Muhammed Computer Technology (MCT)
37.7K subscribers
528 photos
7 videos
254 files
913 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
🔆ዛሬ ጠቃሚ #የመጽሐፍ 📚 ድረ ገጾችን ልጠቁማችሁ👇👇👇

1⃣. http://gen.lib.rus.ec/
ይህ👆 ድረ-ገጽ ማንኛው አይነት መፅሀፍ ማውረድ የሚያስችሎት
ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠር መፅሀፎች አሉት በዉስጡ
ከሚግኙ መፅሀፎች መካከል👉 #የትምህርት መፅሀፎች፤ #የሳይኮሎጂ መፅሀፎች፤
#ፍልስፍና መፅሀፎች ፤ #የታሪክ መፅሀፎች ይገኙበታል፡፡

2⃣. http://sci-hub.org/
ይህ👆 ድህረ-ገጽ ከ64 ሚሊዮን በላይ #የጥናት ወረቀት
የሚገኝ ሰለሆነ በቀላሉ ማዉረድ ይቻለሉ ፡፡

✔️በዚህ👆 ድረ- ገጽ የተለያዩ መጻፎች በተለያ ምርጫ እና አይነት ያገኛሉ።

3⃣. https://bookboon.com/
ይህ👆 ድረገጽ ማንኛው አይነት የነጻ መጻፍ የሚያገኝበት
ሲሆን በየትኛዉም የክፍል ደረጃ 👨‍🎓 ላሉ #ተማሪዎች አንዲዉም
በማንኛው የስራ ሁኔታ ላይ ላሉ ሰዎች ጠቃሚ ድርገጽ ነው፡፡

4⃣. http://bookzz.org/
#ቡክዚ 👆 አለማችን ለይ ትልቅ የመጻሀፍ #ላይብረሪ ያለው ሲሆን በአማካኝ 2.6 #ሚሊዮን መጻሀፍ በ ድረገጹ ይገኛል።

5⃣. www.allitebooks.com/
ይህ 👆 ድረገጽ ብዙ የቴክኖሎጂ #መጽሀፍት ያሉት ሲሆን የፕሮግራሚንግ፤ ግራፊክስ ፤ የኮምፒተር አጠቃቀም እና
የተለዩ የትምህርት መጻሃፎች📚 ያገኛሉ፡፡
👍62❤6👏3👎2👌1
DV ያለ ፓስፖርትና ፖስፖርት የለው ሰው እንዴት መሙላት እንደምንችል በምርጥ አቀራረብ በቪዲዮ ይዠላችሁ ቀርብልያለሁ የ YouTube ቻናል ሰብስክራይቭ ያድርጉ!
👇👇👇ቪዲዮውን ይመልከቱ👇👇👇
https://youtu.be/qT1Q3FatMt0
https://youtu.be/qT1Q3FatMt0
https://youtu.be/qT1Q3FatMt0
https://youtu.be/qT1Q3FatMt0
👍65❤1
💻 ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል😨?

እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን🤔።

✔1. Power option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

✔2.Disable unwanted start up programs

ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል

Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።

✔3.Defragment and optimize drive Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ

✔4. Delete unnecessary temporary file Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

✔5. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

✔6. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

✔7. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

✔8. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ
👍125😁7🔥5🥰5❤4👏1🕊1
💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
=========================

■ ጠቃሚ መረጃ ነው!! ላልደረሰው ያዳርሱ አሁኑኑ ሼር ያድርጉት፡፡

❖መጀመሪያ ከላይ የለቀቅንላችሁን መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ።
⁉️ ሶፍትዌሩን ለማግኘት ከፈለጋችሁ ከቴግራም ቻናሌ ማግኘት ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

◕መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

♨️የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል አሁኑኑ ሼር ያድርጉ፡፡
━━━━━━ ⊙ ━━━━━━

🗣➹share &Join Us
👇🏾👇🏾👇🏾
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍93👏9🔥5❤3🥰2😁1
ጎግል ፕሌይ ስቶር ብልሽት ለማስተካከል

✅ Google Play Store በአብዛኛዎቹ የAndroid ዘመናዊ ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ ሲሆን በሆነ ምክንያት በዲቫይሱ(ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ መሥራት ሊያቆም ሊያጋጥም ይችላል፡፡

✅ በዚህም ምክንያት በዲቫይሱ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮችን የቅርብ ግዜ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮችን ዳውንሎድ አድርገን መጫን እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የቅርብ ግዜ ማድረግ አንችልም፡፡

✅ Google Play መደብር በእርስዎ ዲቫይስ ላይ የማይሰራ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት አንዳንድ መንገዶችን እጠቁማለሁ

1. የዲቫይሱን ቀን እና ሰዓት ቅንብር(ሴቲንግ) ያስተካክሉ
የተሳሳተ ቀን እና የጊዜ ገደብ ሲኖርዎት የGoogle አገልጋዮች ከአሳሽዎ ጋር ማመሳሰል ችግሮች ያጋጥማቸዋል ለማሰተካከል ወደ ሲስተም ሴቲንግ በመሄድ «ቀን እና ሰዓት» ማስተካከል ይጠበቅብዎታል፡፡
“Automatic date & time” and “Automatic time zone” እንዲሰራ ክፍት ያድርጉ ወይም ማኑዋሊ ቀን እና ሰዓት ያስተካክሉ፡፡

2. ጎግል ፕሌይ ስቶር ከዚህ በፊት ይዞት የነበረውን ዳታ ማጽዳት
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ከዚህ በፊት ተጠቅመናቸው የነበረው ሶፍትዌሮች ዝርዝ ይዞ ይቀመጣል(Cached data) ይሄ በምንፈልገው ጊዜ በፍጥነት ለመክፈት ኢንተርኔት ግንኙነቱ ፍጥነት ባይኖረውም ይረዳናል ነገር ግን Cached data አንዳንድ ጊዜ በPlay Store ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡

✅ በGoogle Play ላይ Cached data ለማጽዳት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: ስቶሬጂ በመክፈት “CLEAR CACHE“.

3. የቅርብ ግዜ የሆነ ጎግል ፕሌይ ስቶር መጫን
በየጊዜው ሶፍትዌሮችን የሚሰሩ ዴቨሎፐሮች ለሰሩት ሶፍትዌር የቅርብ ግዜ ማድረጊያ አብዴተር የሚለቁ ሲሆን በዚህ የቅር ማድረጊያ ላይ የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ይካተታል፡፡.
በተመሳሳይ መልኩ Google የ Play ስቶር አብዴተር በየጊዜው የሚያወጣ ሲሆን እንደሚኖሩበት አገር የሚለቀቀው አብዴት ሊዘገይ ይችላል በቀጥታ የቅርብ ማድረጊያውን(APK ፋይል) ማግኘት ከቸኮሉ APKMirror በማለት ኢንተርኔት መጠቀሚያ ብሮውዘር ላይ ፈልገው ማውረድ ይችላሉ፡፡

4. ጎግል ፕሌይ ስቶር ወደነበረበት የመጀመሪያው ቨርዥን መመለስ
አንዳንዴ የቅርብ ጊዜ የተደረገ የጎግል ፕሌይ ስቶር ስሪት በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ስለሆንም አብዴት የተደረገው በማጥፋት ዲቫይሱን ስንገዛ የነበረውን(factory version ) ጊዜ መመለስ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች በመከተል እናጥፋ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Uninstall Updates”

5. ጎግል ፕሌይ ሰርቪስ መስራቱን ማረጋገጥ
Google Play Services ዋናው ተግባራት የGoogle አገልግሎቶች የሆኑትን Google Play ስቶር፣ ጎግል ማፕ፣ ጎግል ፕላስ ወዘተ አገልግሎቶች አውቶማቲካሊ ግንኙነት እንዲያደርጉ እና አብዴት የሚያደርግ የሚረዳ በመሆኑ እንደ ተጨማሪ መፍትሄ በመውሰድ Google Play Services መስራቱን ያረጋግጡ፡፡

