Muhammed Computer Technology (MCT)
37.7K subscribers
528 photos
7 videos
254 files
913 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
Server(ሰርቨር) ምንድን ነው?
ሰርቨር ማለት በሁለት ይከፈላል እነሱም Hardware Server and Software Server በማለት።

ሰርቨር ማለት ከስሙ እንደምንረዳው አገልጋይ ማለት ሲሆን ለ Client Devices አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው። በዚህም የሶፍትዌር ሰርቨር የምንላቸው
ዌብ ሰርቨር፣ ዶሜን ኔም ሰርቨር፣ ሜይል ሰርቨር በጥቂቱ መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ስርቨር የሆኑ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጥቀስ ይቻላል ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ሰርቨር፣ ኡቡንቱ ጥቂቶች ናቸው።

Hardware Server የምንለው የኮምፒውተር አይነት ሲሆን መረጃን ለመያዝ የሚያገለግልና በክሊያንት ኮምፒውተሮች መረጃውን እንዲደርስና ዋና መረጃው የሚቀመጥበት ማለት ነው። ሰርቨር ኮምፒውተር በጣም በጣም ከፍተኛ የሆነ መረጃን የመያዝ አቅም ያለው፣ መረጃን ፕሮሰስ የማድረግ አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመስራት አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ በዋጋ፣ በአካላዊ ከመደበኛው ኮምፒውተር የሚተልቅ እቃ ነው።

በአንድ ሰርቨር ኮምፒውተር ለብዙ ክሊያንት ኮምፒውቲንግ እቃዎች(ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ ደስክቶፕ፣ ካሜራ፣ ፕሪንተር ወዘተ...) በአንድ ላይ ኔትወርክ በመጠቀም እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ መረጃውን እንዲጋሩ ያደርጋል።

Client Devices የምንለው ማንኛውም የኮምፒውቲንግ እቃዎች ከሰርቨሩ ጋር በመግናኘት መረጃዎችን አሳሾችን(Browsers) በመጠቀም መረጃን የምንጠቀምበት እቃዎችን ያካትታል ለምሳሌ አሁን የምንጠቀምበት ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል ስልክ ስልካችን ክሊያንት ዲቫይስ የሆነበት ምክንያት ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቱቭ ስንጠቀም መረጃውን ከሰርቨር ኮምፒውተር ላይ ኔትወርክ በመጠቀም የሚያመጣልንና ስለምንጠቀም ነው። በአጠቃላይ ሰርቨር ኮምፒውተር ማለት በጣም ብዙ መረጃዎችን አምቆ የያዘ ለተጠቃሚዎች በክሊያንት ኮምፒውተር አማካኝነት በመጠቀም መረጃን ከሰርቨር ኮምፒውተር በማምጣት ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ነው።

