Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
የኮሮና ቫይረስ ዋነኛው የመተላለፊያ መንገዱ በአፋችንና በአፋንጫችን በሚወጡ ፈሳሾች/Drop/ አማካኝነት ነው።
ነገር ግን አንደ Disease
Control and Prevention (CDC) ገለፃ በአፋችንና በአፋንጫችን ከሚወጡት ፈሳሾች ጋር ባይወዳደሩም በመጠኑም ቢሆን እቃዎች ላይ በመቆየት ይተላለፋሉ ብሏል።
ምንም እንኳ ግልፅ የሆነ ጥናት እስካሁን ባይገኝም።
ኮሮና ቫይረስ በዕቃዎች ላይ የሚቆይበት ጊዜ እንደ አየር ፀባይ የሚወሰን ሲሆን የአየር ፀባይ ከ5°C-11°C ባለው የሙቀት መጠን ለይ ቫይረሱ በከፋተኛ ሁኔታ ይሰራጫል። የመገልገያ ቁሳቁሶች ላይም የሚቆይበት ጊዜ ከፍ ይላል።
አንዳንድ ጥናቶች እንደጠቆሙት ከፍተኛ ሙቀት ማለትም ከ30°C እና ከዛ በላይ በሆነ የአየር ፀባይ ላይ COVID -19 ከሰዎች ላይ ካልሆነ በቀር አየር ላይና እቃዎች ላይ ተቋቁሞ ለመቆየት ይቸገራል ይላሉ።
እንደ National Institute of Allergy and
Infectious Disease (NIAID) ጥናት COVID-19 እቃዎች ላይ የሚቆይበት ጊዜ እንደ አየር ፀባዩ ሁኔታ እንደሆነ ገልጾ
ከ18°C-25°C ባለው ሙቀት ላይ ኮሮና ቫይረስ እቃዎች ላይ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቋይ እንደሚከተለው አስቀምጧል።
ምንጭ DR.FINOT
የቻይናዋ ውሃን ከተማ ከ76 ቀናት በኋላ ለእንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆናለች
*******
የኮሮና ወረርሽኝ መነሻ ናት በተባለችው የውሃን ከተማ የሚገኙ ሰዎች ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንቅስቃሴ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
ጤናማነታቸው የተረጋገጠና ይህንኑ የሚመሰክር አረንጓዴ ኩፖን ምልክት የያዙ ነዋሪዎቿ አሁን ወደየትም አገር መጓዝ ይችላሉ ተብሏል፡፡
የባቡር መንገዶቿ፤ የመኪና አውራ ጎዳናዎቿም ለመጀመርያ ጊዜ በሙሉ ኃይል ክፍት ሆነዋል፡፡
ባለስልጣናት ይህንን ሁኔታ እንደ ስኬት ሲቆጥሩት ነዋሪዎች ግን የተለያየ ልምድ የወሰዱበት እና በሰው ልጅ ታሪክ አከራካሪ ገደብ ሆኗል፡፡
የ11 ሚሊዮን ቻይናዊያን መኖርያ የሆነችው ውሃን ለ11 ሳምንታት ሙሉ በሙሉ ተዘግታ፤ እንቅስቃሴዋ ታግዶ ከርማ ነበር፡፡
በቻይና ወረርሽኙ ከተነሳ ወዲህ 3300 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የሚበዙቱ የዚች ከተማ ነዋሪዎች እንደነበሩ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ቀን 30/07/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት
ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያውያን እየተመለከታችሁትና እየታዘባችሁት እንደሆነው ዓለም በአስቸጋሪ የፈተና ምእራፍ እያለፈች ነው፡፡ ዓለም ይሄንን መሰል ነገር ሲገጥማት ከመቶ ዓመት በኋላ የመጀመሪያ ነገር ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሮና (ኮቪድ -19) የዓለም ሁለንተናዊ ችግር ሆኖ ብቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ የመፍትሔ ርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ሕዝቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ፣ የሕክምና ተቋማት እንዲዘጋጁ፣ የመከላከያና የሕክምና መሣሪያዎች ከውጭ እንዲገቡ፣ የማቆያ ሥፍራዎች እንዲዘጋጁ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፤ አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች በቤት እንዲወሰኑ፣ ብዙ ሕዝብ ሊሰበሰብባቸው የሚችሉ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎታቸውን ሕዝብ ሊሰበሰብ በማይችልበት መንገድ እንዲከውኑ፣ በአብዛኛው ሥፍራዎች የሕዝብ ትራንስፖርት እንዲቋረጥ፣ ለአስቸጋሪ ጊዜ የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ሥራ እንዲሠራ ተደርጓል፡፡
መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ የሚከተለው ስትራቴጂ በመከላከል ላይ ያተኮረ ነው፡፡
1. ኅብረተሰቡን አስተባብሮ በባለሞያዎች ምክር መሠረት ለመከላከል መቻል
2. ከመከላከል ያለፈ ነገር ሲመጣ ለማከም የሚያስችሉ ዐቅሞችን ማዳበር፡፡
3. የከፋው ነገር ከመጣም አስቀድሞ በመዘጋጀት እንደየ አስፈላጊነቱ ተገቢ ውሳኔዎችን እያሳለፉ መሄድ፡፡
እስካሁንም በዚህ መንገድ ነው የተጓዝነው፡፡
አሁን ያሉን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በቫይረሱ የተያዙ ወገኖች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው፡፡ ይሄም በመሆኑ ሁላችንም ያለንን ዐቅም ሁሉ አስተባብረን ወገኖቻችንን ከዚህ ወረርሽኝ ለመከላከልና የታመሙትንም ለማዳን ማዋል አለብን፡፡ ያለንበት ጊዜ ሕዝብና ሀገርን ለማዳን ሲባል አስቸጋሪ የተባሉ ውሳኔዎችን መወሰን ያለብን ጊዜ ነው፡፡ ይህም ውሳኔ፣ እንደ ግለሰብ፣ እንደ ማኅበረሰብ፣ እንደ ተቋምና እንደ መንግሥት የሚወሰኑ ናቸው፡፡
