Muhammed Computer Technology (MCT)
38.4K subscribers
496 photos
7 videos
217 files
839 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100👆👆👆 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል። ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ ይጨምራል። እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ ይረዳሉ። በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት ያግዛሉ።
የዩቱብ ቻናል ለመክፈት እና ብር ማግኘት ለምትፈልጉ ሁሉ ቀለል ያለች ገለጻ አዘጋጅቸላችሁዋለሁ
ክፍል ➊ Part ➊
ቀልድ አደለም ሂወትን ሊቀይር የሚችል ብር ነው በዚ ስአት የተወሰኑ ሰወች ብቻ ናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኙት እናንተም ስለስራው ብዙ መረጃ ሳይኖራችሁ ብዙ ወቹ ጥሩ እየሰሩ ግን ብር የማያገኙ እንዲሁም አስቀያሚውን የዩቱብ ህግ በመጣስ የለፉበትንም ያጣሉ እና እችን የተወሰነች እና ጠቃሚ መረጃ ላካፍላችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ #YouTube ላይ የራሳችሁን ታለንት ነው የምትለቁበት
ለምሳሌ ➱ እኔ ቻናሌ ላይ Technology ነክ ነገር ነው በመስራት የምለቀው እናንተም
Music Entertainment
Sport News
Vine Film
#ላልጨርሰው_አልጀምረው
በፈለጋችሁት ነገር በመነሳት መልቀቅ እና ብራችሁን መዛቅ ትችላላችሁ በተጨማሪ የግድ የራሳችሁ ስራ ይሁን ማለቴ አደለም
ለምሳሌ ➱ እንዴ ሙሌ ምነካህ እኔ በ Sport ነክ ልሰራ አስቤያለሁ ግን ኢትዮጵያ ሆኘ እንዴት ስለ እንግሊዝ ፕሪሜርሊግ መስራት እችላለሁ የሚሉ አይጠፉም እና የግድ ከዛ መሆንና አይጠበቅብህም ከተለያዩ ቦታወች ላይ ቪዲዮ በማቀናጀት ኢዲት እና በራስህ አገላለጽ ማቅረብ ትችላለህ ግን #ሌላ_ሰዉ_የለቀቀዉን ሙሉ በሙሉ መልቀቅ #አይቻልም
ክፋል 2️⃣ Part ➋
➠ ቻናል ለመክፈት የሚያስፈልገን በቀላሉ
Computer(PC) አያስፈልግም ካለን እሰየው
YouTube የሚያስጠቅም ስልክ ከፈለግንም ስልካችንን እንደ Computer(PC) መጠቀም ትችላላችሁ Google Chrome በመግባት desktop site በማረግ
2 ደግሞ YouTube_App ጋ በመግባት
1 ኢሜል አካውንት
ከዛ Youtube.Apk ውስጥ በመግባት ኢሚላችን በመጠቀም ሳይን ኢን ማረግ ቻናል ክሬት ማረግ በቃ ቻናል ተከፈተ ከዛ ስራችን መልቀቅ እንችላለን መረሳት የሌለበት የከፈትነውን ቻናል ፒሲ ወይም በስልካችን google chrome በመጠቀም ቬሪ ፋይ ማረግ ይኖርብናል ስልካችን ላይ የሚመጣውን ኮድ ስናስገባ ነው አለበለዚያ ቪሪፉይ ካላረግነው ከ15 ደቂቃ በላይ ያላቸውን ቪዲዮ መልቀቅ አትችሉም።
ክፍል ❸ Part ❸
➱ በዋናነት የብዙ ሰው ራስ ምታት የሆነው ቻናል ያላችሁ እንዲሁም አዲስ ቻናል የከፈታችሁ ኡፍ ቻናሌ ብዙ ሰብስክራይብ እና እይታ የለውም ይላሉ አሪፋ👌 10 መላ ልንገራችሁ ከትላልቆች ዩቱዩበሮች ጎን ለመቆም እና በወር
እስከ 1,000,000ብር 😱😒🤔ለማግኘት
➊ የቻናላችሁን ስም ቀላል እና ማንም ፈልጎ የሚያገኘው ማረግ
ለምሳሌ:- Ethiopia music, Etho movie
አንዳንድ ሰወች ግን ይሸወዳሉ xx new boy 21 fashion,um mal.21,tgo ethiopiawit konjo♥❌❌❌❌👊
❷ ጥርት ያለ #Video መልቀቅ
❸ ጥርት ያለ ድምጽ ይኑረው ከምስሉ እንዲያውም ሰው መታገስ የማይችለው
❹ የሰራችሁትን ቪዲዮ
#telegram, በዋናነት #Facebook, #Instagram, #WhatsApp የተለያዩ ቦታ ሼር ማረግ 100% በጣም ቻናሌን ለውጦታል ተጠቀሙበት
❺ ለሰራችሁት ቪዲዮ የሚመሳሰል እና ሰው ፈልጎ የሚያገኘው ማረግ
ለምሳሌ:- ዳንስ ከሆነ #Ethio_Dance 👍
❌❌ ቀውጢ አለምን ያፈዘዘ የዳንስ ቪዲዮ👊👊👊
❻ ለሰራነው ቪዲዮ የሚስብ የፊት ገፅ ማዘጋጀት(ታምብኔል)😍
❼ ከሰራነው ቪዲዩ ሀሳብ ማስቀመጫ ሳጥን(ዲስክርቢሽን ቦክስ ላይ የሌሎች የሰራነውን የቪዲዮ ሊንክ ማስቀመጥ
❽ ቶሎ ቶሎ ቪዲዮ መልቀቅ ቢያንስ በሳምንት 1
