት ዜጎች አካላዊ ርቀት የመጠበቅን መመሪያ ተግባራዊ እንዲያደርጉ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን።
* ሁኔታው ተጨማሪ ድጋፍን የሚጠይቅ ከሆነ ሁሉም ጡረታ የወጡ እንዲሁም በትምህርት ላይ ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀርባለሁ።
* የተለያየ መጠን እና ዓይነት ያላቸው መገልገያዎችን ያየዙ ከ134 በላይ ተቋማት ተለይተው መከላከያ፣ ለይቶ መቆያ እና ለሕክምና እንዲሆኑ ተለይተዋል። ስለዚህ ሁሉም ዜጎች አልጋዎች፣ ፍራሾች፣ አንሶላዎች፣ የመተንፈሻ ቬንትሌተሮች እና ሌሎች መገልገያዎችን ለማሰባሰብ በመሥራት ላይ የሚገኘውን ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
* የማክሮ-ኢኮኖሚ ንዑስ ኮሚቴው የኢኮኖሚ ዘርፉን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ አማራጮችን ለመቀየስ በልዩ ልዩ ዘርፍ ከተሰማሩት ዐበይት የኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ሲያካሂድ ቆይቷል። ይህንን ተከትሎ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የሚከተሉት እርምጃዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ
* የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የገቢ ዕቃዎች እና ግብዓቶች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ይደረጋል
• የፋይናንስ ዘርፉን ጤንነት አስጠብቆ ለማስቀጠል እና ባንኮች በኮሮና ቫይረስ ለተጎዱ ደንበኞቻቸው ጊዜያዊ የብድር እፎይታ እና ተጨማሪ ብድር ለመስጠት እንዲያስችላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ 15 ቢሊዮን ብር ለግል ባንኮች ያቀርባል።
• የውጭ ምንዛሬ የሚያስፈልጋቸው እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ ዕቃዎች እና ግብዓቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለሚያስግቡ አስመጪዎች ባንኮች ቅድሚያ በመስጠት እንዲያስተናግዱ
• *በፋይናንስ አገልግሎት የተነሳ ገጽ ለገጽ መገናኘት እና የብር ንክኪን ለመቀነስ እንዲቻል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
በሞባይል አማካኝነት የሚደረግ ክፍያ እና ገንዘብ የማስተላለፍ ጣሪያውን ከፍ ያደርጋል፡፡
• የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለውጭ ገበያ በሚቀርብ አበባ ላይ የጣለው ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ገደብ በጊዜያዊነት
እንዲነሳ ተደርጓል፡፡
• ኩባንያዎች የተሻለ የገንዘብ ፍሰት እንዲኖራቸው ለማስቻል፣ የገቢዎች ሚኒስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስ አመላለስ ሂደቱን በተለየ መልኩ እንዲያፋጥን ይደረጋል፡፡
• የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የሸቀጦች እጥረት እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠር በንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በኩል የበለጠ ክትትል እንዲደረግ።
ምንጭ፦ EBC
#የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ
አርብ መጋቢት 18 እስከ ጠዋቱ 12:50 ሰዓት ድረስ
ክቡራን የሰው ልጆች በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ ፣ ባለፉት 24 ሰዓት የኮሮና ቫይረስ አስደንጋጭ ቁጥሮች ተመዝግበውበታል
በአሜሪካ የቫይረሱ ኬዝ ከቻይና በልጧል ፣ በጣልያን የሟቾች ቁጥር ከቻይና በሁለት እጥፍ ከፍ ብሏል
በጣልያን በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 712 ሰው ሞቷል
በስፔን ለመጀመሪያ ግዜ በ1 ቀን ውስጥ 718 ሰው ሞቷል
በፈረንሳይ በ24 ሰዓት 365 ሰው ሲሞት ለመጀመሪያ ግዜ ሆኗል
አልጄሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 3 ሰው ሞቶባታል
ግብፅም በ24 ሰዓት ውስጥ 3 ሰው ሰው ሞቶባታል
ደቡብ አፍሪካ ያገኘችው 218 አዲስ ኬዝም ሪከርዷ ነው
ይግረማችሁ አሜሪካ እስካሁን በትኛውም ሀገር ያልታየ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 17,224 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች
ኒውዮርክ ብቻ 38,977 ኬዝ ተገኝቶባት 466 ሰው ሞቷል
የቫይረሱ ስርጭት በከፍትኛ ፍጥነት እየጨመረ ይገኛል ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ በመላው አለም ሪከርድ የሆነ 60,841 አዳዲስ ኬዝ ተገኝቷታ። በ24 ሰዓት ውስጥ የታየው የሞት መጠንም እስካሁን ከነበረው ሁሉ ከፍተኛው ነው 2,792 ሰዎች ሞተዋል።
አሁን ላይ ቫይረሱ 199 ሃገራትን አዳርሶ በመላው አለም 532,237 ሰዎችን አጥቅቶ 24,089 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል።
