Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac
and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም
ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ
የሆነ
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል
ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን
ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው
የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር
ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና
የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ
ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል
እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም
የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
• ከመለዋወጫ አንፃር በሃገራችን Toshibaን የሚያክል
ላፕቶፕ የለም፡፡ከተበላሸ እና እክል ካጋጠመው
በተመጣጣኝ
ዋጋ መለዋወጫ ማግኘት ይቻላል፡፡ Acer ላፕቶፕም
የተሻለ
መለዋወጫ አለው፡፡
• ከጥራት አኳያ ደግሞ APPLEን የሚደርስ የለም፡፡ HP
እና
DELLም የተሻሉ ብራንዶች ሆነው መለዋወጫ ግን
እንደልብ
ማግኘት አይቻልም፡፡
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች 1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system) 2 የስክሪን መጠን (Screen Size) 3 ሲፒዩ(CPU) 4 ራም(RAM) 5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type) 6 የምስል ጥራት (Image Quality) 7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life) 8 ብራንድ (Brand) ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው? በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን…»
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት
1. ጥሩ አድማጭ መሆን
ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡
2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን
በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡
3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ
የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡
4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ
ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡
5. አቀማመጥን ማስተካከል
ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡
6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት
እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡
7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ
ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡
8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት
ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡
9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር
በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡
via ሥነ ልቡና - Psychology
❤1
#Basic_computer_Questions
1. The length of IP address is? Ans. 32 bits
2. Facebook was launched in? Ans. 2004
3. The docx file contains? Ans: MS Office Word
4. The file extension DLL stands for? Ans. Dynamic Link Library
5. The extension of a MS Access Database is? Ans. mdb.
6. The key combination used to permanently delete a file from Windows computer? Ans. Shift + delete
7. Shortcut Key to open a new document is? Ans. Ctrl + N
8. Data is permanently stored in? Ans. Hard Disk
9. What are the steps to upgrade a 32-bit version to a 64-bit version of Windows? Ans. It cannot be upgraded
10. To change a lowercase letter to uppercase and uppercase letter to lowercase select? Ans. Sentence Case
11. CSS stands for: Ans. Cascading Style Sheets
12. The general format of the URL is as follows: Ans. type: // Address /path /
13. The computer abbreviation “OS” stands for: Ans. Operating System
14. The shortcut key to delete a file without sending to recycle Bin is: Ans. Shift + Del
15. How many versions of Windows 8 for PC have been released? Ans. 3 versions
16. A group of 8 bits is called: Ans. Byte
17. To subscript a text, shortcut key is: Ans. Ctrl + <
18. The file extension .jsp stands for: Ans. Java Server Page
19. What is the full form of WWW? Ans. World Wide Web
20. The microphone converts the sound into: Ans. Electrical Signals
21. A device which connects multiple nodes to the network is: Ans. A hub
22. Windows 7 was released in which year?
23. What is Windows XP? Ans. An operating system
24. ATM stands for: Ans. Automated Teller Machine
25. Which one of these is used to find information on World Wide Web? Ans. Search Engine
26. “.gif” is an extension of which type of file? Ans. Image
27. Who is the founder of IBM Company? Ans. Thomas J. Watson
28. Volatile Memory is: Ans. Ram
29. When you delete an object, Windows XP sends it to: Ans. Recycle Bin
30. A folder in windows c can’t be made with the name: Ans. Con/Com1/Com2/Com3
31. Copying a software without purchasing it is _________ . Ans. Software Piracy
32. Ctrl + F2 shortcut is used for:
33. What is the use of Firewall in a computer? Ans. For security
34. What is the full form of ISO? Ans. International Standard Organization
35. A network that covers large area, city, country and World is called: Ans. WAN
36. The transfer of data from one place to another is called: Ans. Data Communication
37. Green wavy lines under text indicate? Ans. Grammatical Mistake
38. SQL is a : Ans. Structured Language
39. Windows 8 was released in which year? Ans. 2011
40. Which one is an Operating System? Ans. Windows Vista
41. A Terabyte represents about: Ans. 1 trillion bytes
42. The file extension PNG stands for: Ans. Portable Network Graphic File
43. The card which is used for internet: Ans. Modem Card
44. In Windows 10, what is the shortcut key to Open programs that are pinned to task bar? Ans. Windows + [1][2][3][…]
45. What is meaning of .mng? Ans. Multiple Network Graphic
46. Windows 7 is preceded by which version of the windows? Ans. Windows Vista
47. What is the name of new built-in browser includes in Windows 10? Ans. Super Internet Explorer Pro
48. Analog signal is measured in: Ans. Volts
49. In Windows 7, what is the shortcut key for creating a New Folder? Ans:Ctrl + Shift + N
50. What is the full form of TCP? Ans. Transmission Control Protocol
51. Arithmetic Logic Unit (ALU) can do: Ans. Logical Operation, Mathematical Operation
52. The total number of function keys in a computer keyboard are: Ans. 12
53. A bit can be _______ . Ans. 1 or 0
54. Which of the following protocol is used to access Webpages on World Wide Web? Ans. HTTP
55. Which of the following option is not true for FORTRAN? Ans. Translation
56. A network that covers small geographic area or single or group of buildings is called: Ans. LAN
