Muhammed Computer Technology (MCT)
37.6K subscribers
528 photos
7 videos
254 files
913 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
በኮምፒውተራችን ላየሆኑ hidden የሆኑ ፉይሎች ለማግኘት እንዳስቀመጥናቸው እርግጠኛ የሆናቸው
(ከላይ ያለውን ምስሉን ይመልከቱ!)
ፋይሎችእና ፎልደሮች ተደብቀው ነገር ግን ከእይታችን ሊሰወሩ ይችላሉ፡፡ ይህ በሚያጋጥመን ጊዜ ኮምፒውተራችን እንዲያሳየን የሚደርገውን ቅንብር በማስተካከል እንድንመለከት ያስችለናል ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቅደም ተከተል የተቀመጡትንመንገዶች በመከተል የኮምፒውተርዎን ቅንብር ያስተካክሉ፡ –
1. Start የሚለው ምልክት በመጀመርሪያ እንመርጣለን
2 በመቀጠል ኮንትሮል ፓናል (control panel)
3. ከሚቀርቡለን ምርጫ ውስጥ Appearance and
Personalizationየሚለው ላይ ክሊክ እናደርጋለን
4. ቪው (view) የሚለውን እንጫናለን ከዚያ አድቫንስድ
ሴቲንግ (advancing setting) እናገኛለን
5. በመጨረሻም Show hidden files, folders, anddrives ክሊክ ካደረግን በኋላ ok የሚለውን መርጠን እናጠናቅቃለን፡፡
ሌላ አማርጭ
አንዳንድ ጊዜ በፍላሽ ዲስክ የያዝነው መረጃ ይደበቅብናል። ከተደበቀበት ሁሉንም ፎልደሮችና ፋይሎችን ለማውጣት ስንፈልግ ከይ በጠቀስኩት አግባብ ለምሳሌ ፍላሽ ዲስካችን Removable Disk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን እንጫንና attrib -s -h /s /d ብለን እንጽግና ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ሁሉም የተደበቀው ፋይል ሁሉ ይወጣልናል ማለት ነው። ሞክሩትና እዩት!

ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም #Subscribe በማድረህ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
👍5
አፕል የረቀቁ የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችን አስተዋወቀ

ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል ከዚህ ቀደም ከነበሩት የላቁ ናቸው የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችንና አዲስ አይፓድ አስተዋወቀ።

በዚህም አፕል አራት ስልኮችን ያስተዋወቀ ሲሆን እነሱም አይፎን 13 ሚኒ፣ አይፎን 13፣ አይፎን 13 ፕሮ እና አይፎን 13 ፕሮ ማክስ የተባሉ ናቸው።

አይፎን 13 ፕሮ እና አይፎን 13 ፕሮ ማክስ ከጀርባቸው ሦስት ካሜራዎች ተገጥመውላቸዋል። አፕል ካሜራዎቹ "እጅጉን የረቀቁ የካሜራ ሥርዓት ናቸው"

13 ስልኮች ከተለመዱት በተጨማሪ በሮዝ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለማት አሸብረቀው መጥተዋል።

አዳዲሶቹ አይፎኖች ሚሞሪ መጠንም ወደ 500 ጊጋ ባይት ከፍ ብሏል። በአይፎን-12 ምርቶች ውስጥ ዝቀተኛ ሚሞሪ 64 ጊጋ ባይነት ነበር። አይፎን-13 ግን ዝቅተኛ የመያዝ አቅሙ ወደ 128 ጊጋ ባይት ከፍ እንዲል ሆኗል።

አፕል ብዙ ደክሞ የተለያየ 'ፊቸር' ያላቸውን ስልኮች ይፋ ከሚያደርግባቸው ምክንያቶች መካከል ዋነኛው የቀደመውን አይፎን ስልክ የያዙ ደንበኞቹ በአዳዲስ ሞዴሎች እንዲተኳቸው ለማበረታታት እንደሆነ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ የኢንቨስትመንት ተቋሙ ዌብቡሽ እንደሚለው በመላው ዓለም የሚገኙ የአፕል ምርት የሆኑ ስልኮችን የያዙ 250 ሚሊዮን ሰዎች ባለፉት 3.5 ዓመታት ስልካቸውን በአዲስ አይፎን ሞዴል አልቀየሩም።
ዋጋ

አይፎን 13 ሚኒ ከ938 ዶላር ጀምሮ፣ አይፎን 13 ከ1076 ዶላር ጀምሮ፣ አይፎን 13 ፕሮ ከ1312 ዶላር ጀምሮ እንዲሁም አይፎን 13 ፕሮ ማክስ 1450 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ለገበያ ቀርበዋል።