❾ ለሰራነው ቪዲዮ #እርእሱን በ #አማርኛ
እና በ #English ቋንቋ ማድረግ
❿ ጥሩ ጥሩና ወቅታዊ ነገሮችን ሰው ምን ይፈልጋል ምን ብለቅ ይታይልኛል የሚለው ላይ ማተኮር
❶❶ ሁሌም ከኛ የሚሻል ሰው እንዳለ ማወቅ አለብን እና የሌሎችን #Channel_Video ሁሉን ነገር በማየት ልምድ ተሞክሮ መውሰድ ከምር ያልኩዋችሁን ካረጋችሁ ይሳካላችሁዋል።
ክፋል ❹ Part ❹
➠1 ክፋያ መቀበል የምትጀምሩት ቻናል በከፈታችሁ እስከ 1 አመት ድረስ ቻናላቹ
1000subscribe(ተከታይ) እና 4000ስአት ማለትም 240,000ደቂቃ ከታየ ብራችሁን መዛቅ ትጀምራላችሁ ኢትዮጵያ ውስጥ እንኩዋን ደስ አላችሁ መቀበል ተጀምሮዋል ክፋያው በየ ወሩ ነው
ቢያንስ ጥሩ ምትሰሩ ከሆነ በወር ከ50,000 ብር በላይ ታገኛላችሁ
✨የዩቱብን ህግ ልንገራችሁ
የመጀመሪያው
❶ የሰው ቪዲዮ ስትለቁ ባለቤቱ ካመለከተ 3 እድል ነው ሚሰጠው ከነጭራሹ ቻናላችሁ ይዘጋል ክፍያ ብትጀምሩም እንኩዋን
ብዙ ሰው ለሰብስክራይብ እና እይታ ሲል ችግር ውስጥ ይገባል
❷ እርእሱና ቪዲዮው የማይመሳሰል ከሆነ ሰወች እሪፓርት ካረጉ ይዘጋል ለምሳሌ የሳምንቱ ምርጥ ፊልም ብላችሁ ሙዚቃ ሌላ ነገር ከለቀቃችሁ ማለት ነው
❸ የናንተ ያልሆነ ቪዲዮ የኔነው ብላችሁ የሰው ለማዘጋት ሪፓርት ብታረጉ የናንተ ካሎነ ይዘጋል
በዩቱብ አንድን ቪዲዮ ቀድሞ የለቀቀ የዛ ቪዲዮ ባለቤት ነው።🛎
🛎5ተኛውን እና የመጨረሻውን ነው።
ክፍል ❺ Part ❺
💰💰ዩቲዩብ ስንት ይከፍለናል? 💰💰
ዩቲዩብ ላይ ክፍያው ያው እንደሰራችሁት ስራ መጠን ይከፍላል እናም ጥሩ ምትሰሩ ከሆነ በወር እስከ 1000$ እሰከ 30,000 እንዲሁም በጣም በጣም ከሰራን በወር በትንሹ እስከ 100,000ብር ይከፍላችሀል ብሩ ሚከፈለው በየወሩ ነው እናም ማወቅ ያለባችሁ ነገር በወር ውስጥ ከ100$ በታች ከሰራችሁ ማውጣት አትችሉም ብሩን ለማውጣት ከ100$ በላይ መሆን አለበት ለምሳሌ በዚ ወር 50$ ቀጣይ ወር 50$ ከሰራው በቀጣይ ወር የሁለቱን ወር 100$ ይከፍላችሀል ይህን የሚከፍለው ግን እላይ እንደነገርኳቹ 1000 ሰብስክራይበር እና 4000 ሰዓት እይታ በ12 ወር ውስጥ ስታገኙ መክፈል ይጀምራል።
#እንዴት_ነው_ትምህርቶቹ_ተመቻችሁ?
የናንተን አብሮነት እኛን እንደተበራታቱን ያደርገናል።🛎
via ኢትዮጵያን ሀከርስ
HDMI ዲጂታል ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ማገናኛ
.......................................................................
HDMI ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው ዲጂታል ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ለማገናኘት የምንጠቀምበት ባለ19 ፒን ማገናኛ ሲሆን ዲዛይን የተደረገው በኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድምጽ እና ምስል በአንድ ጊዜ በአንድ ገመድ ለማስተላለፍ ተደርጎ ነው፡፡
ኤችዲኤም አይ በቐሚነት በቴሌቪዥኖች፣ የቲቪ ሪሲቨሮች ሳጥን፣ የብሉ ሬይ ማጫዎቻዎች፣ በጌም ካውንሱሎች፣ በቪዲ መቅጃ ካሜራዎች እንዲሁም በዲጂታል ካሜራዎች ላይ እና በኮምፒውተሮች ላይ እናገኘዋለን፡፡
ኤችዲኤምአይ/ HDMI በጣም ጥሩ ትልቅ ነገር እነዚህን ሁሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በጋራ ለማስጠቀም የሚያስችል ሲሆን ንጹህና የጠራ ያልተወሳሰበ የዲጂታል ምልከታ ድምጽ ለማስተላለፍ የተሻለው አማራጭ ነው፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ኤችዲኤምአይ 1.0 ተሰርቶ ለገበያ የቀረበው ታህሳስ 2002 እ.ኤ.አ ሲሆን በየጊዜው የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እቃዎች እየተሰሩ ሲመጡ እና ሲሻሻሉ በነሱ ላይ እንዲሰራ ራሱን ላይ መጠነኛ ለውጦች እያሳደገ መቱዋል (ቨርዥን 1.0፣ 1.1፣ 1.2፣ 1.2ኤ፣ 1.3፣ 1.3ኤ፣ 1.3ቢ፣1.3ቢ1፣1.3ሲ፣ 1.4፣ 1.4ኤ፣ 1.4ቢ፣ 2.0) ፡፡
ጥር 2017 ጀምሮ ኤችዲኤምአይ 2.1ን አቅርባል ይሄም ቨርዥን የቅርብ ግዜ ከፍተኛ የምስል ጥራት፣ ከፍተኛ ብርሃን፣ ኮንትራስት፣ብዙ ቀለማት ያለው፣ 3ዲ ግራፊክስ እቃዎች ላይ የሚሰራ ሲሆን ከቀድሞዎቹ ስሪቶች ጋር ወደ ኋላ ይሰራል፡፡
ኤችዲኤምአይ በሶስት አይነት ይከፈላል ለትልልቅ እቃዎች ማገናኛ የምንጠቀምበት ታይፕ ኤ 13.9 mm x 4.45 mm/ 14 mm x 4.55 መጠን፣ Mini-HDMI ታይፕ ሲ 10.42 mm x 2.42 mm ለትንንሽ እቃዎች ማገናኛ እና Micro-HDMI ታይፕ ዲ 6.4 mm x 2.8 mm መጠን ናቸው፡፡
የኤችዲኤምአይ መሳሪያዎች በሚገዙበት ጊዜ የትኞቹን ባህሪያት ለእርስዎ በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ ለማስተዋል ሁኔታዎች ዙሪያ ይህ ጽሑፍ ይረዳዎታል፡፡
ምንጭ፡-ኢንፎቶፒያዝ ቴክኖሎጂ
ኢንተርኔት ስትጠቀሙ በምንድ ነው?
Anonymous Poll
31%
በቀጥታ በብር
69%
በጥቅል አገልግሎት package
በስልካችንና በላፕቶፕ እንዴት ከሁለት ሰዎች በላይ በአንድ ላይ ሁነው ዙም(ZOOM) app ተጠቅመን በቪዲዮና በድምጽ እንዴት ማውራትና እንደምንችል ነገ ይዜላችሁ እቀርባለሁ።
እንድታውቁት ትፈልጋላችሁ? ሀሳባችሁን ጻፉልኝ
መልካም አዳር!
ZOOM (ዙም) ተጠቅመን ሁለትና ከዚያ በላይ ሁነን ማውራት እንችላለን እንዴትስ አካውንት መክፈት እንችላለ?
አፕሊኬሽኗን በቴሌግራም ቻናሌ https://t.me/MuhammedComputerTechnology
በመግባት ታገኛላችሁ ወይም google play store ላይ በመግባት ታገኛላችሁ አውርዳችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
መጀመሪያ አፕሊኬሽኗን ማውረድና በስልካችን ወይም በላፕቶፓችን መጫን ይኖርብናል። ከተጫነ በኋላ አፑን በመክፈት እንደሚከተለው ምን ምን ማድረግ እንዳለብን እንደሚከተለው አብራርቸዋለሁ። ሙሀመድ አሚን ነኝ ፔጁን like invite ለሌሎች እንዲደርሳቸው እናድረግ!
1 Join Meeting በኢሜይል meeting create ያደረገው ሰው Meeting ID Passcode በኢሜይላችሁ የተላከላችሁን በማስገባት መጀመር ይቻላል ከዚህ ላይ ዙም አካውንት በመክፈተም ሳትከፍቱም ይሰራላችኋል እንዴት ይላካል ጨርሳችሁ ስታነብቡት ይገባችኋል።
2 Sign Up አዲስ account ለመክፈት ስትፈልጉ
3 Sign In ከዚህ በፊት accou ከፍታችሁ ለመግባት ስትፈልጉ መግቢያ ነው
📍📍📍 Sign Up 📍📍📍
በመጀመሪያ ደረጃ ወደ ስራ ከመግባታችን በፊት email ሊኖረን ይገባል። email የሌለው ካለ አሁን መክፈት ይኖርባችኋል። ካካላችሁ መቀጠል እንችላለን።
◄◄◄◄◄◄◈◈◈◄◄▻▻▻◈◈◈▻▻▻▻▻▻▻
📍sign up የሚለውን ስንነካ የሚመጣልን Birth Date መጀመሪያ እንሞላለን ቀን/ወር/ዓ.ም ለምሳሌ 10 10 1990 ይህንን ካስገባችሁ በኋላ email firstname lastname ትሞላላችሁ ክዛም sign up የሚለውን ትጫናላችሁ ከዛም " we sent an email to verify your account" የሚል ይመጣል ስለዚህ በኢሜይላችሁ የተላክ verification ሊንክ አለ ኢሜይላችሁ ውስጥ በመግባት ከzoom የተላከ ከዚህ በታች እንዳለው ይመጣላችኋል
Hello Muhammed Amin,
Welcome to Zoom!
To activate your account please click the button below to verify your email address:
Activate Account( በሰማያዊ ሳጥን ያለች) 
Or paste this link into your browser:
https://us04web.zoom.us/activate?comqvWFpbC5jb20BAGQAABZjT3I3UzBWR1JlcUNXcE91ODFYb3p3AAAAAAAAAAAAAA&fr=client
ከላይ ያለውን መልዕክት ስትገቡ ታግኛላችሁ። ስለዚህ Activate Accou የሚለውን በሰማያዊ ያለችውን መጫን ትችላላችሁ ወይም https://............./ የሚለውን ሊንክ ወደ browser ላይ copy paste በማድረግ ኢንተርን ወይም go እንላለን።
ከዛም Are you signing up on behalf of a school?
⚫️Yes ⚫️No
የሚል ይመጣል እናንተ No የሚለውን ይጫኑና continue የሚለውን ይጫኑ የሚመጣላችሁ
1 Account Info
2 Invite Colleagues
3 Test Meeting
First name Muhammed
Last name Amin
Password ABcd@1234 ይህ ምሳሌ ነው
Confirm password ABcd@1234
📍Password must:
📍Have at least 8 characters
📍Have at least 1 letter (a, b, c...).
📍Have at least 1 number (1, 2, 3...)
Include both uppercase and lowercase characters
የሚለውን በሙሉ እንሞላለን ማለት ነው
ከዛም continue የሚለውን እንጫናለን።
🛑 Invite Colleagues የሚለውን skip this step ማለት ትችላላችሁ ከዛውጭ ግን አብሯችሁ ከናንተ ጋ ለማውራት የምትጋብዙትን ሰው ኢሜይል ማስገባት ትችላላችሁ።
🛑Excellent! Now it's time to start meeting.
Your personal meeting url:
https://us04web.zoom.us/j/4325014571?pwd=OEhE
🛑ለመጀመር Start Meeting Now የሚለው እንጫናለን ማለት ነው
ከዛም ወደ ኢሜይላችን የሚላክልን
Hi Muhammed Amin,
Muhammed Amin has joined your Personal Meeting Room. 
🛑Start Meeting á‹¨áˆšáˆˆá‹áŠ• ይጫኑ🛑
Thank you for choosing Zoom.
-The Zoom Team
start meeting የሚለውን ሲጫኑ ወይም zoom አፕ ላይ በመሄድ sign in ይጫኑ email እና password ይጠይቃችኋል ቅድም account ስትከፍቱ የሰጣችሁትን email and password አስገቡ ከዛም ይከፍትላችኋል ማለት ነው።
🛑እንደከፈተ meeting & chat የሚል እንዲሁም
New meeting
Join
Schedule
Share screen
ከታች በኩል
meet & chat
meetings
Contacts
Sheeting
የሚል አለ እነዚህን አንድ በአንድ እናያለን
🛑New Meeting የሚለው ሚቲንጉን ለማስጀመር ነው ይህ ማለት ለመወያየትና ሌሎች ተወያዮችን ለማስጀመር ይህንን መንካት ይጠበቅብናል።
Join የሚለው ሌላ ሰው ከናንተ ጋር ለመወያየት ከፈለገና Id ከላከላችሁ Id በማስገባት ያንን ሰው ማግኜት ትችካላችሁ።
🛑schedule የሚለው ይህ ዋናው ነገር ነው ውይይት ማድረግ የምትፈልጉበትን ቀንና ሰአት የምትወስኑበት ነው።
🛑zoom meeting አስገቡ ለምሳሌ ለሙሀመድ አሚን የሪሰርች ማቅረቢያ ሰአት
Date ለምሳሌ 16/09/2020 መስከረም 05/01/2013 ማለት ነው
from 6:00 am ከጠዋቱ 12:00 ማለት ነው
to 6:30 am እስከ ጠዋቱ 12:30 ማለት ነው
password እራሱ ይሰጣችኋል
🛑ከላይ በኩል ለማጥፈት ከፈለጋችሁ cancel and ስኬጁል አድርጋችሁ ከጨረሳችሁ done የሚለውን ይጫኑ በነገራችን ላይ ከላይ ያለውን ሰአት ቀን ወደ የምትፈለጉት መቀየር ትችላላችሁ።
🛑ስለዚህ done ከተጫናችሁ ጨረሳችሁ ማለት ነው
ከዛ from ይልና የናንተን email ያመጣዋል to ከሚለው ላይ ደግሞ ከናንተ ጋ ለመሰብሰብ ለምትፈልጉት ሰውን email በማስገባት ከላይ በኩል ▻ ምልክትን በመጫን ትልካላችሁ ማለት ነው።
የተላከለት ሰው በኢሜይሉ በመግባት የተላከለትን ሊንክ ወይም Meeting ID: Passcode: ያስገባል ማለት ነው ግን ከዚህ ላይ እናንተ meeting start ማስጀመር አለባችሁ ማለት ነው።
🛑ሌላው ሰው participants ከሚለው ላይ እናንተ የጋበዛችሁት ሰው መግባቱን ያሳያችኋል ከዛም እንዲገባ ከፈለጋችሁ admit ትሉታላችሁ ማለት ነው።
አሁንም ሌሎች ሰዎችን መጨመር ከፈለጋችሁ
🛑participants ውስጥ inviteን በመጫን ለሚላክለት ሰው email በማስገባት መላክና መጨመር ትችላላችሁ
🛑share screen
የስልካችሁን ወይም የላፕቶፕ ስክሪን ማጋራት ከፈለጋችሁ ተጫኑ ለማጋራት meeting start መሆን አለበት
🛑Setting ገብታችሁ ማስተካከል ትችላላችሁ።
ያልገባችሁ ካለ comment inbox አድርጉልኝ።
🛑ሙሀመድ አሚን 05/01/2013
🛑copy paste ስታደርጉ credit ስጡኝ።
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ
💻ላፕቶፓችን ላይ ያለውን ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን
መጠቀም እንችላለን⁉️
▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃

❶. cmdን በአድሜኒስትሬተር ያሩጡት (right click በማድረግ run as
administrator የሚለውን መጫን)

❷. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ:netsh
wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted
network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው።

❸. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት: netsh wlan set
hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname key=password

♨️ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን: KEY የሚለው የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን

❹. በመቀጠል የኔትዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click
በማድረግ : Allow other network users to connect through this
computer's internet connection የሚለውን እንመርጥያ።

ከስር ካለው ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን። ከዛም OK በለን እንወጣለን

❺. በመጨረሻ ወደ CMD ተመልሰን:
ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ
እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን።

❻. አሁን ሞባይላችንን wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም
መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር እንችላለን።

═════════════════
▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
╚═════📌Share📌════╝
✳️ ኦርጅናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ እንዴት መለየት ይቻላል። እነዚን መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ።

🏷 የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም
ፌክ ሳምሰንግ ስልክ

1. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም
2. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል
3. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል
4. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል
5. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን
ይመለከታሉ፡፡

🏷 የስልኩን ፍጥነት እና ትእዛዞችን አፈጻፀም በመገምገም

1. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል
2. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡
3. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም

🏷 የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም

1. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ Settings የሚለዉን ይጫኑ
3. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና #Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም ወደ ስልክ መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡

🔔 *#0*# #አጠቃላይ መገምገሚያ
🔔 *#1234# or *#9999# ስልኩ የሚጠቀመዉን
#ሶፍትዌር እና #ሞደም ማወቂያ
🔔 *#12580*369# #ስለ ስልኩ #ሶፍትዌር እና #ሀርድዌር ማወቂያ
🔔 *#06# #የስልኩን ኢንተርናሽናል #መለያ ቁጥር
ማወቂያ
🔔 *#9998*246# #የስልኩን #የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ
ሳምሰንግ ኪይ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡

1. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት ላይ
ይጫኑት
2. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት
3. ሶፍትዌሩ ስልኩን ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል፤
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
📌ለጠቅላላ እውቀት ከታች የተዘረዘሩት መስራቾቹ
እነማን እንደሆኑ አስቀምጠንላቿል።
1. Google— Larry Page and Sergey Brin
2. Facebook~Mark Zuckerberg
3. Telegram~was started in 2013 by the brothers Nikolai and Pavel Durov.
4. Yahoo~David Filo and Jerry Yang
5. Twitter~Jack Dorsey and Dick Costolo
6. Internet~Tim Berners Lee
7. LinkedIn~ Reid Hoffman, Allen Blue and Koonstantin Guericke
8 Email~Shiva Ayyadurai
9. Gtalk~Richard Wah kan
10 WhatsApp~aurel Kirtz
11. Hotmail~Sabeer Bhatia
12. Wikipedia~Jimmy Wales
13. You tube~Steve Chen, Chad Hurley and JawedKarim
14. Rediff~Ajit Balakrishnan
15. Nimbuzz~Martin Smink and Evert Jaap Lugt
16. Myspace~ Chris Dewolfe and Tom Anderson
17. Ibibo~ Ashish Kashyap
18. OLX~ Alec Oxenford and Fabrice Grinda
19. Skype~Niklas Zennstrom,JanusFriis and Reid
Hoffman
20. Opera~Jon Stephenson von Tetzchner and Geir
lvarsoy
21. Mozilla Firefox~Dave Hyatt and Blake Ross
ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ እንዴት ማስተካከል ይቻላል?
በተለያዩ አጋጣሚዎች ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፣ ይህ ሁኔታ ሲፈጠር ከመደናገጥ ይልቅ ቀላል የሆኑ አካሄዶችን በመከተል
ስልክዎ. እንዳይበላሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ከሁሉም በፊት ስልክዎን በፍጥነት ከዉሀ ዉስጥ ማዉጣት ይኖርቦታል፡፡
ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ በቆየ ቁጥር ዉሀ ወደ ስልክዎ ዋና ክፍሎች ዉስጥ የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
ሊከተሉዎቸዉ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን እንመልከት፡
በፍጹም ሊያደርጉዎቸዉ የማይገቡ ነገሮች
• ስልክዎን እንዳያበሩት
ስልክዎ ላይ የሚገኙትን ቁልፎች አይንኩ
•ስልክዎን አያወዛዉዙት ወይም ስልክዎ ከሌሎች ነገሮች ጋር አያጋጩት
•የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች አይንቀሉ፡፡
ስልክዎ የዉሀ ብልሽት
አመላካች(Liquid Damage Indicator(LDI)) ተገጥሞለታል፣
የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች የሚከፍቱት ከሆነ ይህ የዉሀ ብልሽት
አመላካች አክቲቭ(Active) ይሆናል፡፡
ይህ ደግሞ ከስልኩ አምራች
ድርጅት የሚሰጠዉን Warranty ያሳጣዎታል፡፡
በትንፋሽዎ ዉሀዉን ለማድረቅ አይሞክሩ፣
ምክንያቱም ስልክዎ
ላይ በሚተነፍሱበት ጊዜ ዉሀ ወደ ዉስጠኛዉ የስልክዎ ክፍል ዉስጥ ሊገባ ስለሚችል ነዉ፡፡
ስልክዎን በማንኛዉም አይነት. የሙቀት መሳሪያ ለማድረቅ አይሞክሩ፡፡
ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ ከብልሽት የሚከላከሉባቸዉ አካሄዶች
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
1) ስልክዎን ከዉሀ ዉስጥ ሲያወጡት እየበራ ከሆነ ያጥፋት እና ቀጥ አድርገዉ ይያዙት፡፡
2) የስልክዎን ከቨር በመክፈት ባትሪ፣ሲም ካርድ እና ሚሞሪ ካርዱን ያዉጡ፡፡
3) ደረቅ ጨርቅ ወይም ማድረቂያ በመጠቀም ስልክዎን ያድርቁ፡፡
ዉሀ ወደ ሌላ የስልክ ክፍሎች እንዳይተላለፍ ይጠንቀቁ፡፡
4) በጐድጓዳ ሰሀን ላይ ያልተቀቀለ ሩዝ ይጨምሩ እና ስልክዎን ሩዝ ዉስጥ ይክተቱት፡፡ ሩዝ ዉሀን የመምጠጥ አቅሙ በጣም ከፍተኛ ስለሆነ አብዛኛዉን ጊዜ ስማርት ስልኮችን እና ታብሌቶችን ለማድረቅ ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡
5) ስልክዎ በሩዝ ዉስጥ ለአንድ ወይም ሁለት ቀን እንዲቆይ ያድርጉ፡፡ በእነዚህ ቀናቶች ዉስጥ ስልክዎን ለማብራት እንዳይሞክሩ፡፡
6) ከጥቂት ቀናቶች በሗላ ስልክዎን ከሩዝ ዉስጥ ያዉጡ እና ባትሪዉን አስገብተዉ ያብሩት፡፡
ስልክዎ አሁንም ካልበራ ባትሪዉን ቻርጅ ያድርጉት፣
ቻርጅ ተደርጎም የማይበራ ከሆነ ባትሪዉ ብልሽት አጋጥሞታል ማለት ነዉ፡፡
ባትሪ ይቀይሩለት ወይም ወደ ስልክ ሰሪዎች ይዉሰዱት፡፡
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ #ወንድም #እህቶች አሉን
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
በቴሌግራም ቻናሌ በመግባት ብዙ መረጃዎችን ማግኜት ትችላላችሁ።
1.✳️ MotherBoard:
◽️Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡
◽️ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ (Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡
2.✳️ Central Processing Unit (CPU):
◽️ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡
◽️ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡
◽️ የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡
3.✳️ Random Access Memory (RAM):
◽️RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡
◽️RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
◽️የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል።
4.✳️ Hard Drive:
◽️Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ ሙዚቃዎችን፤ ምስሎችን፤ ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡
◽️Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
5.✳️ Power Supply Unit:
◽️Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡
አንድሮይድ ስልክዎት ፍጥነት ጎታታ ሆኖ አስቸገረዎት?
የአንድሮይድ ስልክዎን ፍጥነት ወደቀድመው ለመመለስ እነዚህን ቀላል የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀሙ፡፡
1. ችግሩን ለመለየት ይሞክሩ
የስልክ ፍጥነት ችግር በበርካታ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል፡፡
እነዚህን ችግሮች ምናልባት የተከሰቱት ኮራብት በሆኑ አፕልከሽኖችና ፋይሎች፤በRAMና በstorage መጣበብ ወይም
በቫይረስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ማወቅ ስንችል latest የሆኑ ስልኮች እራሳቸው cleaner አላቸው።
በነዚህ አፕልኬሽኖች ታግዘው የስልክዎን ብቃት
(performance) ሪፖርት ማየት ይችላሉ፡፡ ቀጥሎም የሚከተሉትን ዘዴዎችን ይሞክሩ፡፡

2. አላስፈላጊ የሆኑ አፕልከሽኖችን ያጥፉ
ተጠቅመው የማያውቅትን አፕልከሽኖችን ያጥፉ ወይም freeze ያርጓቸው(ለ latest ስልኮች)
3. የአፕልከሽኖችን cach data ያጥፉ
ካች ዳታ ማለት አፕልከሽኖች ለሌላ ጊዜ ለፍጥነት እንዲረዳቸው
በራሳቸው የሚያስቀምጡት ዳታ ነው ነገር ግን ይህ ዳታ እየበዛ
ስሄድ የስልኩን የውስጥ storage ቦታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊይዝ ይችላል።
ካች ዳታ ለማጥፋት setting =>apps(all application)
ውስጥ ገብተን በየአንዳንዱ አፕልኬሽን ውስጥ እየገባን "clear cache" የምለውን በመምረጥ ካች ዳታ ማጥፋት ይቻላል፡፡
4. የስልክዎን ስቶረጅ( storage ) ያጽዱ
የስልክዎ storage አላስፈላጊ በሆኑ ፋይሎች ተጣቦ ሊሆን ይችላል። እነዚህን ፋይሎች ማጥፋት በተለይም የስልኩን
የውስጥ ስቶሬጅ(internal storage) ማጥፋት ለስልክዎ ስራ ጥሩ የመተንፈሻ ቦታ ይሰጣል፡፡
5. (widgets), በአንመሽን የተሞሉ launcher እና(animated launchers and live wallpapers ) አይጠቀሙ።
ውድጌቶች(widgets), በአንመሽን የተሞሉ ላውንቸረችንና ዋልፔፐሮች(animated launchers and live
wallpapers ) የስልካችንን ራምና ፕሮሰሰር ሊያጣብቡና ሊያጨናንቁ ስለሚችሉ ውድጌቶችን ያለመጠቀም ይምረጣል፡፡
በተጨማሪም ውድጌቶች(widgets), በአንመሽን የተሞሉ
ላውንቸረችንና ዋልፐፐሮች(animated launchers and live
wallpapers ) የባትሪ ጠላቶች ናቸው፡፡
6. በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን አይጠቀሙ
በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን መክፈት ከስልካችን አቅም በላይ
ሆኖ የስልኩን ፕሮሰሰርና ራም ልያጨናንቅና ልያስቸግር
ይችላል፡፡ስለዚህ በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን አይጠቀሙ፡፡
7. ፎርማት(format) ያድርጉ (ፋክተሪ ሪሲት)
ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች አንድሮይድ ስልክዎን ፍጥነት
ልያሻሽሉ ይችላሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ልያጠፉ አይችሉም፡፡
ፎርማት(format) ማድረግ ግን ወደ ቀድመው ፍጥንት ልመልስ
ይችላል፡፡ ነገር ግን ስልከዎን ፎርማት ከማድረገዎ በፊት ባክአፕ
(backup) ማድረግ የግድ ነው።
(ለሚወዱት ሼር አድርጉት)
┈┈┈┈◎◎❍❍┈┈┈┈
⚠️ መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ contact group channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
🎖የኮምፒውተር ሶፍትዌር ለማውረድ የሚጠቅሙ ምርጥ ድረገጾች፥
1. getintopc.com
ይህ ድረገጽ ትላልቅ ሳይዝ ያላቸውን ሶፍትዌሮች ለማውረድ ተመራጭ ነው። ለምሳሌ ያህል driver pack(11GB size) ከዚህ ድረገጽ ማውረድ ይቻላል። በተጨማሪም ዊንዶውስ 10,8.1,8,7, እና ማይክሮሶፍት ኦፊስ ማውረድ ይቻላል።
2. oceanofgames.com
3. filehippo.com
4. cnet.com
5. softonic.com
6. download.com
7. softpedia.com
8. Tucows.com
9. freewareFiles.com
10. majorGreeks.com
11. snapfiles.com
12. filecluster.com
13. geardownload.com
14. soft32.com
15. softonic.com
16. freewarehome.com
17. freedownloadcenter.com
18. opensourcemac.org
19. lo4d.co
20. fileEagle.com
21. P30download.com

═════════════════
▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ contact/group/channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

