Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
Muhammed Computer Technology (MCT) pinned «# በኢትዮጵያ_የኮሮና_ቫይረስ_ኬዝ_ሙሉ_መረጃ የወቅቱ የአለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው መጋቢት 03-2012 ሲሆን ዛሬ ላይ በ19ኛ ቀኑ የተጠቂዎች ቁጥር 23 ደርሷል። እስኪ በሀገራችን የተገኘው 23ቱን ኬዞች እናስታውሳቸው መጋቢት 3-2012 የመጀመሪያው ታማሚ 1. የ48 አመት ጃፓናዊ የካቲት 25 ከቡርኪናፋሶ የመጣ መጋቢት 05-2012 ላይ…»
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምላሽ አሰጣጥን (የኮቪድ-19) አስመልክቶ የተዘጋጀ ዕለታዊ መግለጫ
-------------------
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህ መረጃ እስከ ተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ በአጠቃላይ 1013 የላቦራቶሪ ምርመራ ያደረገ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 66 የላብራቶሪ ምርመራ አካሄዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት (3) ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጧል፡፡ በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ አምስት (25) ደርሷል፡፡
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሁለት ግለሰቦች የ30 ዓመትና የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ በመጋቢት 15 ፣2012 ዓ.ም ወደ ሀገር የገቡ ሲሆን በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን የበሽታውን ምልክት ታይቶባቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ሶስተኛዋ ታማሚ የ60 ዓመት እድሜ ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 6፣2012 ዓ.ም ከፈረንሳይ የተመለሱና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሶስቱም ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ አንድ (21) ታማሚዎች ሲኖሩ ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ሁለት ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡ ነገይቻላን ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገበር እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል::
የጁምዐ እና የጀመዐ ሰላትን አስመልክቶ የዑለማ ምክር ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ:–
★★★★★★★★★★★★★★★
ወረርሽኙ ዛሬ ከደረሰበት ደረጃና ከስርጭቱ ፍጥነት እንዲሁም ከአስቸጋሪነቱ እና ከገዳይነቱ አንፃር የጁምዐ እና የጀመዐ ሰላት ለመተውና ለማስቆም የሚያስገደድ ሸሪዐዊ ምክንያት በመሆኑ ፈታዋ ከተሰጠበት ከዛሬ መጋቢት 22 ቀን 2012 ጀምሮ በሽታው በሰው ልጆች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት መቆሙ በጤና ባለሙያዎች እስከሚረጋገጥበት ጊዜ ድረስ የጁምዐ እና የጀመዐ ሰላት ታግዶ እንዲቆይ የኡለማ ምክር ቤት ወስኗል።
#የኮኮሮና_ቫይረስ_ስርጭት_ወቅታዊ_መረጃ
√ ማክሰኞ መጋቢት 22 ምሽት 02:00 ላይ
በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሟቾቹ ቁጥር 40 ሺህ ያለፈ ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 824,559 ደርሰዋል። በአሜሪካ ብቻ የተጠቂዎች ቁጥር 175 ሺህ አልፏል ፣ በእንግሊዝ በአንድ ቀን ሪከርድ የሆነ በርካታ ሰው ሞቶባታል
በጣልያን ዛሬም የ837 ሰው ሕይወት ተቀጭቷል
ስፔን ዛሬ 553 ሰው ሞቶ 6461አዲስ ኬዝም ተገኝቷል
በብሪታኒያ ዛሬ 381 ሰው ሞቶ 3,009 ኬዝም ተገኝቷል
አሜሪካ ዛሬ ብቻ እስካሁን 283 ሰው ሲሞትባት 11,881 አዲስ ኬዥም አስተናግዳለች ነጠቅላላው 175,669 ኬዝና 3,424 ሞት አስተናግዳለች።
በኢራን 141 ሰው ሲሞት +3,110 አዲስ ኬዝ ተገኝቷል
ኔዘርላንድ ዛሬ +175 ሰው ሞቶባት 845 እዲስ ኬዝም አላት
በቤልጅየም ዛሬ 192 ሰው ሞቶ 876 አዲስ ኬዝም ተመዝግቧል
በሳውዲ አረቢያ ዛሬ 110 አዲስ ኬዝና 2 ሞት የተመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ የቫይረሱ ኬዝ 1,563 ሲሆን 10 ሞትም ተገኝቶባታል
በእስራኤል ዛሬ 136 አዲስ ኬዝና 1 ሞት የተመዘገበ ሲሆን በጠቅላላ በሀገሪቱ 4,831 ኬዝና የ17 ሰዎች ሕይወት ደግሞ ተቀጥፏል።
በአረብ ኢምሬትስ ዛሬ 53 ኬዝና 1 ሞት ተገኝቷል