እያንዳንዱ አይፎን 13 ስልክ እንደ ሚሞሪ መጠኑ ዋጋው ይለያያል።

አፕል ዎች 7 እና አይፓድ

አፕል ከስልክ በተጨማሪ ተሻሽሎ የቀረበውን አዲሱን አፕል ዎች አስተዋውቋል።

አዲሱ አፕል ዎች 7 የገዘፈ ስክሪኑ ላይ ኪቦርድ ተግጥሞለታል። አቧራ መቋቋም ይችላልም ተብሏል።

የአፕል ኩባንያ አለቃ ቲም ኩክ አዲሶቹን የአፕል አይፓዶች ሲያስተዋውቁ፤ የአይፓድ ሽያጫቸው ባለፈው ዓመት 40 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።

በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት ለማስተማር መገደዳቸው የአይፓድ ተፈላጊነትን ጨምሮታል።

አዲሶቹ አይፓዶች ከዚህ ቀደም ከነበሩት የአፕል አይፓዶች 20 በመቶ የፈጠኑ ይሆናሉ ብለዋል።

የአፕል አይፓዶች ከ329 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ለገበያ ቀርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በርካታ ስማርት ስልኮችን ለገበያ በማቅረብ የደቡብ ኮሪያው ሳምንስንግ መሪነቱን እንደያዛ ነው። አፕል ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዟል።

የቻይና ኩባንያ የሚያመርታቸው ዢዮሚ ስልኮች በገበያ ደርሻ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ኦፖ እና ቪቮ የተሰኙት ስልኮች ደግሞ አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ብሏል

አፕል ያስተዋወቃቸው አዲሶቹ አይፎን 13 ስልኮች ይዘው ከመጡት ገጽታዎች [ፊቸሮች] መካከል የበርካቶችን ቀልብ የሳበው፤ 'በፖርትሬይት ሞድ' ቪዲዮ መቅረጻቸው ነው።

ከዚህ ቀደም ከአይፎን 7 ወዲህ ያሉ የአፕል ስልኮች በፖርትሬይት ሞድ ፎቶ ማንሳት እንጂ ቪዲዮ መቅረጽ አያስችሉም ነበር።

ፖርትሬይት ሞድ ለምሳሌ አንድን ሰው ከጀርባው ያለውን ዳራ በማደብዘዝ ፎቶ በሚነሳው ሰው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ቀልብ መሳብ የሚችል ምስል ማንሳት ያስችላል።

አይፎን 13 ደግሞ ይህን ወደ ቪዲዮ ከፍ አድርጎታል። የአፕል ኩባንያ አለቃ ቲም ኩክ እንደሚሉት ከሆነ ተጠቃሚዎች በፕሮትሬይት ሞድ ቪዲዮ ከቀረጹ በኋላ ኤዲት ማድረግ የሚያስችለው አይፎን-13 ስልክ ብቻ ነው ይላሉ።

ከዚህ በተጨማሪ አዳዲሶቹ አይፎን ስልኮች ተግባራትን በፍጥነት መከወን የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቶላቸዋል።

የስክሪን ግጽታቸው የተሻለ ብርሃን አለው። የባትሪ አገልግሎት ከዚህ ቀደም ከነበሩት አይፎን ስልኮች በ2.5 ሰዓት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪም አይፎን 13 ስልኮች በሮዝ፣ በሰማያዊ እና በቀይ ቀለማት አሸብረቀው መጥተዋል።
Via BBC
👍7❤1
ዌብሳይት በማሰራት የሚሰጡትን አገልግሎት እንዲሁም የሚያመርቱትን ምርት ኦንላይ በማቅረብ ይሽጡ! ምርትዎን ያስተዋውቁ፣ አገልግሎትዎን ያስተዋውቁ!
ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው በቀላሉ በማንኛውም ቦታ ተደራሽ ለመሆን ዌብሳይ ያስፈልግዎታል ስለሆነም በቀላል ዋጋ ምርጥ ገቢ የሚያገኙበት ዌብሳይት ያሰሩ!
ከዚህ በፊት የሰራናቸውን ዌብሳይቶችን መጎብኘት ይችላሉ!
ዌብሳይቱን ስንሰራ የሞባይል አፕ ሰርተን እናስረክበዎታለን!
www.safeway7.com
www.mametechsolution.com
www.4wcomputers.com
www.ethiotechnologys.com
www.bournworks.com

በቅናሽ ያሰሩ ዌብሳይቱን!
በ0929273364 ይደውሉ!