57. Which one of the following is Internet Protocol? Ans. TCP/IP
58. The upper most bar showing the name of the application is called: Ans. Title Bar
59. Which of the following is the founder of Facebook? Ans. Mark Zuckerberg
60. Shortcut for Save as command is: Ans. F12
61. By
👍1
1. The major language of World Wide Web is
(A) HTML
(B) PHP
(C) ASP.NET
(D) Java
2. HTML is an abbreviation for?
(A) HiTech Meaningful Language
(B) HyperText Meaningful Language
(C) HiTech Markup Language
(D) HyperText Markup Language
3. ___________ is a device from where the information is sent.
(A) Transmitter
(B) Spreadsheet
(C) Simulation
(D) Modulation
4. __________ is a mathematical model of a real system in the form of a computer program.
(A) Transmitter
(B) Spreadsheet
(C) Simulation
(D) Modulation
5. LAN is an abbreviation for?
(A) Large Access Network
(B) Local Access Network
(C) Large Area Network
(D) Local Area Network
6. In peer-to-peer networking,
(A) there is only one server and many clients
(B) there is only one client and many servers
(C) every computer is capable of playing the role of server
(D) every computer is capable of playing the role of client, server or both at the same time
7. URL is an abbreviation for?
(A) Universal Resource Locator
(B) Uniform Resource Locator
(C) Universal Resource Location
(D) Uniform Resource Location
8. The network in which we connect each node to the network along a single piece of network cable is called
(A) Bus Network Topology
(B) Star Network Topology
(C) Ring Network Topology
(D) None of these
9. The network in which we connect each network node to a central device (hub) is called
(A) Bus Network Topology
(B) Star Network Topology
(C) Ring Network Topology
(D) None of these
10. FTP is an abbreviation for?
(A) File Transfer Position
(B) File Transfer Protection
(C) File Transfer Protocol
(D) File Transfer Possibility
ANSWERS: MCQS
1. A
2. D
3. A
4. C
5. D
6. D
7. B
8. A
9. B
10. C
👍1
Important_Abbreviations
*Kbps* Kilobits Per Second
*LAN* Local-Area Network
*LCD* Liquid Crystal Display
*LED* Light Emitting Diode
*LPT* Line Printer
*LPT1* First Parallel Printer Port
*LPT2* Second Parallel Printer Port
*MP3* MPEG Player lll
*MP4* MPEG Player IV
*Mbps* Megabits Per Second
*Microsoft* Micro Computer Software
*MPEG* Motion Picture Experts Group
*NTFS* New Technology File System
*OCR* Optical Character Readers
*OMR* Optical Mark Reader
*OS* Operating System
*PDF* Portable Document Format
*PNG* Portable Network Graphics
*POST* Power On Self-Test
*PPM* Pages Per Minute (Generally refers to the Speed of a Printer)
*PS/2* Personal System/2
*RAM* Random Access Memory
*RGB* Red Green Blue
*ROM* Read-Only Memory
*RTF* Rich Text Format
Founders and their INVENTIONS !!
Founder of Apple Computers – Steve Jobs
Founder of Artificial Intelligence – John McCarthy
Founder of Bluetooth – Ericsson
Father of Computer – Charles Babbage
Father of ‘C’ Language – Dennis Ritchie
Founder of Email – Shiva Ayyadurai
Founder of Google – Larry Page and Sergey Brin
Founder of Internet – Vint Cerf
Father of ‘Java’- James Gosling
Father of JQuery – John Resig
Founder of Keyboard – Christoper Latham Sholes
Founder of Linux – Linus Torvalds
Founder of Microsoft – Bill Gates and Paul Allen
Founder of Mobile Phones – Martin Cooper
Founder of Mouse – Douglas Engelbart
Founders of Oracle – Ed Oates, Larry Ellison, Bob
Miner
Founder of Php – Rasmus Lerdorf
Founder of USB – Ajay V.Bhatt
Founder of WWW – Tim Berners-Lee
Founder of Yahoo – Jurry Yang and David Filo
በአንድ ቀን ብቻ በኢትዮጵያ 1 ሺህ 652 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 22 ሺህ 252 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 652 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የዛሬው ውጤት በሀገሪቱ በአንድ ቀን ብቻ የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር ሆኗል።
ይህንን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 ሺህ 894 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመልክተዋል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ17 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 509 ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት 199 ሰዎች በፅኑ መታመማቸውንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
📌 የምርጦች ምርጥ አፕሊኬሽን ዝርዝር....
🔰Es File Explorer - ምርጥ አስፈላጊ File Explorer አፕ
🔰Mx player pro - ምርጥ ቪዲዮ ማጫወቻ
🔰Musicolet - ምርጥ Audio ማጫወቻ
🔰Avast Premium - ምርጥ Anti-Virus App
🔰CCleaner pro - ምርጥ Junk Remover (Blackhat ሀከሮች ይጠቀሙታል)
🔰B16 - Best Selfie App
🔰App Locker - ምርጥ አፕ መቆለፊያዎች
🔰CM security pro- ምርጥ የደህንነት አፕ
🔰Brave Browser - ምርጥ Browser ከChrome የተሻለ
🔰Bluemail - ምርጥ ኢሜይል አፕ
🔰Vyper VPN - ምርጥ VPN app
🔰ADM Pro - ምርጥ Download Manager
🔰Vidmate - ምርጥ ቪዲዮና ኦዲዮ ማውረጃ
🔰SHAREit - ምርጥ ፋይል መላላኪያ (ከዜንደር ይበልጣል)
🔰Smart Kit 360 - ከ36 በላይ አፖችን በ10mb ብቻ የያዘ ገራሚ አፕ
🔰Telegraph - ምርጥ የቴሌግራም Unofficial አፕ
🔰Aero WhatsApp - ምርጥ የWhatsapp Messenger App
🔰GB Instagram - ምርጥ የኢንስታግራም App
🔰Speedify - ምርጥ የኢንተርኔት ፍጥነት መጨመሪያ app
🔰WPS Office - Pdf,DOCX,..በአንድነት ማንበቢያ
🔰Fyn Geez - ምርጥ ኢትዮጵያዊ Keyboard App
🔰FBlite 2020 - ምርጥ Facebook Lite App (Dark Mode አለው)
Like & Share
ምንጭ Galaxy tech solution
👍3❤1
computer.shortcut.keys.app.apk
5.2 MB
ሙሉ keyboard shortcut keys በማውረድ ስልካችሁ መጫን ትችላላችሁ
👍4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 10 ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 12 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 10 ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ።
- ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር
- ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
- ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
- ታከለ ኡማ፤ የማዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር
- ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
- ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
- ንጉሡ ጥላሁን፤ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር
- እንደአወቅ አብቴ፤ የብረታ ብረት ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
- ፍቃዱ ጸጋ፤ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
- ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ
❤2👍1
ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል? እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን።

1. Power option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

2.Disable unwanted start up programs

ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል

Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።

3.Defragment and optimize drive Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ

4. Delete unnecessary temporary file Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

5. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

6. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

7. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

8. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ
👍1😁1
🍡የዘመናዊ ኮምፒዉተር አፈጣጠርና እድገት አጭር ታሪክ

🍢1950ዎቹ - በ "ቫኪዩም ቲዩብ" ብቻ ይሰሩ የነበሩት ኮምፒዉተሮች መጠናቸዉ የአንድ ቤት መጠን እስኪያክል ድረስ እጅግ ግዙፍ የነበሩ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ እጅግ ቀርፍፍ ነበሩ። በወቅቱ እነዚህን ኮምፒዉተሮች በብቸኝነት ይጠቀምባቸዉ የነበረዉ የአሜሪካ ሚሊቴሪ ተቋም ሲሆን ዋጋቸዉም የትም የሌለ ነበር።

🍢1960ዎቹ - በትራንዚስተሮች መፈጠር የተነሳ ቀርፍፍዉን የ"ቫኪዩም ቲዩብን" አሰራርን በመቀየር የኮምፒዉተሮች የአካል መጠን መቀነስ ሲቻል ብቃታቸዉንም ማሻሻል ተቻለ። በዚህ ወቅት ነበር ሜይንፍሬም (mainframe) የተባሉ ፈጣንና ወድ ኮምፒዉተሮች ተፈጥረዉ ከማሊቴሪና የመንግስት ተቋም አልፎ ለግል ድርጅቶች ጥቅም መዋል የጀመሩት።

🍢1970ዎቹ - በመቶዎች የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮችን ያካተተ ኢንቴግሬትድ ሰርኪዩት "Intergrated Circute Board" አንድ ክፍልን ሊሞላ የሚችል መጠን ያለዉን የሜይንፍሬም ኮምፒዉተር አሳንሶ በጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ ኮምፒዉተር "Desktop" እንዲፈጠር አስቻለ።

🍢1980ዎቹ - በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮች እጅግ በጣም ትኝሽ መጠን ባለዉ የኮምፒዉተር ቺፕ ዉስጥ ህያዉ መሆን የኮምፒዉተር በጣም አንሶ በአንዲት ቦርሳ ዉስጥ የሚገባና ከድርጅት አልፎ ለግል ጥቅም መዋል የሚችልበት "Personal Computer (PC)" ዘመን ተወለደ። ኮምፒዉተሮች ጠረጴዛ ላይ ከመቀመጥ አልፈዉ ጭን ላይ የሚቀመጡበትን መጠን ይዘዉ "laptop" በሚል ስያሜ ብቅ አለ።

🍢1990ዎቹ - የኢንተርንት መወለድ ኮምፒዉተሮች እርስ በእርሳቸዉ እና በሌላ ቦታ ከሚገኝ ከፍተኛ አቅምና የመረጃ ብዛት ያለዉ የኮምፒዉተር ስብስብ "datacenter" ጋር ተገናኝተዉ ከዚህ ቀደም በራሳቸዉ አቅም ብቻ ከሚሰጡት አገልግሎት እጅግ የላቀ ጥቅምን በፍጥነት መስጠት እንዲችሉ አደረገ።

🍢2000ዎቹ - ለእጃችን መዳፍ እንኳን የማይሞሉ፣ ነገር ግን ብቃታቸዉ ከአንድ መጠኑ ከፍ ካለና ምርጥ ከሚባል ኮምፒዉተር ያልተናነሰ ተግባር ማከናወን የሚችሉ እንደ ረቀቀ ስልክ (Smartphone) ያሉ ተንቀሳቃሽ ቁሶች (mobile devices) በስራ ላይ ዋሉ። ከስልኮችም አልፈዉ ታብሌቶቻችን፣ ሰዓቶቻችን፣ የቤት ቁሶቻችን፣ መኪናዎቻችን እና ልብሶቻችን ሳይቀሩ የኮምፒዉቲንግ ብቃት እየተካተተላቸዉ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ ይህ ዘመን አብሮን ባለ ኮምፒዉተር ላይ ብቻ ከመደገፍ ይልቅ እንደ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ (Cloud computing) እና የመሴሰሉት የተራቀቁ በኢንተርኔት ተገናኝተዉ መሰራት የሚችሉ እና ከእኛ ርቀዉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተበታትነዉ በሚገኙ እጆግ ፈጣን ኮምፒዉተሮች አማካኝነት በርካታ ተግባር ማከናወን ተቻለ። ቀደም ሲል እንደተጠቀሰዉ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ ማለት የኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች ሶፍትዌርኝ፣ ሃርድዌርን፣ መረጃን አና የተለያዩ ዲጂታል አሠራሮችን በራሳቸዉ ኮምፒዉተር ላይ ከመጫን ይልቅ ካሉበት ሰርቨሮች በኢንተርኔት አማካኝነት በየትኛዉም ጊዜና ቦታ ልክ መቦራትና ዉሃ ቤታችን ድረስ እንደሚመጣዉ ከአገለግሎት ሰጪዎች ላይ በሚፈልጉት መጠን መጠቀም የሚያስችል አሠራር ነዉ።

ይህ ሁሉ ፈጽሞ የበቃ በማይመስልበት ሁኔታ የኮምፒዉተር እድገትና ፍጥነት ሩጫዉን ቀጥሏል። ከላይ የተጠቀሰዉን አስደናቂ የኮምፒዉተር የለዉጥ እድገት ህያዉ ያደረገልን የMoore's Law ወደ ፍጻሜ እየመጣ ያለ ይመስላል።
ምክንያቱም የትራንዚስተሮች እጅግ አናሳ በሆነ መጠንና በጣም በተጠቀጠቀ ሁኔታ በአነስተኛ ቦታ ላይ እንዲያርፉ የሚደረግበት የቺፕ አሠራር የመጨረሻ ገደቡና ጥጉ ላይ እየደረሰ ስለመጣ ነዉ። አንድን ትራንዚስተር ምንም ያህል እናሳንሰዉ ብንል ከአቶሚክ መጠን በታች ልናደርገዉ አንችልም። ይህ ሂደት ወደ ፍጻሜዉ እየተቃረበ የመምጤቱን ጉዴይ ባለሞያዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና አምራቾችም ይስማሙበታል። የትንቢቱ ባለቤት ጎርደን ሙር እራሱ በ2015 ዓ.ም. በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ከ50 ዓመታት በፊት የተነበየዉ Moore's Law ማክተማያዉ እየተቃረበ እንደመጣ ጠቁሟል።

ኮምፒዉተር እስከዛሬ በዚህ አይነት የረቀቀ የእድገት ሂደት ዉስጥ ካለፈ፣ "ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?" የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮ ይመጣል።

🍢 "ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?"

በእርግጥ ቀጣዩቹ ኮምፒዉተሮች ምን አይነት ይሆኑ ይሆን? የወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች በጨረር፣ በኳንተም የፊዚክስ ህግ እና በሰዉነታችን ዉስጥ በሚገኙ በዲኤንኤ አማካኝነት የሚሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም በማንኛዉም ቁስ ላይ ተለጥፈዉ የሚገኙ፣ ወይም ደግሞ የራሳችን ኮምፒዉተር ሳያስፈልገን በሌላ ቦታ ተቀምጠዉ በኢንተርኔት አማካኝነት ያላቸዉን አቅም ሙሉ በሙሉ ከፈለግነዉ ቦታ ሆነን መጠቀም የምንችልባቸዉ አይነቶችም ሊሆኑ ይችላሉ።

የፋይበር ኦፕቲክስ "Finer-optic" ወይንም በጨረር አማካኝነት መረጃን ከአንድ ኮምፒዉተር ወደ ሌላዉ በፈጣን ሁኔታ በማስተላለፉ አሰራር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በፋይበር ኦፕታክስ የሚተላለፉ መረጃዎች በኤሌትሪክ ሽቦ ዉስጥ ከሚተላለፉት ፍጥነታቸዉ በእጅጉ የተሻለ ሲሆን፣ በተጨማሪም እንደ ኤሌክትሮማግኔቲክ ያሉ የተለያዩ ጣልቃ ገብ ግብዓቶች አሠራሩን አያደናቅፉትም ። ታድያ ለምን ከኤሌትሪክ ትራንዚስተር ይልቅ በጨረር የሚሰራ ኮምፒዉተር መስራት አይቻልም? ይህን ማድረግ ከተቻለ የኮምፒዉተሮችን የዉስጥ የመረጃ አቀማመር አቅም እጅጉን እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል። ምንም እንኳን ተመራማሪዎች በዚህ ዙርያ ተስፋ ሰጪ የሙከራ ስራዎች ቢያከናዉኑም መጠኑ ያነሰና በብዛት ተመርቶ በኮምፒዉተሮች ዉስጥ ሊገጠም የሚችልን በጨረር የሚሠሩ ቺፕ ህያዉ ለማድረግ ሙሉ ስኬትን እስከአሁን አላገኙም።

በጨረር አማካኝነት የሚሰሩ ኮምፒዉተሮችን ለመፍጠር በሚደረገዉ ምርምር የኢትዮጵያዉ ዶክተር ሰለሞን አስፍ እጅ አለበት። ዶክተር ሰለሞን የበርካታ ፈጠራ ስራዎች ባለቤት ሲሆን በዋናነት የሚታወቅበት የፈጠራ ስራዉ በተለመደዉ አሠራር በኤሌትሪክ ከሚሰሩ ትራንዚስተሮች ይልቅ ኮምፒዉተሮች በብርሃን ጨረር (optical pulse) አማካኝነት መረጃን ለማስላት የሚችሉበትን ሙከራ ያደረገበት የምርምር ስራዉ ነዉ። ይህ ግኝት ለወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች አሁን ካሉት ማሽኖች እስከ አንድ ሺህ እጥፍ ፍጥነት እንደሚሰጣቸዉ ሲጠበቅ፣ የኤሌክትሪክ ፍጆታንም በእጅጉ ይቆጥባል ተብሏል። የዶክተር ሰለሞን ዋና ግኝት ፎቶዲቴክተር (photodetector) የሚባሉትና የብርሃን ጨረር መልዕክትን (optical signals) አጉልተዉ የሚያስተላልፉ ቁሶች (በሞያዊ አጠራራቸዉ "amplifiers") እንዴት አድርገዉ መልዕክትን ለማይክሮፕሮሰሰሮች በሚገባ መንገድ በማስተላለፍ ጨረር መልዕክቶችን ወደ ኤሌክትሪክ መልዕክት (electrical signals) በመቀየር ለኮምፒዉተር አሰራር ጥቅም እንዲዉሉ ማድረግ ነዉ።
ምንጭ ዶትኮም ቲቪ ሾው
👍1
ከዚህ በፊት በVPN ሲሰሩ የነበሩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ማለትም ቴሌግራም፣ ፌስቡክ.... የመሳሰሉ በማለው ኢትዮጵያ በሚባል ደረጃ ያለ VPN መስራት ጀምረዋል። በስልክዎ ላይ Install ያደረጉትን VPN Disconnect በማድረግ ካላስፈላጊ ወጪ ያዳኑ!!
💥ስልካችሁ📲 ላይ #አፕልኬሽን ስትከፍቱ :⬇️⬇️⬇️

🌟This Application Stopped Working‼️
🌟Crashing‼️
🌟Won’t open‼️
🌟Won’t respond‼️
🌟Isn’t working properly‼️

🔆እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ⬇️

1⃣.#Restart እና #Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።👍

⚠️ስልካችሁን?? #Restart አድርጉት።

⚠️Setting➡️ Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን📲 Operating System #Update አድርጉ።

⚠️_Playstore ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።

2⃣.*Update Google Play Services *

⚠️ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።

3⃣. አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ *Setting* ውስጥ ገብታችሁ #Forced\Stop አድርጉት።

⚠️System App ካልሆነ #Uninstall❌ ያድርጉት።

4⃣. Clear App and Cache ይሞክሩ።

⚠️Setting➡️ Manage apps➡️ ያስቸገራችሁን አፕ➡️ Clear Data and Clear Cache.

5⃣. እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች📲 ይስተካከላሉ?? ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል።

⚠️ኮፒ ስልኮችንና ብዙ ጊዜ Hard Reset የተደረጉ ስልኮችን አይጨምርም‼️ እነሱ ስልኮች📲 ሌላ ታሪክ ውስጥ ናቸው።😁

⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ

ምንጭ :- wsa computer solution
የወደዳችሁት ሁሉ ሼር እያደረጋችሁ ለወዳጅዎ #ያጋሩ እኛንም ያበረታቱን !
✏️ጥናታዊ ጽሑፍ ለምታዘጋጁ # ተመራቂ ተማሪዎች ስለምትሠሩት Proposal እና Research ትንሽ እገዛ
እንዴት ናችሁ? በመጀመሪያ ደረጃ የሚመርጡት የጥናት ርዕስ መነሻውና መድረሻውን ሥነፍኖት በትክክል የተረዱትን መሆን ይገባዋል። ጥናታዊ ጽሑፍ መጨረሻ መታወቅ ያለበት ውጤቱ ነው እንጂ ሂደቱ መሆን የለበትም። ህደቱን ገና ከመጀመሪያው በትክክል እና በግልጽ (Accurately and clearly) መረዳትና ማወቅ ለውጤታማነት ተገቢ ነው። የጥናቱ ንድፈ ሀሳብ (Proposal) በሚገባ የሚመራ መንገድ መሆን አለበት። ጥናትን በተመለከተ ምሁራኑ የሚሉትን አንድ ታላቅ ገለፃ ላስታውሳችሁ "A research is as good as its propsal" -(የአንድ ጥናት ጥሩነት እንደ ንድፈ ሀሳቡ/ዕቅዱ/ ጥሩነት ይታወቃል) እንደማለት ነው። በመሆኑም የተወሰነ ምክረ ሃሳብ እገዛ ለማድረግ ጥቂት ነገር ላስታውሳችሁ። ልብ ሊባል የሚገባው ግን የግል ድጋፍ እንጂ የተቋም ይፋዊ format እያሳወቅሁ አለመሆኑን ነው።
.
#1ኛ. #Title ፦ ርዕስ ለመመረጥ የመጀመሪያው ትኩረት ከሙያዎት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ያስተውሉ። ከዚህ ባለፈ ሙያዎትን ተጠቅመው በአካባቢዎ ባለው ማህበረስብ ውስጥ ያለውን ችግር በመፍታት አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉበት ቢሆን ይመረጣል። ከዚህ አንጻር "ይህንን አይነት መፍትሔ ብሠራለትስ" የሚሉትን ችግር መርጠው አጭር እና ገላጭ የሆነ የጥናት ርዕስ መምረጥ ነው። ከተቋሙ አካባቢ ወጣ ያሉ ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ርዕሶች መሆንም ይችላሉ።
.
#2ኛ. #Introduction_to_your_title ፦ በዚህ ርዕስ ሥር ስለ ጥናቱ ርዕስ ምንነት ገለጻ ማድረግ ነው። በዚህ ርዕስ ሥር የሚያካትቷቸው ይዘቶች defnitions, theories, materials used, tests, methods, constructions systems, types, ..... የመሳሰሉት ቢሆኑ መልካም ነው።
.
#3ኛ. #Background_to_your_title ፦ ይህ ደግሞ ስለሚያጠኑት ጥናት ታሪካዊ ዳራ/አመጣጥ (hisorical status) ገለጻ ማድረግ ነው። [who start investigate first, which country use, improvement (ማን ጀመርው? የት ቦታ? መቼ? በምን ተጀምሮ ወዴት ተሻሻለ all improvements፣ አሁን የት ደረሰ፣ .....) የሚሉትን የርዕሳችሁን ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስካለበት ድረስ ብቻ የምታስቀምጡበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ እርስዎ ሊጨምሩበት ወይም ሊቀይሩት ወይም ሊያስተካክሉት የሚችሉበትንም ጎን ጠቆም ማድረፍ መልካም ነው።
.
#4ኛ. #Statement_of_the_problem ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው።
.
#5ኛ. #Objectives {General and Specific}፦ ጠቅላይ/ዋና ዓላማ ከአንድ ዓረፍተ ነገር ባይበልጥ ከበዛ ደግሞ ከሁለት በላይ እንዳይሆንይመከራል። በዝርዝር ዓላማ (specific objectives) የሚቀመጡት ደግሞ በዋና ዓላማ ዉስጥ የሚገኙ በጥናቱ መከናወን የሚታወቁ የተለያዩ መልሶችን ታስቀምጣላችሁ።
.
#6ኛ. #Scope_of_the_Research ፦ ይህ የሚገልጸው የጥናትችሁን ስፋተ-ሜዳ ነው። ምን ምን እንደሚያጠቃልል ወይም እንደሚዳስስ፣ ምን ምንን ደግሞ እንደሚተው /እንደማያጠቃልል/ ከነምክንያቱ፣ ለምን አይነት ተግባር የሚውል እንደሆነ ... በአጠቃላይ የጥናቱን መጠነ-ስፋት ወይም ይዘት የሚያስረዳ ይሆናል።
.
#7ኛ. #Litrature_review ፦ [በርዕሱ ዙሪያ እስካሁን የተጠኑ ጽሁፎች ምን ብለዋል?] “ማን የተባለው ሰው በየትኛው መጽሐፉ/ጥናቱ የትኛው ገጽ ላይ ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን ምን ብሏል?“ የሚለውን መረጃ የያዘ ነው። በ"Litrature" ሥር የሚያካትቱት የቀደሙ ህትመቶች ማስረጃ ከእርስዎ ጥናት ጋር ተያያዥ ሀሳብ ያላቸውን ብቻ ነው። እርስዎ የማይዳሡትን ነገር በዚህ ርዕስ ሥር ማስገባት ከማንዛዛት እና ትርጉም አልባነት አያልፍም፣ ይልቁንም ሥራዎትን ውጤት (value) እና ተቀባይነት (acceptance) ሊያሳጣ ይችላል። በዚህ ሥር የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች reference specification [books, quastionary, journals, published apers, recorded interviews, vedio evidences] መሆን አለባቸው እንጂ guide specification [oral speeking, internet notes, handouts, non published documents] ላይ ያገኙትን ነገር ባይጠቀሙ ይመከራል። የተጠቀሙትን ምንጭም ከነመገኛ ገፁ አብረው ዋቢ ማስቀመጥም ተገቢ እና ግዴታ ነው።
.
#8ኛ. #METHODOLOGY ፦ ይህ ደግሞ ዋናው የጥናት ሂደት መረብ ነው። ትናቱ የሚከናወንበት አካባቢ (study area)፣ ናሙና የሚወሰድበት የናሙና አወሳሰው ሥነዘዴ - ሥነዘዴው የተመረጠበትን ማስረጃ ምክንያት ጨምሮ (sampling system)፣ ከንድፈ ሀሳብ እስከ ፍጻሜ ያለውን የሚያሳይ የጥናቱ መነሻና መድረሻ ፍሰት (research deign - ብዙ ጊዜ በ"Chart" ሊገለፅ ይችላል) መካተት አለባቸው። ከዚህ በተጨማሪ ቤተሙከራዊ ጥናት (Experimental research) ከሆነ የተለያዩ የቤተሙከራ ፍተናዎች (laboratory tests) የሚሠሩበት ስለሆነ የሚሰሩት ሙከራዎች (tests) የሚያስፈልጉ መሥሪያ ነገሪች (materials), መሥሪያ መሳሪያዎች (equipments), የሙከራ ሂደቶች (procedures to be used) የሚሉት ይዘቶች በግልፅ መታወቅ አለባቸው።
ከቤተሙከራ ውጪ ከሆነ ደግሞ አንዳንዶቹ ተግባራዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፍልስፍናዎች ስለሆኑ የሚጠቀሙትን ሂደት ማስቀመጥ ተአቢ ነው። (ምሳሌ ~ መኪና መሥራት፣ በፀሀይ ጉልበት የሚሰራ ባቡር መሥራት ሊሆን ይችላል)።
በሌላ በኩል Theoretical or statistical data analaysis ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች ከሆኑ ደግሞ የሚጠቀሟቸው የቃለመጠይቅ ጥያቄዎች (interiview questions)፣ የሚያስሞሉት የሰነድ ጥያቄ (questionair formats for data statistics)፣ የሚጠቀሟቸው የኮምፒዉተር ፕሮግራም (softwares to be used)፣ የሚፈልጉት ስታቲካዊ መረጃ (statistic data)፣ የሚሳተፉት ባለድርሳዎች (participants /responsible bodies)፣ የጥናት ማመዛዘኛ መንገድ (analaysis statics method..) የመሳሰሉትን ማካተት ተገቢ ሲሆን ይህ "Methodology" የሚባለው ክፍል አንድ ሰው በየትኛው ሥነዘዴ እንደሠራ የክንውን ሂደቱን የሚያስቀምጥበት ክፍል ነው።
❖አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

✠A) ማውጫ (Table of contents)

ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡ ማውጫ ሁሉንም ምዕራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

✠B) አጭር መግለጫ (Executive Summary)

ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው ሃሳቦች
☞ ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር
☞ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ
☞ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ
☞የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ
☞ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም
☞ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡

✠C) መግቢያ (Back Ground)

ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-
☞ ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ
☞ ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው
☞ ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡

✠D) ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale)

ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ
ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡

✠E) የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective)

ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ
ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡

✠F) የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description):-

☞ የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ
☞ ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ
☞ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት
☞ የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት
☞ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ አለበት፡፡

✠G) የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization):-

☞ ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ
☞ የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር
☞ የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡

✠H) የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮችና ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries):-

☞ ተጠቃሚዎች (Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡
☞ ያገባኛል ባዮች (stakeholders):-
የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (Primary stake holders)፡-በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡

✠I) የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation):-

የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው በማን፤ እንዴት፤ መቼና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡

✠J) ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption):-

☞ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡
☞ ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡

✠K) ክትትና ግምገማ (Monitoring and Evaluation):

ይህ ርዕስ የሚይዛቸው፡-
☞ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት እንደሚቀርብ
☞ የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት
☞ የግምገማ ዕቅድን
☞ ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ

✠L) የፕሮጀክቱ ቀጣይነት (sustainability):

ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡
የወደዳችሁት ሁሉ ሼር እያደረጋችሁ ለወዳጅዎ #ያጋሩ እኛንም ያበረታቱን !
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ
https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ሾለ
ዚህ ፔጁን 👍#ላይክ 👉#ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።