Muhammed Computer Technology (MCT)
38.4K subscribers
496 photos
7 videos
217 files
839 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ስለጓግል(Google) ምን ያህል የዉቃሉ።
✅ከጉግል በፊት ሕይወት ምን ትመስል ነበር?
✅ አንድ መረጃ በፍጥነት ሲፈልጉ ምን ያደርጉ እንደነበር ያስታውሱታል?
✅ ምንም ይፈልጉ ምን፤ የአንድን ቃል ትርጓሜ እና አፃፃፍም ይሁን የቦታ ጥቆማ፤ ብቻ የሆነ ነገር ሲፈልጉ ወደ ጉግል መሮጥ የተለመደ ሆኗል። 'ዕድሜ ይስጠውና' ጉግል ፊት ነስቶን አያውቅም፤ 'ጎግለው' እንዲል የሃገሬ ሰው።
✅ በየሰከንዱ ይላል ፎርብስ የተሰኘው መፅሄት መረጃ. . .በየሰከንዱ 40 ሺህ ሰዎች 'ይጎግላሉ'፤ በቀን 3.5 ቢሊዮን እንደማለት ነው።
✅ ጉግል ሁሉ ነገር ሆኗል፤ ማስታወቂያ በሉት፣ የቢዝነስ ዕቅድ እንዲሁም ግላዊ መረጃ መሰብሰቢያ ነው።
✅ እንግዲህ እውነታውን ልናፈራርጠውም አይደል፤ እናማ ስለጉግል አንድ ሚስጢር እንንገርዎት።
መረጃ ፍለጋ ወደ ጉግል በሮጡ ቁጥር ጉግል ስለእርስዎ የተወሰነ መረጃ ይሰበስባል።
✅«ግን ምን ያህል መረጃ?» አሉን?፤ መልካም! እነሆ የጠየቁንን ጨምሮ ስለጉግል ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች።
1⃣ ስያሜው ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።
በእንግሊዝኛው 'googol' ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።
እና ከተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።
2⃣ የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው 'Backrub' ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።
ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ።
ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።
3⃣ የተንጋደደ ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።
እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።
ውጤቱ አዩት?
4⃣ ፍየሎች ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው።
አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ።
ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።
5⃣ እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'
ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።
ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።
6⃣ ዱድል
ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።
ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።
አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።
7⃣. ለሌሎች ያመለጠ ዕድል
በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።
ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።
አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።
8⃣. መሪ ቃላት
'ከይሲ አይሁኑ' ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።
'ምን አገባው' የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።
9⃣. ምግብማ ግድ ነው
ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።
9⃣ የጉግል ባልንጀራ
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ስለ ቴክኖሎጅ የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት በዚህ
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ቻናላችንን ይቀላቀሉ 🙏🙏🙏
ላፕቶፕ ሲገዙ ማገናዘብ ያለብዎ አጭር አስፈላጊ ነገሮች⤵
1.➡ምን ሊሰሩበት አስበዋል?
✔ ብዙ ሚፅፉ ከሆነ ኪቦርዱን ማየት ይገባል
✔ ጌም ሚያበዙ ከሆነ ግራፊክስ ካርዱንና ስፒከሩን
ይመልከቱ
✔ለቪዲዮ ቅንብር (editing or software Engineering) ከሆነ ከፍተኛ የፕሮሰሰር አቅም ፣ ትልቅ ሳይዝ ራም high definition (HD) ስክሪን
መኖሩን ያረጋግጡ
2 ➡አዲስ ከካምፓኒው እንደመጣ ( brand new ) ነው
ወይም በብልሽት ምክንያት ተመልሶ ካምፓኒው
ገብቶ የተሰራ (Refurbished ) መሆኑን ያረጋግጡ
3.➡የስክሪን ወይም የዲስፕለይ መጠን: ለርሶ ትክክለኛዉን የስክሪን መጠን ይምረጡ
(13.3” ,15.6”,17.3”)
4.➡የላፕቶፑን ስፔሲፊኬሽን በጥልቀት ይመርምሩ
✔ፕሮሰሰር (intel core 2 dou, core i3, core i5,
core i7 or AMD and others)
✔ራም (ስንት እንደሆነ 1GB,2GB,3GB,4GB , 8G and above)
✔ ሀርድ ዲስክ (160 GB, 250GB, 320GB,500GB, 750GB and above)
✔ዲቪዲ ወይም ብሉሬይ ድራይቭ ( re-writable )
5.➡ባትሪ ይህ በጣም ወሳኝ ነው ። ሊደራደሩበት
አይገባም! ቢያንስ 3 ሰአት እና ከዛ በላይ ቢሆን አሪፍ ነው
6.➡የሚፈልጉት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይምረጡ:
ማክሮሶት ዊንዶውስ (windows 7, windows
8,windows10) , mac, Ubuntu,Linux ወዘተ
በዚህ ሰአት ማይክሮሶፍት ዊንዶወስ 7 እና 8 ማቅረብ አቁሙዋል so ዊንዶውስ 10 ቢመርጡ ይመከራል!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👌 በOpera mini ላይ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ኮኔክሽኑ በጣም
ቀርፋፋ ሆኖ ከተቸገሩ መፍትሄ ዛሬ ይዤ ቀርብያለው .... 👇
የተጠቀሱትን 9 እስቴፓችን በመከተል ችግሩን መቅረፍ ይችላሉ።
step1. በመጀመሪያ Opera miniውን ይክፈቱ።
step2. በመቀጠልም Address Bar ውስጥ ገብተው www.
የሚለውን ያጥፉ።
step3. ከዛም Address Bar ውስጥ opera:config ብለው ይፃፉ።
step4. ከዛም Power Settings ይመጣሎታል።
step5. የመጀመሪያውን Option "Large placeholders for
images" የሚለውን YES ከሆነ NO አድርጉት።
step6. ከዚያም ሁለተኛውን Option "Fit text to screen" የሚለውን
YES ከነበረ NO ያድርጉት።
step7. በመቀጠልም ሶስተኛውን Option 'Loading timeout'
የሚለውን 20 ያድርጉት።