ሰሞኑን የተሰሩ ዌብሳይቶች እርሶም በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ!
1ኛ www.safeway7.com ይባላል ይህ ድርጅት የግል ሲሆን የፈርኒቸር እቃዎችን የሚሽጥ ድርጅት ነው ስለሆነም የሚሰራቸውን ስራ online በማድረግ አሰራሩን ዲጅታል እያደረገ ነው
2ኛ 4wcomputers ይባላል ይህ የግል የኮምፒውተር(ላፕቶፕና ደስክቶፕ) ሽያጭ እንዲሁም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎችን የሚሽጥ ነው ስለሆነም በጥሩ ሁኔታ ዌብሳይቱን ሰርተንለታል ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ!
www.4wcomputers.com
3ኛ Ethio Technology ይባላል ይህ ዌብሳይት ስለቴክኖሎጅ መረጃዎችን የሚያቀርብልን ሲሆን በተጨማሪም Online ሽያጭ ሊያሰራ የሚችል ዌብሳይት ነው። ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልክት ይችላሉ!
www.ethiotechnologys.com
4ኛ mame tech solution ይባላል ይህ ዌብሳይት እኛ በፌስቡክ፣ ቴሌግራምና ዩቱብ በተጨማሪ በዚህ ዌብሳት አገልግሎት እየሰሁ እገኛለሁ ስለሆነም ከታች ያለውን የዌብሳይት አድራሻ በመጠቀም ይማሩ መረጃ ያግኙ!
www.mametechsolution.com

5ኛ www.bournworks.com ይባላል የግል ድርጅት ሲሆን ማስታወቂያዎችን ይሰራል ኦንላይን ስራዎችንም ይሰራል።
ለግል፣ ለመንግሥት ድርጅቶች ዌብሳይቶችን ማሰራት ለምትፈልጉ በቅናሽ ያሰሩ ዌብሳይቱን!
በ0929273364 ይደውሉ! ወይም በቴሌግራም ( @ma2323me) ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
👍3
SafewayManufacturing_1_1.0.apk
1.5 MB
ሰሞኑን የተሰሩ ዌብሳይቶች እርሶም በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ!
1ኛ www.safeway7.com ይባላል ይህ ድርጅት የግል ሲሆን የፈርኒቸር እቃዎችን የሚሽጥ ድርጅት ነው ስለሆነም የሚሰራቸውን ስራ online በማድረግ አሰራሩን ዲጅታል እያደረገ ነው
አፑን ስልክዎ ላይ በመጫን ይሞክሩት!
👍4❤1
ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የሚያገለግሉ 9 የ አንግሮይድ አፖች

ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም። ዘመን አፈራሽ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ሞባይል ስልኮን ክኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮን ኤዲት አንዲያደርጉ ያስችሎታል። እኛም 9 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ ያገለግላሉ ያልናቸውን አፖች የዘን ቀርበናል።

1, FilmoraGo በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የ ዓንድሮኢድ ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። የመቁረጥ ፣ ገጽታዎችን መቀየር ፣ ሙዚቃን የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ ሊከናወኑ ይችላሉ ፡፡ እንዲሁም ለ Youtube ለ Instagram እና ለ Facebook ሚሆኒ ቪዲዮችን መስራት ይችናሉ
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.wondershare.filmorago

2, Adobe Premiere Clip: አዶቤ ፕሪሚየር ክሊፕ ማንኛውንም ቪዲዮ ከእርስዎ የ ስማርት ፎን በፍጥነት እንዲያርትዑ ያስችልዎታል። ለመጠቀም ፈጣን እና አዝናኝ ነው። ስለ ክሊፕ በጣም ጥሩው ባህሪ አውቶማቲክ ቪዲዮ መፍጠር ችሎታ ነው ፣ ማለትም ፣ መተግበሪያው በመረጣቸው ማንኛቸውም ፎቶዎች ወይም ቅንጥቦች አማካኝነት ቪዲዮዎችን በራስ-ሰር ለእርስዎ መፍጠር ይችላል ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adobe.premiereclip

3, VideoShow ብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ ሲሆን በነጻ በ Play Store ውስጥ ለሚገኙት ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች አንዱ ነው። VideoShow ለአጠቃቀም ቀላል እና ለአጠቃቀም ቀላል ነው ፡፡ ከዋና ዋና ተግባራት ፊልተሮችን ፣ ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም ቀጥታ ስርጭትን በማከናወን ቪዲዮዎን ማስዋብ ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.xvideostudio.videoeditor

4, PowerDirector ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ሙሉ ለሙሉ የ አንግሮይድ ቪዲዮ ኤዲተር ነው ፣ ግን ከመቆጣጠሪዎች ጋር ለመግባባት የተወሰነ ጊዜ ሊወስድዎት ይችላል። ሆኖም ፣ አንዴ በዚህ መተግበሪያ ኤክስ ኤክስፐርት ከሆኑ ባለሙያዎችን መፍጠር እና በሰከንዶች ጊዜ ውስጥ ምርጥ የሚባሉ ቪዲዮዎችን መስራት ይችላሉ ፡፡ ከቪድዮዎ ውስጥ ለመምረጥ ከ 30 በላይ የተለያዩ የትራንዚሽን ምርጫዎች አሉት ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.cyberlink.powerdirector.DRA140225_01
5, KineMaster ከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነገጽ ጋር በመጣመር KineMaster ለ Android ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው። የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ “copy paste” መጠቀም ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር KineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ይረዳል። በቪዲዮ መቁረጥ የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ፣ ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን ብሎግ ማስገባት ይችላሉ

የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nexstreaming.app.kinemasterfree

6, Quik እጅግ በጣም ጥሩ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ኩዊክ ሌላ ብልጥ መንገድ ነው ፡፡ ፈጣን እና ነፃ ነው። የራስዎን ታሪኮች በኩዊክ ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ። ስለ ኩዊክ በጣም ጥሩው ነገር አውቶማቲክ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎች ይዞ መምጣቱ መሆኑ ነው ፡፡ ቪዲዮዎችን crop ማድረግ ፣ ማሳመሪያዎችን ፣ ጽሑፎችን መጨመር እና ማንኛውንም Audio መምታት በፍጥነት ማመሳሰል ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.stupeflix.replay

7, VivaVideo ብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት። መተግበሪያው በቀጥታ ከ አንግሮይድዎ ፕሮፌሽናል-የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው። ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ ፡፡ በውስጡ የማይንቀሳቀስ ዘገምተኛ(slow motion) ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ሰሪ እና የተንሸራታች ማሳያ(slideshow maker) ሰሪ አለው።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.quvideo.xiaoying

8, Funimate video editor በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል። የዕለት ተዕለት አፍታዎችን ወዲያውኑ ወደ የፈጠራ ቪዲዮዎችን መለወጥ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ሜዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት ። አጭር ቪዲዮዎችን ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ ከ 1 በላይ የላቁ አማራጮች አሉት ፡፡

የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.avcrbt.funimate

9, Magisto መደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፣ ፎቶግራፎችን ፣ audio ፣ ጽሑፎችን ፣ የቪዲዮ ውጤቶችን እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል ፡፡ አንድ ወይም ከዛ በላይ ቪዲዮ ክሊፕ እና ለድምጽ ማጫወቻው አንድ ዘፈን ይምረጡ እና መተግበሪያው በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አውቶማቲካሊ ቪዲዮ ይፈጥራል።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.magisto
👍3
ምርጥ የResearch ቻናል።

❓ትምህርት እየተማሩ ነው? ወይም ለመማር አስበዋል?
❓ጥናትና ምርምር(Research) እየሰሩ ነው?
❓ስለ Research እውቀትዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
❓ስለ SPSS ማውቅ ይፈልጋሉ?
⁉️የምንረዶት ጉዳይ አለ?