ክሊያንትና ሰርቨር ኮምፒውተር የሚገናኙበት ፕሮቶኮል TCP/IP ይባላል። TCP/IP በዋናነት መልእክቶች ከሰርቨር ኮምፒውተር ወደ ክሊያንት ኮምፒውተር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ ሲሆን በLAN Local Area Network ወይም በWAN Wide Area Network ክሊያንት ኮምፒውተሮችን ከሰርቨር ኮምፒውተሮች ጋር በማስተሳሰር መረጃን መለዋወጥ ያስችላል።
👍76❤15🔥3🥰3
ቫይረስ /Virus/  የኮምፒውተር ቫይረስ እራሱን ሌሎች ፋይሎች ላይ በማጣበቅ የሚያባዛ እና ተላላፊ ማልዌር ነው፡፡ ቫይረስ እራሱን ከተለያዩ ሶፍትዌሮች ጋር ባማጠባቅ እንደ ወርድ ዶኩሜንት ሊሆን ይችላል እኛ ፐሮገራሞቹን ስንከፍት እሱም አብሮ በመቀስቀስ የሚራባ ነው፡፡ በተጨማሪም ኔትዎርክ እና አንተርኔትንም ጨምሮ ማለት ነው፤ በፈላሽ ዲስክ፤ሜሞሪ ካርደ እና ሲዲዎችን በመጠቀም ይተላለፋል፡፡
ቫይረስ እንደሌሎቹ ማዌሮችን ኮምውተራችን በመበከል ኮምውተራችን ፍጥነቱን ይቀንሳል፤ ዳታ ያጠፋል ዋይንም ይሰርቃል፡፡ ከበድ ያሉ ቫይረሶች የክፒውተራችንን ሃረድዋር ጭምር ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ሃረድ ዲስክን በመጉዳት ኦፐሬቲንግ ሲይሰተማችን ክራሽ እነዲዲርግ ያደርጋሉ፡፡ 
⭕️ ወርም/Worm/ 
ወርሞች በአብዛኛው ተንሰራፍተው የሚገኙ ማዌሮች ናቸው፡፡ በኔትዎርክ አማካኝነት እራሳቸውን ችለው የኦፐሬቲንግ ሲይስተማችንን ድክመት በመጠቀም የሚባዙ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ኔትዎርክን በማጨናነቅ የእንተርኔት ፍጥነት ይቀንሳሉ ፤ የኮምፒውተራችን ፕሮሰሰር በአላስፋለጊ ትዛዞች በማጨናነቅ ኮምውተራችን ቀርፋፋ ያደርጋሉ፡፡
ከቫይረስ ጋር የሚለያቸው ወርሞች የሰዎችን ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው እራሳቸውን ማባዛት ከመቻላቸው በላይ በኢሜሎች አታች ተደርገው ወደ ኮምፒውተራችን ሊገብ ይችላሉ፡፡ ቫይረስ ግን ለመባዛት የግድ እኛ የተበከለውን ፍላሽ ዲስክ መክፈት ይንም የተበከለ ወርድ ፋይል መክፈት ይኖርብናል፡፡ 
በማልዌር የተጠቁ ኮምፒውተሮች የሚያሳያቸው ምልክቶች 
ማልዌሮች የሚያደርሱት ጉዳት እና ምልክት እንደ ማልዌሩ አይነት፤እንደ ኮምፒውተሩ አይነት እና እነደ ሚጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲሰይሰም ቢለያይም አብዛኛው ጊዜ ግን አንድ ኮምፒውተር በማልዌር ሲጠቃ ከስር የተገለጹትን ምልክቶች ያሳያል
⭕️ የኮምፒውተር ፍጥነት መቀነስ 
የኢንተረኔት ፍጥነት መቀነስ ( የኢንተርኔ ፍጥነት የቀነሰው ከ ኢንተርኔ አገልግሎት ከሰጠን አካል አለመሆኑን እረግጠኛ መሆን የኖርብናል) 
 â­•️ የዌብ ብራውሰራችን ማዝገም 
ከእኛ እውቅና ውጪ በተለያየ ስም የተፈጠሩ ፈይሎች ወይን የተደበቁ ፋይሎች 
⭕️ የማናውቀው አይኮን ዴስክቶፓችን ላይ ሲገኝ 
⭕️ ፕሮገራሞች ካለእኛ ትዛዝ ሲከፈቱ ወይንም ሲዘጉ 
⭕️ áŠĽáŠ› ያላክነው ኢሜይል ተልኮ ከሆነ 
⭕️ ፌስቡክ ላይ እኛ ፖስት ያላደረግነው እና ካልታወቀ ምንጭ በእኛ ስም ፖስት የሚደረግ ከሆነ 
⭕️ የዴስክቶፕ ከለር መዛባት 
⭕️ አንዳድ ፕሮገራሞች አልከፍት ማለት በተለይ ታስክ ማናጀር አልከፈት ካለ ኮምፒውተራችን በማልዌር ተጠቅቶ ሊሆን ሰለሚችል ከተች የተገለጹትን መፍትሄዎች መተግበር ያስፈልጋል
🛑 እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎች 
ማልዌሮች ኮምፒውተራችንን በመበከል አደጋ ከማድረሳቸው በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የሚፈጠረውን ችግር በከፍተኛ መልኩ መቀነስ ይቻላል፡፡ አንዴ ገብተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ ግን ወደኋላ መመለሾ በጣም አዳጋች ነው የሚሆነው ስለዚህ ቅድመ ጥንቃቅ ማድረገ የተሸለ አማራጭ ነው፡፡ 
🛑 ምንጊዜም አንቲቫይረስ መጠቀም 
🛑 የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶች ተአማኝነት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል 
🛑 በተቻለን መጠን አንቲቪረሳቻንን አፕቱዴት ማድረግ 
🛑 á‰€áˆ‹áˆ የሆኑ በነጻ ዶወንሎደ አድርገን የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶቸ 
1️⃣ McCaffe 
2️⃣ Avira 
3️⃣ Microsoft Security Essential 
4️⃣ Avast
🛑ዳውንሎድ የምናደርገው ሶፍትዌር በተለይ ቶረንት ፋይሎችን ከመክፈታችን በፊት ስካን ማድረግ ከማናውቀው አካል በኢሜላችን የሚላኩ የተላያዩ ዳውንሎድ ሊንኮችን ከመክፈት መቆጠብ ፤በተወሰነ ጊዜ ልዩነት ኮምፒውተራችንን ፉል ስካን ማድረግ፡፡
👍58❤6👏6👎1
አዲስ Smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ማገናዘብ የሚገባዎ 13 ነገሮች ከምሳሌ ጋር ~+
መግዛት ያሰቡት smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል።ማንኛውም smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ስልኩ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን 13 መመዘኛዎች ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
1~ ፕሮሰሰር(Processor)
ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821) ቢሆን ይመረጣል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።
2 ~ ካሜራ
ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 13mp(Megapixels) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 8mp በቂ ነው።
3 ~ ባትሪ
ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 3500mAh(Miliamp Hour) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh በቂ ነው።
4 ~ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች አሉ።ለምሳሌ samsung galaxy ስልኮች ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።
5 ~ Storage
ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ(microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።
6 ~ Headphone Jack
HeadPhone 3.5mm audio
jack ቢሆን ይመረጣል።
7 RAM ከተቻለ ከ4GB በላይ ቢሆን ጥሩ ነው ነገርግን ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB በቂ ነው
8 USB File transfer USB 2.0 በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆ ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው.
9 Physical Size በኢንች ለናንተ የሚቸውንም መምረጥ አለባችሁ በተለይ ለአያያዝ ምቹ መሆኑን አረጋግጡ።
10 የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።
11 Display: 6.5 inches በጣም ምርጥ ነው ለአያያዝ ምቹ ነው።
12 Resolution 1080 x 2400 pixels ቢሆን ይመከራል
13 Data 4G LTE ለመጠቀም ያመች ዘንድ 4G Support የሚያደርግ ቢሆን ይመረጣል

ምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
Camera : 8000 x 6000 pixels, 1920 x 1080 pixels, 30 fps
SIM card : Nano-SIM
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
USB: 2.0, Micro USB
Bluetooth: 5.0
Positioning: GPS, A-GPS, GLONASS, BeiDou
👍99👏4🔥3😁2❤1
ፌስቡክዎ መጠለፉን ለማወቅና ከጠለፋ እራስዎን ያውጡ!
1. Setting and Privacy ይግቡ
2. Setting ይንኩ
3. Security
4. Security and login
5. Where you are logged in ከዚህ ውስጥ በምን ሞባይል ወይም ኮምፒውተር፣ የት ቦታና ሀገር፣ በምን ብራውዘር፣ ወይም አፕልኬሽን፣ መቼ ቀን ከዚህ በፊት እንደከፈታችሁት ያሳያችኋል። ነገር ግን ደግሞ Active now በሚል በአረንጓዴ የተጻፈው አሁን የከፈታችሁበትን ይነግራችኋል። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Session ስትመለከቱ የናንተ ካልሆነና የሚያጠራጥር ከሆነ ከታች ላይ Logout All Sessions የሚለውን በመጫን Logout የሚለውን በመጫን እራስዎን ከጠላፋ ማውጣት ይኖርብዎታል።
የተጠለፈ መሆኑ ከተጠራጥሩ በፍጥነት Password መቀየር ይኖርብዎታል።
ከአምስተኛው ተራ ቁጥር በመቀጠል ካለው Step Where you are logged in በታች Login ከሚለው በታች Change password የሚለውን በመጫን current password እና New password በማስገባት Save Changes የሚለውን ይጫኑ።

