Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
የኮምፒዉተራችን storage space ሲሞላብን እንዴት ማስለቀቅ እንችላለን
የኮምፒዉተርዎ storage space ሞልቶበት ተቸግረዋል፡፡ እንግዲያዉስ የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ
1. Windows Disk Cleanup
ለብዙዎች እፎይታን የሰጠ tool ሲሆን የኮምፒዉተራችንን ስቶሬጅ የሞሉብንን የተለያዩ ፋይሎች በማጥፋት ብዙ ትርፍ storage space እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ኮምፒዉተራችን ላይ የማንጠቀምባቸዉ እና የማይጠቅሙን ጊዜያዊ ፋይሎችን (temporary files) በማጥፋት ኮምፒዉተራችን ላይ ብዙ ቦታ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡
Windows Disk Cleanup ለመጠቀም የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Computer window (Start -> Computer)
2. hard-drive ላይ Right-Click በማድረግ ‘Properties’ የሚለዉን መምረጥ
3. ‘General’ tab ዉስጥ ‘Disk Cleanup’ የሚለዉን click ማድረግ
4. Windows scan አድርጎ ምን ያህል ቦታ ማስለቀቅ እንደምንችል ያሳዉቀናል
5. ከ drive ላይ ማጥፋት የምንፈልጋቸዉን ፋይሎች መርጠን ok ማለት
2. የማንጠቀምባቸዉን ፕሮግራሞች Uninstall ማድረግ
አብዛኞቹ ኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች የኮምፒዉተራቸዉን ቦታ የሚያጣብባቸዉ የጫኗቸዉ ሶፍትዌሮች እና ጌሞች ናቸዉ፡፡ የማንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮች Uninstall በማድረግ ቦታ መቆጠብ እንችላለን፡፡ ከኮምፒዉተሮ ላይ የማይፈልጉትን ሶፍትዌር ለማጥፋት የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Start -> Control Panel -> Uninstall a program
2. ብዙ ቦታ የያዘዉን ሶፍትዌር ለማወቅ በ size ቅደም ተከተል ይደርድሯቸዉ፡፡
3. ማጥፋት የፈለጉትን ሶፍትዌር መርጠዉ Uninstall የሚለዉን ይጫኑ፡፡
3. የተደጋገሙ ፋይሎችን ያጥፉ
ዊንዶዉስ በራሱ የተደገሙ ፋይሎችን ለይቶ የሚያጠፋ ሲስተም የለዉም ስለዚህ ይህንን ስራ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህንን የሚያደርጉ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ Duplicate Sweeper አንዱ ነዉ፡፡ Duplicate Sweeper ኮምፒዉተራችን ላይ ያሉ የተደጋገሙ ፋይሎችን scan አድርጎ ያቀርብልናል፡፡ እኛም ከዘ ዉስጥ የተደገሙ መሆናቸዉን እያረጋገጥን ማጥፋት እንችላለን፡፡
4. ጊዜያዊ ፋይሎች (Temporary Files)
በ Windows Disk Cleanup አማካኝነት ጊዜያዊ ፋይሎችን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አይተናል፡፡ ነገርግን Windows Disk Cleanup ሊያገኛቸዉ የማይችሉ እንደ browser ያሉ የጫንናቸዉ ሶፍትዌሮች የፈጠሩትን ጊዜያዊ ፋይሎች ለማጥፋት የሚያስችለን ሌላ መንገድ Google Chrome ን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ እናያለን፡፡
1. Google Chrome ን ይክፈቱ
2. settings menu ይክፈቱ
3. More tools የሚለዉን ይምረጡ
4.Clear Browsing data የሚለዉ ዉስጥ በመግባት ማጥፋት የሚፈልጉትን ጊዜያዊ ፋይል
መርጠዉ ያጥፉ
5. Recycle Bin ዉስጥ ያሉ ፋይሎችን ያጥፉ
ከኮምፒዉተራችን ላይ ያጠፋናቸዉ ፋይሎች permanently delete ካላደረግናቸዉ መልሰን ብንፈልጋቸዉ ማግኘት እንድንችል Recycle Bin ዉስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ከላይ ባሉት መንገዶች ያጠፋናቸዉ ፋይሎችም Recycle Bin ዉስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ Recycle Bin ያሉ ፋይሎች ግን ከኮምፒዉተራችን ላይ የያዙትን storage space እንደያዙ ነዉ የሚቆዩት፡፡ ስለዚህ storage space ለማስለቀቅ እነዚህን የማንፈልጋቸዉ ፋይሎች ከRecycle Bin ዉስጥ ማጥፋት ይኖርብናል፡፡
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ!
👉#ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፔጁን 👍#ላይክ 👉#ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።
1👍1
useful information
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1382 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ ሰባት (17) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ ስልሳ ሁለት (162) ደርሷል፡፡
#የታማሚዎች_ዝርዝር_ሁኔታ
ታማሚ 1 - የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአ/አ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ የስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው።
ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 3 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 4 - የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 5 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 6 - የ65 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 7 - የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአ/አ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።
ታማሚ 8 - የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታ አፋር (የተገኘው አ/አ) ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 9 - የ50 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 10 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 11 - የ53 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአ/አ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው።
ታማሚ 12 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 13 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 14 - የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 15 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 16 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 17 - የ41 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
👍1
ለቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት
*********
የዩኒቨርሲቲያችን አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት
ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ ለሁሉም ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት አሰጣጥን በተመለከተ ዛሬ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ተማሪና መምህር ፊት ለፊት ተገናኝተው መማር ማስተማሩ ወደ ክፍል እስኪመለስ እና ከኮረና ቫይረስ (COVID-19) ስጋት ነፃ እስክንወጣ ድረስ የተስተጓጎለውን ትምህርት አማራጭ መንገዶችን ተጠቅሞ ማስኬድ እንደሚገባ በአገር ዓቀፍ ደረጃ መወሰኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ባላችሁበት ሁሉ ሰላምና ጤና አብዝተን የምንመኝላችሁ ውድ ተማሪዎቻችን የሚከተሉትን ተግባራት እንድታደርጉ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
*
1ኛ. የቅድመ ምረቃ (የመጀመሪያ ዲግሪ) መደበኛ ተማሪዎች የተጫኑና ወደፊትም የሚጫኑ የትምህርት መርጃዎችንና መጻሕፍቶችን በ <National Academic Digital Library of Ethiopia> ድረ ገፅ
http://ndl.ethernet.edu.et የምታገኙ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አብዛኞቹ መማሪያ ቁሳቁሶች (Course materials) ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገፅ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ስለተጫኑ ተማሪዎቻችን እየገባችሁ በማውረድ (Download በማድረግ) ማንበብ አለባችሁ፡፡
ሳትዘናጉ የተጫነላችሁን(upload የተደረገላችሁን) የኮርስ መማሪያዎች (materials) በትክክል ካጠናችሁና ካነበባችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲያችሁ በምትመለሱበት ሰዓት የአጭር ጊዜ ማካከሻ ትምህርት ተሰጥቷችሁ ለፈተና የምትቀርቡና ተመራቂዎች ለምረቃ፣ ሌሎቻችሁ ወደ ቀጣዩ ደረጃ (ዓመት) ትሸጋገራላችሁ፡፡
2ኛ. የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በ <microsoft teams> ወይም <zoom> ከአማካሪዎቻችሁ ጋር እየተገናኛችሁ የመመረቂያ ፅሁፎቻችሁን እንድታጠናቅቁ እያሳሰብን በርካታ የመመረቂያ ጽሑፍ ናሙናዎችን (samples) በ < National Academic Digital Repository of Ethiopia> ድረ ገፅ https://
nadre.ethernet.edu.et/ የምታገኙ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በተጨማሪም እንደ ኢሜይል፣ ቴሌግራም፣ ስካይፒ፣ ዋትስ አፕ፣ ቫይበርና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ዘዴዎችን ተጠቅማችሁ የምርመር ስራዎቻችሁን መስራት ይኖርባችኋል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ በተገቢው መንገድ ጥናታዊ ፅሁፋችሁን ከአማካሪዎቻችሁ ጋር እየተወያያችሁ ጨርሳችሁ የቃል ፈተና በቴክኖሎጂ (online) የምታቀርቡ ሲሆን የዚህ ዓመት ምረቃ መርሃ ግብራችን የተጠበቀ መሆኑን ማስታወስ እንወዳለን፡፡
ኮርስ ያልጨረሳችሁ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በ <microsoft teams> ወይም <zoom> በኦንላይን ከመምህራኖቻችሁ ጋር በመገናኘት የመማሪያ መረጃዎችን (course materials) የምታገኙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
3ኛ. የተከታታይ ኘሮግራም ተማሪዎች ባላችሁበት ሆናችሁ ከአሁን በፊት የወሰዳችሁትን የኮርስ መማሪያ (course materials)፣ ያልወሰዳችሁ ደግሞ በክፍል ተወካዮቻችሁ አማካይነት ከመምህራን፣ ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ኮሌጅ ዲኖች እንዲሁም ከተከታታይና ርቀት ኘሮግራሞች ዳይሬክቶሬት ጋር እየተመካከራችሁ ሞጁሎቻችሁን እና መማሪያ ፅሁፎችን በመውሰድ እንድታጠኑ እንዲሁም ከላይ በተራ ቁጥር 1 በተገለጸው መሠረትም ማቴሪያሎችን በማውረድ እንዲትጠቀሙ እያሳሰብን የአጭር ማካካሻ ትምህርት ተሰጥቷችሁ፣ ፈተናዎችንም ወስዳችሁ ወደ ቀጣዩ ሴሚስቴር የምትሸጋገሩ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማስታወሻ፡
::::::::::::::::::::::
ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጡ አቅጣጫዎችንም ሆነ ዩኒቨርሲቲያችን አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩት ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ድረ ገፅ እና ፌስቡክ አድራሻችን የምንገልፅ ይሆናል፡፡
ድረ ገፅ፡
www.uog.edu.et
ፌስቡክ፡
@TheUniversityofGondar
*******
**
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት
ሚያዚያ24/2012 ዓ.ም
👍2
በኢትዮጵያ 25 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
******
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1847 የላብራቶሪ ምርመራ ሃያ አምስት (25) ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት (187) መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
የአዳዲሶቹ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተም፦
• 3ቱ - የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣
• 3ቱ - በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣
• 19ኙ - የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ጨምሮ ገልጿል፡፡
ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵውያን ናቸው፤ ሃያ አራቱ ወንዶች፣ አንዷ ሴት ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ17 እስከ 65 ዓመት ነው፡፡
ከታማሚዎቹ መካከል 21ዱ ከአዲስ አበባ፣ ሁለቱ ከደቡብ ክልል ሀዲያና ከንባታ ዞኖች እንዲሁም ሁለቱ ከኦሮሚያ ክልል ቦረና ለይቶ ማቆያና አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን የተገኙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
# ሰበር_ዜና - 29 ሰዎች ዛሬ በኮሮና ተያዙ።
"ዶክተር ሊያ ታደሰ - REPORT59"
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2171 የላብራቶሪ ምርመራ ሃያ ዘጠኝ (29) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ (239) ደርሷል፡፡