✅በአማርኛ ና በእንግሊዝኛ በግልጽና ቀላል አገላለጽ ስለ Research ጽንሳ ሀሳብ ጀምሮ ጽሑፎችን ያገኛሉ።

💻በጥናትና ምርምር ዙርያ የማማከር አገልግሎትም እንሰጠለን።
👇👇👇👇👇👇👇
@researchRC
@researchRC
@researchRC
@researchRC
@researchRC
👆👆👆👆👆👆👆👆
👍4
ሁሉንም የትምህርት ፍኖተ ካርታ መረጃ በዚህ ልልቀቅላችሁ?
Anonymous Poll
95%
አዎ ያስፈልገናል!
5%
ይቅር አያስፈልገንም!
👍2
የት/ት ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ በሚሆኑ ት/ቤቶች በየክፍል ደረጃ የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
😁= ቅድመ መደበኛ (KG) ለሁለት አመት የሚሠጥ:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= አካባቢ ሳይንስ
3ኛ= ሙያ
4ኛ= ሂሳብ
5ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው፡፡
😁በመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ
3ኛ= እንግሊዘኛ
4ኛ= ሂሳብ
5ኛ= አካባቢ ሳይንስ
6ኛ= የግብረገብ ት/ት
7ኛ= ሙያ
8ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው፡፡
😁በመጀመሪያ መካከለኛ ደረጃ ከ7ኛ-8ኛ ክፍል የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= የአገር አቀፍ ቋንቋ
3ኛ=እንግሊዘኛ
4ኛ= ሂሳብ
5= ሳይንስ
6ኛ= ህብረተሰብ
7ኛ= ስነ -ዜጋ
8ኛ= ሙያ
9ኛ= IT
10ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው::
👍3❤2
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ የመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የክ/ጊዜ ብዛት::
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 40 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 6 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 30 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሰዓት ከጥዋቱ 2:15-6:30 የጥዋት ሸፍት ከ6:45-11:00 የከሠዓት ሸፍት ሆኖ 15 ደቂቃ ዕረፍት አለው፡፡
😁የት/ት ሠዓት በየሸፍቱ 4ሰዓት ነው፡፡
😁በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 4 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ እና የዓመቱ ሰዓት 104 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ ክ/ጊዜ 3፣ በሳምንት 2ሠዓት እና በአመት78 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= እንግሊዘኛ የሳምንት ክ/ጊዜ 4 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና የአመቱ 104 ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ= ሂሳብ በሳምንት5 ክ/ጊዜ በሳምንት 3ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት130ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ= አካባቢ ሳይንስ በሳምንት 5 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 3ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት 130 ሰዓት አለው፡፡
😁6ኛ= የግብረገብ ት/ት በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁7ኛ= የሙያ ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁8ኛ= የሰውነት ማጎልመሻ ት/ት በሳምንት 3ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁በአጠቃላይ በሳምንት 30 ክ/ጊዜ ወይም 20 ሰዓት እና በዓመት 780 ሰዓት አለው:: ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
😁መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍4❤1
የኮምፒዉተራችን storage space ሲሞላብን እንዴት ማስለቀቅ እንችላለን
የኮምፒዉተርዎ storage space ሞልቶበት ተቸግረዋል፡፡ እንግዲያዉስ የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ
1. ለብዙዎች እፎይታን የሰጠ መፍትሔ ሲሆን የኮምፒዉተራችንን ስቶሬጅ የሞሉብንን የተለያዩ ፋይሎች በማጥፋት ብዙ ትርፍ storage space እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ኮምፒዉተራችን ላይ የማንጠቀምባቸዉ እና የማይጠቅሙን ጊዜያዊ ፋይሎችን (temporary files) በማጥፋት ኮምፒዉተራችን ላይ ብዙ ቦታ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡
✅ Delete unnecessary temporary file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።
2. የማንጠቀምባቸዉን ፕሮግራሞች Uninstall ማድረግ
አብዛኞቹ ኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች የኮምፒዉተራቸዉን ቦታ የሚያጣብባቸዉ የጫኗቸዉ ሶፍትዌሮች እና ጌሞች ናቸዉ፡፡ የማንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮች Uninstall በማድረግ ቦታ መቆጠብ እንችላለን፡፡ ከኮምፒዉተሮ ላይ የማይፈልጉትን ሶፍትዌር ለማጥፋት የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Start -> Control Panel -> Uninstall a program
2. ብዙ ቦታ የያዘዉን ሶፍትዌር ለማወቅ በ size ቅደም ተከተል ይደርድሯቸዉ፡፡
3. ማጥፋት የፈለጉትን ሶፍትዌር መርጠዉ Uninstall የሚለዉን ይጫኑ፡፡
3. የተደጋገሙ ፋይሎችን ያጥፉ
ዊንዶዉስ በራሱ የተደገሙ ፋይሎችን ለይቶ የሚያጠፋ ሲስተም የለዉም ስለዚህ ይህንን ስራ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህንን የሚያደርጉ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ Duplicate Sweeper አንዱ ነዉ፡፡ Duplicate Sweeper ኮምፒዉተራችን ላይ ያሉ የተደጋገሙ ፋይሎችን scan አድርጎ ያቀርብልናል፡፡ እኛም ከዘ ዉስጥ የተደገሙ መሆናቸዉን እያረጋገጥን ማጥፋት እንችላለን፡፡
4. ጊዜያዊ ፋይሎች (Temporary Files)
በ Windows Disk Cleanup አማካኝነት ጊዜያዊ ፋይሎችን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አይተናል፡፡ ነገርግን Windows Disk Cleanup ሊያገኛቸዉ የማይችሉ እንደ browser ያሉ የጫንናቸዉ ሶፍትዌሮች የፈጠሩትን ጊዜያዊ ፋይሎች ለማጥፋት የሚያስችለን ሌላ መንገድ Google Chrome ን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ እናያለን፡፡
