Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
#አለምአቀፍ_የኮሮና_ስርጭት_ከምሽቱ_2:00_አርብ_መጋቢት_25_2012
በመጀመሪያ ሁላችንም በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ ውድ ወንድሞችና እህቶች።
በተቻለን መጠን በመንግሥትና በሀይማኖት አባቶቻችን የሚነገረንን ከሮናን ለመከላከል የሚወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እናድርግ።
ከዚህ በታች በአለማችን የተከናወነውን የCOVID-19 ወይም ኮሮና መረጃን እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራለሁ።
➤በሽታው ከ 200 አገራትን በላይ አዳርሷል
➤በአለማችን ላይ የቫይረሱ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን አንድ ሚሊዮን አልፏል አጠቃላይ ኬዝ 1,072,860 ሲሆን አጠቃላይ ሞት ደግሞ 56,905 እስከዛሬ ድረስ በቫይረሱ ሞተዋል። እንዲሁም እስከዛሬ ድረስ 226,050 ከበሽታው አገግመዋል።
➤እስከ ዛሬው እለት በሀገራችን 35 በኮሮና ቫይርስ የተያዙና ሶስት ሰዎች ከበሽታው ያገገመ እንዲሁም ዛሬ 6 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል መሆኑም መረጃው ያሳየናል።
➤በአለማችን ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው አሜሪካ ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 264,159 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 19,282 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
እንዲሁም 644 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
➤በአለማችን በሁለተኛነት ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው ጣሊያን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 119,827 ሲሆን በ 24 ሰአታት ብቻ 4,685 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን በሶስተኝነት ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው ስፔን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 117,710 ሲሆን በ 24 ሰአታት ብቻ ደግሞ 5,645 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን ብዙ በአራተኝነት ኬዞችን ያስመዘገበችው ጀርመን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 89,838 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 5,044 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን ብዙ በአምስተኛነት ኬዞችን ያስመዘገበችው ቻይና ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 81,620 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 31 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል። በዚህም ቻይና በጣም ከሚገባው በላይ በሽታውን እየተቆጣጠረች መሆንን ያሳየናል።
➤በ 6ኛ ፈረንሳይ በጠቅላላ ኬዝ 59,105 አዲስ ኬዝ አልተሞላም መረጃው እንደተሞላ update አደርገዋለሁ።
➤በ 7ኛ ኢራን በጠቅላላ ኬዝ 53,183 አዲስ ኬዝ 2,715
➤በ 8ኛ እንግሊዝ ስትሆን በጠቅላላ ኬዝ 38,168 አዲስ ኬዝ 4,450
=============================
የሞት መረጃ
----------
1ኛ ጣሊያን ጠቅላላ 14,681 አዲስ ሞት 766 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
2ኛ ስፔን ጠቅላይ ሞት 10,936 አዲስ ሞት 587 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
3ኛ አሜሪካ ጠቅላይ ሞት 6,715 አዲስ ሞት 644 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
4ኛ ፈረንሳይ ጠቅላላ ሞት 5,387 አዲስ መረጃው አልተሞላም እንደተሞላ update አደርገዋለሁ።
4ኛ እንግሊዝ ጠቅላይ ሞት 3,605 አዲስ ሞት 684 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
5ኛ ቻይና ጠቅላላ ሞት 3,322 አዲስ ሞት 4 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
6ኛ ኢራን ጠቅላይ ሞት 3,294 አዲስ ሞት 134 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
-----------------------------
አዘጋጅ ሙሀመድ አሚን
አላህ ሀገራችን አለማችንን ከዚህ በሽታ ነጻ ያድርግልን።
ሁላችንም በዱአ(ጸሎት) እንድርግ።
መልካም ምሽት።
የመረጃ ምንጭ ወርልዶሜትርስ።
══════❁✿❁ ══════
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
# አለምአቀፍ_የኮሮና_ስርጭት_ከጠዋቱ_1 :00_ቅዳሚ_መጋቢት_26_2012
በመጀመሪያ ሁላችንም በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ ውድ ወንድሞችና እህቶች።
በተቻለን መጠን በመንግሥትና በሀይማኖት አባቶቻችን የሚነገረንን ከሮናን ለመከላከል የሚወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እናድርግ።
ከዚህ በታች በአለማችን የተከናወነውን የCOVID-19 ወይም ኮሮና መረጃን እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራለሁ።
➤በሽታው ከ 200 አገራትን በላይ አዳርሷል
➤በአለማችን ላይ የቫይረሱ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን አንድ ሚሊዮን አልፏል አጠቃላይ ኬዝ 1,098,762 ሲሆን አጠቃላይ ሞት ደግሞ 59,172 እስከዛሬ ድረስ በቫይረሱ ሞተዋል። እንዲሁም እስከዛሬ ድረስ 228,923 ከበሽታው አገግመዋል።
➤በአሳለፍነው 24 ሰአታት አጠቃላይ
⓵ አዲስ ኬዝ 82,941
⓶ አዲስ ሞት 5,973
➤በአሳለፍነው 24 ሰአታት ከፍተኛ ሞት ያስነዘገቡ ሀገራት
⓵ አዲስ ሞት 1,321 አሜሪካ
⓶ አዲስ ሞት 1,120 ፈረንሳይ
⓷ አዲስ ሞት 950 ስፔን
⓸ አዲስ ሞት 766 ጣሊያን
⓹ አዲስ ሞት 684 እንግሊዝ
⓺ አዲስ ሞት 168 ጀርመን
⓻ አዲስ ሞት 148 ኔዘርላንድ
⓼ አዲሰ ሞት 134 ኢራን
⓽ አዲሰ ሞት 132 ቤልጄም
⓾ አዲስ ሞት 69 ቱርክ
➤እስከ ዛሬው እለት በሀገራችን 35 በኮሮና ቫይርስ የተያዙና ሶስት ሰዎች ከበሽታው ያገገመ እንዲሁም ባሳለፍነው 24 ሰአታት ውስጥ 6 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል መሆኑም መረጃው ያሳየናል።
➤በአለማችን ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው አሜሪካ ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 277,161 ሲሆን ባሳለፍነው 24 ሰአታት ውስጥ ደግሞ 32,284 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
እንዲሁም 1,321 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
➤በአለማችን በሁለተኛነት ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው ጣሊያን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 119,827 ሲሆን ባሳለፍነው 24 ሰአታት ውስጥ 4,585 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን በሶስተኝነት ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው ስፔን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 119,199 ሲሆን ባሳለፍነው 24 ሰአታት ውስጥ ደግሞ 7,134 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን ብዙ በአራተኝነት ኬዞችን ያስመዘገበችው ጀርመን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 91,159 ሲሆን ባሳለፍነው 24 ሰአታት ውስጥ ደግሞ 6,365 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን ብዙ በአምስተኛነት ኬዞችን ያስመዘገበችው ቻይና ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 81,620 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 31 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል። በዚህም ቻይና በጣም ከሚገባው በላይ በሽታውን እየተቆጣጠረች መሆንን ያሳየናል።
➤በአለማችን ብዙ በስድስተኝነት ኬዞችን ያስመዘገበችው ፈረንሳይ ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 64,338 ሲሆን ባሳለፍነው 24 ሰአታት ውስጥ ደግሞ 5,233 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን ብዙ በሰባተኝነት ኬዞችን ያስመዘገበችው ኢራን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 91,159 ሲሆን ባሳለፍነው 24 ሰአታት ውስጥ ደግሞ 6,365 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን ብዙ በስምንተኝነት ኬዞችን ያስመዘገበችው እንግሊዝ ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 38,168 ሲሆን ባሳለፍነው 24 ሰአታት ውስጥ ደግሞ 4,450 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
=============================
የሞት መረጃ
----------
1ኛ ጣሊያን ጠቅላላ 14,681 አዲስ ሞት 766 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
2ኛ ስፔን ጠቅላይ ሞት 11,198 አዲስ ሞት 850 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
3ኛ አሜሪካ ጠቅላይ ሞት 7,392 አዲስ ሞት 1,321 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