✅ በተጨማሪም Two factor Authentication On ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ይህ On መሆኑ ምንም እንኳን የፊስቡክ አካውንትዎን Password ሰው ቢያውቅብዎ በስልካችሁ የሚላከውን Security code እስካላወቁ ድረስ መክፈትና መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ On በማድረግ እንድትጠቀሙ እመክራለሁ። በፈለጋችሁ ሰአት Off ማድረግ የምትችሁ ይሆናል!

እራስዎን ከጠላፊዎች ይከላከሉ!
👍83❤22🥰5🔥4
🔳 የአመራር ዘይቤዎች ወይም አቀራረቦች
🔶 መግቢያ
የአመራር ዘይቤዎች ፤ መሪዎች በተቋም ውስጥም ሆነ ከተቋም ውጭ ከሌሎች(ከተከታዮች) ጋር ያላቸውን ግንኙነት ፣ ራሳቸውን እና የሥራ መደባቸውን እንዲሁም እንደ መሪዎች ውጤታማ መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን የሚያዩባቸው አቀራረቦች ናቸው፡፡

በማንኛውም ሁኔታ እና ቦታ ሊያገለግል የሚችል ሁሉም ሰው የተስማማበት አንድ ወጥ የአመራር ዘይቤ
የለም፡፡ አንድ መሪ የተለያዩ የአመራር ዘይቤዎችን ለይቶ ማወቁ እንደ ሁኔታውና የአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ዘይቤውን በመቀያየር የተሻለ ውጤትና ስኬት ሊያስመዘግብ ይችላል፡፡
መሠረታዊ የአመራር ዘይቤዎች
1️⃣ አምባገነናዊ የአመራር ዘይቤ
2️⃣ ዲሞክራሲያዊ የአመራር ዘይቤ
3️⃣ ታገሽ / ጣልቃ የማይገባ / የአመራር ዘይቤ

1️⃣ አምባገነናዊ የአመራር ዘይቤ
🔶 በመመሪያ እና በቁጥጥር የተሞላ ነው፡፡
🔶 አብዛኛውን ውሳኔ የሚወስነው መሪው ነው፡፡
🔶 አምባገነናዊ መሪዎች ግልጽ መዋቅር እና የማይለወጡ ሚናዎች ያስቀምጣሉ፡፡
🔶 የተከታዮቻቸውን ሚና የሚወስኑት እና የሚያደራጁት መሪዎች ናቸው፡፡
🔶 መሪዎች ከተከታዮቻቸው ጋር ከመገናኘት ይልቅ በአስተዳደራዊ ጉዳዮች የተጠመዱ ናቸው፡፡
🔶 የ “ካሮት እና ዱላ " አቀራረብ ነው፡፡

✅ ጥቅሞቹ
🔶 ሁሉም ነገር በመሪዎች ቁጥጥር ሥር ስለሚሆን ፤ ጭንቀት ይቀንስላቸዋል፡፡
🔶 ተከታዮቻቸውን ስለማያማክሩ ውሴኔዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ይወስናሉ፡፡
🔶 ውሳኔዎች ቶሎ በመወሰናቸው ሠራተኞች ጊዜያዊ ደስታ ያገኛሉ፡፡

✅ ጉዳቶቹ
🔶 ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል የአመራር ዘይቤ አይደለም፡፡
🔶 መሪዎች ሲኖሩ ሠራተኞች ሥራቸውን ይሠራሉ ፤ መሪዎች በሥራ ቦታ ሳይኖሩ ሲቀሩ ፤ ሠራተኞች
ሥራቸውን በአግባቡ አያከናውኑም፡፡
🔶 በጊዜ ሂደት የሠራተኞችን ክህሎት ይገድላል ፣ የሠራተኞችን ሞራል ይጎዳል ፣ በመጨረሻም ሠራተኛው
በመሪው ላይ ብቻ ጥገኛ እንዲሆን ስለሚያደርገው ራሱን ችሎ ውሳኔዎችን እንዳይወስን ያደርገዋል፡፡

✅ መቼ ነው የምንጠቀመው?
🔶 ሠራተኞች በተቋሙ ላይ ከፍተኛ እምነት ሲኖራቸው፡፡
🔶 በተቋሙ ውስጥ የሚሠሩ ሥራዎች ቀጥተኛ ሲሆኑ፡፡
🔶 ውሳኔዎች በፍጥነት እንዲወሰኑ ሲፈለግ፡፡ ለምሳሌ ሀገር ሲወረር
🔶 ሥራውን መሪው እንዲመራው ኃላፊነት ሲሰጠው፡፡
🔶 ሠራተኞች ለሥራው አዲስ ሲሆኑ ፣ በቂ ሥልጠና ካላገኙ ፣ የሥራዎችን ቅደም ተከተል ካለወቁ እና
በአጠቃላይ ለሠራተኞች ግልፅ የሥራ መመሪያ ሲያስፈልግ፡፡

2️⃣ ዲሞክራሲያዊ ወይም አሳታፊ የአመራር ዘይቤ
🔶 መሪው ሥልጣኔ የሚረጋገጠው በምመራቸው ሰዎች ዘንድ ተቀባነት ሲኖረው ነው ብሎ ያምናል፡፡
🔶 የበለጠ አሳታፊ ሲሆን ፤ ፖሊሲዎች የሚወጡት በቡድን ውይይት እና በቡድን ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት
ነው፡፡
🔶 መሪዎች ለእርስ በርስ እና ከተከታዮቻቸው ጋር ላላቸው ግንኙነት ትኩረት ይሰጣሉ፡፡
🔶 መሪዎች ውሳኔዎች እና ውሳኔዎች ለሚያስከትሉት ኃላፊነት ከተከታዮቻቸው ጋር ይጋራሉ፡፡
🔶 የተለመደ እና ለረጅም ጊዜ ሊያገለግል የሚችል የአመራር ዘይቤ ነው፡፡