1. Google Chrome ን ይክፈቱ
2. settings menu ይክፈቱ
3. More tools የሚለዉን ይምረጡ
4.Clear Browsing data የሚለዉ ዉስጥ በመግባት ማጥፋት የሚፈልጉትን ጊዜያዊ ፋይል
መርጠዉ ያጥፉ
5. Recycle Bin ዉስጥ ያሉ ፋይሎችን ያጥፉ
ከኮምፒዉተራችን ላይ ያጠፋናቸዉ ፋይሎች permanently delete ካላደረግናቸዉ መልሰን ብንፈልጋቸዉ ማግኘት እንድንችል Recycle Bin ዉስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ከላይ ባሉት መንገዶች ያጠፋናቸዉ ፋይሎችም Recycle Bin ዉስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ Recycle Bin ያሉ ፋይሎች ግን ከኮምፒዉተራችን ላይ የያዙትን storage space እንደያዙ ነዉ የሚቆዩት፡፡ ስለዚህ storage space ለማስለቀቅ እነዚህን የማንፈልጋቸዉ ፋይሎች ከRecycle Bin ዉስጥ ማጥፋት ይኖርብናል፡፡
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
👍8😁2
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ መካከለኛ የመጀመሪያ ደረጃ ከ7ኛ-8ኛ ክፍል የክ/ጊዜ ብዛት::
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 40 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 6 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 30 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሰዓት ከጥዋቱ 2:15-6:30 የጥዋት ሸፍት ከ6:45-11:00 የከሠዓት
ሸፍት ሆኖ 15 ደቂቃ ዕረፍት አለው፡፡
😁የት/ት ሠዓት በየሸፍቱ 4ሰዓት ነው፡፡
በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 2 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና የዓመቱ ሰዓት 52 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ ክ/ጊዜ 2፣ በሳምንት 1ሠዓት ከ20 ደቂቃ እና በአመት52 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= እንግሊዘኛ የሳምንት ክ/ጊዜ 4 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና የአመቱ 104 ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ= ሂሳብ በሳምንት4 ክ/ጊዜ በሳምንት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና በዓመት104ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ= አጠቃላይ ሳይንስ በሳምንት 4 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና በዓመት 104 ሰዓት አለው፡፡
😁6ኛ= የህብረተሰብ ት/ት በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁7ኛ= የስነ-ዜጋ ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁8ኛ= የጥበብ ስራ ት/ት በሳምንት 2 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 1ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና በዓመት 52ሰዓት አለው፡፡
😁9ኛ=የአይቲ ት/ት በሳምንት 2ክ/ጊዜ በሳምንት 1ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁10ኛ=የሰውነት ማጎልመሻ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁11ኛ=የሙያ(የእጅ) ስራ በሳምንት 2 ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20 ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁በአጠቃላይ በሳምንት 30 ክ/ጊዜ ወይም 20 ሰዓት እና በዓመት 780 ሰዓት አለው:: ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍1
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች (ከ9ኛ-10ኛ ክፍል) የክ/ጊዜ ብዛት::
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 40 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 6 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 30 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሰዓት ከጥዋቱ 2:15-6:30 የጥዋት ሸፍት ከ6:45-11:00 የከሠዓት ሸፍት ሆኖ 15 ደቂቃ ዕረፍት አለው፡፡
😁የት/ት ሠዓት በየሸፍቱ 4ሰዓት ነው፡፡
*በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የእንግሊዘኛ= የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 3 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 3 ሰዓት እና የዓመቱ የት/ት 78 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= ሒሳብ =በሳምንት 4 ክ/ጊዜ ( 2ሠዓት ከ40 ደቂቃ) እና በአመት 104 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= ባዮሎጂ =በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት) እና የአመቱ 78 ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ= ኬሚስትሪ በሳምንት3 ክ/ጊዜ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78 ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ= ፊዚክስ በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78 ሰዓት አለው፡፡
😁6ኛ= ጂኦግራፊ በሳምንት 2 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 1ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁7ኛ= ታሪክ ት/ት በሳምን 2 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 1ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁8ኛ= ሲቪክስ በሳምንት 2 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 1ሰዓት ከ20 ደቂቃ እና በዓመት 52ሰዓት አለው፡፡
😁9ኛ=የአይቲ ት/ት በሳምንት 2ክ/ጊዜ በሳምንት 1ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁10ኛ=ኢኮኖሚክስ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
*ንዑስ ድምር:-
========
የሳምንት ክ/ጊዜ 26 (17ሰዓት ከ20 ደቂቃ) እና በዓመት 676 ሰዓት ይሆናል፡፡
*ተጨማሪ አማራጭየት/ት አይነቶች:-
===================
😁1ኛ=የአፍ መፍቻ ቋንቋ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓትአለው፡፡
2ኛ=አገር አቀፍ ቋንቋ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው፡፡
😁3ኛ=የውጭ ቋንቋ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ)እና 52ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ=የሰውነት ማጎልመሻ በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ=የሙያ ት/ት በሳምንት 2ክ/ጊዜ (1ሰዓት ከ20ደቂቃ) እና በዓመት 52 ሰዓት አለው::
ንዑስ ድምር በሳምንት 4ክ/ጊዜ (2ሰዓት ከ40 ደቂቃ)እና በዓመት 104 ሰዓትአለው
*በአጠቃላይ ድምር:-
=========================
በሳምንት 30 ክ/ጊዜ ወይም 20 ሰዓት እና በዓመት 780 ሰዓት አለው:: ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
😁መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍6
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች (ከ11ኛ-12ኛ ክፍል) ሶሻል ዲፓርትመንት የክ/ጊዜ ድልድል:
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 45 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 7 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 35 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሠዓት በየፈራቃው 4ሰዓት ከ40 ደቂቃ ነው፡፡
😁በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
$ ቋንቋ እና ሶሻል ሳይንስ ት/ት ክፍል!
=====================
😁1ኛ= የእንግሊዘኛ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 4 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 3 ሰዓት እና የዓመቱ የት/ት 117 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= ሒሳብ ክ/ጊዜ 4፣ በሳምንት 3ሠዓት እና በአመት 117 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= ጂኦግራፊ የሳምንት ክ/ጊዜ 3 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና የአመቱ 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁4ኛ= ኢኮኖሚክስ በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁5ኛ= ታሪክ ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁ኛ6=የአይቲ ት/ት በሳምንት 3ክ/ጊዜ በሳምንት 2ሰዓት ከ15ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
ቋሚ የት/ት አይነቶች ክ/ጊዜ ብዛት ድምር=20ሲሆን:-
በዚህ ዘርፍ ፊልድ (የሙያ) ተጨማሪ አማራጭ የት/ት አይነቶች:-
===================
😁1ኛ=የአፍ መፍቻ ቋንቋ እና ስነ ጽሑፍ በሳምንት 4ክ/ጊዜ (3ሰዓት ) እና በዓመት 117 ሰዓት አለው፡፡
😁2ኛ=ማህባራዊ ስራ በሳምንት 4ክ/ጊዜ (3 ሰዓት ) እና በዓመት 117 ሰዓት አለው፡፡
😁3ኛ=ስነ ሰብ በሳምንት 4ክ/ጊዜ (4ሰዓት) እና 117ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ=ሰነ-ዜጋ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (3ሰዓት) እና በዓመት 117ሰዓት አለው፡፡
የፊልድ ክ/ጊዜ ድምር 15 ክ/ጊዜ ነው፡፡
😁 በአጠቃላይ በሳምንት 35 ክ/ጊዜ ወይም 26ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 1023 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው::
$ ቢዝናስ የት/ት ክፍል የክ/ጊዜ ድልድል:-
==================
😁1ኛ=እንግሊዘኛ በሳምንት 4ከ/ጊዜ (3ሰዓት) እና በዓመት 117ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ=ሒሳብ በሳምንት 4ክ/ጊዜ (3ሰዓት) እና በዓመት 117ሰዓት አለው፡፡
😁3ኛ=ጂኦግራፊ በሳምንት 3ክ /ጊዜ (2ሰዓት:ከ15 ደቂቃ) እና በዓመት 78 ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁4ኛ=ታሪክ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት 15ደቂቃ) እና በዓመት 78ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁5ኛ=ኢኮኖሚክስ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓትከ15 ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁6ኛ=ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት ከ15ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁ስለዚህ ቋሚ የት/ት አይነቶች ክ/ጊዜ ብዛት ድምር 20 ነው፡፡
በዚህ ዘርፍ የሙያ ፊልድ ተጨማሪ የት/ት አይነቶች:-
😁1ኛ=አካውንቲንግ እና ፋይናንስ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት ከ15ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው::
😁2ኛ=ባንኪንግ እና ኢንሹራንስ በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓትከ15ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁3ኛ=የቢሮ አስተዳደር በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓትከ15 ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45ደቂቃ አለው፡፡
😁4ኛማርኬቲንግ በሳምንት 3ክ/ጊዜ 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 78 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
😁5ኛ=ሆቴልና ቱሪዝም በሳምንት 3ክ/ጊዜ (2ሰዓት ከ15ደቂቃ) እና 78ሰዓት ከ45 ደቂቃ ሲኖራው በድምሩ የሙያ ዘርፍ 15ክ/ጊዜ ይይዘል::
በአጠቃላይ በሳምንት 35ክ/ጊዜ (26ሰዓትከ15ደቂቃ) እና በዓመት 1023 ሰዓት ከ45ደ ቂቃ አለው፡፡
ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
😁መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍3👏1🤩1
የጥንቃቄ መልእክት ለሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚወች ።
ሼር በማድረግ ማህበረሰባችንን ከዚህ ጥፋት እንታደግ!
አጭበርባሪወች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችን ስልክ ቁጥር በተለያየ መንገድ ካገኙ በኋላ ፤ የባንክ ቁጠባ እድለኞች ሽልማት የደረሳቸው በማስመሰል ሜሴጅ ይልካሉ ፤