አልጄሪያ ዛሬ ብቻ 9 ሰው ሲሞትባት 132 ተጨማሪ ኬዝም አላት
ማይናማር ፣ ታንዛኒያ ማዮቴ እና ቤላሩስ ለሀገራቸው የመጀመሪያ የሆነ የሞት ሪፓርት አድርገዋል
በሀገራችን ዛሬ 3 ኬዝ ተገኝቶ ጠቅላላ የተጠቂዎች ቁጥር ወደ 25 ከፍ ሲል 2ቱ ማገገማቸውም ጤና ሚኒስትር አሳውቋል።
824,559 ጠቅላላ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ
40,673 ጠቅላላ እስካሁን የሟቾች ቁጥር
174,359 እስካሁን አገግመው የወጡ
609,527 አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው
578,617 መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ (95%)
30,910 አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ (5%)
* መረጃዎቹ እየመረጥን ያቀረብነው እንጂ የሁሉንም ሀገራት አለመሆኑን እንድታውቁልን እንዲሁም ይህ የዛሬ ወቅታዊ እንጂ የ24 ሰዓት ውጤት አይደለም።
────────────
👍👍👉👉አንቺ ( አንተ ) ለኔ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ሰዎች መሐል ( አንዱ ) አንዷ ነሽ (ነህ)።
እናም ከወረርሽኙ በኋላ ላይሽ(ህ) እፈልጋለሁ 💞💞💚💛💖
❤ ከኮሮና ቫይረስ በኋላ ማየት ለምትፈልጉት ሰው ሁሉ ይሄንን መልዕክ ላኩላቸው ።🔴🔵🔴🔵🔺🔻
የምትወዱኝ ከሆነ ለኔም መልሰው ይላኩልኝ ። 💯💯stay at home✔✔✔✔🔑🔑🔑🎯🎯
## ## ለማስታወስ ፣። ሼር
ነገ በፈረንጆቹ April 1 ነው በዚህ ቀን ደግሞ በርካታ የውሸት ጉዳዮች የሚስታናገዱበት April fool's የሚሉት የፈረንጆች ቀልድ አለ ይህ ጉዳይ በእኛ ሀገርም ከአመታት ወዲህ ተቀብለውት ሰውን በሀሰት ማስደንገጥ እየተለመደ ይገኛል።
ስለዚህ አሁን ለማስታወስ የመጣነው ነገ በርካታ የውሸት መረጃዎች ሊለቀቁ ስለሚችሉ እንድትጠነቀቁ ለማስታወስ ነው በዚህ አጋጣሚ በኮሮና ቫይረስ ላይ የሀሰት ወሬዎች ልኖሩ ይችላሉ።ጥንቃቄ
ሼር በማድረግ ወዳጆን ነገ እንዳይሸወደ፣ እንዳይደነግጥ ያስታውሱት።
#የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ
እሁድ መጋቢት 23 እስከ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ድረስ
እንደምን አደራችሁ ክቡራን የሰው ልጆች ፣ በአለማችን ከ200 ሀገራትና ግዛቶችን ያዳረሰው የወቅቱ የሰው ልጆች ፈተና የሆነው የኮሮና ቫይረስ 858,892 ሰዎችን ለክፎ 42,158 ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳርጓል
እንዲሁም 4,378 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
178,100 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል
638,634 ሰዎች አሁን ላይ ቫይረሱ ይገኝባቸዋል
────────────
በጣልያን ቫይረሱ አሁንም የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ +837 ሰዎች ሲሞቱባት ተጨማሪ +4,053 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
───────────
አሜሪካ በቫይረሱ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 2ኛዋ ሀገር ነች +748 ሰዎች ሲሞቱባት +24,748 አዳዲስ ኬዞችንም አስተናግዳለች።
───────────
ስፔንም በቫይረሱ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 2ኛዋ ሀገር ከአሜሪካ ጋር እኩል +748 ሰዎች ሲሞቱባት +7,967 አዳዲስ ኬዞችንም አስተናግዳለች።
─────
በጠቅላላ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
1ኛ 12,428 ጣልያን
2ኛ 8,464 ስፔን
3ኛ 3,889 አሜሪካ
4ኛ 3,523 ፈረንሳይ
5ኛ 3,305 ቻይና
6ኛ 2,898 ኢራን
በሚገርም ሁኔታ ቻይና በሽታውን እየተቆጣጠረችው ትገኛለች በዚህ በ 24 ሰአት ብቻ የሞተባት የሰው ብዛት 5 ብቻ ነው አዲስ በበሽታው የተያዘባት 79 ብቻ ነው።
──────────────
በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት
1ኛ 188,530 ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ
2ኛ 105,793 ጣልያን
3ኛ 95,923 ስፔን
4ኛ 81,518 ቻይና
5ኛ 71,880 ጀርመን
6ኛ 52,138 ፈረንሳይ
7ኛ 44,605 ኢራን
───────────────
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው መጋቢት 03-2012 ሲሆን ዛሬ ላይ የተጠቂዎች ቁጥር 26 ደርሷል።
──────────────
የኮሮና ቫይረስን በጋራ እና በግል እንከላከል
የእጃችንን ንፅህና በአግባቡ እንጠብቅ
ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ አንገኝ
ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀት እንጠብቅ!
