Muhammed Computer Technology (MCT)
37.7K subscribers
528 photos
7 videos
254 files
913 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ሃርድዌር እና ሶፍትዌር
ስልካችን ከመጠገናችን በፊት የሃርድዌር እና የሶፍትዌር ሃሳብ ምን እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነዉ ። ሀርድዌር ማለት ልናየዉ ልንዳስሰዉ የምንችለዉ የስልካችን የዉስጥም ሆነ የዉጪ ክፍል ማለት ነዉ ። ማንኛዉም የሀርድዌር ክፍል ትንሽም ሆነ ትልቅ የራሱ የሆነ ክብደትና ቀለም ይኖረዋል ። በሌላ አባባል የስልካችን የሃርድዌር ክፍል የሚዳሰስ ዕቃ ነዉ ማለት ነዉ ። ለምሳሌ ከቨር : የባትሪ ማስቀመጫ ክፍሉ : ስክሪን በተጨማሪ ስልካችን ተከፍቶ ወይም ከፈታነዉ በኋላ ልናያቸዉ የምንችል ማንኛዉም አይሲ: ሬዚስተር :ካፓሲተር :ኢንደክተር በሙሉ የስልካችን ሀርድዌር ክፍል ነዉ ።
ሶፍትዌር ማለት ስልካችን የሚሰራበት ፕሮግራም ማለት ነዉ ። ይህ ማለት በአይናችን የማናየዉ የማንዳስሰዉ ነገር ግን ስልካችን ስርአቱን ሳያዛባ እንዲሰራ የሚያደርግ መንገድ ማለት ነዉ ። የስልካችንን ሶፍትዌር እራሱን አንየዉ እንጅ ስራወቹን ማየት እንችላለን ለምሳሌ :- ስክሪናችን ላይ ስዓት : ምስል : የኔትወርክ ምልክት እንዲሁም ማንኛዉም ጥሁፍ እንዲመጣ እና እንዲሰራ የሚያደርገዉ ሶፍትዌሩ ነዉ ። እነኚህን ምስሎች ወይም ጽሑፎች በእጃችን መንካት አንችልም ። እነኚህን ጽሑፎችና ምስሎችን ለመንካት ብንሞክር ለመንካት የምንችለዉ የሀርድዌር ክፍል የሆነዉን ስክሪኑን ነዉ ።
አንድ ስልክ በስርአቱ እንዲሰራልን ሁለቱም ክፍሎች ማለትም ሀርድዌር እና ሶፍትዌር በአግባቡ መስራት አለባቸዉ ። አንዳቸዉ እንኳ ቢበላሹ ስልካችን በስርአቱ ሊሰራ አይችልም ። የሶፍትዌሩን ችግር ለመፍታት ፍላሸር ቦክስ ያስፈልገናል /ከኮምፒውተር በተጨማሪ/። አንዳንድ ጊዜ ቀለል ያሉ የሶፍትዌር ችግሮች በኮድ ልናስተካክላቸዉ እንችላለን ። ይህ ማለት የተወሰኑ ቁጥሮችን በማስገባት ችግሩን መፍታት እንችላለን ማለት ነዉ ። ምሳሌ :-ሪስቶር ማድረግ ።
የሀርድዌር ችግር ሲገጥመን እንደችግሩ አይነትና መጠን መፍቻ : ካዉያ : ዲሲ :ቲነር: ብሎወርና የመሳሰሉትን መሣሪያዎች በመጠቀም እንጠግናለን የአንዳንድ የማይበራ ወይም ጸጥ ያለ ስልክ ችግር ሶፍትዌር ነው ወይም ሃርድዌር ነዉ ብሎ ለመለየት ስልኩ የሚያሳየንን ምልክት በማየት ወይም ዲሲ ፓወር ሰፕላይ በመጠቀም ማወቅ ይቻላል ። የስልካችንን ሶፍትዌር ወደ ተሻለ ፕሮግራም መቀየር /upgrade/ ማድረግ እንችላለን ።
አንዳንድ ጊዜ የሀርድዌርና ሶፍትዌር ሃሳብ በተሳሳተ መንገድ ሲገለጽ ይስተዋላል ።
ሃርድዌር ማለት የሚታይ ክፍል ሶፍትዌር ደግሞ የማይታይ ክፍል ብሎ ማስቀመጥ የተሳሳተ ነዉ ። ምክንቱም የስልኮችን የሶፍትዌር ስራ ማየት ይቻላል ። ለምሳሌ :- የስልኮች ስክሪን ላይ የምናየዉ የኔትወርክ ምልክት : ቀን : ስአትና ሜኑ: ስክሪንሴቨር: ጋለሪ: ፎቶግራፎች የመሳሰሉትን የሶፍትዌር ስራዎች ማየት ይቻላል ።
ሆኖም የአንድን ስልክ ሶፍትዌር ፕሮግራሙን ማየት ግን አይችልም ። ስለዚህ የሚታይ ክፍል እና የማይታይ ክፍል ብሎ ከመለየት ይልቅ ሃርድዌር የሚዳሰስ እና ሶፍትዌር የማይዳሰስ ክፍል ብሎ መለየት የተሻለነዉ ።
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍57❤8😁1🤯1
በዛሬው የ ኮምፒውተር ትሪክ የምናየው እንዴት በቀላሉ ዊንዶውስ ጄኒውን (እውተኛ) እንደምናደርግ ነው ::