124,326 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል
383,822 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል
364,465 ሰዎች በመካከለኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ
19,357 ሰዎች ደግሞ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው
───────────────
────────────
ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ሞት ያስተናገዱ ሀገራት
+718 ስፔን
+712 ጣልያን
+365 ፈረንሳይ
+268 ዩናይትድ ስቴትስ
+157 ኢራን
ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
+17,224 ዩናይትድ ስቴትስ
+8,271 ስፔን
+6,615 ጀርመን
+6,203 ጣልያን
+3,922 ፈረንሳይ
───────────────
────────────
በጠቅላላ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
8,215 ጣልያን
4,365 ስፔን
3,292 ቻይና
2,234 ኢራን
1,696 ፈረንሳይ
በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
85,594 ዩናይትድ ስቴትስ
81,340 ቻይና
80,589 ጣልያን
57,786 ስፔን
43,938 ጀርመን
───────────────
────────────
የኮሮና ቫይረስን በጋራ እና በግል እንከላከል
የእጃችንን ንፅህና በአግባቡ እንጠብቅ
ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ አንገኝ
ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀት እንጠብቅ
የተጨናነቁ የትራንስፖርት አመራጮችን አንጠቀም
የጤና ባለሞያዎችን ምክር ሁሌም እንተግብር
የጤና ሚኒስቴር መምሪያዎችን እንከታተል
ስለ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ትክክለኛ መረጃ ከWHO ፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከህበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ያግኙ!
በተጨማሪ በነፃ የስልክ መስመሮች 8335 / 952 ላይ ደውለው መረጃዎችን ያግኙ
በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ውስጥ
√ ከፍተኛ ትኩሳት
√ ሳል
√ ለመተንፈስ መቸገር ዋነኞቹ ናቸው
# በቅድመ_ጥንቃቄ_እና_በፀሎት_እንበርታ
√ መረጃ አይናቅም ስለዚህ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ። ሰላም ለምድራችን ይሁን
───────────────
────────────
እግር_ኳስ_The_Beautiful_Game በልዩነት በጥራት( የተዘጋጀ )
───────────────
────────────
√ የመረጃ ምንጭ ያደረኩት:- ወርልዶሜትር ዌብሳይትን ነው
How to create log in form in HTML&CSS:
ይሞክሩት ሙሀመድ አሚን
<!DOCTYPE html>
<html>
<head>
<title>LOG IN</title>
<style>
/*css*/
body {
}
div{
border:solid black;
border-radius:10px;
background-color:black;
text-align:center;
filter:opacity(85%);
height:80px;
overflow:auto;
margin-left:100px;
margin-right:100px;
-webkit-transition:margin 2s ,height 2s;
transition:margin 2s ,height 2s;
}
div:hover{
margin-left:20px;
margin-right:20px;
height:250px;
}
div ,h1{
color:white;
}
# l {
color:green;
}
# i {
color:green;
}
div input{
border:solid white 1px;
border-radius:10px;
margin-top:20px;
padding-left:10px;
color:white;
background-color:black;
-webkit-transition:background-color 2s;
transition:background-color 2s;
}
div input:hover{
background-color:green;
}
div button{
border:solid black 1px;
border-radius:5px;
width:50px;
height:30px;
margin-top:20px;
background-color:white;
-webkit-transition:background-color 1s;
transition:background-color 1s;
}
div button:hover{
background-color:green;
}
</style>
</head>
<body>
<div>
<h1>
<span id="l">L</span>OG
<span id="i">I</span>N
</h1>
<br />
<input type="email" placeholder="example@email.com"/>
<br />
<input type="password" placeholder="pass word"/>
<br />
<button>log in</button>
</div>
</body>
</html>
#የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ
አረብ መጋቢት 18 እስከ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት ድረስ