መልካም ውሎ ይሁንላችሁ!
አዘጋጅ ሙሀመድ አሚን
ስፒዶሜትር ዌብሳይት ላይ ነው
ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ ሲፅፉ ካልፈጠኑ ወይም መፃፍ ካልቻሉ የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ ይመልከቱ እና ይለማመዱ።
==============================
• ሀ ፡ h ሁ ፡hu ሂ ፡hi ሃ ፡ ha ሄ ፡hy ህ ፡he ሆ ፡ho
• ለ ፡l ሉ ፡lu ሊ፡li ላ ፡la ሌ፡ly ል፡le ሎ፡lo
• ሐ፡shift +h ሑ፡shift +hu ሒ፡shift +hi ሓ፡shift +ha ሔ፡ shift + hy ሕ፡shift +he ሖ፡shift +ho
• መ፡m ሙ፡mu ሚ፡mi ማ፡ma ሜ፡my ም፡me ሞ፡mo
• ሠ፡shift + s ሡ፡shift + su ሢ፡shift + si ሣ፡shift+sa ሤ፡shift + sy ሥ፡shift + se ሦ፡shift + so
• ረ፡r ሩ፡ru ሪ፡ri ራ፡ra ሬ፡ry ር፡re ሮ፡ro
• ሰ፡s ሱ፡su ሲ፡si ሳ፡sa ሴ፡sy ስ፡se ሶ፡so
• ሸ፡caps locks ሹ፡caps lock+su ሺ፡caps lock+si ሻ፡caps lock+sa ሼ፡caps lock+sy ሽ፡caps lock+se ሾ፡caps lock+so
• ቀ፡q ቁ፡qu ቂ፡qi ቃ፡qa ቄ፡qy ቅ፡qe ቆ፡qo
• በ፡b ቡ፡bu ቢ፡bi ባ፡ba ቤ፡by ብ፡be ቦ፡bo
• ተ፡t ቱ፡tu ቲ፡ti ታ፡ta ቴ፡ty ት፡te ቶ፡to
• ቸ፡c ቹ፡cu ቺ፡ci ቻ፡ca ቼ፡cy ች፡ce ቾ፡co
• ነ፡n ኑ፡nu ኒ፡ni ና፡na ኔ፡ny ን፡ne ኖ፡no
• ኘ፡shift +n ኙ፡shift +nu ኚ፡shift+ni ኛ፡shift +na ኜ፡ shift +ny ኝ፡shift + ne ኞ፡shift +no
• ከ፡ka ኩ፡ku ኪ፡ki ካ፡ka ኬ፡ky ክ፡ke ኮ፡ko
• ኸ፡capslock+ shift+ h ኹ፡capslock+shift+hu ኺ፡ capslock+shift +hi ኻ፡capslock+
• Shift +ha ኼ፡ Capslock+ Shift +hy ኽ፡Capslock+ Shift+ he ኾ፡Capslock+ Shift + ho
• ኀ፡ capslock + h ኁ፡ capslock + hu ኂ፡ capslock + hi ኃ፡ capslock + ha ኄ፡ capslock + hy ኅ፡ capslock + he ኆ፡ capslock + ho
• አ ፡ x ኡ፡xu ኢ፡xi ኣ፡xa ኤ፡xy እ፡xe ኦ፡xo