4ኛ ፈረንሳይ ጠቅላላ ሞት 6,507 አዲስ ሞት 1,120 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
4ኛ እንግሊዝ ጠቅላይ ሞት 3,605 አዲስ ሞት 684 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
5ኛ ቻይና ጠቅላላ ሞት 3,322 አዲስ ሞት 4 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
6ኛ ኢራን ጠቅላይ ሞት 3,294 አዲስ ሞት 134 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
-----------------------------
አዘጋጅ ሙሀመድ አሚን
አላህ ሀገራችን አለማችንን ከዚህ በሽታ ነጻ ያድርግልን።
ሁላችንም በዱአ(ጸሎት) እንድርግ።
መልካም ምሽት።
የመረጃ ምንጭ ወርልዶሜትርስ።
══════❁✿❁ ══════
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputer
Technology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/
mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
# ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍2
⚠⚠⚠መጪዎቹ ቀናት አስጨናቂ ናቸው⚠⚠⚠
የአሜሬካ ድምጽ ሬዲዮ (VOA) በኢትዮጵያ የCOVID-19 ስጋትን አስመልክቶ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አረጋግጠውልኛል ያለውን የትንበያ መረጃ አጋርቷል።
እንደትንበያው በቀጣዮቹ ሳምንታት በሀገራችን የኮሮና ወረርሽኝ ወደ አስጊ ሁኔታ ሊሸጋገር ይችላል።
• በጥቂት ሳምንታት ውስጥም የሀገሪቱን የጤና አገልግሎት ስርዓት ሊያሰናክል ይችላል፤
• ከሁሉ የከፋ ሁኔታ ቢፈጠር ለሚሆን አዝማሚያ የሚያዘጋጅ ሙከራ በማድረግ ላይ ነው፤
• 28 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች (ኢትዮጵያውያን) ለቫይረሱ ሊጋለጢ ይችሉ ይሆናል፤
• ቁጥሩ 9,700 የሚደርስ ሰው በመጪዎቹ 4 ሳምንታት ውሥጥ በፅኑ ለታመሙ ህሙማን የሚሰጥ ህክምና አገልግሎት ሊያስፈልገው ይችላል፤
• ማኀበራዊ መራራቅ የሚለው አስፈላጊ ጥንቃቄ በተግባር ላይ ውሎም 30,000 ያህል ሰው ለቫይረሱ የሚጋለጥበት ሁኔታ ይፈጠራል፤
ወገኔ!
ይህንን ሁሉ ስትሰማ የሚያዋጣህ መጨነቅ እና መጠበብ አይደለም። የሚያዋጣህ ከፈጣሪ ጋር ለራስህን እና ለቤተሰብህ የሚቻልህን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ ነው።
____
✅እንጸልይ
✅እንራራቅ
✅እጆቻች_እንታጠብ
⏩ምንጭ:- doctor alle
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 መድረሱን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ
********
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 89 ሰዎች ውስጥ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በመረጋገጡ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 እንደደረሰ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት፤ ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሦስቱም ግለሰቦች የውጭ አገሮች ጉዞ ታሪክ ያላቸውና ሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው።
''የመጀመሪያው ግለሰብ የ29 ዓመት ወንድ ሲሆን መጋቢት 10 ቀን ከዱባይ የመጣና በበሽታ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው ነው'' ብለዋል።
ሁለተኛው የ34 ዓመት ወንድ መጋቢት 23 ከዱባይ የመጣና በማቆያ የነበረና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው መሆኑ ታውቋል።
ሶስተኛዋ የ35 ዓመት ሴት በመጋቢት 25 ከስውዲን የመጣችና በማቆያ የነበረች መሆኗን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ አዛውንት አገግመዋል።
ዛሬ ከቫይረሱ ያገገሙትን የ85 አዛውንት ጨምሮ በድምሩ አራት ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ኢዜአ
በተደጋጋሚ የምንጠቀማቸው መሰረታዊ የኮምፒውተር አቋራጭ ቁልፎች
⓵ Ctrl+O ➤Open a file in current software program
⓶ Ctrl+A ➤Select all text.
⓷ Ctrl+B ➤Change selected text to be Bold
⓸ Ctrl+I ➤Change selected text to be in Italics
⓹ Ctrl+U ➤Change selected text to be Underlined
⓺ Ctrl+F ➤ Open find window for current document or window.
⓻ Ctrl+S ➤Save current document file.
⓼ Ctrl+XCut âž¤selected item.
⓽ Ctrl+C ➤Copy selected item.
⓾ Ctrl+V ➤Paste
⓫ Ctrl+Y ➤Redo last action
⓬ Ctrl+Z ➤Undo last action
⓭ Ctrl+K ➤Insert hyperlink for selected text
⓮ Ctrl+P ➤Print the current page or document.
⓯ Home➤Goes to beginning of current line.
⓰ Ctrl+Home ➤Goes to beginning of document.
⓱ End ➤Goes to end of current line.
⓲ Ctrl+End ➤Goes to end of document.
⓳ Shift+Home ➤Highlights from current position to beginning of line.
⓴ Shift+End ➤Highlights from current position to end of line.
21 Ctrl+Left ➤arrowMoves one word to the left at a time.
22 Ctrl+Right arrow➤Moves one word to the right at a time.
23 Ctrl+Esc ➤Opens the START menu
24 Ctrl+Shift+Esc ➤Opens Windows Task Manager
25 Shift+Del ➤Permanent delete.
26 Ctrl+Ins ➤Copy selected item
27 Shift+Ins ➤Paste
28 Alt+Tab ➤Switch Windows
29 WinKey+Tab ➤Switch Windows
30 Alt+F4 ➤Close the currently active program
31 Alt+Enter ➤Open the Properties for the selected item (file, folder, shortcut, etc.)
32 Alt+F ➤File menu options in current program.
33 Alt+E ➤Edit options in current program
34 Alt+Tab ➤Switch between open programs
35 F1➤ Universal Help in almost every Windows program.
36 F2 ➤Rename a selected file
37 F5 ➤Refresh the current program window
37 Ctrl+N ➤Create a new or blank document in some software programs.
══════❁✿❁ ══════
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
❤1
እነሆ ሌላ የኔ ትውልድ ጀግና!
በኮሮና ለተያዙ ወገኖቻችን የመተንፈሻ ማገዣ ማሽን (Ventilator) ለመሥራት ዝግጁ ነኝ ይለናል። ኢዘዲን ካሚል ይባላል! ገና የ19 ዓመት ተማሪ ነው። 28 የፈጠራ ሥራዎች አሉት! በ13ቱ ዓለም አቀፍ ፓተንት አገኝቶባቸዋል። በፎቶው ላይ በቀኝ በኩል የምታዩት የቅርብ ጊዜ ፈጠራው ከሰሞኑ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይሆን ዘንድ በእጅ መክፈትና መዝጋት አልያም መጫንም ሳይጠይቅ፣ ሳሙና ጨምሮ እጅን የሚያስታጥብ መሳሪያ ነው። በሚያስደስት መልኩ ድጋፍ አግኝቶ በብዛት እየተመረተ፣ በተለይም በወልቂጤ ሪፈራል ሆስፒታልና በከተማዋ እየተሰራጨ እንደሆነም ነግሮኛል። ኢትዮጵያ ማህጸነ ለምለም እንደሆነች ምስክር የሆኑ፣ በክፉ ቀን ለወገናቸው የሚደርሱ ብዙ ወጣቶችን ገና እናያለን።
ታዲያ ይህ ባለ ምጡቅ አእምሮ ለጋ ወጣት የመተንፈሻ ማገዣ መሳሪያ (Ventilator) ለመሥራት የሚያስፈልጉት ሁለት ትልልቅ ማሽኖች ብቻ እንደሆኑ ነግሮኛል። እንግዲህ ሁላችንም ልንተባበረው ይገባል።
እንዴት ላግዘው? ካላችሁኝ
አንደኛ - ይሄን መልእክት ሼር በማድረግና በመደዋወል ሌሎች አቅም ያላቸው ሰዎች ጋር አዳርሱልን።
ሁለተኛ - አቅሙ ያላችሁ ሰዎች እየደወላችሁ በምትችሉት እንድታግዙት ይሁን - 0977448535፤ በተለይ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ ባለሐብቶችና የባዮ-ሜዲካል ኢንጂነሪንግ ባለሙያዎች ሊረባረቡ ይገባል።
ሦስተኛ - የሚዲያ ባለሙያዎች እቃዎቹ እንዲመረቱና እንዲዳረሱ በቂ ሽፋን እንድትሰጡት እጠቁማለሁ።
# የሚሠሩእጆች # የኔትውልድ
(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 5 ተጨማሪ ሰዎች መገኘታቸው ተገለፀ
******
አምስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የዛሬዎቹን ጨምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 43 መድረሱን ኢንስቲትዩቱ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የታማሚዎች ሁኔታ ፦

- ሶስቱ ታማሚዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። አንደኛው ታማሚ ኤርትራዊ ነው። ሌላኛው ታማሚ ደግሞ ሊቢያዊ ነው።

