Muhammed Computer Technology (MCT)
37.7K subscribers
528 photos
7 videos
254 files
913 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ወደ ትግበራ ስራ ገብተናል!

የኮምፒውተራይዝድ ሬጅስትራር ሲስተም ለ6 ኮሌጆች ምክትል ዲኖች፣ የሬጅስትራር ሀላፊዎች፣ የሬጅስትራር ባለሙያዎች፣ ለICT መምህራን የ2 ቀን ስልጠና ለ26 የስልጠና ተሳታፊዎች በመስጠት የተጠናቀቀ ሲሆን ከስልጠና በኋላ ለሶስት ኮሌጆች ሲስተሙ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ሁኗል!

በዚህም በአማራ ክልል 4 ኮሌጆች ደቡብ ክልል 1 ኮሌጅ ስራውን እየተጠቀሙበት ነው

ነገ ለ2 ኮሌጆች ሲስተሙን እንዲጠቀሙበት የመጫን ስራ ይሰራል።

ለዚህም ለቲሊሊ፣ ለአንከሻ፣ ዳንግላ፣ ለአዲስ ቅዳምና ቻግኒ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች፣ ለአዊ ብሄረሰብ ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች የስራውን ጥራት፣ ቅልጥፍና፣ ችግር ፈችነቱን በማየት ተግባራዊ እንዲሆን ስላደረጋችሁ በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ!

በተጨማሪም የግል፣ የመንግስት ኮሌጆች ሲስተሙን የምትፈልጉ ካላችሁ።

በ 0929273364 መደወል ይቻላል!
👍812👎1
ቴሌግራም (Telegram) እና ቢዝነስ
🔶 ቴሌግራም (Telegram) በአገራችን በጣም ተወዳጅ የሆነ የመልዕክት መለዋወጫ (Instant Messaging) አፕ/መተግበሪያ ነው። ተወዳጅ ከሆነበት ምክንያት አንዱ በአነስተኛ ዳታ መጠቀም መቻሉ ነው። ቴሌግራምን በስልካችንም ሆነ ከስልካችን አካውንት ጋር አገናኝተን በኮምፒውተራችን ላይ መጠቀም እንችላለን።
🔶 ቴሌግራም በተለይ አገራችን ውስጥ ከሌሎች የመልዕክት መለዋወጫ (Instant Messaging) አፖች/መተግበሪያዎች በላቀ ሁኔታ ተወዳጅ ስለሆነ ለለቢዝነሶች ከፍተኛ ጥቅም አለው።
ቢዝነሶች በነኝህ መልኮች ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

🔶 ቴሌግራም ቻነል በመፍጠር  

ቴሌግራም ላይ አካውንት ያለው ሰው ቻነል መፍጠር ይችላል። የመጀመሪያዎቹን 200 ተከታዮችም ያለምንም እገዳ ከኮንታክቶቹ ላይ በማስገባት ተከታይ (Subscriber) ማድረግ ይችላል። ከ200 በላይ የሆነውን ግን ለኮንታክቶቹ መልዕክት በመላክ ተከታይ (Subscriber) እንዲሆኑ መጋበዝ ይችላል። ዋናው ነገር ቻነል መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን በሚገባ አገልግሎቶቹን ወይም ምርቶቹን በየጊዜው በመለጠፍ ለተከታዮቹ ማስተዋወቅ ነው። ተወዳጅ የሆነ ምርት ወይም አግልግሎት ካለው እና አቀራረቡ ሳቢ ከሆነ በቀላሉ ብዙ ተከታዮች ይኖሩታል።

🔶 ቴሌግራም ቻት ግሩፕ  በመፍጠር

ይሄ ከቻነል የሚለየው አባላቱ መወያየት የሚችሉበት ሲሆን ሌላ ሰውም የ ግሩፑ አባል እንዲሆን ማስገባት ይችላሉ። የግሩፑ አድሚኖች ተገቢ ያልሆነ ነገር እየተለጠፈ እንዳልሆነ መከታተል እና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።

