Muhammed Computer Technology (MCT)
38.9K subscribers
472 photos
7 videos
206 files
830 links
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው!
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
አስተያየት ካላችሁ @mctplc ልታገኙኝ ትችላላችሁ
በተጨማሪም የ YouTube ቻናል 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ጥሩ ቪዲዮችን ማግኘት ይችላሉ!
Download Telegram
ሲም ካርድ ምንድን ነው?
🔷 ሲም ማለት ነው የተመዝጋቢ ማንነት ሞዱል.SIM stands for Subscriber Identity Module ከማንኛውም የሞባይል ስልክ በጣም አስፈላጊ አካል ነው ፡፡ በአንዳንድ አገሮች ICC (Integrated Circuit Card ) and UICC ( Universal Integrated Circuit Card ) በመባልም ይታወቃል ፡፡ በቀላል አነጋገር ሲም ካርድ በመሠረቱ SIM Card is a or ማይክሮ መቆጣጠሪያን መሠረት ያደረገ የመዳረሻ ሞዱል (microcontroller-based access module) ወይም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ መረጃን የሚያከማች (a small portable memory chip) ፣ የ 16 አኃዝ ወይም የ 17 አኃዝ ኮድ ያለው ሲሆን ግን እንደየሀገሩ ይለያያል የኔትወርክ አጓጓዥ መረጃን እና የሚያከማች አነስተኛ ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቺፕ ነው ፡፡ ልዩ የተጠቃሚ መታወቂያ / የሞባይል ስልክ ቁጥር ነው።

የሲም ካርድ ሲም ካርዶች በ 3 መሠረታዊ መጠኖች ይገኛሉ መደበኛ ፣ ማይክሮ እና ናኖ ፡፡ ከነዚህ ሶስት መጠኖች ውስጥ መደበኛ መጠኑ የመጀመሪያው ነው ፡፡ ማይክሮ እና ናኖ ሲም ካርዶች ከመደበኛው ሲም ካርድ ዙሪያ ያለውን ተጨማሪ ፕላስቲክን በመቁረጥ አነስተኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል ፡፡ ለተሻለ ግንዛቤ የሚከተለውን ምስል ይመልከቱ ፡፡

የሲም ካርድ ዓይነቶች ሲም ካርዶች በዋናነት 2 አይነቶች ናቸው - GSM (ጂ.ኤስ.ኤም) እና
CDMA (ሲዲኤምኤም) ናቸው።

GSM ማለት (Global System for Mobiles) SIM ለሞባይል ዓለም አቀፍ ስርዓት ማለት ነው፡፡ በማንኛውም የሞባይል ስልክ ውስጥ ሊገባና ሊወጣ ይችላል፡፡
CDMA ማለት ሲተነተን Code Division Multiple Access ማለት ነው፡፡ አንዴ ከመጀመሪያው ስልክ ውስጥ ሊወገድ ወይም ሊወጣ አይችልም።

eSIM ካርድ በአሁኑ ጊዜ eSIM Card ተብሎ የሚጠራ አዲስ የሞባይል ስልክ ግንኙነት ቴክኖሎጂ አለ ፡፡ eSIM ማለት Embedded ሲም ማለት ነው፡፡ እንደ GSMና CDMA SIM አይነት አይደለም ገና ስልኩ ሲሰራ አብሮ ከስልኩ ጋ ተጣብቆ የሚመረት ነው እንዲሁም በ eSIM ላይ ያለው መረጃ እንደገና ሊፃፍ ስለሚችል የኔትወርክ ኦፕሬተርዎን መለወጥ ይችላሉ ፡፡


ሲም ካርድ ክፍሎች እና ተግባር በሲም ካርድ ላይ የተለያዩ የወረዳ ክፍሎች የተለያዩ ተግባራት አሏቸው ፡፡ የሚከተለው የአንድ ሲም ዋና ዋና ክፍሎች ናቸው ፡፡
🔷 1. VCC ( Power Supply )
የሲም የኃይል አቅርቦት ፒን ነው ፡፡ 5V DC ኃይልን ይደግፋል ፡፡ ሲም ካርዱ እንዲሰራ ይህ የቪ.ሲ ፒን ከ 5V DC ጋር መቅረብ አለበት ከዚያም በሲም ካርዱ ውስጥ የተካተተው IC(Integrated Circuit) ብቻ ነው የሚሰራው ፡፡

🔷 2. RST ( Reset )

የሲም ካርዱን Signal እና ግንኙነቶችን (Communication) እንደገና ለማስጀመር የሚያገለግል ፒን ነው ፡፡ ይህንን ፒን ሲጠቀሙ ሲም ሁሉንም የወቅቱን Signal ዳግም በሚያድስ ነባሪው ሞድ ያደርገዋል ፡፡ የ RESET ፒን በሞባይል መሳሪያዎች ወይም በሲም ካርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይሠራል። በአጠቃላይ ሲም ተጠቃሚዎች ይህንን ተግባር እንዲጠቀሙ አነስተኛ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