እንደምን አመሻችሄ ክቡራን የሰው ልጆች ፣ በአለማችን ከ200 ሀገራትና ግዛቶችን ያዳረሰው የወቅቱ የሰው ልጆች ፈተና የሆነው የኮሮና ቫይረስ 587,990 ሰዎችን ለክፎ 26,909 ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳርጓል
እንዲሁም 2,841 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
132,440 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል
428,641 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል
────────────
በጣልያን ቫይረሱ አሁንም የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +919 ሰዎች ሲሞቱባት ተጨማሪ +5,909 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
───────────────
────────────
ስፔንም በቫይረሱ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 2ኛዋ ሀገር ነች +569 ሰዎች ሲሞቱባት +6,273 አዳዲስ ኬዞችንም አስተናግዳለች።
───────────────
በጠቅላላ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
1ኛ 9,134 ጣልያን
2ኛ 4,934 ስፔን
3ኛ 3,292 ቻይና
4ኛ 2,378 ኢራን
5ኛ 1,995 ፈረንሳይ
6ኛ 1,518 አሜሪካ
──────────────
በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
1ኛ 99,116 ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ
2ኛ 86,498 ጣልያን
3ኛ 81,340 ቻይና
4ኛ 64,059 ስፔን
5ኛ 50,178 ጀርመን
6ኛ 32,964 ፈረንሳይ
7ኛ 32,332 ኢራን
───────────────
የኮሮና ቫይረስን በጋራ እና በግል እንከላከል
የእጃችንን ንፅህና በአግባቡ እንጠብቅ
ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ አንገኝ
ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀት እንጠብቅ!
መልካም አዳር ይሁንላችሁ!
ምንጭ
https://www.worldometers.info/coronavirus/
ሊንኩን በመጫን የሁሉንም ሀገር በኮሮና ቫይረስ የተጠቁትን ሀገሮች ምን ያህሎ ሰው እንደሞተ ለማወቅ ትችላላቹሁ በየቀኑ ግን ቁጥሩ እየጨመረ ነው ፡፡
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
# የኮኮሮና_ቫይረስ_ስርጭት_ወቅታዊ_መረጃ
√ እሑድ መጋቢት 20 እስከ ጠዋቱ 04:00 ድረስ
በመላው አለም በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሞቱት ሰዎች ቁጥር 30 ሽህ አልፏል። ጠቅላላ የቫይረሱ ኬዝም 664,621 ደርሷል
30,889 ሰዎች እስካሁን በቫይረሱ ሞተዋል
142,368 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል
491,361 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል
466,131 ሰዎች በመካከለኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ
25,230 ሰዎች ደግሞ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው
በአሜሪካ የኬሮና ቫይረስ ጉድ እያፈላ ነው። ጠቅላላ ያስተናገደችው ኬዝ 123,776 የደረሰ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም 2,229 ሆኗል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ በአሜሪካ የተመዘገበው +19,452 አዳዲስ ኬዝ የትኛውም ሀገር ላይ ታይቶ አይታወቅም። የሞቱት 525 ሰዎችም በአንድ ቀን ለሀገሪቱ ሪከርድ ሆኗል።
በኒውዮርክ ብቻ ባለፉት 24 ሰዓት 277 ሰው የሞተ ሲሆን 7,137 እዲስ ኬዝም ተገኝቷል። አሜሪካ ካላት ጠቅላላ ኬዝም 53,393 የሚሆኑት ከኒውዮርክ ናቸው።
ጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 889 ሰው ሞቶባት 5,974 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች። ጠቅላላ ሟቾችም 10,023 ሆኗል
ስፔንም ባለፉት 24 ሰዓት 844 ሰው ሞቶባት 7,516 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች። ጠቅላላ ሟቾችም 5,982 ሆኗል
ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 4ኛዋ ሀገር ነች። 319 ሟችና 4,611 አዳዱስ ኬዝ አስተናግዳለች
──────────
√ የመረጃ ምንጫችን:- ስፒዶሜትር ድህረ ገፅ ነው
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች ተገኙ
******
በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡
ምንጭ EBC
👍1
# በኢትዮጵያ_የኮሮና_ቫይረስ_ኬዝ_19_ደርሷል
በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡
#ታማሚ 1
የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን መጋቢት 8፣ 2012 ከብራሰልስ ቤልጅየም እንዲሁም መጋቢት 10፣2012 ዓ.ም ወደ ካሜሮን የጉዞ ታሪክ የነበራት ሲሆን ግለሰቧ የበሽታው ምልክት ስለታየባት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ አድርጋለች፡፡ ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በመጋቢት 19፣2012 ዓ.ም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል፡፡
# ታማሚ 2 እና 3
የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር፡፡ ግለሰቦቹ በመጋቢት 19፣2020 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 በመጠቀም ማግኘት ይቻላል።
ምንጭ:- ጤና ሚኒስትር
ሊንኩን በመጫን የሁሉንም ሀገር በኮሮና ቫይረስ የተጠቁትን ሀገሮች ለማወቅ ትችላላቹሁ በየቀኑ ግን ቁጥሩ እየጨመረ ነው ፡፡
https://www.worldometers.info/coronavirus/
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ተገኙ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ተገኙ።
በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ግለሰቦች የ38 ዓመት ወንድ እና የ35 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።
ሁለቱም ግለሰቦች በተለያዩ ቀናት ወደ ዱባይ የጉዞ ታሪክ የነበራቸው ሲሆን የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ምንጭ FBC
#የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ
እሁድ መጋቢት 20 እስከ ከምሽቱ 1:45 ሰዓት ድረስ
እንደምን አመሻችሁ ክቡራን የሰው ልጆች ፣ በአለማችን ከ200 ሀገራትና ግዛቶችን ያዳረሰው የወቅቱ የሰው ልጆች ፈተና የሆነው የኮሮና ቫይረስ 702,368 ሰዎችን ለክፎ 33,178 ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳርጓል
እንዲሁም 2,321 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
149,215 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል
519,975 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል
────────────
በጣልያን ቫይረሱ አሁንም የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +756 ሰዎች ሲሞቱባት ተጨማሪ +5,217 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
───────────────
────────────
ስፔንም በቫይረሱ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 2ኛዋ ሀገር ነች +624 ሰዎች ሲሞቱባት +5,564 አዳዲስ ኬዞችንም አስተናግዳለች።
───────────────
በጠቅላላ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
1ኛ 10,779 ጣልያን
2ኛ 6,606 ስፔን
3ኛ 3,300 ቻይና
4ኛ 2,640 ኢራን
5ኛ 2,329 አሜሪካ
──────────────
በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
1ኛ 131,403 ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ
2ኛ 97,689 ጣልያን
3ኛ 81,439 ቻይና
4ኛ 78,799 ስፔን
5ኛ 60,659 ጀርመን
6ኛ 38,309 ኢራን
───────────────
የኮሮና ቫይረስን በጋራ እና በግል እንከላከል
የእጃችንን ንፅህና በአግባቡ እንጠብቅ
ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ አንገኝ
ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀት እንጠብቅ!
መልካም አዳር ይሁንላችሁ!
#የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ
ሰኞ መጋቢት 21 እስከ ጠዋቱ 01:30 ሰዓት ድረስ
ውድ የሀገሬ ልጆች በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ ፣ ባለፉት 24 ሰዓት የኮሮና ቫይረስ በመላው አለም 3,110 ሰዎችን የገደለ ሲሆን 58,865 አዲስ ተጠቂዎችም ሪፖርት ተደርገዋል
───────────
ስፔን ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት ቀዳሚዋ ሀገር ነች 821 ሰዎች ሲሞቱባት +6,875 አዳዲስ ኬዞችንም አስተናግዳለች።
────────────
በጣልያን ቫይረሱ አሁንም የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +756 ሰዎች ሲሞቱባት ተጨማሪ +5,217 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
────────
ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በርካታ ሰው የሞተባት 3ኛ ሀገር ነች። 292 ሰዎች ሲሞቱባት ++2,599 አዲስ ኬዝም አስተናግዳለች።
────────
አሜሪካ በ24 ሰዓት ውስጥ በርካታ ኬዝ ያስተናገደች ሀገር መሆኗን ቀጥላለሽ (+18,469) እንዲሁም 264 ሟቾች እንዳሉባትም ሪፖርት አድርጋለች
─────────
ኔዘርላንድ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው ካጡት ውስጥ ነች 132 ሰዎች ሲሞትባት +1,104 አዳዲስ ኬዝ አስተናግዳለች።
────────────
በኢራን ባለፉት 24 የሞቱባት ሰዎች 123 ሲሆኑ +2,901 አዳዲስ ተጠቂዎችንም አስተናግዳለች።
────────────
በብሪታኒያ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 209
ሰው የሞተ ሲሆን +2,433 ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘዋል።
────────
ቻይና ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 5 ሰዎች የሞቱባት ሲሆን +45 አዳዲስ ኬዝ እንዳለባትም ሪፖርት አድርጋለች።
──────────────
ደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +93 አዳዲስ ኬዝና 1 ሞት ያስተናገደች ሲሆን በጠቅላላው 1,280 ኬዝ በማስተናገድም ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ነች።
────────────
ግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት +33 አዳዲስ ኬዝ እና 4 ተጨማሪ ሟች የተገኘባት ሲሆን በጠቅላላው 40 ሞት አስተናግዳ በአፍሪካ በርካታ ሰው የሞተባት ሀገርም ሆናለች።
────────────
አልጄሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ 2 ተጨማሪ ሰው ሞቶባት +57 አዳዲስ ኬዞችንም አግኝታለች ። አጠቃላይ 31 ሰው ሞቶባታል።
───────────
ሞሮኮ በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ +77 የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያገኘችና 1 ተጨማሪ የሞት ሪፖርትም አላት። ጠቅላላ 26 ሰው ሞቶባታል
────────────
በሀገራችን ትላንት ብቻ 5 አዲስ ታማሚ የተገኘ ሲሆን በሀገራችን ያለው ጠቅላላ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ 21 ደርሶ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 2ቱ አገግመው 2 ጃፓናዊ ታማሚዎችም ወደ ሀገራቸው ሄደዋል።
ካሜሮን 4 ሰው ሞቶባት 48 አዲስ ኬዝም አስተናግዳለች
ዲ.ሪ. ኮንጎ በ24 ሰዓት 16 አዲስ ኬዝና 2 ሟች አለባት
አንጎላ በ24 ሰዓት 2 አዲስ ኬዝና 2 ሟች አለባት
ቡርኪናፋሶ 1 ሰው ሞቶባት 15 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች
ቱኒዚያ በ24 ሰዓት 34 አዲስ ኬዝ እስተናግዳለች
ኮትዲቯር በ24 ሰዓት 64 አዲስ ኬዝና 1 ሟች አለባት
ሞሪቲየስ 1 ሰው ሞቶባት 5 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች
────────────
ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ሞት ያስተናገዱ ሀገራት
+821 ስፔን
+756 ጣልያን
+292 ፈረንሳይ
+264 ዩናይትድ ስቴትስ
+209 ብሪታኒያ
ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
+18,469 ዩናይትድ ስቴትስ
+6,875 ስፔን
+5,217 ጣልያን
+4,740 ጀርመን
+2,901 ኢራን
+3,809 ፈረንሳይ
────────────
በጠቅላላ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
10,779 ጣልያን
6,803 ስፔን
3,304 ቻይና
2,640 ኢራን
2,606 ፈረንሳይ
በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
142,178 ዩናይትድ ስቴትስ
97,689 ጣልያን
81,470 ቻይና
80,110 ስፔን
62,435 ጀርመን
አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 33,980 ሺህ ሆኗል
ጠቅላላ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ 722,347 ደርሷል
ጠቅላላ ከቫይረሱ ያገገሙትም 151,766 ሆነዋል
አሁን ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች 536,601 ናቸው
በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙት 509,920 ሆነዋል
በአሳሳቢ ደረጃ የሚገኙትም 26,681 ሰዎች ናቸው
────────────
√ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በጋራ እንከላከል።
# በቅድመ_ጥንቃቄ_እና_በፀሎት_እንበርታ
√ መረጃ አይናቅም ስለዚህ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ
√ ቁጥራዊ መረጃዎቹን ያገኘሁት :- ስፒዶሜትር ዌብሳይት ላይ ነው
───
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህምድ ይፋ አድርገዋል።
በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ_19) በሽታ የተያዙ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን ለማሳወቅ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ባደረገው ተጨማሪ ስልሳ ስድስት (66) የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች በማረጋገጡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሶስት (23) ደርሷል፡፡
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ግለሰቦች በአማራ ክልል ባህር ዳር ነዋሪ የሆኑ የ37 ዓመት ሴትና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ የሆኑ የ32 ወንድ ዓመት ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ ዕለት አስቀድሞ አንደኛዋ ታማሚ መጋቢት 10 ከዱባይ እንዲሁም ሁለተኛው ታማሚ መጋቢት 12 ከአሜሪካ የገቡ ናቸው፡፡ ሁለቱም ታማሚዎች የበሽታው ምልክት በማሳየታቸው በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዘቸው ተረጋግጧል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚዎቹ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ሰዎች የመለየትና ክትትል ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ሁለቱም ታማሚዎች በአማራ ክልል የለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ አስራ ዘጠኝ (19) ታማሚዎች ሲኖሩ አንድ ታማሚ በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ሁለት ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ሲሆን ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡ ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገበር እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
መጋቢት 21 ፣ 2012 ዓ.ም
👍1
# በኢትዮጵያ_የኮሮና_ቫይረስ_ኬዝ_ሙሉ_መረጃ
የወቅቱ የአለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው መጋቢት 03-2012 ሲሆን ዛሬ ላይ በ19ኛ ቀኑ የተጠቂዎች ቁጥር 23 ደርሷል።
እስኪ በሀገራችን የተገኘው 23ቱን ኬዞች እናስታውሳቸው
መጋቢት 3-2012 የመጀመሪያው ታማሚ
1. የ48 አመት ጃፓናዊ የካቲት 25 ከቡርኪናፋሶ የመጣ
መጋቢት 05-2012 ላይ የተገኘባቸው
2 የ44 አመት ጃፓናዊ
3 47 አመት ጃፓናዊ
4 42 አመት ኢትዮጵያዊ
ከመጀመሪያው ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ያላቸውና ሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ
መጋቢት 07-2012 የተገኘበት
5. የ34 አመት ኢትዮጵያዊ መጋቢት 04 ከዱባይ የገባ
መጋቢት 08-2012 የተገኘባት
6. የ59 አመት እንግሊዛዊት የካቲት 23 ከዱባይ የገባች
መጋቢት 10-2012 ላይ የተገኘባቸው
7. የ44 አመት ጃፓናዊ ከመጀመሪያው ታማሚ ጋር የተነካካ
8. የ85 አመት ኢትዮጵያዊት የካቲት 23 ከውጭ የመጡ
9. የ39 አመት ሆስትሪያዊ መጋቢት 6 የገባ
መጋቢት 13-2012 ላይ የተገኘባቸው
10. የ28 አመት ኢትዮጵያዊ ከቤልጅየም መጋቢት 5 ገባ
11. የ43 አመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ መጋቢት 10 ገባ
መጋቢት 14-2012 ላይ የተገኘበት
12- የ34 አመት ኢትዮጵያዊ መጋቢት 04 ከዱባይ የገባ
መጋቢት 18-2012 ላይ የተገኘባቸው
13- የ72 ዓመት ሞሪሸሳዊ መጋቢት 5 ከኮንጎ ብራዛቪል የመጡ
14- የ61 ዓመት የአዳማ ከተማ ኢትዮጵያዊ ይፕትም ያልተጓዙ
15- የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት መጋቢት 12 ከእስራኤል ተመላሽ
16- የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት የውጭ ጉዞ ያላደረገች
መጋቢት 20-2012 ላይ የተገኘባቸው
17- የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ መጋቢት 10 ከካሜሮን የመጣ
18- የ14 አመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ከተማ ነዋሪ
19- የ48 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ከተማ ነዋሪ
20- የ38 ዓመት ወንድ የዱባይ የጉዞ ታሪክ የነበረው
21- የ35 ዓመት ሴት የዱባይ የጉዞ ታሪክ የነበራት
መጋቢት 21-2012 ላይ የተገኘባቸው
22- የ37 ዓመት ሴት የባህር ዳር ነዋሪ ከዱባይ ተመላሽ
23- የ32 ዓመት ወንድ በአዊ ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ ከአሜሪካ ተመላሽ
√ ጠቃሚ መረጃ ስለሆነ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «# በኢትዮጵያ_የኮሮና_ቫይረስ_ኬዝ_ሙሉ_መረጃ የወቅቱ የአለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው መጋቢት 03-2012 ሲሆን ዛሬ ላይ በ19ኛ ቀኑ የተጠቂዎች ቁጥር 23 ደርሷል። እስኪ በሀገራችን የተገኘው 23ቱን ኬዞች እናስታውሳቸው መጋቢት 3-2012 የመጀመሪያው ታማሚ 1. የ48 አመት ጃፓናዊ የካቲት 25 ከቡርኪናፋሶ የመጣ መጋቢት 05-2012 ላይ…»
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