ይህ ውሳኔ በዛሬው ትውልድ ላይ ብቻ የምንወስነው ውሳኔ አይደለም፡፡ በልጅ ልጆቻችን ላይ ጭምር የምንወስነው ነው፡፡ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ላይ የምንወስነው ብቻ አይደለም፤ በነገዋና በከነገ ወዲያዋ ኢትዮጵያ ላይ ጭምር የምንወስነው ውሳኔ ነው፡፡ የኛ የመሪዎቹ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋ ውሳኔ በታሪክ የሚመዘገብ ነው፡፡ ይሄንን አስቸጋሪ ጊዜ ልናልፈው የምንችለው በአካል ተራርቀን በመንፈስ ግን አንድ ሆነን ከቆምን ብቻ ነው፡፡ የያንዳንዳችን ሀብት የሁላችን፣ የእያንዳንዳችንም ችግር የሁላችን መሆን አለበት፡፡ አንዱ በልቶ ሌላው ተርቦ፣ አንዱ ሠርቶ ሌላው ሥራ አጥቶ፣ አንዱ መኖሪያ አግኝቶ ሌላው ውጭ አድሮ፣ አንዱ አትርፎ ሌላው ከሥሮ ይሄንን ችግር ለማለፍ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ይህ ችግር የመጣው በህልውናችን ላይ በመሆኑ፡፡ ይህ ችግር የተጋረጠው ሰው ሆኖ በመኖርና ባለመኖር ላይ በመሆኑ፡፡ መንግሥት ችግሩን በደረሰበት ልክ ለመቋቋም ተዘጋጅቷል፡፡ የምንወስዳቸው ውሳኔዎች ክብደት እንደ ችግሩ ክብደት የሚወሰን ነው፡፡ ታሪክ እዚህ አድርሶናል፡፡ ሀገርና ትውልድ በእጃችን ላይ ነው፡፡ በዚህ ዘመን በምንሠራው ሥራ ወይ እንመሰገናለን ወይ እንወቀሳለን፡፡ ከምንም በላይ ግን በጊዜውና በዐቅማችን ማድረግ ያለብንን ካላደረግን የበለጠ እንወቀሳለን፡፡ ይህ ደግሞ ሁላችንንም ኢትዮጵያውያንን የሚመለከት ነው፡፡ ከተረፍን አብረን ነው፡፡ ከከሠርንም አብረን ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣጡ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡ ይህም በሕገ መንግሥቱ ዐንቀጽ 93 መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ይሄንን መሳይ ዐዋጅ ብዙ ሀገሮች ካወጁ ሰንብተዋል፡፡ እኛ እስክንዘጋጅና ሁኔታው የግድ እስኪለን ጠብቀናል፡፡ ጊዜው ሲጠይቅ ግን ዐውጀናል፡፡ ሀገርን ለማዳንና ትውልድን ለመታደግ ከዚህ በላይ ልንወስን እንደምችልም መታወቅ አለበት፡፡ ዜጎቻችንም ከዚህ በላይ ግዴታቸውን ለመወጣት ወገባቸውን አጥብቀው መጠበቅ አለባቸው፡፡
በዚህ ወቅት ሁላችሁም ችግሩን ለመቋቋም ከሚሠሩት አካላት ጋር አብራችሁ እንድትቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ችግሩን ለማባባስ የሚሠሩ ካሉ ግን፣ በሕጉ መሠረት የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን፡፡
ወገኖቼ፤
ኢትዮጵያውያን የሚያምርብን መረዳዳቱና መደጋጋፉ ነው፡፡ ድኾችን እንርዳ፡፡ በአካባቢያችን ላሉት ዐቅመ ደካሞች እንድረስላቸው፡፡ የቤት ተከራዮቻችንን ዕዳ እንካፈላቸው፡፡ ከቻልን አናስከፍላቸው፤ ካልቻልን ቅናሽ እናድርግላቸው፡፡ ያም ካልሆነ ይህ ጊዜ እስኪያልፍ እንታገሣቸው፡፡ በዚህ ወቅት ተከራዮችን ከቤት ማስወጣት ፈጣሪም፣ ታሪክም ሕግም ይቅር የማይሉት ወንጀል ነው፡፡ ማናችን አልፈን ማናችን እንደምንተርፍ ለማናውቅበት ጊዜ ከመተባበር የተሻለ መሻገሪያ የለንም፡፡ የግል ባለሀብቶች የሠራተኞቻቸው ሕይወት እንዲያስጨንቃቸው አደራ እላለሁ፡፡ መንግሥት የኢኮኖሚ ችግሮቻችንን ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ እየወሰነ አብሯችሁ እንደሚሆን በዚህ አጋጣሚ እገልጥላችኋለሁ፡፡
ለሌሎች ወገኖቻቸውና ለሀገራቸው ሲሉ ቤታቸውን፣ ሆቴላቸውን፣ አዳራሾቻቸውን፣ የእምነት ተቋሞቻቸውን፣ መኪኖቻቸውን፣ ገንዘባቸውንና እህላቸውን የሰጡ ዜጎቻችንን ስናይ ይሄንን አስቸጋሪ ወቅት ከፈጣሪ ጋር ሆነን ልናልፈው እንደምንችል ርግጠኞች እንሆናለን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከወገኖቻቸው መከራ ለማትረፍ የሚሽቀዳደሙ፣ ከመከራ እንኳን የማይማሩ ሰዎችን ስናይ መንገዱ ከባድ እንዳይሆንብን እንሠጋለን፡፡ በጎ አድራጊዎችን የምናመሰግነውን ያህል መንገዳችንን ይበልጥ ፈታኝ የሚያደርጉብንን ስግብግቦች ግን ለሕዝብና ለሀገር ስንል አስተማሪ የሆነ ቅጣት ለመቅጣት እንገደዳለን፡፡
የሕክምና ባለሞያዎቻችንን በሚቻለው ሁሉ እንርዳ፡፡ ያለ እነርሱ ግንባር ቀደምነት ትግሉን ልናሸንፍ አንችልም፡፡ የሕክምና ባለሞያዎችን ማክበር፣ ማመስገንና በጉዟቸው ሁሉ መተባበር ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል፡፡ ለሕክምና ባለሞያዎች ተገቢውን ሁሉ አለማድረግ እጅን በእጅ እንደመቁረጥ ነው፡፡ ከእነርሱ በተጨማሪ የመከላከያ አባላት፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የውኃ አቅርቦት እንዳይስተጓጎል የሚሠሩ ባለሞያዎች፣ የሚዲያ ባለሞያዎች፣ የመገናኛ መሥመሮቻችን ላይ 24 ሰዓት የሚያገለግሉ ዜጎች፣ እኛ ቤት እንድንውል እነርሱ ውጭ የሚውሉ ሠራተኞች ተገቢው ምስጋናና ድጋፍ ከቤተሰባቸውም፣ ከማኅበረሰባቸውም ያስፈልጋቸዋል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ አርሶ አደሮቻችን የበልግ ወቅት እንዳያልፍብን ራሳቸውን ከቫይረሱ እየተጠነቀቁ በምርት ሥራ ላይ ጠንክረው እንዲሳተፉ አደራ እላቸዋለሁ፡፡ ከቫይረሱ ባልተናነሰ የእርሻ ምርት መቀነስና የእርሻ ምርት አለመኖር ሀገራችንንና ሕዝቧን ይጎዳል፡፡ እናንተ ሀገር መጋቢዎች ስለሆናችሁ፣ እየተጠነቀቃችሁ ካለፈው የተሻለ ምርት ለማምረት ትጉ፡፡ መንግሥትም አስፈላጊውን ሁሉ ሞያዊና ድጋፍ ያደርግላችኋል፡፡
የኢንዱስትሪ ምርቶቻችንም ፈጽመው መቆም የለባቸውም፡፡ ለሠራተኞቻችን ሕይወት እየተጠነቀቅን፣ በወረርሽኙ ምክንያት የሚያጋጥመንን ተግዳሮት ሁሉ እየተቋቋምን በፋብሪካ ምርቶች ላይ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናድርግ፡፡ ከበተለይም ከውጭ የምናመጣቸውን ምርቶች ለመተካት ለሚደረገው ጥረት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላችሁ
ገልጥላችኋለሁ፡፡ በተለይ ግን በምርት ዝውውር ጊዜ ከፍተኛ የሆነውን የመጨረሻ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለአፍታም ቢሆን እንዳትዘነጉት ይሁን፡፡
ይህ ጊዜ ያልፋል፡፡ ሀገራችን ከዚህ የሚስተካከሉና ከዚህም የሚብሱ ፈተናዎችን አልፋለች፡፡ ዓለማችን በየዘመናቱ የከፉ ተግዳሮቶችን አልፋ ነው እዚህ ዘመን የደረሰችው፡፡
የሚሰጡንን መመሪያዎች በሚገባ እናክብር፣ የጤና ባለሞያዎች የሚሉንን ለሕይወታችን ስንል እንስማ፡፡ በኮሮና አይቀለድም፡፡ ጉዳዩ ከመኖርና ካለመኖር ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ይሄንን ፈተና ለማለፍ ባለ ሦስት መዓዝን ትብብር ያስፈልገናል፡፡ ወደ ጎን እኛ እርስ በርሳችን፡፡ እያንዳንዳችን ደግሞ ከፈጣሪያችን ጋር፡፡ እኔ ከሌላው ወገኔ ጋር፣ ሌላው ወገኔ ከእኔ ጋር፣ እኔና ሌላው ወገኔ ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት መሥመር መቼም መቋረጥ የለበትም፡፡
በርትተንና ተረባርበን የሚጠበቅብንን እናድርግ፣ ጸንተንና በተሰበረ ልብ ሆነን ወፈደ ፈጣሪ እንለምን፡፡ ፈጣሪ ከእኛ ጋር ነው፡፡ መከራውን ያቀልልናል፤ ፈተናውን ያሳልፈናል፤ ማዕበሉን ያሻግረናል ብለን እናምናለን፡፡ የሃይማኖት አባቶች ያዘዙንን ጥንቃቄ እየፈጸምን ያዘዙንንም ጸሎት ተግተን እንጸልይ፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «ገልጥላችኋለሁ፡፡ በተለይ ግን በምርት ዝውውር ጊዜ ከፍተኛ የሆነውን የመጨረሻ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለአፍታም ቢሆን እንዳትዘነጉት ይሁን፡፡ ይህ ጊዜ ያልፋል፡፡ ሀገራችን ከዚህ የሚስተካከሉና ከዚህም የሚብሱ ፈተናዎችን አልፋለች፡፡ ዓለማችን በየዘመናቱ የከፉ ተግዳሮቶችን አልፋ ነው እዚህ ዘመን የደረሰችው፡፡ የሚሰጡንን መመሪያዎች በሚገባ እናክብር፣ የጤና ባለሞያዎች የሚሉንን ለሕይወታችን ስንል እንስማ፡፡ በኮሮና…»
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 225 ሰዎች ውስጥ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ ቁጥሩም ወደ 55 ከፍ ብሏል።
ďťż
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለ2 ሺህ 496 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
ዛሬ የተገለጸውን ጨምሮም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 55 ከፍ ብሏል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሦስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያውያን ናቸው፤ ሁለቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውም ናቸው።
ሁለቱም የ29 ዓመት ዕድሜ ያላቸውና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት ዕድሜ ያለውና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው።
ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለውም፤ ነገር ግን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ እንደተደረገበት ተገልጿል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል አንድ ሰው ወደ ጽኑ ሕሙማን ማቆያ መግባቱንና ይህም በጽኑ ሕሙማን መቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎች ቁጥር 2 እንዳደረሰው ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ባሉበት ክልል በተዘጋጀ የነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።
ኅብረተሰቡ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግም ነው ያሳሰቡት።
በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል አራቱ አገግመዋል፤ ሁለቱ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።
ሰበር ዜና
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 225 ሰዎች ውስጥ ሶስት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ። ቁጥሩም ወደ 55 ከፍ ብሏል።
ďťż
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለ2 ሺህ 496 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
ዛሬ የተገለጸውን ጨምሮ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 55 ከፍ ብሏል ነው።
ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሶስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ (2) የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
ሁለቱ ግለሰቦች የ29 ዓመት እድሜ ያላቸው እና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት እድሜ ያለው እና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው።
ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ እንደተደረገበት ተገልጿል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል አንድ ሰው ወደ ጽኑ ህሙማን ማቆያ መግባቱንና ይህም በጽኑ ህሙማን መቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎች ቁጥር ሁለት (2) እንዳደረሰው ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ባሉበት ክልል በተዘጋጀ የነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።
ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
ቻይና የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዎቹን ሁለት የህመም ደረጃዎች ለማከም የተጠቀመችባቸውን የባህል መድሃኒቶች ለኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ ልትሰጥ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር ከቻይና የባህል ሃኪሞችና ተመራማሪዎች ጋር ቫይረሱን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል፡፡
ቻይና የባህላዊ መድሃኒቶችን በመጠቀም ስኬታማ በሆነ መልኩ የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠር የቻለችባቸው መንገዶችን ለኢትዮጵያ ለማጋራት ፍቃደኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡
በተለይ የቫይረሱ ህመም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ለማከም የተጠቀመችባቸውን ሁለት የመድሃኒቶች ዓይነቶች ለኢትዮጵያ በድጎማ መልክ ለመስጠት ተስማምታለች፡፡
ረጅም እድሜ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ የባህል ህክምና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረትም በቴክኖሎጂ፣ በቁሳቁስ እና በሙያም እደግፋለሁ ብላለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.) የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ ሀገር ከተጀመሩ ስራዎች ጎንለጎን የቻይና ድጋፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህላዊ መድሃኒቶችም ህጋዊ ማዕቀፍ ኖሯቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የተጀመረው ጥረት እንዲሳካም የቻይናን ልምድ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች ብለዋል፡፡
ምንጭ
Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" እንገድልሃለን ይሉኛል። አልፈራም። ግድ አይሰጠኝም። አሁን እኔን የሚያስጨንቀኝ የሰው ሞት ነው::"
(ዶ/ር ቴውድሮስ አድሃኖም)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
"እንገድልሃለን ይሉኛል። አልፈራም። ግድ አይሰጠኝም። አሁን እኔን የሚያስጨንቀኝ የሰው ሞት ነው:: ሰደቡኝ ብዬ ራሴን ልከላከል ጊዜ ማጥፋት አልፈልግም። እኔ የሰው ነፍስን ማዳን ላይ ነው ማተኮር የምፈልገው።ከፈለጉ 3 ቀን፣3 ወር፣ 3 ዓመት ከቻሉም 300 እየቱሳደቡ ይቆዩ።"
(ዶ/ር ቴውድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ፣ የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ሊቀመንበር) (ይህን በአማርኛ የተተረጎውን ቪድዮ ይመልከቱ)
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
በለይቶ ማቆያ የነበሩ 554 ግለሰቦች ጊዜያቸውን ጨርሰው መውጣታቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
አዲስ ሚድያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) ሚያዝያ 1/2012
በለይቶ ማቆያ ከ14 ቀናት ቆይታ በኋላ የተለቀቁት 554 ግለሰቦች በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮናቫይረስ ነጻ መሆናቸውም ተረጋግጧል።
ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት፤ የለይቶ ማቆያ የኮሮናቫይረስ በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዳይስፋፋ ከሚያደርጉ የዓለም የጤና ድርጅት ምክረ ሃሳቦች ውስጥ አንዱ ነው።
በአገሪቱም የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ሁሉም ከውጭ የሚመጡት መንገደኞች በለይቶ ማቆያ እንድቀመጡ ተወስኗል ብለዋል።
ይህም ውሳኔ በሠላም ሚኒስቴር አስተባበሪነት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲሁም ከጸጥታ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት ከተለያዩ አገራት ወደ ኢትዮጰያ የመጡ መንገደኞች በራሳቸው ወጪ በሆቴሎች ክትትል እየተደረገለቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በአስገዳጅ ሁኔታ ከተለያዩ አገራት ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን በዩኑቨርሲቲዎችና በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመንግሥት ወጪ እንዲቆዩ መደረጋቸውን ተናግረዋል።
የአስገዳጅ የለይቶ ማቆያው ከተጀመረ እስካሁን ድረስ አስፈላጊ ምርመራ ተድርጎላቸው 14 ቀን የለይቶ ማቆያ ጊዜያቸውን የጨረሱ 554 ሰዎች ከለይቶ መቆያ መውጣታቸውን ጠቁመዋል።
የለይቶ ማቆያ ጊዜያቸውን የጨረሱት ግለሰቦች ወደ ማኅበረሰቡ ከተቀላቀሉ በኋላ ኅብረተሰቡ ከመድሎና ማግለል ነጻ በሆነ አኳኋን ሊቀበላቸው ይገባል ብለዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም በአሁኑ ወቅት 2 ሺህ 36 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ አስፈላጊው የጤና ክትትል በባለሙያዎች እየተደረገባቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በአገሪቱ የተጀመረው የ14 ቀናት የለይቶ ማቆያም የበሽታውን ስርጭት ለማቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ 56 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በጽኑ ህሙማን ክፍል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የታዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሆኗል፤ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ከ89 ሺህ አልፏል።
አምስት_ነፃ_የሶፍትዌር_ድህረ_ገፆች_እጠቁማችኋለሁ!
ከዚህ በታች ያሉ የነጻ ሶፍትዌር ማውረድ(download) የምንችልባቸው ድረገጾች ናቸው የማንኛውም ለኛ የሚጠቅሙን ለምሳሌ
1. Browsers
2. Office & News
3. Desktop apps
4. Learning
5. Games
6. File Sharing
7. Multimedia
8. Personalization
9. Security & VPN
10. Social & Messaging
11. System Tuning & Utilities
ከላይ የተጠቀሱትን ማንኛውንም የነጻ ሶፍትዌሮችን ማግኝት ትችላላችሁ
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዌብሳይ አድራሻዎችን በመጠቀም ኢንተርኔት ባለበት በየትኛውም ቦታ ማውረድና መጠቀም ትችላላችሁ
⓵👉www.filehippo.com
⓶👉www.cnet.com
⓷👉 www.sofpedia.com
⓸👉www.filepuma.com
⓹👉www.filehorse.com
ስለ ስልክ ቫይረስ ምንያህል ያቃሉ
What is Virus ??
#Virus ማለት የ Computer Code ወይም Program ሲሆን ብዙ ግዜ የሚሰራው ወይም
የሚፈጠረው የ Computer እውቀት ባላቸው ሰወች እና ስለ Computer ጠልቀው በ ተማሩ ሰወች ነው
ቫይረስ ስንል ብዙ አይነት ቫይረሶች አሉ
➲Spyware Virus
➲Malware Virus
➲Ransonware Virus
➲Adware Virus
➲Trojan Horse Virus ናቸው
እንደ ስማቸው ሁሉ ስራቸውም ይለያያል
የ#Virus ዋና አላማው እና ስራው ምን ምን ናቸው
⓵ ስልካችንን ማበላሸት (Damage) ማድረግ
የስልኩን Software ቫይረሱ በሚያጠቃበት ግዜ ስልኩ Dead ይሆናል ይህ ማለት ስልካችን Samsung ከሆነ ስንከፍተው Samsung ይልና ቀጥ ብሎ ይቆማል አይከፈትም ማለት ነው
⓶ በጣም ጠቃሚ ፋይል ማጥፋት እና መደበቅ
ስልካችን ላይ ሆነ MemoryCard ላይ ያሉትን ማንኛውም (File)
ለምሳሌ
Music Photo Video Application Document ያለ ምንም ምህረት ያጠፋል (Format) ያደረጋቸዋል ያለኛ ትዛዝ እና ፍቃድ
⓷ ስልካችንን በማናውቀው Password ወይም Pattern መቆለፍ እና መዝጋት
ይህ ማለት ስልካችንን የዘጋንበትን የሚስጥር Password ይቀይርና የራሱን Password
በማስገባት ይቆልፍብናል ማለትም ስልካችንን
ሙሉ በ ሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር ያደርገዋል እኛ ስልኩን ማዘዝ አንችልም ማለት ነው
⓸ ስልካችንን(OS)Operating System ስራ ማዛባት እና ስልኩ እንዲዘባርቅ ማድረግ
ይህ ማለት ስልካችን ስራውን በትክክል እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆናል ይህ ማለት እኛ ስልኩን
ሳንነካው ሳናዘው በራሱ (File)መክፈት መዝጋት
ስልኩን Flight Mode ላይ ማድረግ
ስልኩን Switch Off ማድረግ ከዛ ስልኩን መልሶ መክፈት. ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን በራሱ ይሰራል
⓹ Software File ማጥፋት
የ ስልካችንን Software File Delete ማድረግ
=> Software File Delete ከሆነ ስልኩን ማስተካከል ከባድ ይሆናል
ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ ያለ ባለቤቱ ፍቃድ በራሱ መብት ይሰራል.
ስለ #ቫይረስ አደገኛነት ጉዳት እና አላማ ይህን ካልን ስለ መከላከያው እና ስለ መፍትሄው ደግሞ እናያለን
እንዴት አድርገን ስልካችንን ከአደገኛ ቫይረስ መጠበቅ እና መከላከል እንችላለን
⓵ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት ማንኛውንም ነገር ከ ማውረድ መቆጠብ
ለምሳሌ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ
ዌብሳይት Application ወይም File (Download) በምናደርግበት time #ቫይረሱ Download ከምናረገው Application ወይም File ጋር አብሮ ወደ ስልካችን በቀላሉ ይገባል
ለምን ቢባል Fake የሆኑ #ድረገጾች ላይ #ቫይረሶች ብዙግዜ ስለሚለቀቁ ነው ሰለዚህ ከታወቀ እና ታማኝነት ካለው ዌብሳይት ብቻ የምንፈልገውን File ማውረድ ይጠበቅብናል
⓶ Bluetooth Email እና G-mail ክፍት አድርጎ አለመተው ተጠቅመን ከ ጨረስን በኋላ መዘጋቱን #Check Up ማድረግ
⓷ የስልካችንን #Software Update ማድረግ
በሰአቱ እና በግዜ
ስልካችን የSoftware Update ጥያቄ ሲጠይቀን #ችላ አለማለት ወድያውኑ ስልኩን Update መድረግ
የስልካችን Software Update ከተደረገ ስልካችን በ ቫይረስ የመጠቃት እድል በጣም ዝቅተኛ ነው
የ ስልካችንን Software Update ለማድረግ መጀመሪያ
#Setting ውስጥ እንገባለን ከዛ መጨረሻ ላይ #About Phone
የሚል አለ እሱን እንዴ #Click እንላለን ከዛ
Software Update የሚለውን #Click ማለት
⓸ ትክክለኛ እና #Original Antivirus መጠቀም
ስልካችን ላይ ያለውን ሁሉኑም Application እና File #Scan ማድረግ Scan በምናደርግበት ግዜ Virus ያለበት Application ወይም File ከተገኘ ወዲያውኑ ማጥፋት
#Remove ማድረግ
እነዚህን Original Antivirus
ከ PlayStore በ ማዉረድ ተጠቀሙ
➷➷➷➷➷➷
➊ #Norton Antivirus
➋ #KasperskyAntiVirus
➌ #BT Virus Protect: Mobile Anti-Virus & Security App
እነዚህ Antivirusሶች የሚሰሩት በ Data እና በ Wifi Connection
⓹ ቫይረስ በዋናነት ከሚገባበት መንገድ አንዱ በ #Email ለምሳሌ በ
#G -mail ነው
Email ለምሳሌ በ G-mail በምንጠቀምበት ግዜ ከማናውቃቸው ሰወች #Link ሲላክልን ቶሎ መክፈት የለብንም ምክንያቱም የተላከው ከ #Hackerሮች (Linkኩም) ቫይረስ ሊሆን ስለሚችል በፍፁም መክፍት የለብንም
⓺ ስልካችን ላይ ያሉትን ሁሉኑም Application # Update ማድረግ ለምን ቢባል አንዳንድ
Applicationኖች ከ ቆይታ ብዛት የተነሳ ወደ ቫይረስ ይቀየራሉ ስለዚህ ሁሉኑም Application በየጊዜው Update ማድረግ አለብን
ስልካችን ላይ ያሉ Applicationኖችን Update ለማድረግ መጀመሪያ ወደ PlayStore ላይ እንገባለን ከዛ (My APP) ዉስጥ እንገባለን ከዛ Update መሆን ያለበት Application ካለ እራሱ ይህን Application Update አድርግ ብሎ ይጠቁመናል ከዛ Update የሚለውን #Click ማድረግ
⓻ Wifi በምንጠቀምበት ግዜ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ
Wifi ከፍተን በምንጠቀምበት ሰአት ብዙ
Notification ወደ ስልካችን ይገባሉ በዚህ ግዜ
ወድያውኑ Notificationኑ ፍቃድ ይጠይቀናል
(Allow or Decline) ብሎ ይጠይቀናል ?
Notificationኑ ቫይረስ ይሁን አይሁን እኛ
አናውቅም ነገርግን እኛ ችላ በማለት ወይም ትኩረት ባለመስጠት (Allow) ብለን እንፈቅዳለን በዛን ሰአት Notification መስሎ የመጣው #ቫረስ በፍጥነት ወደ ስልካችን በመግባት ስልካችንን ያበላሻል ስለዚህ ማንኛውንም Notification
ወደ ስልካችን ሲመጣ ዝምብለን ከመክፈት መታቀብ አለብን
⓼ ማንኛውንም Application ከሰው ስንቀበል
ስለ Applicationኑ ምንነት እና ስራ በደንብ መረዳት አለብን ይህ ማለት Applicationኑ ጎጂ ሆነ ጥሩ የሚለውን እንድናውቅ ይረዳናል
ስለዚህ ማንኛውንም Application ስልካችን
ላይ ከመጫናችን እና ከ መቀበላችን በፊት ስለ
Applicationኑ በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል
⓽ "ቢያንስ ለ 3 የፌስቡክ ግሩፕ ላይ ሼር ያድርጉልኝ " ሼር አድርግ ቀላል እኮነው ሼር አድርግ🙏🙏🙏
⚠⚠⚠በተጨማሪም #FightCOVID19⚠⚠⚠
⚠ እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ይታጠቡ
⚠ አትጨባበጡ/አትሳሳሙ
⚠ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ይቀንሱ
⚠ አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አይውጡ
⚠ አካላዊ ርቀቶትን በእጅጉ ይጠብቁ
⚠ ትኩሳት ፣ ሳልና ትንፋሽ ማጠር...ምልክት ከታየባችሁ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ነፃ የስልክ መስመሮች ይደውሉ ፦
➡አዲስ አበባ - 8335 /952 ፣ ትግራይ ክልል - 6244 ፣ አፋር ክልል - 6220 ፣አማራ ክልል - 6981 ፣ ኦሮሚያ ክልል - 6955 ፣ ሱማሌ ክልል - 6599 ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል - 6016፣ ደቡብ ክልል - 6929 ፣ ሀረሪ ክልል - 6864 ፣ ጋምቤላ ክልል - 6184 ፣ ድሬዳዋ ከተማ - 6407
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
#የተማሩትን_ማስተማር #
❤2👍1
_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ!
👉#ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፔጁን 👍#ላይክ 👉#ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።
የሜሞሪ ስቶሬጅ መለኪያ ከትንሽ
ወደ ትልቅ መጠን በቅደም ተከተል!
➧8 ቢትስ 1 ባይት
➧1024 ባይት ➤ 1 ኪሎ ባይት
➧1024 ኪሎ ➤ባይት 1ሜጋ ባይት
➧1024 ሜጋ ➤ ባይት 1 ጊጋ ባይት
➧1024 ጊጋ ➤ ባይት 1 ቴራ ባይት
➧1024 ቴራ ➤ ባይት 1 ፔታ ባይት
➧1024 ፔታ ➤ ባይት 1 ኤክዛ ባይት
➧1024 ኤክዛ ➤ ባይት 1 ዜታ ባይት
➧1024 ዜታ ባይት ➤ 1 ዮታ ባይት
➧1024 ዮታ ባይት ➤ 1 ቦርኖቶ ባይት
➧1024 ቦርኖቶ ባይት ➤ 1 ጂኦፕ ባይት
ጂኦፕ ባይት ትልቁ የሜሞሪ ስቶሬጅ መመዘኛ ነው
"ቢያንስ ለ 3 የፌስቡክ ግሩፕ ላይ ሼር ያድርጉልኝ " ሼር አድርግ ቀላል እኮነው ሼር አድርግ🙏🙏🙏
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ!
👉#ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፔጁን 👍#ላይክ 👉#ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።
ስልክ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም
እንዲልላቹ ከፈለጋቹ!...
ብዙ ሰዉ የማያዉቃቸው የሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች!
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ስልክ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም
እንዲልላቹ ከፈለጋቹ!
*21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ
ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ
ስልክ ቁጥርዎ 0910477613 ከሆነ ወደ
*21*091045561# ይደውሉ
ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ!
ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ሲፈልጉ
*21*0144123456# በ0144123456 ቦታ የፈለጉትን
የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ ቁጥር ያስገቡ
ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው
ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ
ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል
*#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም
የሚል መረጃ ይሰጠናል
. ስልክዎ ብዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ
*67*የፈለጉትቁጥር# ብለው
ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ
. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ
*61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ!
ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ
. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ
*62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ
#62# ብለው ይደውሉ!
. ኮል ዌቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው
ይደውሉ! ኮል ዌቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው
ይደውሉ! ኮል ዌቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ
ለማወቅ *#43# መደወል
. ሲደውሉ ስልክ ቁጥርዎ እንዳይታይ ወይም በሌላ ቁጥር
ተክተው ለመደወል ሲፈልጉ #31#"የሚደውሉት ቁጥር" ከዛ
መደወል
☞አንዳንድ ስልኮች #31# ከተደወለ በኀላ የምንደውለውን
ቁጥር ስናስገባ በእኛ አገር ኔትዎርክ ላይሰራ ይች
# የተማሩትን_ማስተማር # ያወቁትን_ማሳወቅ # ብልህነት ነው
# ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/
MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
# ሼር_ያድርጉ
# ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
#ላፕቶፕ_ስንገዛ_ማወቅ_እና_ማየት_ያለብን_ወሳኝ_
ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም
ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ
የሆነ
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል
ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን
ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ
Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
# የተማሩትን_ማስተማር # ያወቁትን_ማሳወቅ # ብልህነት ነው
# ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ!
# ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፔጁን # ላይክ # ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።
👍1
የኮምፒዉተራችን storage space ሲሞላብን እንዴት ማስለቀቅ እንችላለን
የኮምፒዉተርዎ storage space ሞልቶበት ተቸግረዋል፡፡ እንግዲያዉስ የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ
1. Windows Disk Cleanup
ለብዙዎች እፎይታን የሰጠ tool ሲሆን የኮምፒዉተራችንን ስቶሬጅ የሞሉብንን የተለያዩ ፋይሎች በማጥፋት ብዙ ትርፍ storage space እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ኮምፒዉተራችን ላይ የማንጠቀምባቸዉ እና የማይጠቅሙን ጊዜያዊ ፋይሎችን (temporary files) በማጥፋት ኮምፒዉተራችን ላይ ብዙ ቦታ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡
Windows Disk Cleanup ለመጠቀም የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Computer window (Start -> Computer)
2. hard-drive ላይ Right-Click በማድረግ ‘Properties’ የሚለዉን መምረጥ
3. ‘General’ tab ዉስጥ ‘Disk Cleanup’ የሚለዉን click ማድረግ
4. Windows scan አድርጎ ምን ያህል ቦታ ማስለቀቅ እንደምንችል ያሳዉቀናል
5. ከ drive ላይ ማጥፋት የምንፈልጋቸዉን ፋይሎች መርጠን ok ማለት
2. የማንጠቀምባቸዉን ፕሮግራሞች Uninstall ማድረግ
አብዛኞቹ ኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች የኮምፒዉተራቸዉን ቦታ የሚያጣብባቸዉ የጫኗቸዉ ሶፍትዌሮች እና ጌሞች ናቸዉ፡፡ የማንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮች Uninstall በማድረግ ቦታ መቆጠብ እንችላለን፡፡ ከኮምፒዉተሮ ላይ የማይፈልጉትን ሶፍትዌር ለማጥፋት የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Start -> Control Panel -> Uninstall a program
2. ብዙ ቦታ የያዘዉን ሶፍትዌር ለማወቅ በ size ቅደም ተከተል ይደርድሯቸዉ፡፡
3. ማጥፋት የፈለጉትን ሶፍትዌር መርጠዉ Uninstall የሚለዉን ይጫኑ፡፡
3. የተደጋገሙ ፋይሎችን ያጥፉ
ዊንዶዉስ በራሱ የተደገሙ ፋይሎችን ለይቶ የሚያጠፋ ሲስተም የለዉም ስለዚህ ይህንን ስራ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህንን የሚያደርጉ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ Duplicate Sweeper አንዱ ነዉ፡፡ Duplicate Sweeper ኮምፒዉተራችን ላይ ያሉ የተደጋገሙ ፋይሎችን scan አድርጎ ያቀርብልናል፡፡ እኛም ከዘ ዉስጥ የተደገሙ መሆናቸዉን እያረጋገጥን ማጥፋት እንችላለን፡፡
4. ጊዜያዊ ፋይሎች (Temporary Files)
በ Windows Disk Cleanup አማካኝነት ጊዜያዊ ፋይሎችን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አይተናል፡፡ ነገርግን Windows Disk Cleanup ሊያገኛቸዉ የማይችሉ እንደ browser ያሉ የጫንናቸዉ ሶፍትዌሮች የፈጠሩትን ጊዜያዊ ፋይሎች ለማጥፋት የሚያስችለን ሌላ መንገድ Google Chrome ን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ እናያለን፡፡
1. Google Chrome ን ይክፈቱ
2. settings menu ይክፈቱ
3. More tools የሚለዉን ይምረጡ
4.Clear Browsing data የሚለዉ ዉስጥ በመግባት ማጥፋት የሚፈልጉትን ጊዜያዊ ፋይል
መርጠዉ ያጥፉ
5. Recycle Bin ዉስጥ ያሉ ፋይሎችን ያጥፉ
ከኮምፒዉተራችን ላይ ያጠፋናቸዉ ፋይሎች permanently delete ካላደረግናቸዉ መልሰን ብንፈልጋቸዉ ማግኘት እንድንችል Recycle Bin ዉስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ከላይ ባሉት መንገዶች ያጠፋናቸዉ ፋይሎችም Recycle Bin ዉስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ Recycle Bin ያሉ ፋይሎች ግን ከኮምፒዉተራችን ላይ የያዙትን storage space እንደያዙ ነዉ የሚቆዩት፡፡ ስለዚህ storage space ለማስለቀቅ እነዚህን የማንፈልጋቸዉ ፋይሎች ከRecycle Bin ዉስጥ ማጥፋት ይኖርብናል፡፡
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ!
👉#ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያጎለብታሉ
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፔጁን 👍#ላይክ 👉#ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።
❤1👍1