step8. ከዛም Save የሚለውን በመጫን ይጨርሱ።
step9. ከዛም Operaዎትን ዘግተው እንደገና መልሰው በመክፈት ፈጣን
የሆነውን ኢንተርኔት ይጠቀሙ።
⚠️ ከተመቾት ለወዳጆት ያጋሩ ..... ሼር
🔎 ቀልጣፋ እና ስኬታማ ከጎግል መረጃ የመፈለጊያ ስልቶች 🔍
✍ የዘወትር የመረጃ መፈለጊያ የሆነው የጎግል ፍለጋችን ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ ስልቶችን ልንጠቁማችሁ ወደናል።
1⃣. ትክክለኛውን ቃል ለመፈለግ ቃሉን በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ማስገባት ለምሳሌ፡- “Android” በማለት ጎግል ብናደርግ ከዚሁ ጉዳይ ጋር ብቻ የተገናኙ መረጃዎችን በሰፊው እናገኛለን።
2⃣. ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ድረ ገጾች ለመፈለግ
በቅርጽም ሆነ በይዘት ተቀራራቢነት ያላቸውን ድረ ገጾች ለማግኘት ወይም እንደ እከሌ አይነቱን ድረ ገጽ ፈልግልኝ ለማለት related: የሚለውን አስቀድመን የድረ ገጹን አድራሻ እናስከትላለን፤
ለምሳሌ፡- ጎግልን related:amazon.com ብለን ብንጠይቀው ከአማዞን ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ድረ ገጾች ውጤት ይሰጠናል።
3⃣. ጎግል የምንፈልገውን ብቻ እንዲፈልግልን ደግሞ ከቃላቱ በፊት የሰረዝ ምልክትን መጠቀም አለብን።
ይህም በተለይ በርካታ ትርጉም ያላቸውን ነገሮች ስንፈልግ የማንፈልገውን ለይቶ በቀላሉ የምንፈልገውን ጉዳይ ማግኘት ያስችላል።
ለምሳሌ፡- terminator –movie ብለን ብንፈልግ የፍለጋ ውጤታችን ቴርሚኔተር ላይ ብቻ ያተኮረ እና ተርሚኔተር ስለተባለው ፊልም ፈጽሞ ያላካተተ ይሆናል።
4⃣. ድረ ገጾች ስለ አንድ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የሰሩትን በቀላሉ ለመፈለግ
አንድ ደረ ገጽ ስለሆነ ነገር ከዚህ በፊት የሰራቸውን ለመመልከት የምፈልገውን ቃል ከጻፍን በኃላ ክፍት ቦታ ሰጥተን site: ብለን በመጻፍ የምንጎበኘውን ድረ ገጽ አድራሻ በማስከተል መፈለግ፤
ለምሳሌ፡- barrack obama. Site: bbc.com ብለን ብንፈልግ ቢቢሲ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን በተመለከተ በድረ ገጹ ላይ ያወጣቸውን ዘገባዎች ለመመልከት እንችላለን።
5⃣. ትርጓሜዎችን ለመፈለግ
የፊደላትን ትርጓሜ ለማወቅ እና ተመሳሳይ ፍቺዎችን ለመፈለግ define: አስቀድመን ቃሉን መጻፍና መፈለግ የተሻለ ውጤት ያስገኝልናል።
ለምሳሌ፡- define:injera ብለን ጎግል ላይ ብንፈልግ ሰለ እንጀራ ዘርዘር ያለ መረጃ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ያለውን ትርጓሜ በስፋት ማግኘት እንችላለን።
በዚህ መንገድ የአንዳንድ ቃላትን ሰያሜ መነሻ እና ትርጉም ለማግኘትም ቀላል ነው።
6⃣. የተለያዩ የፋይል አይነቶችን ለማሰስ
ጎግል የፒዲኤፍ አልያም ፓወር ፖይንት ውጤቶችን እንዲሰጠን ለመጠየቅ የሚከተለውን አማራጭ እንጠቀማለን።
ለምሳሌ፡- “Scientific Journalism” filetype:pdf
7⃣. አዲስ የሆኑ እና ትኩረት የሳቡ አለማቀፍ ጉዳዮችን ለማግኘት
ከምንፈልገው ርዕሰ ጉዳይ በፊት የሃሽታግ ምልክትን ማስቀደም፤ ለምሳሌ #action2017 ብለን በመፈለግ በርካታ መረጃዎችን ማግኘት ያስችላል።
8⃣. በጎግል ወደ ሌላ ቋንቋ ለመተርጎም
ጎግል ትራንዝሌት ቃላቶችን ብቻ ሳይሆን ዘርዘር ያሉ ጽሁፎችንም ለመተርጎም ያስችላል።
ለምሳሌ፡- hello የሚለውን ቃል ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ለመተርጎም translate english to french hello በማለት ጎግል ላይ መፈለግ እንችላለን።
9⃣. የረሳናቸውን ፊደላት ለማስታወስ
ጎግል የዘነጋናቸውን ቃላት እንዲያስታውሰን ኤስትሪክስን (*) መጠቀም እንችላለን። ኤስትሪክስን መጠቀም በተለይ የረሳናቸውን የዘፈን ግጥሞች ለማስታወስ ይረዳል።
ለምሳሌ፡- “Come * right now * me” የሚለውም የዘፈን ግጥም ጉግል ብናደርግ “Come Together” የሚል ርዕስ ያለውን የቢትልስ ሙዚቃ ግጥም ውጤቶች ይሰጠናል።
🔟. የአየር ሁኔታ መረጃ ለማግኘት ደግሞ ዌዘር የሚለውን ቃል ከከተሞቹ አስቀድመን መፈለግ
ለምሳሌ:- weather Adiss ababa
════════════════
Source information science and technology
ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች
1. የሀርድዌር መቃረን
ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡
2. የተበላሸ ራም
ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡
3. ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)
እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡
4. ቫይረስ
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡
5. መጋል
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ ያደርጋል፡፡
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጂ ለማወቅ ከፈለጉ በፌስቡክና በቴሌግራም በመቀላቀል እውቀትዎን ያሳድጉ።
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ ብልህነት ነው
የቴሌግራም ቻናል ይቀላልቀሉ
👇👇👇
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ተደጋጋሚ የሞባይል ስልክ ችግሮች እና መፍትሔዎች
⛔️ ለሌላ ሰዉ ድምጽ ይሰማል፡፡ ነገር ግን በጣም አነስተኛ ሲሆን ወይም የራቀ ድምጽ ሲሆን 909 ወይም 904 መደወል ♥ጥሪዉ ሲጀምር የድምፅ መጨመሪያ ቁልፍን በመጫን ድምጥን መጨመር ♥ችግሩ ካልተፈታ ስፒከር ቀዳዳን ማፅዳት ♥ከላይ የተገለጡት መንገዶች ካልተፈታ ስፒከሩን መቀየር ይኖርብናል፡፡
⛔️ የስልካችን ጥሪ ከተወሰኑ ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች በሆአላ ይቋረጣል፡፡ የስልካችን የጥሪ መቼት ላይ የጥሪ ገደብ /ኮል ታይም ሊሚት/Call time limit/ የሚለውን ማጥፍት በተለይ ቻይና ስልክ ላይ auto quick end የሚል መቼትን ማጥፍት፡፡
call record
General call setting
More
Auto quick -end
Off
⛔️ የቻይና ስልኮች ላይ ኪፓዱ ላይ ያለዉ ብርሀን ይታያል፣ በተጨማሪም ስክሪኑ ላይ ምስሎች ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የስክሪኑ ብርሀን የማይታይ ከሆነ
ሁሉም የቻይና ስልኮች ስክሪናቸዉ ላይ ሶስት፣ አራት ወይም አምስት የስክሪን ዳዩድ መስመሮች ይገኛሉ፡፡ እነኝህ መስመሮች ከስክሪኑ ጋር የተበየዱበት ሊድ ሊለቅ ወይም ስክሪኑ ከቦርዱ ጋር የተበየደበት ቦታ ላይ የስክሪን ብርሀን መስመሮች ተላቀዉ ከሆነ በድጋሜ ፔስትና ሊድ በመጠቀም እያንዳንዱን እግር በአግባቡ መበየድ፡፡
⛔️ Insert SIM የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ
ሲም ካርዱ የሚሰራ መሆን አለመሆኑን የሚሰራ ስልክ በመጠቀም ማየት የሲም መርገጫ ብረቱን በእጃችን መጫን ሲም ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ
⛔️ እንደ 1110,6030,2600,2610,2310,1600 ያሉ ኖኪያ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲም ተጠቅመን Insert
Sim የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ
ቻርጅ ኮኔክተሩን ማፅዳት ወይም መቀየር
ቻርጅ ኢንተርፌስ አካባቢ በቲነር ማፅዳት
⛔️ ባትሪ ሲገባበት ቫይብሬተር የሚያደርግ ከሆነ / ስልኩን ሳናበራዉ ልክ ባትሪ እንደገባበት በራሱ ቫይብሬት የሚያደርግ ከሆነ/
DCT3 ስልክ ከሆነ ዩአይ አይሲን መቀየር
ሌሎች ስልኮች ላይ ፓወር አይሲ መቀየር
⛔️ ኔት ወርክ የሌለው ስልክ አንቴና ኢንተርፌስ ወይም ከቦርዱ ጋር በአግባቡ መግጠሙን ማረጋገጥ ቦርዱን በቲነር ማጠብ አንቴና ስዊቹን ማሞቅ ኔትወርኩ አሁንም ካልተስተካከለ ደግሞ አንቴና ስዊች መቀየር
⛔️ እኔ የምናገረው ይሰማል ሌላ ሰዉ የሚናገረዉ አይሰማኝም ስፒከሩን መቀየር
⛔️ ሰዉ የሚያወራው የሚሰማ ከሆነ ነገር ግን እኛ የምናወራው የማይሰማ ከሆነ ማይኩን መቀየር
⛔️ ወጭ ጥሪ ያደርጋል ነገር ግን አይቀበልም
ኮል ዳይቨርት በርቶ ከሆነ ማጥፍት
⛔️ ከቁጥሮቹ መካከል አንዱ ብቻ ተነጥሎ የማይሰራ ከሆነ ቁጥሩ ላይ የሚያርፈዉን አልሙኒየም ማፅዳት
⛔️ ተንሸራታች ስልክ ላይ ያሉት ቁልፎች አይሰሩም ፣ከታች ያሉት ቁጥሮች በሙሉ ይሰራሉ
ኬብል መቀየር
⛔️ የምን ሰማዉ ድምጽ ይንጫጫል/ ከሌላ ሰዉ ጋር ስንነጋገር/ ስፒከር መቀየር
⛔️ ቁጥሮች መደዳ የማይሰሩ ከሆነ ኪፓድ አይሲን ምሞቅ ወይም መቀየር
⛔️ ስልኩ ክፍለሃገር ሲሄድ ኔትወርኩ አይሰራም
ኔትወርክ ፊልተሩን መቀየር
⛔️ ስልክ ስናወራ የቁልፍ መጫን ድምፅ ይሰማናል/ ሳንነካዉ በራሱ ቁጥር ይደረድራል/ ኪፓድ አይሲን መቀየር
⛔️ ኔትወርክ ሙሉ ሁኖ ልክ ስንደዉል ኔትወርኩ ዜሮ ይሆናል ፓወር አምፕሊፋየሩን ማሞቅ ወይም መቀየር
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።
🛑 መልቲ ሜትር በመጠቀም እንዴት ስልክ ላይ የሚገኙ electronic ዲቫይሶችን መለካት ይቻላል⁉️
🛑 Resistor - መልቲሜትሩን ኮንቲኒቲ ላይ ካደረግነዉ ቡሃላ ቀዪንና ነጩን ፕሮብ ሪዚስተሩ ላይ ማገናኘት ድምፅ(beep sound) ካሰማ ይሰራል
ድምፅ ካላሰማ አይሰራም።
🛑 Capacitor - ከላይ እንዳደረግነዉ እናረግና
ድምፅ ካሰማ አይሰራም ድምፅ ካላሰማ ይሰራል ።
🛑 Diode -ድምፅ ካሰማ አይሰራም ድምፅ ካላሰማ ይሰራል ።
🛑 LED - መልቲሜትራችንን buzzer mode ላይ ካደረግን ቡሃላ ledዉ መብራት ከሰጠ ይሰራል
ካልበራ ደግሞ አይሰራም።
🛑 Ringer - መልቲሜትሩን buzzer mode ላይ ካደረግን ቡሃላ መልቲሜትሩ (ከ 8-10) ካነበበ ይሰራል
መልቲሜትሩ (ከ4-5 ወይም ከ12-14)ካነበበ አይሰራም
🛑 Vibrator - ringer mode አድርገን (ከ8-16) ካነበበ ይሰራል።
🛑 Speaker(earpiece) መልቲሜትሩን buzzer mode አድርገን መልቲሜትሩ (ከ25-30) ካነበበ ይሰራል
🛑 Microphone(mic) - መልቲሜትሩን buzzer mode አድርገን መልቲሜትሩ (ከ600-1800) ካነበበ ይሰራል
🛑 Keypad - መልቲሜትሩን ኮንቲኒቲ ላይ ካደረግነዉ ቡሃላ ድምፅ(beep sound) ካሰማ ይሰራል ድምፅ ካላሰማ አይሰራም።
🛑 Battery connector - መልቲሜትሩን 20V dc ላይ ካደረግን ቡሃላ የbattery connecteru +ve እና -ve ላይ እናደርግና (ከ1.5-3.5V ) ካነበበ ይሰራል
🛑 battery - መልቲሜትሩን 20V dc ላይ ካደረግን ቡሃላ የባትሪዉ+ve እና -ve ላይ እናደርግና (3.7 በላይ) ካነበበ ይሰራል ቻርጅ ለማድረግ 3.0,3.2 እና ከዛ በላይ መሆን አለበት።
🛑 On/off switch- መልቲሜትሩን 20V dc ላይ
ቡሃላ የswitchu +ve እና -ve ላይ እናደርግና (ከ2.5-3.7) ካነበበ ይሰራል ከተመቻቹ #ሼር #ይደረግ
Via Mobile Problem Solution
ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ እንዴት ቡቴብል ወይም እንደ ሲዲ ከፍላሽ እንዲነሳ ወይም ኮምፒውተራችንን ፍላሽ በመጠቀም ፎርማት ለማድረግ የሚከተለውን ሂደት መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ለሌሎች ጓደኞቻችሁ ሼር በማድረግ አድርሷቸው፡፡
እባክዎ ከመጀመርዎ በፊት ፍላሹ ላይ ጠቃሚ ፋይል ካለዎት ወደ ሌላ ቦታ ኮፒ ያድርጉ።
በመጀመሪያ ኮምፒዩተራችን ላይ 'command prompt' ወይም 'cmd' እንከፍታለን። ( 'cmd'ን ለመክፈት በመፈለጊያችን ላይ cmd ብለን search እናደርጋለን. Cmd ሲመጣልን right click አድርገን run as administrator የሚለውን በመጫን cmdን እንከፍታለን)
Cmd ከከፈትን በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዞች በቅደም ተከተል እናስገባለን። እያንዳንዱን ትእዛዝ ከጻፍን በኋላ ENTER ቁልፍን እንጫናለን
1. DISKPART
2. LIST DISK (አሁን በኮምፒውተሩ ላይ ያሉትን ዲስኮች ይዘረዝርልናል. ለማጽዳት የፈለግነውን ፍላሽ ቁጥር ከለየን በኋላ ወደ ሶስተኛው ትእዛዝ እንሄዳለን። ምሳሌ.disk 1)
3. SELECT DISK * (በኮከቡ ፋንታ ሁለተኛው ትእዛዝ ላይ የለየነውን የፍላሽ ቁጥር እናስገባለን)
4. CLEAN (በዚህ ጊዜ ፍላሹ ላይ ያለውን ማንኛውም ነገር ያጠፋዋል)
5. CREATE PARTITION PRIMARY (ለፍላሹ ይዘት ይፈጥራል)
6. SELECT PARTITION 1
7. ACTIVE (ይህ ፍላሹን ዝግጁ ያደርገዋል)
8. FORMAT FS=ntfs (ይህ ፋላሹን በጥልቀት በመሰረዝ በውስጡ ያሉትን ማንኛውም ቫይረስ ወይም ሌላ ችግር ያጠፋል። ሂደቱ የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስድ እስከሚጨርስ በትዕግስት እንጠብቀዋለን)
9. ASSIGN (አዲስ ለፈጠርነው ፍላሽ የፊደል ስም ይሰጥልናል)
10. EXIT (ፕሮሰሱን ይጨርስልናል)
አሁን አዲሱን ፋላሻችንን መንቀልም ሆነ መጠቀም እንችላለን። ይህንን መንገድ በመጠቀም ማንኛውንም ችግር ያለበት ፍላሽ ማስተካከል እንችላለን እንዲሁም ማንኛውንም operating system copy በማድረግ ኮምፒውተራችንን ፎርማት ማድረግ እንችላለን ።
ይህ መረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ ፔጁን LIKE እና SHARE ያድርጉ።
እናመሰግናለን!!!
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።
​​✳️ የፌስቡክ አፈጣጠር ታሪክ፡

