Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 መድረሱን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ
********
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 89 ሰዎች ውስጥ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በመረጋገጡ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 እንደደረሰ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት፤ ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሦስቱም ግለሰቦች የውጭ አገሮች ጉዞ ታሪክ ያላቸውና ሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው።
''የመጀመሪያው ግለሰብ የ29 ዓመት ወንድ ሲሆን መጋቢት 10 ቀን ከዱባይ የመጣና በበሽታ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው ነው'' ብለዋል።
ሁለተኛው የ34 ዓመት ወንድ መጋቢት 23 ከዱባይ የመጣና በማቆያ የነበረና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው መሆኑ ታውቋል።
ሶስተኛዋ የ35 ዓመት ሴት በመጋቢት 25 ከስውዲን የመጣችና በማቆያ የነበረች መሆኗን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ አዛውንት አገግመዋል።
ዛሬ ከቫይረሱ ያገገሙትን የ85 አዛውንት ጨምሮ በድምሩ አራት ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ኢዜአ
በተደጋጋሚ የምንጠቀማቸው መሰረታዊ የኮምፒውተር አቋራጭ ቁልፎች
⓵ Ctrl+O ➤Open a file in current software program
⓶ Ctrl+A ➤Select all text.
⓷ Ctrl+B ➤Change selected text to be Bold
⓸ Ctrl+I ➤Change selected text to be in Italics
⓹ Ctrl+U ➤Change selected text to be Underlined
⓺ Ctrl+F ➤ Open find window for current document or window.
⓻ Ctrl+S ➤Save current document file.
⓼ Ctrl+XCut âž¤selected item.
⓽ Ctrl+C ➤Copy selected item.
⓾ Ctrl+V ➤Paste
⓫ Ctrl+Y ➤Redo last action
⓬ Ctrl+Z ➤Undo last action
⓭ Ctrl+K ➤Insert hyperlink for selected text
⓮ Ctrl+P ➤Print the current page or document.
⓯ Home➤Goes to beginning of current line.
⓰ Ctrl+Home ➤Goes to beginning of document.
⓱ End ➤Goes to end of current line.
⓲ Ctrl+End ➤Goes to end of document.
⓳ Shift+Home ➤Highlights from current position to beginning of line.
⓴ Shift+End ➤Highlights from current position to end of line.
21 Ctrl+Left ➤arrowMoves one word to the left at a time.
22 Ctrl+Right arrow➤Moves one word to the right at a time.
23 Ctrl+Esc ➤Opens the START menu
24 Ctrl+Shift+Esc ➤Opens Windows Task Manager
25 Shift+Del ➤Permanent delete.
26 Ctrl+Ins ➤Copy selected item
27 Shift+Ins ➤Paste
28 Alt+Tab ➤Switch Windows
29 WinKey+Tab ➤Switch Windows
30 Alt+F4 ➤Close the currently active program
31 Alt+Enter ➤Open the Properties for the selected item (file, folder, shortcut, etc.)
32 Alt+F ➤File menu options in current program.
33 Alt+E ➤Edit options in current program
34 Alt+Tab ➤Switch between open programs
35 F1➤ Universal Help in almost every Windows program.
36 F2 ➤Rename a selected file
37 F5 ➤Refresh the current program window
37 Ctrl+N ➤Create a new or blank document in some software programs.
══════❁✿❁ ══════
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
❤1
እነሆ ሌላ የኔ ትውልድ ጀግና!
በኮሮና ለተያዙ ወገኖቻችን የመተንፈሻ ማገዣ ማሽን (Ventilator) ለመሥራት ዝግጁ ነኝ ይለናል። ኢዘዲን ካሚል ይባላል! ገና የ19 ዓመት ተማሪ ነው። 28 የፈጠራ ሥራዎች አሉት! በ13ቱ ዓለም አቀፍ ፓተንት አገኝቶባቸዋል። በፎቶው ላይ በቀኝ በኩል የምታዩት የቅርብ ጊዜ ፈጠራው ከሰሞኑ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይሆን ዘንድ በእጅ መክፈትና መዝጋት አልያም መጫንም ሳይጠይቅ፣ ሳሙና ጨምሮ እጅን የሚያስታጥብ መሳሪያ ነው። በሚያስደስት መልኩ ድጋፍ አግኝቶ በብዛት እየተመረተ፣ በተለይም በወልቂጤ ሪፈራል ሆስፒታልና በከተማዋ እየተሰራጨ እንደሆነም ነግሮኛል። ኢትዮጵያ ማህጸነ ለምለም እንደሆነች ምስክር የሆኑ፣ በክፉ ቀን ለወገናቸው የሚደርሱ ብዙ ወጣቶችን ገና እናያለን።
ታዲያ ይህ ባለ ምጡቅ አእምሮ ለጋ ወጣት የመተንፈሻ ማገዣ መሳሪያ (Ventilator) ለመሥራት የሚያስፈልጉት ሁለት ትልልቅ ማሽኖች ብቻ እንደሆኑ ነግሮኛል። እንግዲህ ሁላችንም ልንተባበረው ይገባል።
እንዴት ላግዘው? ካላችሁኝ
አንደኛ - ይሄን መልእክት ሼር በማድረግና በመደዋወል ሌሎች አቅም ያላቸው ሰዎች ጋር አዳርሱልን።
ሁለተኛ - አቅሙ ያላችሁ ሰዎች እየደወላችሁ በምትችሉት እንድታግዙት ይሁን - 0977448535፤ በተለይ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ ባለሐብቶችና የባዮ-ሜዲካል ኢንጂነሪንግ ባለሙያዎች ሊረባረቡ ይገባል።
ሦስተኛ - የሚዲያ ባለሙያዎች እቃዎቹ እንዲመረቱና እንዲዳረሱ በቂ ሽፋን እንድትሰጡት እጠቁማለሁ።
# የሚሠሩእጆች # የኔትውልድ
(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 5 ተጨማሪ ሰዎች መገኘታቸው ተገለፀ
******
አምስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የዛሬዎቹን ጨምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 43 መድረሱን ኢንስቲትዩቱ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የታማሚዎች ሁኔታ ፦

- ሶስቱ ታማሚዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። አንደኛው ታማሚ ኤርትራዊ ነው። ሌላኛው ታማሚ ደግሞ ሊቢያዊ ነው።

- አንደኛው ታማሚ የአዲስ አበባ ነዋሪ የ26 ዓመት ወንድ ሲሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪኩ እንደሚያሳየው ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

- ሁለተኛው የ60 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን የኮንጎ የጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆይ ውስጥ የነበረ ነው።

- ሶስተኛው #ለጉብኝት አዲስ አበባ የመጣ የ45 ዓመት ወንድ ከካናዳ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

- አራተኛዋ ታማሚ የ27 ዓመት ሴት ስትሆን ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ሌስተር ሲቲ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች ናት።

- አምስተኛው ታማሚ የአዲስ አበባ ነዋሪ የ30 ዓመት ወንድ ሲሆን ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ነው።
# update_corona_virus_እሰከ_7 :00_ድረስ
# share
በዓለም በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ64 ሺህ በለጠ ፡፡ በፈረንጆቹ 2019 መገባደጃ ላይ በቻይና ውሃን ግዛት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የአለም ስጋት መሆኑን ቀጥሏል፡፡
እስከ 7:00 ሰዓት ድረስም በዓለም 1 ሚሊየን 205 ሺህ 825 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 64 ሺህ 978 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል 2 መቶ 47 ሺ 961 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡
አውሮፓዊቷ ሀገር ስፔን ደግሞ ጣልያንን በመብለጥ 126,168 ሰዎች ተጠቅተውባት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
አሜሪካ በሽታው ጠንቶባታል የተጠቂዎች እና ሟቾች ቁጥር በእጥፍ ሲጨምር ተጠቂዎች 311 ሺ አልፈዋል የሟቾቹም ቂጥር ወደ 9,000 እየተጠጋ ይገኛል፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች ተገኝተው ቁጥሩ 43 ደርሷል
በኮቪድ-19 ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበባቸው ሀገራት ዝርዝር ፦
• ጣልያን - 15,362
• ስፔን - 11,947
• ዩናይትድ ስቴትስ - 8,454
• ፈረንሳይ - 7,560
• ዩናይትድ ኪንግደም 4,313
• ኢራን - 3,452
• ቻይና - 3,326
• ኔዘርላንድ - 1,651
• ጀርመን - 1,395
• ቤልጂየም - 1,283
• ስዊዘርላንድ - 666
• ቱርክ - 501
• ብራዚል - 431
• ስውዲን - 391
• ፖርቹጋል - 266
• ካናዳ - 231
• ኢንዶኔዥያ - 191
★መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት like our page
★መረጃውን ከወደዱት ለሌሎች እንዲደርስ share
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ
*****
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህይወታቸውን ያጡት አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ ናቸው፡፡
ታማሚዋ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡
ይሁንእንጂ ከመጋቢት ታማሚዋ 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል፡፡
ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያነስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከልም የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስበዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሁለተኛ ሰው መሞቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አሳውቀዋል !
በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሞት መመዝገቡን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በኢትዮጵያ በዛሬው እለት ሁለተኛ ሰው ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለፁት፥ ታማሚው በለይቶ ማቆያ ከመጋቢት 24 ጀምሮ ህክምና ሲደረግላቸው የነበርና ከገባበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ላይ የነበረ ነው።
ታማሚው ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ህይወቱ እንዳለፈም ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ በዚህም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በራሳቸውና በጤና ሚንስቴር ስም በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የመጀመረያው ሞት ዛሬ ጥዋት ላይ የተመዘገበ ሲሆን፥ ህይወታቸውን ያጡት የ60 ዓመት ታማሚዋ ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ ነበሩ።
በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።
ቀሪዎቹ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ማኅበረሰቦች ናቸው ተብለው የተመረመሩ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
ዛሬ በቫይረሱ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።
ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ሕክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ሕሙማን ማቆያ ይገኛሉ።
ምንጭ፦ ኢዜአ
በኢትዮጵያ አንድ የ9 ወር ህጻንን ጨምሮ ተጨማሪ 8 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተያዙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 264 ሰዎች ውስጥ 8 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንድ የዘጠኝ ወር ህጻን የተያዘ ሲሆን እናቱም ቫይረሱ ተገኝቶባታል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል አንዱ ኤርትራዊ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 52 አድርሶታል ነው ያሉት።
በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠ 8 ሰዎች መካከል አምስቱ ከዱባይ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።
ከእነዚህም ውስጥ አንድ የዘጠኝ ወር ህጻንና ወላጅ እናቱ ይገኙበታል።
አንድ የ25 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ከታይላንድ መጥታ በለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች ሲሆን፤ አንድ የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን የንክኪ ሁኔታውም በመጣራት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ወጣቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።
ሌላኛዋ የ30 ዓመት ሴት ኤርትራዊት ስትሆን ከእንግሊዝ ለንደን መጥታ በአዲስ አበባ በለይቶ ማቆያ ክትትል እያደረገች የምትገኝ ናት።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ አቅም እየጨመረ መጣቱንም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።
አራቱ ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
የኮሮና ቫይረስ ዋነኛው የመተላለፊያ መንገዱ በአፋችንና በአፋንጫችን በሚወጡ ፈሳሾች/Drop/ አማካኝነት ነው።
ነገር ግን አንደ Disease
Control and Prevention (CDC) ገለፃ በአፋችንና በአፋንጫችን ከሚወጡት ፈሳሾች ጋር ባይወዳደሩም በመጠኑም ቢሆን እቃዎች ላይ በመቆየት ይተላለፋሉ ብሏል።
ምንም እንኳ ግልፅ የሆነ ጥናት እስካሁን ባይገኝም።
ኮሮና ቫይረስ በዕቃዎች ላይ የሚቆይበት ጊዜ እንደ አየር ፀባይ የሚወሰን ሲሆን የአየር ፀባይ ከ5°C-11°C ባለው የሙቀት መጠን ለይ ቫይረሱ በከፋተኛ ሁኔታ ይሰራጫል። የመገልገያ ቁሳቁሶች ላይም የሚቆይበት ጊዜ ከፍ ይላል።
አንዳንድ ጥናቶች እንደጠቆሙት ከፍተኛ ሙቀት ማለትም ከ30°C እና ከዛ በላይ በሆነ የአየር ፀባይ ላይ COVID -19 ከሰዎች ላይ ካልሆነ በቀር አየር ላይና እቃዎች ላይ ተቋቁሞ ለመቆየት ይቸገራል ይላሉ።
እንደ National Institute of Allergy and
Infectious Disease (NIAID) ጥናት COVID-19 እቃዎች ላይ የሚቆይበት ጊዜ እንደ አየር ፀባዩ ሁኔታ እንደሆነ ገልጾ
ከ18°C-25°C ባለው ሙቀት ላይ ኮሮና ቫይረስ እቃዎች ላይ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቋይ እንደሚከተለው አስቀምጧል።
ምንጭ DR.FINOT
የቻይናዋ ውሃን ከተማ ከ76 ቀናት በኋላ ለእንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆናለች
*******
የኮሮና ወረርሽኝ መነሻ ናት በተባለችው የውሃን ከተማ የሚገኙ ሰዎች ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንቅስቃሴ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
ጤናማነታቸው የተረጋገጠና ይህንኑ የሚመሰክር አረንጓዴ ኩፖን ምልክት የያዙ ነዋሪዎቿ አሁን ወደየትም አገር መጓዝ ይችላሉ ተብሏል፡፡
የባቡር መንገዶቿ፤ የመኪና አውራ ጎዳናዎቿም ለመጀመርያ ጊዜ በሙሉ ኃይል ክፍት ሆነዋል፡፡
ባለስልጣናት ይህንን ሁኔታ እንደ ስኬት ሲቆጥሩት ነዋሪዎች ግን የተለያየ ልምድ የወሰዱበት እና በሰው ልጅ ታሪክ አከራካሪ ገደብ ሆኗል፡፡
የ11 ሚሊዮን ቻይናዊያን መኖርያ የሆነችው ውሃን ለ11 ሳምንታት ሙሉ በሙሉ ተዘግታ፤ እንቅስቃሴዋ ታግዶ ከርማ ነበር፡፡
በቻይና ወረርሽኙ ከተነሳ ወዲህ 3300 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የሚበዙቱ የዚች ከተማ ነዋሪዎች እንደነበሩ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ቀን 30/07/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት
ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያውያን እየተመለከታችሁትና እየታዘባችሁት እንደሆነው ዓለም በአስቸጋሪ የፈተና ምእራፍ እያለፈች ነው፡፡ ዓለም ይሄንን መሰል ነገር ሲገጥማት ከመቶ ዓመት በኋላ የመጀመሪያ ነገር ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሮና (ኮቪድ -19) የዓለም ሁለንተናዊ ችግር ሆኖ ብቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ የመፍትሔ ርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ሕዝቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ፣ የሕክምና ተቋማት እንዲዘጋጁ፣ የመከላከያና የሕክምና መሣሪያዎች ከውጭ እንዲገቡ፣ የማቆያ ሥፍራዎች እንዲዘጋጁ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፤ አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች በቤት እንዲወሰኑ፣ ብዙ ሕዝብ ሊሰበሰብባቸው የሚችሉ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎታቸውን ሕዝብ ሊሰበሰብ በማይችልበት መንገድ እንዲከውኑ፣ በአብዛኛው ሥፍራዎች የሕዝብ ትራንስፖርት እንዲቋረጥ፣ ለአስቸጋሪ ጊዜ የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ሥራ እንዲሠራ ተደርጓል፡፡
መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ የሚከተለው ስትራቴጂ በመከላከል ላይ ያተኮረ ነው፡፡
1. ኅብረተሰቡን አስተባብሮ በባለሞያዎች ምክር መሠረት ለመከላከል መቻል
2. ከመከላከል ያለፈ ነገር ሲመጣ ለማከም የሚያስችሉ ዐቅሞችን ማዳበር፡፡
3. የከፋው ነገር ከመጣም አስቀድሞ በመዘጋጀት እንደየ አስፈላጊነቱ ተገቢ ውሳኔዎችን እያሳለፉ መሄድ፡፡
እስካሁንም በዚህ መንገድ ነው የተጓዝነው፡፡
አሁን ያሉን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በቫይረሱ የተያዙ ወገኖች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው፡፡ ይሄም በመሆኑ ሁላችንም ያለንን ዐቅም ሁሉ አስተባብረን ወገኖቻችንን ከዚህ ወረርሽኝ ለመከላከልና የታመሙትንም ለማዳን ማዋል አለብን፡፡ ያለንበት ጊዜ ሕዝብና ሀገርን ለማዳን ሲባል አስቸጋሪ የተባሉ ውሳኔዎችን መወሰን ያለብን ጊዜ ነው፡፡ ይህም ውሳኔ፣ እንደ ግለሰብ፣ እንደ ማኅበረሰብ፣ እንደ ተቋምና እንደ መንግሥት የሚወሰኑ ናቸው፡፡
ይህ ውሳኔ በዛሬው ትውልድ ላይ ብቻ የምንወስነው ውሳኔ አይደለም፡፡ በልጅ ልጆቻችን ላይ ጭምር የምንወስነው ነው፡፡ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ላይ የምንወስነው ብቻ አይደለም፤ በነገዋና በከነገ ወዲያዋ ኢትዮጵያ ላይ ጭምር የምንወስነው ውሳኔ ነው፡፡ የኛ የመሪዎቹ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋ ውሳኔ በታሪክ የሚመዘገብ ነው፡፡ ይሄንን አስቸጋሪ ጊዜ ልናልፈው የምንችለው በአካል ተራርቀን በመንፈስ ግን አንድ ሆነን ከቆምን ብቻ ነው፡፡ የያንዳንዳችን ሀብት የሁላችን፣ የእያንዳንዳችንም ችግር የሁላችን መሆን አለበት፡፡ አንዱ በልቶ ሌላው ተርቦ፣ አንዱ ሠርቶ ሌላው ሥራ አጥቶ፣ አንዱ መኖሪያ አግኝቶ ሌላው ውጭ አድሮ፣ አንዱ አትርፎ ሌላው ከሥሮ ይሄንን ችግር ለማለፍ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ይህ ችግር የመጣው በህልውናችን ላይ በመሆኑ፡፡ ይህ ችግር የተጋረጠው ሰው ሆኖ በመኖርና ባለመኖር ላይ በመሆኑ፡፡ መንግሥት ችግሩን በደረሰበት ልክ ለመቋቋም ተዘጋጅቷል፡፡ የምንወስዳቸው ውሳኔዎች ክብደት እንደ ችግሩ ክብደት የሚወሰን ነው፡፡ ታሪክ እዚህ አድርሶናል፡፡ ሀገርና ትውልድ በእጃችን ላይ ነው፡፡ በዚህ ዘመን በምንሠራው ሥራ ወይ እንመሰገናለን ወይ እንወቀሳለን፡፡ ከምንም በላይ ግን በጊዜውና በዐቅማችን ማድረግ ያለብንን ካላደረግን የበለጠ እንወቀሳለን፡፡ ይህ ደግሞ ሁላችንንም ኢትዮጵያውያንን የሚመለከት ነው፡፡ ከተረፍን አብረን ነው፡፡ ከከሠርንም አብረን ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣጡ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡ ይህም በሕገ መንግሥቱ ዐንቀጽ 93 መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ይሄንን መሳይ ዐዋጅ ብዙ ሀገሮች ካወጁ ሰንብተዋል፡፡ እኛ እስክንዘጋጅና ሁኔታው የግድ እስኪለን ጠብቀናል፡፡ ጊዜው ሲጠይቅ ግን ዐውጀናል፡፡ ሀገርን ለማዳንና ትውልድን ለመታደግ ከዚህ በላይ ልንወስን እንደምችልም መታወቅ አለበት፡፡ ዜጎቻችንም ከዚህ በላይ ግዴታቸውን ለመወጣት ወገባቸውን አጥብቀው መጠበቅ አለባቸው፡፡
በዚህ ወቅት ሁላችሁም ችግሩን ለመቋቋም ከሚሠሩት አካላት ጋር አብራችሁ እንድትቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ችግሩን ለማባባስ የሚሠሩ ካሉ ግን፣ በሕጉ መሠረት የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን፡፡
ወገኖቼ፤
ኢትዮጵያውያን የሚያምርብን መረዳዳቱና መደጋጋፉ ነው፡፡ ድኾችን እንርዳ፡፡ በአካባቢያችን ላሉት ዐቅመ ደካሞች እንድረስላቸው፡፡ የቤት ተከራዮቻችንን ዕዳ እንካፈላቸው፡፡ ከቻልን አናስከፍላቸው፤ ካልቻልን ቅናሽ እናድርግላቸው፡፡ ያም ካልሆነ ይህ ጊዜ እስኪያልፍ እንታገሣቸው፡፡ በዚህ ወቅት ተከራዮችን ከቤት ማስወጣት ፈጣሪም፣ ታሪክም ሕግም ይቅር የማይሉት ወንጀል ነው፡፡ ማናችን አልፈን ማናችን እንደምንተርፍ ለማናውቅበት ጊዜ ከመተባበር የተሻለ መሻገሪያ የለንም፡፡ የግል ባለሀብቶች የሠራተኞቻቸው ሕይወት እንዲያስጨንቃቸው አደራ እላለሁ፡፡ መንግሥት የኢኮኖሚ ችግሮቻችንን ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ እየወሰነ አብሯችሁ እንደሚሆን በዚህ አጋጣሚ እገልጥላችኋለሁ፡፡
ለሌሎች ወገኖቻቸውና ለሀገራቸው ሲሉ ቤታቸውን፣ ሆቴላቸውን፣ አዳራሾቻቸውን፣ የእምነት ተቋሞቻቸውን፣ መኪኖቻቸውን፣ ገንዘባቸውንና እህላቸውን የሰጡ ዜጎቻችንን ስናይ ይሄንን አስቸጋሪ ወቅት ከፈጣሪ ጋር ሆነን ልናልፈው እንደምንችል ርግጠኞች እንሆናለን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከወገኖቻቸው መከራ ለማትረፍ የሚሽቀዳደሙ፣ ከመከራ እንኳን የማይማሩ ሰዎችን ስናይ መንገዱ ከባድ እንዳይሆንብን እንሠጋለን፡፡ በጎ አድራጊዎችን የምናመሰግነውን ያህል መንገዳችንን ይበልጥ ፈታኝ የሚያደርጉብንን ስግብግቦች ግን ለሕዝብና ለሀገር ስንል አስተማሪ የሆነ ቅጣት ለመቅጣት እንገደዳለን፡፡
የሕክምና ባለሞያዎቻችንን በሚቻለው ሁሉ እንርዳ፡፡ ያለ እነርሱ ግንባር ቀደምነት ትግሉን ልናሸንፍ አንችልም፡፡ የሕክምና ባለሞያዎችን ማክበር፣ ማመስገንና በጉዟቸው ሁሉ መተባበር ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል፡፡ ለሕክምና ባለሞያዎች ተገቢውን ሁሉ አለማድረግ እጅን በእጅ እንደመቁረጥ ነው፡፡ ከእነርሱ በተጨማሪ የመከላከያ አባላት፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የውኃ አቅርቦት እንዳይስተጓጎል የሚሠሩ ባለሞያዎች፣ የሚዲያ ባለሞያዎች፣ የመገናኛ መሥመሮቻችን ላይ 24 ሰዓት የሚያገለግሉ ዜጎች፣ እኛ ቤት እንድንውል እነርሱ ውጭ የሚውሉ ሠራተኞች ተገቢው ምስጋናና ድጋፍ ከቤተሰባቸውም፣ ከማኅበረሰባቸውም ያስፈልጋቸዋል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ አርሶ አደሮቻችን የበልግ ወቅት እንዳያልፍብን ራሳቸውን ከቫይረሱ እየተጠነቀቁ በምርት ሥራ ላይ ጠንክረው እንዲሳተፉ አደራ እላቸዋለሁ፡፡ ከቫይረሱ ባልተናነሰ የእርሻ ምርት መቀነስና የእርሻ ምርት አለመኖር ሀገራችንንና ሕዝቧን ይጎዳል፡፡ እናንተ ሀገር መጋቢዎች ስለሆናችሁ፣ እየተጠነቀቃችሁ ካለፈው የተሻለ ምርት ለማምረት ትጉ፡፡ መንግሥትም አስፈላጊውን ሁሉ ሞያዊና ድጋፍ ያደርግላችኋል፡፡
የኢንዱስትሪ ምርቶቻችንም ፈጽመው መቆም የለባቸውም፡፡ ለሠራተኞቻችን ሕይወት እየተጠነቀቅን፣ በወረርሽኙ ምክንያት የሚያጋጥመንን ተግዳሮት ሁሉ እየተቋቋምን በፋብሪካ ምርቶች ላይ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናድርግ፡፡ ከበተለይም ከውጭ የምናመጣቸውን ምርቶች ለመተካት ለሚደረገው ጥረት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላችሁ
ገልጥላችኋለሁ፡፡ በተለይ ግን በምርት ዝውውር ጊዜ ከፍተኛ የሆነውን የመጨረሻ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለአፍታም ቢሆን እንዳትዘነጉት ይሁን፡፡
ይህ ጊዜ ያልፋል፡፡ ሀገራችን ከዚህ የሚስተካከሉና ከዚህም የሚብሱ ፈተናዎችን አልፋለች፡፡ ዓለማችን በየዘመናቱ የከፉ ተግዳሮቶችን አልፋ ነው እዚህ ዘመን የደረሰችው፡፡
የሚሰጡንን መመሪያዎች በሚገባ እናክብር፣ የጤና ባለሞያዎች የሚሉንን ለሕይወታችን ስንል እንስማ፡፡ በኮሮና አይቀለድም፡፡ ጉዳዩ ከመኖርና ካለመኖር ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ይሄንን ፈተና ለማለፍ ባለ ሦስት መዓዝን ትብብር ያስፈልገናል፡፡ ወደ ጎን እኛ እርስ በርሳችን፡፡ እያንዳንዳችን ደግሞ ከፈጣሪያችን ጋር፡፡ እኔ ከሌላው ወገኔ ጋር፣ ሌላው ወገኔ ከእኔ ጋር፣ እኔና ሌላው ወገኔ ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት መሥመር መቼም መቋረጥ የለበትም፡፡
በርትተንና ተረባርበን የሚጠበቅብንን እናድርግ፣ ጸንተንና በተሰበረ ልብ ሆነን ወፈደ ፈጣሪ እንለምን፡፡ ፈጣሪ ከእኛ ጋር ነው፡፡ መከራውን ያቀልልናል፤ ፈተናውን ያሳልፈናል፤ ማዕበሉን ያሻግረናል ብለን እናምናለን፡፡ የሃይማኖት አባቶች ያዘዙንን ጥንቃቄ እየፈጸምን ያዘዙንንም ጸሎት ተግተን እንጸልይ፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ገልጥላችኋለሁ፡፡ በተለይ ግን በምርት ዝውውር ጊዜ ከፍተኛ የሆነውን የመጨረሻ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለአፍታም ቢሆን እንዳትዘነጉት ይሁን፡፡ ይህ ጊዜ ያልፋል፡፡ ሀገራችን ከዚህ የሚስተካከሉና ከዚህም የሚብሱ ፈተናዎችን አልፋለች፡፡ ዓለማችን በየዘመናቱ የከፉ ተግዳሮቶችን አልፋ ነው እዚህ ዘመን የደረሰችው፡፡ የሚሰጡንን መመሪያዎች በሚገባ እናክብር፣ የጤና ባለሞያዎች የሚሉንን ለሕይወታችን ስንል እንስማ፡፡ በኮሮና…»
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 225 ሰዎች ውስጥ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ ቁጥሩም ወደ 55 ከፍ ብሏል።
ďťż
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለ2 ሺህ 496 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
ዛሬ የተገለጸውን ጨምሮም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 55 ከፍ ብሏል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሦስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያውያን ናቸው፤ ሁለቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውም ናቸው።
ሁለቱም የ29 ዓመት ዕድሜ ያላቸውና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት ዕድሜ ያለውና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው።
ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለውም፤ ነገር ግን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ እንደተደረገበት ተገልጿል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል አንድ ሰው ወደ ጽኑ ሕሙማን ማቆያ መግባቱንና ይህም በጽኑ ሕሙማን መቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎች ቁጥር 2 እንዳደረሰው ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ባሉበት ክልል በተዘጋጀ የነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።
ኅብረተሰቡ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግም ነው ያሳሰቡት።
በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል አራቱ አገግመዋል፤ ሁለቱ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።