Muhammed Computer Technology (MCT)
37.6K subscribers
528 photos
7 videos
254 files
913 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
✅ ኮምፒውተር ላይ በፎልደር ውስጥ ያለን ፋይል እንዴት ሌላ ሰው እንዳይከፍትብንና Delete እንዳያደርግብን ማድረግ እንችላለንን?
✅ ከኮምፒውተር፣ ከፍላሽ፣ ከሀርድዲስክ ያለን ፋይል እንዴት መደበቅ እንችላለን? እንደገና ደግሞ ከደበቅንበት ማውጣት እንችላለን?
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ይመልከቱት!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/4IdgIEE675s
https://youtu.be/4IdgIEE675s
https://youtu.be/4IdgIEE675s
https://youtu.be/4IdgIEE675s
👍3
መረጃ የሚሰርቀው የቻርጀር ገመድ
*******************************
ማርክ ግሪን የተባለ የደህንነት ተመራማሪ OMG የተሰኘው የቻርጀር ገመድ የተጠቃሚውን መረጃ በመውሰድ ወደ ሌላ ቦታ እንዲያስተላልፍ አድርጎ መስራቱ ተነገረ፡፡ ይህም ገመድ በተለይ ሀከሮች (የመረጃ መንታፊዎች) ከተለያዩ ኮምፒውተሮችና የሞባይል ስልኮች ላይ የሚፈልጉትን መረጃ ማስተላለፍ እንዲችሉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡ ገመዱ ከተሰካበት ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ ያሉ የይለፍ ቃላትንና ሌሎች ምስጢራዊ መረጃዎችን ለመመንተፍ ሁነኛ ዘዴ ተደርጎም ተወስዷል፡፡
ከዚህ በፊት የነበረው ላይትኒንግ የተሰኘው ገመድ ስልኮቻችንን ከኮምፒውተር ጋር በማያያዝ ሀይል መሙላት የሚያስችል የነበረ ሲሆን ማርክ ግሪንና ጓደኞቹ ለዚህ ገመድ ማሻሻያ አድርገውለታል፡፡ አሁን ላይ ገመዱ መረጃን አከማችቶ ከመያዝ በተጨማሪ በውስጡ በተገጠመለት የ WiFi ቺፕ አማካኝነት መረጃውን ወደ ሌሎች ቦታዎች ማስተላለፍ ይችላል፡፡
ማርክ ግሪን ይህንን ገመድ በዚህ መልክ ያሻሻለበትን ምንያት ሲናገር በቴክኖሎጂው ዙሪያ ያሉ ሰዎች ይህን ማድረግ አይቻልም የሚል እምነት የነበራችው በመሆኑ፤ በተለይም መረጃን ለማከማቸት እና ለማስተላለፍ የሚረዱ ቁሶችን በገመዱ ውስጥ መግጠም ያስቸግራል ስለሚሉ ይህ እንደሚቻል ለማሳየት እንደሆነ ተናግሯል፡፡
አንድ ሰው ይህን ገመድ በመጠቀም ስልኩን ቻርጅ ሲሞላ ወይም መረጃ ሲያስተላልፍ ገመዱ ስራውን ውስጥ ለውስጥ ይሰራል፡፡ ሀከሮችም ገመዱ የሚሰራውን ስለሚያውቁ ባዘጋጁት የመረጃ ቋት በኩል ሆነው ይጠባበቃሉ፡፡
ይህም የሚያሳየን የምንጠቀማቸውን ኬብሎች ምንነት መለየት እንዳለብን ነው፡፡ በተለይ ከፍተኛ የሆኑ ሀገራዊ ተቋማትና ድርጅቶች ውስጥ የምንጠቀማቸው የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ምንነት በሙያተኛ ተጣርቶ መጠቀም ይገባናል፡፡
ምንጭ techxplore
(Technology and Innovation Institute, Ethiopia)
👍4
ትዊተር አጠቃቀምና አከፋፈት በአጭሩ
ሱሌማን አብደላ
ፖስት ስታደርጉ ቢያንስ 30 ደቂቃ እየጠበቃችሁ ይሁን። ሪቲዊትም ስታደርጉም እንደዚሁ 30 ደቂቃ እየጠበቃችሁ ይሁን። የጥላቻ ንግግር አንዲትም ቃል ትሁን አትቀላቅሉ። follow ስታደርጉ ቢያንስ በ20 ደቂቃ ውስጥ አንድ ሰው ብቻ አድርጉ።
..
Twitter አካውንት ከፍታችሁ ስልክ ቁጥር ጨምራችሁ ስልኩን አልቀበልም ላላችሁና
የሚስጥር ቁጥር አልክም ላላችሁ
ጎግል ክሮም ከሌላችሁ አውርዱ ካላችሁ
እዛው ጎግል ክሮም ላይ ( www Twitter .com ) ብላችሁ ሰርች አድርጋችሁ አዲስ አካውንት መክፈት ትችላላችሁ
ስትከፍቱ
_ትክክለኛ ስማችሁን
_ኢሜላችሁን
_የተወለዳችሁበትን ቀን እና አ_ም
የምትከፍቱት በስልክ ቁጥር አይደለም በምትጠቀሙበት ኢሜይል ነው። ከላይ እንዳልኩት ስልክ ቁጥራችሁን አልቀበል ላላችሁና የሚስጥር ቁጥር አልክም ላላችሁ ነው ። ኢሜላችሁ መልዕክት መቀበል የሚችል መሆን አለበ። ይሄንን አስተካክላችሁ ከተጠቀማችሁ ፓስወርድ ወይም የሚስጥር ቁጥር በምን ልላክላች ብሎ አማራጭ ይጠቃችኋል።
ስልክ ቁጥር አትጨምሩ
እታች ኢሜይል የሚል አለ እሷን ትነካላችሁ
ከዛ ቀጥታ በኢሜል ይልክላችሏል። የተላከውን ቁጥር ታስገባችሁ ።ይከፍታል ትክክለኛ የናተን ፎቶ እና profile አድርጉ
skip የሚለውን ስትነኩት ይከፍታል። የምትፈልጉትን ምንድን ነው ዜና? እግርኳስ ? ..ወዘተ አማራጭ ያመጣላችኋል።
ዜና ከሆነ የእናንተ ምርጫ News የሚለውን ብቻ ለአንድ ቀን ምረጡ። ኢትዮጵያዊያን ሆነው ትዊተር የሚጠቀሙ ሰዎችን ለመከታተል ከፈጋጋችሁ ሰርች የሚለውን ተጭናችሁ
@... የፈለጋችሁትን ሰው ስም ፅፋችሁ ሰርች አድርጋችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።
ለሀገር እና ለህዝብ ለመታገል የቲዊተር አካውንት አውጡ
👍3
እንኳን ለ2014 በሰላም አደረሳችሁ። አዲሱ አመት የሠላም የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ፣ እንዲሁም አዲስ ተስፋ ፣ ራዕይ ፣እቅድ የምታዩበት እንዲሆንላችሁ ከልቤ እመኝላችኋለሁ።
፧
፧
❤❤❤መልካም አዲስ አመት❤❤❤ለሁሉም።
👍2
የኮምፒውተር ስክሪን ወደ ፈለጋችሁት አቅጣጫ ለማዞር(ለመገልበጥ)
🔷 CTRL and ALT keys, press UP ARROW , መደበኛ(ትክክለኛ) የስክሪን እይታ

🔷 CTRL + ALT + DOWN ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደታች ይገለበጣል

🔷 CTRL + ALT + LEFT ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደ ግራ ይገለጣል.

🔷 CTRL + ALT + RIGHT ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደ ቀኝ ይገለበጣል
ሞክሩት ከዚህ በፊት ስክሪኑ ተገልብጦባችሁ ደንግጣችሁ ከነበር በዚህ መንገድ መቀያየር ትችላላችሁ።
ይሞክሩት
RAM, HARD DISK AND POWER SUPPLY ምንድን ናቸው?
✅RAM
ራም (ራንደም አክሰስ ሜሞሪ) ኮምፒውተር በፍጥነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም (ኦኤስ) ፣ Application ፕሮግራሞች እና መረጃዎች በአሁኑ ወቅት በሚቀመጡበት የኮምፒተር መሣሪያ ውስጥ ሃርድዌር ነው ፡፡
#RAM የሚጠቅመው #የተቀሰቀሱ/የተከፈቱ #ፕሮግራሞች #በፍጥነት እንዲሰሩ የሚጠቅም ነው፡፡ የ RAM ተግባር በተለዋጭነቱ ምክንያት ራም ቋሚ መረጃዎችን ማከማቸት አይችልም።
ይህ ሊሆን የሚችለው #ኮምፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ #ፕሮግራሞች ለጊዜው (ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ) ለምሳሌ #HHD ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም #ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ #ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ከፍቷል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ከፍቷል #ፎቶ ወይም ቪዲዮ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና ቪዲዮ #ፕሮግራሞች ከፍቷል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች #እስከተከፈቱ ድረስ #ራም ለጊዜው ተሸክሞ ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር #የኮምፕዩተሩም #ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም፡፡ #ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ቦርድ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡

✅Hard_disk

#ዳታዎችን በቋሚነት #ለመያዝ ነው፡፡ #የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) #የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት #ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት #የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ የሆነ #ሰነድ ጽፈው ለመያዝ ከፈለጉ የሚይዘው #HHD ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው HHD ዋና ቦርድ ላይ የሰካል፡፡ HHD ዳታ ሲያነብና ሲጽፍ #ማግኔታዊ ነው

#Power_Supply

#የኤሌክትሪክ ሃይልን መጥኖ #ለተለያዩ የአካል ክፍሎች ማደል ነው፡፡ ሁሉም #የኮምፕዩተር አካል ክፍሎች #አንድ አይነት የኤሌክትሪክ ሃይል #(ቮልት) አይጠቀሙም፡፡ ስለዚህ የሃይል #አዳዩ ቮልቱን መጥኖ ለሁሉም ክፍሎች ይልካል፡፡ #ለምሳሌ 12 ቮልት፣ 9 ቮልት፣ 6 ቮልት፣ 48ቮልት ሊሆን ይችላል፡፡ #ፓወር ሳፕላይ እራሱን የቻለ #ማራገቢያ አለው #Power Supply Fan ይባላል፡፡

እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍8
✍ የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው?
🔸Network ሰጪ ድርጅቶች በመላው አለም ላይ ይገኛሉ። በሀገራችንም ethio telecom ይገኛል። በሌሎች ሀገራት ደግሞ ከ አንድ በላይ network አቅራቢ ድርጅቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት በመንግስት ስር ሳይሆን በግል ተቋማት ስር ስለሆኑ ነው።ለዚህም ጎሮቤታችን Kenya ጥሩ ማሳያ ናት። ከአንድ በላይ የመኖሩ ጥቅም ህዝቡ የተሻለ አማራጭ ያገኛል ድርጅቶቹም የተሻለ ነገር ለማቅረብ ፉክክር ዉስጥ ይገባሉ። አንድ አንድ network ሰጪ ድርጅቶች ደግሞ አለም አቀፍ እውቅና አላቸው።
🔘ለምሳሌ T-mobile, verizon, orange, vodafone.....
እነዚህ ድርጅቶች ከሚፎካክሩቸው መንገዶች አንዱ ደንበኞችን ለመሳብ ሲሉ የስልክ ቀፎዎችን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ። ይህን የሚያደርጉት ደንበኞቻቸው የአየር ሰአት በገዛቸዉ ቁጥር ተጠቃሚ ስለሚሆኑ ነው። ነገር ግን በዚህ መንገድ የተገዙ የስልክ ቀፎዎች ከተገዙበት የnetwork ሰጪ ተቋማት ውጪ ያሉ sim cardoችን አይቀበሉም ይህም ምክንያቱ በ security code ስለሚቆለፉ ነው። እንደዚህ አይነት ስልኮች ሀገር ስለቀየሩ ሳይሆን እንቢ የሚሉት ከተገዙበት የ network ሰጪ ድርጅት ዉጪ ባሉ network ሰጪ ድርጅቶች sim card ስለማይሰሩ ነው።

🔹የተዘጉ ስልኮች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ።
Sim not valid, wrong sim,unknown sim, phone restricted, contact service provider.....

🔘ከ network ሰጪ ድርጅቶች የተገዛ ስልክ ለመክፈት ሁለት መንገድ አለ።

✅1. Computer , flasher box, እና flasher file በመጠቀም መክፈት ይቻላል።
▪️ይህ ዘዴ አሁን ላይ ethio telecome የሚዘጋቸውን ስልኮችንም ይመለከታል ነገር ግን በዚህ Method ለመክፈት Computer, flasher box እና flasher file ያስፈልገናል።
🔺ስለ Computer ማብራራት አያስፈገኝም ነገር ግን በዚህ Method ትንሽ አሸጋሪ የሚሆነው Universal flasher box ማግኘት ነው ይሄ box የተለያዩ ጥቅሞች ሲኖሩት ከዚህም ውስጥ በስልኩ ሞዴል የራሱን flasher file ከ Google ላይ በማወረድ ከስልኮቻችን ጋር በማገናኘት የትኛውንም ስልክ ማስተካከል እንችላለን ከ hardware ውጪ ምንም አይነት ችግሮችን እንድናስተካክል ያስችለናል።
🔺ይህ universal flasher Box orginale ስልኮችን IMEI create በማድረግ አሁን ላይ ላለው ethio telecome ለሚዘጋቸው ስልኮች ፍቱን መድሃኒት ሲሆን የ flasher box ዋጋ በ Ethiopia 4326birr አከባቢ ሲሆን የተወሰኑ ሞባይል ቤቶች በ addis abeba እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
▫️ለምሳሌ ለመጠቆም ያህል መርካቶ ይርጋ ሃይሌ building ላይ ይህን flasher box ማግኘት ይችላሉ።

✅ 2. ለ ድርጅቱ መጠነኛ ክፍያ በመፈጸም ማስከፈት ሲሆን:-
▪️ለምሳሌ iphone በ icloud የተዘጉ ስልኮችን መጥቀስ ይቻላል እንደዚህ አይነት ስልኮች የ e-commerce እንዲሁም credit card ይጠይቃሉ። ይሄ አገልግሎት ደግሞ እኛ ሀገር ስለሌለ ያለው አማራጭ ውጭ ሀገር በምናቀው ሰው ማስከፈት ነው። ይህ ማለት ድህረ ገፁ ላይ ግብተን የስልኩን ሞዴል ስናስገባ ክፍያ ይጠይቀናል ክፍያውም የሚከናወነው በ ማስተር ካርድ ስለሆነ ክፍያውን ውጪ ሃገር ማስተር ካርድ ባለው ሰው ከባላንሱ ላይ እንዲፈፅምልን በማድረግ ክፍያው ከተፈጸመላቸው ድርጅቱ ኮዱን በሚያስገባው Email አድሬስ ስለሚልክልን ወድያውኑ መክፈት ይቻላል።
⚠️ በ icloud የተዘጉ ስልኮች በማስተር ካርድ በ አሁን ጊዜ የሚያስከፈለው 104$ ዶላር ነው ለዚህም ነው በአዲስ አበባ በተለያዩ የ ሞባይል ቤቶች በተለይ መርካቶ ላይ ከ200$ ዶላር በላይ የሚጠይቁት ጥቅማቸውን በማሰብ ማለት ነው። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለባችሁ ውጪ ሃገር ላይ የ ማስተር ካርድ ቪዛ ኮዱን አስገብቶ ክፍያውን ሊፈፅምላችሁ እና በ Email የሚላክለትን Code ሊልክላችሁ የሚችል ወዳጅ ከሌላችሁ ምንም አይነት አማራጭ የላችሁም ከ200$ ዶላር በላይ ከፍለን ከማስከፈት ውጪ ስልኩን መጠቀም አንችልም።
👍10👏1
✳️ሜሴጅ መቀበል📥 እንጂ መላክ📤 የማይችል⚠️ ስልክ📲 ቢገጥመን ምን እናረጋለን?

◾️ከታች👇 ያለውን #Step ይከተሉ ⬇️

Step 1 :-Menu

Step 2:-Massage

Step 3:-Massage setting

Step 4:-Text massage

Step 5:-Massage center

Step 6:-Massage center number በሚለው ቦታ ላይ +251911299708 መሙላት ተስተካከለ ማለት ነው።

እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍4
በኮምፒውተራችን ላየሆኑ hidden የሆኑ ፉይሎች ለማግኘት እንዳስቀመጥናቸው እርግጠኛ የሆናቸው
(ከላይ ያለውን ምስሉን ይመልከቱ!)
ፋይሎችእና ፎልደሮች ተደብቀው ነገር ግን ከእይታችን ሊሰወሩ ይችላሉ፡፡ ይህ በሚያጋጥመን ጊዜ ኮምፒውተራችን እንዲያሳየን የሚደርገውን ቅንብር በማስተካከል እንድንመለከት ያስችለናል ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቅደም ተከተል የተቀመጡትንመንገዶች በመከተል የኮምፒውተርዎን ቅንብር ያስተካክሉ፡ –
1. Start የሚለው ምልክት በመጀመርሪያ እንመርጣለን
2 በመቀጠል ኮንትሮል ፓናል (control panel)
3. ከሚቀርቡለን ምርጫ ውስጥ Appearance and
Personalizationየሚለው ላይ ክሊክ እናደርጋለን
4. ቪው (view) የሚለውን እንጫናለን ከዚያ አድቫንስድ
ሴቲንግ (advancing setting) እናገኛለን
5. በመጨረሻም Show hidden files, folders, anddrives ክሊክ ካደረግን በኋላ ok የሚለውን መርጠን እናጠናቅቃለን፡፡
ሌላ አማርጭ
አንዳንድ ጊዜ በፍላሽ ዲስክ የያዝነው መረጃ ይደበቅብናል። ከተደበቀበት ሁሉንም ፎልደሮችና ፋይሎችን ለማውጣት ስንፈልግ ከይ በጠቀስኩት አግባብ ለምሳሌ ፍላሽ ዲስካችን Removable Disk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን እንጫንና attrib -s -h /s /d ብለን እንጽግና ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ሁሉም የተደበቀው ፋይል ሁሉ ይወጣልናል ማለት ነው። ሞክሩትና እዩት!

ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም #Subscribe በማድረህ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
👍5
አፕል የረቀቁ የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችን አስተዋወቀ

ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል ከዚህ ቀደም ከነበሩት የላቁ ናቸው የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችንና አዲስ አይፓድ አስተዋወቀ።

በዚህም አፕል አራት ስልኮችን ያስተዋወቀ ሲሆን እነሱም አይፎን 13 ሚኒ፣ አይፎን 13፣ አይፎን 13 ፕሮ እና አይፎን 13 ፕሮ ማክስ የተባሉ ናቸው።

አይፎን 13 ፕሮ እና አይፎን 13 ፕሮ ማክስ ከጀርባቸው ሦስት ካሜራዎች ተገጥመውላቸዋል። አፕል ካሜራዎቹ "እጅጉን የረቀቁ የካሜራ ሥርዓት ናቸው"

13 ስልኮች ከተለመዱት በተጨማሪ በሮዝ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለማት አሸብረቀው መጥተዋል።

አዳዲሶቹ አይፎኖች ሚሞሪ መጠንም ወደ 500 ጊጋ ባይት ከፍ ብሏል። በአይፎን-12 ምርቶች ውስጥ ዝቀተኛ ሚሞሪ 64 ጊጋ ባይነት ነበር። አይፎን-13 ግን ዝቅተኛ የመያዝ አቅሙ ወደ 128 ጊጋ ባይት ከፍ እንዲል ሆኗል።

አፕል ብዙ ደክሞ የተለያየ 'ፊቸር' ያላቸውን ስልኮች ይፋ ከሚያደርግባቸው ምክንያቶች መካከል ዋነኛው የቀደመውን አይፎን ስልክ የያዙ ደንበኞቹ በአዳዲስ ሞዴሎች እንዲተኳቸው ለማበረታታት እንደሆነ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ የኢንቨስትመንት ተቋሙ ዌብቡሽ እንደሚለው በመላው ዓለም የሚገኙ የአፕል ምርት የሆኑ ስልኮችን የያዙ 250 ሚሊዮን ሰዎች ባለፉት 3.5 ዓመታት ስልካቸውን በአዲስ አይፎን ሞዴል አልቀየሩም።
ዋጋ

አይፎን 13 ሚኒ ከ938 ዶላር ጀምሮ፣ አይፎን 13 ከ1076 ዶላር ጀምሮ፣ አይፎን 13 ፕሮ ከ1312 ዶላር ጀምሮ እንዲሁም አይፎን 13 ፕሮ ማክስ 1450 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ለገበያ ቀርበዋል።

እያንዳንዱ አይፎን 13 ስልክ እንደ ሚሞሪ መጠኑ ዋጋው ይለያያል።

አፕል ዎች 7 እና አይፓድ

አፕል ከስልክ በተጨማሪ ተሻሽሎ የቀረበውን አዲሱን አፕል ዎች አስተዋውቋል።

አዲሱ አፕል ዎች 7 የገዘፈ ስክሪኑ ላይ ኪቦርድ ተግጥሞለታል። አቧራ መቋቋም ይችላልም ተብሏል።

የአፕል ኩባንያ አለቃ ቲም ኩክ አዲሶቹን የአፕል አይፓዶች ሲያስተዋውቁ፤ የአይፓድ ሽያጫቸው ባለፈው ዓመት 40 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።

በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት ለማስተማር መገደዳቸው የአይፓድ ተፈላጊነትን ጨምሮታል።

አዲሶቹ አይፓዶች ከዚህ ቀደም ከነበሩት የአፕል አይፓዶች 20 በመቶ የፈጠኑ ይሆናሉ ብለዋል።

የአፕል አይፓዶች ከ329 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ለገበያ ቀርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በርካታ ስማርት ስልኮችን ለገበያ በማቅረብ የደቡብ ኮሪያው ሳምንስንግ መሪነቱን እንደያዛ ነው። አፕል ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዟል።

የቻይና ኩባንያ የሚያመርታቸው ዢዮሚ ስልኮች በገበያ ደርሻ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ኦፖ እና ቪቮ የተሰኙት ስልኮች ደግሞ አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ብሏል

አፕል ያስተዋወቃቸው አዲሶቹ አይፎን 13 ስልኮች ይዘው ከመጡት ገጽታዎች [ፊቸሮች] መካከል የበርካቶችን ቀልብ የሳበው፤ 'በፖርትሬይት ሞድ' ቪዲዮ መቅረጻቸው ነው።

ከዚህ ቀደም ከአይፎን 7 ወዲህ ያሉ የአፕል ስልኮች በፖርትሬይት ሞድ ፎቶ ማንሳት እንጂ ቪዲዮ መቅረጽ አያስችሉም ነበር።

ፖርትሬይት ሞድ ለምሳሌ አንድን ሰው ከጀርባው ያለውን ዳራ በማደብዘዝ ፎቶ በሚነሳው ሰው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ቀልብ መሳብ የሚችል ምስል ማንሳት ያስችላል።

አይፎን 13 ደግሞ ይህን ወደ ቪዲዮ ከፍ አድርጎታል። የአፕል ኩባንያ አለቃ ቲም ኩክ እንደሚሉት ከሆነ ተጠቃሚዎች በፕሮትሬይት ሞድ ቪዲዮ ከቀረጹ በኋላ ኤዲት ማድረግ የሚያስችለው አይፎን-13 ስልክ ብቻ ነው ይላሉ።

ከዚህ በተጨማሪ አዳዲሶቹ አይፎን ስልኮች ተግባራትን በፍጥነት መከወን የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቶላቸዋል።

የስክሪን ግጽታቸው የተሻለ ብርሃን አለው። የባትሪ አገልግሎት ከዚህ ቀደም ከነበሩት አይፎን ስልኮች በ2.5 ሰዓት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪም አይፎን 13 ስልኮች በሮዝ፣ በሰማያዊ እና በቀይ ቀለማት አሸብረቀው መጥተዋል።
Via BBC
👍7❤1
ዌብሳይት በማሰራት የሚሰጡትን አገልግሎት እንዲሁም የሚያመርቱትን ምርት ኦንላይ በማቅረብ ይሽጡ! ምርትዎን ያስተዋውቁ፣ አገልግሎትዎን ያስተዋውቁ!
ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው በቀላሉ በማንኛውም ቦታ ተደራሽ ለመሆን ዌብሳይ ያስፈልግዎታል ስለሆነም በቀላል ዋጋ ምርጥ ገቢ የሚያገኙበት ዌብሳይት ያሰሩ!
ከዚህ በፊት የሰራናቸውን ዌብሳይቶችን መጎብኘት ይችላሉ!
ዌብሳይቱን ስንሰራ የሞባይል አፕ ሰርተን እናስረክበዎታለን!
www.safeway7.com
www.mametechsolution.com
www.4wcomputers.com
www.ethiotechnologys.com
www.bournworks.com

በቅናሽ ያሰሩ ዌብሳይቱን!
በ0929273364 ይደውሉ!

ሰሞኑን የተሰሩ ዌብሳይቶች እርሶም በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ!
1ኛ www.safeway7.com ይባላል ይህ ድርጅት የግል ሲሆን የፈርኒቸር እቃዎችን የሚሽጥ ድርጅት ነው ስለሆነም የሚሰራቸውን ስራ online በማድረግ አሰራሩን ዲጅታል እያደረገ ነው
2ኛ 4wcomputers ይባላል ይህ የግል የኮምፒውተር(ላፕቶፕና ደስክቶፕ) ሽያጭ እንዲሁም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎችን የሚሽጥ ነው ስለሆነም በጥሩ ሁኔታ ዌብሳይቱን ሰርተንለታል ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ!
www.4wcomputers.com
3ኛ Ethio Technology ይባላል ይህ ዌብሳይት ስለቴክኖሎጅ መረጃዎችን የሚያቀርብልን ሲሆን በተጨማሪም Online ሽያጭ ሊያሰራ የሚችል ዌብሳይት ነው። ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልክት ይችላሉ!
www.ethiotechnologys.com
4ኛ mame tech solution ይባላል ይህ ዌብሳይት እኛ በፌስቡክ፣ ቴሌግራምና ዩቱብ በተጨማሪ በዚህ ዌብሳት አገልግሎት እየሰሁ እገኛለሁ ስለሆነም ከታች ያለውን የዌብሳይት አድራሻ በመጠቀም ይማሩ መረጃ ያግኙ!
www.mametechsolution.com

5ኛ www.bournworks.com ይባላል የግል ድርጅት ሲሆን ማስታወቂያዎችን ይሰራል ኦንላይን ስራዎችንም ይሰራል።
ለግል፣ ለመንግሥት ድርጅቶች ዌብሳይቶችን ማሰራት ለምትፈልጉ በቅናሽ ያሰሩ ዌብሳይቱን!
በ0929273364 ይደውሉ! ወይም በቴሌግራም ( @ma2323me) ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
👍3
SafewayManufacturing_1_1.0.apk
1.5 MB
ሰሞኑን የተሰሩ ዌብሳይቶች እርሶም በቅናሽ ዋጋ ያሰሩ!
1ኛ www.safeway7.com ይባላል ይህ ድርጅት የግል ሲሆን የፈርኒቸር እቃዎችን የሚሽጥ ድርጅት ነው ስለሆነም የሚሰራቸውን ስራ online በማድረግ አሰራሩን ዲጅታል እያደረገ ነው
አፑን ስልክዎ ላይ በመጫን ይሞክሩት!
👍4❤1
ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የሚያገለግሉ 9 የ አንግሮይድ አፖች

ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም። ዘመን አፈራሽ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ሞባይል ስልኮን ክኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮን ኤዲት አንዲያደርጉ ያስችሎታል። እኛም 9 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ ያገለግላሉ ያልናቸውን አፖች የዘን ቀርበናል።

1, FilmoraGo በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የ ዓንድሮኢድ ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። የመቁረጥ ፣ ገጽታዎችን መቀየር ፣ ሙዚቃን የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ ሊከናወኑ ይችላሉ ፡፡ እንዲሁም ለ Youtube ለ Instagram እና ለ Facebook ሚሆኒ ቪዲዮችን መስራት ይችናሉ
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.wondershare.filmorago

2, Adobe Premiere Clip: አዶቤ ፕሪሚየር ክሊፕ ማንኛውንም ቪዲዮ ከእርስዎ የ ስማርት ፎን በፍጥነት እንዲያርትዑ ያስችልዎታል። ለመጠቀም ፈጣን እና አዝናኝ ነው። ስለ ክሊፕ በጣም ጥሩው ባህሪ አውቶማቲክ ቪዲዮ መፍጠር ችሎታ ነው ፣ ማለትም ፣ መተግበሪያው በመረጣቸው ማንኛቸውም ፎቶዎች ወይም ቅንጥቦች አማካኝነት ቪዲዮዎችን በራስ-ሰር ለእርስዎ መፍጠር ይችላል ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adobe.premiereclip

3, VideoShow ብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ ሲሆን በነጻ በ Play Store ውስጥ ለሚገኙት ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች አንዱ ነው። VideoShow ለአጠቃቀም ቀላል እና ለአጠቃቀም ቀላል ነው ፡፡ ከዋና ዋና ተግባራት ፊልተሮችን ፣ ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም ቀጥታ ስርጭትን በማከናወን ቪዲዮዎን ማስዋብ ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.xvideostudio.videoeditor

4, PowerDirector ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ሙሉ ለሙሉ የ አንግሮይድ ቪዲዮ ኤዲተር ነው ፣ ግን ከመቆጣጠሪዎች ጋር ለመግባባት የተወሰነ ጊዜ ሊወስድዎት ይችላል። ሆኖም ፣ አንዴ በዚህ መተግበሪያ ኤክስ ኤክስፐርት ከሆኑ ባለሙያዎችን መፍጠር እና በሰከንዶች ጊዜ ውስጥ ምርጥ የሚባሉ ቪዲዮዎችን መስራት ይችላሉ ፡፡ ከቪድዮዎ ውስጥ ለመምረጥ ከ 30 በላይ የተለያዩ የትራንዚሽን ምርጫዎች አሉት ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.cyberlink.powerdirector.DRA140225_01
5, KineMaster ከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነገጽ ጋር በመጣመር KineMaster ለ Android ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው። የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ “copy paste” መጠቀም ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር KineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ይረዳል። በቪዲዮ መቁረጥ የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ፣ ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን ብሎግ ማስገባት ይችላሉ

የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nexstreaming.app.kinemasterfree

6, Quik እጅግ በጣም ጥሩ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ኩዊክ ሌላ ብልጥ መንገድ ነው ፡፡ ፈጣን እና ነፃ ነው። የራስዎን ታሪኮች በኩዊክ ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ። ስለ ኩዊክ በጣም ጥሩው ነገር አውቶማቲክ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎች ይዞ መምጣቱ መሆኑ ነው ፡፡ ቪዲዮዎችን crop ማድረግ ፣ ማሳመሪያዎችን ፣ ጽሑፎችን መጨመር እና ማንኛውንም Audio መምታት በፍጥነት ማመሳሰል ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.stupeflix.replay

7, VivaVideo ብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት። መተግበሪያው በቀጥታ ከ አንግሮይድዎ ፕሮፌሽናል-የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው። ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ ፡፡ በውስጡ የማይንቀሳቀስ ዘገምተኛ(slow motion) ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ሰሪ እና የተንሸራታች ማሳያ(slideshow maker) ሰሪ አለው።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.quvideo.xiaoying

8, Funimate video editor በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል። የዕለት ተዕለት አፍታዎችን ወዲያውኑ ወደ የፈጠራ ቪዲዮዎችን መለወጥ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ሜዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት ። አጭር ቪዲዮዎችን ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ ከ 1 በላይ የላቁ አማራጮች አሉት ፡፡

የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.avcrbt.funimate

9, Magisto መደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፣ ፎቶግራፎችን ፣ audio ፣ ጽሑፎችን ፣ የቪዲዮ ውጤቶችን እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል ፡፡ አንድ ወይም ከዛ በላይ ቪዲዮ ክሊፕ እና ለድምጽ ማጫወቻው አንድ ዘፈን ይምረጡ እና መተግበሪያው በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አውቶማቲካሊ ቪዲዮ ይፈጥራል።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.magisto
👍3
ምርጥ የResearch ቻናል።

❓ትምህርት እየተማሩ ነው? ወይም ለመማር አስበዋል?
❓ጥናትና ምርምር(Research) እየሰሩ ነው?
❓ስለ Research እውቀትዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
❓ስለ SPSS ማውቅ ይፈልጋሉ?
⁉️የምንረዶት ጉዳይ አለ?

✅በአማርኛ ና በእንግሊዝኛ በግልጽና ቀላል አገላለጽ ስለ Research ጽንሳ ሀሳብ ጀምሮ ጽሑፎችን ያገኛሉ።

💻በጥናትና ምርምር ዙርያ የማማከር አገልግሎትም እንሰጠለን።
👇👇👇👇👇👇👇
@researchRC
@researchRC
@researchRC
@researchRC
@researchRC
👆👆👆👆👆👆👆👆
👍4
ሁሉንም የትምህርት ፍኖተ ካርታ መረጃ በዚህ ልልቀቅላችሁ?
Anonymous Poll
95%
አዎ ያስፈልገናል!
5%
ይቅር አያስፈልገንም!
👍2
የት/ት ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ በሚሆኑ ት/ቤቶች በየክፍል ደረጃ የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
😁= ቅድመ መደበኛ (KG) ለሁለት አመት የሚሠጥ:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= አካባቢ ሳይንስ
3ኛ= ሙያ
4ኛ= ሂሳብ
5ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው፡፡
😁በመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ
3ኛ= እንግሊዘኛ
4ኛ= ሂሳብ
5ኛ= አካባቢ ሳይንስ
6ኛ= የግብረገብ ት/ት
7ኛ= ሙያ
8ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው፡፡
😁በመጀመሪያ መካከለኛ ደረጃ ከ7ኛ-8ኛ ክፍል የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= የአገር አቀፍ ቋንቋ
3ኛ=እንግሊዘኛ
4ኛ= ሂሳብ
5= ሳይንስ
6ኛ= ህብረተሰብ
7ኛ= ስነ -ዜጋ
8ኛ= ሙያ
9ኛ= IT
10ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው::
👍3❤2
የት/ት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ የመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የክ/ጊዜ ብዛት::
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 40 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 6 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 30 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሰዓት ከጥዋቱ 2:15-6:30 የጥዋት ሸፍት ከ6:45-11:00 የከሠዓት ሸፍት ሆኖ 15 ደቂቃ ዕረፍት አለው፡፡
😁የት/ት ሠዓት በየሸፍቱ 4ሰዓት ነው፡፡
😁በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 4 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ እና የዓመቱ ሰዓት 104 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ ክ/ጊዜ 3፣ በሳምንት 2ሠዓት እና በአመት78 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= እንግሊዘኛ የሳምንት ክ/ጊዜ 4 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና የአመቱ 104 ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ= ሂሳብ በሳምንት5 ክ/ጊዜ በሳምንት 3ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት130ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ= አካባቢ ሳይንስ በሳምንት 5 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 3ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት 130 ሰዓት አለው፡፡
😁6ኛ= የግብረገብ ት/ት በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁7ኛ= የሙያ ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁8ኛ= የሰውነት ማጎልመሻ ት/ት በሳምንት 3ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁በአጠቃላይ በሳምንት 30 ክ/ጊዜ ወይም 20 ሰዓት እና በዓመት 780 ሰዓት አለው:: ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
😁መልካም የት/ት ዘመን!!!
👍4❤1
የኮምፒዉተራችን storage space ሲሞላብን እንዴት ማስለቀቅ እንችላለን
የኮምፒዉተርዎ storage space ሞልቶበት ተቸግረዋል፡፡ እንግዲያዉስ የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ
1. ለብዙዎች እፎይታን የሰጠ መፍትሔ ሲሆን የኮምፒዉተራችንን ስቶሬጅ የሞሉብንን የተለያዩ ፋይሎች በማጥፋት ብዙ ትርፍ storage space እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ኮምፒዉተራችን ላይ የማንጠቀምባቸዉ እና የማይጠቅሙን ጊዜያዊ ፋይሎችን (temporary files) በማጥፋት ኮምፒዉተራችን ላይ ብዙ ቦታ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡
✅ Delete unnecessary temporary file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።
2. የማንጠቀምባቸዉን ፕሮግራሞች Uninstall ማድረግ
አብዛኞቹ ኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች የኮምፒዉተራቸዉን ቦታ የሚያጣብባቸዉ የጫኗቸዉ ሶፍትዌሮች እና ጌሞች ናቸዉ፡፡ የማንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮች Uninstall በማድረግ ቦታ መቆጠብ እንችላለን፡፡ ከኮምፒዉተሮ ላይ የማይፈልጉትን ሶፍትዌር ለማጥፋት የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Start -> Control Panel -> Uninstall a program
2. ብዙ ቦታ የያዘዉን ሶፍትዌር ለማወቅ በ size ቅደም ተከተል ይደርድሯቸዉ፡፡
3. ማጥፋት የፈለጉትን ሶፍትዌር መርጠዉ Uninstall የሚለዉን ይጫኑ፡፡
3. የተደጋገሙ ፋይሎችን ያጥፉ
ዊንዶዉስ በራሱ የተደገሙ ፋይሎችን ለይቶ የሚያጠፋ ሲስተም የለዉም ስለዚህ ይህንን ስራ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህንን የሚያደርጉ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ Duplicate Sweeper አንዱ ነዉ፡፡ Duplicate Sweeper ኮምፒዉተራችን ላይ ያሉ የተደጋገሙ ፋይሎችን scan አድርጎ ያቀርብልናል፡፡ እኛም ከዘ ዉስጥ የተደገሙ መሆናቸዉን እያረጋገጥን ማጥፋት እንችላለን፡፡
4. ጊዜያዊ ፋይሎች (Temporary Files)
በ Windows Disk Cleanup አማካኝነት ጊዜያዊ ፋይሎችን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አይተናል፡፡ ነገርግን Windows Disk Cleanup ሊያገኛቸዉ የማይችሉ እንደ browser ያሉ የጫንናቸዉ ሶፍትዌሮች የፈጠሩትን ጊዜያዊ ፋይሎች ለማጥፋት የሚያስችለን ሌላ መንገድ Google Chrome ን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ እናያለን፡፡
1. Google Chrome ን ይክፈቱ
2. settings menu ይክፈቱ
3. More tools የሚለዉን ይምረጡ
4.Clear Browsing data የሚለዉ ዉስጥ በመግባት ማጥፋት የሚፈልጉትን ጊዜያዊ ፋይል
መርጠዉ ያጥፉ
5. Recycle Bin ዉስጥ ያሉ ፋይሎችን ያጥፉ
ከኮምፒዉተራችን ላይ ያጠፋናቸዉ ፋይሎች permanently delete ካላደረግናቸዉ መልሰን ብንፈልጋቸዉ ማግኘት እንድንችል Recycle Bin ዉስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ከላይ ባሉት መንገዶች ያጠፋናቸዉ ፋይሎችም Recycle Bin ዉስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ Recycle Bin ያሉ ፋይሎች ግን ከኮምፒዉተራችን ላይ የያዙትን storage space እንደያዙ ነዉ የሚቆዩት፡፡ ስለዚህ storage space ለማስለቀቅ እነዚህን የማንፈልጋቸዉ ፋይሎች ከRecycle Bin ዉስጥ ማጥፋት ይኖርብናል፡፡
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
👍8😁2