🔷 3. CLK ( Clock ) ሰዓት-ሲምውን ለprocessor የሰዓት Signal ይሰጣል፡፡
🔷 4. GND (Ground) ሲም የIntegrated Circuit ያለው አነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ ሃርድዌር እንደመሆኑ Ground ተብሎ ተሰይሟል ፡፡ GND አሁን ለሲም ካርዱ ትክክለኛ ሥራ ወረዳውን ያጠናቅቃል ፡፡
🔷 5. VPP ( Voltage Programming Power )
ቀደም ሲል ይህ ፒን በሲም ካርዱ ማህደረ ትውስታ ውስጥ ያለውን ውሂብ ለመፃፍ ወይም ለመሰረዝ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ቮልት ለመሸከም ያገለግላል ነገር ግን አሁን ይህ ስራ በVCC የሚሰራ ስለሆነ በጣም ጠቃሚ አይደለም፡፡
🔷 6. SIM Data I/O Pin

ግብዓት / ውጤት-በሞባይል ስልኮች በሲም ካርድ ውስጥ ያለውን data ለማንበብ እና ለመፃፍ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ እንደ የdata ማስተላለፊያ ፒን የሚሰራ ግማሽ ባለ ሁለትዮሽ የግንኙነት ፒን ነው። ሲም ካርዱ እያነሰ እና እየቀነሰ ሲመጣ አፈፃፀሙ እና አቅሙ በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን በአዲሱ ቴክኖሎጂ እና ምርምርም ምስጋና ይግባው ፡፡
የሲም ካርድ መለዋወጫዎችን እና ተግባሩን ለመረዳት የሚከተለውን ስእል ይመልከቱ ፡፡
ምርጥ አፕሊኬሽን offline አንዴ በስልካችን ከተጫነ ስለ Website development Language የያዘች App ነች በማውረድ ተጠቀሙ!!!
Enjoy💪
❖ ፍላሽ ዲስክ ኮምፒዩተርዎ ላይ ሲሰካ ሾርት ከት እየሆነ ተቸግረዋል?
❑ ፍላሽ ዲስካችን ወይም ኮምፒዩተራችን በቫይረስ ሲጠቃ በውስጡ ያሉት ፋይሎች በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ሾርትከት ይቀየራሉ። ይህም ማለት ዋናው የኛ file(ፋይል) ይደበቅና ለመጠቀም አንችልም ማለት ነው።
❑ የዚህ ቫይረስ ሌላው አስቀያሚ ገጽታ ከኮምፒዩተር ወደ ሌላ ኮምፒዩተር በቀላሉ በፋላሽ አማካኝነት ሊተላለፍ መቻሉ ነው።
✏️ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ዛሬ ይህን ሾርትከት ቫይረስ የምናጠፋበትን Tricks. እናካፍላችኋለን ተከታተሉን።
❑By using CMD❑
 cmd (command prompt) በመጠቀም
ይህ ዘዴ ከሁሉም የተሻለ ውጤታማ ሲሆን ለሀርድ ዲስኮች ለፍላሾች እንዲሁም ለሞባይል ስልኮች ያገለግለናል።
1. በመጀመሪያ cmd እንከፍታለን።
Win + R then we write Cmd ( run፦cmd፦enter)
2. cmd ከከፈትን በኋላ ለማጽዳት የምንፈልገው ፋላሽ ዳይሬክተሪ እንሄዳለን። ( ለምሳሌ ፍላሹ removable disk G ከሆነ G:\ ብለን እንጽፋለን።)
3. በመቀጠል ይህን ኮማንድ እንጽፋለን። G፡*.* /d /s -h -r -s (G ለምሳሌ ሲሆን እናንተ በራሳችሁ ፋላሽ ሆሄ ትቀይሩታላችሁ።)
4. አሁን ኢንተርን ስትጫኑ ከሾርትከት ቫይረስ ተገላገላችሁ ማለት ነው።
መረጃዎቹን ጠቃሚ ሆነው እንዳገኛችኋቸው ተስፋ እናደርጋለን።።
══════❁✿❁ ══════
        🗣➹share &Join Us
    ┗━ ••• ━ ••• ━━•••━━━┛
CV ለማዘጋጀት ከላይ ያሉትን 3 PDF ፋይሎችን በማወረድ መጠቀም ትችላላችሁ👆👆👆
እየተመቻችሁ ነው?
አንዱን ይምረጡ!
Anonymous Poll
96%
ተመችቶኛል 👍
4%
አልተመቸኝም 👎
የኮምፒውተራችንን Hard Drive እንዴት በቀላሉ ፓርቲሽን(partition) መክፈል እንችላለን?
📍በመጀመሪያ ፓርቲሽን በመክፈላችን
ምናገኛቸው ጥቅሞች ምንድናቸው ብለን
ስናስብ እንደየ ፍላጎታችን ሚለያይ ሲሆን
ለሁላችንም ሚሰጠን ዋናው ጥቅም ቢኖር
ፉይላችንን ከ ሲስተም ፋይል ያሉ ፋይሉችንን
ለይተን በማስቀመጥ በተላያዩ ምክንያት ቡት
ማረግ ወይም ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን
መነሳት ሲያቅተው ልናጣ ምንችለውን ፉይል
ለመከላከል የምንጠቀምበት መንገድ ነው
📍ለምሳሌ ከፋብሪካው እንደመጣው በ C:
partiton ብቻ እየተጠቀምን ቢሆንና በ
ቫይረስ ምክንያት ሲስተም ፋይል ቢጠፋ
ሌሎች ፐርሰናል ፉይሎችን አጣን ማለት
ነው።
📍ስለዚህ በቀላሉ እዛው ፓርቲሽን
በመፍጠር የግል ፉይል ለብቻ C: ፓርቲሽን
ለብቻ አድርገን በመጠቀም ፋይላችንን
መከላከል እንችላለን ይህን ካልን ስለ
ፓርቲሽን እንዴት ዊንዶውስ ባዘጋጀልን disk
managment በ መጠቀም እንዴት
መስራት እንችላለን ሚለውን ላሳያችሁ
ወደድኩ
📍በመጀመሪያ ባክአፕ መውሰድ አስፈላጊ ነው
ምንም እንኳ ፕሮሰሱ ፋይል ባያጠፋብንም
ለጥንቃቄ ሲባል ወስደን መጀመር አለብን
📍በመቀጠል ወደ my computer iconላይ
ራይት ክሊክ አርገን manage ሚለውን
ክለክ ስናደርግ አዲስ ዊንዶው ይከፈትልናል
ማለት ነው።
📍በግራ ባለው ዝርዝር ውስጥ
disk managment ሚል በመፈለግ ያንን
እንከፍታለን በመቀጠልም በሚከፈተው
ዊንዶው ውስጥ መሀል ላይ ሁኖ ከታች ባለው
ቦታ ላይ
📍 ያልተከፈለው ፓርቲሽን በ ሰማያዊ
ይታየናል ስለዚህም ማድረግ የፈለግነውን
ፓርቲሽን ላይ ራይት ክሊክ በማድረግ
በሚመጡት ዝርዝሮች ውስጥ shrink
volume የሚል ን በመምረጥ በሚከፈትልን
ዊንዶው መሰረት እንደምን ፈልገው ሳይዝ
በማስገባት ሌላ አዲስ ፓርቲሽን እንፈጥራለን።
⚠️ ማሳሰቢያ የ disk size ስባስገባ ቁጥሩ በ Mega byte(MB) ነው የሚቀመጠው ስለዚህ ለምሳሌ 100 GB ማድረግ ከፈለግኩኝ 1024,000 ብየ ቁጥሩን ማስገባት አለብኝ ማለት ነው ወይም 200GB ማድረግ ብፈልግ 2048,000 ማለት አለብኝ። የ 1 GB ማለት 1024 MB ስለሆነ።⚠️
ይህንን finish ብለን ከጨረስን በኋላ
የከፈትነው ፐርቲሽን እዛው disk
managment ውስጥ በጥቁር ከለር
ይታየናል ስለዚህ ይህንን ፓርቲሽን ላይ ራይት
ክሊክ በማድረግ የጀመረነውን ፓርቲሽን
መፍጠር ለመጨረስ እንጀምራለን።
📍ስለዚህ ራይት ክሊክ ስናደርግ new volume
የሚለውን ስንነካ አዲስ ዊንዶ ይመጣል
ስለዚህ ምንም ነገር ሳንነካ nextን ብቻ
በመጫን መጨረሻም ላይ finish ን
ስንጫን አዲሱ ፓርቲሽን my computer
ውስጥ መታየት ይጀምራል ማለት ነው ።
ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ እንደተለመደው
በመጠየቅ አበረታቱን ስል እላለው
አመሰግናለው
በቤታችን የሚገኙ ዲሾች ቶሎ ቶሎ ለምን ይበላሻሉ? መፍትሄዎቹስ?