• ዐ፡shift +x ዑ፡shift +xu ዒ፡shift +xi ዓ፡shift +xa ዔ፡ shift +xy ዕ፡shift +xe ዖ፡shift +xo
• ወ፡w ዉ፡wu ዊ፡wi ዋ፡wa ዌ፡wy ው፡ we ዎ፡wo
• ዘ፡z ዙ፡zu ዚ፡zi ዛ፡za ዜ፡zy ዝ፡ze ዞ፡zo
• ዠ፡shift + z ዡ፡shift + zu ዢ፡shift + zi ዣ፡shift +zaዤ፡shift + zy ዥ፡shift + ze ዦ፡ shift + zo
• ፈ፡f ፉ፡fu ፊ፡fi ፋ፡fa ፌ፡fy ፍ፡fe ፎ፡fo
• ፐ፡p ፑ፡pu ፒ፡pi ፓ፡pa ፔ፡py ፕ፡pe ፖ፡po
• ገ፡g ጉ፡gu ጊ፡gi ጋ፡ga ጌ፡gy ግ፡ge ጎ፡go
• ደ፡d ዱ፡du ዲ፡di ዳ፡da ዴ፡dy ድ፡de ዶ፡do
• ጠ ፡ shift + t ጡ፡ shift + tu ጢ፡ shift + ti ጣ፡ shift+ta ጤ፡ shift + ty ጥ፡ shift + te ጦ፡ shift + to
• ጨ፡ shift +c ጩ፡shift +cu ጪ፡shift +ci ጫ፡shift+caጬ፡shift +cy ጭ፡shift +ce ጮ፡shift +co
• ጸ፡capslock + t ጹ፡capslock + tu ጺ፡capslock + ti ጻ፡capslock + ta ጼ፡ capslock + ty ጽ፡capslock + t ጾ፡capslock + to
• ፀ፡capslock+ shift + t ፁ፡capslock + shift + tu ፂ፡capslock + shift + ti ፃ፡ capslock + shift + t ፄ፡capslock + shift + ty ፅ፡ capslock + shift + te ፆ፡capslock + shift + to
• ጀ፡j ጁ፡ju ጂ፡ji ጃ፡ja ጄ፡jy ጅ፡je ጆ፡jo
• ቨ፡v ቩ፡vu ቪ፡vi ቫ፡va ቬ፡vy ቭ፡ve ቮ፡vo
• ቋ፡Capslock + qwa ቧ፡Capslock + bwa ቷ፡Capslock + twa ኟ፡Capslock + Shift + nwa ቿ፡Capslock + cwa ሟ፡ Capslock + mwa ቷ፡Capslock + twa ጓ፡Capslock + gwa ፏ፡Capslock + fwa ሯ፡Capslock +• rwa ዷ፡Capslock + dwa ቯ፡Capslock + vwa ኋ፡ Capslock + hwa ዟ፡Capslock + zwa ዧ፡Capslock + Shif +zwa ኗ፡Capslock + nwa ሏ፡ Capslock + lwa ኳ፡Capslock + kwa ሷ፡Capslock + swa ጇ፡Capslock + jwa ጧ፡ Capslock + twa
(መረጃ ጠቃሚ ነዉ!)
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
👍3❤1
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት (3) ሰዎች መገኘታቸው ተረጋግጠዋል::
----------------------------
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህ መረጃ እስከ ተዘጋጀበት ሰዓት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 68 የላብራቶሪ ምርመራ አካሄዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት (3) ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጧል፡፡ በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ ዘጠኝ (29) ደርሷል፡፡
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሶስት ግለሰቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ የመጀመሪያዋ ታማሚ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ጅቡቲ፣ ብራዚል፣ ህንድ እና የመጨረሻ በረራዋ ኮንጎ ብራዛቪል ነው፡፡ የበሽታውን ምልክት በማሳየቷ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆና በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዘች መሆኗ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሁለተኛው ታማሚ የ 26 ዓመት ወንድ ሲሆን የስራ ባህሪው ከተለያዩ ተጓዥ መንገደኞች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡ ሶስተኛው ታማሚ የ32 ዓመት ወንድ ሲሆን ቀደም ብሎ በበሽታው መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ ክትትል ሲደረግለት የነበረ ሲሆን በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሶስቱም ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሌሎች ሰዎች የመለይት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ አምስት (25) ታማሚዎች ሲኖሩ ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡ ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገበር እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡
👍1
#አለምአቀፍ_የኮሮና_ስርጭት_ከምሽቱ_2:00_ረቡዕ_መጋቢት_23_2012
በመጀመሪያ ሁላችንም በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ ውድ ወንድሞችና እህቶች።
በተቻለን መጠን በመንግሥትና በሀይማኖት አባቶቻችን የሚነገረንን ከሮናን ለመከላከል የሚወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እናድርግ።
ከዚህ በታች በአለማችን የተከናወነውን የCOVID-19 ወይም ኮሮና መረጃን እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራለሁ።
➤በሽታው ከ 200 አገራትን በላይ አዳርሷል
➤በአለማችን ላይ አጠቃላይ ኬዝ 903,560 ሲሆን አጠቃላይ ሞት ደግሞ 45,320 ህይወታቸውን አጥተዋል እንዲሁም 190,660 ከበሽታው አገግመዋል።
➤እስከ ዛሬው እለት በሀገራችን 29 በኮሮና ቫይርስ የተያዙና ሁለት ከበሽታው ያገገመ መሆኑም መረጃው ያሳየናል።
➤በአለማችን ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው አሜሪካ ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 200,296 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 11,739 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን በሁለተኛነት ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው ጣሊያን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 110,574 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 4,782 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን በሶስተኝነት ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው ስፔን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 102,136 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 6,213 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን ብዙ በአራተኝነት ኬዞችን ያስመዘገበችው ቻይና ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 81,554 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 36 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል። በዚህም ቻይና በጣም ከሚገባው በላይ በሽታውን እየተቆጣጠረች መሆንን ያሳየናል።
➤በ 5ኛ ጀርመን በጠቅላላ ኬዝ 75,754 አዲስ ኬዝ 4,946
➤በ 6ኛ ፈረንሳይ በጠቅላላ ኬዝ 52,128 አዲስ ኬዝ መረጃው አልተሞላም።
➤በ 7ኛ ኢራን በጠቅላላ ኬዝ 47,593 አዲስ ኬዝ 2,988
➤በ 8ኛ እንግሊዝ ስትሆን በጠቅላላ ኬዝ 29,474 አዲስ ኬዝ 4,324
=============================
የሞት መረጃ
----------
1ኛ ጣሊያን ጠቅላላ 13,155 አዲስ ሞት 727
2ኛ ስፔን ጠቅላይ ሞት 9,053 አዲስ ሞት 589
3ኛ አሜሪካ ጠቅላይ ሞት 4,394 አዲስ ሞት 341
4ኛ ፈረንሳይ ጠቅላይ ሞት 3,523 አዲስ ሞት አልተሞላም
4ኛ ቻይና ጠቅላይ ሞት 3,312 አዲስ ሞት 589
5ኛ ኢራን ጠቅላላ ሞት 3,036 አዲስ ሞት 138
6ኛ እንግሊዝ ጠቅላይ ሞት 2,352 አዲስ ሞት 563
አዘጋጅ ሙሀመድ አሚን
አላህ ሀገራችን አለማችንን ከዚህ በሽታ ነጻ ያድርግልን።
ሁላችንም በዱአ(ጸሎት) እንድርግ።
መልካም ምሽት።
የመረጃ ምንጭ ወርልዶሜትርስ።
══════❁✿❁ ══════
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
(በጣም ጠቃሚ መረጃ)
በቻይና ሰዎች የሰጧቸው ዋና ዋና ጠቃሚ ምክሮች:-
.
#1. ሁለት አይነት ጫማ ይኑርዎት። አንዱ ከቤት ውጪ የሚጠቀሙበት ሲሆን ሌላኛው ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበት ይሆናል። ከቤት ውጪ የሚጠቀሙበትን በፍጹም ወደ ቤት ውስጥ አያስገቡ። ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበትን በፍጹም ወደ ውጪ አያውጡ።
#2. አንድ የተለየ ጠረጴዛ ይኑርዎት። ከውጪ የሚገዟቸውን እቃዎች ለማኖር የሚያገለግል አንድ የተለየ ጠረጴዛ ይኑርዎት። ከውጪ የሚገዟቸውን እቃዎች በሙሉ ለምሳሌ እንደ መድሐኒት: መጠጦች: አትክልቶች እና ሌሎችንም ሳይነኩ ለ24 ሰዓት በጠረጴዛው እንዲቆዩ ያድርጉ።
#3. በተቻለ መጠን የገንዘብ ኖቶችንም ሆነ ሳንቲሞችን አይስጡ: አይቀበሉ። የገንዘብ ኖቶችንም ሆነ ሳንቲሞችን ወደ ወደ ቤት የሚያመጡ ከሆነ ለዚህ ጉዳይ ለይተው ባስቀመጡት ጠረጴዛ ላይ ለ24 ሰዓት አቆይተው ይጠቀሙ።
#4. ሁሉንም አይነት አትክልቶች ማለትም ቀይ ሽንኩርት: ነጭ ሽንኩርት: ድንች እና ሌሎችንም በፈላ ውሃ ሙልጭ አድርገው ይጠቡ። በፈላ ውሃ ሊታጠቡ የማይችሉ አትክልቶችን አይግዙ።
#5. ከቤት ከወጡ በተቻለ መጠን የእጅ ስልክዎን ይዘው አይሂዱ። ይዘው ከወጡ ደግሞ ወደ ቤት ሲመልሱ በአልኮል ያጽዱ።
#6. ከቤት ከወጡ በተቻለ መጠን የቤት ቁልፎችን ይዘው አይውጡ። ይዘው ከወጡ ደግሞ ወደ ቤት ሲመልሱ በአልኮል ያጽዱ።
#7. ከቤት ወጥተው ሲመልሱ እጅዎንና ፊትዎን በሳሙና ይታጠቡ። ቤት እንደተመለሱ የለበሱትን ልብስ አውልቀው እንዲታጠብ ያድርጉ።
#8. ሴት እህቶቻችን ከቤት ስትወጡ ጸጉራችሁ በአግባቡ መጠቅለሉን አረጋግጡ:: ጸጉራችሁን በእጃችሁ አትነካኩ:: ፊታችሁን ጸጉር በነካ እጃችሁ አትንኩ።
#9. አትክልት ለመግዛት ሲሄዱ የእጅ ጓንት ያድርጉ። ወይም አትክልቶችን ሲያነሱ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በሁለቱም እጅዎት ማጥለቅዎትን እርግጠኛ ይሁኑ። ወደ ቤት ሲመልሱ የእጅ ጓንትዎን ማጠብዎን አይዘንጉ። በፕላስቲክ ከረጢቶች ተጠቅመው ከሆነ ወደ ቤት ሲመልሱ ወይም ወዲያውን ከተጠቀሙ በኋላ ያስወግዱ።
#10. ሁልጊዜ ከቤት ከመውጣትዎ በፊት ራስዎን እና የሚያመጧቸውን ነገሮች ደህንነት እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ያቅዱና በቂ ዝግጅት ያድርጉ።
#11. በጣም የግድ ካልሆነ በስተቀር ምግብ ወይም መድሐኒት ለመግዛት ባይሰለፉ ይመረጣል። መሰለፉ ደግሞ የግድ ከሆነ እስከ ሁለት ሜትር ርቀትዎን ይጠብቁ።
#12. ከውሾች እና ድመቶች ጋር ያለዎትን ንክኪ ያስወግዱ።
#13. በተቻለ መጠን አረጋውያን ወደ ውጪ ባይወጡ ይመክራል። ቤት ውስጥ ያሉ ወይም በአካባቢው ያሉ ሰዎች ለአረጋውያን የሚፈልጉትን ነገር ገዝተው ቢያመጡላቸው ይመክራል።
#14. ሁልጊዜ ከቤትዎ ከመውጣትዎ በፊት ከላይ የተጠቀሱትን መልዕክቶች በመመልከት አቅደው ተግባራዊ ያድርጉ።
ኮሮና ለመከላከል
ከላይ የተባሉትን መተግበር!
#ያለፉት_24_ሰአታት_አለምአቀፍ_የኮሮና_ስርጭት_ከጠዋቱ_3:00_ሀሙስ_መጋቢት_24_2012
በመጀመሪያ ሁላችንም በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ ውድ ወንድሞችና እህቶች።
በተቻለን መጠን በመንግሥትና በሀይማኖት አባቶቻችን የሚነገረንን ከሮናን ለመከላከል የሚወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እናድርግ።
ከዚህ በታች በአለማችን የተከናወነውን የCOVID-19 ወይም ኮሮና መረጃን እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራለሁ።
➤በሽታው ከ 200 አገራትን በላይ አዳርሷል
➤በአለማችን ላይ አጠቃላይ ኬዝ 935,197 ሲሆን አጠቃላይ ሞት ደግሞ 47,129 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል። ህይወታቸውን አጥተዋል እንዲሁም 193,989 ከበሽታው አገግመዋል።
➤እስከ ዛሬው እለት በሀገራችን 29 በኮሮና ቫይርስ የተያዙና ሁለት ከበሽታው ያገገመ መሆኑም መረጃው ያሳየናል።
➤በአለማችን ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው አሜሪካ ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 216,003 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 26,473 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
እንዲሁም 1,049 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
➤በአለማችን በሁለተኛነት ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው ጣሊያን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 110,574 ሲሆን በ 24 ሰአታት ብቻ 4,782 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።
➤በአለማችን በሶስተኝነት ብዙ ኬዞችን ያስመዘገበችው ስፔን ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 104,118 ሲሆን በ 24 ሰአታት ብቻ ደግሞ 8,196 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል።

➤በአለማችን ብዙ በአራተኝነት ኬዞችን ያስመዘገበችው ቻይና ስትሆን እስከዛሬ ድርስ 81,554 ሲሆን ዛሬ ደግሞ 36 አዲስ ኬዞችን ተመዝግቧል። በዚህም ቻይና በጣም ከሚገባው በላይ በሽታውን እየተቆጣጠረች መሆንን ያሳየናል።
➤በ 5ኛ ጀርመን በጠቅላላ ኬዝ 77,981 አዲስ ኬዝ 6,173
➤በ 6ኛ ፈረንሳይ በጠቅላላ ኬዝ 56,989 አዲስ ኬዝ 4,861
➤በ 7ኛ ኢራን በጠቅላላ ኬዝ 47,593 አዲስ ኬዝ 2,988
➤በ 8ኛ እንግሊዝ ስትሆን በጠቅላላ ኬዝ 29,474 አዲስ ኬዝ 4,324
=============================
የሞት መረጃ
----------
1ኛ ጣሊያን ጠቅላላ 13,155 አዲስ ሞት 727 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
2ኛ ስፔን ጠቅላይ ሞት 9,381 አዲስ ሞት 923 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
3ኛ አሜሪካ ጠቅላይ ሞት 5,102 አዲስ ሞት 1,049 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
4ኛ ፈረንሳይ ጠቅላላ ሞት 4,032 አዲስ 509 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
4ኛ ቻይና ጠቅላይ ሞት 3,312 አዲስ ሞት 7 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
5ኛ ኢራን ጠቅላላ ሞት 3,036 አዲስ ሞት 138 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
6ኛ እንግሊዝ ጠቅላይ ሞት 2,352 አዲስ ሞት 563 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል።
አዘጋጅ ሙሀመድ አሚን
አላህ ሀገራችን አለማችንን ከዚህ በሽታ ነጻ ያድርግልን።
ሁላችንም በዱአ(ጸሎት) እንድርግ።
መልካም ምሽት።
የመረጃ ምንጭ ወርልዶሜትርስ።
══════❁✿❁ ══════
ይህ መረጃ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ!
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
በተጨማሪም በፌስቡክ ገፄ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net ይህንን ሊንክ በመጫን ፔጁን like በማድረግ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ
የፌስቡክ ፔጁን Like & share ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ስድስት ተጨማሪ ሰዎች ተገኙ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ይህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 35 እንዳደረሰው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ውስጥ አምስቱ ከአዲስ አበባ አንደኛው ደግሞ ከድሬዳዋ ሲሆን፥ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።
በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው የ35 ዓመት እና የ30 አመት ወንዶች ሲሆኑ፥ መጋቢት 10 መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጡ ናቸው ተብሏል።
ሁለቱም ዜጎች አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የገቡ መሆናቸውንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው።
ሶስተኛው የ28 ዓመት ወጣት፣ አራተኛው የ56 ዓመት ወንድ፣ አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።
ሰዎቹ ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ መሆኑንም ተገልጿል።
ስድስተኛዋ ግለሰብ የ33 ዓመት ሴት ስትሆን በድሬዳዋ ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት የነበራት መሆኑም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል ።