Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ካሜራ ከመግዛት በፊት ማየት ያለብን ነጥቦች
አፔቸር(aperture)
በኦፕቲክስ አፔቸር (optics aperture)ማለት ብርሃን የሚጓዝበት ቀዳዳ ወይም ፎቶ ሌንስ ቀዳዳ ሲሆን ቀዳዳው በተለያየ መጠን ብርሃን ማስገባት የሚችል ብቃት አለው። የብርሃን ምጣኔው የሚቆጣጠረው አፈሙዝ ስፋት ሲኖረው ለፎቶ በሚመጥን የብርሃን ምጣኔ በመፍቀድ የፎቶውን የብርሃን ተጋላጭነት (exposure) ይቆጣጠራል። አፔቸር የሚለካው በኤፍስቶፕ(f/
stops) ሲሆን ከ 1.4 እስክ 16 ድረስ ነው። ኤፍስቶፕ ባነሰ ቁጥር ፎቶው ድምቀት ይኖርዋል በተቃራኒው ቁጥሩ በጨመረ ግዜ የፎቶው ድምቀት ወይም ብርሃን መጠን ይቀንሳል።
ISO
አፔቸር በካሜራችን ውሰጥ የሚገባውን የብርሃን መጠን መቆጣጠሪያ ሲሆን አይሶ ደግሞ የፎቶውን መጨለም እና መብራት ይቆጣጠራል። ይህ ማለት የካሜራው ሴንሰር ምንያህል ብርሀን ማስቀመጥ ይችላል ማለት ነው። የአይሶ ቁጥር በጨመረ ቁጥር የፎቶ ግራፉ ድምቀት እየጨመረ ይመጣል በተቃራኒው የአይሶ ቁጥር ሲያንስ ፎቶግራፉ የመጨለም ባህሪ ያሳያል። በዚህ ምክንያት አይሶ ለማታ ፎቶዎች ወይም በቂብርሃን በሌለበት ወቅት ጥሩ ፎቶግራፍ እድናነሳ ይረዳል። አሁን ያሉት ካሜራዎች ISO ሃይላቸው ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ በትንሽ ብርሀን ማለትም በትንሽ የሻማ ብርሀን ከፍተኛ የፎቶግራፍ ጥራት ማንሳት ተችሏል። ትንሽ ISO ማለት ሴንሰሩ ትንሽ ብርሀን የመያዝ አቅም አለው ማለት ሲሆን ትልቅ ISO ማለት ሴንሰሩ ትልቅ ብርሀን የመያዝ አቅም አለው ማለት ነው ። አሁን ያሉ ካሜራዎች ከ100 እስከ 3000 በላይ ISO መጠን አላቸው።
ካሜራ ሸተር (Camera Shutter)
በያንዳንዱ ካሜራዎች ውስጥ የተለያዩ ክፍሎች ሲኖር ከዛ ውስጥ አንዱ ሌንስ ይባላል። ሌንስ (መስታያት ካሜራ) ካሜራ ውስጥ ያለ አካል ሲሆን ብርሃንን በማተኮር ወይም የመበተን ስራን ይሰራል።ሸተር ካሜራ ውስጥ የሚገኘ ሲሆን በካሜራ ሴንሰሩ ፊትለፊት የሚገኝ መጋረጃ መሰል ነው። ይህ መጋረጃው ካሜራው ፎቶ ሲያነሳ ይከፈታል። ካሜራው ፎቶ በሚያነሳበት ግዜ ሸተሩ በደንብ በመከፈት የተቻለውን የብርሀን መጠን በማስገባት ካሜራ ሴንሰር በማሳረፍ ፎቶ ለመፍጠር በቂ ብርሃን ካገኘ በሁሃላ ሸተሩ ይዘጋል።ሸተር ስፖድ ማለት የካሜራው ሸተር የሚከፍት የግዜ ርዝመት ማለት ነው። ይህ ማለት የካሜራ ሴንሰሩ በምን ያህል ግዜ ውስጥ የካሜራ ሴንሰር ለብርሃን ይጋለጣል ማለት ነው። ወይም ካሜራው ፎቶ ለማንሳት የሚወስድበት ግዜ ማለት ነው።
