Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
የስኬታማ አመራሮች አምስት የዉጤት ሚስጥራዊ ባህሪያት
===============================
ለአንድ ተቋም የላቀ ውጤታማነት ትልቁን ሚና የሚይዘው አመራሩ ነው፡፡
የአመራሩ ጥንካሬ ወይም ድክመት አንድን ትንሽ ተቋም አይደለም አገርን
ያህል ነገር ደካማ ወይም ጠንካራ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በተለያዩ ተቋማት
ውስጥ ያሉ አመራሮች የሚመሩት ድርጅት አትራፊም ይሁን ትርፋማ
ያልሆነ እስከ 40 በመቶ ድረስ ውጤታማነቱን የመወሰን አቅም አላቸው፡፡
አመራሩ የበታች ሰራተኞችን ይቀጥራል፣ ያሰራል፡፡ ድርጅቱ ውጤታማ
ባይሆን ተጠያቂው የሚሆነው ስራውን በበላይነት የሚያሰራው ወይም
ደግሞ ስራውን የሚሰሩ ሰዎችን የቀጠረው ነው ሊሆን የሚችለው፡፡
ለዚያም ነው አንድ ድርጅት ሲመሰረት አመራሩ ማነው ተብሎ በቅድሚያ
መለየት ያለበት፡፡
የምንመራው ተቋም የፖለቲካ ፓርቲ ሊሆን ይችላል፣ የእግር ኳስ ክለብ
ሊሆን ይችላል፣ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅትም እንዲሁ፡፡ በተመሳሳይ
መልኩ አትራፊ የንግድ ድርጅትም ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉም እንደ ተቋም
ግን የተቋቋመበትና ሊያሳኩት የሚፈልጉት ራዕይና ግብ አላቸው፡፡ ተቋምን
ተቋም ከሚያሰኙት አንዱ መለያ ባህሪያቸው ሰርቶ ሊያሳካቸው
የሚፈልጋቸው ግልፅ አላማዎች መኖራቸው ነው፡፡ እነዚህን ዳር
ለማድረስ ነው እንግዲህ የአመራሩ ሚና፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የምርጥ አመራር ባህሪያት ምንድን ናቸው?
አንድ አመራር ብቃት የ‹‹BASKET›› ፅንሰ ሃሳብን ያሟላ መሆን
አለበት፡፡ ሁሉም ሰው መሪ መሆን ቢፈልግም መሪ መሆን የሚችሉት ግን
ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ መሪ መሆን ችለውም የላቀ ውጤት ማስመዝገብ
የሚችሉት አሁንም ጥቂቶች ናቸው፡፡ የእጅግ ውጤታማ ሰዎች
አመራሮች አንድ መገለጫዎች ‹‹BASKET›› የተባለውን መስፈርት
የሚያሟሉ መሆናቸው ነው፡፡ ‹‹ባስኬት›› ሲባል ቅርጫት ለማለት ተፈልጎ
አይደለም፡፡ ምህፃረ ቃል ነው፡፡
#1. B- Behavior…ባህሪ!
“Leadership is a potent combination of strategy and
behavior. But if you must be without one, be without
strategy”… Norman Skhwarzkopf
እንደሚታወቀው አንድ አመራር ስለሚጠበቅበት የስራ ኃላፊነት ሊወጣው
የሚያስችለው ባህሪ ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንዱ መሪ እንኳን ለመምራት
ለመመራት የማይሆን ባህሪ ያለው አለ፡፡ እንኳን ሌሎችን ሊመራ ራሱ
መሪ የሚያስፈልገው ሰውም አለ፡፡ የመሪነት ባህሪ ራሱን የቻለ ልዩ ገጽታ
ነው፡፡ ለዚያም ነው ሁሉም ሰው መሪ መሆን የማይችለው፡፡ ለዚያ
ኃላፊነት ዝግጁ የሆነ ባህሪ ሊኖረው ይገባል፡፡ አንድ ሰው በአገራችን
ካለው የሊደርሽፕ ተቋምም ሆነ ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ቢማር
የመሪነት ባህሪ ካልታደለው ወይም ደግሞ በውስጡ ካላዳበረው
ውጤታማ መሪ ሊሆን አይችልም፡፡
መኪና ከፈለግንበት ቦታ ሊያደርሰን የሚችለው ጎማ ሲገጠምለት ነው፡፡
አንድ መሪም እንዲሁ የሚመራውን ተቋም ከዳር ማድረስ የሚችለው
ለአመራርነት የሚያበቃ ባህሪ ሲገጠምለት ነው፡፡ ከየትኛውም ተቋም
ውጤት በስተጀርባ የአመራሮችን ባህሪ እናገኛለን፡፡ ጥሩ ውጤት ያላቸው
ከሆነ ጥሩ የአመራር ባህሪ አላቸው ማለት ሲሆን ውጡቱ ደግሞ
ከተጠበቀው በታች ከሆነም ባህሪያቸው የዚያኑ ያህል ሆኗል ማለት
ይቻላል፡፡
አንድ የእግርኳስ አሰልጣኝ ለአሰልጣኝነት የሚሆን ባህሪ ከሌለው ቡድኑ
ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ አንድ የፖለቲካ ተቋም /ፓርቲ/ መሪ
ፖለቲካዊ መድረክን ወደ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል አፈፃፀም
ከሌለው በተመሳሳይ መልኩ ፓርቲው እንኳን ምርጫ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ
አይደለም የራሱን ህልውና ለማስጠበቅ እንኳን ሊሳነው ይችላል፡፡ አንድ
የንግድ ተቋም አመራር ለንግድ አመራርነት የሚያበቃ ባህሪ ከሌለው
ድርጅቱ አትራፊ ሆኖ ሊዘልቅ አይችልም፡፡ ይህ የሚያሳየን የአመራር
ባህሪ እንደየተቋሙ ባህሪ የሚለያይ መሆኑ ነው፡፡
ለዚያም ነው ታክሲ ሲነዳ የነበረ ሹፌር አውቶብሱን መንዳት የሚሳነው፡፡
አውቶብሱን ለመንዳት የሚያስችል ባህሪ ከዳበረ ግን በጥሩ ሁኔታ
መንዳት ይችላል፡፡ አንድ ቦ ለውጤት ያበቃ ባህሪ ለሌላም ሊያበቃ
የሚችል ሲሆን አንድ ቦታ ላይ ተፈትሾ ያልሰራ ባህሪ ደግሞ በሌላ ቦታ
ላይም ሊራ አይችልም፡፡ ሆኖም ለብዙ ተቋማት ውድቀት ትልቁ ምክንያት
ያ ተቋም የሚፈልገውን ልዩ የአመራር ባህሪ ካለመኖር ወይም ደግሞ
ካለማዳበር የሚመነጭ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚያም ነው አንዳንዴ
በአመራር ብቃታቸው ሌላ ቦታ ውጤታማ ሆነው በሌላ ድርጅት ላይ
ሲቀጠሩ ድርጅቱን ሊጥሉት የሚችሉት፡፡ ይህም ማለት ባህሪ በየጊዜው
የሚዳብር፣ እንደምንመራው ተቋም ባህሪም በአዲስ መልክ የሚሻሻልና
ውጤትን የሚወስን አንዱ የመሪዎች ወሳኝ ገፅታ መሆኑን ነው፡፡
#2. A Attitude… አመለካከት
“If your actions inspire others to dream more, learn
more, do more and become more, you are a leader”
John Quincy Adams
ይህ የመሪዎች ሌላኛው ውጤት ቀያሪ መገለጫቸው ነው፡፡ የመሪዎች
ገንቢ አመለካት ለገንቢ ውጤት የሚያበቃ ኃይል አለው፡፡ አንድ መሪ
የድርጅቱን ራዕይ የራሱ ራዕይ አድርጎ ከመነሳት ይጀምራል፡፡ አንዳንድ
አመራሮች በአንድ ተቋም ላይ ለመሪነት ሲመረጡ ወይም ደግሞ ሲሾሙ
የድርጅቱን ራዕይ ላያውቁት ወይም ደግሞ ላያምኑበት ከቻሉ ግለሰቡና
ተቋሙ አልተዋወቁምና ከዚህ መሰል አመራር ውጤት መጠበቅ ማለት
ከጠራ ሰማይ ላይ ዝናም ይጥላል ብሎ ጥላ እንደመያዝ ነው
የሚቆጠረው፡፡ እንዲሁም የትኛውም የንግድ ተቋም ስራውን
የሚገዳደሩት ተወዳዳሪ ተቋማት አሉ፡፡ የንግድ ድርጅትን ብንወስድ
ከእነሱ ካልተሻለ ሊጥሉት የሚችሉ ተወዳዳሪዎ አሉት፡፡ በንግድ ውስጥ
ያለው አማራጭ፣ ወይም መምራት አልያም መውጣት ነው፡፡ ከፊት
መሪዎች ውስጥ አንዱ መሆን መቻል አለበት፡፡ የእግርኳስ ክለብንም
ብንወስድ እንዲሁ ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲም ተፎካካሪዎች አሉት፡፡
በመሆኑም የትኛውም ተቋም በአሸናፊነት መንፈስ የተገነባ አመራር
ያስፈልገዋል፡፡ ተቋሙ ከሌሎች ተሽሎ የሚገኝ ተቋም እንደሆነና እሱም
ያንን በተግባር እውን ማድረግ እንደሚችል የሚያምን፣ ቁርጠኝነቱ
ያለው፣ አመራር ያስፈልጋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ራሱንና ተቋሙን አሳንሶ
የሚመለከት አመራር እኩል ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡
እንዲሁም የድርጅቱ ውጤት የእኔ ውጤት ነው፤ የድርጅቱ ውድቀት የእኔ
ውድቀት ነው ብሎ የሚያምን አመራርም ያስፈልጋል፡፡ የትም ቦታ አንድ
መሪ ስራውን ቀይሮ ቢወጣ ለሌላ አመራርነት ሊታጭ የሚችለው ከአሁን
ቀደም በመሪነት ደረጃ ያመጣቸው ውጤቶች ታይተው ነው፡፡ የመሪው
ህልውና በቀጥታ ከተቋሙ ህልውና ጋር ይያያዛል፡፡ ዛሬ ላይ ለውጤት
ያበቃ ባህሪ ነገ ሌላ ቦታ ላይ ይኸው ባህሪ አብሮት ይዘልቃል፡፡
ተቃራኒውም እንዲሁ ነው፡፡ በመሆኑም በአመራርነት ደረጃ ላይ
እስከተቀመጠ ድረስ የተቋሙ ውጤት የእኔ ውጤት ውድቀቱም የእኔ
ውድቀት ነው ብሎ ማመን መቻል ይኖርበታል፡፡ ይህ እንደ መሪ
የሚያስፈልግና ለውጤት የሚያበቃ አመለካከት ነው፡፡
#3. S-skill…ችሎታ
“A man who wants to lead the orchestra must turn his
back on the crowd!” Mad Lucado
መሪነት ራሱን የቻለ ችሎታም ነው፡፡ ከሚመሯቸው በላይ የላቀ ችሎታን
ይጠይቃልና አውቶብስ መንዳት ራሱን የቻለ ችሎታ ነው፡፡ ተቋምን
መሾፈርም እንደዚሁ፡፡ የትኛውን ማርሽ በየትኛው ጊዜ ላይ ወስኖ
መጠቀም እንዳለበት መረዳት የሚችል፤ የትኛውን
👍3
ተተኪ አመራሮችን በኮችንግ፣ በስልጠና
እንዲሁም ከበላይ ካሉ አመራሮች ስር በመሆን እንዲሰሩ በማድረግ
ማብቃት እንችላለን፡፡ በተላዩ የድርጅቱ ክፍሎችና ቅርንጫፎች ውስጥ
በማዟዟር ልዩ ልዩ እውቀትን፣ ልምድንና ችሎታን እንዲያዳብሩ ካደረግን
በኋላ ወደ ላይ ማምጣት እንችላለን፡፡
መንፈሳችን ስለወደዳቸው፣ ደስ ስላለን ወይም ስለመሰለን
የምነቀጥራቸው ወይም ደግሞ የምንተካው ሰዎች መኖር የለበትም፡፡ ደስ
ስላለን ብቻ መኪናችን እንዲነዳልን ቁልፍ ሰጥተን በመኪናው ውስጥ
ተሳፍረን የምንሄድ ስንቶቻችን ነን? አናደርገውም፡፡ ተቋምም እንዲሁ
ነው፡፡
ፍ መንካት
እንዳለበትና እንደሌለበት ማወቅ የሚችል፤ አቅጣጫን የመረዳት ችሎታ፣
የመኪናውን ባህሪ የመረዳትና ማስተካከል የሚችል ችሎታ
ያስፈልገዋል፡፡ አንድ የተቋም አመራርም በተግባር የተፈተሸ ልዩ ልዩ
ችሎታዎች ያስፈልጉታል፡፡ ገንዘብ የማስተዳደር ችሎታ፣ ሰው አስተዳድሮ
የማሰራት ችሎታ፣ ስሜቱን የመቆጣጠር ችሎታ፣ ውጤታማ
ኢንቨስትመንት የማድረግ ችሎታ፣ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ፣ የማቀድ
ችሎታ፣ የወደፊቱን የመተንበይ ችሎታ፣ እያለ ይቀጥላል፡፡ አንድ አመራር
ጥሩ ገንቢ አመለካከት ቢኖረው እንኳን ትክክለኛ ችሎታ በሌለበት ሁኔታ
ያለትክክለኛ ትግበራ የሚጠበቀውን ትክክለኛ ውጤት ለማምጣት
ያስቸግረዋል፡፡
#4. K- Knowledge…
“It the blind lead the blind, both shall fall in the
ditch”… Jesus Christ
በእርግጥ ችሎታ የሚዳብረው ከማወቅ ነው፡፡ ለአመራርነት የሚያበቁ
ችሎታዎችን ለማዳበር በቅድሚያ ስለችሎታዎቹ መሰረታዊ እውቀት
ሊኖረው ይገባል፡፡ ሁሉም አይነት እውቀት አይደለም፣ ለትክክለኛ ቦታ
የሚሆን ትክክለኛ እውቀት እንጂ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፣ ስለሚመራው
ተቋምም ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን ሊያውቅ ይገባል፡፡ እንዲሁም
የሚመራው አንድን የንግድ ተቋም ከሆነ ስለንግድ አሰራር መሰረታዊ
እውቀት ያስፈልገዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ በአገራችን የድርጅቱ ባለቤት
ስለሆኑ ብቻ እንጂ መሰረታዊ የንግድ ‹‹ሀሁ›› እውቀት ኖሯቸው
ድርጅታቸውን የሚመሩ ሰዎች ጥቂት ናቸው፡፡
አንድ ሰው የሚመራው የእግርኳስ ክለብን ከሆነ ደግሞ ስለ እግርኳስ
መሰረታዊ እውቀትን ሊጨብጥ ይገባል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲም ከሆነም
ስለፖለቲካና አገራዊ አመራር ትክክለኛ እውቀት ያስፈልገዋል፡፡
ምክንያቱም እውቀቱ ችሎታውን ይወስናል፤ ችሎታውን ተግባሩን፡፡
ተግባሩ ደግሞ ባህሪውን ይቀርፃል፡፡ በመጨረሻም የግለሰቡንና
የተቋሙን ውጤት፡፡
ለምሳሌ በአገራችን ያሉ መካከለኛና ከፍተኛ የሚባሉ ኢንተርፕራይዞች
በቀጥታ ለመመራት ያለባቸው በቢዝነስ ሁለተኛ ዲግሪ ባላቸው
ባለሙያዎች ሲሆን ብዙዎቹን ስንመለከት ግን ይህን ሚዛን አያልፉም፡፡
ለዚያም ነው የሚመሯቸው ተቋሞች ወደ ላይና ወደ ታች ሲሉ
የምናያቸው፡፡ በፓርቲም ደረጃ እንዲሁ በፖለቲካል ሳይንስ በቂ ግንዛቤ
ያላቸውን አመራሮች ይጠይቃል፡፡ አለበለዚያ አላዋቂ ሳሚ እንዳይሆን
ራሳችንን መፈተሽ ይገባል፡፡ ለትክክለኛ ተቋምና ለትክክለኛ የአመራር ቦታ
ብቁ የሚያደርግ ትክክለኛ እውቀት!!
#5. E- Experience… ልምድ
“Leadership and (experience) are indispensable to
each other”… John f. Kennedy
ከላይ ያሉት የአመራር ችሎታዎች የሚዳብሩት በልምድ እና በልምምድ
ውስጥ ነው፡፡ እንዲሁም የአመራርነት ባህሪ በራሱ የልምድ ውጤት
ነው፡፡ ከአሁን ቀደም አንድ ሰው ያዳበረው ልምድ ውጤት የማያመጣ
ወይም የውድቀት ከሆነ ባህሪውም ይሄንኑ ነው፡፡ በእርግጥ የአመራር
ችሎታዎቹም ቢሆኑ ውድቀትን የሚያላብሱ ናቸው የሚሆኑት፡፡ በሥራ
ማስታወቂያዎች ላይ ‹‹በዘርፉ ይህን ያህል የሥራ ልምድ›› የሚባለውም
ለዚያ ነው፡፡ የአንድን አመራር ልምድ በቀላሉ ለመረዳት ‹‹ከአሁን ቀደም
ምን ያህል ድርጅቶች አቋቁመህ ወይም መርተህ ለውጤት
አብቅተሃል?›› የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ አንዳንዱ ረጅም ዓመት
የመምራት ልምድ ኖሮት ሊሆን ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቦታው ላይ
መቆየቱ አይደለም፡፡ ድርጅቱን ከየት አንስቶ የት አደረሰው? የገጠሙትስ
ተግዳሮቶች ምን ነበሩ? እንዴትስ በመፍታት ተቋሙን ለውጤት አበቃው?
ነው ጨዋታው፡፡ አመራርነት ስልጣን አይደለም ውጤት እንጂ፡፡ ማዕረግ
አይደለም፡፡ አፈፃፀም እንጂ ረጅም ዓመታት በመምራት መቆየትም
አይደለም ረጅም የሚያስከነዳ ውጤትን ማስጨበጡ ላይ ነው ቁም
ነገሩ፡፡
#6. T- Talent… ልዩ ብቃት
“Your are your master, only you have the master key to
pen the inner locks!”
…Leonardo Davienchi
ይህ የአመራርነት የመጨረሻው ማስተሪ ይሉታል ባለሙያዎች፡፡ መሰጠት
እንደማለት ነው፡፡ ታለንት በተፈጥሮ የተሰጠን ሊሆን ይችላል፡፡
በትምህርትና ልምምድም ወደ ማስተርነት የተቀየረም ሊሆን ይችላል፡፡
ከላይ ያሉት ውጤት ተኮር እውቀቶች፣ ውጤት ተኮር ችሎታዎች፣ ውጤት
ተኮር አመለካከቶች፣ ውጤት ተኮር ልምዶች በየጊዜው በዳበሩ ቁጥር
ግለሰቡ ለዚያ ቦታ የሚኖረው ልቀት ያለው አመራር (Leadership
excellence) ወደ ፍፁም ብቃት ይሸጋገራል፡፡ ውጤታማ አመራርነት
ለግለሰቡ ቋንቋው፣ ተግባሩ፣ መንፈሱ፣ መሆን ሲጀምር ሊደርሺፕ በራሱ
ታለንት ወደ መሆን ተሸጋገረ እንለዋለን፡፡
ለዚህ መሰሉ ሰው ውጤታማ አመራርነትን አውቆት ወይም አስቦበት
ሳይሆን ሳያውቀው ሁሉ የሚተገብረው ነው የሚሆነው (autopilot)፡፡
የሊደርሽፕ ማስተሪ ማለት ይህ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአመዛኙ የምናየው
የትምህርት ማስተርስ እንጂ ውጤትና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ማስተሪ
አይደለም፡፡ ይህ ምናልባት የትምህርት ተቋሞቻችን አንዱ ክፍተት ሊሆን
ይችላል፡፡
ለምሳሌ እኔ ባለፍኩበት የህክምና ሳይንስ ተቋም ማለትም አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ እንደ ህክምና ሳይንስ አመለካከታችን በሔታክራተሳዊ
ኤቲክስ፣ እውቀቱ ረጅም ዓመታት የሚፈጅ፣ ከመጀመሪያው ዓመት ጀምሮ
በፍፁም ተግባር ላይ የተንተራሰ፣ ለሶስት ዓመታት ያህል ከሲኒየር
ሐኪሞች ስር በመሆን እንደ ሐኪም ህሙማንን በመመርመርና በማገዝ፣
በተለያዩ ሆስፒታሎች በመዘዋወር ውስጥ ተሞክሮ የተገነባበት በመሆኑ
አንድ የህክምና ዶክተር ከተመረቀ ጀምሮ በየትኛውም ቦታ ላይ
የሚገጥሙትን የስራ ላይ ተግዳሮቶች መወጣት ይችላል፡፡ ድንገተኛ ቀዶ
ህክምና አስፈልጓቸው በገጠሩ በቂ መብራት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ
እንኳን ቀዶጥገና አድርገው ህይወት ያተረፉ፣ እንደዚሁም በቀዶ ህክምና
ያዋለዱ ተመራቂ ጓደኞች ነበሩኝ፡፡ በመሆኑም ሁሉም የትምህርት
ተቋማት ከላይ ያሉትን የአመራር ገጽታዎችን በተሞላ መልኩ የገነቡ
ተተኪ ወጣቶችን ለማፍራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይ
የህክምና ሳይንስ ኮሌጆችን ተሞክሮ ቢወስዱ የሚል እምነት አለኝ፡፡
እንዲሁም በዓለማችን ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ከሆነው
የአሜሪካው ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሚመረቁ አምስት ሰዎች
ውስጥ አንዱ በአምስት ዓመት ውስጥ ውጤታማ የድርጅት ባለቤት
ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ደግሞ አለማቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ
የአንዱ አገር ዲቪዥን የበላይ አመራር ሆኖ የመቀጠር እድል አለው፡፡
ይህ የሚያሳየው ዩኒቨርሲቲው የሚያወጣቸው ተማሪዎች
የ‹‹BASKET›› ፅንሰ ሃሳብን በተላበሰ መልኩ ስለሚያስተምሯቸው
ነው፡፡ በነገራችን ላይ የስመ ገናናው ኢሲኤክክስ መስራች ዶ/ር እሌኒ
ገ/መድህን የዚህ ዩኒቨርሲቲ ውጤት ናት፡፡ ዩኒቨርሲቲ በንግድ ሳይንስ
ካስተማራቸው ውስጥ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ 30 በህይወት ያሉ
ቢሊየነር ነጋዴዎችን ማፍራት የቻለው ከዚህ አንፃር ነው፡፡ እንግዲህ
ቢሊየነሮቹ ይህን ያል ከሆኑ መልቲ ሚሊየነሮቹ ምን ያህል ይሆኑ?
ሚሊየነሮቹስ? እጅግ ብዙ፣ ይህን በእኛ ሀገር ብንፈትሽ ስንቶቹ የንግድ
ሳይንስ ተማሪዎች የት ደርሰዋል? ብለን ማንሳትና ማጥናትም አለብን፡፡
እናም በየትኛውም ተቋማት ውስጥ ለምንቀጥራቸው አመራሮች
እንደመመልመያ መስፈርትም ሆነ መገምገሚያነት እንዲሁም ተተኪ
አመራሮችን ወደ ላይ ለማምጣት የ‹‹B ASKET›› መርህን መከተል
እንችላለን፡፡ በምንመራው ተቋም ውስጥም ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡
እንዲሁም በዚህ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ተተኪ አመራሮችን በኮችንግ፣ በስልጠና እንዲሁም ከበላይ ካሉ አመራሮች ስር በመሆን እንዲሰሩ በማድረግ ማብቃት እንችላለን፡፡ በተላዩ የድርጅቱ ክፍሎችና ቅርንጫፎች ውስጥ በማዟዟር ልዩ ልዩ እውቀትን፣ ልምድንና ችሎታን እንዲያዳብሩ ካደረግን በኋላ ወደ ላይ ማምጣት እንችላለን፡፡ መንፈሳችን ስለወደዳቸው፣ ደስ ስላለን ወይም ስለመሰለን የምነቀጥራቸው ወይም ደግሞ የምንተካው ሰዎች መኖር የለበትም፡፡ ደስ ስላለን…»
① Motherboard
〰️〰️〰️〰️〰️
❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡
❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡
②Central Processing Unit (CPU)
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡
❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡
❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡
③ Random Access Memory (RAM)
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡
❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል
④Hard Drive
〰️〰️〰️〰️〰️
❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡
❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
⑤Power Supply Unit
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «① Motherboard 〰️〰️〰️〰️〰️ ❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡ ❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር…»
🔰android ማለት በአሁን ሰዓት በጣም ምርጥና ተወዳጅ የOS/Operating System አይነት ነው!

🔰ይህንን ሲስተም ከሚጠቀሙ ታዋቂ ስልኮች በጥቂቱ
👉SAMSUNG
👉HUWAWEI
👉ONEPLUS
👉NOKIA
👉HTC
👉XIAOMI
👉TECNO
👉SONY
👉LG...........etc

| የስልካችሁን ሶፍትዌር Version ለማየት Setting >> About device >> Android Version ላይ ማየት ትችላላችሁ |

🔰1:ALPHA(አልፋ)የመጀመሪያ
የተለቀቀበት አመት:23/09/2008 የversion ቁጥር:android 1.0

🔰2:BETA(ቤታ)ሁለተኛ
የተለቀቀበት አመት:09/02/2009
የversion ቁጥር:android 1.1

🔰3:CUP CAKE(ካፕ ኬክ)ዘቢብ(ቆርኪ)
የተለቀቀበት አመት:27/04/2009
የversion ቁጥር:android 1,4

🔰4:DONUT(ዶናት)
የተለቀቀበት አመት:15/09/2009
የversion ቁጥር:android 1.6

🔰5:ECLAIR(ኤክላር)
የተለቀቀበት አመት:26/10/2009
የversion ቁጥር:android 2.0/2.1

🔰6:FROYO(ፍሮዮ)አይስክሬም
የተለቀቀበት አመት:20/05/2010
የversion ቁጥር:android 2.2/2.2.3

🔰7:GINGERBREAD(ጂንጀርብሬድ)
የዝንጅብል ዳቦ
የተለቀቀበት አመት:06/12/2010
የversion ቁጥር:android 2.3/2.3.7

🔰8:HONEYCOMB(ሀኒ ኮምብ)የማር እሸት
የተለቀቀበት አመት:22/02/2011
የversion ቁጥር:android 3.0/3.2

🔰9:ICE CREAM SANDWICH(አይስክሬም ሳንድዊች)
የተለቀቀበት አመት:18/10/2011
የversion ቁጥር:android 4.0

🔰10:JELLY BEAN(ጄሊ ቢን)
የተለቀቀበት አመት:09/07/2012
የversion ቁጥር:android 4.1

🔰11:KITKAT(ኪትካት)የቸኮሌት ብራንድ
የተለቀቀበት አመት:31/10/2013
የversion ቁጥር:android 4.4

🔰12:LOLLIPOP(ላሊፓፕ)የከረሜላ አይነት
የተለቀቀበት አመት:12/11/2014
የversion ቁጥር:5.0

🔰13:MARSHMALLOW(ማርሽሜሎ)
የተለቀቀበት አመት:05/10/2015
የversion ቁጥር:6.0

🔰13:NOUGAT(ኖጋት)
የተለቀቀበት አመት:22/08/2016
የversion ቁጥር:7.0

🔰14:OREO ኦሪዮ(የብስኩት አይነት)
የተለቀቀበት አመት:23/09/2018
የversion ቁጥር :android 8.1

🔰14:Pie ፒ
የተለቀቀበት አመት:October 17 2018
የversion ቁጥር :android 9.0

🔰
የተለቀቀበት አመት:September 3, 2019 (በቅርቡ )
የversion ቁጥር :Android 10.0:

🔰 ማስታወሻ 🔰
⚡️የስልካችን ቨርዢን በጨመረ ቁጥር
በጣም አዳዲስ አፖችና ጌሞች የመጠቀም እድላችን የሰፋ ነው
⚡️ ከነዚህ ውስጥ በአሁን ሰዓት አሪፍ የሚባሉት ከ6.0 በላይ ያሉት ናቸው
⚡️ ከሶስተኛው ስሪት ጀምሮ ያሉት ስሞች በጣፋጭ ምግቦች ስም የተሰየሙ ናቸው
⚡️ ሌላው የሚገርመው ነገር ከ1 ጀምሮ ያሉት በአልፋቤት ቅደም ተከተል ነው የተሰየሙት A,B,C,D,E,F,G,H,I,J,K,L,M,N,O,P...
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍4
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «🔰android ማለት በአሁን ሰዓት በጣም ምርጥና ተወዳጅ የOS/Operating System አይነት ነው! 🔰ይህንን ሲስተም ከሚጠቀሙ ታዋቂ ስልኮች በጥቂቱ 👉SAMSUNG 👉HUWAWEI 👉ONEPLUS 👉NOKIA 👉HTC 👉XIAOMI 👉TECNO 👉SONY 👉LG...........etc | የስልካችሁን ሶፍትዌር Version ለማየት Setting >> About device >> Android Version ላይ ማየት…»
እንዴት ቴሌቪዥን ሳያስፈልገን የደስክቶፕ ኮምፒውተር ሞኒተር(ስክሪን) በመጠቀም ቴሌቪዥን ማድረግ እንችላለን?
በመጀመሪያ የሚያስፈልጉንን ነገሮችን ልዘርዝርላችሁ
1ኛ የደስክቶፕ ሞኒየር
2ኛ ሪሲቨር(ከዲሽ ጋር የተገናኘ)
3ኛ የደስክቶፕ ሞኒተር VGA ገመድ
4ኛ VGA to HDMI cable converter(ከቪጂኤ ወደ ኤችዲአምአይ የሚቀይርልን ገመድ) ይችን ገመድ በፎቶ እንደምትመለከቷት ትንሽ ናት በገበያ ላይ ያለች ዋጋዋ ከ 200-350 አካባቢ ናት
ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ነገሮች ማሟላት ይኖርባችኋል ማለት ነው።
የአሰራር ቅደም ተከተል
1ኛ የዲሽ ሪሲቨራችንን በቀጥታ ከዲሹ ጋር መገናኘቱን በትክክል መረጋገጥ ይኖርብናል
2ኛ የደስክቶፕ ሞኒተሩን ከራሱ VGA ገመድ መገናኘት ይኖርበታል
3ኛ የደስክቶፕ የተገናኘውን VGA ገመድ ከHDMI converter ጋር እናገናኛለን ያለ ማለት ባለ15 male pin ያለ ወደ ባለ15 female pin እናገናኛለን
4ኛ HDMI converter ከVGA ገመዱ ጋር ከላይ በ3ኛ ተራ ስላገናኘነው የHDMI port ወስደን ወደ ሪሲቨር የHDMI Port እናገናኛለን ከፎቶ እንደምትመለከቱት በቀይ ምልክት አድርጌበታለሁ።
5ኛ አለቀ በቀጥታ መመልከት ብቻ ነው።
6ኛ እስኪ የተሰማችሁን አስተያየት ከታች ጻፉልኝ
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍1
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «እንዴት ቴሌቪዥን ሳያስፈልገን የደስክቶፕ ኮምፒውተር ሞኒተር(ስክሪን) በመጠቀም ቴሌቪዥን ማድረግ እንችላለን? በመጀመሪያ የሚያስፈልጉንን ነገሮችን ልዘርዝርላችሁ 1ኛ የደስክቶፕ ሞኒየር 2ኛ ሪሲቨር(ከዲሽ ጋር የተገናኘ) 3ኛ የደስክቶፕ ሞኒተር VGA ገመድ 4ኛ VGA to HDMI cable converter(ከቪጂኤ ወደ ኤችዲአምአይ የሚቀይርልን ገመድ) ይችን ገመድ በፎቶ እንደምትመለከቷት ትንሽ ናት በገበያ…»
ኡቡንቱን ከዊንዶው 10/7/8 ጋር አጫጫን (Dual Boot)??

1. መጀመሪያ fast boot እናጠፋለን።
Control panel > Hardware and Sound > Power Options > System Settings ...Change settings የሚለው ክሊክ እናደርጋለን እዛው በመቀጠልም Turn on fast start up የሚለው ላይ ✅ ካለ እናጠፋለን።

2. አዲስ partition እንፈጥራለን።
Disk management እንገባለን ከዛ ለኡቡንቱ(Ubuntu) የሚሆን partition በትንሹ 20 GB የሚሆን ቦታ ካለን ላይ Shrink እናደርጋለን። Unallocated መፍጠራችን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

3. Boot እንሰራለን ።
Power ISOን ወይንም Rufusን በመጠቀም ፍላሽ ዲስክ /usb drive/ ላይ boot እንሰራለታለን።

4. ኮምፕዩተራችን Restart እናደርጋለን በመቀጠልም ልክ ኮምፒዩተር እንደተነሳ F12/F9/F10.. እንጫናለን ከዛም ካሉት ምርጫዎች Usb ወይንም Sandisk የሚለውን እንመርጣለን።

5. ምርጫዎች ይመጣሉ ከእነርሱም ውስጥ Install Ubuntu የሚለውን እንመርጣለን።ከዛም ሴታፑ ይጀምራል።

6. ቋንቋ ያስመርጣል.. የምንፈልገውን እንመርጣለን....ከዛም Continue እንላለን።
ለምሳሌ English ከሆነ የፈልኩት English እመርጣለው።

7. Keyboard layout የሚል ምርጫ ያመጣል እሱንም English(Us) የሚለውን እንመርጣለን ከዛም Continue የሚለውን እንነካለን።

8. Normal installation የሚለውን እንመርጣለን ከዛም Continue እናደርጋለን

9. Something else የሚለውን እመርጣለን ከዛም continue እንላለን ።

10. Partition list ይመጣል።እዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን 3 partition ነው create የምናደርገው። እነርሱም
🔸 Root
🔸 Swap area
🔸 Home ናቸው።
Free space የሆነው ከላይ unallocated partition ያደረግነው ነው። እሱ ላይ select እናደርግና ከታች + ምልክትን እንነካለን።
ለምሳሌ unallocated የሆነው partition 25 GB ከሆነ

🔸Home
Size = 10GB
Type = primary
Location = Beginning partition
Use = Ext4 journaling files system
Mount = /home

🔸Swap area
Size = 6 GB
Use = swap area

🔸Root
Size = 9GB
Type = primary
Location = Beginning
Use = Ext4 journaling file system
Mount = /

Continue እንላለን።

11. Location አስገባ የሚል ይመጣል ከዛም Continue እናላለን።

12. User name እና password እናስገባለታለን።

13. Installation አድርጎ ከጨረሰ በኋላ PC restart እንዲደረግ instruction ያሳየናል በመቀጠልም Restart የሚለውን button እንጫናለን። restart ካደረገ በኋላ ምርጫ ይሰጠናል windows 10/7/8 እና Ubuntu።
ብ
ዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ኡቡንቱን ከዊንዶው 10/7/8 ጋር አጫጫን (Dual Boot)?? 1. መጀመሪያ fast boot እናጠፋለን። Control panel > Hardware and Sound > Power Options > System Settings ...Change settings የሚለው ክሊክ እናደርጋለን እዛው በመቀጠልም Turn on fast start up የሚለው ላይ ✅ ካለ እናጠፋለን። 2. አዲስ partition እንፈጥራለን። Disk…»