📡 የዲሽ መጠን አነስተኛ መሆን

የመጀመርያው ነገር የዲሽ መጠን ባነሰ ቁጥር የመሳብ አቅሙ ይቀንሳል። ዲሽ ለመግዛት ያሠባችሁ 90cm በታች በትገዙ የተሻለ ሲሆን የተለያዩ ሳተላይቶችንም ደርበን ለመጠቀም 60 አይሆንም።

🔦 የLNB መድከም

- በተለምዶ የዲሽ አናት የምንለው LNB ብዙ ጊዜ ከማገልገሉ የተነሳ የመሳብ ቅሙ ይቀንሳል ወይም በከፊል ይቃጠላል ።ስለዚህ በሀይላንድ መሸፈን በዝናብ ምክንያት ለሚቃጠሉ መፍትሄ ነው።

📎 የዲሽ ገመድ (Cable) መቆራረጥ

- ወደ ሪሲቨራችን የሚገባው ገመድ ቢያንስ ከሁለት ቦታ በላይ የተቆራረጠ ከሆነ Strength ስለሚቀንስ አስቡበት።
የኬብል Connector- ገመዱን ከLNB ወይም ከSwitch ጋር የሚያገናኘልን ብረቶች ለዝናብ የተጋለጡ ከሆነ በዝገት ምክንያት ማስተላለፍ ስለሚያቆሙ ዝናብ የማይነካቸው ቦታ ማድረግ ወይም መሸፈን ።

🏡 የዲሽ ማስቀመጫ ጣሪያ ሁኔታ

የዲሽ ማስቀመጫ ጣሪያ በዚህ ስራ ከፍተኛ የሆነ ሚና አለው። ጣሪያ ከስር በርካታ አግዳሚዎች ከሌሉትና የቆርቆሮው ጌጅ ዝቅተኛ ከሆነ በቀላሉ ቦታውን ይለቅቃል።

🌴 የአካባቢው በዛፍ (በግንብ) የመሸፈን ሁኔታ

ሳተላይት የሚመጣው አግድም ከሆነ በዛፍም ሆነ በግንብ በቀላሉ የመከለል ችግር ይገጥመዋል። የዲሹ አቅጣጫ ወደ ምዕራብ ከሆነ ዲግሪ እየቀነሰ ሲመጣ እንዲሁም የዲሹ አቅጣጫ ወደ ምስራቅ ከሆነ ዲግሪ እየጨመረ ሲመጣ።ስለዚህ ጥሩ የሆነ ቦታ ለማስቀመጥ ሞክሩ።

🕳 የዲሽ ማስቀመጫ ጣውላ መበስበስ

አብዛኛው ተጠቃሚ የዲሽ ማስቀመጫው ጣውላ ስለሆነ ፀሐይና ዝናብ ሲፈራረቅበት ይበሰብሳል። ማያያዣ ሚስማሮች መልቀቅና መነቃነቅ
ከጊዜ በኋላ ጣውላው ሲበሰብስ ሚስማሮች እየለቀቁ ሲሄዱ ዲሹ በትንሽ ነፋስ መጫወት ይጀምራል ስክራች ያደርጋል ስለዚህ የበሠበሠ ከሆነ አይታችሁ መቀየር።

🎛 የስዊች መድከም/አለመስራት

- Switch ለዝናብ ውሀ ከተጋለጡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ይበላሻሉ።ስለዚህ ዝናብ በማያገኛቸው ቦታ ማድረግ ይመከራል።

👨🏽‍🔧 የዲሽ ባለሙያው ክህሎት ችግር

-አንዳንድ ባለሙያዎች ለስራው ጀማሪዎች በመሆናቸው ምክንያት በትክክል Quality ላይመጣላቸው ይችላል። ትክክለኛ ባለሙያ ማግኘታችሁን ማወቅ አለባችሁ።

👩🏽‍💻 የተጠቃሚው ስህተት

- በተለይ እዚህ ላይ ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው ችግር ከሪሲቨሩ ጀርባ የሚሰካውን ኮኔክተር መነካካትና የአሉሚኒየሙን ከቀጫጭን ሽቦዎች ከመዳቡ ወፍራም ሽቦ ጋር ማገናኘት። ይህም እንዳይፈጠር በፕላስተር በማስያዝ እንዳይነቀል ወይም እንዳይገናኙ ማድረግ ትችላላችሁ።

👦🏽 ህፃናት Menu ውስጥ በመግባት የማይነካኩ Settingኦችን የመነካካት ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ስለሆነም አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ውስጥ እንዳይገቡ setting ዎችን በpassword መቆለፍ መፍትሄ ሊሆን ይችላል።


ስለዚህ አላስፈላጊ ወጪ በየጊዜው ላለማውጣት እነኚህን ነገሮች በደንብ ተጠንቀቁ።
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። አሁንም የአዳዲስ ቪዲዮዎችን እያዘጋጀሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረህ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶችሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
@MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።
የlaptop ኮምፒዩተሮች CPU ሲያሜ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡
ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ እናወዳድራለን፡፡ ከዛሬ በኃላ ግን በትክክለኛው ስያሜ እንገመግማለን፡፡

❖በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?
እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡

🖱የኮምፒዩተሮቻችን CPU ስም እነዚህም ፊደላት ከያዘ፡

“K” – Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር የሚደረግ CPU ናቸው፡፡
ለምሳሌ Core i7-6700k እና Core i7-5820k ባሉ የሞዴል ቁጥር መጨረሻ ላይ unlocked(ያልተቆለፈ) ስለሆሀን Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) የተሠሩ ናቸው ፡፡ ይህ ማለት Unloc Processors ከፋብሪካ ዋና ፍጥነቶች በበለጠ ፍጥነት ከመጠን በላይ ሊጫኑ ይችላሉ ፡፡ የተቆለፉ ማቀነባበሪያዎች (Processors) ከመጠን በላይ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) አይችሉም።
ስለዚህ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ አምብዛም ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core i5-8600K

“H” – High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው CPU ናቸው።

“Q” – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል CPU ናቸው፡፡

🖱በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች ወስጥ አንዱ ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core i7-7700HQ

”M” – Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) የደረጋል፡፡

“Y” - Extremely low Power

“U” – Ultra low Power

ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core i5-7200U
ብዙ ሰዉ የማያዉቃቸው የጂኤስኤም ሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች!
1. ስልክዎ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ!
ወደ *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ!
ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0910654321 ከሆነ ወደ *21*091065432# ይደውሉ
ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! ከላይ የተገለጸው በ900 ቦታ የፈለጉት
ሌላ ትክክለኛ የስልክ ቁጥር ያልሆነም ማድረግ ይችላሉ! *21*666# ብለው
እንዳይደዉሉ!
➜ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ለማድረግ ሲልጉ
*21*0144123456# በ0144123456 ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ
ስልክ ቁጥር ያስገቡ
ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ
ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል
*#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ
ይሰጠናል
2. ስልክዎ ብዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *67*የፈለጉትቁጥር# ብለው
ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ
3. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ!
ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ
4. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ
*62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ!
5. ኮል ወይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል
ወይቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮልወይቲንግ አክቲቬት
መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል
💠System32 ምንድን ነው?