ረዥም ሸተር ስፒድ በምንጠቀምበት ግዜ ሴንሰሩ ለከፍተኛ ብርሃን ይጋለጣል በዚህ ግዜ ፎቶው ደብዛዛ ይሆናል። ረዥም ሸተር ስፒድ ባለግዜ ተንቀሳቃሽ ነገሮች በፎቶ ላይ ደብዛዛ ይሆናሉ።ብዙ ግዜ በመኪና ማስታወቂያ ለይ የመኪናው ፍጥነት እዳለው ለማስመሰል እንጠቀማለን። አጭር ሸተር ስፒድ ተጠቀምን ማለት ደግሞ ሴንሰሩ ለተወሰነ ግዜ ብቻ ለብርሃን ተጋለጠ ማለት ሲሆን ይህ ማለት ቅዝፈታዊ ፎቶዎች ማንሳት ይቻላል። ሸተር ስፒድ ትንሽ ከሆነ የፎቶግራፍ የመደብዘዝ ሁኔታ ይቀንሳል። ለምሳሌ በፍጥነት የሚያለፍ እቃን በ1/30 ሰከንድ እና በ1/200 ሰከንድ ፎቶ ብናነሳ 1/30 ሰከንድ ፎቶግራፍ ደብዘዝ ያለ ሲሆን 1/200 ሰከንድ ደግሞ ቀጥያለ ወይም ያልደበዘዘ ፎቶ ይወጣወል።
ሜጋፒክስል
ሜጋፒክስል ማለት የሚሊዮን ፒክስል ጥርቅም ነው። ፒክስል ደግሞ የዲጂታል ምስል የሚገኘ አካል ሲሆን የምስሉ አነስተኛ መለኪያ ነው። ፒክስልን እንደ ነጥም ማሰብ ይቻላል። ነጥብ ተሰብስበው መስመር እንደሚሰሩ ሁሉ ፒክስል ተሰባስቦ ደግሞ ምስል ይሰራሉ ግን እደ ነጥብ አይቆጠሩም ማለት አደለም። የሜጋፒክስሉ ቁጥር ብዛት የአንድ ምስል ልቀት(resolutions) ይወስናል እና ተጨማሪ ሜጋፒክስሎች ያለው ዲጂታል ምስል ተጨማሪ ልቀት አለው ማለት ነው።በዲጂታል ፎቶግራፍ ላይ ከፍተኛ ልቀት መኖሩ ጠቃሚ ነው። ይህም ካሜራ የበለጠ ምስሎችን ለመፍጠር ብዙ ፒክሴሎችን እንደሚጠቀም ይህም የበለጠ ትክክለኛ ምስል ለመፍጠር ይረዳል። የካሜራ ሴንሰሮች ፒክስል ተብለው የሚጠሩ ብርሃን ተቀባዮች በውስጡ ይዞል።እያንዳንዳቸው እነዚህ ተቀባይም የብርሃኑን በመለካት ይመዘግባሉ። አንድ ሴንሰር እነዚህን አይነት ተቀባዮች በሚሊየን አይነት ይኖሩታል። ስለዚህ ሚሊየን ተቀባዮች ሜጋ ፒክስል ተብለው ይጠራሉ።
ብዙ ፒክስል አለ ማለት የፎቶግራፍ ጥራት ይጨምረዋል ማለት ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ ገበያ ላይ ያሉ ስልኮች እስከ 25 ሜጋፒክስል ድረስ ሲኖሩ የሳምሰንግ እና አይፎን ስልኮች ለምን ከ13 ሜጋፒክስል ሆነው እንዴት በጥራት ይበልጣሉ? ይህነን ለመመለስ ከላያ የተጻፉትን የካሜራ ባህራት ማየት ትሩ ነው። በነዚህ ስልኮች በላቀ መልኩ ይተገበራሉ በተጨማሪም የፎቶግራፍ ጥራቱ በሜጋፒክስሉ ብቻ ሳይሆን በሴንሰሩ የቁመት መጠን ይወሰናል። ለምሳሌ ካሜራው 30 ሜጋፒክስል ሆኖ ፒክስል ሴንሰሩ ትንሽ ከሆነ የ20 ሜጋፒክስሉ ትልቅ ሴንሰር ያለው የላቀ ጥራት አለው ማለት ነው። ስለዚህ ስልክ ወይም ካሜራ በምንገዛበት ግዜ ሜጋፒክስሉ ለይ ብቻ ትኩረት አለማረግ ተገቢ ነው።
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/
MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍1
#የሀያላን_አገር_መሪዎች_ፈጣሪን_ተማጸኑ ..
ጣሊያን ዛሬም ደግሞ 793 ዜጎቿን አጥታለች፡፡
በ4ቀን ውስጥ ብቻ ከ'3000 በላይ ዜጎቿ
ይህችን አለም የተሰናበቱባት የጣሊያኑ ጠ/ሚ/ር ኮንቴ እንባ እየተናነቃቸው የሚከተለውን ብለዋል፡፡
=============••••••••••••••••••===========
"ወረርሽኙን መቆጣጠር አልቻልንም። በአካልና በአእምሮ
እየሞትን ነው። ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ እንደምንችል
አላውቅም። በምድር ላይ አለ የተባለ መፍትሄ አልቀረንም።
አሁን የቀረን ወደ ሰማይ ብቻ ነው።"
==============••••••••••••••••••===========
የኢጣልያ ጠቅላይ ሚኒስተር ...ኮንቴ
ያአሏህ ማረን ያረሂሙ
ሰላም ሰላም ወንድም እህቶች እንዴት ናችሁ ይሄው ዛሬ ቀኑ ደርሶ ክላስ ልንጀምር ነው
ስለዚህ የምንማራቸውን course outline ከዚህ በታች እዘረዝራቸዋለሁ
1 የኮምፒውተር መግቢያ
2 የኮምፒውተር ታሪካዊ አመጣጥና እድገት
3 የኮምፒውተር አይነቶች
4 የኮምፒውተር ሃርድዌር አካላት
5 የኮምፒውተር ሶፍትዌር
6 የኮምፒውተር የመረጃ መቀበያ አካላት input devices
7 የኮምፒውተር ውጤት መግለጫ መሳሪያዎች output devices
8 ማዘርቦርድ mother board
9 central processing unit CPU
10 መረጃ ማስቀመጫ መሳሪያዎች data storage device
ከላይ 10 የዘረዘርኳቸውን አንድ በአንድ እናያለን ማለት ነው ይሄንን ከጨረስን ወደ አድቫንስድ እንሄዳለን
ይህንን በሁለቱም ቋንቋ የተዘጋጄ ነው በአማርኛ እና በ እንግሊዝኛ ይቀርባል። ስለዚህ እንድትከታቱኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
በነገራችን ላይ በዚህ ግሩፕ 3 አይነት ሰዎች አሉ ብዙም ስለኮምፒውተር እውቀት የማይኖራቸው(እንደዚህ ስላችሁ ቅር እንዳይላችሁ) መካከለኛ እንዲሁም ከፍተኛ ስለኮምፒውተር እውቀት ያላቸው አሉ። ከተሳሳትኩ እንድታርሙኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ። ስለዚህ ሀሳብ አስተያየት ስጡኝ
https://t.me/joinchat/KPglFhgByUl5eskmbeIsbA
በዚህ ግሩፕ ይቀላቀሉ
እንዳያመልጣችሁ
ዛሬ የማሳያችሁ እንዴት  "Window Key + R" በአንድ ላይ ስንጫን  Run Window ይመጣልናል ከዛም ከዚህ በታች ያሉትን አቋራጭ ቁልፎችን በመጻፍ ስለኮምፒውተራችን መረጃ ማግኜትና ኮምፒውተራችንን መቆጣጠር እንችላለን
1) Compmgmt.msc 👉Computer management    
2) devmgmt.msc  👉Device manager
3) diskmgmt.msc 👉Disk management
4) dfrg.msc 👉Disk defragevent
5) vwr.msc 👉Event viewe
6) rfsmgmt.msc 👉Shared folder
7) sgpedit.msc 👉Group policies  
8) lusrmgr.msc 👉Local user and groups
9) perfmon.msc 👉Performance monitor
10) services.msc  👉Various Services
11) msconfig 👉System Configuration Utility
12) regedit 👉Registry Editor
13) msinfo32 👉System Information 14) winver 👉Shows current version of windows
15) mailto: 👉Opens default email client
16) cmd 👉Opens command prompt
17) perfmon.msc 👉Performance monitor
18) rsop.msc 👉Resultant set of policies
19) secpol.msc 👉Local security setting
20) swin.ini 👉Windows loading information
21) shutdown /s 👉Shutdown
22) shutdown /r  👉Restart
23) shutdown /h  👉Hibernate
25) የተሰማችሁን ሀሳብ comment box ላይ ጻፉልኝ
26) ሼር ያድርጉት
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👏1
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ዛሬ የማሳያችሁ እንዴት  "Window Key + R" በአንድ ላይ ስንጫን  Run Window ይመጣልናል ከዛም ከዚህ በታች ያሉትን አቋራጭ ቁልፎችን በመጻፍ ስለኮምፒውተራችን መረጃ ማግኜትና ኮምፒውተራችንን መቆጣጠር እንችላለን 1) Compmgmt.msc 👉Computer management     2) devmgmt.msc  👉Device manager 3) diskmgmt.msc 👉Disk management 4) dfrg.msc…»
የኮሮና መከላከያና መረጃ ጥሪ ማዕከላት፦
በአገር ደረጃ ፡ 8335
የትግራይ ክልል፦ 6244
የአማራ ክልል፦ 6982
የኦሮሚያ ክልል፦ 6955
የደቡብ ክልል፦ 6599
ድሬዳዋ ከተማ፦ 6407
በስፔን የሟቾች ቁጥር 2 ሺህ አልፏል ዛሬ 434 ሞቶባታል
በጣልያን ዛሬም 602 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል
አሜሪካ ዛሬ ብቻ 7,295 አዲስ ተጠቂዎችን አግኝታለች
ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ብቻ 128 አዲስ ኬዝ አግኝታለት
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ስለ ቫይረሱ ስርጭት ያሉት አለ
በኒውዮርክ ዛሬ ብቻ +5,085 አዲስ ኬዝ አግኝታለች
ከቫይረሱ ማገገም የቻሉትም 100 ሺህ አልፈዋል
ቻይና ላይ የቫይረሱ ስርጭት በቁጥጥራቸው ስር ያደረጉት ይመስላል። ዛሬ የተመዘገበው አዲስ ኬዝ 39 ብቻ ሲሆን በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ከሚገኙት 1,749 ሰዎች ውስጥ ዛሬ 9 ሞተውባታል።
በደቡብ አፍሪካ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 128 ሰዎች ይፕትፕገኙ ሲሆን በጠቅላላው 402 ኬዝ በማስተናገድ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች።
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ ፈጣ የኮነ ስርጭትን እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል።
" በኮሮናቫይረስ የተያዘው የመጀመሪያው ሰው ሪፖርት ከተደረገ በኋላ፤ የመጀመሪያዎቹ 100 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ለመያዝ 67 ቀናት ወስደዋል። ቀጣዮቹ 100 ሺህ ሰዎች የተያዙት በ11 ቀናት ውስጥ ሲሆን ፤ ሦስተኛ 100 ሺህ ሰዎች የተያዙት ግን በ4 ቀናት ውስጥ ነው” በማለት የቫይረሱን አስደንጋጭ የስርጭት ፍጥነት አመላክተዋል። via- BBC አማርኛ
ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ገና 24 ሰዓት ሳይሞላ 7,796 አዲስ ኬዝ ያስተናገደች ሲሆን 79 ሰዎችም ሞተውባታል። በጠቅላላው በሀገሪቱ የተመዘገበው ኬዝ 41,342 ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ወደ 498 ከፍ ብሏል።
ስፔን ከጣልያን ቀጥሎ በርካታ ሰዎቿን እያጣች ያለች ሀገር ስትሆን ዛሬም 435 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሀገሪቱ የተመዘገበው ጠቅላላ የሟቾች ቁጥርም 2,207 ደርሷል። ስፔን በአለማችን በርላታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያለባት 4ኛ ሀገርም ነች (33,089 ሰው ተጠቅቷል)
በቫይረሱ የሚያዘው የሰው ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ቢሆንም መልካም የሚባለው ዜና አገግመው ከሆስፒታል የሚወጡት ሰዎችም የዛኑ ያክል በርከት ብሏል። አሁን ላይ በመላው አለም 101,069 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ሪፖርት ተደርጓል።
የፌደራል የመንግስት ሰራተኞች ከነገ ጀምሮ ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚተላለፍ ስራቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮቪድ19 ገደብ የለሽ ስርጭት ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውዥንብር ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል።
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው የፌደራል የመንግስት ሰራተኞች ከነገ መጋቢት 16 ጀምሮ ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚተላለፍ ስራቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳልፏል።
# ሰበር አስደሳች መረጃ!!
22 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ነፃመሆናቸው ተረጋግጧል!!
==============================
ከጃፓናዊው ግለሰብ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 22 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋገጠ
# አርሲ መጋቢት 15/2012
# ሼር_ይደረግ !!
በአርሲ ዞንና በአዳማ ከተማ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ግለሰብ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 22 ግለሰቦች ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ዛሬ ወደ ቤታቸው መሸኘታቸውን የአዳማ ጤና መምሪያ ገለጸ።
የአዳማ ከተማ ጤና መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ሳሚራ ሙሐመድ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በመጀመሪያ ቫይረሱ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 22 ግለሰቦች በክልል ደረጃ በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርጎ ነበር ።
18ቱ ከአርሲ ዞን 4ቱ ደግሞ ከአዳማ ከተማ መሆናቸውን ኃላፊዋ ገልፀው ላለፉት 14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ መደረጉን አስረድተዋል ።
በኦሮሚያ ሪጅናል ላቦራቶሪ በኩል ከ22ቱ ግለሰቦች ናሙና በመውሰድ ወደ ማእከል ተልኮ የሁሉም ውጤት ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል ።
በለይቶ ማቆያ ማእከሉ በህክምና ባለሙያዎች ክትትል ሲደረግባቸው መቆየቱንም ኃላፊዋ ተናግረዋል ።
በሌላ ባኩል ከ10 ቀን በፊት ከኳታርና ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ሶስት ግለሰቦች በበሽታው ተጠርጥረው በትናንትናው ዕለት ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን የገለፁት የመምሪያ ኃላፊዋ ናሙና ተወስዶ ውጤቱ እየተጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል ።
አዳማ ከተማ አዲስ አበባ ቀጥላ የቱሪዝም ፣ንግድና ኮንፈረስ ከተማ ከመሆኗም ባለፈ የሀገሪቷ መግቢያና መውጫ በሮች መተላለፊያ በመሆኑዋ በተለያየ መንገድ ከውጭ ሀገር በሚገቡት ሰዎች ላይ ክትትል እያደረግን እንገኛለን ብለዋል።
በዚህም ከአራት ቀን በፊት ከቱርክ የመጣ አንድ ኢትዮጵያዊን ጨምሮ ከውጭ ሀገር የገቡ 16 ዜጎች በያዙበት ሆቴሎችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለአስራ አራት ቀናት እንዲቆዩና በጤና ባለሙያዎች ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ገልፀዋል ።
እስከ አሁን ድረስ በክትትል ላይ በሚገኙ ሰዎች ላይ የህመም ምልክት አልታየም ብለዋል ።
በበሽታው የምርመራ ሂደት ላይ የህክምና ባለሙያዎች በቂ ክህሎትና ግንዛቤ እንዲያገኙ የማሰልጠንና የማዘጋጀት ሥራ መጠናቀቁንም ገልጸዋል።
በከተማዋ በከንቲባው የሚመራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከመስተዳድሩ እስከ ቀበሌ ድረስ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ በተለይ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን የመለየት፣ለአቅመ ደካሞች፣ማረሚያ ቤቶች፣አረጋዊያንና የጎዳና ተዳዳሪዎች ቅድሚያበመስጠት የንፅህና መጠበቂያ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ፤ ነው ብለዋል።
በበሽታው ምልክት ተጠርጥረው በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ወደ ለይቶ ማቆያ ከገቡትና ናሙናቸው ከተወሰደው 40 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 38 ከበሽታው ነፃ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የኦሮሚያ ሪጅናል ላቦራቶሪ ሃላፊ አቶ ዳባ ሙለታ ናቸው።
ከጅማና ከኢሉ አባቦር ዳሪሙ ወረዳ የመጡ የተቀሩት የሁለት ግለሰቦች ውጤትም ዛሬ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከአቶ ዳባ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል
ኢዜአ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «# ሰበር አስደሳች መረጃ!! 22 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ነፃመሆናቸው ተረጋግጧል!! ============================== ከጃፓናዊው ግለሰብ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 22 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋገጠ # አርሲ መጋቢት 15/2012 # ሼር_ይደረግ !! በአርሲ ዞንና በአዳማ ከተማ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ግለሰብ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 22 ግለሰቦች…»
ዩንቨርሲቲዎች ተማሪዎችን በጊዜያዊነት እንዲያሰናብቱ መወሰኑን የሳይንስ እና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ ወደቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ውሳኔ አሳልፏል፤ ውሳኔ የተላለፈው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተማሪዎች የከፋ ችግር እንዳይደርስባቸው በማሰብ እንደሆነ ተገልጿል።
ዩንቨርሲቲዎች ተማሪዎችን በትራንስፖርት ወጪ ሸፍነው ወደየቤተሰቦቻቸው አንዲያደርሱ ሁኔታወች እየታዩ መሆኑንም በሚኒስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ደቻሳ ጉርሙ ለአብመድ ተናግረዋል።
የቫይረሱ ስርጭት ሰዎችን መጉዳት በማይችልበት ደረጃ መሆኑ ሲታወቅ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚተላለፍም ተገልጿል።
Source Amhara Mass Media Agency