◽️ የፌስቡክ መስራች እና ባለቤት የሆነው ማርክ ዙከርበርግ ከክፍል ጓደኞቹ ኤድዋርዶ ሳቨርን ፣ ዱስቲን ሞስኮቭዝ እና ክሪስ ሂዩዝ ጋር ፌስቡክን ሲፈጥሩ ገና የሃርቨርድ ዩኒቨርስቲ የኮምፒተር ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ። በሚያስደንቅ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም ተወዳጅ የሆነው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ፌስቡክ መጀመሪያ ሲፈለሰፍ የሰወችን ፎቶ በመለጠፍ የትኛው ያምራል የሚለውን ለማወዳደር ታስቦ የተሰራ ነበር።

🔺የፌስቡክ አጀማመር

◽️ እ.ኤ.አ በ 2003 በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነው ዙከርበርግ FaceMash ለተባለ የድረገፅ እና መጠቀሚያ ሶፍትዌር ሰራ። የኮምፒተር እውቀቱንም በመጠቀም ወደ ሃርቫርድ የደህንነት አውታረመረብ (Security Network) ሰብሮ በመግባት የተማሪዎች መታወቂያ ለይ ያሉ ምስሎችን በመሰብሰብ ያለፈቃድ FaceMash ለይ መለጠፍ ቻለ። ከዚያም ይህን ዙከርበርግን ድረገፅ የሚጎበኙ ተማሪዎች ከሚመጡላቸው ጥንድ ጥንድ ፎቶዎች አንዱ ያምራል አንዱ አያምርም እያሉ እንዲመርጡ ይጠየቃሉ።

◽️ FaceMash ጥቅምት 28 ቀን 2003 ከተከፈተ ከጥቂት ቀናት በኋላ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተዘጋ። ከዚያም ዩኒቨርስቲው ዙከርበርግን የሰዎችን ደህንነት በመጣስ ፣ የቅጂ መብቶችን በመጣስ እና የግለሰቦችን ግላዊነት በመጣስ ከባድ ክሶች ከሰሰው። ዙከርበርግ በዚህ በድርጊቱ ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ መባረር ቢገጥመውም በእሱ ላይ የተጣሉ ሁሉም ክሶች በመጨረሻ ተሽረውለታል።

🔺 The Facebook፡

◽️ እ.ኤ.አ. የካቲት 4 ቀን 2004 ዙከርበርግ TheFacebook የተባለ አዲስ ድረገፅ ከፈተ። TheFacebook በሃርቫርድ በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው ይበልጥ መተዋወቅ እንዲችሉ እንዲረዳቸው ታስቦ የተሰራ ነበር። ነገር ግን ከስድስት ቀናት በኋላ የሃርቫርድ ተማሪዎች የሆኑት ካሜሮን ዊንክለቮስ ፣ ታይለር ዊንክሌቮስ እና ዲቪ ናሬንድራ ዙከርበርግ ሀሳባቸውን እንደሰረቀባቸው በመናገር ዙከርበርግን ሲሰሱት ዙከርበርግ እና The Facebook ችግር ውስጥ ገቡ። ሆኖም ግን እነዚህ የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢዎች ከዙከርበርግ ጋር ተወያይተው ጉዳዩን ከፍርድ ቤት ውጭ ፈቱት።

◽️ The Facebook በመጀመሪያ ለሃርቫርድ ተማሪዎች የተከለከለ ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ዙከርበርግ ድረገፁን ለማሳደግ እንዲረዱት ጥቂት የትምህርት ቤት ጓደኞቹን አስገባቸው። ለምሳሌ ኤድዋርዶ ሳቬሪን በቢዝነሱ ፣ ዱስቲን ሞስኮቭዝ በፕሮግራሚንግ ባለሙያነት ፣ አንድሪው ማኮሉም የጣቢያው ግራፊክ አርቲስት አንድ ላይ በመሆን ድረገፁን ወደ ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ለማስፋፋት ችለዋል።

🔺የፌስቡክ-እድገት

◽️ እ.ኤ.አ በ2004 የNapster መስራች እና ባለሀብት ሴአን ፓርከር የፌስቡክ ፕሬዝዳንት ሆነ። ኩባንያውም የድረገፁን ስም ከTheFacebook ወደ Facebook የቀየረው። በቀጣዩ ዓመት ኢንቬስት ካፒታል ኩባንያ አኬል ፓርትነርስ በፌስቡክ ላይ 12.7 ሚሊዮን ዶላር ኢንቬስት ያደረገ ሲሆን ይህም ፌስቡክን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የመገናኛ የኔትወርክ እንዲፈጠር አስችሎታል።

◽️ እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 2006 ፌስቡክ ቢያንስ 13 ዓመት የሆነ እና እውነተኛ የኢሜል አድራሻ ያለው ማንኛውም ሰው ፌስቡክ መቀላቀል እንደሚችል አስታውቋል። እ.ኤ.አ. በ2009 ፌስቡክ በዓለም ላይ በጣም ጥቅም ላይ የዋለው የማኅበራዊ የአውታረ መረብ አገልግሎት ሊሆንም ችሏል።

◽️ የፌስቡክ ትርፍ በመጨረሻ ዙከርበርግን የዓለም ወጣቱ Multi billionaire እንሆን አስችሎታል። እ.አ.አ በ2010 ዙከርበርግ ከሌሎች ሀብታም ነጋዴዎች ጋር በመተባበር ቢያንስ ግማሽ ያህሉን ሀብት ለበጎ አድራጎት ድርጅት ለመስጠት ቃል ገብቷል። ዙከርበርግ እና ባለቤቱ የኢቦላ ቫይረስን ለመዋጋት 25 ሚሊዮን ዶላር ለግሰዋል። 99% የፌስቡክ ሼር በትምህርት ፣ በጤና ፣ በሳይንሳዊ ምርምር እና በጉልበት ለማሻሻል እንደሚረዱ አስታውቀዋል።
እናመሰግናለን!!!
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።
መረጃውና ትምህርቱ እየተመቻችሁ ነው?
Anonymous Poll
97%
👍
3%
👎
​✳️ የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "Backup" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን?

◽️ በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች ለመያዝ የሚውሉ መገልገያዎችን እንጠቁምዎ:-

◽️ ፍሎፒ ዲስክ /Floppy Disk/:- ትንሽና አነስተኛ መጠን ያለው ዲስክ ሲሆን አቅሙም 1.4 MB ነው፡፡ ጠቃሚ መረጃዎችን በፍሎፒ ዲስክ ለመያዝ በርካታ ዲስኮች ያስፈልጉናል፡፡ የድሮ ኮምፒውተሮች በብዛት ፍሎፒ ዲስክ መጠቀሚያ የነበራቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚመረቱ ኮምፒውተሮች አብዛኞቹ አገልግሎቱ የላቸውም፡፡

◽️ ዚፕ ድራይቭ /Zip Drive/፡- ዚፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር MB መጠን ያላቸው ፋይሎችን /data/ የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ዚፕ ድራይቮችን ለመጠቀም የግድ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካት /hook up/ ይኖርባቸዋል፡፡

◽️ ቴፕ ድራይቭ / Tape Drive/፡- ቴፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር GB (በሺዎች የሚቆጠር MB) መጠን ያላቸው ፋይሎችን ይይዛል፡፡ ይህም ተጨማሪ ድራይቭ በመሆኑ የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት ይኖርበታል፡፡

◽️ ሲዲ በርነር /CD Burner/፡- ሪከርድ የሚያደርጉ ሲዲዎች /CD-Rs/ እስከ 700 MB የሚሆኑ ፋይሎች የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ አሁን ላይ የምንጠቀምባቸው አብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ሲዲ በርነር /CD Burner/ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹም ዲቪዲ በርነር /DVD Burners/ አላቸው፡፡ ዲቪ ዲ አር ኤስ /DVD-Rs/ እስከ 4.7 GB ፋይል የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ስለዚህ በአማራጭ የመጠባበቂያ ፋይል መያዣ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡

◽️ ፍላሽ ድራይቭ /Flash Drive/፣ የ ኤስ ቢ ድራይቭ /USB Drive/ እና ተምብ ድራይቭ /Thumb Drive/፡- ለአንድ ነገር የተለያየ ስያሜ ቢኖርም በኮምፒውተሮቻችን የዩ ኤስ ቢ /USB/ ፋይል መቀበያ በኩል በቀላሉ የሚሰኩ ተነቃይ ድራይቨሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ድራይቨሮች ከ10 MB የሚጀምሩ ሲሆን 1 GB፣ 2 GB፣ 4 GB፣ 8 GB፣ 16 GB፣ 32 GB፣ 64 GB … እያሉ አሁን ላይ 4TB ፋይል የመያዝ አቅም ያላቸው ፍላሽ ድራይቮች በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍላሽ ዲስኮች በቀላሉ በኪስ የሚያዙና ተንቀሳቃሽ ቢሆኑም በቀላሉ ወድቀው ሊጠፉ የሚችሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡

◽️ ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ /External hard Drive/:- ኤክስተርናል ሀርድ ድርይቭ በኮምፒውተር ሲስተሞቻችን ውጪ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ፋይሎችን የምናስቀምጥበት መሣሪያ ነው፡፡ ይህ መሣሪያ /Drive/ ፋይሎችን ይዞ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል እና ከኮምፒውተራችን ጋር በዩ ኤስ ቢ /USB/፣ በፋየርዋየር /Firewire/ ኮኔክሽን ወይም በገመድ አልባ /wirelesely/ ሊገናኝ የሚችል ነው፡፡

◽️ ታይም ማሽን /Time Machine/፡- Time Mac ለተጠቃሚዎች አማራጭ የኤክስተርናል ፋይል መጠባበቂያ መያዣ መንገድ ነው፡፡ ይህ መጠባበቂያ መያዣ ዘዴ ለ24 ሰዓት በቀጥታ ፋይሎቻችንን ለማስቀመጥ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ፋይሎች ተረስተው ለጉዳት እንዳይጋለጡ ያግዛል፡፡ ታይም ማሽን በመጠባበቂያው የሚይዘው የተመረጡ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ድራይቨሩን ነው፡፡

◽️ ኔትወርክድ የሆነ የመረጃ ማካማቻ /Networked Attached Storage/:- ይህ ከአንድ በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮች በኔትወርክ ተገናኝተው መረጃ የሚቀመጥበት ሥርዓት ሲሆን ይህም በስርዓት የተደረደሩ፣ ያልተደጋገሙ የፋይል ማከማቻ ኮኒቲነሮችን እና በርካታ የዲስክ ድራይቭ አካላትን የያዘ ነው፡፡ ይህም በፍጥነት መረጃ ለማግኘት፣ በቀላሉ መረጃዎችን ለማስተዳደርና ለማስተካከል የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡

◽️ ስውር የበይነ መረብ መረጃ ማከማቻ /Cloud Storage/:- ይህ የፋይል ማከማቻ ዓለም አቀፍ የመረጃ ማከማቻ ሥርዓት ሲሆን በኔትወርክ አማካኝነት በመገናኘት መረጃዎቻችን ክላውድ ተብሎ በሚጠራ የመረጃ መጠባበቂያ ሥርዓት /Cloud Server/ ውስጥ የምናስቀምጥበት መንገድ ነው፡፡ በርካታ የክላውድ ማማቻ ዓይነቶች በበየነ-መረብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እነዚህም በነጻ ወይም በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ iCloud፣ Dropbox፣ Google Drive እና OneDrive የታወቁ የመረጃ ማከማቻ መንገዶች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ የሚከማቹበት ሥፋራ በመራጃ በለቤቶቹ ቁጥጥር ሥር ባለመሆኑ የመረጃዎቹ ደህንነት አስተማማኝ እንደስጋት ይታያል፡፡

◽️ ፕሪንት ማድረግ /Printing/:- ምንም አንኳን መረጃዎቻችን በሶፍት ኮፒ የምናስቀምጠውን የህል የተማቹ ባይሆኑ ኮምፒውተሮቻችን በተለያየ ምክንያት ለቀናት አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙበት አጋጣሚ ቢፈጠር ፕሪንት ያደረግናቸው ፋይሎች እጅጉን ይጠቅሙናል፡፡
​​​​✳️ Arduino Programming
◽️ Banzi በ2005 (እ.ፈ.አ) የተጀመረው Arduino (ሲነበብ አርድዊኖ) የኤሌክትሮኒክስ ፕሮጀክቶች ለመስራት የምንገለገልበት የቴክኖሎጂ ውጤት ነው!

◽️ አርድዊኖ ፕሮግራማብል (Program ከጻፍን በኋላ ምንጭንበት) ሰርኪውት ቦርድና (Circuit Board) IDE (Integrated Development Environment, ኮድ ወይም ፕሮግራም ምንጽፍበት ሶፍትዌር) ያካትታል!

◽️ C/C++ የፕሮግራም መጻፍያ ቋንቋ (programming language) ላይብረሪዎች በመጠቀም ስራውን ሚከውነው አርድዊኖ, ኮምፒተራችንን በመጠቀም IDEው ላይ የጻፍነውን ኮድ በUSB ኬብል በመጠቀም ሰርኲት ቦርዱ ላይ መጫን ይኖርብናል!

◽️ የአርድዊኖ ቦርድ ማይክሮኮንትሮለር (microcontrollers) ስር የሚካተት ሲሆን ከማይክሮፕሮሰሰርስ (microprocessors, እንደነ Raspberry_Pi, የአርድዊኖ ዓይነት ፕሮግራማብል ቦርድ) ካሉት የሚለየው የራሱ Firmwareና Operating System ስለሌለው ነው!

◽️ አርድዊኖ በምንጽፈው ኮድ ተመስርቶ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ለምሳሌ የሰዎችና ስፒከሮች ድምጽ (Voice Sensor), የመብራትና የጸሀይ ብርሃን (Light sensor), የሰዎች እንቅስቃሴ (Movement Sensor) ወይም ጽህፎች (Text Inputs) እንደ ግብአት በመጠቀም ሌላ ውጤት (Output) መፍጠር ይችላል!

◽️ የአርድዊኖ ፕሮግራም ለመጻፍ/ለመጠቀም የአርድዊኖ ሰርኲት ቦርድ (ምስሉ ላይ ያለው ለምሳሌ, አርድዊኖ ኡኖ, $39 ይሸጣል) መግዛትና
አርድዊኖ IDE (በነጻ ይገኛል) ሊኖረን ይገባል!

◽️ በአርድዊኖ ከተሰሩ ስራዎች ለመጥቀስ ያክል የጣት አሻራ, የርቀት መለክያ እቃዎችና የህጻናት ማጫዎቻ ሮቦት አሻንጉሊቶች ይገኙበታል
።
ውድ የቻናሌ ተከታታዮች የት ሆነው ነው የሚከታተሉኝ?
Anonymous Poll
28%
አዲስአበባ
9%
ባህርዳር
2%
አዳማ
4%
ሀዋሳ
6%
ጎንደር
1%
አሶሳ
2%
ድሬዳዋ
8%
ደሴ
5%
ደ/ማርቆስ
36%
ሌላ
Microsoft የሰራቸው Operating ሲስተሞችና የተሰሩበት ዓመት በፈረንጆቹ
📍Windows 1.0 (1985)
📍Windows 2.0 (1987)
📍Windows 3.x (1990, 1992)
📍Windows 95 (1995)
📍Windows 98 (1998)
📍Windows ME (2000)
📍Windows XP (2001)
📍Windows Vista (2006)
📍Windows 7 (2009)
📍Windows 8 (2012)
📍Windows 8.1 (2013)
📍Windows 10 (2015)
📍Windows 10X (2020) (only for Tablets)
# የዌብሳይት_ጥቆማ
=============
የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ
#5 የነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ድህረገፆች
(ብዙ መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ ሼር ያድርጉት)
1) Stanford Engineering Everywhere(SEE)
ይህ ድረገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው። ድረገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።
2) MIT Open እና Courseware
የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው # የድረገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች
# የኢንተርኔት ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው። ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።
3) GitHub.com
በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድህረገጽ ነው። እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድህረገጽ ዓይነት ነው።
4) W3 Schools
ይህ ድህረገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፡ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት ይሰጣል።
በተጨማሪም # በድረገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።
5) Codecademy
አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድህረገጽ ነው። በተለይ # ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።
ብዙ # መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ # ሼር ያድርጉት..
#ኦርጅናል Samsung smart ሞባይሎችን በቀላሉ ማወቅ ይፈልጋሉ?
መጀመሪያ *#06# ብለዉ ሲደውሉ የ IMEI ቁጥሩ ለምሣሌ 351532046393715 እዚህ ላይ ከመጀመሪያ ይቁጠሩ ''04" በ 7ና8ኛ ድጅት ይገኛል
ስለዚህ 7&8 ከሆነ የchina low quality ነው
🛑 80 or 08 የጀርመን fair quality.
🛑 10 or 01 የfinland good quality.
🛑◽00 ከሆነ original factory በጣም አሪፍ quality.
🛑 13 Azerbaijan ከሆነ በጣም መጥፎ (bad) quality.
🛑 03 or 04china ግን ጥሩ ከ 00,01 ያነሰ ነው።
🛑 ልብ ይበሉ 05 China ,Brazil,USA, Finland ሊሆን ይችላል።
🛑 06 China, mexico, Brazil ሊሆን ይችላል ።
✅ The numbers 05 or 50 indicates that your galaxy smartphone is manufactured either in
Brazil, USA or Finland
✅ The numbers 08 or 80 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in
Germany Or China
✅ The numbers 01 or 10 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in
Finland
✅ The numbers are 02 or 20 indicates that your galaxy smartphone is assembled in UAE or India
✅ The numbers 03 or 30 indicates that your phone is made in China or South Korea
✅ The numbers 04 or 40 indicates that your phone is made in China or UK
✅ The numbers 06 or 60 indicates that your galaxy smartphone is manufactured either in
Hong Kong, China, Mexico or France
✅ The numbers 00 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in the Original Factory
✅ The numbers 13 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Azerbaijan
✅ The numbers 07 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Germany
✅ The numbers 20 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Germany
✅ The numbers 70 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Finland
✅ The numbers 91 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Finland
✅ The numbers 41 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in the UK
✅ The numbers 44 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in the UK
✅ The numbers 18 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Singapore
✅ The numbers 67 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in the US
✅ The numbers 71 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in Malaysia
✅ The numbers 81 indicates that your galaxy smartphone is manufactured in China
ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ምንድነው?
ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ምንድነው?በኮምፒዩተር ኢንዳስትሪ እንደፋሽን ቦግ ብልጭ የሚሉ ቴክኖሎጂዎች በየግዜው ይከሰታሉ። ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ከዚህ አንጻር ተጠቃሽ የሚባል ቴክኖሎጂ ነው። ቃሉን በቀጥታ ወደ አማርኛ ከተረጎምነው “ዳመና ላይ ማስላት” ማለት ሲሆን ይህ ዓይነት ትርጉም መስጠት አንገታችንን ቀና አድርገን ዳመና ፍለጋ መዞር እና ግራ መጋባት ልያስከትል ይችላል።
በአጭሩ ሲገለጽ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ የኮምፒተር አገልግሎቶች፤ ማለትም ሰርቨሮች፣ የውሂብ ማጠራቀምያዎች፣ አውታረመረቦች፣ ሶፍትዌሮች እና ሌሎች አገልግሎቶችን ኢንተርኔት (ክላውድ) ተጠቅሞ የሚያቀርብልን ቴክኖሎጂ ነው። ይህ ማለት ውሂብ ወይም ዳታ የምናስቀምጠው በኮምፒተራችን ሳይሆን፤ ሌሎች ድርጅቶች በሚቆጣጠሩት ኮምፒዩተር ነው ማለት ነው። ያስቀመጥነውን ውሂብ ማግኘት ስንፈልግ፣ ኢንተርኔትን ተጠቅመን ወደ የግላችን ኮምፕዩተር መገልበጥ ወይም እዛው ክላውድ ላይ እያለ በ ማሰሻ(browser) ከፍተን ማየት እንችላለን። ይሁን እና ክላውድ ኮምፒዩቲንግ ውሂብ ማከማቻ ጎተራዎች ብቻ አይደለም በ አገልግሎት መልክ የሚያቀርብልን፤ ማንኛውም ኮምፒተራችን ላይ ማድረግ የምንችለውን ተግባር በተሻለ ፍጥነት እና ዋጋ ማከናወን የሚይስችለን ቴክኖሎጂ ነው።
ከክላውድ ኮምፕዩቲንግ መምጣት በፊት፤ ሶፍትዌር የሚያመርቱ እና የሚጠቀሙ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ብዙ ዓይነት ሶፍትዌር እና ሃርድዌር ገዝተው ይጠቀሙ ነበር። ይህ ውድ እና ውስብስብ ከመሆኑም በላይ፤ ለአጭር ግዜ ብቻ መጠቀም የምንፈልገውን ሃርድዌር ከመግዛት ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረም። በዚህም ምክንያት ወደ ገበያ ለመግባት የሚፈልጉ ድርጅቶች ከጅምሩ ብዙ ወጪ ማውጣት ግድ ይላቸው ነበር። ድርጅቶች ከጅምሩ ምን ያክል የውሂብ ማጠራቀምያ (storage)፣ የማስያ ጉልበት(processing power) ወዘተ…. እንደምያስፈልጋቸው በቀላሉ መገመት አይችሉም።
ድርጅታቸው ከሚፈልገው በላይ ጉልበት ያላቸው ሃርድዌር ከገዙ ለ አላስፈላጊ ወጪ ይጋረጣሉ፤ ካሳነሱት ደግሞ ሲስተማቸው ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ይታገላል። ይህንን ዓይነት ችግር ለመፍታት ክላውድ ኮምፒዩቲንግ ወሳኝ ቴክኖሎቹ ሁኖ ብቅ ካለ ሰነባብቷል።
እንደ አማዞን፤ ማይክሮሶፍት እና ጉግል የመሳሰሉ ድርጅቶች ብዙ ክፍተኛ አቅም ያላቸውን ኮምፒተሮችን አዘጋጅተው ለድርጅቶች እና ግለሰቦች ያከራያሉ። ለምሳሌ አንድ ሰው 100 ኮምፒተሮችን ተጠቅሞ ውስብስብ የሆነ የ ኮምፒተር ሲሙሌሽን መስራት ቢፈልግ፤ 100 ኮምፒተሮችን መግዛት አይጠበቅበትም ማለት ነው። ከ አማዞን እነዛን ኮምፒተሮች ተከራይቶ ተገቢውን ሶፍትዌር ኮምፒተሮቹ ላይ በርቀት(ኢንተርኔት ተጠቅሞ) ይጭናል። የፈለገውን ስራ አከናውኖ የተገኘውን ውጤት ወደ ራሱ ኮምፒተር መውስድ ይችላል። ይህ ሰውዬ እንደዚህ በማድረጉ ብዙ ነገር አትርፏል።
አንደኛ ስራው መጀመርያ እንዳሰበው በ 100 ኮምፒተሮች ብቻ የማይከናወን ከሆነ በቀላሉ ተጨማሪ ኮምፒተሮችን ማሰማራት ይችላል። ለዚህም ነው ክላውድ ኮምፒዩቲንግ ተለጣጭ (elastic) ባህሪ አለው የሚባለው።
ሁለተኛ ሰውዬው የሚከፍለው ብር ልክ እንደ ውሃ እና ኤሌክትሪክ፤ በተጠቀመበት መጠን ነው፤ እነዛን 100 ኮምፒተሮች ለ አንድ ሰዓት ብቻ ከተጠቀመ፣ የሚከፍለው በዛ ልክ ብቻ ነው።
ስለ ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ጥቅም እና ምንነት አንድን ምሳሌ በማንሳት አውርተናል። ይሁን እና ክላውድ ኮምፕዩቲንግ ሳናውቀው በብዙ መልኩ እንጠቀምበታለን። የሞባይላችን ውሂብ መጠባበቅያ(backup) ስናስቀምጥ፤ ኢሜል ስንጠቀም ወዘተ… ውሂባችን ክላውድ ላይ እይተቀመጠ ነው። ለዛም ነው ስልካችን ቢጠፋም አስፈላጊውን ቅጽ በመሙላት የጠፉብንን ውሂቦች የምናገኘው። ፌስቡክ ደግሞ ካየነው ሙሉ በሙሉ ክላውድ መሰረት ያደረገ አፕሊኬሽን ነው፤ ምክንያቱም ኢንተርኔት እስካለን ድረስ ማንኛውንም ፌስቡክ ላይ ያደረግነውን እንቅስቃሴ በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነን ማየት ስለምንችል።
በተለምዶ ኮምፒተራችን ላይ ጭነን የምንጠቀምባቸው ሶፍትዌሮች በብዛት ወደ ክላውድ እየተዘዋወሩ ነው። ለምሳሌ አብዛኞቻችን ከምንጠቀምበት የ ከማይክሮሶፍት ኦፊስ ምርት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ግን ሙል በሙሉ ክላውድ ላይ የተመሰረተ ጉግል ዶክስ የሚባል ምርት በ ጉግል ለተጠቃሚዎች ቀርቧል።
⚫️ ዩቲዩብ (You Tube)

◽️ቻድ ሀርሊ፣ ስቲቭ ቻን፣ እና ጃዉድ ካሪም በተሰኙ ሶስት ግለተሰቦች ቪዲዮን በድረ-ገጽ ለብዙሃን ለማሳየት ታስቦ የተሠራዉ ዩቲዩብ ለጥቅም የዋለዉ በ2005 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ነበር። በተፈጠረ በዓመቱ የጉግል ኩባንያ ዩቲዩብን በመግዛት የኢንተርኔት ዘርፉን ተቆጣጠረበት። የመጀመሪያዉ የዩቲዩብ ቪድዮ የተጫነዉ በ2005 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ጃዉድ ካሪም በተባለ ከዩቲዩብ መስራቾች አንዱ በሆነዉ ግለሰብ ነበር። ይህ ቪድዮ ከተጫነበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ በመቶ ሚሊዮኖች፣ የሚቆጠሩ ቪድዮዎች ተጭነዋል። ዩቲዩብን ተወዳጅና ስኬታማ ያደረገዉ በየትኛዉም የዓለም ክፍል የሚገኝ ማንኛዉም ሰዉ ቪዲዮዉን በቀላሉ እና በፍጥነት በመላዉ ዓለም እንዲታይ ማስቻሉ ነዉ። ይህ ደግሞ ግለሰቦች ፍጹም ኖሯቸዉ የማያዉቀዉን በዓለም አቀፍ ደረጃ በቢሊየኖች የመታየት ሃይልን አጎናጽፏቸዋል። በርካቶች የተለያየ ችሎታቸዉን አሳይተዉ ታዋቂና ባለጸጋ ለመሆንም በቅተዋል።

. ከ1.5 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚ ያለዉ ዩቲዩብ በየወሩ በአጠቃላይ ቢደመር ከ3.25 ቢሊዮን ሰዓት በላይ ርዝመት ያለዉን ቪድዮ ለእይታ ያቀርባል። ጉግል ሰዎች በሚጭኗቸዉ በእነዚሁ ቪድዮዎች ላይ ማስታወቂያን በማሳየት ከዩቲዩብ ብቻ በየዓመቱ ከ4 ቢሊዮን ዶላር (የ2016 ዓ.ም. መረጃ) በላይ ገቢ በየዓመቱ ያገኛል። ቪድዮዎቻቸዉን በዩቲዩብ የሚለቁ ግለሰቦችም ቪድዮዎቻቸዉ በታዩ ቁጥር ተያይዘዉ ከሚታዩት ማስታወቂያዎች ላይ ገንዘብን ያፍሳል።
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።