- አንደኛው ታማሚ የአዲስ አበባ ነዋሪ የ26 ዓመት ወንድ ሲሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪኩ እንደሚያሳየው ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

- ሁለተኛው የ60 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን የኮንጎ የጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆይ ውስጥ የነበረ ነው።

- ሶስተኛው #ለጉብኝት አዲስ አበባ የመጣ የ45 ዓመት ወንድ ከካናዳ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

- አራተኛዋ ታማሚ የ27 ዓመት ሴት ስትሆን ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ሌስተር ሲቲ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች ናት።

- አምስተኛው ታማሚ የአዲስ አበባ ነዋሪ የ30 ዓመት ወንድ ሲሆን ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ነው።
# update_corona_virus_እሰከ_7 :00_ድረስ
# share
በዓለም በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ64 ሺህ በለጠ ፡፡ በፈረንጆቹ 2019 መገባደጃ ላይ በቻይና ውሃን ግዛት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የአለም ስጋት መሆኑን ቀጥሏል፡፡
እስከ 7:00 ሰዓት ድረስም በዓለም 1 ሚሊየን 205 ሺህ 825 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 64 ሺህ 978 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል 2 መቶ 47 ሺ 961 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡
አውሮፓዊቷ ሀገር ስፔን ደግሞ ጣልያንን በመብለጥ 126,168 ሰዎች ተጠቅተውባት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
አሜሪካ በሽታው ጠንቶባታል የተጠቂዎች እና ሟቾች ቁጥር በእጥፍ ሲጨምር ተጠቂዎች 311 ሺ አልፈዋል የሟቾቹም ቂጥር ወደ 9,000 እየተጠጋ ይገኛል፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች ተገኝተው ቁጥሩ 43 ደርሷል
በኮቪድ-19 ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበባቸው ሀገራት ዝርዝር ፦
• ጣልያን - 15,362
• ስፔን - 11,947
• ዩናይትድ ስቴትስ - 8,454
• ፈረንሳይ - 7,560
• ዩናይትድ ኪንግደም 4,313
• ኢራን - 3,452
• ቻይና - 3,326
• ኔዘርላንድ - 1,651
• ጀርመን - 1,395
• ቤልጂየም - 1,283
• ስዊዘርላንድ - 666
• ቱርክ - 501
• ብራዚል - 431
• ስውዲን - 391
• ፖርቹጋል - 266
• ካናዳ - 231
• ኢንዶኔዥያ - 191
★መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት like our page
★መረጃውን ከወደዱት ለሌሎች እንዲደርስ share
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ
*****
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህይወታቸውን ያጡት አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ ናቸው፡፡
ታማሚዋ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡
ይሁንእንጂ ከመጋቢት ታማሚዋ 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል፡፡
ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያነስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከልም የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስበዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሁለተኛ ሰው መሞቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አሳውቀዋል !
በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሞት መመዝገቡን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በኢትዮጵያ በዛሬው እለት ሁለተኛ ሰው ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለፁት፥ ታማሚው በለይቶ ማቆያ ከመጋቢት 24 ጀምሮ ህክምና ሲደረግላቸው የነበርና ከገባበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ላይ የነበረ ነው።
ታማሚው ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ህይወቱ እንዳለፈም ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ በዚህም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በራሳቸውና በጤና ሚንስቴር ስም በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የመጀመረያው ሞት ዛሬ ጥዋት ላይ የተመዘገበ ሲሆን፥ ህይወታቸውን ያጡት የ60 ዓመት ታማሚዋ ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ ነበሩ።
በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።
ቀሪዎቹ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ማኅበረሰቦች ናቸው ተብለው የተመረመሩ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
ዛሬ በቫይረሱ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።
ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ሕክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ሕሙማን ማቆያ ይገኛሉ።
ምንጭ፦ ኢዜአ
በኢትዮጵያ አንድ የ9 ወር ህጻንን ጨምሮ ተጨማሪ 8 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተያዙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 264 ሰዎች ውስጥ 8 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንድ የዘጠኝ ወር ህጻን የተያዘ ሲሆን እናቱም ቫይረሱ ተገኝቶባታል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል አንዱ ኤርትራዊ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 52 አድርሶታል ነው ያሉት።
በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠ 8 ሰዎች መካከል አምስቱ ከዱባይ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።
ከእነዚህም ውስጥ አንድ የዘጠኝ ወር ህጻንና ወላጅ እናቱ ይገኙበታል።
አንድ የ25 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ከታይላንድ መጥታ በለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች ሲሆን፤ አንድ የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን የንክኪ ሁኔታውም በመጣራት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ወጣቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።
ሌላኛዋ የ30 ዓመት ሴት ኤርትራዊት ስትሆን ከእንግሊዝ ለንደን መጥታ በአዲስ አበባ በለይቶ ማቆያ ክትትል እያደረገች የምትገኝ ናት።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ አቅም እየጨመረ መጣቱንም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።
አራቱ ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
የኮሮና ቫይረስ ዋነኛው የመተላለፊያ መንገዱ በአፋችንና በአፋንጫችን በሚወጡ ፈሳሾች/Drop/ አማካኝነት ነው።
ነገር ግን አንደ Disease
Control and Prevention (CDC) ገለፃ በአፋችንና በአፋንጫችን ከሚወጡት ፈሳሾች ጋር ባይወዳደሩም በመጠኑም ቢሆን እቃዎች ላይ በመቆየት ይተላለፋሉ ብሏል።
ምንም እንኳ ግልፅ የሆነ ጥናት እስካሁን ባይገኝም።
ኮሮና ቫይረስ በዕቃዎች ላይ የሚቆይበት ጊዜ እንደ አየር ፀባይ የሚወሰን ሲሆን የአየር ፀባይ ከ5°C-11°C ባለው የሙቀት መጠን ለይ ቫይረሱ በከፋተኛ ሁኔታ ይሰራጫል። የመገልገያ ቁሳቁሶች ላይም የሚቆይበት ጊዜ ከፍ ይላል።
አንዳንድ ጥናቶች እንደጠቆሙት ከፍተኛ ሙቀት ማለትም ከ30°C እና ከዛ በላይ በሆነ የአየር ፀባይ ላይ COVID -19 ከሰዎች ላይ ካልሆነ በቀር አየር ላይና እቃዎች ላይ ተቋቁሞ ለመቆየት ይቸገራል ይላሉ።
እንደ National Institute of Allergy and
Infectious Disease (NIAID) ጥናት COVID-19 እቃዎች ላይ የሚቆይበት ጊዜ እንደ አየር ፀባዩ ሁኔታ እንደሆነ ገልጾ
ከ18°C-25°C ባለው ሙቀት ላይ ኮሮና ቫይረስ እቃዎች ላይ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቋይ እንደሚከተለው አስቀምጧል።
ምንጭ DR.FINOT
የቻይናዋ ውሃን ከተማ ከ76 ቀናት በኋላ ለእንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆናለች
*******
የኮሮና ወረርሽኝ መነሻ ናት በተባለችው የውሃን ከተማ የሚገኙ ሰዎች ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንቅስቃሴ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
ጤናማነታቸው የተረጋገጠና ይህንኑ የሚመሰክር አረንጓዴ ኩፖን ምልክት የያዙ ነዋሪዎቿ አሁን ወደየትም አገር መጓዝ ይችላሉ ተብሏል፡፡
የባቡር መንገዶቿ፤ የመኪና አውራ ጎዳናዎቿም ለመጀመርያ ጊዜ በሙሉ ኃይል ክፍት ሆነዋል፡፡
ባለስልጣናት ይህንን ሁኔታ እንደ ስኬት ሲቆጥሩት ነዋሪዎች ግን የተለያየ ልምድ የወሰዱበት እና በሰው ልጅ ታሪክ አከራካሪ ገደብ ሆኗል፡፡
የ11 ሚሊዮን ቻይናዊያን መኖርያ የሆነችው ውሃን ለ11 ሳምንታት ሙሉ በሙሉ ተዘግታ፤ እንቅስቃሴዋ ታግዶ ከርማ ነበር፡፡
በቻይና ወረርሽኙ ከተነሳ ወዲህ 3300 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የሚበዙቱ የዚች ከተማ ነዋሪዎች እንደነበሩ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