Muhammed Computer Technology (MCT)
38.6K subscribers
490 photos
7 videos
211 files
839 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
የኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ለመማር የምትፈልጉ፣ የተማራችሁ ምርጥ ምርጥ መጽሀፎች ታገኛላችሁ! ከዚህ በታች ባለው link በመግባት ማውረድና ማንበብ ትችላላችሁ።
If you’re interested click on the link below link to download.
👇
https://books.goalkicker.com/
የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች
አንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የሚጎረብጡ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችንን ከሚጎረብጡ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሞባይል ባትሪ ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ፣ በዚህ ዙሪያ ለሳይቴክ ደንበኞች መላ የሚሆን ነገር አናቀርብላቸውም ብለን አሰብን… ምን ትላላችሁ?
ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ የተሰሩት ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) ሲሆን ይሄም ባትሪ በአግባቡ ካለመጠቀም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ ይደክማል፤ ያረጃል፡፡ ይሄም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡ የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው ሲሆን ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ የሚያስግሩባቸውን ምክንያች እና ባትሪን በተሻለ መጠቀም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች እንደሚከተለው እንጠቁማችኋለን፡፡
የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡-
1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም
ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡
2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡
3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር
በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት
ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ
የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
6. 2 ደቂቃ ቢያቆይዎት ነው፤ ነገር ግን ይሄን መረጃ ሼር ብታደርጉት የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል፡፡ አሁኑኑ ሼር አድርጉት፡፡
✅✅✅የጡረታ አበል ስሌት ምሳሌዎች✅✅✅
1. ዕድሜ በመድረሱ ለሚጠየቅ የዘለቄታ ጡረታ አበል ስሌት
 ለሲቪል የመንግስት ሠራተኛ
በህግ የተወሰነው የጡረታ መውጫ ዕድሜ በመድረስ ከስራ ለሚሰናበት ሲቪል የመንግስት ሠራተኛ ለመጀመሪያ 10 ዓመት ለፈፀመው አገልግሎት 30% ከ10 ዓመት በላይ ለተፈፀመ ለእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት በ1.25 በማባዛት ከ30% ጋር በመደመር የሚገኘው መቶኛ ውጤት ከመጨረሻዎቹ 36 ወራት አማካይ ደመወዝ ጋር ተባዝቶ የሚሰላ ይሆናል፡፡
ለምሳሌ፡-
የ28 ዓመት አገልግሎት ያለው ሲቪል የመንግስት ሠራተኛ ለመጀመሪያው 10 ዓመት አገልግሎት 30%፣ ከአስር ዓመት በላይ ያለው 18 ዓመት አገልግሎት 18×1.25 = 22.5% ሲሆን በአጠቃላይ 30% + 22.5% = 52.5% ነው፡፡ የመጨረሻዎቹ 36 ወራት አማካይ ደመወዙ 5000.00 ከሆነ የባለመብቱ የዘለቄታ የጡረታ አበል 5,000.00 x 52.5% = 2,625.00 ብር ይሆናል፡፡
 ለመከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ አባላት
በህግ የተወሰነው የጡረታ መውጫ ዕድሜ በመድረስ ከስራ ለሚሰናበት የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባል ለመጀመሪያ 10 ዓመት ለፈፀመው አገልግሎት 30% ከ10 ዓመት በላይ ለተፈፀመ ለእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት በ1.65 በማባዛት ከ30% ጋር በመደመር የሚገኘው መቶኛ ውጤት ከመጨረሻዎቹ 36 ወራት አማካይ ደመወዝ ጋር ተባዝቶ የሚሰላ ይሆናል፡፡
ለምሳሌ:-
የ28 ዓመት አገልግሎት ያለው የመከላከያ ሠራዊት ወይም የፖሊስ አባል ለመጀመሪያው 10 ዓመት አግልግሎት 30%፣ከአስር ዓመት በላይ ያለው 18 ዓመት አገልግሎት 18×1.65 = 29.7% ሲሆን በአጠቃላይ 30% + 29.7%= 59.7% ነው፡፡ የመጨረሻዎቹ 36 ወራትአማካይ ደመወዙ 5,000.00 ከሆነ የባለመብቱየዘለቄታ የጡረታ አበል 5,000.00 x 59.7% = 2,985.00 ብር ይሆናል ፡፡
2. በጤና ጉድለት የዘለቄታ ጡረታ አበል ስሌት
ከ10 ዓመትና በላይ አገልግሎ በጤና ጉድለት ምክንያት ከሥራ ለሚሰናበት ስቪል የመንግስት ሰራተኛ ወይም የመከላከያ ሰራዊትና ፖሊስ አባል የጡረታአበል የሚወሰነው በዕድሜ ለጡረታ በመድረስ ምክንያት በሚሰራው የጡረታ አበል ስሌት መሰረት ነው፡፡
ሊድን የማይችል የሥራ ላይ ጉዳት የዘለቄታ ጡረታ አበል
የመንግስት ሠራተኛው ጉዳት ከደረሰበት ቀን በፊት የነበረው የወር ደመወዙ 47 በመቶ በመያዝ ይሰላል፡፡
ለምሳሌ፡-
ሠራተኛው ላይ ጉዳት ከደረሰበት ቀን በፊት ባለው ወር ደመወዙ 4,000.00 ብር ቢሆን 4,000.00 × 47% = 1,880.00 ብር የዘለቄታየጉዳት ጡረታ አበል ያገኛል፡፡
⏺⏺⏺1. የዳረጎት (የአንድ ጊዜ) ክፍያ⏺⏺⏺
1.1 የአገልግሎት እና የጤና ጉድለት ዳረጎት
ከ10 ዓመት ያነሰ አገልግሎት የፈጸመ የመንግስት ሠራተኛ ዕድሜው ለጡረታ በመድረሱ ከሥራ ሲሰናበት ወይም ከ10 ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈፅሞ በጤና ጉድለት ምክንያት ለማንኛውም ደመወዝ ለሚያስገኝ ስራ ብቁ ያለመሆኑ በህክምና ቦርድ ተረጋግጦ ከሥራ ከተሰናበተ የአንድ ጊዜ የዳረጎት ክፍያ ያገኛል፡፡
የአንድ ጊዜ የዳረጎት ክፍያ የሚሰላው የመንግስት ሰራተኛው ከሥራ ከተሰናበተበት ወይም ለማንኛውም ሥራ ብቁ ያለመሆኑን የሚገልጽ የህክምና ቦርድ ማስረጃ ከተሰጠበት ወር በፊት ያለው መደበኛ የወር ደመወዝ በአገልግሎት መጠን ተባዝቶ፣ለሲቪል ሰራተኛ በ1.25፣ ለመከላከያ ሠራዊትና ለፖሊስ አባል በ1.65 ታስቦ የአንድ ጊዜ ዳረጎት ይከፈላል፡፡
ምሳሌ 1፡-
አንድ የሲቪል ሠራተኛ አገልግሎቱ 5 ዓመት የሆነ ሠራተኛ ደመወዙ 3,000.00 ቢሆን 3,000.00 X 5 X 1.25 = 18,750.00 የአንድ ጊዜ ዳረጎት አበል ይከፈለዋል፡፡
ምሳሌ 2፡-
አንድ የመከላከያ ሠራዊት ወይም የፖሊስ አባል አገልግሎቱ 5 ዓመት ቢሆንና ደመወዙ 3,000.00 ቢሆን 3,000.00 X 5 X 1.65 = 24,750.00 ብር የአንድ ጊዜ ዳረጎት አበል ይከፈለዋል፡፡
1.2 ሊድን የሚችል የሥራ ላይ ጉዳት ዳረጎት/የአንድ ጊዜ ክፍያ/
የመንግስት ሠራተኛው ጉዳት ከደረሰበት ቀን በፊት ባለው ወር የተከፈለው መደበኛ የወር ደመወዝ መጠን ሲባዛ 5 ሲባዛበ12 ወራት ሲባዛ በ47% ሲባዛ የጉዳት መጠን በመቶኛ ይሆናል፡፡ የጉዳት መጠኑ ከ10 በመቶ በላይ መሆን አለበት፡፡
የሥራ ላይ ጉዳት ስሌት= ደመወዝ X 47% X 5 X 12 X የጉዳት መጠን በመቶኛ ይሆናል፡፡
የጉዳት መጠኑ ከ10 በመቶ በላይ መሆን አለበት፡፡
ለምሳሌ፡-
ሠራተኛው ከጉዳት በፊት የነበረው ደመወዝ 4,000.00 ብር ቢሆን እና የጉዳት መጠኑ 20 በመቶ ከሆነ 4,000.00 × 47% ×5 × 12 × 20%= 22,560.00 ብር የአንድ ጊዜ ክፍያ ያገኛል፡፡
ከተመቻችሁ ሼር ይደረግ
ምንጭ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputer
Technology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ።
የስልካችን📲 ሚሞሪ ምድነዉ የሞላዉ?
መፍትሄዉስ?
***************
***************
✅የአብዛኞቻችን የራስምታት🤔 የሆነብን በስልካችን ላይ ቪድዮ ሙዚቃ✅አፕልኬሽን ስንጭን ሙሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage avaliable) የሚለዉን pop up dialog እንዴት ሚሞሪያችን #free አድርገን አንደምናስተካክል እናያለን።

