Muhammed Computer Technology (MCT)
37.7K subscribers
528 photos
7 videos
254 files
913 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
የስልኮቻችንን ባትሪ ዕድሜ ለማራዘም እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ፍጆታን ለመቀነስ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ባለሙያዎች አስቀምጠዋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን ተግባራት ቢያከናውኑ የስክዎን ባትር እድሜ ያራዝማሉ፤ የኢንተርኔት አጠቃቀም ወጪን ይቀንሳሉ።
1. የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ባክግራውንድ(ዳታ) እንዳይሰሩ ማድረግ
2. ሞባይል ስልክዎን ቻርጅ ላይ ሰክተው አለመጠቀም
3. የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ወደ ስልክዎ ማሳወቂያ እንዳይልኩ ማድረግ
4. አቅጣጫ መፈለጊያ፣ ብሉቱዝ፣ 3ጂ/4ጂ እንዲሁም ዋይፋይ በማንጠቀምበት ጊዜ ማጥፋት
5. ትላልቅ ፋይሎችን ለማውረድ ገመድ አልባ ኢንተርኔት(ዋይፋይ) ብቻ መጠቀም
6. የሞባይል መተግበሪያዎችን ለማሻሻል ዋይ ፋይን ይጠቀሙ
7. ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ጊዜ የሞባይልዎን ኢንተርኔት(ዳታ) ይዝጉ
8. አገልግሎት የማይሰጡ ወይም ጊዜ ያለፈባቸውን መተግበሪያዎችን ከስልክዎ ያስወግዱ
9. ሁልጊዜ የስልክዎ ስክሪን የሚጠፋበትን ደቂቃ ያሳጥሩ፤ ከተቻለም ወደ ሰኮንዶች ይቀንሱ
10. ለስልኩ የተሻለ ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ይጫኑለት።
👍116❤26👏5
ምርጥ 11 የኮምፒዉተር ሶፍትዌር ማዉረጃ ሳይቶች

1) getintopc
https://getintopc.com
የተለያዩ ክራክ የተደረጉና ምርጥ ነጻ ሶፍትዌሮችን በማቅረብ የሚታወቅ ምርጥ ዌብሳይት ነው። በመሆኑም በዚህ ዌብሳይት የፈለጉትን ሶፍትዌሮችን በመፈለግ ማግኘት የሚያስችል በመሆኑ በብዙ ሰዎች ዘንድ ተፈላጊ ነው።

2) Download
https://download.cnet.com

የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡

3) FileHippo
https://filehippo.com

ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡ ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅመናል፡፡

4) ZDNet
https://downloads.zdnet.com

ይህ ሳይትም እንደሌሎቹ ብዙ የ ሶፍትዌር አማራጮችን የያዘ እና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሳይት ነዉ፡፡

5) Softpedia
https://www.softpedia.com

Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡

6) Tucows
https://www.tucows.com/downloads

ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡

7) FreewareFiles
https://www.freewarefiles.com

ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡

8) MajorGeeks
http://m.majorgeeks.com

ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ዩሰር ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡

9) FileCluster
https://www.bytesin.com

FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የ WordPress Themes፣ ዜናዎችን እና ሶፍትዌር ካምፓኒዎችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡

10) Soft32
https://www.soft32.com

በ 2003 የተመሰረተ ሲሆን የ ሶፍትዌር ዳይሬክተሪዉን ቶሎ ቶሎ update በማድረግ ይታወቃል፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux እንዲሁም ለ ሞባይል የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ሲኖሩት ለ iPhone ተጠቃሚዎች ብቻ ራሱን የቻለ ክፍል አዘጋጅቷል፡፡ ከ 85,000 በላይ ሶፍትዌሮች ሲይዝ ጥያቄዎቻችንን መጠየቅ የምንችልበት ፎረምም አለዉ፡፡

11) File Horse
https://www.filehorse.com

እንደ ሌሎቹ ሳይቶች በቁጥር ብዙ ሶፍትዌሮችን ያካተተ ባይሆንም በጣም ታወቂ እና ጥራት ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የምናወርዳቸዉ ፋይሎችም ቫይረስ እንደሌለዉ የሚያረጋግጥ ሲስተም አካቷል፡፡ ነጻ ሶፍትዌሮችን ስለያዘ በክፍያ የሚገኙ ሶፍትዌሮችንም አማራጭ ነጻ ሶፍትዌር ልናገኝበት እንችላለን፡፡
telegram channel
👇👇👇Join👇👇👇
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍119❤20👏7😁5🔥2
የኮምፒውተር ሀርድ ዲስክን እንዴት መክፈል እንችላለን?
ዛሬ የምናየው እንዴት አድርገን አንድ ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ከዚያ በላይ ክፍልፋዮች እንደምንቀይር ነው።
ለምሳሌ Local disk C: ካለን ከሁለት ለመክፈል ለምሳሌ
#1_right click on My computer
#2_ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን
#3_ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
#4_ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን
#5_ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
#6-ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
ማስጠንቀቂያ:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈክ ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
#7_ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
#8_click on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::
ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም።
እስኪ ለምሳሌ 152 GB ለመክፈል ብንፈልግ ስንት ብለን መጻፍ ይጠበቅብናል? ኮሜንት ላይ ይጻፉልኝ!
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍80❤15🔥2🥰2😁2👎1
ልታውቋቸው የሚገቡ Commands እንዴት አድርገን የኮምፒውተራችንን Users ማስተዳደር እንችላለን?
🔶 በመጀመሪያ ደረጃ Command Prompt ወይም CMDን እንከፍታለን።
ለምክፈት በ3 አማርጮች እንጠቀማለን
1ኛ Start-> All Program -> Accessories -> Command Prompt
2ኛ Crtl+R በመጫን CMD ብለው በመጻፍ OKን ይጫኑ
3ኛ start -> Search Box ላይ CMD ወይም Command Prompt ብለው ይፈልጉ። ከዛም ከሶስቱ 1ን አማራጭ ተጠቅመው ሲከፍቱት Black Screen ይመጣላችኋል። ከዛም ከታች ከ1-8ኛ ድረስ ያለውን ተግባራቶችን ይሞክሩ።
አዘጋጅ Muhammed Computer Technology
✅ 1ኛ net user ይህ ኮማንድ የሚጠቅመን ከኮምፒውተራችን ያሉንት Users ይዘረዝርልናል። እንዲሁም ከማንኛውም ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚል አካውንት አለ እሱ ምን እንደሆነ ከታች መልሱን ያገኛሉ።
✅ 2ኛ net user muhammed /add ይህ ኮማንድ ከኮምፒውተራችን ላይ muhammed የሚባል User Create(እንዲፈጠር ያደርግልናል)
✅ 3ኛ net user muhammed * ይህ ኮማንድ ከላይ ለፈጠራችሁት muhammed ለሚባል User ወይም ከዚህ በፊት ላለ User ለምሳሌ amin የሚባል ቢኖር Muhammed በሚለው ፈንታ amin የሚለውን ስታስገቡ ለUseሩ Password እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል። ትኩረት‼️ሁለት ጊዜ password እንድታስገቡ ይጠይቃችኋል ሁለቱም password ተመሳሳይ መሆን አለበት። እንዲሁም ፓስውርድ ስታስገቡ እይታያችሁም ወይም ፓስወርድ ስትጽፉ አይታያችሁም ግን በውስጥ ታዋቂነት እየጻፈ ስለሆነ ግራ እንዳትጋቡ።
ነገርግን ለUseሩ password ነስጠት ባትፈልጉ ዝም ብላችሁ 2 ጊዜ Enterን መጫን ብቻ ነው።
✅ 4ኛ net user muhammed /add * ይህ ኮማንድ የሚያገለግለን አንድን User ከነ password Create(መፍጠር) ብትፈልጉ ይህንን መጠቀም አለባችሁ። ኮማንዱ በመጀመሪያ ደረጃ User create ያደርግና በተመሳሳይ ፓስወርድ እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል። password ማስገብት ከፈለጋችሁ አስገቡ ግን password ማስገባት ካልፈለጋችሁ Enterን 2 ጊዜ ይጫኑ።
ይህ ማለት ከላይ ተ.ቁ 2ና 3ን በአንድ ጊዜ ለመስራት ያገለግለናል።
✅ 5ኛ net localgroup Administrators muhammed /add ይህ ኮማንድ ከላይ የፈጠርነው user ምን ጊዜም Standard User ነው የሚሆነው።
በኮምፒውተር ተጠቃሚዎች አይነት Users Type በ3 ይከፈላል 1ኛ Administrator 2ኛ Standard User 3ኛ Gusts ናቸው።
እነዚህ Users ለምሳሌ ከላይ የፈጠርነው User Muhammed የሚባለው ከላይ ባለው ኮማንድ ሲፈጠር Standard User ነው። Standard User ደግሞ በኮምፒውተሩ ላይ ሙሉ የሆነ የመቆጣጠር አቅም የለውም የግድ ምን መሆን አለበት Administrator መሆን አለበት።
ስለዚህ ከላይ ያለውን 5ኛ ተ.ቁን Command መጠቀም ይኖርብናል።
✅ 6ኛ net localgroup Administrators muhammed /del ይህ ኮማንድ በተ.ቁ 5 ላይ muhammed የሚባለውን User ወደ Administratorነት ቀይረነዋል ነገር ግን ወደ Standar User ለመቀየር ከተፈለገ 6ኛውን ኮማንድ መጠቀም አለብን ማለት ነው። ይህም Muhammed የሚባለውን User ከ Administrator Account Type ወደ Standard User Account Type ቀየርነው ማለት ነው።
✅ 7ኛ ከማንኛው ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚባል User አለ ይህ User ለአደጋ ጊዜ ተብሎ የተቀመጠ User አለ ይህ User ከኮምፒዩተሩ ተደብቆ ሁኖ ነው ያለው ይህንን User መሉ በሙሉ ከኮምፒውተሩ ማጥፋት አይቻልም ነገርግን ሌሎች የተፈጠሩ User Account ማጥፋት ትቻላል። ለእናንተ የምመክራችሁ User Accountችን ሊጠፋብን ይችላል የሚል ስጋት ካለባችሁ Administrator የሚባለውን User Account Active ማድረግ አለባችሁ አሁን እሱን እናያለን!
🛑 net user Administrator active:yes
ከኮምፒውተሩ የተፈጠረን User Account ሳናጠፋ Inactive ለማድረግ ወይም እንዳይሰራ ለማድረግ ለምሳሌ muhammed የሚለውን እንዳይሰራ ለማድረግ።
🔷 net user muhammed active:no ይህ ኮማንድ muhammed የሚባለው user inactive ሁኗል ማለት ነው። እንደገና ግን Active ለማድረግ ከፈለጋችሁ
🔶 bet user muhammed active:yes የሚለውን ኮማንድ ተጠቀሙ።
✅ 8ኛ ከኮምፒውተሩ ያለውን User Account ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ከፈለጋችሁ ለምሳሌ muhammed የሚባለውን ማጥፈት ብትፈልጉ
🛑 net user muhammed /del
ማስጠንቀቂያ ይህ ኮማንድ ለምሳሌ muhammed የሚባለውን user መረጃ ሙሉ በሙሉ ነው የሚያጠፋው ያ ማለት በውጡ ያስቀመጣቸው Desktop ላይ My Documents ላይ My Music ላይ My Picture ላይ ያስቀመጣቸውን ሙሉ መረጃ ያጠፋብናል ስለዚህ ትኩረት ማድረግ አለባችሁ።
ግን ለትምህርት ለምሳሌ እንደእስካሁኑ muhammed የሚባል User Account ላይ እንደ መለማመጃ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
👇👇👇በቪዲዮ ከገለጋችሁ👇👇👇
✅ እንዴት የኮምፒተር Usersና (Password) በCMD መስበር አንችላለን How to Crack Computer Password? 👇👇

https://youtu.be/9BHgunGi2vc
#ይሞክሩት!
ከተመቻችሁ ለሌሎች እንዲደርሳቸው #ሼር ቢያደርጉ ጥሩነት ነው።
👍90❤14👏5🤬1
የኮምፒውተር 32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት እና ጥቅም
ምንድነው?
=======================================
ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት
ይዘን
ቀርበናል ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን
ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ
(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር
ለመወሰን
ያግዛል፡፡ የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት
በሚል
የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም
አይነት እክል
የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና
ሶፍትዌሮች
ይወስኑታል፡፡
1. 32 ቢት ፕሮሰሰር
32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ
የሚገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና
ኤኤምዲ እየሰሩ
ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ኦፕሬቲን ሲስተም እና
ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት
ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ
ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 95፣
98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው
የተሰሩ ናቸው፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም
መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን
የሚችለው
32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡
2. 64 ቢት ፕሮሰሰር
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ
አይቢኤም IBM
7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም
እስከ 2000
ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ
አልነበረም:: ማይክሮሶፍት 64
ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም ለገበያ አቀረበ
በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64
ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ
ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡ 64 ቢት
ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር
64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል
ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን
ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡ ማስታወሻ 64 ቢት
ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ
ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ
ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን
ሲስተም ላይ
የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት
ፕሮግራሞች/
ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን
አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት
አንዱ
ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64
ቢት
ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad
core፣ በsix
core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ
ነው፡፡
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው
በኮምፒውተሩ
ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት
ፕሮሰሰር
ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም
የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር
ከ4GB
በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣
ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም
አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64
ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት ቢሆኑ ይመረጣል።
ሼር ማድረግዎን አይርሱ፤፤ መልካም ቀን ይሁንልዎ
Like እና Share ማድረግ አይርሱ!
====================
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍227❤63🤯9👏8👎6🤔5🔥2
ስማርት ስልኮቻችን ሀይል እንዴት መሙላት አለብን…?
በርካታ ተግባራትን የሚያከናውኑበት ስማርት ስልክዎ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ ተችገረዋል?
የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅመው የስልክዎን ባትሪ ቢያንስ ሙሉ ቀን እንዲያስጠቅምዎትስ ጥረት አድርገዋል?
በቴክኖሎጂው መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች የስልካችን ባትሪ በፍጥነት እያለቀ የምንቸገረው በሶስት ምክንያቶች መሆኑን ይገልፃሉ።
የመጀመሪያው በስማርት ስልኮቻችን የጫንናቸው መተግበሪያዎች መብዛት እና እያወቅንም ይሁን ሳናውቅ ተከፍተው ባትሪ መብላታቸው
ነው።
የስማርት ስልካችን ላይ ሙጭጭ ብለን አልላቀቅ ማለትም ሌላኛው የባትሪ እድሜን የሚያሳጥር ልማድ ነው።
ሶስተኛው እና ዋነኛው የባትሪ ህይወትን የሚያሳጥረው ተብሎ በባለሙያዎች የተጠቀሰው ደግሞ የሀይል አሞላላችን (ቻርጅ አደራረጋችን መሆኑ ተገልጿል።
ብዙዎቻችን የስማርት ስልካችን ባትሪ ሙሉ በሙሉ ሲያልቅ ቻርጅ ማድረግ እንዳለብን እናምናለን።
በአንዳንዶቻችን ዘንድ ደግሞ ቻርጅ እንደሰካን ሞባይላችንን መጠቀም የባትሪውን አገልግሎት ያራዝማል የሚል አመለካከት አለ።
ይሁን እንጂ የሞባይል ባትሪ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ “መጨናነቅን” አይወድም ነው የሚለው ባትሪ ዩኒቨርሲቲ የተሰኘ ኩባንያ።
ስልካችንን ቻርጅ እያደረግን መጠቀም የባትሪውን እድሜ ያሳጥራልም ይላል።
ስለ ስማርት ስልክዎ ባትሪ ከመጨነቅ የሚገላግሉ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችም ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች አስቀምጧል።
የስልክዎ ባትሪ ሙሉ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ሞባይሉን ከቻርጀሩ ይንቀሉት፡
ኩባንያው እንደሚለው የስማርት ስልካችን ባትሪ ከአቅሙ በላይ ቻርጅ ሲደረግ የረጅም ጊዜ አገልግሎቱ እየወረደ ይመጣል።
ስልካችን 100 ፐርሰንት ቻርጅ ከሆነ በኋላ እንደተሰካ መተው ለከፍተኛ መጨናነቅ በመዳረግ የባትሪውን ሀይል የመያዝ አቅም ይቀንሰዋል።
(እስከ 100 ፐርሰንት ቻርግ ማድረግም ለመጀመሪያ ጊዜ ካልሆነ አስፈላጊ አይደለም፡
ከአድካሚ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ ጡንቻዎችን ማፍታታት እንደሚገባ ሁሉ ስልካችንም ሙሉ በሙሉ በሀይል ከተሞላ በኋላ ከቻርጀሩ መንቀል ይገባል።
ባትሪውን ከሙቀት ይጠብቁት
የስማርት ስልክ ባትሪዎች በቀላሉ በሙቀት ይግላሉ።
ለዚህም ነው አፕል ራሱ የአይፎን ስልኮችን ቻርጅ ስታደርጉ መሸፈኛ (ኬዞቹን ብታወጡት በማለት የሚመክረው።
ስለሆነም ስልካችን ቻርጅ ስናደርግ መሞቁን ካስተዋልን ሽፋኑን ማውጣት ይኖርብናል።
የባትሪያችን ጤና ለመጠበቅ ስማርት ስልካችን ቻርጅ የምናደርግበት አካባቢ የፀሀይ ሙቀት የሌለበት ቢሆንም ጥሩ ነው።
100 ፐርሰንት ላይ እስከሚደርስ መጠበቅ የለብንም፡
እንደ ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ ከሆነ ከፍተኛ ቮልቴጅ ባትሪውን ስለሚያጨናንቀው ባትሪን መቶ በመቶ ሀይል መሙላት አያስፈልግም።
ስማርት ስልካችን ቀኑን ሙሉ ቻርጅ ማድረግም በባትሪው እድሜ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብሏል።
ቻርጅ ለማድረግ የባትሪውን ማለቅ አይጠብቁ።
ስልካችን ቻርጅ ለማድረግ ባትሪው ተሟጦ እስኪያልቅ መጠበቅ የለብንም።
ባገኘነው አጋጣሚ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን ሀይል ይዞ የመቆየት አቅም ያሳድገዋል።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ስልቶች የስማርት ስልካችን ባትሪ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል እና ቀኑን ሙሉ ከስጋት ነፃ እንድንሆን ይረዳናል ።
እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበኝ!
ምስጋናየ ከልብ ነው!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
👉#ስለኮምፒውተር ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ይህ የኔ የፌስቡክ ገጽ ነው ስለሆነም ፔጄን ላይ ጠቃሚና ወቅታዊ መረጃዎች ያገኛሉ
በቴሌግራም መከታተል ለምትፈልጉ https://t.me/mame309 በዚህ የቴሌግራም ቻናል ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኛላችሁ
ስለዚህ ፔጁን 👍#ላይክ 👉#ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ
#በይበልጥ_ስለኮምፒውተር_ይማራሉ
#ፔጄን_like_share_ያድርጉ_መረጃ_እንዲደርሳችሁ🙏👍
👍82❤9👏2🥰1
የእቅድ form.pdf
643.9 KB
የንግድ ሥራ አቅድ

የንግድ ሥራ ዕቅድ፣ ስኬታማ ንግድ ለመጀመር፣ ለመገንባትና ለመምራት በጣም አስፈላጊ ሰነድ ነው፡፡ እንዲሁም አስፈላጊውን ካፒታል ለማሰባሰብ /ለማሳደግ/ እና የኢንቨስተሮችን ፍላጎት ለመሳብ/ለመያዝ/ ውጤታማ መሳሪያ ነው፡፡ የንግድ ሥራ እቅድ የንግዱን ግባችና ዓላማዎች በግልፅና በተጨመቀ መልኩ የሚገልፅና ለእሱም ስኬት የአሰራር ስልቱን የሚያመለክት መሣሪያ ነው፡፡ እንዲሁም የንግድ ሥራ እቅድ ለአምራቾች/አገልግሎት ሰጭዎች ፍላጎት ላላቸው ኢንቨስተሮችና አቅራቢዎች ለንግዱ ግቦች የላቀ የመገናኛ መሣሪያ ነው፡፡
በርካታ የንግድ ሥራዎች በእቅድና በዝግጅት እጥረት ምክንያት ይወድቃሉ፡፡ ስኬታማ ለሆነ ንግድ ሥራ ከዚህ በታች የተዘጋጀው መመሪያ ለአምራቹ/ለአገልግሎት ሰጪው የንግድ እቅድ መረጃ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ በበለጠ ለመረዳት ይረዳል፡፡ የመረጃው በዝርዝር መምሪያ ትክክለኛ መሆን፣ ተቋማት፣ ባንኮች፣ ኢንቨስተሮችና አቅራቢዎች ድጋፍ ሲጠይቅ ፈጥኖ ምላሽ ለመስጠት ያመቻል፡፡ በአጠቃላይ አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው ራሱ የንግድ እቅድ ለማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት፡፡
የንግድ እቅድ ንግዱ ምን እንደሚሰራ፣ እንዴትና የት እንደሚሰራ አና የንግዱ ካፒታል እንዴት እንደሚገነባና እንዴት እንደሚመራ የሚከተሉትን ምዕራፎች ጨምሮ መሰረታዊ ክፍሎቹን ያብራራል፡፡
• ግላዊ መረጃዎች
• ያሉና የሚገዙ የመሥሪያ መሣሪያዎች
• ስራው የሚካሄድበት ህንፃና መሬት
• የዓመታዊ ምርቱ/አገልግሎት እቅድ
• ለዓመት የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎች
• ዓመታዊ የሽያጭ እቅድ
• ሌሎች ዓመታዊ የስራ ማስኬጃ ወጭዎች
• የዓመታዊ ትርፈና ኪሳራ መግለጫ

በቀጣዮ ፅሁፍ ዕቅድ ለማቀድ የሚረዱ ጠቃሚ ሰነዶችን አቀርብላችሀለዉ።
ድጋፍ ከፈለጉ
+251912688642
በቴሌግራም አካውንት ያግኙን
https://t.me/Research100stock
👍50❤5🥰1👏1
የንግድ ድርጅት ምስረታ አይነቶች

የንግድ ድርጅት አይነቶች

በአደረጃጀታቸውና በአሰራራቸው የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች አሉ፡፡ በአጠቃላይ ድርጅቶችን ለትርፈ የተቋቋሙና አትራፊ ያልሆኑ ብለን በሁለት መክፈል እንችላለን፡፡ እንደገናም በግል ባለቤትነት የተያዙ እና የመንግስት ብለን በሁለት መክፈል ይቻላል፡፡ በእኛ ሀገር በመንግስት የተያዙ የንግድ ድርጅቶችን ሳይጨምር ሶስት አይነት የንግድ ድርጅቶች ያሉ ሲሆን እነሱም፡-

፨የግለሰብ
፨ ነጋዴ
፨የንግድ ማህበራትና
፨የኀብረት ሥራ ማህበራት ናቸው፡፡

እነዚህ የንግድ ድርጅቶች እያንዳንዳቸው የተለያየ ባህሪና ውስጣዊ አደረጃጀት ያላቸው ሲሆን የተለያየ ጠቀሜታም አላቸው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ሰው ወደ ንግድ ተግባር ከመግባቱ በፊት ከእነዚህ የንገድ ድርጅት አይነቶች የበለጠ የሚስማማቸውን በመምረጥ ህጋዊ እውቀና ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ የተሻለ የሚሉትን ለመምረጥ ደግሞ ስለእያንዳንድ የንግድ ድርጅት አይነት በቂ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ስለ እነዚህ የንግድ ድርጅቶች በዝርዝር እንመለከታለን፡፡

ጠቃሚ ናቸው ብዬ ያመንኩባቸዉን መረጃዎች አደርሳችኋለሁ እናንተም ጠቃሚ ናቸዉ ብላችሁ ካመናቹባቸዉ ለሌሎች አጋሯቸዉ።

ድጋፍ ከፈለጉ
+251912688642
በቴሌግራም አካውንት ያግኙን
https://t.me/Research100stock
👍52❤8👎1
Model Exam version 3.pdf
594.1 KB
ለኮምፕዩተር ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ፡ ይህንን ጥያቄ መውጫ ፈተና ላይ የማስታውሳቸው ጥያቄ ስለሆነ በደንብ ስሯቸው፡፡ ለቀጣይም ይጠቅማችኋል፡ ሌላ የመውጫ ፈተና ጥያቄ የማስታውሳቸው ካለ ወደ እናንተ እልክላችኋለሁ፡፡ እስከዛ በትዕግስት ይጠብቁን፡፡
Model Exam version 7.pdf
1021.2 KB
ለኮምፕዩተር ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ፡ ይህንን ጥያቄ መውጫ ፈተና ላይ የማስታውሳቸው ጥያቄ ስለሆነ በደንብ ስሯቸው፡፡ ለቀጣይም ይጠቅማችኋል፡ ሌላ የመውጫ ፈተና ጥያቄ የማስታውሳቸው ካለ ወደ እናንተ እልክላችኋለሁ፡፡ እስከዛ በትዕግስት ይጠብቁን፡፡

---Join---

https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍45🔥4👏4❤2
all Exit exam with Ans and Note.zip
12.6 MB
ገራሚ ለኮምፕዩተር ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ፡ ይህንን ጥያቄ መውጫ ፈተና ላይ የማስታውሳቸው ጥያቄ ስለሆነ በደንብ ስሯቸው፡፡ ለቀጣይም ይጠቅማችኋል፡ ሌላ የመውጫ ፈተና ጥያቄ የማስታውሳቸው ካለ ወደ እናንተ እልክላችኋለሁ፡፡ እስከዛ በትዕግስት ይጠብቁን፡፡

---Join---

https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍58❤15😱3