6. ጎግል ፕሌይ ስቶርን ዘግቶ መክፈት
ይህ በአብዛኛው ተጠቃሚዎች የሚተገበሩበት የተለመደ ዘዴ ነው፡፡ ማድረግ ያለብዎት ነገር Google Play Storeን በመዝጋት እንደገና ማስጀመር( ለሌሎች አፕ ይሰራል) ችግሩን ሊፈታው ይችላል
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Force Stop” የሚለውን በመጠቀም መዝጋት እና እንደገና ይክፈቱ

7. ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት
ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ተመራጭ መፍትሄ ሲሆን ብዙውን ግዜ ይሰራል ምክንያቱም ስማርትፎን ስልኮች አጥፍተን ዳግም ማስጀመር በዲቫይሱ ላይ ያሉትን አፕ ያረጋጋል፡፡ በተቻለ መጠን አንድ አፕ ከወትሮው የተለየ ተግባር ካመጣ ዳግም አጥፍተን ስናስጀምር የተሻለ አፈጻጸም እና ችግሩን መፍታት ይችላል፡፡

8. ዲቫይሱን አንድሮድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዳግም ማስጀመር
ከላይ በጠቀስኩት መፍትሄ ምንም የማይሰራ ከሆነ ዲቫይሱን ፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ማድረግ በዚህ ሂደት በዲቫይሱ ላይ ያሉትን ዳታ፣ የተጫኑ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር እንደዚሁም የተጠቃሚውን አካውንት የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠፋል፡፡
በርካታ ችግሮች በዲቫይሱ ላይ ካልገጠመዎት በስተቀር የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ባትጠቀሙ እመርጣለሁ ዳግም ለማስጀመር ከወሰኑ ሚሞሪው ያውጡ መጠባበቂያ መውሰድዎን አይርሱ፡፡

ይሄን ችግር ለመፍታት ሊያግዝ የሚችል የተሻለ መፍትሄዎች ካለዎት አስተያየትዎን ይስጡን እንዲሁም ለ ጉዋደኞቹዎ ያካፍሉ
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍66👏6❤5
በኢትዮጵያ የፔሮል ሲስተም በምርጥ አቀራረብ በማይክሮ ሶፍት ኢክስኤል ክፍል እንድንና ሁለትን በትክክል ይመልከቱት
✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel መስራት አንችላለን? ክፍል -1
👇👇👇👇👇

https://youtu.be/rNcfrxbTyxo

✅ ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel እንዴት መስራት አንችላለን ክፍል 2 Payroll Part 2
👇👇👇👇

https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
👍46❤6😁1
*The most important words*
1.*PAN* - permanent account number.
2. *PDF* - portable document format.
3. *SIM* - Subscriber Identity Module.
4. *ATM* - Automated Teller machine.
5. *IFSC* - Indian Financial System Code.
6. *FSSAI(Fssai)* - Food Safety & Standards Authority of India.
7. *Wi-Fi* - Wireless fidelity.
8. *GOOGLE* - Global Organization Of Oriented Group Language Of Earth.
9. *YAHOO* - Yet Another Hierarchical Officious Oracle.
10. *WINDOW* - Wide Interactive Network
Development for Office work Solution.
11. *COMPUTER* - Common Oriented Machine. Particularly United and used under Technical and Educational Research.
12. *VIRUS* - Vital Information Resources Under Siege.
13. *UMTS* - Universal Mobile Telecommunications System.
14. *AMOLED* - Active-matrix organic light-emitting diode.
15. *OLED* - Organic light-emitting diode.
16. *IMEI* - International Mobile Equipment Identity.
17. *ESN* - Electronic Serial Number.
18. *UPS* - Uninterruptible power supply.
19. *HDMI* - High -Definition Multimedia
Interface.
20. *VPN* - Virtual private network.
21. *APN* - Access Point Name.
22. *LED* - Light emitting diode.
23. *DLNA* - Digital Living Network Alliance.
24. *RAM* - Random access memory.
25. *ROM* - Read only memory.
26. *VGA* - Video Graphics Array.
27. *QVGA* - Quarter Video Graphics Array.
28. *WVGA* - Wide video graphics array.
29. *WXGA* - Widescreen Extended Graphics Array.
30. *USB* - Universal serial Bus.
👍78❤10👏6😁2
​Are you looking for programming trainings?

Strongly encourage you to check out
TOFI TECHNOLOGIES PLC. (TT)

I think you need to look for a place where you can get some hands on training on the software they use and how it works and more likely to be successful in the workplace. 

Also, make sure you have a
good understanding of the business and the industry before you get started

📌 programming course.
course will include the following topics:


📚Frontend with javascript, html, css and bootstrap (4 months training)
📚Java for Android studio (4 months training)

📚 Backend with Nodejs, Express and Mysql (3 months training)
📚 basic cyber security (1 month training)

contact 📨

web:- https://tofitech.net
telegram:-  tofitechno.t.me
phone number:- +251902077707

📍 adress
Ayer tena peniel tower 3rd floor
👍24👏4
ከF1 እስከ F12 ያሉ #የዊንዶውስ
ቁልፎች አገልግሎት

የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

ካላወቃችሁ አትጨነቁ፡፡ ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው:: ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::

ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል .... ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡

🏷 በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው
የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function
Key እንላቸዋለን፡፡
በዋናነትም ከሌሎች #ቁልፎች ጋር
በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ
ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና
ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው
ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡

◽️F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው
ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን #የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ
Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡
◽️F2
#የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር
F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt
+ Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
◽️F3
ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift +
F3 መጫን #የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን
አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን
ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
◽️F4
አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 #መጫን
ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ
አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን
ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ
#የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን
ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን
ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ
ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4
ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt +
F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት
ነው፡፡
◽️F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5
መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ
Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡
◽️F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን
አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው
ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ
ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን #ወደቀጣዩ
የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
◽️F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ
#Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም
ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
◽️F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ #Startup menu
ለመግባት የጠቅማል፡፡
◽️F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን
በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን
#Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { }
ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት
CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ
ለማጥፋት
◽️F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን #ራይት ክሊክ
እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
◽️F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን
የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን
ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
◽️F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ #የ Save as ማስኮትን
ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡
👍65🎉3😁2❤1
ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች

1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡
5. ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
7. Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::
10. ኮምፒውተርዎን update ያድርጉ!
👍68👏7
✅🔸የዓለማችንን መልክ የቀየሩት 20ዎቹ የምንግዜም ታላላቅ ኢኖቬሽኖች
========================
▫️በሰው ልጆች ረዥም የህይወት ጉዞ ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚና እንዲ በቀላሉ የሚገለፅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሰዎች ወደዚች ምድር ከመጡ አንስቶ አካላዊውን ዓለም ለመግራት የሚያስችሉ የተለያዩ ፈጠራዎችንና የኢኖቬሽን ውጤቶች ያለማቋረጥ ሲተገብሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች አለም አሁን ያላትን መልክ ያጎናፀፏት እና የቀጣዩንም ትውልድ እጣ ፋንታ በበጎም ይሁን በክፉ የመወሰን አቅማቸው በእጅጉ የተጠበቀ ነው፡፡ አለማችን እስካሁን ያየቻቸውን የኢኖቬሽን ውጤቶች ለሰው ልጆች ከሰጡት ግልጋሎት እና በታሪክ ውስጥ ካላቸው የገዘፈ ተጽዕኖ አንፃር የሚከተሉት ኢኖቬሽኖች ከምንግዜም ታላላቆቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ በዘመን ቅደም ተከተል እንመልከታቸው፡