🔶 ቴሌግራም ቦት (bot)

ቴሌግራም ቦት (bot) በሶፍትዌር የሚሠራ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ፊቸሮች ያሉት የቴሌግራም አካውንት ሲሆን፤ ቦትን ከቻነላችን ወይንም ከቻት ግሩፓችን ጋር በማቀናጀት የተለያዩ ሥራዎችን እንዲሠራልን ማድረግ እንችላለን።
ቴሌግራም በቀላሉ ቢዝነሳችንን የምናስተዋወቅበት መንገድ ስለሆነ ሳንውል ሳናድር https://telegram.org/ ላይ በመግባት መጠቀም መጀመር አለብን።
👍55👎62🥰2
MuhammedAminWebsite_1_1.0.apk
156.1 KB
በዌብሳት አድራሻየ በመግባት ጥሩ ጥሩ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ!
በተለይ ለተመራቂ የITና ተያያዥ ለማስተርስና ለመጀመሪያ ድግሪ የሪሰርች መረጃዊችን ማግኜት ይቻላል።
www.mameamin.6te.net
ወይም ቴሌግራም ቻናሌ ላይ በመግባት የዌብሳቴን App በማውረድ በስልካችሁ ጭናችሁ መጠቀም ትችላላችሁ!
ከላይ ያለውን 👆👆👆 MuhammedAminWebsite_1_1.0 የሚለውን አፕሊኬሽን በማውረድ መጠቀም ይቻላል

website ማሰራት ከፈለጉ በ0929273364 ይደውሉ!
👍32😁3👏1
~+ አዲስ Smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ማገናዘብ የሚገባዎ 13 ነገሮች ከምሳሌ ጋር ~+
መግዛት ያሰቡት smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል።ማንኛውም smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ስልኩ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን 13 መመዘኛዎች ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
1~ ፕሮሰሰር(Processor)
ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821) ቢሆን ይመረጣል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።
2 ~ ካሜራ
ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 13mp(Megapixels) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 8mp በቂ ነው።
3 ~ ባትሪ
ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 3500mAh(Miliamp Hour) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh በቂ ነው።
4 ~ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች አሉ።ለምሳሌ samsung galaxy ስልኮች ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።
5 ~ Storage
ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ(microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።
6 ~ Headphone Jack
HeadPhone 3.5mm audio
jack ቢሆን ይመረጣል።
7 RAM ከተቻለ ከ4GB በላይ ቢሆን ጥሩ ነው ነገርግን ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB በቂ ነው
8 USB File transfer USB 2.0 በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆ ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው.
9 Physical Size በኢንች ለናንተ የሚቸውንም መምረጥ አለባችሁ በተለይ ለአያያዝ ምቹ መሆኑን አረጋግጡ።
10 የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።
11 Display: 6.5 inches በጣም ምርጥ ነው ለአያያዝ ምቹ ነው።
12 Resolution 1080 x 2400 pixels ቢሆን ይመከራል
13 Data 4G LTE ለመጠቀም ያመች ዘንድ 4G Support የሚያደርግ ቢሆን ይመረጣል

ምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
Camera : 8000 x 6000 pixels, 1920 x 1080 pixels, 30 fps
SIM card : Nano-SIM
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
USB: 2.0, Micro USB
Bluetooth: 5.0
Positioning: GPS, A-GPS, GLONASS, BeiDou
👍11616👏5👎2🥰1
Telegra ካርድ እየበላ አስቸግሮታል?
ካርድ የሚጨርስበት ምክኒያት የተላኩልን message በራሱ ግዜ dawnload ስለሚያደርግባችሁ ስለሆነ የሚከተለውን ይሞክሩት
ቴግራማችሁ ላይ ትገቡና በግራ በኩል ከላይ ሶስት መስመሩን ትጫኑና settings የሚለውን ትፈልጉና ትጫናላችህ ከዛ ብዙ አማራጭ ያመጣ ከሱ ዉስጥ data and storage የሚለውን ትጫናላችሁ እዛ ዉስጥ authomatic media dawnload የሚል አለ ቀጥሎ ከሱ ታች when using mobile data የሚለውን ትጫናላችሁ እዛ ውስጥ
photos
voice message
videos
file
music
Gif
የሚሉትን ሁሉንም የራይት ምልክት(checkbox) ያለበትን ታጠፋላችሁ
ከዛ በኋለ በራሱ ግዜ ፎቶም ይሁን ሌሎችንም ዳውንሎድ አያደርግም
እንደተመቻችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ይህን ማረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ #Share አድርጉላቸው
ፔጁንም Like አድርጉ አስተያትም መጻፍ ይቻላል
👍17531👎2
ፈጠራ በተግባር!
ኢንኩቤተር የሚፈልግ ካለ በትዕዛዝ ከ50-2500 እንቁላል ማስፈልፈል የሚችል እንዳቅመዎ ከትንሽ እስከትልቁ ማዘዝ ይችላሉ። ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ። አድራሻ አማራ ክልል እንጅባራ ለበለጠ መረጃ በ0921513273 ይደውሉ።
👍43👏8🥰31
ንግድ ላይ ተሰማርተዋል?
E-Commerce ዌብሳይት በርግጠኝነት ያስፈልግዎታል!

በአሁኑ ሰአት ሁሉም ነገር አሰራራችን በሙሉ ዲጅታላይዝ እየሆነ መጥቷል።
መሸጥና መግዛት በኢንተርኔት አማካኝነት እየሆነ መጥቷል ለዚህም እርስዎ ማንኛውንም የሽያጭና የግዥ ስርአትዎን በ E-Commerce ዌብሳይት አማካኝነት መሸጥ መለወጥና በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ተደራሽ መሆን ይጠበቅብዎታል። እርስዎን በዲጅታል አለም ታዋቂ መሆን ይጠበቅብዎታል።
ስለሆነም
የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ
የኮንስትራክሽን እቃዎች
የድለላ ስራዎች
የሆቴሎች
ለመንግስትና ለግል ኮሌጆች
በተጨማሪም እርስዎ በሚያስፈልግዎ መስክ
በተመጣጣኝ ዋጋ ስለምንሰራ በታላቅ ደስታ ነው። እርሶም እራዎን ቀልጣፋና ዘመናዊ ያድርጉ!

ለማንኛውም ኮምፒውተራይዝድ ስራ እናማክራለን!

Muhammed Computer Technology(MCT)
ቴሌግራም አድራሽ @ma2323me
☎️ 0929273364
👍62🖕4🔥32😁2👏1
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)

2 የስክሪን መጠን (Screen Size)

3 ሲፒዩ(CPU)

4 ራም(RAM)

5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)

6 የምስል ጥራት (Image Quality)

7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)

8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡

1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡

2. የስክሪን መጠን ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር
ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡

3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Corei5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና
የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡

4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ
ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 8ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡

5. የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ (copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል
እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡

7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም
የሚቆዩ ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡

8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶች ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን
👍11310👏4👎2🥰1
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ንግድ ላይ ተሰማርተዋል? E-Commerce ዌብሳይት በርግጠኝነት ያስፈልግዎታል! በአሁኑ ሰአት ሁሉም ነገር አሰራራችን በሙሉ ዲጅታላይዝ እየሆነ መጥቷል። መሸጥና መግዛት በኢንተርኔት አማካኝነት እየሆነ መጥቷል ለዚህም እርስዎ ማንኛውንም የሽያጭና የግዥ ስርአትዎን በ E-Commerce ዌብሳይት አማካኝነት መሸጥ መለወጥና በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ተደራሽ መሆን ይጠበቅብዎታል። እርስዎን በዲጅታል አለም…»