‼️ግን ለምን ይመጣል?

✅የ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስራ(አፕልኬሽን install ለማድረግ ፋይል ለማስቀመጥ ...) የመስራያ ቦታ ሲያጣ ይከንን #Notification ያሳየናል።

✅የአንድሮይድ አፕልኬሽኖች ማስቀመጫ storage አይነት ይጠቀማሉ።

1⃣ ለ አፕሌክሽኖቹ ለራሳቸዉ የሚወስዱት #memory አለ።

2⃣ ለራሳቸዉ ለ አፕልኬሽኑ #data ማስቀመጫ የሚጠቀሙበት #memory አለ።

3⃣ ለአፕልኬሽኑ #catch ጊዜያዊ ፋይል ማስቀመጫ #memory አለ።

✅እነዚህ #Catch ላይ የተቀመጡ ፋይሎች ጣም ብዙ ቦታ ሊይዙ ይችላሉ።

መፍትሄ👇👇

✅ቆይ መጀመራያ እስቶሬጃችሁን ምን ምን እንደሞላዉ እዩት።

የስልካችሁ ለማየት #Internal storage ምን ምን እንደሞላዉ ለማየት ከታች ያሉትን ስፔፖች ይከተሉ ።

1⃣ #Setting ዉስጥ ይግቡ

2⃣ ከዛ #Storage የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ ።

✅አዚህጋ የ RAM,Internal Storage,SD Card የያዙትን መጠን በ% ያሳያችሗል።

3⃣ Internal Storage የሚለዉን ይጫኑት ።

✳️Avaliable :አሁን ያላችሁ #free የሆነ የሚሞሪ መጠን ነወ።

✳️System ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ለራሱ እና ከስልኩ ገር ለሚመጡ ለአንዳንድ አፕልኬሽኖች(እግደ Setting,Chrome,Phone,GMail,Google,Contacts,Photo. ..) ለማስቀመጥ የተጠቀመበት #memory ያሳየናል።