▫️1. እሳት (FIRE) - ስለእሳት ስናነሳ ብዙዎች የሚከራከሩበት ጉዳይ ቢኖር እሳት ተፈለሰፈ ከሚባል ይልቅ ተገኝቷል የሚለው ሃሳብ እጅግ ተስማሚ መሆኑን ነው፡፡ ቀደምት የሰው ዘሮች እሳትን እንዴት መፍጠር እና መቆጣጠር እንደሚችሉ ከማወቃቸው በፊት የእሳትን አደጋዎች በየአጋጣሚው ተመልክተው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የእሳትን ምንነት ከተረዱና የሚሰጣቸውን ጥቅም ካወቁ በኋላ እሳትን እንደ አንድ ትልቅ መገልገያ መጠቀም ጀምረዋል፡፡ አንዳንድ የአርኪዎሎጂ አጥኝዎች እሳት ጥቅም ላይ የዋለው ከ2 ሚሊዮን አመት በፊት ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ 125 ሺ አመታት እንዳስቆጠረ ይገልፃሉ፡፡ ይህ ክርክር ምንም ተባለ ምንም በሰው ልጆች ታሪክ ታላቅ ግኝት የሆነው እሳት ሰዎች ራሳቸውን ከተለያዩ ነገሮች እንዲከላከሉ እና ማብሰል የሚባለውን ትልቅ ክህሎት እንዲረዱ ያስቻል አስገራሚ ግኝት ነው፡፡

▫️2. ተሽከርካሪ ጎማ (WHEEL) - ይህ ፈጠራ የተገኘው በ3500 ዓመተ ዓለም (B.C) በሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን ነበር፡፡ የሜሶፖታሚያ ህዝቦች ይህንን አስገራሚ ፈጠራ የሸክላ ቁሳቁሶችን ለማበጃጀት ሲጠቀሙበት የቆየ ቢሆንም ከሶስትና አራት መቶ አመታት በኋላ ፈጠራው ለሰረገላ ማሽከርከሪያ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የመሳሪያው ተፅዕኖ እጅግ እየናኘ ሄዷል፡፡ ተሽከርካሪ ጎማ ለሰው ልጆች የመጓጓዣ እና የንድግ ስርዓት መፈጠር ትልቅ ሚና ያለው ግኝት ነው፡፡

▫️3. ኦፕቲካል ሌንሶች (OPTICAL LENSES) - የሰዎችን የእይታ አቅም ይበልጥ ለመጨመር እንደ ኦፕቲካል ሌንሶች ያሉ አስገራሚ ግኝቶች እጅግ ወሳኝ ነበሩ፡፡ ረዥም የፈጠራ ሂደት የነበራቸው እነዚህ ግኝቶች በጥንቱ የግብፅ እና የሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን እንደበለፀጉ የሚታመን ሲሆን ከግሪክ የተገኙት የብርሃን ንድፈ ሃሳቦች ደግሞ ለግኝቱ እውን መሆን ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ ኦፕቲካል ሌንሶች እንደቴሊቭዥን፣ ፎቶግራፍ እና ፊልም ያሉ ትልልቅ የሚዲያ ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጠሩ መንገድ የጠረጉም ናቸው፡፡

▫️4. ኮምፓስ (COMPASS) - ይህ እንቅስቃሴን ለመምራት የተዘየደው የቴክኖሎጂ ግኝት የሰው ልጆችን የአሰሳ ጥበብና አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ በመወሰድ ተተኪ የማይገኝለት አስገራሚ ግኝት ነው፡፡ የመጀሪያዎቹ ኮምፓሶች በተፈጥሮ የመግነጢሳዊ ይዘት ባላቸው የማዕድን ቁራጮች ወይም (lodestone) አማካኝነት የተሰሩ ሲሆን፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 300 እና 200 አመተ አለም አካባቢ በቻይና እንደተሰሩም ይነገራል፡፡

▫️5. ወረቀት (PAPER) - በ100 ዓመተ አለም አካባቢ በቻይና የተፈለሰፈው ይህ ግኘት የሰው ልጆችን የፅህፈት እና ሃሳብን የማጋራት ልምድ በእጅጉ የቀየረ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ከዚህ ጊዜ በፊት በግብፅ እና በሜክሲኮ የስልጣኔ ዘመናት የተፈለሰፉት እንደ ፓፒረስና አሜት ያሉ የመፃፊያ ቁሶች ለወረቅት መፈጠር አስተዋፅዖ ቢኖራቸውም በቻይና የነበረው ግኝት ግን አሁን ላለው የወረቀት ቴክሎጂ ትልቅ መሰረት የጣለ ነው፡፡
▫️6. ባሩድ (GUNPOWDER) - ከተለያዩ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች ተቀይጦ የሚሰራው ይህ ተቀጣጣይ ፈንጂ በ9ኛው ክፍለ ዘመን በቻይና እንደተፈለሰፈ የሚነገር ሲሆን ለዘመናዊው የጦር ቴክኖሎጂ መስፋፋትም ፈር ቀዳጅ የሚባል ነው፡፡ ይህ ግኘት በሰው ልጆች የውጊያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳደረ መሆኑም ይነገርለታል፡፡

▫️7. ማተሚያ (PRINTING PRESS) - እንደአውሮፓውያኑ በ1439 በጀርመናዊው ዮሃንስ ጉተንበርግ የተፈጠረው ይህ መሳሪያ ለሰው ልጆች የአዲስ ህይወት መጀመሪያ ዘመን ተደርጎ በብዙዎች ይወሰዳል፡፡ ይህ አስገራሚ ቴክኖሎጂ በሰዎች እጅ እየተፃፈ የሚሰራጨውን አድካሚ የፅህፈት ስርዓት በሜካናይዝድ ማሽን በመተካት የእውቀት አድማስ በሰዎች ዘንድ በቀላሉ እንዲሰፋፋ እና የሃይማኖት አስተምህሮዎች በአለም ላይ በፍጥነት እንዲናኙ ያስቻለ አስገራሚ ግኘት ነው፡፡

▫️8. ኤሌክትሪክ (ELECTRICITY) - የኤሌክትሪክ ፈጠራ ብዙ ብሩህ አዕምሮዎች ለሺህና ከዚያ በላይ አመታት አስተዋፅዖ ያደረጉበት እፁብ ድንቅ የሆነ የቴክኖሎጂ ግኝት ነው፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ፍራንክሊን ስለኤሌክትሪክ የነበረውን የአለም መረዳት አንድ እርምጃ ያራመደ የመሪነት አበርክቶት እንደነበረው የሚገለፅ ሲሆን በምርምር ዘርፍ ደረጃ ለመስኩ የሰጠው ሁለንተናዊ ትኩረት የቴክኖሎጂውን እድገት በእጅጉ አፋጥኖታል፡፡ ከዚህ ሂደት በማስከተል በ1879 የቶማስ ኤዲሰን የብርሃን አምፖል መፈጠር የኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ወደሰዎች እንዲቀርብ ያስቻለ ክስተት ነው፡፡ ይህ የምንግዜም ታላቅ ፈጠራ የሰው ልጆችን የህይወት መንገድ እስከወዲያኘው የቀየረ ግሩም ቴክኖሎጂ ነው፡፡

▫️9. የእንፋሎት ሞተር (STEAM ENGINE) - በስኮትላንዳዊው የፈጠራ ባለሙያ ጀምስ ዋት ከ1763 እስከ 1775 ተሰራ የሚባለው የእንፋሎት ሞተር ሌላኛው ለሰው ልጆች ትልቅ መሰረት የጣለ አስደናቂ የፈጠራ ውጤት ነው፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ ግኝት በጊዜው ለነበሩት ባቡሮች፣ መርከቦች እና በጠቅላለው ለኢንዱስትሪው አብዮት ዋና የሃይል ምንጭ በመሆን ተከትሎ ለመጣው የሰው ልጅ አብርሆት ታላቅ ውለታ ያደረገ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡

▫️10. የነዳጅ ሞተር (INTERNAL COMBUSTION ENGINE) - በ19ኛው ክፍለዘመን የተዋወቀው ይህ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በመጀመሪያ በቤልጄሚያዊው ኢንጅነር ኢትየን ሌኖየር (በ1859) የተፈጠረ ሲሆን ከጥቂት አመታት በኋላ በጀርመናዊው ኒኮላስ ኦቶ ይበልጥ ሊሻሻል ችሏል፡፡ ይህ አስገራሚ ፈጠራ የኬሚካል ኢነርጂን ወደ ሜካኒካል ኢነርጂ በመቀየር ቀድሞ የእንፋሎት ሞተር ሲሰጥ የነበረውን ግልጋሎት በተሻለ ሁኔታ በመተካት ለዘመናዊ መኪናዎችና አውሮፕላኖች ማገልገል የቻለ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡

▫️11. ስልክ (TELEPHONE) - የስኮትላንድ ተወላጁ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል በሰው ልጆች የመገናኛ ጥበብ ውስጥ ትልቅ አብዮት የፈጠረውን የስልክ ቴክኖሎጂ በራሱ ስም ያስመዘገበ ታላቅ የፈጠራ ባለሙያ ቢሆንም ከሱ ቀደምና እሱ በነበረበት ዘመንም ብዙ የፈጠራ ባለሙያዎች ለቴክኖለጂው ማበብ የራሳቸውን አሻራ ጥለዋል፡፡ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል አንደአውሮፓውያኑ በ1876 በኤሌክተሪክ ስልክ የመጀመሪያውን ፓትንት ካገኘ በኋላ የሰው ልጆች እርስ በእርስ የመገናኘት ልምድ እስወዲያኛው ተቀይሯል፡፡
👍38👏1😁1
▫️12. ክትባት (VACCINATION) - የክትባት ግኘት ለአንዳንዶች አከራካሪ ፈጠራ ቢሆንም ብዙዎች እንደሚገልፁት ከሆነ ግን በአለም ላይ የተከሰቱ በሽታዎችን በማጥፋት እና የሰው
ልጆችን በመታደግ በኩል እስካሁን ከታዩ አስደናቂ ግኝቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡ በአለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ክትባት እንደአውሮፓውያኑ በ1796 ለፈንጣጣ (smallpox) በሽታ የተሰራው ክትባት ሲሆን ኤድዋርድ ጄነር በተባለ ተመራማሪ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ክትባት በኋላ በ1885 በፈረንዊው ኬሚስትና ባዮለጂስት ሊዩስ ፓስተር የተሰራው የሬቢስ (rabies) ቫይረስ ክትባት ደግሞ ለዘመናዊው የመድሃኒት ቴክኖሎጂ ትልቅ በር የከፈተ ነበር፡፡

▫️13. መኪና (CARS) - ተሽከርካሪ መኪናዎች የሰዎችን የጉዞ ስርዓት እና ተያይዞ የመጣውን የከተሞች ባህሪ እስከወዲያኛው የቀየረ ግሩም የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው፡፡ ተሽከርካሪ መኪናዎች በዘመናዊው ቅርፃቸው በአለም ላይ ብቅ ማለት የጀመሩት በ19ነኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ አመታት ላይ ሲሆን በዋናነት በጀርመናዊው ካርል ቤንዝ እና ባልደረቦቹ የተከናወኑ ናቸው፡፡ ካርል ቤንዝ እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1885 የመጀመሪያዋን ሞተር ብስክሌት ተግባራዊ ካደረገ በኋላ የመኪና ቴክኖሎጂ በአለም ላይ እየናኘ ሄዷል፡፡

▫️14. አውሮፕላን (AIRPLANE) - በ1903 በአሜሪካውያን ወንድማማቾች ለውጤት የበቃው ይህ አስገራሚ ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን የረዥም ርቀት ጉዞ ፈጣን አማራጭ በመስጠት የትራንስፖረት ኢንዱስትሪን እስከወዲያኛው የቀየረ ነው፡፡ የአውሮፕላን ቴክኖሎጂ የአለም ሰዎችን ይበልጥ እንዲቀራረቡ በማድረግ የባህል፣ የምጣኔ ሃብት እና የእውቀት ልውውጦችን ይበልጥ ያዳበረ ቢሆንም በቴክኖሎጂው የማብሰሪያ ጊዚያት በአለም ላይ ለተከሰተው አለምአቀፍ ጦርነት ሌላ አባባሽ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

▫️15. ፔኒሲሊን (PENICILLIN) - እንደአውሮፓውያኑ በ1928 በስኮትላንዳዊው ሳይንቲስት አሌክዛንደር ፍሌሚንግ የተቀመረው ይህ ግኘት የፋርማሲዩቲካል ዘርፉን አንድ እርምጃ በማራመድ የመጀመሪያውን አንቲባዮቲክ መድሃኒት ለአለም ያስተዋወቀ ነው፡፡ ፔኒሲሊን እጅግ ብዛት ያላቸው ተላላፊ ባክቴሪያዎችን በመከላከል ለረዥም ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ አንቲባዮቲክ ሲሆን ለዘመናዊው የመድሃኒት ቴክኖሎጂም ፈር ቀዳጅ የሚባል ነው፡፡

▫️16. ሮኬቶች (ROCKETS) - ቀደምት የሚባለው የሮኬት ቴክኖሎጂ ሙከራ በቻይና የስልጣኔ ዘመናት እንደነበር የሚወሱ የታሪክ ማዛግብቶች ቢኖሩም አሁን ላይ የሚታወቀው ዘመናዊ የሮኬት ቴክኖሎጂ ግን በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተዋወቀ ነው፡፡ ይህ ግኝት በሰው ልጆች የህዋ ምርምር እና የጠፈር አሰሳ ላይ ትልቅ አበርክቶት የነበረው ፈጠራ ሲሆን በወታደራዊው ዘርፍም የማይናቅ አስተዋፅኦ ያለው ነው፡፡

▫️17. የኒውክለር ማብሊያ (NUCLEAR FISSION) - አተሞችን ይበልጥ ጥቃቅን ወደሆኑ ቅንጣቶች መከፋፈል እና በዚህም ከፍተኛ መጠን ያለው ኢነርጂ የመፍጠር ሂደት የኒውክለር ኃይል ማመንጫዎች እና አቶሚክ ቦምቦች እንዲፈጠሩ አስችሏል፡፡ ይህ አስገራሚ ግኘት በ20ኛው ክፍለ ዘመን በዚህ ዘርፍ ዙሪያ ሲሰሩ በነበሩ ስመጥር የፊዝክስ ሊቃውንት የተከናወነ ቢሆንም የኒውክለር ማብሊያውን በዋናነት በመስራት ረገድ ጀርመናውያኑ ኦቶ ሃን እና ፍሪትዝ ስታስመን አንዲሁም የኦስትሪያ ተወላጅ የሆኑት ሊዝ ማይትነር እና ኦቶ ፍሪሲች በቀዳሚነት ይጠቃሳሉ፡፡

▫️18. ሴሚኮንዳክተሮች (SEMICONDUCTOR) - የአሜሪካ ወይም የአለም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ማዕከል ከሆነችወ ሲልከን ቫሊ ቅጽል ስም ጀርባ የሚገኘው የሴሚኮንዳክተር ግኘት ብዙ ነገሩ ከሲልከን የተሰራ ሲሆን የአፈጣጠር ሁኔታውም በኤሌክትሪክ ዘመን እና እየመጣ በሚገኘው ዲጂታል ዘመን መካከል ላይ ነበር፡፡ የመጀመሪያው የሴሚኮንዳክተር ቁስን የያዘ መሳሪያ እንደአውሮፓውያኑ በ1947 የተዋወቀ ሲሆን በአሜሪካውያኑ ጆን ባርደን እና ዋልተር ብራታን የተሰራ ነው፡፡

▫️19. የግል ኮምፒውተሮች (PERSONAL COMPUTER) - አንደአውሮፓውያኑ በ1970ዎቹ የተፈጠሩት የግል ኮምፒውተሮች የሰው ልጀችን ሁለንተናዊ አቅም በማሳደግ በኩል ተወዳዳሪ አልነበራቸውም፡፡ በ1974 በማይክሮ ኢኒስትሩመንቴሽን እና ቴሌሜትሪ ሲስተም (MITS) የመጀመሪያ የሚባለው የግል ኮምፒውተር ከተዋወቀ በኋላ ቀጥለው የመጡት እንደ አፕል፣ ማይክሮሶፍት እና አይ ቢ ኤም ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ዘርፉን እስከወዲያኛው አራቀውታል፡፡

▫️20. በይነ መረብ (INTERNET) - አሁን አሁን የሰው ልጅ እስትንፋስ እስከመሆን የደረሰው ይህ አስገራሚ ግኘት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ሙከራዎች ሲደረጉበት የቆየ ቢሆንም አሁን በምናውቀም መልኩ ለሰው ልጆች መድረስ የጀመረው ከ1990ዎቹ ጀምሮ ነው፡፡ በጊዜው አንግሊዛዊው ቲም በርነር-ሊ የመጀመሪያውን የበይነ መረብ መግባቢያ የአለም አቀፍ ድር (WWW) ከቀመረ በኋላ አጠቃላይ የአለም መልክ ሊቀየር ችሏል፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ንግዳችን፣ ፖለቲካችን፣ መዘናኛችን የፈለጋችሁን ስም ስጡት ብቻ ሁለ ነገራችን በኢንተርኔት እና በኢንተርኔት ሁኗል፡፡
👍60❤3👏3
ኮምፒውተር ላይ ማንኛውንም ፍላሽና ኤክስተርናል ሀርድ ዲስክ ሲሰካ እንዳይሰራ ማድረግ እንዴት እንችላለን በቪዲዮ ይመልከቱ 👇👇👇
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
1. የኛን መረጃ ሌላ ሰው ያለእኛ ፈቃድ እንዳይወስድብን ለመዝጋትና
2ኛ. ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።
👇👇👇ቪዲዮውን ይመልከቱ👇👇👇
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs

👇👇👇ቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ👇👇👇
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍50❤4
ፕሮጀክት ቀረፃ

አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

1⃣ ማውጫ (Table of contents)
ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡
ማውጫ ሁሉንም ምዕራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

2⃣ አጭር መግለጫ (Executive Summary)
ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው የሚገቡ ሃሳቦች

✅ ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር
✅ ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ
✅ ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ
✅የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ
✅ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም
✅ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡

3⃣መግቢያ (Back Ground)
ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-
✅ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ
✅ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው
✅ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡

4⃣ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale)
ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡

5⃣የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective)
ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡
ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡

6⃣የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description):-

✅ የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ
✅ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ
✅የፕሮጀክቱ ቀጣይነት
✅የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት
✅ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ አለበት፡፡

7⃣የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization):-

✅ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ
✅የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር
✅የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡

8⃣የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮች ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries):-

✅ተጠቃሚዎች (Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡
✅ያገባኛል ባዮች (stakeholders):-
የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (Primary stake holders)፡-

በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡

9⃣የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation):-

የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው በማን፤ እንዴት፤ መቸና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡

1⃣0⃣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption):-

✅ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡

✅ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡

1⃣1⃣ ክትትና ግምገማ (Monitoring and Evaluation):
ይህ ርዕስ የሚይዛቸው፡-

✅የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት እንደሚቀርብ
✅ የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት
✅ የግምገማ ዕቅድን
✅ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ

1⃣2⃣ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት (sustainability):
ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡
ምርጥ የResearch ቻናል።

❓ትምህርት እየተማሩ ነው? ወይም ለመማር አስበዋል?
❓ጥናትና ምርምር(Research) እየሰሩ ነው?
❓ስለ Research እውቀትዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
❓ስለ SPSS, Stata, matlab ማውቅ ይፈልጋሉ?
⁉️የምንረዶት ጉዳይ አለ?

💻በጥናትና ምርምር ዙርያ የማማከር አገልግሎትም እንሰጠለን።

✅ ለሪሰርች ፕሮፖዛል - Proposal
✅ ለመጠይቅ - Questionnaire
✅ ለመረጃ ትንተና - Data Analysis
✅ ለየውሂብ አቀራረብ እና ትርጓሜ - Data Interpretation and presentation

S E R V I C E S (አገልግሎት)
--------------------
+ Assignment / አሳይመንት
+ Research / ሪሰርች
+ Proposal / ፕሮፖዛል
+ Term Paper / ተረም ፔፐር
+ Case study/ ኬዝ ስተዲ
+ Article Review
+ Mini research
Any other Questions
✅በአማርኛ ና በእንግሊዝኛ በግልጽና ቀላል አገላለጽ ስለ Research ጽንሳ ሀሳብ ጀምሮ ጽሑፎችን ያገኛሉ።
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
👆👆👆👆👆👆👆👆
👍71😁5❤4🥰3
864 እንቁላል መፈልፈል የሚችል ኢንኩቬተር fully automatic incubator .
0921513273 ይደውሉ!
👍23👏5
በኢንተርኔት አጭበርባሪዎች እንዳትታለሉ!
መፍትሄዎቹን ልብ ይበሉ!

✅ በሰለጠነው ዓለም በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈጸም ማታለል የተለመደ ነው፡፡ ይሁንእንጂ ይህ ችግር ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል። በኢንተርኔት የሚፈጸም ማጭበርበር  á‰ áˆ¸áˆ›á‰žá‰˝ ላይ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኪሣራ እያስከተለ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። 

✅ ከዚሁ ጎንለጎን በኮምፒውተር ቫይረስ አማካኝነት የሚሰነዘረው ጥቃትም በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መካከል ጉዳት ማድረሱን የተለያዩ ምንጮች በቅርብ ጊዜ ገልጸው ነበር፡፡

✅ ለማንኛውም ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁንም ይሁን ወደፊት የዚህ ችግር ተጠቂ መሆኗ አይቀርምና እንዲህ ካለው አደጋ እያንዳንዱ ዜጋ ራሱን መጠበቅ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ማሳወቅ ተገቢ ነው፡፡

✅ በመጀመሪያ ግን የኢንተርኔት ላይ አታላዮች ከሚጠቀሙባቸው በርካታ ማጭበርበሪያ ዘዴዎችን እንመልከት።

✅ የማታለያ ዘዴዎቻቸው ምንድናቸው?

የኢንተርኔት አጭበርባሪዎች ከተለያዩ ሰዎች ጋር የሚገናኙት በኢሜይል አማካኝነት ነው። ከገንዘብ ጉዳይ ጋር የተያያዙ የግል መረጃዎችን የሚጠይቅ የማታለያ መልእክት ፊሺንግ ኢሜይል ይባላል። ታዲያ በዚህ ዓይነቱ ኢሜይል የሚጠቀሙ አጭበርባሪዎችም ሕጋዊ የሚመስል ድረ ገጽ ተጠቅመው ሰዎችን በማታለል ፓስወርድ፣ የክሬዲት ካርድ ቁጥራቸውን ወይም የባንክ ሒሳብ መረጃቸውን እንዲሰጧቸው ያደርጋሉ።

✅ እንደነዚህ ካሉት ፊሺንግ ኢሜይሎች መካከል አንዳንዶቹ ምንም ዓይነት መረጃ ባትሰጥ እንኳ አጭበርባሪዎች የፈለጉትን ነገር እንዲያገኙ ይረዷቸዋል። ምክንያቱም አንድን ኢሜይል መክፈትህ ብቻ ስፓይ ሶፍትዌር የሚባል ፕሮግራም ወደ ኮምፒውተርህ እንዲገባ ሊያደርግና በኮምፒውተርህ የምታከናውናቸውን ነገሮች ሊመዘግቡ ይችላሉ። አንዳንዶቹ የምትጫናቸውን የኮምፒውተር ቁልፎች የሚመዘግቡ ሲሆን አጭበርባሪዎቹ በዚህ ተጠቅመው የይለፍ ቃልህን እና የግል መረጃዎችህን መስረቅ ይችላሉ። ሌሎች ፕሮግራሞች ደግሞ አጭበርባሪ ወደሆኑ ድረ ገጾች የሚመሩህ ሊሆኑ ይችላሉ። 

✅ ታዲያ ከእነዚህ አታላዮች እንዴት መጠንቀቅ ይቻላል
መፍትሄዎቹ አጭርና ግልጽ ናቸው፡፡ በመጀመሪያ አጠራጣሪ ወደሆኑ ድረ ገጾች የሚመሩ ኢሜይሎች ሲደርሱህ ጥንቃቄ አድርግ። እንዲህ ያሉ ኢሜይሎችን ስትከፍት አጭበርባሪዎች ትሮጃን ሆርስ ወይም ትሮጃን በሚባለው ፕሮግራም አማካኝነት አንተ ሳታውቅ ኮምፒውተርህ ውስጥ ያሉ የግል መረጃዎችህን ሊያገኙ ይችላሉ። 

✅ አጭበርባሪዎች ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘትና መረጃዎችን ለመስረቅ የሚያግዟቸውን ስፓይ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተርህ ላይ ለመጫን ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች መካከል የብልግና ምስሎችና ጽሑፎች የሚገኙባቸው ድረ ገጾች፣ ምንጫቸው የማይታወቅ ሶፍትዌሮችን የሚያቀርቡ ድረ ገጾች እና አንዳንድ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ይገኛሉ። አንዳንዴ ደግሞ የማይታመን ትርፍ ወይንም ገንዘብ እንደሚያስገኙ ለሚገልጹ የኢሜይሎች መልእክቶች መልስ መስጠት አያስፈልግም።

✅ ምናልባት በኢንተርኔት አማካኝነት ሥራ የምትፈልግ ከሆነም አጭበርባሪዎች፣ የማታለያ ድረ ገጾችን በመጠቀም “የመመዝገቢያ ክፍያ” እና ሌላው ቀርቶ ከገንዘብ ጋር የተያያዙ የግል መረጃዎችን ሊሰበሰቡ ይችላሉ።

✅ እነዚህ አጭበርባሪዎች ወደ ትላልቅ ኩባንያዎች ወይም ገንዘብ ነክ ተቋማት ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው የድርጅቶቹን የመረጃ ማዕከል ጥሰው በመግባት መረጃዎችን መስረቅ እየቻሉ ይገኛሉ። በአሁኑ ጊዜ አጭበርባሪ ሠራተኞችና የኮምፒውተር መረጃ ጠላፊዎች የሰረቋቸውን የክሬዲት ካርድ መረጃዎችንና የግለሰቦችን ሙሉ መረጃዎች በኢንተርኔት ላይ የሚሸጡበት የደራ ገበያ እንዳለ አንዳንድ ምንጮች ይገልጻሉ።

✅ ስለዚህ አንተም ከላይ ከተጠቀሱ ጥንቃቄዎች በተጨማሪ በኢንተርኔት እንዳትጭበረበር የኮምፒውተርህ መከላከያ (ፋየርዎል) ሁልጊዜ የሚሠራ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የቫይረስ መከላከያ ፕሮግራሞች ወይንም አንቲቫይረስ መጫን እና ሌሎች ፕሮግራሞች ጊዜ ያለፈባቸው አለመሆናቸውን ዘወትር ማረጋገጥ ብልህነት ነው፡፡ 

📌 እናንተስ ምን ትላላችሁ! በኢንተርኔት ላይ ላለመታለል ምን አይነት ጥንቃቄዎች ሊወስዱ ይገባል!
👍100🙏11😁1
የዲጂታል ዘመን አመራር ማለት በዲጂታል ዘመን ያለ አመራር ነው እንጂ አሰራሩ ዲጂታል የሆነ ድርጅት ብቻ የሚመራ አመራር ማለት አይደለም። እንደሚታወቀው ይህ ዘመን የመረጃ ዘመን እንደሆነ እሙን ነው። በዚህ የመረጃ
ዘመን(Information Age) መረጃ ጉልበት መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ ማለት አንድን ውሳኔ ለመወሰን አንድ ሰው በቂ፣ ትክክለኛ እና ጊዜውን የጠበቀ መረጃ ያስፈልገዋል። የመረጃ ዘመን ሲባል የዓለም ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎችን በወሳኝ ደረጃ የመረጃ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ለማመላከት ነው።

👇👇👇መርጥ ቪዲዮ ይመልከቱት👇👇👇
https://youtu.be/us8s1G9ikHA
https://youtu.be/us8s1G9ikHA
https://youtu.be/us8s1G9ikHA
https://youtu.be/us8s1G9ikHA
👍26🥰1😁1
1 ዉጤታማ ሪፖርትና እቅድ ማዘጋጀት ይቻላል?
2 ስልታዊ እቅድ ማለት ምን ማለት ነዉ?
3 የሪፖርት አሰራር ቅደም ተከተል
4 በሪፖርት ስራ ዉስጥ መካተት የሚገባቸዉ ጠቃሚ ነጥቦች

~~ዉጤታማ ሪፖርትና እቅድ ማዘጋጀት ይቻላል?~~
መግቢያ
ጫና የበዛበት ስራ ላይ ብዙ ጊዜዎን እያሳለፉ ነዉ፤ ነገር ግን ዉጤታማ ሆነዉ አያዉቁም ተዲያ ችግሩ ምን ላይ ነዉ ብለዉ ራሰዎን ጠይቀዉ ያዉቃሉ? ምናልባት በዉስን ስኬቶች ዉስጥ ራሰዎን ደብቀዉ ይሆናል ነገር ግን ያለወት ክህሎት (skill) እና የነበረዎት ጥረት ከዚህ የተሻለ ዉጤት ሊያስገኝ ይችል ነበር፡፡ ታዲያ ለምን ዉጤታችን በጥረታችን ልክ አልሆነም?
ብዙ ሰዎች ስራ በመቀያየር ሂደት ዉስጥ ብዙ ጊዚያቸዉን ሲያባክኑ ይታያል አንዳንዶች ደግሞ በጥድፊያ ዉጤትን ይናፍቃሉ የሚሳካላቸዉ ግን ጥቂቶች ናቸዉ፡፡ የዚህ ሁሉ ችግር መነሻዉ ስራችን በዉጤታማ እቅድ ላይ ያልተመሰረተ ሲሆን እንደሆነ ምን ያህሎቻችን እናዉቃለን?

✅ ለመሆኑ ዉጤታማ እቅድ ለማቀድ አስፈላጊ የሚባሉት ነገሮች ምንድን ናቸዉ?
🔷 ሃሳበዎትን ግልጽ ማድርግ (clarify your ideas)
🔷 ተግባረዎት ላይ ማተኮር (focus your effort)
🔷 ጊዜዎን ባግባቡ መጠቀም(use your time)
🔷 ያለዉን አቅም መጠቀም(use your resources and productivity)
🔷 የመፈጸም አቅምና እድለዎን ማሳደግ(increase your chance of achieving)

✅ SMART እቅድ ማልት ምን ማለት ነዉ?
🔶 1.የተለየ ወይም የተወሰነ(Specific)
ግባችን ግልጽና የተለዩ መሆን አለባቸዉ፤ ካልሆነ ግን የምንፈልገዉን ዉጤት ማምጣት አንችልም፡፡ እቅዳችንን በምንነድፍበት ጊዜ የሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ትኩርት ማድረግ ያስፈልጋል:
📌 እቅዱን በዉጤት ለማጠናቀቅ ምን ይጠበቅብኛል?
📌 የእቅዱ ዉጤት ምን ያህል ጠቀሜታ አለዉ?
📌 እነማን ይሳተፋሉ?
📌 የት ነዉ እቅዱ ተግባራዊ የሚሆነዉ?
📌 እቅዱን ለማሳካት ምን አቅም አለ(sources)?
ትልቅ ዉጤት የሚያመጣ እና ማህበረሰቡን ሊጠቅም የሚችል እቅድ ማቀድ ፈልገዋል፤ በቅድሚያ ማሰብ ያለበዎት " የሚፈለገዉን አይነት እቅድ ለማቀድ በቂ ክህሎትና ልምድ አለኝ እንዲሁም እቀዱን ለማሳካትና ለመምራት በቂ እዉቀት አለኝ ተገቢዉን ዉጤት እንደማመጣም እርግኛ ነኝ ብለዉ መነሳት እጂግ አስፈላጊ ነዉ፡፡

🔶 2. ሊለካ የሚችል(Measurable)
ሊለካ የሚችል ግብ በጣም ጠቃሚ ነዉ፤ ስለዚህ እቅዳችን ቀስ በቀስ ወደፊት ሊራመድ የሚችልና አሳታፊ መሆኑን ማወቅ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡ ተራማጅ እና አሳታፊ እቅድ የሚባለዉ አስፈላጊ ተግባራት ላይ ያጠነጠነ፣ በተያዘለት ጊዜ እየሄደ ያለ እና ሂደቱ ስኬታማ ሊሆን እንደሚችል አመላካች የሆነ መሆን አለበት፡፡
⚪️ ሊለካ የሚችል እቅድ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ያጠነጠነ ነዉ
📌 ምን ያህል?
📌 ስንት?
📌 በምን ያህል መጠን ይሳካል?
ምሳሌ
በቀጣይ በጄት አመት በከተማ ሀ ለ3000 ወጣቶች ስራ መፍጠር፡፡ ይህ እቅድ የሚከተሉትን ጉዳዩች ማሟላት አለበት፤ 3000=የከተማ ሀ የገቢ መጠን፣ 3000=አቅርቦት፣ 3000=የፈጻሚ አካላት ቁርጠኝነት፡፡

🔶 3.ዉጤታማ (Achievable)
ግባችን በእዉነታ እና ሊደረስበት በሚችል መልኩ መታቀዱ ለዉጤታማነታችን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ እቅዳችን ዉጤታማ እንዲሆን ከዚህ በፊት ያጋጠሙንን ችግሮች እና መልካም እድሎችን በሚገባ መመልከት በጣም ጠቃሚ ነዉ፡፡
ዉጤታማ እቅድ ለማቀድ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ያስፈልጋል
📌እንዴት እቅዴ በዉጤት ሊጠናቀቅ ይችላል?
ግቦቸ ምን ያህል እዉነታነት አላቸዉ, ለምሳሌ ከፋይናንስ አቅርቦት አንጻር?
ምሳሌ
በዚህ በጄት አመት የእንጅባራ ከተማ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦትን 100% ማድረስ፡፡ ይህ እቅድ በእዉነታ ላይ የተመሰረተ መሆኑን የምናዉቀዉ
በከተማዋ ይህን እቅድ ለማሳካት ምቹ ሁኔታዎች አሉ ወይ
በከተማዋ ይህን እቅድ ለማሳካት የሚያስፈልጉ አቅሞች አሉ ወይ የሚሉትን ጥያቄዎች ከመለስን በኋላ ይሆናል፡፡

🔶 4. ቀጥተኛ ግንኙነት ያለዉ(Relevant)
ይህ ማለት ግቦቻችን ቀጥታ ሊፈቱ ከሚገባቸዉ ነገሮች ግንኙነት መኖራቸዉን እና ከሌሎች ግቦች ጋር ሊጣጣም የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ማለት ነዉ፡፡ ሁላችንም ለእቅዳችን ስኬት የሚያግዘን አካል እንፈልጋለን ነገር ግን ግቦቻችን ሊያግዙን ከሚፈልጉ አካላት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ከሌላቸዉ ሊያግዙን እንደማይችሉ መገንዘብ ጠቃሚ ነዉ፡፡
🔶 ይህ ተግባር ከሚከተሉት ጥያቄዎች ጋር ቀጥተኛ 📌 ግንኙነት ሊኖረዉ ይገባል
📌 ግቦቻችን ከሚፈለጉት ዉጤቶች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸዉ?
📌 ልናሳካ ያሰብነዉ እቅድ ወቅቱን የጠበቀ ነዉ?
📌 እቅዳችን ከፍላጎታችን እና ከጥረታችን ጋር አብሮ የሚሄድ ነዉ?
📌 የህን እቅድ ለመስራት እኔ ትክክለኛዉ ሰዉ ነኝ?
📌 እቅዴ አሁን ካለዉ አጠቃላይ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ጋር የማይጋጭ ነዉ?
ምሳሌ
በከተማ ሀ ደረጃዉን የጠበቀ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ መገንባት፡፡ ከዚህ እቅድ በፊት በከተማ ሀ በቂ የሰለጠነ የሰዉ ሃይል መኖሩን፣ ይህ ስራ ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን፣ ቢሰራ እንኳን በቂ ገቢያ መኖሩን፣ ይህን እቅድ ለማሳካት የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ ስለመኖራቸዉ መረጋገጥ አለበት፡፡

🔶 5. በጊዜ የተለካ(Time-bound)
እያንዳነዱ ግብ የራሱ ጊዜ አለዉ መቸ ታቅዶ፤ በምን ሂደት ዉስጥ አልፎ መቸ እንደሚጠናቀቅ በግልጽ መታወቅ አለበት፡፡ ይህ የጊዜ ክፍፍል ዋናው የዉጤታማ እቅድ አካል መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
በጊዜ የተለካ እቅድ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ አለበት:
📌 መቸ?
📌 ለሚቀጥሉት 6 ወራት መሰራት ያለባቸዉ ጉዳዩች ምንድን ናቸዉ?
📌 ባለፉት 6 ወራት ምን ምን ተግባራት ተሰሩ?
📌 ዛሬ ምን ሰራሁ?
ምሳሌ
በ2015 በጀት አመት 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን እራሳቸዉን እንዲችሉ ማድረግ፡፡ በዚህ ግብ ስር ዉጤቱን ለማረጋገጥ በ3 ወራት ዉስጥ 75 እንደዚሁም በ6 ወራ ዉስጥ 150 የጎዳና ተዳዳሪወች ራሳቸዉን ማስቻል እንደተቻለ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ይህ ካልሆነ እቅዳችን በተያዘለት ጊዜ ተግባሩን እያሳካ አለመሆኑን ያሳየናል፡፡

~~ስልታዊ እቅድ ማለት ምን ማለት ነዉ?~~
✅ ስልታዊ እቅድ(Systematic planning) ማለት አንዱ የእቅድ ሂደት ሲሆን ነገር ግን ሂደቱ ሳይንሳዊ ሂደትን እና ሃሳባዊ ንድፍ ይዞ የሚጓዝ ነዉ፡፡ ስልታዊ እቅድ የግድ ግልጽ አላማዎችና ታአማኒ የሆነ ዉጤት ሊያመጣ የሚችል ነዉ፡፡ ስልታዊ እቅድ የጋራ ስሜት፣ ዉጤት ተኮር(graded approach) እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለእቅዱ ተመጣጣኝ የሆኑ ግበአቶች እና ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸዉን በማረጋገጥ የሚታቀድ የእቅድ አይነት ነዉ፡፡ ስልታዊ እቅድን ለማቀድ የሚመለከታቸዉን ሁሉ አካላት፣ተቋማት ማካተት እና ግለሰቦች እንዲሁም እቅዱ ተግባራዊ የሚሆንበት ቦታ ላይ የሚገኙ ማህበረሰቦች ሁሉ መካተት አለባቸዉ፡፡ በዚህ መልኩ የታቀደ እቅድ የማህበረሰቡን ተሳትፎ በቀላሉ ለማገኜትም ሆነ ዉጤቱ ተአማኝ እንዲሆን ከፍተኛ ጥቅም አለዉ፡፡
👍43❤1
🔶 ስልታዊ እቅድ ለማቀድ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል
📌 1.ችግሮችን መለየት
📌 አንገብጋቢና ቅድሚያ ሊሰጣቸዉ የሚገቡ ችግሮችን መለየት
📌 በቂ ግብአቶችና የጊዜ መጠን ማስቀመጥ
🔶 2.አማራጭ ዉሳኔዎችን መለየት
ዉሳኔዎችን ማጤን
የተለያዩ ቸማራጮችን መመልከት
🔶 3.የመረጃ ግበአቶችን መለየት
ስላለዉ ግበአት መረጃ መሰብብ
የመረጃ ምንጮችን መለየት
ለተግባራችን የሚጠቅሙ መረጃዎችን መለየት
ናሙና መዉሰድና የትንተና ዘዴዎችን መለየት

🔶 4.እቅድ ተግባራዊ የሚሆንባቸዉን ቦታዎች መለየት
📌 ጂኦግራፊካል ቦታዎችን መለየት
📌 የህዝቡን ብዛትና ፍላጎት መለየት
📌 የት መረጃ መሰብሰብ እንዳለበት መለየት
📌 የጊዜ ሰሌዳ ማዉጣት
🔶 5.የተግባር ክንዉኖችን መለየት
📌የሚመለከታቸዉን ብቻ የህብረተሰብ ክፍሎች መለየት
📌 ተግባራትን በቅደም ተከተላቸዉ መሰረት ማስኬድ

🔶 6.ስህተቶችን መቀነስ
📌 ስህተቶችን በየጊዜዉ ለማረም መሞከር
📌 ለስህተት የሚያጋልጡ የመረጃ ምንጮችን መለየት
📌 የመረጃዎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ
🔶7. መልካም አጋጣሚ የሚፈጥሩ አሰራሮችን መለየት
📌 ትክክለኛ የዉጤት መለኪያዎችን መጠቀም
📌 ስታስቲካል ቁጥሮችን መጠቀም
📌 አመቺ ናሙናዎችንመዉሰድ
📌 የተገኙ ማንኛዉንም መረጃዎችን በዶክሜንት መያዝ

~የሪፖርት አሰራር ቅደም ተከተል~~
ሪፖርት ስናዘጋጅ የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች መከተል ያስፈልጋል፡፡
🔶 1.ርእስ– በዚህ ወስጥ የሚካተቱት የመስሪያ ቤቱ እና የሰራዉ ሰዉ ስም እና ሪፖርቱ የተሰራበት ቀን ናቸዉ፡፡
🔶 2.አጭር መግለጫ – ይህ የሚጠቅመዉ የሪፖርቱን ዋና ዋና ጭብጦች፣ የተጠቃለለ ሃሳብ እና ዋና ዋና ጥንካሬዉን ለማስገንዘብ ነዉ፡፡ በአጠቃላይ አንባቢዎች ሙሉ ሪፖርቱን ሳያነቡ ዋና ዋና ነጥቦችን እንዲያዉቁና በቀላሉ መረጃ እንዲያገኙ ታስቦ የሚጻፍ የሪፖርቱ ዋና ሃሳብ ነዉ፡፡
🔶 3.መግቢያ – የሪፖርቱ የመጀመሪያዉ ገጽ መግቢያ ነዉ፡፡ በመግቢያዉ ዉሥጥ ያጋጠሙ ችግሮች እና አንባቢዉ አንባቢዉ የሪፖርቱን ምንነት የሚረዳበት አጠቃላይ ሃሳብ ይቀርብበታል፡፡ በተጨማሪም የሙያዊ ሃሳቦች ትርጉም እና የርእሱ ዋና ዋና ጽንሰ ሃሳቦች ይካተቱበታል፡፡

🔶 4.ሃተታ – ሃተታ የሪፖርቱ ዋና አካል ነዉ፡፡ በዚህ ዉስጥ በርካታ ክፍሎች ይኖራሉ፡፡ ለሪፖርቱ ግበአትነት የተሰበሰቡ መረጃዎች ሁሉ በቅደም ተከተላቸዉ ይገለጽባቸዋል፡፡ በዚህ ዉስጥ በጣም ጠቃሚ የሆኑት መረጃዎች በቅድሚያ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
🔶 5.ማጠቃለያ– ይህ ሁሉም የሪፖርቱ ሃሳቦች ተጨምቀዉ የሚገለጹበት ሁኔታ ነዉ፡፡ መጠንቀቅ ያለብን ነገር በማጠቃለያ ሃሳብ ዉስጥ ከሪፖርቱ ጭብጥ ዉጭ የተወሰኑ ሰዎች የፈጠሩት የጓዳ ቋንቋ(jargon) መጠቀም የለብንም፡፡
🔶 4.የታየ ለዉጥ – በዚህ ዉስጥ ሪፖርቱ ሊሰጥ የሚችለዉ ጥቅምና የታዩ ለዉጦች ይገለጹበታል በተጨማሪም ቅድሚያ የተሰጣቸዉ ጉዳዩች ይገለጹበታል፡፡
🔶 5.ተጨማሪ መግለጫ– በዚህ ሂደት ዉስጥ የመረጃ ምንጮች እና ቴክኒካል መረጃዎች ይዘረዘሩበታል፡፡
Remember that the information needs to be organized logically with the most important information coming first.

~በሪፖርት ስራ ዉስጥ መካተት የሚገባቸዉ ጠቃሚ ነጥቦች~
📌 ግልጽ የሆኑ ስሞችን መጠቀም፣ በሪፖር ስራ ዉስጥ የተግባሪዉ እና ተግባሩ የሚከናወንበት ቦታ ስም በግልጽ መቀመጥ አለበት”
📌 የግል ሃሳብን አለማካተት
የተሰሩ ስራዎችን እና በመሰራት ላይ ያሉ ስራዎች ጭማሬም ሆነ የተቀነሰ የግለሰብ ሃሳብ ሳይካተትባቸዉ በግልጽ መቀመጣቸዉን ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ የተሰሩ ስራዎች አጭር፣ ግልጽ እና ሁሉም ሰዉ በቀላሉ ሊረዳዉ በሚችለዉ መልኩ መቀመጥ አለባቸዉ፡፡

📌 ግልጽ እና በተወሰነ ሃሳብ ላይ ያጠነጠነ መሆን ይገባዋል.
📌 ያልተወሳሰበ እና ቀላል ቋንቋ መጠቀም.
📌 በእንቀጾች የተከፋፈለ እና ዘገበዊ ይዘት ቢኖረዉ ይመረጣል.

ምሳሌ
ቅደም ተከተሉን የጠበቀ የሪፖርት ፎርማት:
Members to which the report is meant for
📌 ርእስ -------------------------------
📌 የሪፖርቱ አካላት
[ስም፣ ተቋም፣ ቦታ፣ ሃላፊ፣አባላት]
ቀን፣ ሰአትና መገኛ
-------------------------------------------------
አላማ
---------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የተፈጸሙ ጉዳዩች (Issues) ------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
አሁን ያለበት ሁኔታ
•
•
አፈጻጸም
•
•
የወደፊት ግብ
•
•
📌 የሪፖርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች / Main Body of the Report---------------------------------------------------------------------
📌 የተገኙ ዋና ዋና ዉጤቶች------------------------------------------------------------------------------------------------------
©አህመድ ከበደ 2012

እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍104❤3🔥2🥰1