System32 ፎለደር ሆኖ፣ ከ Windows 2000 ጀምሮ በእያንዳንዱ Windows ቨርዥኖች ላይ ተካቷል። የሚገኘውም በ C:\Windows\System32 ሲሆን እና Windows ስራውን በትክክል እንዲያከናውን የሚያስችሉ ሁሉንም ፋይሎች፤ ፎልደሮችን በውስጡ አካቷል።
System32 በጣም ብዙ ፋይሎችን ነው የያዘው፣ እያንዳዳቸው ምን እንደሚሰሩ ለማየት ይሄን ፎረም ሊንክ ተጭነህ ማየት ትችላለህ፣ Symantec's forums።
በአጠቃላይ የSystem32 ፋይሎች በሁለት መክፈል እንችላለን:

💠DLL(Dynamic Link Library) ፋይሎች:-

የተለያዩ ፕሮግራሞች የ Windows ክፍልን አክሰስ ማድረግ እንዲችሉ መንገዱን ይከፍቱላቸዋል እና በዛው የተሰጣቸውን task ያከናውናሉ። ምሳሌ፣ አንዱ የ DDL ፋይል ኮምፒውተሩ ሙዚቃ እንዲያጫውት ሲያደርግ፣ ሌላኛው ደሞ automatic Windows Updates ይሆናል የሚያከናውነው።
ብዙዎቹ DDL የሚጀምሩት ኮምፒተርህን ስታስነሳው ነው። Windows ያለነርሱ መነሳት አይችልም፣ ለዛ ነው የ DDL errors ማስተካከል እንዲሁ ቀላል የማይሆነው!

💠EXE(Executable) ፋይሎች:-

እነዚህ ፋይሎች፣ የሶፍትዌር መተግበሪያና utilities ችን የያዘ ነው። የተለያዩ ሶፍትዌሮችን፣ እንበልና Chrome ወይም Word ን ስትከፍት በተመሳሳይ የነርሱን Executable ፋይላቸውን ነው የምታስጀምረው። ግን የ System32 EXE ፋይሎች ከዛም በላይ ናቸው፣ ለ Task Manager ወሳኝ የሆነው ስለ winlogon.exe ማንሳት እንችላለን፣ ያለዚህ ፋይል ወደ ኮምፒተርህ sign in ብለህ እራሱ መግባት አትችልም!

💠 System32 ፎልደርን ባጠፋውስ?

ሲጀምር ሲስተሙ እንዲሁ በቀላሉ System32 ን እንድታጠፋ አይፈቅድልህም፣ Administrative privilege ይጠይቃል። Admin ብትሆን እራሱ System32 ፎለደር በአንዴ ማጥፋት አትችልም፣ ምክንያቱም በ System32 ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞች በስተዃላ እየሮጡ ስለሆነ። ያለው አማራጭ ፎልደሩ ውስጥ ገብተህ አንድ በአንድ መደለት ነው። ሙሉ ፋይሎችን በዚህ መንገድ ካጠፋሃቸው በዃላ ኮምፒተርህ ያለተለመደ ባህሪ ማሳየት ይጀምራል:
💎 መንቀራፈፍ
💎 መፍዘዝ | መደንዘዝ
💎 በመጨረሻም ከነአካቴው ለምትሰጠው ትዕዛዝ መልስ መስጠት ያቆማል፣ shutdown ብትለው እራሱ ምላሽ የለም። እንደምንም hard shutdown(shutdown በተንን ለተወሰኑ ሰከንዶች በመያዝ) አድርገህ ዘጋኸው፣ ግን እስከ ወዲያኛው ነበር የዘጋኸው(መልሰህ ማስነሳት አትችልም)። System restoreማለትም አትችልም(የቱን ፋይል? system32 ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ፋይሎችኮ አጥፍታቸዋል)።

የመጨረሻ መፍትሄ፣ እንደ አዲስ Windows OS መጫን!
ለIT, Computer Science እንዲሁም ተያያዥ ትምህርቶች የመጀመሪያ ዲግሪ የመመረቂያ ፕሮጀክት Documentation ከፈለጋችሁ 👇👇👇
@EthiopiaDigitalLibrary
ማግኘት ይችላሉ
🍡የዘመናዊ ኮምፒዉተር አፈጣጠርና እድገት አጭር ታሪክ

🍢1950ዎቹ - በ "ቫኪዩም ቲዩብ" ብቻ ይሰሩ የነበሩት ኮምፒዉተሮች መጠናቸዉ የአንድ ቤት መጠን እስኪያክል ድረስ እጅግ ግዙፍ የነበሩ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ እጅግ ቀርፍፍ ነበሩ። በወቅቱ እነዚህን ኮምፒዉተሮች በብቸኝነት ይጠቀምባቸዉ የነበረዉ የአሜሪካ ሚሊቴሪ ተቋም ሲሆን ዋጋቸዉም የትም የሌለ ነበር።