📝 የተማሩትን ማስተማር፣ ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
╚═════📌Share📌════╝
🔘ቴሌግራምን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ?
🔐መፍትሄውን እነሆ🔐
❖.ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatsapp, viber, imo, tango.....etc
📌ቴሌግራም እንደ whatsapp, viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል
❖. ይህ ዘዴ ሌሎች hack ማድረጊያ hacking Tricks ሳያስፈልገን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም
ማለትም የራሳችን ቴሌግራም አፕሊኬሽን ላይ ወይም pc ላይ ቴሌግራም install በማድረግ የምንፈልገውን ቁጥር በማስገባት ኮዱን ካስላክን ብኋላ ኮዱን የምናገኝበት አጋጣሚ ካለ....
❖. በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉኝ
❶ Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።
■Note: እራስዎ በሌላ አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል ስለዚህ በደንብ ይመልከቱ።
📌ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት።
☛ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ የእናንተን አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።
❷ Security ደግሞ ለማጠናከር
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password ***..ግን የ gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።
❖ ይህ ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።
❖ የሚጠቅመው እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
❖ ሌላ ሰው በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
❖ ማንም ሰው ለመግባት በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም።
⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት።
⚠️ከላይ ያሳየናችሁ ዘዴ ቴሌግራማችሁን በቀላሉ ኮዱን ወስደው በናንተ ቁጥር እንዳይጠቀሙ ነው እንጂ የተለያዩ hacking ዘዴን በመጠቀም ሃክ ከመደረግ አይከለክልም ለምሳሌ ☛Kali linux.
═════════════════
▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
╚═════📌Share📌════╝
🖥3️⃣2️⃣ ቢትⒷⒾⓉ እና 6️⃣4️⃣ ቢትⒷⒾⓉ ሲፒዮ ልዩነት
እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡
የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡
🔆32 ቢት ፕሮሰሰር🔆
32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡
ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡
🔆64 ቢት ፕሮሰሰር🔆
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡
🔆ማስታወሻ🔆
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)
🛑 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡
🛑 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆኑ የተገደዱ ሲሆን ይሄም የፕሮሰሰር አምራቾች 64 ቢት ፕሮሰሰር በስፋት ወደገበያ እያቀረቡ ነው፡፡
═════════════════
▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
╚═════📌Share📌════╝
ፌስቡክ ገጽ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
ቴሌግራም ቻናል https://t.me/MuhammedComputerTechnology
❖ ፍላሽ ዲስክ ኮምፒዩተርዎ ላይ ሲሰካ ሾርት ከት እየሆነ ተቸግረዋል?
❑ ፍላሽ ዲስካችን ወይም ኮምፒዩተራችን በቫይረስ ሲጠቃ በውስጡ ያሉት ፋይሎች በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ሾርትከት ይቀየራሉ። ይህም ማለት ዋናው የኛ file(ፋይል) ይደበቅና ለመጠቀም አንችልም ማለት ነው።
❑ የዚህ ቫይረስ ሌላው አስቀያሚ ገጽታ ከኮምፒዩተር ወደ ሌላ ኮምፒዩተር በቀላሉ በፋላሽ አማካኝነት ሊተላለፍ መቻሉ ነው።
✏️ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ዛሬ ይህን ሾርትከት ቫይረስ የምናጠፋበትን Tricks. እናካፍላችኋለን ተከታተሉን።
❑By using CMD❑
 cmd (command prompt) በመጠቀም
ይህ ዘዴ ከሁሉም የተሻለ ውጤታማ ሲሆን ለሀርድ ዲስኮች ለፍላሾች እንዲሁም ለሞባይል ስልኮች ያገለግለናል።
1. በመጀመሪያ cmd እንከፍታለን።
Win + R then we write Cmd ( run፦cmd፦enter)
2. cmd ከከፈትን በኋላ ለማጽዳት የምንፈልገው ፋላሽ ዳይሬክተሪ እንሄዳለን። ( ለምሳሌ ፍላሹ removable disk G ከሆነ G:\ ብለን እንጽፋለን።)
3. በመቀጠል ይህን ኮማንድ እንጽፋለን። G፡*.* /d /s -h -r -s (G ለምሳሌ ሲሆን እናንተ በራሳችሁ ፋላሽ ሆሄ ትቀይሩታላችሁ።)
4. አሁን ኢንተርን ስትጫኑ ከሾርትከት ቫይረስ ተገላገላችሁ ማለት ነው።
መረጃዎቹን ጠቃሚ ሆነው እንዳገኛችኋቸው ተስፋ እናደርጋለን።።
══════❁✿❁ ══════
        🗣➹share &Join Us
    ┗━ ••• ━ ••• ━━•••━━━┛
✅ #Technology_Abbreviatios እናቃቸዋለን❓ እስቲ ለዛሬ የተወሰኑትን እንያቸው...
*The most important words*
1.*PAN* - permanent account number.
2. *PDF* - portable document format.
3. *SIM* - Subscriber Identity Module.
4. *ATM* - Automated Teller machine.
5. *IFSC* - Indian Financial System Code.
6. *FSSAI(Fssai)* - Food Safety & Standards Authority of India.
7. *Wi-Fi* - Wireless fidelity.
8. *GOOGLE* - Global Organization Of Oriented Group Language Of Earth.
9. *YAHOO* - Yet Another Hierarchical Officious Oracle.
10. *WINDOW* - Wide Interactive Network
Development for Office work Solution.
11. *COMPUTER* - Common Oriented Machine. Particularly United and used under Technical and Educational Research.
12. *VIRUS* - Vital Information Resources Under Siege.
13. *UMTS* - Universal Mobile Telecommunications System.
14. *AMOLED* - Active-matrix organic light-emitting diode.
15. *OLED* - Organic light-emitting diode.
16. *IMEI* - International Mobile Equipment Identity.
17. *ESN* - Electronic Serial Number.
18. *UPS* - Uninterruptible power supply.
19. *HDMI* - High -Definition Multimedia
Interface.
20. *VPN* - Virtual private network.
21. *APN* - Access Point Name.
22. *LED* - Light emitting diode.
23. *DLNA* - Digital Living Network Alliance.
24. *RAM* - Random access memory.
25. *ROM* - Read only memory.
26. *VGA* - Video Graphics Array.
27. *QVGA* - Quarter Video Graphics Array.
28. *WVGA* - Wide video graphics array.
29. *WXGA* - Widescreen Extended Graphics Array.
30. *USB* - Universal serial Bus.
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ።