Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
#ላፕቶፕ_ስንገዛ_ማወቅ_እና_ማየት_ያለብን_ወሳኝ_
ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም
ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ
የሆነ
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል
ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን
ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ
Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
# የተማሩትን_ማስተማር # ያወቁትን_ማሳወቅ # ብልህነት ነው
# ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ!
# ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፔጁን # ላይክ # ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።
👍1
የኮምፒዉተራችን storage space ሲሞላብን እንዴት ማስለቀቅ እንችላለን
የኮምፒዉተርዎ storage space ሞልቶበት ተቸግረዋል፡፡ እንግዲያዉስ የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ
1. Windows Disk Cleanup
ለብዙዎች እፎይታን የሰጠ tool ሲሆን የኮምፒዉተራችንን ስቶሬጅ የሞሉብንን የተለያዩ ፋይሎች በማጥፋት ብዙ ትርፍ storage space እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ኮምፒዉተራችን ላይ የማንጠቀምባቸዉ እና የማይጠቅሙን ጊዜያዊ ፋይሎችን (temporary files) በማጥፋት ኮምፒዉተራችን ላይ ብዙ ቦታ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡
Windows Disk Cleanup ለመጠቀም የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Computer window (Start -> Computer)
2. hard-drive ላይ Right-Click በማድረግ ‘Properties’ የሚለዉን መምረጥ
3. ‘General’ tab ዉስጥ ‘Disk Cleanup’ የሚለዉን click ማድረግ
4. Windows scan አድርጎ ምን ያህል ቦታ ማስለቀቅ እንደምንችል ያሳዉቀናል
5. ከ drive ላይ ማጥፋት የምንፈልጋቸዉን ፋይሎች መርጠን ok ማለት
2. የማንጠቀምባቸዉን ፕሮግራሞች Uninstall ማድረግ
አብዛኞቹ ኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች የኮምፒዉተራቸዉን ቦታ የሚያጣብባቸዉ የጫኗቸዉ ሶፍትዌሮች እና ጌሞች ናቸዉ፡፡ የማንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮች Uninstall በማድረግ ቦታ መቆጠብ እንችላለን፡፡ ከኮምፒዉተሮ ላይ የማይፈልጉትን ሶፍትዌር ለማጥፋት የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Start -> Control Panel -> Uninstall a program
2. ብዙ ቦታ የያዘዉን ሶፍትዌር ለማወቅ በ size ቅደም ተከተል ይደርድሯቸዉ፡፡
3. ማጥፋት የፈለጉትን ሶፍትዌር መርጠዉ Uninstall የሚለዉን ይጫኑ፡፡
3. የተደጋገሙ ፋይሎችን ያጥፉ
ዊንዶዉስ በራሱ የተደገሙ ፋይሎችን ለይቶ የሚያጠፋ ሲስተም የለዉም ስለዚህ ይህንን ስራ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህንን የሚያደርጉ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ Duplicate Sweeper አንዱ ነዉ፡፡ Duplicate Sweeper ኮምፒዉተራችን ላይ ያሉ የተደጋገሙ ፋይሎችን scan አድርጎ ያቀርብልናል፡፡ እኛም ከዘ ዉስጥ የተደገሙ መሆናቸዉን እያረጋገጥን ማጥፋት እንችላለን፡፡
4. ጊዜያዊ ፋይሎች (Temporary Files)
በ Windows Disk Cleanup አማካኝነት ጊዜያዊ ፋይሎችን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አይተናል፡፡ ነገርግን Windows Disk Cleanup ሊያገኛቸዉ የማይችሉ እንደ browser ያሉ የጫንናቸዉ ሶፍትዌሮች የፈጠሩትን ጊዜያዊ ፋይሎች ለማጥፋት የሚያስችለን ሌላ መንገድ Google Chrome ን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ እናያለን፡፡
1. Google Chrome ን ይክፈቱ
2. settings menu ይክፈቱ
3. More tools የሚለዉን ይምረጡ
4.Clear Browsing data የሚለዉ ዉስጥ በመግባት ማጥፋት የሚፈልጉትን ጊዜያዊ ፋይል
መርጠዉ ያጥፉ
5. Recycle Bin ዉስጥ ያሉ ፋይሎችን ያጥፉ
ከኮምፒዉተራችን ላይ ያጠፋናቸዉ ፋይሎች permanently delete ካላደረግናቸዉ መልሰን ብንፈልጋቸዉ ማግኘት እንድንችል Recycle Bin ዉስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ከላይ ባሉት መንገዶች ያጠፋናቸዉ ፋይሎችም Recycle Bin ዉስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ Recycle Bin ያሉ ፋይሎች ግን ከኮምፒዉተራችን ላይ የያዙትን storage space እንደያዙ ነዉ የሚቆዩት፡፡ ስለዚህ storage space ለማስለቀቅ እነዚህን የማንፈልጋቸዉ ፋይሎች ከRecycle Bin ዉስጥ ማጥፋት ይኖርብናል፡፡
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ!
👉#ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፔጁን 👍#ላይክ 👉#ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።
1👍1
useful information
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1382 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ ሰባት (17) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ ስልሳ ሁለት (162) ደርሷል፡፡
#የታማሚዎች_ዝርዝር_ሁኔታ
ታማሚ 1 - የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአ/አ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ የስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው።
ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 3 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 4 - የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 5 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 6 - የ65 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 7 - የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአ/አ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።
ታማሚ 8 - የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታ አፋር (የተገኘው አ/አ) ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 9 - የ50 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 10 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 11 - የ53 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአ/አ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው።
ታማሚ 12 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 13 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 14 - የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 15 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 16 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 17 - የ41 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
👍1