🍢1960ዎቹ - በትራንዚስተሮች መፈጠር የተነሳ ቀርፍፍዉን የ"ቫኪዩም ቲዩብን" አሰራርን በመቀየር የኮምፒዉተሮች የአካል መጠን መቀነስ ሲቻል ብቃታቸዉንም ማሻሻል ተቻለ። በዚህ ወቅት ነበር ሜይንፍሬም (mainframe) የተባሉ ፈጣንና ወድ ኮምፒዉተሮች ተፈጥረዉ ከማሊቴሪና የመንግስት ተቋም አልፎ ለግል ድርጅቶች ጥቅም መዋል የጀመሩት።

🍢1970ዎቹ - በመቶዎች የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮችን ያካተተ ኢንቴግሬትድ ሰርኪዩት "Intergrated Circute Board" አንድ ክፍልን ሊሞላ የሚችል መጠን ያለዉን የሜይንፍሬም ኮምፒዉተር አሳንሶ በጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ ኮምፒዉተር "Desktop" እንዲፈጠር አስቻለ።

🍢1980ዎቹ - በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮች እጅግ በጣም ትኝሽ መጠን ባለዉ የኮምፒዉተር ቺፕ ዉስጥ ህያዉ መሆን የኮምፒዉተር በጣም አንሶ በአንዲት ቦርሳ ዉስጥ የሚገባና ከድርጅት አልፎ ለግል ጥቅም መዋል የሚችልበት "Personal Computer (PC)" ዘመን ተወለደ። ኮምፒዉተሮች ጠረጴዛ ላይ ከመቀመጥ አልፈዉ ጭን ላይ የሚቀመጡበትን መጠን ይዘዉ "laptop" በሚል ስያሜ ብቅ አለ።

🍢1990ዎቹ - የኢንተርንት መወለድ ኮምፒዉተሮች እርስ በእርሳቸዉ እና በሌላ ቦታ ከሚገኝ ከፍተኛ አቅምና የመረጃ ብዛት ያለዉ የኮምፒዉተር ስብስብ "datacenter" ጋር ተገናኝተዉ ከዚህ ቀደም በራሳቸዉ አቅም ብቻ ከሚሰጡት አገልግሎት እጅግ የላቀ ጥቅምን በፍጥነት መስጠት እንዲችሉ አደረገ።

🍢2000ዎቹ - ለእጃችን መዳፍ እንኳን የማይሞሉ፣ ነገር ግን ብቃታቸዉ ከአንድ መጠኑ ከፍ ካለና ምርጥ ከሚባል ኮምፒዉተር ያልተናነሰ ተግባር ማከናወን የሚችሉ እንደ ረቀቀ ስልክ (Smartphone) ያሉ ተንቀሳቃሽ ቁሶች (mobile devices) በስራ ላይ ዋሉ። ከስልኮችም አልፈዉ ታብሌቶቻችን፣ ሰዓቶቻችን፣ የቤት ቁሶቻችን፣ መኪናዎቻችን እና ልብሶቻችን ሳይቀሩ የኮምፒዉቲንግ ብቃት እየተካተተላቸዉ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ ይህ ዘመን አብሮን ባለ ኮምፒዉተር ላይ ብቻ ከመደገፍ ይልቅ እንደ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ (Cloud computing) እና የመሴሰሉት የተራቀቁ በኢንተርኔት ተገናኝተዉ መሰራት የሚችሉ እና ከእኛ ርቀዉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተበታትነዉ በሚገኙ እጆግ ፈጣን ኮምፒዉተሮች አማካኝነት በርካታ ተግባር ማከናወን ተቻለ። ቀደም ሲል እንደተጠቀሰዉ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ ማለት የኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች ሶፍትዌርኝ፣ ሃርድዌርን፣ መረጃን አና የተለያዩ ዲጂታል አሠራሮችን በራሳቸዉ ኮምፒዉተር ላይ ከመጫን ይልቅ ካሉበት ሰርቨሮች በኢንተርኔት አማካኝነት በየትኛዉም ጊዜና ቦታ ልክ መቦራትና ዉሃ ቤታችን ድረስ እንደሚመጣዉ ከአገለግሎት ሰጪዎች ላይ በሚፈልጉት መጠን መጠቀም የሚያስችል አሠራር ነዉ።

ይህ ሁሉ ፈጽሞ የበቃ በማይመስልበት ሁኔታ የኮምፒዉተር እድገትና ፍጥነት ሩጫዉን ቀጥሏል። ከላይ የተጠቀሰዉን አስደናቂ የኮምፒዉተር የለዉጥ እድገት ህያዉ ያደረገልን የMoore's Law ወደ ፍጻሜ እየመጣ ያለ ይመስላል።
ምክንያቱም የትራንዚስተሮች እጅግ አናሳ በሆነ መጠንና በጣም በተጠቀጠቀ ሁኔታ በአነስተኛ ቦታ ላይ እንዲያርፉ የሚደረግበት የቺፕ አሠራር የመጨረሻ ገደቡና ጥጉ ላይ እየደረሰ ስለመጣ ነዉ። አንድን ትራንዚስተር ምንም ያህል እናሳንሰዉ ብንል ከአቶሚክ መጠን በታች ልናደርገዉ አንችልም። ይህ ሂደት ወደ ፍጻሜዉ እየተቃረበ የመምጤቱን ጉዴይ ባለሞያዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና አምራቾችም ይስማሙበታል። የትንቢቱ ባለቤት ጎርደን ሙር እራሱ በ2015 ዓ.ም. በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ከ50 ዓመታት በፊት የተነበየዉ Moore's Law ማክተማያዉ እየተቃረበ እንደመጣ ጠቁሟል።

ኮምፒዉተር እስከዛሬ በዚህ አይነት የረቀቀ የእድገት ሂደት ዉስጥ ካለፈ፣ "ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?" የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮ ይመጣል።

🍢 "ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?"