✅ ጥቅሞቹ
🔶 ውሳኔዎች በጋራ ስለሚወሰኑ ፤ ሠራተኞች በፈፁም መሰጠት ሥራቸውን ያከናውናሉ፡፡
🔶 በሠራተኛው ውስጥ የባለቤትነት ስሜት ይፈጠራል፡፡
🔶 መሪዎች ኖሩም አልኖሩም ሠራተኞች ሁል ጊዜ የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነተ በታማኝነት ይወጣሉ፡፡

✅ ጉዳቶቹ
🔶 ሁሉም ሰው በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ስለሚሳተፍ ፤ ውሳኔዎች ይዘገያሉ፡፡
🔶 ሁሉንም ሰው በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ማሳተፉ መልካም ነገር ቢሆንም ፤ ለእያንዳንዱ ጉዳይ
ሠራተኞችን ለውሳኔ መሰብሰብ ፤ በጊዜ ሂደት ማለቂያ ወደሌላቸው ስብሰባዎች ሊያመራ ስለሚችል፤
ሠራተኞች ሊሰላቹ ይችላሉ፡፡

✅ መቼ ነው የምንጠቀመው?
🔶 ሠራተኞች በቂ የሥራ ዕውቀት ፤ ክህሎት እና ልምድ ሲኖራቸው፡፡
🔶 ሁሉም የቋሙ አባላት በእኩል ወይም ተቀራራቢ መጠን የራሳቸውን ፈጠራ እና ዕውቀት ለተቋሙ
የሥራ እንቅስቃሴ ማበርከት ሲችሉ፡፡
🔶 ለውጦችን ተቋማዊ ለማድረግ ፣ የቡድን ችግሮችን ለመፍታት እና መሪዎች ለአንድ ጉዳይ ግልፅ
አቅጣጫ ለማስቀመጥ ተጨማሪ ግብዓቶች ሲያስፈልጓቸው፡፡

3️⃣. ታጋሽ / ጣልቃ የማይገባ / የአመራር ዘይቤ
🔶 አንዳንድ ጊዜ “አትንካ ዘይቤ " በመባል ይታወቃል፡፡
🔶 አብዛኞቹን ውሳኔዎች ለሠራተኞች በመስጠት ለውሳኔዎቹ ሠራተኞችን ተጠያቂ የሚያደርግ እና
በመሪው ዝቅተኛ ክትትል የሚደረግበት የአመራር ዘይቤ ነው፡፡
🔶 ሠራተኞች ራሳቸውን በማነሳሳት ለአብዛኞቹ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ኃላፊነት ይወስዳሉ፡፡
🔶 ይህ የአመራር ዘይቤ ጠቃሚ የሚሆነው ሠራተኞች የተማሩ ፣ ስለ ሥራቸው በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ
ሲኖራቸው ፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው ሲሆኑና የራስ ተነሳሽነት ሲኖራቸው ነው፡፡
🔶 መሪዎች ለሥራ ውጤትም ሆነ ሥራውን ለሚሠሩት ሠራተኞች ደንታ የላቸውም፡፡

ምርጥ የአመራር የቴሌግራም ቻናል!
Vision Leadership Development Firm

Our Core Services:
1. Short - Term Trainings( 3 to 10 days)
2. Research and Development
3. Personal Development
4. Developing and Maintaining High-Performing Team
5. Organizational Leadership Issues

Dream, Believe, Achieve!

Mobile:- +251940145151

👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership
👍70🤔3👏1😁1
የተለያዩ መፅሐፍትን በpdf አዲስና ቆየት ያሉ መፅሐፍትን

📗ከልቦለድ እስከ ኢልቦለድ :

📔ከፍልስፍና እስከ ሳይኮሎጂ

📕ከግለታሪክ እስከ ታሪክ:

📓ከግጥሞች እስኪ ወጎች

📚ከሰባተኛ እስከ 12 ያሉ የተማሪዎች መማሪያ መፅሐፍት(STB) እና የመምህራን(TG)
መፅሐፍን ሚያገኙበት ሁሉንም አሟልቶ የያዘ ባይነቱ ለየት ያለ ዘመናዊ #የPDF ላይብረሪ ነው!
•እንኛ ጋር #ከ1900 በላይ PDF መፅሐፍቶች አሉን የሌለን የለም:: መተው ይጎብኙን 100% ይደሰቱበታል!
(ብሔረ መፃሕፍት ዘ-ኢትዮጵያ📚)
@ETHIO_PDF_BOOKS
@ETHIO_PDF_BOOKS
@ETHIO_PDF_BOOKS
👍33❤14🥰3😁2👎1👏1
መሪ የተከታዮችን አስተሳሳብና ባህርይ ወይም ተግባር በተቀመጠው ራይዕ መሰረት ይቃኛል ወይም እንዲቃኝ ያደርጋል፡፡
ምርጥ የአመራር የቴሌግራም ቻናል!

Mobile:- +251940145151
ማለም ፥ ማመን ፥ ማሳካት !

👇👇👇Join ይግቡ👇👇👇
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership
👍18
አንድ ዌብሳይት ጥሩ ነው የምንለው ምን ምን ሲያካትት ነው?

ድርጅቶት ወይም የግል ዌብሳይቶ መኖሩ ብቻ ብዙ ላይጠቅም ይችላል። የዲጂታል መገኛዎ ውበት ከቢሮው ውበት እኩል ሊያስጨንቆት ይገባል። ይህንን ስንል አሁን ያለው የድርጅቶ ዌብሳይት (ወደፊት የሚያሰሩት) ጥሩ ነው ለመባል ቢያንስ በእነዚህ መመዘኛዎች ተፈትኖ ማለፍ አለበት።

1. ምክንያታዊነት

ዌብሳይቱ ለምንድነው ያስፈለገው? አላማው ምንድነው? ማን ይመለከትልኛል? ምን መግለጽ አለበት? የሚሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ አለበት። ይህ ካልሆነ በተመልካቹ ዘንድ ቅሬታ ይፈጥራል ለፍተውና ገንዘቦትን አውጥተው ያሰሩት ድረ ገጾ የሚፈለገውን ጥቅም ሳያስገኝ ይቀራል።

2. ለአጠቃቀም ቀላል

ዌብሳይቶ ለአጠቃቀም ቀላል መሆን ይጠበቅበታል። ደንበኛዎ የሚፈልገውን ነገር ሳይጨናነቅ፤ ሳይጉላላ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ተደርጎ መሰራት ይኖርበታል። ለአጠቃቀም ቀላል ዌብሳይት ማሰራት ጥሩ ባለሞያ የሚፈልግና ዋነኛ መመዘኛ ነው።

3. ይዘት

ዌብሳይቶ ምን መረጃ ይዟል? ስለድርጅቴ በአግባቡ ገልጾልኛል ወይ? ደንበኞቼ ስለ አገልግሎቴ በቀላሉ መረዳት ይችላሉ? የሚሉት ነገሮች መታሰብ ይኖርባቸዋል። የዲጂታል ይዘቶች እንደ ወረቀት ይዘቶች በጹሑፍ ብቻ ሳይሆን በግራፊክስ፤ በምስል፤ በኢንፎግራፊክስ የሚቀመጡ ጭምር ናቸው ይህም ተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲረዱ ያስችላቸዋል።

4. ፍጥነት

ዌብሳይቶ ሲዘገይ ከኔትወርክ ችግር ብቻ ከመሰሎት ተሳስተዋል። የተሰራበት ጥራትና የተጠቀማቸው የኮዲንግ መንገዶች ለዌብሳይቱ ፍጥነት እጅግ ወሳኝ ናቸው። ስለዚህ ሥራዎትን በጥሩ ባለሞያ ካሰሩ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

5. ተግባቦት

የተሰራው ዌብሳይት በኮምፒውተር ሲመለከቱት እንዲሁም በስልክና በታብሌት ሲመለከቱት በሦስቱም ላይ እንደቅርጻቸው ተግባብቶ ካልሰራ ዌብሳይቶ ጥሩ አልተሰራም ማለት ነው። በመሆኑም የድርጅቶ ዌብሳይት ከኮምፒውተር እንዲሁም ከስልክና ከታብሌት ተግባቢ መሆኑንን ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል።

6. በቀላሉ መገኘት (SEO)

ሰዎች በተለያዩ መንገድ አገልግሎት ሲፈልጉ የእርሶን ዌብሳይት በቀላሉ ማግኘት መቻል ይጠበቅባቸዋል። ለዚህ የሚያግዙ ቴክኒካል ጉዳዮች በአግባቡ መሰራት ይጠበቅበታል። ጥራት ያለው ዌብሳይት እንዳሎት ይህንንም ማረጋገጥ ይኖርቦታል።

7. ልዩ እና የሚታወስ

በጣም ስኬታማ የተባሉ ዌብሳይቶች ከሌሎች ልዩ የሚያደርጋቸውን ባህሪይ የያዙ ናቸው። የእርሶን ዌብሳይት ልዩ ለማድረግ በርካታ መንገዶችን መጠቀም ይችላሉ ለምሳሌ የዲዛይን ጥራት፣ ጥሩ ይዘት፣ ደረጃውን የጠበቀ ግራፊክስ፣ መረጃዎችና ጠቃሚ መሳሪያዎችን ማንሳት ይቻላል። የደንበኛዎትን ቀልብ ገዝተው መያዝ ከፈለጉ ዌብሳይቶ ሰዎች እነዲጎበኙት በቂ ምክንያት እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠበቅቦታል።

8. ደኅንነቱ የተጠበቀ

በዚህ ዘመን የቢሮዎት ደኅንነት ብቻ ሳይሆን በበይነ መረብ ተጠቅመው የሚያካሂዱት እንቅስቃሴዎችም ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆን ይጠበቅበታል። ለደንበኛዎም ሆነ የእርሶ ደኅንነት እንዲሁም መረጃ የሚያስጠብቅ ጥብቅ ድረገጽ ሊኖሮት ያሻል።

ለግል፣ ለመንግሥት ድርጅቶች ዌብሳይቶችን ማሰራት ለምትፈልጉ በቅናሽ ያሰሩ ዌብሳይቱን!
በ 📱📱📱 #0929273364 ይደውሉ! ወይም በቴሌግራም ( @ma100me) ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
👍44❤5👎2👏1
ምርጥ ላፕቶፕ ይግዙ!
Hp envy

Intel core i5

Generation-6th

Storage-1000gb +128gb ssd

Ram-8gb
nvych 15.6 fhd resolution

Graphics-nvidia GTX 4gb dedicated

With one year warranty

📞 0923479869
👍52🤔4❤1
Truecaller-Pro-v9.14.7_@ApkPlex.apk
22.5 MB
🕹 TrueCaller Pro v9.14.7

ℹ️ Category: #Utility ✏
🚫 Hack:
Premium Unlocked 🔐
👥 Feedback: 7.916.749 🌟4.5 🌟
💸 Price: Free‼️

#share
#አዲስ ቁጥር ሲደወልላችሁ የቁጥሩን ባለቤት የሚነግራችሁ አፕ እንዴት ይሰራል???
#True_caller android app
የሚሰራበት ሃሳብ በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ነው።

✅አፑን መጀመሪያ ስትጭኑት የሚጠይቃችሁ ዋናው ከስልካችሁ የሚፈልገው ፈቃድ phone book or contact list ለማንበብ ነው ልክ ፈቃድዱን ሥትሰጡት ስልካችሁ ላይ ያለውን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ ከነ ስማቸው ወደራሱ central database server (ማእከላዊ መረጃ ማጠርቀሚያ ሰርቨር) በመላክ ይመዘግበዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ይህን አፕ በጫኑት ቁጥር ስልካቸው ላይ ያሉትን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ ወደ መረጃ ማጠራቀሚያው ይልከዋል።
ከዛ አዲስ ቁጥር ሲደወልላችሁ ወዲያውኑ ስልክ ቁጥሩን ከራሱ database ይፈልገዋል እና ያለውን መረጃ ያመጣላችኋል።

አስራሩ ባጨሩ ሲገለጽ: ሰጥቶ መቀበል እንደማለት ነው ። እናንተ ስልካችሁ ላይ ያሉትን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ እንዲወስድ ትፈቅዱለታላችሁ እሱ ደሞ የማታውቁት ስልክ ሲደወልላችሁ የስልኩ ባለቤት ማን እንደሆነ ይነግራችኋል።

✅ሌላኛው መንገድ Facebook ን በመጠቀም ነው አፑ ሌላ የsignup (መመዝገቢያ መንገድ አለው) ይህም በፌስቡክ signup ማድረግ ነው። በፌስቡክ login ስትሉ የፌአቡክ አካውንታችሁን መረጃ የማንበብ አቅም አለው ይህም የፌስቡክ ጓደኞቻችሁን እንዲያነብ ፈቃድ ይኖረዋል አልዚህ በተመሳሳይ መንገድ የጓደኞቻችሁን ስልክ፣ ፎቶ ስም እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን መሰብሰብ ይችላል።
👍112🥰6❤2
Google Drive: ፋይሎችን ለመፍጠር, ለማጋራት እና መረጃን በአንድ ቦታ በማስቀመጥ በፈለግነው በየትኛውም ቦታ ሁነን መረጃውን እንድንጠቀም የሚያግዘን ነው።

Google Drive ተጠቃሚዎች በመስመር ላይ(online) ፋይሎችን እንዲያከማቹ እና እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችል በደመና ላይ የተመሰረተ (Cloud based) የማከማቻ አገልግሎት ነው። Google Drive  áŠ áŒˆáˆáŒáˆŽá‰ľ የጀመረው April 24, 2012 G.C ሲሆን ጥቅሙ ተጠቃሚዎች መረጃን Cloud ላይ እንዲያስቀምጡ ይረዳል።

Google Drive ለተጠቃሚዎች እስከ 15 GB á‰ áŠáŒť መረጃ ማስቀመጥ የሚያስችል ሲሆን . Google One ባለ 100 GB, 200 GB, 2 TB በተፈለገው አማራጭ በክፍያ መረጃን እንድናስቀምጥ አገልግሎቱ ክፍት ነው.

አገልግሎቱ የተጻፉ ሰነዶችን፣ ፎቶዎችን እና ሌሎችንም በሁሉም የተጠቃሚ መሳሪያዎች፣ በሞባይል ፣ ታብሌቶች እና ፒሲዎችን ጨምሮ ኢንተርኔትን በመጠቀም አገልግሎቱን መጠቀም ያስችላል።

Google Drive ከኩባንያው ሌሎች አገልግሎቶች እና ስርዓቶች ጋር Integrated የሆነ ሲሆን Google Docs፣ Gmail፣ Android፣  Chrome áŁ YouTube፣ Google Analytics  áŠĽáŠ“ Google+ን ጨምሮ።
ጎግል ድራይቭ እንደ ማይክሮሶፍት OneDrive፣ Apple iCloud፣ Box፣ Dropbox እና SugarSync ተመሳሳይ አገልግሎት ይሰጣል።

Google Drive እንዴት እንደሚሰራ

በGoogle Drive ለመጀመር ተጠቃሚው ወደ ጎግል አካውንት መፍጠር ወይም ወደ ጎግል አካውንት መግባት አለበት። áŠ¨á‹šá‹Ťáˆ ተጠቃሚው "drive.google.com" የሚለውን ከBrowser URL ላይ ይጽፋል ወይም ሊንኩን ይነካል ወይም Drive የሚል አፕ ስልካችን ላይ በመፈለግ መክፈት ይቻላል። ከዛም ሲከፈት "My Drive" የሚል ይመጣል። በዚህም ውስጥ ፎልደሮችን፣ መጽሀፎችን፣ ፎቶዎችን...... መጫን እንችላለን።
👍74❤8👏6👎3
የlaptop ኮምፒዩተሮች CPU ሲያሜ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡
ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ እናወዳድራለን፡፡ ከዛሬ በኃላ ግን በትክክለኛው ስያሜ እንገመግማለን፡፡

❖በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?
እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡

🖱የኮምፒዩተሮቻችን CPU ስም እነዚህም ፊደላት ከያዘ፡

“K” – Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር የሚደረግ CPU ናቸው፡፡
ለምሳሌ Core i7-6700k እና Core i7-5820k ባሉ የሞዴል ቁጥር መጨረሻ ላይ unlocked(ያልተቆለፈ) ስለሆሀን Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) የተሠሩ ናቸው ፡፡ ይህ ማለት Unloc Processors ከፋብሪካ ዋና ፍጥነቶች በበለጠ ፍጥነት ከመጠን በላይ ሊጫኑ ይችላሉ ፡፡ የተቆለፉ ማቀነባበሪያዎች (Processors) ከመጠን በላይ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) አይችሉም።
ስለዚህ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ አምብዛም ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-8600K

“H” – High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው CPU ናቸው።

“Q” – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል CPU ናቸው፡፡

🖱በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች ወስጥ አንዱ ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i7-7700HQ

”M” – Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) የደረጋል፡፡

“Y” - Extremely low Power

“U” – Ultra low Power

ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-7200U
👍88🔥3👎1🥰1
🔷 CTRL and ALT keys, press UP ARROW , መደበኛ(ትክክለኛ) የስክሪን እይታ

🔷 CTRL + ALT + DOWN ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደታች ይገለበጣል

🔷 CTRL + ALT + LEFT ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደ ግራ ይገለጣል.

🔷 CTRL + ALT + RIGHT ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደ ቀኝ ይገለበጣል
ሞክሩት ከዚህ በፊት ስክሪኑ ተገልብጦባችሁ ደንግጣችሁ ከነበር በዚህ መንገድ መቀያየር ትችላላችሁ።
👍66❤10🔥5
Firewall ምንድን ነው? ጥቅሙስ?

ኮምፒውተርዎ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉ
ባጭሩ የኮምፕዩተር ቫይረስ ማለት ልክ እንደ ማንኛውም ፕሮግራም ሆኖ ግን አላማውና አሰራሩ ሌላ ኮምፕዩተር ለመበከል ነው።

ማንኛውም የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለቫይረስ ኢላማ ነው። የኮምፕዩተር ቫይረስ በግለሰብ፣ በድርጂቶች፣ በመንግስቶች፣ በነጋዴወች ወዘተ ይሰራል።

የሌላውን አበላሽተው ለመደሰትም ቫይረስ የሚሰሩ ግለሰቦች አሉ። የዚህንም ያህል የታመሙ ሰወች አሉ። ሁሉም የየራሱ አላማ አለው። የኮምፕዩተር ቫይረስ ውስብስብ ግን መጠኑ ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር ሲነጻጻር በጣም ትንሽ ነው። ብዛቱ ሳይሆን ክብደቱና ይዘቱ ትንሽ ሆኖ ግን አደገኛ ነው።

አንቲ ቫይረስ፤ አንቲ ቫይረስ የተሰራው የኮምፕዩተር ቫይረስን ለመከላከል ነው። አሁን ከቅርብ አመታት ወዲህ እራሱ ዊንዶውስ አንቲ ቫይረስ(Windows Defender) በነጻ ለተጠቃሚው ይሰጣል። ሆኖም ግን ሌሎችም የሚሸጡ ነጋዴወች አሉ። ተጠቃሚው እራሱ የትኛውን አንቲ ቫይረስ መግዛት እንደሚፈልግ ይወስናል ማለት ነው። እንደጥራቱ ይለያያል።

የነጻ አንቲ ቫይረሶችም አሉ። በሰፊውና ባይነቱ ለመከላከል ግን የሚገዛው ይሻላል። ለማንኛውም ዊንዶውስ በየጊዜው ስለሚጠቃ አንቲ ቫይረስም ቢሆን ሁሉንም ጥቃት አይከላከልም። አንቲቫይረስ እየሰሩ የሚሸጡ ነጋዴወችም እራሳቸው ቫይረስ ይሰራሉ እየተባለ ይታማሉ።

ፋየርዎል ያልተፈቀደ የኮምፒዩተር ኔትወርክን በመጠቀም ከኮምፒውተር የሚገባንና የሚወጣን ያልተፈቀደ ግንኙነትን ለመከላከል የተነደፈ የደህንነት ስርዓት ነው።
 
ፋየርዎል ከኮምፒዩተር በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባውን እና የሚወጣውን የኔትወርክ ትራፊክ ይቆጣጠራል። 

ፋየርወል በእንግሊዘኛው እሳት የሚከላከል ግድግዳ እንደማለት ነው። ፋየርወል ከውጭ ወደ ኮምፒውተራችን በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባን ቫይረስ መሰል የመረጃ በካይ፣ አጥፊ፣ ሰራቂ፣ ሰላይ ፕሮግራሞች እንዳይገቡ በመጠኑም ቢሆን የሚከላከል ሲሆን በጣም ጠቃሚና ለመረጃ ደህንነት አስፈላጊ የኮምፒውተር ማስተካከያ ነው።

ስለዚህ ኮምፒውተታችንን ከኢንተርኔት ጋር የምናገናኝ ከሆነ የኮምፒውተራችንን Firewall on ማድረግ ይጠበቅብናል ማለት ነው። ስለዚህ ለኮምፕዩተርም መከላከያ የሚሆን ፋየርወል አለ።

ለምሳሌ፣ የእርስዎ የግል ኮምፒውተር ፋየርዎል áŠ¨áˆŒáˆˆá‹ ወይም ፋየርውሉ ዝግ(Off) ከሆነ ቫይረሶች፣ ማልዌር እና ሰርጎ ገቦች(ሀከር) ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ።

ሁለት አይነት ፋየርወሎች አሉ። አንደኛው ከኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ጋር አብሮ እዛው ተጠቃሚው ያገኘዋል። (መጨረሻ ላይ ያለውን Step ይከተሉ) ለምሳሌ የዊንዶውስ ኮንትሮል ፓነል ላይ ሄዶ ፋየርወሉን እንደ አስፈላጊነቱ (ከፍተኛ ወይም መካከለኛ) መጠን ላይ መርጦ መቀስቀስ ይቻላል። የሚገዙ አንቲቫይረስ ፕሮግራሞችም የራሳቸው ፋየርወል አላቸው። ሌሎችም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ፋየርወል አላቸው።

የኮምፒውተታችንን ፈየርወል ለማስተካከል ቅደም ተከተል Windows 10, 8, 7: ላይ Control Panel > System and Security > Windows Firewall > Turn Windows Firewall on or off
✅ the bubble next to Turn off Windows Firewall (not recommended) and then select OK.
✅To disable the firewall for private and public networks, select Turn off Windows Firewall (not recommended) in both sections.
👍60🔥6❤2👏2😁2
በቅናሽ ኮምፒውተር ይፈልጋሉ?
Hp elitebook
core i5
6th generation
Storage 1000gb
Ram-8gb
Inch-14
Price 26,500
📞 0923479869

በቅናሽ ኮምፒውተር ይፈልጋሉ?
ZAN የኮምፒውተር የሽያጭ ማእከል
👍👍👍በቅናሽ የሚያገኑበት
🔶 ኦሪጅናል ላፕቶፕ ኮምፒውተር
🔶 ኦሪጅናል ዴስክቶፕ ኮምፒውተር
🔶 ኦሪጅናል ባትሪ
🔶 ኦሪጅናል ቻርጀር
የፈለጉትን በአዲስና በመጠኑ ያገለገሉ እቃዎችን በቅናሽ ዋጋ ማግኘት ይችላሉ!
አድራሻ:- አዲስ አበባ, መገናኛ, ዘፍመሽ ፕላዛ, 3ኛ ፎቅ, 322 ቁጥር
ይደውሉ! Mobile #0923479869
በቴሌግራም ቻናላችን በመግባት እቃዎቻችንን ማግኘት ይችላሉ!.
👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/zanlaptop
https://t.me/zanlaptop
https://t.me/zanlaptop
👍17❤1
Delete Format የተደረገ ሜሞሪ፣ ፍላሽ፣ ኮምፒውተር ሀርድዲሰክ ፋይል እንዴት መመለስ እንችላልን HOW TO RECOVER DELRTED DATA Amharic👇👇👇

https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
👍30🥰5👏4👎1
የሜሞሪ ስቶሬጅ መለኪያ ከትንሽ
ወደ ትልቅ መጠን በቅደም ተከተል!
8 ቢትስ ↔1 ባይት
1024 ባይት 1 ኪሎ ባይት
1024 ኪሎ ባይት↔ 1ሜጋ ባይት
1024 ሜጋ ባይት 1 ጊጋ ባይት
1024 ጊጋ ባይት↪1 ቴራ ባይት
1024 ቴራ ባይት 1 ፔታ ባይት
1024 ፔታ ባይት↔ 1 ኤክዛ ባይት
1024 ኤክዛ ባይት↪1 ዜታ ባይት
1024 ዜታ ባይት 1 ዮታ ባይት
1024 ዮታ ባይት↪1 ቦርኖቶ ባይት
1024 ቦርኖቶ ባይት 1 ጂኦፕ ባይት
ጂኦፕ ባይት ትልቁ የሜሞሪ ስቶሬጅ መመዘኛ ነው
👍59👏11❤10
#የድረገጽ_ጥቆማ

በነፃ የቢዝነስ ኮርሶችን መውሰድ ትፈልጋላችሁ❔

አዎ ከሆነ መልሳችሁ፤ እንደሚከተለው ይቀርባል...

🌐 ዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ድረገጽ፤ በነፃ የቢዝነስ ኮርሶች የምታገኙበትን ነው፡፡ አለም አቀፍ የንግድ ሴንተር (International Trade Centre)፤ በንግድ ስራ ዙሪያ የተለያዩ ኮርሶችን በኢንተርኔት በነፃ ይሰጣል፡፡ ድርጅቱ አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶችን ለመደገፍ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ ኮርሶችም የሚያተኩሩት:-

- በኤክስፖርት ቢዝነስ ላይ

- በስራ ፈጠራ (ኢንተርፕረነርሺፕ) ላይ

- ዲጂታል ማርኬቲንግ እና የመሳሰሉት ከንግድ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

🌐 ኮርሶቹ በአብዛኛው ከሁለት እሰከ አራት ሳምንት (በሳምንት 2 ሰአታት) የሚወስዱ ናቸው።

🌐 ለመመዝገብም የሚያስፈልግን የራሳችን የኢ-ሜል አድራሻ ሲሆን ትምህርቱም ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት የሚሰጥ ነው፡፡

🌐 በዚህ ድረገጽ ላይ የሚገኙ ኮርሶች አብዛኛዎቹ ለንግድ ስራ የሚሆኑ ስለሆነ የራሳችንን ቢዝነስ ለመክፈት የምንፈልግ ከሆነ፣ የቢዝነስ ድርጅቶች ውስጥ የምንሰራ ወይም የቢዝነስ ትምህርት የምንማር ከሆነ በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡

🌐 ድረገጽ ላይ የሚሰጡትን ኮርሶች ለመውሰድ የሚያስፈልገን ነገሮች:-

1. ድረገጹ ላይ ለመመዝገብ የራሳችን የኢሜል አድራሻ ማዘጋጀት እና

2. ከተመዘገብን በኋላ የምንፈልገውን ኮርስ ከድረገጹ ላይ መርጠን፤ መመዝገብ እና መማር፡፡

🌐 ኮርሶቹን በራሳችን ፍጥነት እዛው ኢንተርኔት ላይ ማንበብ እና መማር እንችላለን፡፡ ኮርሱን ከጨረስን በኋላ መማራችንን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከድረገጹ ላይ ማውረድ እንችላለን። ከታች ሊንኩን በመንካት ድረገጹን ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

https://learning.intracen.org

ምንጭ:- Wede Sera ወደ ስራ
👍64❤12🔥9
👉 ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።

👉ኮምፒውተራችንን ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ እንዳይቀበል አድርገን እንዴት መቆለፍ እንችላለን።

1⃣ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት this pc ወይም my computer ላይ Right Click እናደርጋለን።
2⃣ ከዛም ከሚመጡልን ምርጫዎች ውስጥ Manage የሚለውን እንመርጣለን።
3⃣ ቀጥሎም Device Manager
4⃣ ከዛም በቀኝ በኩል ካሉት ምርጫዎች Universal Serial Bus Controllers ከሚለው ስር ያለውን drop down arow ወይም የዝርዝር ቀስቱን እንነካለን።
5⃣ ከዛም extensible host controller ላይ ራይት ክሊክ እናደርጋለን ።
6⃣ ከተዘረዘሩት ዉስጥ Disable ክሊክ እናደርጋልን አለቀ👍👍👍
🔴 ወደነበረበት ለመመለስ Enable Device የሚለውን ይጫኑ!

👍አሁን ላፕቶፓችን ወይም ዴስክ ቶፕ ኮንፒተራችን ፍላሽ፣ሃርድዲስክ እንዳያነብ ብሎክ ሁኖል ማለት ነው።
👍83❤5🙏5👏1