በተጨማሪም ወድያውኑ በስልካቸው ደውለው እርስዎ የወሩ የባንካችን እድለኛ ነዎት በመሆኑም በሽልማት የደረሰዎት 300,000 ሺ ብር በአካውንትዎ ገቢ እንዲሆንልዎ መጀመሪያ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ከሆኑ *889# ብለው ያስገቡ በመቀጠል ስንደውልልዎ የራስዎን ሚስጥር ቁጥር (pin code) ያስገቡ በሚል አጭበርባሪወች እራሳቸው የባንክ ሰራተኛ መስለው ካልኩሌሽኑን በስልክ ይመራሉ ፤

በመቀጠል በግለሰቦች አካውንት ያለውን ገንዘብ በሙሉ ወደ እራሳቸው አካውንት በማዞርና ወዲያውኑ ገቢ ያደረጉትን ገንዘብ በማውጣት እየተሰወሩ ከፍተኛ ዘረፋ እየፈፀሙ ስለሆነ ፤ ማንኛውም ሰው ባንክ እየገባ ትክክለኛነቱን ሳያረጋግጥ በስልክ ጥሪ ብቻ እየተታለለ ገንዘቡን እንዳይበላና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን ።
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
( መረጃውን ያደረሰን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፓሊስ መምሪያ የወንጀል መረጃና ክትትል ዋና ክፍል ነው )
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍4❤1🥰1
ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ? አስበውት ያውቃሉ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ?
✅ ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው።
✅ ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
✅ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው።
✅ ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
✅ Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
ምስሉን ይመልከቱ!⁉️
✅ Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
✅ይህ ተግባር የሁልጊዜ ስራችንና ተግባራችን ይሁን።
✅ ከተመቻችሁ ለሌሎች ሰዎች እንዲደርሳቸው #ሼር ይደረግ!
✅ ለፔጁ አዲስ የሆናችሁ ሰዎች #Like #shear ይደረግ።
👍15👏1
#ውድ የ Muhammed Computer Technology የፌስቡክ ገጽ ተከታታዮች። እንደሚታወቀው በፌስቡክና በቴሌግራም ምርጥ አስተማሪ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን እያደረስኳችሁ እገኛለሁ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በYouTube ጠቃሚ ትምህርቶችን ለተመልካች እያቀረብኩ እገኛለህ። ስለሆነም በ1 አመት ብቻ ❤ #28,000 በላይ #Subscribers ማግኘት የቻለ ተወዳጅ ቻናል ሁኗል ስለሆነም በYouTube በምለቀቃቸው Vedios ጠቃሚና አስተማሪ ሰልሆኑ #Subscribe በማድረግ #ይማሩ #ይወቁ
#በቅንነት ሼር አድርጉልኝ!
ያቀቁትን ማሳወቅ የተማሩትን ማስተማር ብልህነት ነው።
YouTube ቻናል ሊንክ
👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍35🔥3❤2👎2🤔2
የኢሜል password ብንረሳዉስ🙈?
የኢሜል ፓስዋርዳችሁ ከጠፋባችሁ ከዚህ በታች ያሉትን እስቴፖች በመከተል የጠፋባችሁን የኢሜል ፓስዋርድ
አጥፍታችሁ #reset በማድረግ በአዲስ መቀየር ትችላላችሁ ።
👇👇
1⃣ ይከከን ማስፈንጠሪያ

https://accounts.google.com/signin/recovery

ተጭናችሁ ወደ #Google account recovery ፔጅ ግቡ።

2⃣ፖስዋርዱ የጠፋባችሁን ኢሜል አድራሻ (email address) አስገብታችሁ #forget password የሚለዉን በተን ተጫኑ።

3⃣የምታስታዉሱትን የ ኢሜል ፓስዋርድ እንድታስገቡ ይጠይቃችሗል።

✅እዚህ ላይ ያስታወስችሁትን የጠፋዉን ፖስዋርድ አስገቡ እና #Next የሚለዉን በተን ተጫኑ።

✅ብትሳሳቱም አትጨነቁ አካዉንታችሁን አይዘገሠዉም።

4⃣ከዛ #Google የሜረጋገጫ #Verification code
ኢሜሉን ስትከፍቱ ባስገባችሁት ስልክ ቁጥር ይልክላችሗል።

በምን ይልካል?

✅#Text or Call የሚል ሲመጣ የሚፈልጉትን የመቀበያ መንገድ ይምረጡ።

5⃣የተላከላችሁን ባለ 6 #digit የማረጋገጫ ኮድ አስገቡ።

6⃣ከዛ አዲስ ፖስዋርድ እንድታስጋቡ ይጠይቃችሗላ።

✅የፈለጉትን ፖስዋርድ እና ኮንፌርሜሽን ፓስዋርድ(መጀመሪያ ያስገባችሁትን ደግማችሁ አስገቡ) አስገብታችሁ
#Next የሚለዉን ሲጫኑ የጠፋዉ ፖስዋርድ በአዲስ ፓስወርድ ተቀየረ ማለት ነዉ።
ከተመቻችሁ ሼር
👍16👏1
15GB ነፃ Storage እንዲሁም ወደ Google Drive ፋይል መጫንና ከ ወደ ሌላሰው በኢሜይል(Email) እንዴት መላክ እንችላለን ፋይል ማስቀመጥ ይቻላል?
15GB ነጻ ፋይል ማስቀመጫና ከ25MB በላይ ፋይልን ለሌላ አካል ኢሜይል ማድረግ እንችላለን? ብዙ ግዜ ከ25MB በላይ ኢሜይል ለመላክ እምቢ ላላችሁ ሰዎች መፍትሄው ከዚህ በታ ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ
https://youtu.be/HEvXJo8E3k0
https://youtu.be/HEvXJo8E3k0
👍2😁1
ኮምፒውተር ላይ ማንኛውንም ፍላሽና ኤክስተርናል ሀርድ ዲስክ ሲሰካ እንዳይሰራ ማድረግ
1. የኛን መረጃ ሌላ ሰው ያለእኛ ፈቃድ እንዳይወስድብን ለመዝጋትና
2ኛ. ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።
👇👇👇ቪዲዮውን ይመልከቱ👇👇👇
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
👍6