✳️Owners እኛ የጫናቸዉን አፕሌኬሽኖች, ፎቶዎች,ያሳየናል።
አዉድዮ ፋይሎች እና Catch ሚሞሪ ላይ ያሉት ፋይሎች የያዙትን የሚሞሪ መጠን ያሳየናል።

✅አሁ ከላይ ካየሐችሁት ዉስጥ ብዉ ቦታ ይዞ ሚሞራያችሁን የሞላዉን ትመርጣላችሁ።

✅አፕልኬሽን ከሆነ ብዙ ጊዜ የማትጠቀሙበትን #uninstall ማድረግ።

✳️uninstall ለማድረግ #Setting->Apps ከዛ uninstall ለማድረግ የፈለጋችሁትን አፕልኬሽን መርጣችሁ ስትጫኑት uninstall የሚል ሲመጣ አሱን ይጫኑት።

✅ፎቶ ከሆነ የማትፈልጉትን ፎቶ አየመረረጣችሁ ማጥፋት አለባችሁ።

✅Video ከሆነ የማትፈልጉትን #Video እየመረጣችሁ ማጥፋት።

✅Audio ከሆነም አሸዛዉ ምረጡና አጠያጥፉ

✅ የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ እና እንደ Other#Screenshot የመሣሠሉትን ፋይሎች ያጥፉ

✅Clear data የሚለዉን በመጫን #catch ሚሞሪ ላይ ያሉትን ፋይሎችያጥፉ

✅ሌላኛዉ አማራጭ ትላልቅ ፋይሎችን ከ Internal Memory ላይ #Cut አድርጎ ወደ SD card ላይ ፔስት ማድረግ ነዉ።

✅ሌላዉ አማራጭ SD Card የስልኩ defalu ፍይል (Apps,photo,video,audio በቂ ሁሉንም ነገር)
ማስቀመጫ ማድረግ ነዉ።

ይከን ለማድረግ
👇
✳️Setting-> Storage->default write disk የሚለዉጋ Phone Storage የሚለዉን ተመርጦ ታገኙታላችሁ አናተ SD card የሚለዉን ይምረጡ።

ስለተከታተላችሁኝ አመሠግናለሁ🙏

ስልኩ እየሞላበት የተቸገረ ጓደኛችሁ ስለሚኖር #Share አድርጉላቸዉ።

ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
በዚህ ጊዜ Internet ተጠቃሚ ሆኖ ሌላው ቢቀር ስለ 2G , 3G , እና 4G ማያቅ ሰው ሚኖር አይመስለኝም፣ ዛሬ እነዚን በስም ብቻ ምናቃቸውን ግን አብዛኞቻችን ምን እንደሆኑ ማናውቀውን ነገር ይዤላችሁ ቀርብያለው
ከዛሬ 40 አመታት ጀምሮ 5 የተለያዩ የስልክ ኔትዎርክ Generation ኖረው ለማየት በቅተናል፣ እናም እነዚህ ኔትዎርኮች ምን እንደሆኑ እና እንዴት እንደነበሩ እንደሚከተለው ቀርቦላችዋል
1G
1G ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በ1980ዎቹ ነበር: ይህ ፈር ቀዳጅ የሆነው ኔትዎርክ Analogue Technology ነው የሚጠቀመው። ያኔ ለመጀመርያ ጊዜ ሲሰራ ለድምፅ አገልግሎት ብቻ ታስቦ ነበር የተሰራው ፣ ትልቁ እና በጣም ከፍተኛ ፍጥነቱ 2.5kbps ነበር
2G
ስልኮች ትልቅ ለውጥ ያመጡት የምንጠቀመው ኔትዎርክ ከ 1G ወደ 2G ባደግንበት ሰአት ነበር : የሁለቱ ማለትም የ 1G እና 2G ትልቁ ልዩነት ለ Radio Signal 1G Analogue ሲጠቀም 2G ደሞ Digital ነው የሚጠቀመው። ይህ በ1990ዎቹ ይፋ የሆነው ኔትዎርክ ከመጣ በዋላ ትንንሽ ዳታ የሚጠቀሙትን እንደ SMS እና MMS ተጠቃሚዎች ሆነናል : ኔትዎርካችን ከ1G ወደ 2G መቀየሩ ከያኔ ጀምሮ እዝከዛሬ ምንጠቀማቸውን እንደ call hold, Conference call, እንድንጀምር አርጎናል። ትልቁ እና በጣም ፈጣን ፍጥነቱ እስከ 64 kbps ነበር።
በመሃል 3G ከመምጣቱ በፊት እንደ 2.5G እና 2.75G ኔትዎርኮች መጥተው ነበር
3G
3G ኔትዎርክ በዚህ ሰአት ምድራችን ላይ ያሉትን ትላልቅ wireless ቴክኖሎጂዎች እንድናውቅ እና እንድንወዳቸው ምክንያት ሆኖናል : እንደ web browsing, email, video downloading......የመጡት በአብዛኛው በ smart ቀፎዎች አማካኝነት 3Gን ከተዋወቅም በዋላ ነው ፤ በ3G በጣም ብዙ በ2G ልናረግ ማንችላቸውን ነገሮች ማድረግ እንችላለን። 3G ይፋ የሆነው በ2001(g.c) ነው እናም ይህ ብዙ ነገር የቀየረው ኔትዎርክ ይፋ ከሆነ በዋላ በ ሜድያው ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገር በብዙ ቦታ ትልቅ ለዋት መለወጥ ችልዋል : 3G እስከ 2mbps ሚያህል ፍጥነት አለው።
ልክ እንደ 2G, 3G ኔትዎርክም ወደ 4G ከማደጉ በፊት ወደ በመሃል 3.5G እና 3.75G ሆኖ ነበር
4G
ልክ ከላይ ሁለቱን ኔትዎርኮች እንዳነፃፀርነው 4Gም ከ 3G በጣም ይለያል : በጣም ለየት ያለ ፍጥነት በጣም ምርጥ የሆነ ጥራት አለው : በ4G ማይቻል ነገር የለም ።
ለ4G ከፍተኛ ፍጥነት ምንጠቀምበት ነገር እይተንቀሳቀሰ ከሆነ እስከ 100mbps ሲሆን ብዙም ሳንንቀሳቀስ ደግም እስከ 1Gbps ሊደርስ ይችላል
5G
5G በዚህ ሰአት በጣም ፈጣኑ እና በጥራት ማንም ማይወዳደረው ኔትዎርክ ነው : 5G ከ 4G እስከ 35 እጥፍ ፍጥነት አለው ያም ማለት 35Gbps ማለት ነው እንግዲ!
👋ሰላም ሰላም ዛሬ ምናውራው ስለ facebook🔵ነው ቁም ነገር ትይዙበታላችሁ አስባላው።

🔵ፌስቡክ🔵

🔵ፌስቡክ በመጀመሪያ ለኮሌጅ ተማሪዎች የተሰራ የማህበራዊ ትስስር ድር ጣቢያ ሲሆን አሁን ግን እድሜው ከ 13 ዓመትና ከዛ በላይ ለሆኑ ለማንም ክፍት ነው ፡፡

🔵የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን መገለጫዎች በፎቶዎች ፣ በቪዲዮዎች እና ስለራሳቸው መረጃ በመፍጠር የራሳቸውን መገለጫዎች መፍጠር እና ማበጀት ይችላሉ ፡፡

🔵ጓደኞች የሌሎችን ጓደኞች መገለጫዎች ማሰስ እና በገጾቻቸው ላይ መልዕክቶችን መጻፍ ይችላሉ ፡፡

🔵እያንዳንዱ የፌስቡክ መገለጫ ጓደኞቹ አስተያየቶችን የሚለጥፉበት “ግድግዳ” አለው ፡፡ ግድግዳው በሁሉም የተጠቃሚ ጓደኞች ሊታይ የሚችል በመሆኑ የግድግዳ ወረቀቶች በመሠረቱ የህዝብ ውይይት ናቸው ፡፡

🔵ስለዚህ ፣ በጓደኞችዎ ግድግዳ ላይ የግል መልዕክቶችን ላለመጻፍ አብዛኛውን ጊዜ ተመራጭ ነው ፡፡ በምትኩ ፣ አንድ ሰው ከኢሜል መልእክት ጋር በሚመሳሰል የግል ኢንቦክስ ውስጥ የሚመጣውን የግል መልእክት መላክ ይችላሉ ፡፡

🔵ፌስቡክ እያንዳንዱ ተጠቃሚ የግላዊነት ቅንጅቶችን እንዲያስተካክል ይፈቅድለታል ፣ ይህም በነባሪነት በጣም ጥብቅ ነው። ለምሳሌ አንድ የተወሰነ ሰው እንደ ጓደኛ ካልጨመሩ ያ ሰው መገለጫዎን ማየት አይችልም ፡፡

🔵ሆኖም ፣ በአውታረ መረብዎ ውስጥ ያሉ ተጠቃሚዎች (እንደ ኮሌጅዎ ወይም እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢ ያሉ) ተጠቃሚዎች የመገለጫዎን በከፊል ወይም በሙሉ እንዲመለከቱ ለማስቻል የግላዊነት ቅንብሮችን ማስተካከል ይችላሉ ፡፡

🔵እንዲሁም ከመረጥካቸው የተጠቃሚዎች ዝርዝር የተወሰኑ የመገለጫዎ ክፍሎችን ለመደበቅ የሚያስችሎት ‹ውስን መገለጫ› መፍጠር ይችላሉ ፡፡

የተወሰኑ ጓደኞች ሙሉ መገለጫዎን እንዲመለከቱ የማይፈልጉ ከሆኑ ወደ “ውስን መገለጫዎ” ዝርዝር ውስጥ ሊያክሏቸው ይችላሉ።

🔵ሌላው ከማይስፔስ ለየት የሚያደርገው የፌስቡክ ገፅታ መተግበሪያዎችን በመገለጫዎ ላይ የማከል ችሎታ ነው ፡፡ የፌስቡክ አፕሊኬሽኖች በተለይ ለፌስቡክ መገለጫዎች የተዘጋጁ ትናንሽ ፕሮግራሞች ናቸው ፡፡

🔵አንዳንድ ምሳሌዎች ሱፐር ፖክን (የፌስቡክ “ፖክ” ተግባርን የሚያራዝም) እና ፉንዌልን (በመሰረታዊው “ግድግዳ” ባህሪ ላይ የሚገነባውን) ያካትታሉ ፡፡ ሌሎች ትግበራዎች እንደ ዜና ምግቦች እና የአየር ሁኔታ ትንበያዎች ያሉ መረጃ ሰጭዎች ናቸው ፡፡

🔵እንዲሁም ተጠቃሚዎች በመገለጫዎቻቸው ውስጥ እንደ ጄትማን ወይም ቴትሪስ ያሉ አነስተኛ የቪዲዮ ጨዋታዎችን እንዲጫወቱ የሚያስችሏቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የቪዲዮ ጨዋታ መተግበሪያዎች አሉ ፡፡

🔵አብዛኛዎቹ የጨዋታ መተግበሪያዎች ከፍተኛ ውጤቶችን ስለሚቆጥቡ ጓደኞች እርስ በእርስ ወይም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን ሊወዳደሩ ይችላሉ ፡፡

🔵ፌስቡክ ለጓደኞች መገናኘት እንዲችሉ እና ድር ጣቢያ መገንባት ሳያስፈልጋቸው ግለሰቦች በድር ላይ መኖር እንዲችሉ ቀላል መንገድን ይሰጣል ፡፡

🔵ፌስቡክ ስዕሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመስቀል ቀላል ስለሚያደርገው ማንኛውም ሰው የመልቲሚዲያ መገለጫ ማተም ይችላል ማለት ይቻላል ፡፡

💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ 👥
በዌብሳት አድራሻየ በመግባት ጥሩ ጥሩ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ!
በተለይ ለተመራቂ የITና ተያያዥ ለማስተርስና ለመጀመሪያ ድግሪ የሪሰርች መረጃዊችን ማግኜት ይቻላል።
www.mameamin.6te.net
ወይም ቴሌግራም ቻናሌ ላይ በመግባት የዌብሳቴን App በማውረድ በስልካችሁ ጭናችሁ መጠቀም ትችላላችሁ!
ከላይ ያለውን 👆👆👆 MuhammedAminWebsite_1_1.0 የሚለውን አፕሊኬሽን በማውረድ መጠቀም ይቻላል
ተከቴሌግራምራም አካዉንታችሁ ማወቅ ያለባችሁ በጣም ጠቃሚ ነገሮች።
=============================================

️በማታዉቁት🤔 ስልክ ቁጥር ሁል ጊዜ እየተደወላችሁ ተቸግራችሗል?
ስልኬን ከየት አገኘኸው/ሽዉ ስትሉ ቸግራቹሃል ስለዚህ ስልካችሁን ቴሌግራም #Setting ላይ በመግባት ማስተካከል አለባችሁ።

ለማስተካከል
👇👇
1⃣ ቴሌግራም አካዉንታችሁ ላይ ይግቡ እና #Settings የሚለዉን ይምረጡ

2⃣ # Privacy and security የሚለዉን ይምረጡ

3⃣ Phone Number የሚለዉን ይምረጡ

4⃣ Who can see my phone number የሚል ይመጣል።

✅ከዛ ስር Everybody,My Contacts, Nobody የሚል አማራጭ ሲመጣ ስልኮን ስልካችሁ ላይ ያሉት ኮንታክቶች #Contacts እንዲያገኙት ከፈለጋችሁ My Contact የሚለዉን ይምረጡ።

✅ስልክ ቁጥራችሁን ማንም እንዳያገኘዉ ከፈለጋችሁ Nobody የሚለዉን ይምረጡ።

✅ስልክ ቁጥራችሁን ሁሉም ቴሌግራም ተጠቃሚ እንዲያየዉ Every Body የሚለዉን ይምረጡ።

✅እዛዉ Privacy and Security Setting ዉስጥ ሆናችሁ ብዙ ነገር ማስተካከል ትችላላችሁ።
✳️አንድሮይድ ስልካችንን እንዴት በ #Xender ተጠቅመን ከላፕቶፓችን💻 (ኮምፒውተራችን) ጋር ማገናኘት እንችላለን?

1️⃣. Update የሆንዉን #Xender ስልካችን📲 ላይ እንጭናለን።

2️⃣ #Xender እንከፍታለን።

3️⃣ Connect to PC የሚለዉን እንጫናለን።

4️⃣ WI-Fi Hotspot የሚለዉን እንጫናለን።

5️⃣ ወደላፕቶፓችን እንሄድና WI-Fi ከፍተን ስልካችን📲 ላይ በሚነግረን አድራሻ አይተን #Connect እንላለን Xender_AP6911 ሌላም ሊሆን ይችላል።

6️⃣ #Connect መሆኑን ከረጋገጥን በሁዋላ ማንኛዉንም ኢንተርኔት🌐 የምንጠቀምበተን ብሮውዘር ከፍተን ስልካችን📲 ላይ የሚያሳየንን አይፒ “ http://192.168.43.1:33455/ ” አስገብተን Connect እንላለን / #ሌላም IP ሊሆን ይችላል /

7️⃣ ስልካችን ላይ #Accpet እንላለን አበቃ። ከዛማ ላፐቶፓችን💻 ላይ ከስልካችን📲 ላይ ያሉን መተግበሪያዎች ጨምሮ ሁሉንም ፋይሎችን እንደ ፎቶ ቪዲዮ ልክ ኢንተርኔት እምንጠቀም እስኪመስለን እናገኛቸዋለን፡፡ ከፈለግን ላፐቶፓችን ላይ #Backup መውሰድ ፡ ኮፒ ማድረግ ወደስልካችን መጫን….

‼️ማሳሰቢያ ፡- ይህን ስንሰራ ሞባይል📱 ዳታ #መዝጋት ይኖርብናል ፡ አለበለዚያ ወደ ላፕቶፓችን💻 ሼር ስለሚሆን ካርድ ይበላናል፡፡
📌ስለ Android
🔺Android ማለት በሰውየው ስም የተሰየመ OS ሲሆን በአሁን ሰዓት በጣም ምርጥና ተወዳጅ የOS/Operating System አይነት ነው!
📌ይህንን ሲስተም ከሚጠቀሙ ታዋቂ ስልኮች በጥቂቱ
◽️Samsung
◽️Huawei
◽️Nokia
◽️LG
◽️Sony
◽️Xiaomi
◽️One Plus
◽️Google Pixel
◽️HTC
◽️ZTE
◽️Asus
◽️Accer
◽️Oppo
◽️Doro
◽️Alcatel
◽️Tecno
◽️itel
◽️infinix
◽️Vodafone ... ወዘተ

🔺የስልካችሁን ሶፍትዌር Version ለማረጋገጥ
Setting >> About device >> Android Version ላይ በመግባት ማየት ትችላላችሁ
ከዚህ በታች የስልካችን OS ከመጀመሪያው ጀምሮ እስካሁን ያለውን በቅደም ተከተል አስቀምጠናል
🔺1 : Alpha
🔺2008
🔺Version : android 1.0
🔺2 : Beta
🔺2009
🔺Version : android 1.1
🔺3 : Cup Cake
🔺2009
🔺Version : android 1.4
🔺4 : Donut
🔺2009
🔺Version : android 1.6
🔺5 : Éclair
🔺2009
🔺Version : android 2.0/2.1
🔺6 : Froyo
🔺2010
🔺Version : Android 2.2/2.2.3
🔺7 : Gingerbread
🔺2010
🔺Version : Android 2.3/2.3.7
🔺8 : Honeycomb
🔺2011
🔺Version : Android 3.0/3.2
🔺9 : Icecream Sanwich
🔺2011
🔺Version : Android 4.0
🔺10 : Jellybean
🔺2012
🔺Version : Android 4.1
🔺11 : Kitkat
🔺2013
🔺Version : Android 4.4
🔺12 : Lollipop
🔺2014
🔺Version: Android 5.0
🔺13 : Marshmallow
🔺2015
🔺Version : Android 5.0
🔺14 : Nougat
🔺2016
🔺Version : Android 7.0
🔺15 : Oreo
🔺2018
🔺Version : Android 8.1
🔺16 : Pie
🔺2018
🔺Version : Android 9.0
🔺17 : Queen Cake
🔺2019
🔺Version : Android 10
📝 NOTE
◽️️የስልካችን Version በጨመረ ቁጥር በጣም አዳዲስ App አና GAME የመጠቀም እድላችን የሰፋ ነው!
◽️️ከነዚህ ውስጥ በአሁን ሰዓት አሪፍ የሚባሉት ከ5.0 በላይ ያሉት ናቸው!
◽️️ከሶስተኛው ስሪት ጀምሮ ያሉት ስሞች በጣፋጭ ምግቦች ስም የተሰየሙ ናቸው!
◽️️ሌላው የሚገርመው ነገር ከ1 ጀምሮ ያሉት በአልፋቤት ቅደም ተከተል ነው የተሰየሙት A-B-C-D-E-F-G-H-I-J-K-L-M-N-O-P-Q...
◽️️ከአሁን በኋላ በR የሚጀምር Version እንደሚሰሩለት ማወቅ አያዳግትም!
🔺SHARE - JOIN🔺
ስለ ስልካችሁ ሙሉ መረጃ ማወቅ ከፈለግችሁ ከላይ ያለውን app በማወረድ ማወቅ ትችላላችሁ Phone Info 3.6.8 👆👆👆
እርካሽ የኢንተርኔት አገልግሎት የት ነው የሚገኘው?
በህንድ የኢንተርኔት አገልግሎት ዋጋ ለምን ዝቅተኛ ሆነ?
ለአንድ ጊጋ ባይት (GB) የብሮድ ባንደ ኢንተርኔት አገልግሎት አሜሪካ በወር 12.37 ዶላር ታስከፍላለች፣ እንግሊዝ ደግሞ 6.6 ዶላር የምታስከፍል ሲሆን የዓለም ሀገራት አጠቃላይ አማካይ ዋጋ ሲታይ ደግሞ ለአንድ ጊጋ ባይት ብሮድባንድ አማካይ ዋጋ 8.53 ዶላር ነው።
ነገር ግን ከዚህ አንጻር ሲታይ ህንድ ምንም አታስከፍልም ማለት ይቻላል። ህንድ ለአንድ ጊጋ ባይት የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት የምትተጠይቀው ክፍያ 0.26 ዶላር ብቻ ነው። እንደዚያም ሆኖ ደግሞ በርካታ ህንዳውያን ከ 0.10 ያነሰ ክፍያን እንደሚፈጽሙ ይናገራሉ።
ጂዮ የተባለው የቴሌኮም ኩባንያ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 280 ተጠቃሚዎችን በማፍራት የህንድ ሦስተኛው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሆኗል። በ21 ዶላር የሚሸጥና በወርሃዊ ክፍያ እስከ 1 ዶላር እየከፈሉ 4G ኔተዎርክ ያለው ስልክ ያለቅድመ ክፍያ ያከፋፍላል።
ይህም ተመራጭ ካደረጉት ምክኒያቶች አንዱ ነው። እስከ ታህሳስ ወር ድረስ በነበረ መረጃ በህንድ ዋጋው ርካሽ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሞባይል ብሮድባንድ ተጠቃሚዎች ቁጥር 500 ሚሊዮን ደረሷል። ባለ ገመድ ብሮድ ባንድ ተጠቃሚዎች በአንጻሩ ወደ 18 ሚሊዮን ዝቅ ብለዋል።
ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ የጂዮ አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው። በሌላ በኩል ካሊባዳ ሳስማለ የተሰኘው ኩባንያ 40 ጊጋ ባይት ከ6 ዶላር ባነሰ ዋጋ ለመሸጥ እና ጥቅም ላይ ያልዋለ ኢንተርኔት ጥቅል ግዥ ለሚቀጥለው ስድስት ወር እንዲራዘምና ከአማዞን ነጻ ቪዲዮ የሚያዩበትን አሰራር እየዘረጋ ነው።
ተንታኞች እንደሚሉት ይህን ያክል ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያ እንዲኖር ያደረገው የጂዮ ቴሌኮም መምጣት ነው።ምክንያቱም ጂዮ ደንበኞችን ለመያዝና ተፎካካሪዎችን ከገበያ ለማሰወጣት ያደረገው ነው ይላሉ።
ጂዮ ከ2 ዓመት በፊት ሲመጣ በህንድ 10 የቴሌኮም ኩባንያዎች ነበሩ። አሁን ግን ሌሎቹ በገበያ እየተሸነፉ ወጥተው አራት ብቻ ቀርተዋል። የቴሌኮም ኩባንያዎች በኔትወርክ ዝርጋታ ካልተሳተፉና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እስካላመጡ ድረስ ዋጋው በዚሁ ሊቀጥል እንደሚችል መንግሥት ተናግሯል።
የጂዮ ቴሌኮም መምጣት በህንድ የተጠቃሚዎቹን አቅም በ10 እጥፍ አሳድጓል። በግለሰብ ደረጃ እስከ 10 ጊጋባይት በአማካይ የሚጠቀሙ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል። ይህ ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ነጻ የድምጽ ጥሪን ጨምሮ የቅድመ ክፍያ አገልግሎትም ስላለው በርካታ ህንዳዊያን እንደአማራጭ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ውስጥ ተጨማሪ የጂዮ ሲም ካርድን ይይዛሉ።
የክፍያው ሁኔታም በዚህ ምክንያት ይጨምራል፤ የለም አይጨምርም እያሉ የተለያዩ ሃሳቦችን በማንሳት ባለሙያዎች ትንታኔያቸውን ያስቀምጣሉ። ህንዳዊያን ግን ቀጣዩ ጊዜ ምንም ይሁን ምንም ከሁለት ዓመታት ወዲህ ነጻ በሚያስብል ደረጃ የዓለማችንን ባለ ዝቅተኛ ክፍያ የኢንተርኔት አገልግሎት እየተጠቀሙ ነው።
በህንድ 1 ነጥብ 17 ቢሊዮን የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ሲኖሩ ከ55 በመቶ በላይ የሚሆኑት በከተሞች የሚኖሩ ናቸው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
አንዳንድ የኮምፒውተር ክፍሎች ማብራሪያ
1. #RAM (Random Access Memory)
ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል::
(1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB በላይ ራም ይኖራቸዋል::
:
2. #ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot)
ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን::
:
3. #Heat_sinker
ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም
#Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ #CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል::
:
4.#Fan
ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው::
#CPU ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን::
:
#CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው::ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው::
#CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም
:
1. #Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው::
:
2. #Arthmatic and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል::
:
3. #Regster
ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው::ይሂም
#Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው::
#Port (ፓርት)
:
port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው:: መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ::
የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ # ኤሌክትሪክ # ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው::
#Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል)
power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው:: የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል::
#ሞደም (Modem):-ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው::
:
#ኪቦርድ Keybord:-መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት.ቁጥሮች.ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን::
ስለ አማዞን ይህንን ያውቁ ኑሯል?!??
• አማዞን የአለማችን ትልቁ ደን ሲሆን 40 በመቶ በሚሆኑት የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ላይ አርፏል፡፡
•ጥቅጥቅ ደኑ 9 ሃገራት ላይ የሚያርፍ ሲሆን 2/3ተኛው ወይም 60 በመቶው የአማዞን ክፍል የሚገኘው ብራዚል ነው፡፡
•ስፋቱ የህንድን ሁለት እጥፍ ያክላል፡፡
•አማዞን ሃገር ቢሆን ኖሮ የአለማችን 9ኛው ትልቁ ሃገር ይሆን ነበር፡፡
•በደኑ ውስጥ ከ30ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይኖራሉ ከነዚህ ውስጥ የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ እና 2ሺህ አባላት ያላቸው 350 ነባር ጎሳዎች ይገኙበታል፡፡
•ከ350 ነባር ጎሳዎች መካከል 100 ጎሳዎች እርስ በእርስ ተገናኝተው አያውቁም፡፡
•አማዞን በአለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አጥቢ አንስሳት፤አዕዋፋት እና በደረት የሚሳቡ ፍጡራን የሚገኙበት ደን ነው፡፡
•በየሁለት ቀናት ልዩነት አዳዲስ የእጽዋት ወይም የእንስሳት ዝርያዎች በአማዞን ይፈጠራሉ፡፡
•40 ሺህ የእጽዋት እና 1300 የአዕዋፍ ዝርያዎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡
•በጥቅጥቅ ደኑ 400 ቢሊዮን ዛፎች ይገኛሉ፡፡
•የአለማችን 20 በመቶ ኦክስጅን የሚመረተው በአማዞን ደን በመሆኑ “የፕላኔታችን ሳንባ ” በመባልም ይታወቃል፡፡
•አማዞን ከ90 እስከ 140 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ካርቦን በውስጡ በመያዝ የካርቦን ልቀቱን ይቆጣጠራል፡፡
•80 በመቶ የአላማችን ምግብ በአማዞን የበቀለ ነው፡፡
•120 የሚጠጉ የመድሃኒት አይነቶች የሚገኙት ከዚሁ ደን ነው፡፡
•አናኮንዳን የመሳሰሉ አደገኛ የእንስሳት ዝርያዎች የሚገኙት እዚሁ አማዞን ጫካ ውስጥ ነው፡፡
•ደኑ ጥቅጥቅ ያለ በመሆኑ እጽዋቱ ጸሃይ የሚያገኙት ከ2 እስከ 5 በመቶ ብቻ ነው ፡፡
ምንጭ፡ ሲ ኤን ኤን እና የተለያዩ ድረ ገጾች
SD ፣ HD ፣ 4K እና 8K ምንድን ናቸው?
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የቴክኖሎጅ ርቀት እና ምጥቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን በተለይ ከእይታ(ምስል) ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች ደግሞ ለማመን የሚከብዱ ተአምራት እየሆኑ መጥተዋል ።
የምስል ጥራት በፒክስል የሚለካ ሲሆን በ3 ዋና ዋና ደረጃዎች ይከፈላል።

እነሱም፦
➀ SD [standard_definition]-መደበኛ ጥራት
➁ HD [High definition] - ከፍተኛ ጥራት
➂ UHD [Ultra high definition ]- ከመጠን ያለፈ ጥራት ናቸው።

ፒክስል ስንል አንድን ምስል ለመስራት የሚያስችል ትንሿ ነጥብ(ስኩዌር ◾)ማለታችን ነው።
የፒክስሎች ስብስብ ሪዞሉሽን ሊሰኝ ይችላል።

ለምሳሌ ፦ ከአንድ ምስል ላይ አንድ ስኩየር (ልክ ኬሚስትሪ ላይ atom እንደምንለው) ወስደን ብንመለከት የወርድ ነጥቦች ስብስብ ብዛት × የቁመት ነጥቦች ስብስብ ብዛት ፒክስል ይባላል ማለት ነው ።

🔴720 × 480 pi ሲባል
720=የወርድ(w)ነጥቦች ብዛት እና
480= ቁመት(h) ነጥቦች ብዛት በአንድ ሊከፈል በማይችል ስኩዌር ውስጥ ማለታችን ነው ። ፒክስል በበዛ ቁጥር ጥራት ይጨምራል። በሌላ በኩል የምስሉ MB ም ይጨምራል ።

በየዘመናቱ የመጡ የምስል ጥራት እድገትን ብንመለከት ከመጀመሪያው እስከ አሁን ድረስ የሚከተሉትን ይመስላል።

✔SD= 720 × 480
◾PAL= 768 × 576
◾NTSC= 720 × 534 (የድሮ ሪሲቨሮች)
✔HD= 2K
◾HD = 1280 × 720
◾Full HD =1920 x 1080
✔UHD=
◾4K= 3840 × 2160 (16:9 YouTube size)
◾5K= 5120 × 2700
◾6K = 6144 × 3160
◾8K = 7680 × 4320 አሁን የደረስንበት የመጨረሻው ቴክኖሎጅ።

ሀገራችን ላይ በስፋት በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው ሰው ቤት የሚገኘው Full HD እና 4K ሪሲቨር ሲሆን አልፎ አልፎ 8Kም ይኖራል። ነገር ግን እዚ ላይ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ቢኖር ባለ 8K ቻናልን ለመመልከት ሪሲቨራችን እንዲሁም ቲቪያችን የግዴታ 8K ሊሆን ይገባል። አለበለዚያ የቻናሉ ጥራት ምን ያህል እንደሆነ ለመለየት እንቸገራለን ። ያ ማለት HD ቻናሎችን በAV ኬብል እንደመመልከት ይሆናል ማለት ነው።
የቴሌግራም ቻናሌ 👇
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
com.webdevelopment.apk
4.8 MB
👆ምርጥ አፕሊኬሽ ነው ብዙ ፕሮግራም ላንጉጅን የያዘች app አውርዳችሁ በስልካችሁ በመጫን ተጠቀሙ፣ እወቁ፣ ተለወጡ።