ጄኒውን ማድረግ ማለት original የ window CD በምንገዛበት ጊዜ አብሮት የሚሰጠንን product key በምናስገባበት ጊዜ ጄኒውን ያደርገዋል። ኦርጅናል ካልሆነ ግን በተለያየ መንገድ ማድረግ ዘዴዎች አሉት።

የ Genuine አስፈላጊነት የ ፕሮግራሙ አምራች የሆነው ማይክሮሶፍት እንዲያቀው እና የፈለግነውን ሶፍትዌር እንድንጭን እንዲሁም የ ኮምፒዩተራችንን ደህንነት በ ማይክሮሶፍት እንዲጠበቅ ይረዳናል።

Genuine ወይም Activate ያልሆነ ኮምፒዩተር ከታች የ ሰአት ቦታው አከባቢ ምልክት ያሳየናል። አለበለዚያም setting ውስጥ ገብተን update and privacy የሚለው ውስጥ ስንገባ እናገኘዋለን።

ለዛሬ የ window እናያለን!

1. በመጀመሪያ (cmd) ብለን ሰርች ባር ላይ ትጸፋለችሁ በመቀጠል Right click the Command Prompt listing and select “Run as Administrator” ራይት ክሊክ አድርጋችሁ ራን ቱ አድሚንትሬተር የሚለውን ትቻናላችሁ
2. ዊንዶው ላይ “SLMGR -REARM” ብላችሁ ትጽፋላችኁ ከዛ
ኢንተርን እንጫናለን command successfully executed. Restart now የሚቀጥለው ሜሴጅ ሲመጣ ኮምፒውተራችንን restart ok እናደረጋለን።

በYouTube ለመመልከት ከፈለጉ!👇👇👇👇
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
👍57❤2👏2
👬 ልዩ ጥቆማ‼️‼️
አዲስ አበባ ከተማ ላይ ምን መግዛት ይፈልጋሉ????

👉ከመኖርያ ቤት፣ እስከ ንግድ፣ ቤት
👉 እናም የተለያዩ ህንፃወች ሆቴል አፓርታማ ባዶ ቦታ፣ የፈለጉት ሁሉም ከእኛ ጋር አለ

👍👉 ከስር ያለውን ሊንክ Join በማድረግ
👉 በቴሌግራም ቻናላችን ሁሉንም ይመልከቱ Join👇👇👇
https://t.me/Joni9971
https://t.me/Joni9971
https://t.me/Joni9971
👍15❤1
የአመራርና የስራ አመራር ልዩነቶች ምንድን ናቸው?
ምርጥ አቀራረብ 👇👇👇ይመልከቱት👇👇👇
https://youtu.be/HWOe8vj-XJQ
https://youtu.be/HWOe8vj-XJQ
https://youtu.be/HWOe8vj-XJQ
https://youtu.be/HWOe8vj-XJQ
👍29❤1
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዷቸው የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
=============
1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ

• የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤
• የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤
• የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤
• የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤

2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ

• አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤
• ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤ አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤
• ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤
• ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤

• ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤
• ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤

4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ

• ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤
• የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤

5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ

• አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤
• የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤
• ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤

6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ

• እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤
• ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤
• አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤

7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ

• ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤
• ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤
• ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

©ኢመደኤ
👇👇👇Join on Telegram👇👇👇
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍60🥰6🎉2❤1🔥1👏1
ኮምፒውተር ላይ ማንኛውንም ፍላሽና ኤክስተርናል ሀርድ ዲስክ ሲሰካ እንዳይሰራ ማድረግ እንዴት እንችላለን በቪዲዮ ይመልከቱ 👇👇👇
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
1. የኛን መረጃ ሌላ ሰው ያለእኛ ፈቃድ እንዳይወስድብን ለመዝጋትና
2ኛ. ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።
👇👇👇ቪዲዮውን ይመልከቱ👇👇👇
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
https://youtu.be/zqtpTxn4KQs
👍32👏1😁1
ኮምፒውተርዎ Activate Windows Go To Settings To Activate እያለ ተማርረዋል? Windows(not genuine) ኮምፒውተራችንን ኦሪጅናል ማድረግ እንዴት እናድርግ?
👇👇👇በዚህ ቪዲዮ ይሞክሩት👇👇👇
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
https://youtu.be/QBnngsfOH4E
👍33
👬 ልዩ ጥቆማ‼️‼️
አዲስ አበባ ከተማ ላይ ምን መግዛት ይፈልጋሉ????

👉ከመኖርያ ቤት፣ እስከ ንግድ፣ ቤት
👉 እናም የተለያዩ ህንፃወች ሆቴል አፓርታማ ባዶ ቦታ፣ የፈለጉት ሁሉም ከእኛ ጋር አለ

👍👉 ከስር ያለውን ሊንክ Join በማድረግ
👉 በቴሌግራም ቻናላችን ሁሉንም ይመልከቱ Join👇👇👇
https://t.me/Joni9971
https://t.me/Joni9971
https://t.me/Joni9971
👍17❤3👏2🔥1
✳️የሳይበር ጥቃት SMS Phishing

🔻ይህን Method በመጠቀም የATM ፤ የEmail ፤ የfacebook ወ.ዘ.ተ የሚስጥር ቁጥሮች በቀላሉ ይሰረቃሉ።

🔻SMS Phishing በቀላሉ ወደናንተ Fake የሆኑ SMS በመላክ ሊያጠቋችሁ ይችላሉ።

〽️ለምሳሌ፦ Facebook Account እንዴት ሊሰርቁ እንደሚችሉ እንመልከት...

1⃣. Facebook page በመግባት Forget Account የሚለውን ይጫናሉ

2⃣. የናንተን User Name በመጠቀም Verification Number እንዲላክ ያደርጋሉ Fbookም ወደናንተ Verification Number ይልካል

3⃣. Fake Phone Number በመጠቀም የራሳቸውን Phishing SMS ወደናንተ ይልካሉ። የሚልኩት SMS ለምሳሌ ፦ የFacebook አካውንታችሁን በተሻለ Secure ለማድረግ የደረሳችሁን 6 digit Verification Number መልሰው ይላኩ

⚠️From Facebook Company

‼️Notes ፦ የሚደርሳችሁ በEnglish language ሊሆን ይችላል በተጨማሪም በጣም እውነት የመሰሉ SMS ነው የሚጠቀሙት እና የሞባይል ቁጥርም የሚፈልጉትን ሀገር መርጠው ሊጠቀሙ ስለሚችል በቀላሉ ልንሸወድ እንችላለን።

4⃣. 6 digit Verification Number ለነሱ ላክን ማለት BOOM Facebook አካውንታችንን በድጋሜ ልናገኘው አንችልም ማለት ነው።

‼️ ማስጠንቀቂያ ‼️

🔻በምንም አይነት ስልክ ቁጥር ይሁን ከየትኛውም አይነት ሀገር... ከላይ እንደገለፅኩት አይነት ጥያቄ ቢያቀርቡላችሁ የትኛውንም አይነት SMS እንዳትልኩ።
👍50❤8
ለተመራቂ ተማሪዎች የሪሰርች ፕረዘንቴሽን ፓወርፖይንት (PowerPoint) ማዘጋጀት እንዴት እንችላለን? ለተመራቂ ተማሪዎች How to prepare PowerPoint Presentation? ከታች ያለው ሊንክ በማየት መጠቀም ትችላላችሁ
👇👇👇ቪዲዮውን ይመልከቱት 👇👇👇

https://youtu.be/oNv5u8Ru-3Q

ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/c/MuhammedComputerTechnology
👍31🔥2😁2👎1
✅RAM
ራም (ራንደም አክሰስ ሜሞሪ) ኮምፒውተር በፍጥነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም (ኦኤስ) ፣ Application ፕሮግራሞች እና መረጃዎች በአሁኑ ወቅት በሚቀመጡበት የኮምፒተር መሣሪያ ውስጥ ሃርድዌር ነው ፡፡
#RAM የሚጠቅመው #የተቀሰቀሱ/የተከፈቱ #ፕሮግራሞች #በፍጥነት እንዲሰሩ የሚጠቅም ነው፡፡ የ RAM ተግባር በተለዋጭነቱ ምክንያት ራም ቋሚ መረጃዎችን ማከማቸት አይችልም።
ይህ ሊሆን የሚችለው #ኮምፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ #ፕሮግራሞች ለጊዜው (ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ) ለምሳሌ #HHD ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም #ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ #ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ከፍቷል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ከፍቷል #ፎቶ ወይም ቪዲዮ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና ቪዲዮ #ፕሮግራሞች ከፍቷል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች #እስከተከፈቱ ድረስ #ራም ለጊዜው ተሸክሞ ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር #የኮምፕዩተሩም #ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም፡፡ #ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ቦርድ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡

✅Hard_disk

#ዳታዎችን በቋሚነት #ለመያዝ ነው፡፡ #የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) #የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት #ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት #የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ የሆነ #ሰነድ ጽፈው ለመያዝ ከፈለጉ የሚይዘው #HHD ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው HHD ዋና ቦርድ ላይ የሰካል፡፡ HHD ዳታ ሲያነብና ሲጽፍ #ማግኔታዊ ነው
👍56❤3👏3
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአንድ ደቂቃ 50 ሳንቲም የአገልግሎት በማስከፈል ላይ ይገኛል
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ በ25 ከተሞች አገልግሎት እጀምራለሁ አለ።
ከሁለት ዓመት በፊት በወጣ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ጨረታ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያውን የደንበኞች የቴሌኮም አገልግሎቱን በድሬዳዋ አስጀምሯል።

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ከነሀሴ ጀምሮ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ኩባንያው በመነሻ ኮዱ 07 በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች አካሂዷል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮች ለድሬዳዋ ደንበኞቹ በመሸጫ ሱቆች ይፋ ያደረገ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር የሚቆይ የሙከራ አገልግሎት ተጀምሯል።
ድርጅቱ የድምጽ አገልግሎቱን በደቂቃ ከሳፋሪ ኮም ስልክ ቁጥሮች ወደ ሳፋሪኮም እና ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶች በደቂቃ 50 ሳንቲም የሚያስከፍል ሲሆን ለኢንተርኔት ደግሞ በ10 ብር 120 ሜጋ ባይት፣ 900 ሜጋ ባይቱን በ50 ብር እንዲሁም ሁለት ጌጋ ባይት መጠን ያለውን ኢንተርኔት ደግሞ በ100 ብር ለ30 ቀናት በመደበኛነት በመሸጥ ላይ ነው።
ኩባንያው አክሎም እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ 2015 ድረስ ባሉት ስምንት ወራት ውስጥ በ25 የኢትዮጵያ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደሚጀምር ለአልዓይን አስታውቋል።
አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ጅማ፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች ከተሞች በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል።

በኢትዮጵያ ከ126 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም ፈቃድ ተሰጠ

በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር እስከ 2023 ድረስ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ 25 በመቶ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለግማሹ ህዝብ እንዲሁም በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ ደግሞ 98 በመቶ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የቴሌኮም አገልግሎት የመስጠት እቅድ አለኝም ብሏል።
ሳፋሪኮም ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕን ያካተተ ነው።
ተቋሙ ዓለም አቀፍ አጋርነት ለኢትዮጵያ በሚል በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ህጋዊ ፍቃድ መቀበሉ ይታወሳል።

ምንጭ አል-ዐይን
👍60👎10🔥6❤1
ስለአመራር አምስት ዐባይት ስህተቶች
✅ አመራር እና ሥራ አመራር አንድ ናቸው፡፡ አመራር በሌሎች ሰዎች ላይ በጎ ተፅዕኖ በማሳደር
እንዲከተሉት ማድረግ ሲሆን ሥራ አመራር ደግሞ የሚያተኩረው አሰራሮች እና ሥርዓቶችን ባሉበት
መጠበቅ ላይ ነው፡፡
✅ ሥራ ፈጣሪዎች መሪዎች ናቸው፡፡ እውነታው ግን ሥራ ፈጣሪዎች መልካም አጋጣሚዎችን በመለየት
እና ከእነርሱ ገንዘብ የማግኘት ክህሎት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡
✅ ዕውቀት እና ጥሩ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ሰዎች መሪዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆኑን ብዙ
የዩኒቨርሲቲ መምህራን ምንም ዓይነት የአመራር መገለጫ የሌቸውም፡፡
✅ ከፊት የሄደ ሰው ሁሉ መሪ ነው፡፡ ከፊት መሄድ ብቻ ሳይሆን በፈቃደኝነት የሚከተሉአቸው ሰዎች
ጭምር ሊኖሩአቸው ይገባል፡፡
✅ ማዕረግ ወይም የተቋም የበላይ ኃላፊ መሆን የአመራር ምንነትን ይገልጻል፡፡ እውነታው ሲታይ ግን
አመራር ተጽዕኖ መፈጠር፣ ኃላፊነት እና ለተከታዮች ጥልቅ የፍቅር ስሜት መኖር ነው፡፡

🔶 የተለያዩ የአመራነት ስልጠና በመስጠት ላይ ነን
✅ ለመንግስታዊ ተቋማት
✅ ለግል ተቋሞች
እየሰጠን ሲሆን እናንተም ስልጠናውን ማግኘት ለምትፈልጉ
በስልክ ቁጥራችን

☎️+251940145151
ይደውሉ

ማለም ፥ ማመን ፥ ማሳካት !

👇👇👇የቴሌግራም አድራሻችንን ይጎብኙ👇👇👇
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership
https://t.me/visionleadership

ድረ ገጻችን ይጎብኙ
www.visionldf.com
www.visionldf.com
www.visionldf.com
👍28❤4😁1
ኮምፒውተራች ላይ save የተደረገ የWIFI ፓስዎርደ እዴት ማወቅ እንችላለን

follow these steps 👇👇👇
1 CMD እንከፈታለን
2 netsh በለን ከፃፈን በህዋላ 'enter' እነካለን
3 wlan show profile በለን ከፃፈን በህዋላ 'enter' እነካለን

ከዛ የWIFI ስም ዘርዘር ይመጣል

4 wlan show profile WIFINAME key=clear በለን ከፃፈን በህዋላ 'enter' እነካለን

WIFINAME የሚለውን በፈለግነዉ WIFI ስም እንቀይራለን

ከዛ ስለ WIFI ሙሉ information አናገኛለን
ከምናገኘው ዉስጥ
Key content የሚለው ጋር የተፃፈው password ነው
👍92🥰4👏4❤1
👍61👏12
እንኳን ደስ ያለን!
(ከላይ ያለውን ምስል ይመልከቱ!)
ልፋቴ፣ ድካሜ፣ ጥረቴ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳልል የወረቀትን አሰራር ዲጅታላይዝ እንዲሆን ላደረግኩበት የአእምሮ ጭማቂ ስራየ ፍሬ አፍርቶ እቅና ተሰጥቶኛል የስራው ውጤታማነት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት እውቅና ተሰጥቶታል!

እንደሚታወቀው ለአንድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የሰልጣኞችን መረጃ አያያዝ ስርዓት በማዘመን የወረቀት አሰራርን ዲጅታል ለማድረግ ብዙ ርቀቶችን ተጉዧለሁ ለዚህም ስራየ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ስራው ስራን የሚያቀልል፣ የሚያቀላጥፍ፣ ምቹና ለአሰራር በጣም ምርጥ ነው ይህንን ስራ በዘርፉ ላሉ የሀገራችን ፖሊ ቴክኒክና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆ ደረጃ ያልተተገበረ ብቸኛ ስራ ነው ሲል ጽ/ቤቱ የባለቤትነት መብቱን ለእኔ አጎናጽፎኛል።

ለዚህ ስራየ እውቅና ስለሰጣችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ!

ስራው ምንድን ነው? ምንስ ይሰራል?
ስራው ኮምፒውተራይዝድ የሬጅስትራር ሲሳተም ሲባል ለአንድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የሰልጣኞችን መረጃ አያያዝ ስርዓት አንድ Centralized Computer እንደ Server በመጠቀም መረጃችንን የሬጅስራር ሀላፊና ባለሙያዎችን እንዲሁም በተቀናጀ መልኩ ስራን እንዲሰሩና እንዲያሰሩ የሚያደርግ አሰራር ነው።

የቴክኖሎጅ ሀሳብና ስራ የመነሻ ሀሳብ፣ ችግሩ፣

1ኛ የመረጃ አያያዛችን ስርአታችን ኋላ ቀር የሚባለውን፣ ሀብት፣ ጉልበት፣ ጊዜ የሚፈጅና የሚጠይቅ አሰራር ስለሚሰራ ለማቀረትና ወደ ዲጂታሉ የቴክኖሎጂ አለም እያንዳንዱ ኮሌጅ፣ ክልላችን ብሎም ሀገራችን ውስጥ ያሉ ኮሌጆችን በማስተሳሰር የመረጃ አያያዛችን ወጥ በሆነ መልኩ ዲጂታ እንዲሆን በማሰብ

2ኛ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ ለምሳሌ ስንቱ የግልና የመንግስት ኮሌጆች አሰልጥነው ያስመረቋቸውን ሰልጣኞችን መረጃ ጠፍቶባቸው ወይም በሌላ ምክንያት የሚጉላላና የሚያለቅስ ሰው በመብዛቱ ይህንን ችግር ለመፍታት

3ኛ ፕሮጀክቱ እንደ ክልል ወጥ በሆነ መልኩ በክልላችን እያንዳንዱ ኮሌጅ ከዚህ በፊት ያስመረቃቸውንና ወደ ፊት የሚያስመርቃቸውን ሰልጣኞችን ሴንትራላይዝድ በሆነ መልኩ መረጃው ክልል ላይ እንዲቀመጥ ለማድርግ ይህም በመደረጉ ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦና ጥቅም እንዳለው ይታወቃል።

4ኛ ቴክኖሎጂው በመጠቀም በጣም ቀላል ሲሆን በአማርኛ የተዘጋጀ ሲሆን ማንኛውም ኮሌጅ ተግባራዊ ለማድረግ ቢፈልግ ባለሙያዎችና በ2 ቀን ስልጠና ብቻ ሰልጥነው ወደ ስራ መግባች ይችላሉ።

ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል
1ኛ ጥቅም መረጃ ማየትና መተንተን
2ኛ የሰልጣኞች certificate and trainee copy automatically ሲሳተሙ እንዲሰራው ተደርጓል

3ኛ አንድ ሰልጣኝ መረጃውን ሲወስድ የወሰደውን መረጃ በፎቶ በማስቀረት ሲሳተሙ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል
ኮሌጁ
4ኛ ሰልጣኞች ኮልልጅ ውስጥ የሚከፍላቸውን ክፍያዎች አብሮ ዲጂታል በሆነ መልኩ ምዝገባው እንዲዲያዝ ተደርጓል።
4ኛ የኮሌጅ ውስጥ የCOC የምዝገባ ቅጹን መሰረት በማድረግ ከዚህ በፊት በወረቀት የነበረው የምዝገባ ስርአት እንዲካተት ተደርጓል።
5ኛ የሬጅስትራር ባለሙያዎች የሚይዟቸውና የሚያስተደድሯቸው ሙያዎች ስለሆነ የሚመለከታቸውን ሙያ እንዲይዙና እንዲያስተዳድሩ ያደርጋል ለምሳሌ አንድ ባለሙያ ICT, Construction መያዝ ቢኖትበት እነዚህን ሙያዎችን ብቻ ይዞ በሀላፊነት ይሰራል።
6ኛ ከመረጃ ደህንነት አንጻር Database Backup በማድረግ በየጊዜው መረጃው የሚያዝ ይሆናል።

7ኛ ማንም ሰልጣኝ ቢመጣ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብቻ የሚፈልገውን አገልግሎት አግኝቶ መሄድ ይችላል።
8ኛ በሬጅስትራር ቢሮ ውስጥ ያሉ ሁሉም የባለሙያዎችና የአስተባባሪውን ኮምፒውተር ጨምሮ በLocal Area Network (LAN) የተያያዙ ሲሆን 1 ኮምፒውተር ሲስተሙ የሚቀመጥበት እንደ ሰርቨር ተጠቅምን መረጃውን በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ Access እንዲደረግ ተደርጎ ነው የተሰራው።

እነዚህ ዋና ዋና የሲስተሙ ተግባሮች ሲሆኑ በጣም ብዙ የተካተቱ ነገሮች አሉት!

በእያንዳንዱ ኮሌጅ ተግባራዊ ቢደረግ ምንም አይነት ውጭ የማያስወጣ፣ ቀላል፣ ቀልጣፋ፣ ፈጣን፣ ነው። ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀማችን በዜሮ ውጭ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው ለማለት እወዳለሁ።

ስራው ተግባራዊ የሆነበት ቦታ

1ኛ በአማራ ክልል እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
2ኛ በደቡብ ክልል ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

ስራውን የትኛውም የሀገራችን ክፍል ላሉ የግልና የመንግስት ኮሌጆች ለማግኘት ከፈለጉ በተመጣጣኝ ክፍያ መውሰድ የሚቻል መሆኑን እገልጻለሁ።

ስለሆነም አሰራራችንን ዲጅታላይዝ በማድረግ ስራችንን ፈጣን፣ ቀልጣፍ፣ ምቹና ቀላል እናድርግ!

የምን ተስፋ መቁረጥ! አሁንም ወደፊት ወደ ዘመናዊነት!

ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ ከጥቅሙ፣ ከተፈላጊነቱ አንጻር
ሙሀመድ አሚን
የስራ ቦታ እንጂባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ሀለፊነት የኮሌጁ ምክትል ዲንና የኢ/ኤ/ቴ/ሽ ቡድን መሪ
ስ.ቁ 0929273364
የቢሮ ስልክ +251-(0) 58227 1395
እንጅባራ
❤‍🔥192👍144👏37❤33😁2
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ብዙ ማስታወሻ የሚወስዱ አፕሊኬሽኖች አሉ ነገርግን ብዙ ሰዎች እንደ Google Keep፣ Evernote ወይም Microsoft OneNote ባሉ ትልልቅ ስሞች ላይ ይሳቡ ይሆናል።
አዲስ ነገር ለመሞከር ከፈለጉ፣ WeNoteን ይመልከቱ።
ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ የእርስዎ ማስታወሻዎች፣ የተግባር ዝርዝሮች፣ አስታዋሾች ወዘተ መተግበሪያ ነው፣ ነገር ግን እንደ አዶ ለማስታወሻዎች ማበጀት፣ የይለፍ ቃሎች ጀርባ ማስታወሻዎችን መቆለፍ፣ ማስታወሻዎችን በሁኔታ አሞሌዎ ላይ መጣበቅ እና ሌሎች ብዙ ባህሪያትን የያዘ መተግበሪያ ነው።

ፕለይስቶር ላይ በመግባት ወደ ስልካችን መጫን እንችላለን።
ይህች አፕልኬሽን ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ እንዲሁም በማንኛውም የሶሻል ሚዲያ ላይ የምናገኛቸውን ማስታወሻዎችን ለመያዝ ያገለግላል።

ማስታወሻ ለመያዝና መጻፍ ብትፈልጉ ይህችንን አፕልኬሽን በመጠቀም ኖት መያዝ እንችላለን።
ይህ አፕልኬሽን ከጎግል ድራይቭ ጋር በማገናኘት አፕልኬሽኑ ላይ የተቀመጡት ማስታዎሻዎች በየግዜው ባክአፕ መያዝ ትችላላችሁ። ይህ ጥቅም(ባክአፕ) ለምሳሌ አፕልኬሽኑ ቢጠፋ፣ ዲሌት ቢሆን፣ ስልኩ ቢጠፋ፣ ስልኩ ቢበላሽ፣ በሌላ ስልክ ከፍተን ማስታወሻውን እንደገና ማግኘት ያስችለናል።
ባክአፕ ለማድረግ ኢሜይል የሚጠይቅ ሲሆን ኢሜይል አድራሻ በማስገባት መረጃውን መያዝ ያስችለናል።
ሌላው ጥቅም
በፈለግነው ካታጎሪ ስያሜ በመስጠት ማዘጋጀት ያስችለናል።
ℹ️ ካላንደር የተዘጋጀለት ነው።
ℹ️ በፈለግነው View style ለእይታ ምቹ በሚሆን መልኩ እንድናዘጋጅ ያደርገናል።
ℹ️ በፍጥነት የገለግነውን መረጃ ጽሁፍ በመጻፍ ከኖታችን ላይ እንድንፈልግ ያስችለናል።
ℹ️ በፈለግነው አይነት Sorting type ሶርት ማድረግ ያስችለናል።

እንዲሁም የተለየ መተግበሪያ ሳያስፈልግዎት አስታዋሾችን ለመከታተል አብሮ የተሰራ የቀን መቁጠሪያ አለው፣ እና እንዲሁም በጭራሽ መረጃዎትን እንዳያጡ ከ Google Drive ጋር ማስተሳሰር ይችላል።


መተግበሪያው እንደ ፕሌይ ስቶር መግለጫው የሚያቀርባቸው ባህሪያት ዝርዝር ይኸውና።
✅ የቀለም ማስታወሻዎችን እና የተግባር ዝርዝሮችን መፍጠር ይችላሉ።
✅ ስዕሎችን፣ ስዕሎችን፣ ወይም የእጅ ጽሑፍን እንደ አባሪ በመጨመር መረጃ እንድንይዝ ያደርገናል።
✅ ማስታወሻዎችን፣ የተግባር ዝርዝሮችን ወይም መተግበሪያውን በራሱ በፒን ፣ በይለፍ ቃል ወይም በጣት አሻራ መቆልፍ እንችላለን።
✅ ከ2 የተለያዩ የቅርጸ አይነቶች፣ 5 የተለያዩ የቅርጸ መጠኖች፣ 4 የተለያዩ ገጽታዎች (ጨለማ ሞድ)፣ 5 የተለያዩ እይታዎች፣ 6 የተለያዩ የመደርደር ሁነታዎች እና 12 ምርጫዎችን ቀለም መቀባት እንድትችሉ ተደርጎ የተሰራ ነው።
✅ አስታዋሾች (ሊበጁ የሚችሉ እና በየቀኑ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ ወይም አመታዊ) እና የቀን መቁጠሪያ (ከጨረቃ ቀን መቁጠሪያ ድጋፍ ጋር፣ ግን ምንም የGoogle Calendar ውህደት የለም)
✅ የምትፈልጉትን ማስታወሻ ፒን ማድረግ ያስችላችኋል።
✅ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ከ Google Drive ጋር ማገናኘት ይችላሉ ስለዚህ ማስታወሻዎችን ባክአፕ ያድርጉ
✅ ማስታወሻዎችን እና አባሪዎችን ለኢሜል፣ ኤስኤምኤስ፣ ማህበራዊ አውታረ መረብ እና የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያዎች ማጋራት ይችላሉ።
✅ ከሌሎች መተግበሪያዎች የተጋሩ ማስታወሻዎችን እና አባሪዎችን መቀበል ይችላሉ።
✅ ፈጣን የሆነ ፍለጋ
👍57❤1👎1
Python programming language ምንድን ነው?
Python ታዋቂ የፕሮግራም ቋንቋ ነው።
የተፈጠረው በጊዶ ቫን ሮስም ነው፣ እና በ1991 ተለቀቀ።
ይህ open-source programming language በብዛት በሶፍትዌር ኢንጂነሮች ጥቅም ላይ የሚውል ስሆን የ #back-end Web developers በአሁኑ ግዜ ዕይታቸውን ወደ ፖይተን አዙረዋል። Python ለሳይንትፊክ ካልኩለሽን እንድሁም ሰው ሰራሽ ክህሎት artificial intelligent ዋነኛ ነው ። ከሌሎች አንፃር ለመልመድ ቀላል ነው ።
ከዚህም ውጭ እጅግ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ፓይተን። ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ አስገራም ኮዶች መፃፍ እስክትችሉ ድረስ ተቃሎ በስልኮች ላይ መቷል።

ጥቅም ላይ የሚውለው ለ:
✅ የድር ልማት(web development)(server side) ፣
✅ የሶፍትዌር ልማት ፣
✅ ለሂሳብ፣
✅የስርዓት ስክሪፕት.

ፓይቶን በጣም ቀላል ቋንቋ ነው ፣ እና በጣም ቀጥተኛ አገባብ አለው። የፕሮግራም አዘጋጆች ያለ ቦይፕሌት (ዝግጁ) ኮድ ፕሮግራም እንዲያወጡ ያበረታታል። በፓይቶን ውስጥ በጣም ቀላሉ መመሪያ የ “ህትመት” መመሪያ ነው - እሱ በቀላሉ መስመርን ያትማል (እንዲሁም ከ C በተለየ መልኩ አዲስ መስመርን ያጠቃልላል) ፡፡

ፓይቶን ለመማር ቀላል ፣ ኃይለኛ የፕሮግራም ቋንቋ ነው ፡፡ ቀልጣፋ የከፍተኛ ደረጃ የመረጃ አወቃቀሮች እና ለዕቃ-ተኮር መርሃግብር ቀላል ግን ውጤታማ አቀራረብ አለው ፡፡ የፒቶን የሚያምር አገባብ እና ተለዋዋጭ ትየባ ፣ ከተተረጎመው ተፈጥሮው ጋር ፣ በአብዛኛዎቹ መድረኮች ላይ በብዙ አካባቢዎች ለስክሪፕት እና ፈጣን የትግበራ ልማት ተስማሚ ቋንቋ ያደርጉታል ፡፡

ፓይዘን ተተርጉሟል - ፓይተን በአስተርጓሚው በሚሠራበት ጊዜ ይሠራል ፡፡ ፕሮግራምዎን ከመፈፀምዎ በፊት ማጠናቀር አያስፈልግዎትም ፡፡ ይህ ከ PERL እና ከ PHP ጋር ተመሳሳይ ነው።

ፓይቶን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፣ በተፈጥሮ ቋንቋ ትውልድ ፣ በነርቭ ኔትወርኮች እና በሌሎችም በኮምፕዩተር ሳይንስ የላቁ መስኮች በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ ፓይቶን በኮድ ተነባቢነት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ነበረው እናም ይህ ክፍል ከመሰረታዊ ነገሮች ፓይቶን ያስተምራዎታል ፡፡ ስለዚህ AI ወይም ጥልቅ ትምህርት መማር መጀመር ከፈለጉ ፡፡ ፒቶን መማር ታላቅ ጅምር ነው!

🔴 Python ምን ማድረግ ይችላል?
✅ ፓይተን የድር መተግበሪያዎችን ለመፍጠር በአገልጋይ ላይ መጠቀም ይችላል።
✅ የስራ ፍሰቶችን ለመፍጠር Python ከሶፍትዌር ጋር አብሮ መጠቀም ይችላል።
✅ Python ከመረጃ ቋት ስርዓቶች ጋር መገናኘት ይችላል። እንዲሁም ፋይሎችን ማንበብ እና ማሻሻል ይችላል።
✅ Python ትልቅ መረጃን ለማስተናገድ እና ውስብስብ ሂሳብን ለመስራት ሊያገለግል ይችላል።
✅ Python ለፈጣን ፕሮቶታይፕ፣ ወይም ለምርት ዝግጁ የሆነ ሶፍትዌር ልማት ሊያገለግል ይችላል።

🔴 ለምን Python?
✅ ፓይትርን በተለያዩ መድረኮች (Windows፣ Mac፣ Linux፣ Raspberry Pi፣ ወዘተ) ላይ ይሰራል።
✅ Python ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቀላል አገባብ አለው።
✅ ፓይተን ገንቢዎች ከሌሎች የፕሮግራም አወጣጥ ቋንቋዎች ባነሱ መስመሮች እንዲጽፉ የሚያስችል አገባብ አለው።
✅ ፓይተን የሚሠራው በአስተርጓሚ ስርዓት ነው፣ ይህ ማለት ኮዱ ልክ እንደተጻፈ ሊተገበር ይችላል።
ይህ ማለት ፕሮቶታይፕ በጣም ፈጣን ሊሆን ይችላል.
✅ ፓይትርን በሥርዓት፣ በነገር ተኮር መንገድ ወይም በተግባራዊ መንገድ ሊታከም ይችላል።

🔴 ማወቁ ጥሩ ነው
✅ በጣም የቅርብ ጊዜ ዋናው የፓይዘን ስሪት Python 3 ነው፣ እሱም በዚህ አጋዥ ስልጠና ውስጥ የምንጠቀመው።
✅ ሆኖም፣ Python 2፣ ምንም እንኳን ከደህንነት ዝመናዎች በስተቀር በሌላ ነገር ባይዘመንም አሁንም በጣም ተወዳጅ ነው።
✅ በዚህ ማጠናከሪያ ትምህርት Python በጽሑፍ አርታኢ ውስጥ ይጻፋል።
እንደ ቶኒ፣ ፒቻርም፣ ኔትቤንስ ወይም ግርዶሽ ባሉ የተቀናጀ ልማት አካባቢ ፓይተንን መፃፍ ይቻላል በተለይ ትላልቅ የፓይተን ፋይሎችን ሲያቀናብሩ ጠቃሚ ናቸው።

ምሳሌ print("Hello, World!")
👍55❤8👏2
How to write CV
በቀጣሪዎች ዘንድ ተመራጭ CV እንዴት መፃፍ ይቻላል፡፡
CV ማለት የአንድ ሰው የትምህርትና ሌሎች professional ታሪኮቹን በአጭር መልኩ የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡ ብዙ ግዜ ለስራ ማመልከቻነት እንጠቀምበታለን የራሳችንንም ማንነት በጥሩና ቀለል ባለ መልኩ ለማቅረብ ያስችለናል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት እንዲቀጥሩን ለምንፈልጋቸው ቀጣሪዎች አሰልቺ ያልሆነና ሳቢ የሆነ CV መፃፍ ትልቅ ትኩረት ለማግኘት ያስችለናል፡፡
ታዲያ እንዴት እንዲህ ያለውን CV መፃፍ እንችላለን እና ምን ምን መካተት አለበት የሚለውን እንመልከት፡፡
1 ከቀድሞ ስራ ጋር የተያያዙ የስራ ልምዶች፡፡
2 የትምህርት ሁኔታ እና ሌሎች ተዛማጅ ችሎታዎች
3 አፃፃፋችሁን ለማንበብ እና ለመረዳት ቀለል ባለመልኩ ይሁን
4 የስራ ልምድ ካላችሁ በቀደመው ስራችሁ ያሳካችኋቸውን ነገሮች ጥቀሱ፡፡ ጀማሪ ከሆናችሁ ደግሞ በነፃ አገልግሎት እንዲሁም በተማራችሁበት የትምህርት ተቋም ስታደርጉ የነበረውን መልካም እንቅስቃሴ ጥቀሱ፡፡
5 ፊደላት እና ቃላት አጠቃቀም ትኩረት ማድረግ ፡፡
6 እናንተ በመስሪያ ቤቱ ብትቀጠሩ ልታበረክቱ የምትፈልጉትንና እናንተ በመቀጠራችሁ በመስሪያ ቤቱ
ስኬት ላይ ልትጨምሩ የምትፈልጉትን ጥቀሱ
7 አድራሻችሁን ስትጠቅሱ የተለያዩ አማራጮችን አስቀምጡ፡ ስልክ ኢሜይል፡፡
8 ሪፈረንስ ስትጠቅሱ ስለእናንተ በደንብ ሊገልፅ የሚችል ሰው ይሁን፡፡
9 ከሁለት ገፅ ባይበልጥ መልካም ነው አሰለቺ እንዳይሆን ተጠንቀቁ፡፡
👍122👏8🥰1