Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ላጊ ሆኗል፡፡ እነዚህ ኮምፒውተሮች ለቢት ኮይን ማግኛ ሆነዋል፡፡
ቢትኮይን የሚነሳበት ተቃውሞ አለ?
አዎ፡፡ ለቢትኮይን ዝውውር ጥቅም ላይ የሚውሉ ኮምፒውተሮች በጣም ከፍተኛ ሃይል ይፈልጋሉ፡፡ ከመንግስት እና ባንክ ቁጥጥር ውጪ ስለሚንቀሳቀስና ተቋማዊ አለመሆኑ የህጋዊነት ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሳበታል፡፡ መንግስታት የገንዘብ ዝውውር እገዳ ለመጣል ቢፈልጉ ይህ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡
ቢትኮይንን የሚጠቀሙ ሀገራት አሉ?
አሜሪካ፤ ካናዳ፤ ፊንላንድና ቤልጂየም በተለያየ መልኩ ቢትኮይንን የተቀበሉት ሲሆን ቻይና፤ ሩስያ፤ ቬትናምና ቦሊቪያ ደግሞ እገዳ የጣሉ ሀገራት ናቸው፡፡
ምንጭ ministry of innovation and technology
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ብሎክ ቼይን ምንድነው? ቢትኮይንስ? ብሎክቼን በሚሊየን የሚቆጠሩ የኮምፒውተር መረጃዎችን ባልተማከለ መልኩ የሚመዘግብ የብሎክ ጥርቅም የሖነ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይኸ ቴክኖሎጂ በባንኮች እጅ የሚገኘውን እና በመንግሥታት ግምጃ ቤት ቁጥጥር የሚደረግበትን የገንዘብ ዝውውርና የመረጃ ፍሰት ያልተማከለ ለማድረግ እቅድ አለው። ከዚህ በተጨማሪ ከገንዘብ ዝውውር እስከ የመሬት ባለቤትነት ምዝገባ ያሉ ሥራዎችን ሊከወንበት…»
በመሬት ዙርያ የሚሾሩ ሳተላይቶች ቁጥራቸው ስንት ይደርስ ይሆን? ደግሞስ እርስ በርስ እንዴት አይጋጩም? ደግሞስ እንዴት ወደ መሬት አይፈጠፈጡም?
ከሰሞኑ በአንድ ጊዜ 64 ሳተላይቶችን የማምጠቅ ሐሳብ ተወጥኗል።
ይህ የተወጠነው በደቡብ አፍሪካዊው ባለጸጋ ኢለን ማስከ አማካኝነት ሲሆን «ስፔስ ኤክስ ኤሮስፔስ» ደግሞ ኩባንያው ነው።
በቅርቡ የሚመጥቀው ፋልከን 9 ሮኬት ታሪካዊ የሆነውም ለዚሁ ነው። ከአሜሪካ ምድር የሚነሳው ይህ ሮኬት በአንድ ጉዞ ብቻ 64 ሳተላይቶችን ያመጥቃል።
እነዚህ በኅብረት እንዲመጥቁ የሚደረጉት 64 ሳተላይቶች ከ34 ድርጅቶችና ከ17 አገራት የተሰበሰቡ ናቸው።
• ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት?
ሳተላይቶቹ የተለያየ መጠንና አገልግሎት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። ለስልክ ግንኙነቶች፣ ለኢንተርኔትና በመርከቦች ላይ የሚፈጸሙ የባሕር ላይ ወንጀሎችን ለመከታተል እንዲያገለግሉ የታሰቡም ይገኙበታል።
ለመሆኑ ስንት ሳተላይቶች ሕዋ ላይ እንዳሉ ይታወቃል? ደግሞስ ማንም ተነስቶ ወደ ሕዋ ሊያመጥቃቸው ይችላል? ወይስ ፍቃድ ያሻል? ፍቃድ ካስፈለገ ፍቃድ ሰጪው ማን ነው? ሳተላይቶች እርስበርስ ሊላተሙ የሚችሉበት አጋጣሚስ ይኖር ይሆን?
ለመኾኑ በመሬት ምህዋር የሚዘዋወሩ ሰው ሰራሽ ሳተላይቶች ስንት ይሆናሉ ብለው ይገምታሉ? መቶ? ሺህ? 10ሺህ?
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአውተር ስፔስ ጉዳዮች ቢሮ UNOOSA እንደተገለጸው ዛሬ ላይ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ሳተላይቶች ይገኛሉ። ቁጥሩን በትክክል ለማስቀመጥ ያህል 4921 ሳተላይቶች ምድርን እየተሽከረከሩ ነው።
ነገር ግን ሁሉም በሥራ ላይ ናቸው ማለት አይደለም።
• ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው
ከሥራ ውጭ የሆኑት 2600 ሲሆኑ በሕዋ ላይ እነዚህን ሳተላይቶች ጨምሮ 17ሺህ የሚጠጉ የተለያዩ ሳተላይት ያልሆኑ መሣሪያዎች ይገኛሉ ይላል በደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሕዋ ተመራማሪው ዴቪድ ባርን ሀት። እነዚህ ቁሳቁሶች በድምሩ 7600 ቶን ይመዝናሉ።
ሁሉም የሚገኙት ታዲያ ከመሬት እስከ 35 ሺህ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው።
1. የሳተላይቶቹ መጠን ምን ያህል ነው?
ሳተላይትን ስናስብ መጀመርያ ወደ አእምሯችን የሚመጣው እጅግ ግዙፍና እጅግ ከባድ ከሆኑ ቁሳቁሶች የተሠራ በጣም ትልቅ ቁስ ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን ሁሉም ሳተላይቶች እንደዚያ አይደሉም።
መጠናቸውም ቢሆን ይለያያል። ትንሽ የዳቦ ቅርጫት ከሚያክሉት አንስቶ የከተማ አውቶቡስ እስከሚያህሉት ድረስ አሉ። አንድ መለስተኛ የእግር ኳስ ሜዳ የሚያክሉ ሳተላይቶችም ይገኛሉ።
2. ሳተላይት አገልግሎቱ ምንድነው?
ሁሉም ሳተላይቶች ወደ ምድር አጎንብሰው የመሬት አካልን ፎቶ የሚያነሱ አይደሉም። ዘርፈ ብዙ አገልግሎትን ይሰጣሉ።
የኮሚኒኬሽን ሥራ አንዱ ነው። የስልክ ግንኙነትን፣ የዳታ ስርጭትን የምናገኘው በሳተላይቶች አማካኝነት ነው።
የመሬት ቅኝትና ምልከታን (የጂፒኤስ ሥርዓትን ይጨምራል) የምናውቀው ሳተላይቶች ስላሉ ነው።
• የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ
የሕዋ ጥናትን እንዲሁም የፕላኔት ጥናትን የሚያካሄዱ መልከ ብዙ ሳተላይቶችም ይገኛሉ።
ነገ አዲስ አበባ ይዘንብ ይሆን ወይስ ደመናማ ይሆናል ለማለት የሳተላይት ምስሎች ያስፈልጉናል። የባህር ወጀብን ሳይቀር ምስል አንስቶ የሚልከው ሳተላይት ነው።
የዓለማችን ሳንባ የሚባለው አማዞን ጫካ ውስጥ ምን ያህል ምንጣሮ እየተካሄደ እንደሆነ፣ ቻይና በረሃ ውስጥ አፈናና ግድያ የሚፈጸምበት ማጎርያ እየተገነባ ይሁን አይሁን ሳተላይቶች ፍንጭ ያቀብሉናል።
በቤታችን ቁጭ ብለን የምንኮመኩማቸው የቴሌቪዥን ስርጭቶችና የራዲዮ ሞገዶች የሳተላይት እገዛን የሚሹ ሊሆኑ ይችላሉ።
3. እንዴት ነው ሳተላይት በምህዋሩ መቆየት የሚችለው?
ሳተላይቶች በምድር ዙርያ ሊሾሩ የሚችሉት የመሬት ስበትን ለመቋቋም በሚያስችል ፍጥነት ላይ እንዲሆኑ ስለተደረጉ ነው። አለበለዚያ ወደ መሬት ይወድቁ ነበር።
ይህን ለመረዳት ትንሽ ውስብስብ ቢሆንም በቀላሉ አንድ መድፍ በከፍተኛ ጉልበት በ180 ዲግሪ ቢተኮስ መሬት ላይ ከመውደቁ በፊት በሆነ አቅጣጫ የተወሰኑ ርቀቶችን ይጓዛል። ወደ መሬት የመውደቅ ርቀቱ የሚወሰነው በሚኖረው የፍጥነት ጉልበት ነው።
ሳተላይቶችም ለመሬት ስበት እጅ የማይሰጡበት ምክንያት ፍጥነታቸው ነው።
4. የሳተላይቶችን ዕድሜ ምን ያህል ነው?
ሮኬቶች ሳተላይትን ጭነው ወደ ሕዋ ያመጥቁና ለሳተላይቱ ከተሰናዳለት ቦታ ያኖሩታል። የተስተካከለ ርቀቱን እስኪያገኝ ወራትን ሊወስድ ይችላል። በመጨረሻም ሳተላይቱን በምህዋሩ ላይ ይቀመጣል።
ሳተላይቱ ተሸክሞት ከሄደው ሮኬት ቀስ በቀስ በሚለያይበት ወቅት የሚኖረው ፍጥነት በመሬት ዙርያ ለመቶ ዓመት መሽከርከር ያስችለዋል ይላሉ ባለሞያዎች።
ዋናው ሳተላይት በሕዋ ላይ እንዲቆይ የሚያደርገው ምስጢር የመሳሳብ ፊዚክስ ሲሆን በመሬት ስበት እንዳይወድቅ የሚያግደው ብቸኛው ጉዳይ የእሽክርክሪት ፍጥነቱ ነው።
ለዚያም ነው ከመሬት በቅርብ ርቀት የሚገኙት ሳተላይቶች የሚሾሩበት ፍጥነት ከመሬት ራቅ ብለው ከሚገኙት ይልቅ ፈጣን የሆነው።
• በዓይነ ስውሯ የተሠራው የሚያይ ሻንጣ
ሳተላይቶች የእሽክርክሪት ምህዋራቸውን መለወጥ ቢያስፈልግ እና እርስበርስም እንዳይጋጩ እንዲረዳ የየራሳቸውን ነዳጅ ተጭኖላቸዋል።
ሳተላይቶች ከ5 እስከ 15 ዓመታት አገልግሎት ላይ ሊቆዩ ይችላሉ። ዕድሜያቸው ግን በሚሰጡት አገልግሎትና በሚታጠቁት የነዳጅ መጠን ይለያያል።
5. ሳተላይቶች ሊጋጩ ይችላሉ?
ሊጋጩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ የሚሆን ነገር አይደለም። ምክንያቱም የሚሾሩበት መስመር ከመለያየቱም ባሻገር ሕዋ እጅግ ሰፊ አካል መሆኑ ግጭት እንዳይኖር ያደርጋል።
ይህ ማለት ግን ግጭት በፍጹም አይከሰትም ማለት አይደለም። በአሁኑ ጊዜ እጅግ በርካታ ሳተላይቶችን የማምጠቅ ዕቅድ መኖሩ ሲታይ ግጭት የመከሰቱ ዕድል ዜሮ ነው ማለት አይቻልም።
በየካቲት፣ 2009 አንድ የአሜሪካና አንድ የራሺያ ሳተላይቶች ተላትመው ያውቃሉ። ይህ በታሪክ የተመዘገበ የመጀመርያው የሳተላይቶች ግጭት ነው።
6. ሳተላይቶችን ማን ነው የሚቆጣጠራቸው?
ሳተላይቶች በድርጅቶች ወይም በኩባንያዎች ወይም በመንግሥት አንዳንድ ጊዜም በግለሰቦች ባለቤትነት ሊያዙ ይችላሉ።
በ1967 በተደረገው የአውተር ስፔስ ስምምነት መሠረት እያንዳንዱ ሳተላይት ያመጠቀ አገር የተወሰነ የመቆጣጠር ሥልጣን እንዲኖረው የተደረገው የሬዲዮ ልውውጥ መጠላለፍን ለማስቀረት ጭምር ነው።
በአሜሪካ ለምሳሌ የግል ኩባንያዎች በስፔስ አገልግሎት ላይ ለመሰማራት መጀመርያ ከፌዴራል መንግሥት ፍቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል።
ለኮሚኒኬሽንና ቴሌኮም ሳተላይት ግንኙነት ለማድረግ ከፌዴራል ኮሚኒኬሽን ኮሚሽን ፍቃድ መውሰድ ግድ ነው። ሳተላይትን ወደ ሕዋ ለማምጠቅ ደግሞ የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደርን ፍቃድ ማግኘት ያሻል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ የተባበሩት መነግሥታት ድርጅት የአውተር ስፔስ ጉዳዮች በእንግሊዝኛ ምህጻሩ UNOOSA የሚባለው ኃላፊ መሥሪያ ቤት ነው። በሕዋ ጉዳዮች ዙርያ ሕግ ያረቃል ይቆጣጠራል።
7. ማንም ሳተላይት ወደ ሕዋ ማምጠቅ ይችላል?
አዎ! ዛሬ ማንኛውም ሰው ሳተላይትን ወደ ሕዋ ማምጠቅ የሚችለበት ደረጃ ተደርሷል። የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሳይቀሩ ሳተላይት ገንብተው በማምጠቅ ፕሮግራማቸውን ከሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት ጋር ይጋራሉ።
ከመቼውም ጊዜ በላይ የንግድ ኩባንያዎች ሳተላይት የሚያመጥቁበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። ኾኖም ከፍ ያለ በጀት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ይህ የሳተላይት ኢንዱስትሪም በቢሊዮን
👏1
ይገመታል።
ምንጭ BBC
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «በመሬት ዙርያ የሚሾሩ ሳተላይቶች ቁጥራቸው ስንት ይደርስ ይሆን? ደግሞስ እርስ በርስ እንዴት አይጋጩም? ደግሞስ እንዴት ወደ መሬት አይፈጠፈጡም? ከሰሞኑ በአንድ ጊዜ 64 ሳተላይቶችን የማምጠቅ ሐሳብ ተወጥኗል። ይህ የተወጠነው በደቡብ አፍሪካዊው ባለጸጋ ኢለን ማስከ አማካኝነት ሲሆን «ስፔስ ኤክስ ኤሮስፔስ» ደግሞ ኩባንያው ነው። በቅርቡ የሚመጥቀው ፋልከን 9 ሮኬት ታሪካዊ የሆነውም ለዚሁ ነው። ከአሜሪካ…»
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ስልክ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ!... ብዙ ሰዉ የማያዉቃቸው የሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች! """""""""""""""""""""""""""""""""""""""""" ስልክ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ! *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0910477613 ከሆነ ወደ *21*091045561#…»
ቀጥታ & በማጣመር ዲቫይሶችን ማገናኘት
ኮምፒውተሮችንና ዲቫይሶችን ለማገናኘት ገመዶች ቀለማት በመደርደር በኔትዎርካችን ላይ የምንጠቀማቸውን ዲቫይሶች ስትሬት (ቀጭታ)ና ክሮስኦቨር በማለት እንለያለን
• ቀጥታ የምንጠቀመው በሁለቱም(2) ጫፍ ላይ አርጃ (RJ)45 ላይ የምናስገባው ለሚከተሉት ዲቫይሶች ብቻ ነው
1 ስዊች ከራውተር ጋር ስናገናኝ
2 ኮምፒውተር ከስዊች
3 ኮምፒውተር ከሃብ ጋር ብቻ ናቸው
ይህም ማለት በA ወይም በB አደራደረ ብቻ በሁለቱም ጫፍ በመጠቀም ነው
ክሮስ አቨር(በማጣመር)የምንለው በአንድ ጫፍ በB በሌላኛው ሳይድ በA በመስራት ስንጠቀም ነው ይህም አደራደር የሚጠቀሙት የሚከተሉት ዲቫይሶች ናቸው፡፡
1 ስዊች ከስዊች
2 ስዊች ከሃብ
3 ሀብ ከሃብ
4 ራውተር ከራውተር
5 ኮምፒውተር ከኮምፒውተር
6 ኮምፒውተር ከራውተር ናቸው
ላይክ ሸር ያድርጉ ላልደረሳቼው ያድርሱ (ያለዎትን አስተያየት ይስጡን)
Share your knowledge free for millions
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ቀጥታ & በማጣመር ዲቫይሶችን ማገናኘት ኮምፒውተሮችንና ዲቫይሶችን ለማገናኘት ገመዶች ቀለማት በመደርደር በኔትዎርካችን ላይ የምንጠቀማቸውን ዲቫይሶች ስትሬት (ቀጭታ)ና ክሮስኦቨር በማለት እንለያለን • ቀጥታ የምንጠቀመው በሁለቱም(2) ጫፍ ላይ አርጃ (RJ)45 ላይ የምናስገባው ለሚከተሉት ዲቫይሶች ብቻ ነው 1 ስዊች ከራውተር ጋር ስናገናኝ 2 ኮምፒውተር ከስዊች 3 ኮምፒውተር ከሃብ ጋር ብቻ ናቸው ይህም…»
ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ ሲፅፉ ካልፈጠኑ ወይም መፃፍ ካልቻሉ የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ ይመልከቱ እና ይለማመዱ።
==============================
• ሀ ፡ h ሁ ፡hu ሂ ፡hi ሃ ፡ ha ሄ ፡hy ህ ፡he ሆ ፡ho
• ለ ፡l ሉ ፡lu ሊ፡li ላ ፡la ሌ፡ly ል፡le ሎ፡lo
• ሐ፡shift +h ሑ፡shift +hu ሒ፡shift +hi ሓ፡shift +ha ሔ፡ shift + hy ሕ፡shift +he ሖ፡shift +ho
• መ፡m ሙ፡mu ሚ፡mi ማ፡ma ሜ፡my ም፡me ሞ፡mo
• ሠ፡shift + s ሡ፡shift + su ሢ፡shift + si ሣ፡shift+sa ሤ፡shift + sy ሥ፡shift + se ሦ፡shift + so
• ረ፡r ሩ፡ru ሪ፡ri ራ፡ra ሬ፡ry ር፡re ሮ፡ro
• ሰ፡s ሱ፡su ሲ፡si ሳ፡sa ሴ፡sy ስ፡se ሶ፡so
• ሸ፡caps locks ሹ፡caps lock+su ሺ፡caps lock+si ሻ፡caps lock+sa ሼ፡caps lock+sy ሽ፡caps lock+se ሾ፡caps lock+so
• ቀ፡q ቁ፡qu ቂ፡qi ቃ፡qa ቄ፡qy ቅ፡qe ቆ፡qo
• በ፡b ቡ፡bu ቢ፡bi ባ፡ba ቤ፡by ብ፡be ቦ፡bo
• ተ፡t ቱ፡tu ቲ፡ti ታ፡ta ቴ፡ty ት፡te ቶ፡to
• ቸ፡c ቹ፡cu ቺ፡ci ቻ፡ca ቼ፡cy ች፡ce ቾ፡co
• ነ፡n ኑ፡nu ኒ፡ni ና፡na ኔ፡ny ን፡ne ኖ፡no
• ኘ፡shift +n ኙ፡shift +nu ኚ፡shift+ni ኛ፡shift +na ኜ፡ shift +ny ኝ፡shift + ne ኞ፡shift +no
• ከ፡ka ኩ፡ku ኪ፡ki ካ፡ka ኬ፡ky ክ፡ke ኮ፡ko
• ኸ፡capslock+ shift+ h ኹ፡capslock+shift+hu ኺ፡ capslock+shift +hi ኻ፡capslock+
• Shift +ha ኼ፡ Capslock+ Shift +hy ኽ፡Capslock+ Shift+ he ኾ፡Capslock+ Shift + ho
• ኀ፡ capslock + h ኁ፡ capslock + hu ኂ፡ capslock + hi ኃ፡ capslock + ha ኄ፡ capslock + hy ኅ፡ capslock + he ኆ፡ capslock + ho
• አ ፡ x ኡ፡xu ኢ፡xi ኣ፡xa ኤ፡xy እ፡xe ኦ፡xo
• ዐ፡shift +x ዑ፡shift +xu ዒ፡shift +xi ዓ፡shift +xa ዔ፡ shift +xy ዕ፡shift +xe ዖ፡shift +xo
• ወ፡w ዉ፡wu ዊ፡wi ዋ፡wa ዌ፡wy ው፡ we ዎ፡wo
• ዘ፡z ዙ፡zu ዚ፡zi ዛ፡za ዜ፡zy ዝ፡ze ዞ፡zo
• ዠ፡shift + z ዡ፡shift + zu ዢ፡shift + zi ዣ፡shift +zaዤ፡shift + zy ዥ፡shift + ze ዦ፡ shift + zo
• ፈ፡f ፉ፡fu ፊ፡fi ፋ፡fa ፌ፡fy ፍ፡fe ፎ፡fo
• ፐ፡p ፑ፡pu ፒ፡pi ፓ፡pa ፔ፡py ፕ፡pe ፖ፡po
• ገ፡g ጉ፡gu ጊ፡gi ጋ፡ga ጌ፡gy ግ፡ge ጎ፡go
• ደ፡d ዱ፡du ዲ፡di ዳ፡da ዴ፡dy ድ፡de ዶ፡do
• ጠ ፡ shift + t ጡ፡ shift + tu ጢ፡ shift + ti ጣ፡ shift+ta ጤ፡ shift + ty ጥ፡ shift + te ጦ፡ shift + to
• ጨ፡ shift +c ጩ፡shift +cu ጪ፡shift +ci ጫ፡shift+caጬ፡shift +cy ጭ፡shift +ce ጮ፡shift +co
• ጸ፡capslock + t ጹ፡capslock + tu ጺ፡capslock + ti ጻ፡capslock + ta ጼ፡ capslock + ty ጽ፡capslock + t ጾ፡capslock + to
• ፀ፡capslock+ shift + t ፁ፡capslock + shift + tu ፂ፡capslock + shift + ti ፃ፡ capslock + shift + t ፄ፡capslock + shift + ty ፅ፡ capslock + shift + te ፆ፡capslock + shift + to
• ጀ፡j ጁ፡ju ጂ፡ji ጃ፡ja ጄ፡jy ጅ፡je ጆ፡jo
• ቨ፡v ቩ፡vu ቪ፡vi ቫ፡va ቬ፡vy ቭ፡ve ቮ፡vo
• ቋ፡Capslock + qwa ቧ፡Capslock + bwa ቷ፡Capslock + twa ኟ፡Capslock + Shift + nwa ቿ፡Capslock + cwa ሟ፡ Capslock + mwa ቷ፡Capslock + twa ጓ፡Capslock + gwa ፏ፡Capslock + fwa ሯ፡Capslock +• rwa ዷ፡Capslock + dwa ቯ፡Capslock + vwa ኋ፡ Capslock + hwa ዟ፡Capslock + zwa ዧ፡Capslock + Shif +zwa ኗ፡Capslock + nwa ሏ፡ Capslock + lwa ኳ፡Capslock + kwa ሷ፡Capslock + swa ጇ፡Capslock + jwa ጧ፡ Capslock + twa
(መረጃ ጠቃሚ ነዉ!)
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍3
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ ሲፅፉ ካልፈጠኑ ወይም መፃፍ ካልቻሉ የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ ይመልከቱ እና ይለማመዱ። ============================== • ሀ ፡ h ሁ ፡hu ሂ ፡hi ሃ ፡ ha ሄ ፡hy ህ ፡he ሆ ፡ho • ለ ፡l ሉ ፡lu ሊ፡li ላ ፡la ሌ፡ly ል፡le ሎ፡lo • ሐ፡shift +h ሑ፡shift +hu ሒ፡shift +hi ሓ፡shift +ha ሔ፡ shift + hy ሕ፡shift…»
#የኔትዎርክ_የትውስትድ_ፔር_ገመድ_ኬበል_ከለር_ኮዶች!
ትውስትድ ፔር ገመድ ለኔትዎርክ ስንጠቀምበት ኮምፒውተሮችንና ዲቫይሶችን ለማገናኘት ያሉትን ገመዶች ቀለማት በመደርደር በአለም አቀፍ የተሰጠውን የአደራደር ተራ ከ1 እስከ 8 በማስቀመጥ ወደ አርጃ(RJ)45 ዲቫይስ ውስጥ እናስገባለን በመቀጠልም ለኔትዎርክ ዝርጋ ከሚያስፈልጉት ዋናው እቃ ውስጥ ክሊገፐርን በመጠቀም አርጃ(RJ)45 ዲቫይስ እንጨፈልቃለን ይህን ከማድረጋችን በፌት በአለም አቀፍ ደረጃ የተሰጣቸውን የቀለም አደረራደረር አይነት የሚጠቀሙትን መለየት ያስፈልጋል እነዚህን እንደሚከተልው እናያለን፡፡
በቲውስድ ፔር ገመድ ውስጥ ያለው አንሽድድ ቲውስትድ ፔር ገመድ በ568A ና 568B እንከፍለዋለን ይን ገመድ ያሉትን ስምንት(8) ገመዶች ውስጥ ካሉት ቀለማት ከዚህ በታች ባለው መሰረት እንደረድራቸዋለን
በ568B
1. ነጭና ኦሬንጂ (ብርቱካናማ)
2. ኦሬንጂ(ብርቱካናማ)
3. ነጭና አረንጔዴ
4. ስሚያዊ
5. ነጭና ስሚያዊ
6. አረንጔዴ
7. ነጭና ቡናማ
8. ቡናማ ናቸው
በ568A
1. ነጭና አረንጔዴ
2. አረንጔዴ
3. ነጭና ኦሬንጂ (ብርቱካናማ)
4. ስሚያዊ
5. ነጭና ስሚያዊ
6. ኦሬንጂ(ብርቱካናማ)
7. ነጭና ቡናማ
8. ቡናማ ናቸው
ቀጥታ & በማጣመር ዲቫይሶችን ማገናኘት
ኮምፒውተሮችንና ዲቫይሶችን ለማገናኘት ገመዶች ቀለማት በመደርደር በኔትዎርካችን ላይ የምንጠቀማቸውን ዲቫይሶች ስትሬት (ቀጭታ)ና ክሮስኦቨር በማለት እንለያለን
ቀጥታ የምንጠቀመው በሁለቱም(2) ጫፍ ላይ አርጃ (RJ)45 ላይ የምናስገባው ለሚከተሉት ዲቫይሶች ነው
ስዊች ከራውተር ጋር ስናገናኝ
ኮምፒውተር ከስዊች
ኮምፒውተር ከሃብ ጋር ብቻ ናቸው
ይህም ማለት በA ወይም በB አደራደረ ብቻ በሁለቱም ጫፍ በመጠቀም ነው
ክሮስ አቨር(በማጣመር)የምንለው በአንድ ጫፍ
በB በሌላኛው ሳይድ በA በመስራት ስንጠቀም ነው
ይህም አደራደር የሚጠቀሙት የሚከተሉት ዲቫይሶች
ናቸው፡፡
ስዊች ከስዊች
ስዊች ከሃብ
ሀብ ከሃብ
ራውተር ከራውተር
ኮምፒውተር ከኮምፒውተር
ኮምፒውተር ከራውተር ናቸው

ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👏2
የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "backups" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን?
በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች ለመያዝ የሚውሉ መገልገያዎችን እንጠቁምዎ፡፡-
- # ፍሎፒ_ዲስክ /Floppy Disk/:- ትንሽና አነስተኛ መጠን ያለው ዲስክ ሲሆን አቅሙም 1.4 MB ነው፡፡ ጠቃሚ መረጃዎችን በፍሎፒ ዲስክ ለመያዝ በርካታ ዲስኮች ያስፈልጉናል፡፡ የድሮ ኮምፒውተሮች በብዛት ፍሎፒ ዲስክ መጠቀሚያ የነበራቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚመረቱ ኮምፒውተሮች አብዛኞቹ አገልግሎቱ የላቸውም፡፡
- # ዚፕ_ድራይቭ /Zip Drive/፡- ዚፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር MB መጠን ያላቸው ፋይሎችን /data/ የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ዚፕ ድራይቮችን ለመጠቀም የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት /hook up/ ይኖርባቸዋል፡፡
- # ቴፕ_ድራይቭ / Tape Drive/፡- ቴፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር GB (በሺዎች የሚቆጠር MB) መጠን ያላቸው ፋይሎችን ይይዛል፡፡ ይህም ተጨማሪ ድራይቭ በመሆኑ የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት ይኖርበታል፡፡
- # ሲዲ_በርነር /CD Burner/፡- ሪከርድ የሚያደርጉ ሲዲዎች /CD-Rs/ እስከ 700 MB የሚሆኑ ፋይሎች የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ አሁን ላይ የምንጠቀምባቸው አብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ሲዲ በርነር /CD Burner/ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹም ዲቪዲ በርነር /DVD Burners/ አላቸው፡፡ ዲቪ ዲ አር ኤስ /DVD-Rs/ እስከ 4.7 GB ፋይል የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ስለዚህ በአማራጭ የመጠባበቂያ ፋይል መያዣ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡
- # ፍላሽ_ድራይቭ /Flash Drive/፣ የ ኤስ ቢ ድራይቭ /USB Drive/ እና ተምብ ድራይቭ /Thumb Drive/፡- ለአንድ ነገር የተለያየ ስያሜ ቢኖርም በኮምፒውተሮቻችን የዩ ኤስ ቢ /USB/ ፋይል መቀበያ በኩል በቀላሉ የሚሰኩ ተነቃይ ድራይቨሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ድራይቨሮች ከ10 MB የሚጀምሩ ሲሆን 1 GB፣ 2 GB፣ 4 GB፣ 8 GB፣ 16 GB፣ 32 GB፣ 64 GB … እያሉ አሁን ላይ 4TB ፋይል የመያዝ አቅም ያላቸው ፍላሽ ድራይቮች በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍላሽ ዲስኮች በቀላሉ በኪስ የሚያዙና ተንቀሳቃሽ ቢሆኑም በቀላሉ ወድቀው ሊጠፉ የሚችሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡
- # ኤክስተርናል_ሃርድ_ዲስክ /External hard Drive/:- ኤክስተርናል ሀርድ ድርይቭ በኮምፒውተር ሲስተሞቻችን ውጪ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ፋይሎችን የምናስቀምጥበት መሣሪያ ነው፡፡ ይህ መሣሪያ /Drive/ ፋይሎችን ይዞ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል እና ከኮምፒውተራችን ጋር በዩ ኤስ ቢ /USB/፣ በፋየርዋየር /Firewire/ ኮኔክሽን ወይም በገመድ አልባ /wirelesely/ ሊገናኝ የሚችል ነው፡፡
- # ታይም_ማሽን /Time Machine/፡- Time Mac ለተጠቃሚዎች አማራጭ የኤክስተርናል ፋይል መጠባበቂያ መያዣ መንገድ ነው፡፡ ይህ መጠባበቂያ መያዣ ዘዴ ለ24 ሰዓት በቀጥታ ፋይሎቻችንን ለማስቀመጥ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ፋይሎች ተረስተው ለጉዳት እንዳይጋለጡ ያግዛል፡፡ ታይም ማሽን በመጠባበቂያው የሚይዘው የተመረጡ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ድራይቨሩን ነው፡፡
- # ኔትወርክድ የሆነ የመረጃ ማካማቻ /Networked Attached Storage/:- ይህ ከአንድ በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮች በኔትወርክ ተገናኝተው መረጃ የሚቀመጥበት ሥርዓት ሲሆን ይህም በስርዓት የተደረደሩ፣ ያልተደጋገሙ የፋይል ማከማቻ ኮኒቲነሮችን እና በርካታ የዲስክ ድራይቭ አካላትን የያዘ ነው፡፡ ይህም በፍጥነት መረጃ ለማግኘት፣ በቀላሉ መረጃዎችን ለማስተዳደርና ለማስተካከል የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡
- # ስውር_የበይነ_መረብ_መረጃ ማከማቻ /Cloud Storage/:- ይህ የፋይል ማከማቻ ዓለም አቀፍ የመረጃ ማከማቻ ሥርዓት ሲሆን በኔትወርክ አማካኝነት በመገናኘት መረጃዎቻችን ክላውድ ተብሎ በሚጠራ የመረጃ መጠባበቂያ ሥርዓት /Cloud Server/ ውስጥ የምናስቀምጥበት መንገድ ነው፡፡ በርካታ የክላውድ ማማቻ ዓይነቶች በበየነ-መረብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እነዚህም በነጻ ወይም በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ iCloud፣ Dropbox፣ Google Drive እና OneDrive የታወቁ የመረጃ ማከማቻ መንገዶች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ የሚከማቹበት ሥፋራ በመራጃ በለቤቶቹ ቁጥጥር ሥር ባለመሆኑ የመረጃዎቹ ደህንነት አስተማማኝ እንደስጋት ይታያል፡፡
- # ፕሪንት_ማድረግ /Printing/:- ምንም አንኳን መረጃዎቻችን በሶፍት ኮፒ የምናስቀምጠውን የህል የተማቹ ባይሆኑ ኮምፒውተሮቻችን በተለያየ ምክንያት ለቀናት አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙበት አጋጣሚ ቢፈጠር ፕሪንት ያደረግናቸው ፋይሎች እጅጉን ይጠቅሙናል፡፡
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍2
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "backups" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን? በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች…»
#ላፕቶፕ_ስንገዛ_ማወቅ_እና_ማየት_ያለብን_ወሳኝ_ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም
ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ
የሆነ
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል
ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን
ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ
Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