በእርግጥ ቀጣዩቹ ኮምፒዉተሮች ምን አይነት ይሆኑ ይሆን? የወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች በጨረር፣ በኳንተም የፊዚክስ ህግ እና በሰዉነታችን ዉስጥ በሚገኙ በዲኤንኤ አማካኝነት የሚሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም በማንኛዉም ቁስ ላይ ተለጥፈዉ የሚገኙ፣ ወይም ደግሞ የራሳችን ኮምፒዉተር ሳያስፈልገን በሌላ ቦታ ተቀምጠዉ በኢንተርኔት አማካኝነት ያላቸዉን አቅም ሙሉ በሙሉ ከፈለግነዉ ቦታ ሆነን መጠቀም የምንችልባቸዉ አይነቶችም ሊሆኑ ይችላሉ።

የፋይበር ኦፕቲክስ "Finer-optic" ወይንም በጨረር አማካኝነት መረጃን ከአንድ ኮምፒዉተር ወደ ሌላዉ በፈጣን ሁኔታ በማስተላለፉ አሰራር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በፋይበር ኦፕታክስ የሚተላለፉ መረጃዎች በኤሌትሪክ ሽቦ ዉስጥ ከሚተላለፉት ፍጥነታቸዉ በእጅጉ የተሻለ ሲሆን፣ በተጨማሪም እንደ ኤሌክትሮማግኔቲክ ያሉ የተለያዩ ጣልቃ ገብ ግብዓቶች አሠራሩን አያደናቅፉትም ። ታድያ ለምን ከኤሌትሪክ ትራንዚስተር ይልቅ በጨረር የሚሰራ ኮምፒዉተር መስራት አይቻልም? ይህን ማድረግ ከተቻለ የኮምፒዉተሮችን የዉስጥ የመረጃ አቀማመር አቅም እጅጉን እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል። ምንም እንኳን ተመራማሪዎች በዚህ ዙርያ ተስፋ ሰጪ የሙከራ ስራዎች ቢያከናዉኑም መጠኑ ያነሰና በብዛት ተመርቶ በኮምፒዉተሮች ዉስጥ ሊገጠም የሚችልን በጨረር የሚሠሩ ቺፕ ህያዉ ለማድረግ ሙሉ ስኬትን እስከአሁን አላገኙም።

በጨረር አማካኝነት የሚሰሩ ኮምፒዉተሮችን ለመፍጠር በሚደረገዉ ምርምር የኢትዮጵያዉ ዶክተር ሰለሞን አስፍ እጅ አለበት። ዶክተር ሰለሞን የበርካታ ፈጠራ ስራዎች ባለቤት ሲሆን በዋናነት የሚታወቅበት የፈጠራ ስራዉ በተለመደዉ አሠራር በኤሌትሪክ ከሚሰሩ ትራንዚስተሮች ይልቅ ኮምፒዉተሮች በብርሃን ጨረር (optical pulse) አማካኝነት መረጃን ለማስላት የሚችሉበትን ሙከራ ያደረገበት የምርምር ስራዉ ነዉ። ይህ ግኝት ለወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች አሁን ካሉት ማሽኖች እስከ አንድ ሺህ እጥፍ ፍጥነት እንደሚሰጣቸዉ ሲጠበቅ፣ የኤሌክትሪክ ፍጆታንም በእጅጉ ይቆጥባል ተብሏል። የዶክተር ሰለሞን ዋና ግኝት ፎቶዲቴክተር (photodetector) የሚባሉትና የብርሃን ጨረር መልዕክትን (optical signals) አጉልተዉ የሚያስተላልፉ ቁሶች (በሞያዊ አጠራራቸዉ "amplifiers") እንዴት አድርገዉ መልዕክትን ለማይክሮፕሮሰሰሮች በሚገባ መንገድ በማስተላለፍ ጨረር መልዕክቶችን ወደ ኤሌክትሪክ መልዕክት (electrical signals) በመቀየር ለኮምፒዉተር አሰራር ጥቅም እንዲዉሉ ማድረግ ነዉ።
SPSS Presentation Slide
Note on Data Analysis
በቅድሚያ እነዚህም መረጃዎችን በማውረድ እንድታንቧቸው እጋብዛችኋለሁ።
ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ላይ ቢገቡ ያገኙታል።
👇👇👇👇👇👇
@EthiopiaDigitalLibrary
@EthiopiaDigitalLibrary
@EthiopiaDigitalLibrary
የSPSS Videos እየተዘጋጀ ስለሆነ በትእግስት እንድትጠባበቁኝ ስል እጠይቃችኋለሁ።
ሙሀመድ ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ
#ያውቁትን #ማሳወቅ
#የተማሩትን #ማስተማር
#ብልህነት #ነው
ስለ #ኤሌክትሪካል_ኢንጅነሪንግ ወይም #የኤሌክትሪካል_ቴክኖሎጂ ማወቅ ከፈለጉ ይህን የቴሌግራም #ቻናል መከታተል አልብዎት❗️እኔ በግሌ ወድጀዋለሁ❗️
=========================
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@electrical_tech_nology
@electrical_tech_nology
@electrical_tech_nology
@electrical_tech_nology
@electrical_tech_nology
ስለ VLC Media (ቪዲዮ) ማጫወቻ #ስውር እና #ድብቅ 5 ነገሮች!!
1. የኮምፒውተሮን ዴስክቶፕ መቀረፅ
የኮምፒውተሮን ዴስክቶፕ በመቅረፅ እንደ screen recorder ያገለግለናል፡፡ይህን ለማከናወን VLCን በመክፈት Media ከዛን Convert/Save በመንካት ከሚመጣው ሳጥን Capture Device ታብን በመምረጥ Capture mode ሳጥን ውስጥ ካሉት ዝርዝር ውስጥ ዴስክቶፕ (Desktop)የሚለውን ምርጫ በማድግ መቅዳት ይቻላል፡፡ desired frame rate for the capture ከሚለው ፍሬም ሬቱን 15 በማድረግ ወይም ደግሞ 30 ለፈጣን እንቅስቃሴ አድርገን መቅረፅ እንችላለን፡፡
2. የቪዲዮ ፋይል ፎርማት ወይም ይዘትን መቀየር Convert Video
Media የሚለውን ሜኑ በመምረጥ ካሉት ዝርዝሮች Convert/Save ላይ አድርገን file ታብ ላይ Add የሚለውን በመምረጥ የምንፈልገውን የቪዲዮ ፋይል አስገብተን ወደ ምንፈልገው file format መቀየር እንችላለን፡፡
3. የ YouTube ቪዲዮችን ማጫወት እና ዳውንሎድ ማድረግ (Play and (Safely) Download YouTube Videos)
ይህ ሲባል በቀጥታ የYouTubeን ቪዲዮ ዳውንሎድ ማድረግ ሳይሆን በቅድሚያ ከ YouTube ሊንኩን ኮፒ አድርገን VLC ላይ File ውስጥ Open Network Stream በመክፈት ቪዲዮውን ማጫወት ይቻላል፡፡
ይህንን ቪዲዮ ዳውንሎድ ለማድረግ ደግሞ እየተጫተ Tools ውስጥ በመግባት Codec Information የሚል ዝርዝር በመጫን ከሚከፈተው ቦክስ ወይም ዲያሎግ ከስር Location box ውስጥ ያለውን ሊንክ ኮፒ በማድረግ የሚንጠቀመውን ብሮውሰር (browser) ክሮም ወይም ሞዚላ ላይ እንዲሁም ላይቭ እንድንሰማ አገልግሎትን ይሰጠናል፡፡ View ውስጥ በመግባት Playlist የሚለውን ዝርዝር እንነካለን፤ በመቀጠልም ወደ ታች ስንወርድ Podcasts በመንካት የ “+” ምልክት በመጫን የምንፈልገውን ሊንክ ማስገባት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ This American Life , TED Radio Hour የመሳሰሉ አሉ ወይም ይህን ሊነክ ተጭነው የማያቋርጥ ሙዚቃዎችን ያዳምጡ፡፡
ተከታታዮቻችን እነዚህ የVLC # ስውር እና # ድብቅ 5 ነገሮች ብለን የቀረቡት ነጥቦች ምርጦቹን ሲሆን VLC ብዙ #ስውር እና #ድብቅ የሆኑ ጥሩ ፊቸሮች (features) አሉት፡፡ለዛሬ እናነተ የምታውቋቸውን ስውር እና ድብቅ ነገሮች በኮሜንት ላይ ያካፍሉን፡፡
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በኮምፒውተራችን ላይ hidden የሆኑ ፉይሎች ለማግኘት እንዳስቀመጥናቸው እርግጠኛ የሆናቸው (ፎቶውን ይመልከቱ)
ፋይሎችእና ፎልደሮች ተደብቀው ነገር ግን ከእይታችን ሊሰወሩ ይችላሉ፡፡ ይህ በሚያጋጥመን ጊዜ ኮምፒውተራችን እንዲያሳየን የሚደርገውን ቅንብር በማስተካከል እንድንመለከት ያስችለናል ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቅደም ተከተል የተቀመጡትንመንገዶች በመከተል የኮምፒውተርዎን ቅንብር ያስተካክሉ፡ –
1. Start የሚለው ምልክት በመጀመርሪያ እንመርጣለን
2 በመቀጠል ኮንትሮል ፓናል (control panel)
3. ከሚቀርቡለን ምርጫ ውስጥ Appearance and
Personalizationየሚለው ላይ ክሊክ እናደርጋለን
4. ቪው (view) የሚለውን እንጫናለን ከዚያ አድቫንስድ
ሴቲንግ (advancing setting) እናገኛለን
5. በመጨረሻም Show hidden files, folders, anddrives ክሊክ ካደረግን በኋላ ok የሚለውን መርጠን እናጠናቅቃለን፡፡ Or
start >run >cmd> f:attrib -r -s -h /s /d we can use this
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም #Subscribe በማድረህ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው