Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ጎግል ፕሌይ ስቶር ብልሽት ለማስተካከል

✅ Google Play Store በአብዛኛዎቹ የAndroid ዘመናዊ ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ ሲሆን በሆነ ምክንያት በዲቫይሱ(ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ መሥራት ሊያቆም ሊያጋጥም ይችላል፡፡

✅ በዚህም ምክንያት በዲቫይሱ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮችን የቅርብ ግዜ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮችን ዳውንሎድ አድርገን መጫን እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የቅርብ ግዜ ማድረግ አንችልም፡፡

✅ Google Play መደብር በእርስዎ ዲቫይስ ላይ የማይሰራ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት አንዳንድ መንገዶችን እጠቁማለሁ

1. የዲቫይሱን ቀን እና ሰዓት ቅንብር(ሴቲንግ) ያስተካክሉ
የተሳሳተ ቀን እና የጊዜ ገደብ ሲኖርዎት የGoogle አገልጋዮች ከአሳሽዎ ጋር ማመሳሰል ችግሮች ያጋጥማቸዋል ለማሰተካከል ወደ ሲስተም ሴቲንግ በመሄድ «ቀን እና ሰዓት» ማስተካከል ይጠበቅብዎታል፡፡
“Automatic date & time” and “Automatic time zone” እንዲሰራ ክፍት ያድርጉ ወይም ማኑዋሊ ቀን እና ሰዓት ያስተካክሉ፡፡

2. ጎግል ፕሌይ ስቶር ከዚህ በፊት ይዞት የነበረውን ዳታ ማጽዳት
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ከዚህ በፊት ተጠቅመናቸው የነበረው ሶፍትዌሮች ዝርዝ ይዞ ይቀመጣል(Cached data) ይሄ በምንፈልገው ጊዜ በፍጥነት ለመክፈት ኢንተርኔት ግንኙነቱ ፍጥነት ባይኖረውም ይረዳናል ነገር ግን Cached data አንዳንድ ጊዜ በPlay Store ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡

✅ በGoogle Play ላይ Cached data ለማጽዳት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: ስቶሬጂ በመክፈት “CLEAR CACHE“.

3. የቅርብ ግዜ የሆነ ጎግል ፕሌይ ስቶር መጫን
በየጊዜው ሶፍትዌሮችን የሚሰሩ ዴቨሎፐሮች ለሰሩት ሶፍትዌር የቅርብ ግዜ ማድረጊያ አብዴተር የሚለቁ ሲሆን በዚህ የቅር ማድረጊያ ላይ የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ይካተታል፡፡.
በተመሳሳይ መልኩ Google የ Play ስቶር አብዴተር በየጊዜው የሚያወጣ ሲሆን እንደሚኖሩበት አገር የሚለቀቀው አብዴት ሊዘገይ ይችላል በቀጥታ የቅርብ ማድረጊያውን(APK ፋይል) ማግኘት ከቸኮሉ APKMirror በማለት ኢንተርኔት መጠቀሚያ ብሮውዘር ላይ ፈልገው ማውረድ ይችላሉ፡፡

4. ጎግል ፕሌይ ስቶር ወደነበረበት የመጀመሪያው ቨርዥን መመለስ
አንዳንዴ የቅርብ ጊዜ የተደረገ የጎግል ፕሌይ ስቶር ስሪት በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ስለሆንም አብዴት የተደረገው በማጥፋት ዲቫይሱን ስንገዛ የነበረውን(factory version ) ጊዜ መመለስ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች በመከተል እናጥፋ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Uninstall Updates”

5. ጎግል ፕሌይ ሰርቪስ መስራቱን ማረጋገጥ
Google Play Services ዋናው ተግባራት የGoogle አገልግሎቶች የሆኑትን Google Play ስቶር፣ ጎግል ማፕ፣ ጎግል ፕላስ ወዘተ አገልግሎቶች አውቶማቲካሊ ግንኙነት እንዲያደርጉ እና አብዴት የሚያደርግ የሚረዳ በመሆኑ እንደ ተጨማሪ መፍትሄ በመውሰድ Google Play Services መስራቱን ያረጋግጡ፡፡

6. ጎግል ፕሌይ ስቶርን ዘግቶ መክፈት
ይህ በአብዛኛው ተጠቃሚዎች የሚተገበሩበት የተለመደ ዘዴ ነው፡፡ ማድረግ ያለብዎት ነገር Google Play Storeን በመዝጋት እንደገና ማስጀመር( ለሌሎች አፕ ይሰራል) ችግሩን ሊፈታው ይችላል
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Force Stop” የሚለውን በመጠቀም መዝጋት እና እንደገና ይክፈቱ

7. ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት
ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ተመራጭ መፍትሄ ሲሆን ብዙውን ግዜ ይሰራል ምክንያቱም ስማርትፎን ስልኮች አጥፍተን ዳግም ማስጀመር በዲቫይሱ ላይ ያሉትን አፕ ያረጋጋል፡፡ በተቻለ መጠን አንድ አፕ ከወትሮው የተለየ ተግባር ካመጣ ዳግም አጥፍተን ስናስጀምር የተሻለ አፈጻጸም እና ችግሩን መፍታት ይችላል፡፡

8. ዲቫይሱን አንድሮድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዳግም ማስጀመር
ከላይ በጠቀስኩት መፍትሄ ምንም የማይሰራ ከሆነ ዲቫይሱን ፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ማድረግ በዚህ ሂደት በዲቫይሱ ላይ ያሉትን ዳታ፣ የተጫኑ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር እንደዚሁም የተጠቃሚውን አካውንት የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠፋል፡፡
በርካታ ችግሮች በዲቫይሱ ላይ ካልገጠመዎት በስተቀር የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ባትጠቀሙ እመርጣለሁ ዳግም ለማስጀመር ከወሰኑ ሚሞሪው ያውጡ መጠባበቂያ መውሰድዎን አይርሱ፡፡

ይሄን ችግር ለመፍታት ሊያግዝ የሚችል የተሻለ መፍትሄዎች ካለዎት አስተያየትዎን ይስጡን እንዲሁም ለ ጉዋደኞቹዎ ያካፍሉ
👍30❤8🔥3😁1
Delete Format የተደረገ ሜሞሪ፣ ፍላሽ፣ ኮምፒውተር ሀርድዲሰክ ፋይል ፎቶግራፎችን፣ ቪዲዮዎችን፣ የጠፉ ዶክመንቶችን ለምሳሌ ሪሰርች፣ መጽሀፎችን በቃ ምን አለፋችሁ ማንኛውንም መረጃችሁ ቢጠፋ ምርጥ መፍትሄ ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ።
መታየት ያለበት ቪዲዮ
👇👇ከታች ያለውን ሊንክ ይመልከቱ👇👇
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
❤18👍9👏2
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ አጭበርባሪዎች በዝተዋል፤ ይጠንቀቁ!
******
አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመርን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ ማጭበርበሪያ ዘዴዎችን ተጠቅመው የመረጃና ገንዘብ ምዝበራ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡
አጭበርባሪዎች ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ጥቂቶቹን እና መከላከያ መንገዶችን እንጠቁማችሁ፡፡

1. ፊሺንግ (Phishing)

በዚህ የሶሻል ምህንድስና ጥቃት አጭበርባሪዎች ማኅበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በተለያዩ ዲጂታል የመልእክት መለዋወጫ መንገዶች ሀሰተኛ መልእክቶችን በመላክ ተጠቃሚዎች የግል እና ሌሎች እንደ ሂሳብ፣ የይለፍ ቃል የመሳሰሉ መረጃዎቻቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ፣ እንዲሁም አደገኛ ሊንኮችን እንዲከፍቱ እና ሶፍትዌሮችን እንዲጭኑ ያደርጋሉ፡፡

2. የኢንቨስትመንት ማጭበርበሮች (Investment Scams):

የውሸት በሆኑ ወይም በሌሉ ምርቶች ወይም ንግዶች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያበረታቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ማስታወቂያዎች ተበራክተዋል። ብዙዎችም የምዝበራ ሰለባ ሆነዋል፡፡

3. ነፃ የሙከራ አገልግሎቶች (Free Trial Products):

በሀሰተኛ የምርቶች ነጻ ሙከራ (Free-trial) ማስታወቂያ ሰዎችን በማታለል ለነጻ የምርት ሙከራው እንዲመዘገቡና የክፍያ ካርድ መረጃቸውን እንዲያስገቡ የማድረግ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው፡፡ ተጠቂው ከሱ እውቅና ውጪ ውል ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ክፍያ ያለባለቤቱ እውቅና ተቀናሽ ይሆናል።

4. የኦንላይን ግብይት ማጭበርበሮች

በኦንላይን ግብይት የተለያዩ ምርቶችን በቅናሽ እንሸጣለን በሚል የምዝበራ ተግባር ላይ የተሠማሩ አጭበርባሪዎች አሉና ይጠንቀቁ፡፡

5. ክሊክቤይት (Clickbait)፡

ይህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጠቃሚዎችን ትኩረት የሚስቡ ጉዳዮችን የያዙ ይዘቶችን በማውጣት ተጠቃሚዎች ይበልጥ ለማወቅ ሊንኩን እንዲጫኑ የማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡ ይህን ዘዴ አጭበርባሪዎች ሲጠቀሙበት ተጠቂው ጥቃት አድራሾቹ ወደ ሚመሩት ማስፈንጠሪያ በሚገባበት ጊዜ የግል መረጃውን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል።

6. የውሸት ጓደኛ ጥያቄዎች (Fake Friend Requests)፡

አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመክፈት ወይም የሌሎችን አካውንቶች በመጥለፍ ወደተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የጓደኝነት ጥያቄ ይልካሉ። እነዚህን ጥያቄዎች መቀበል የእርሶን እና የጓደኞቻችሁን መለያ እንዲጠለፍ እና የግል መረጃ እንዲያፈተልክ ያደርጋል።

7. የሥራ እድል ማጭበርበሮች

ሀሰተኛ የስራ እድል ማስታወቂያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት ይተዋወቃሉ። ገቢዎን ያሳድጉ ወይም ከቤት ሆነው ሥራ ይስሩ በማለት አጓጊ ጥቅማጥቅሞችን በመንገር ተጠቃሚው ቶሎ ውሳኔ እንዲወስን (sense of urgency) በማድርግ ማጭበርበሩን ይፈጽማሉ።
እነዚህ አጭበርባሪዎች የተጠቃሚውን መረጃ የግል እና ሊሎች መረጃዎች ይወስዳሉ ወይም ለሥልጠና ወይም ለሌላ ጉዳይ በቅድሚያ ክፍያ ይጠይቃሉ።

8. ስጦታ

በራሳቸውም ሆነ የሌሎችን ስምና ዝና በመጠቀም ሀሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ገፆችን በመክፈት ተከታይ ስትሆኑ፣ ተከታይ ስታስገቡ፣ ልጥፎችን ስታጋሩ፣ አስተያየት ስትሰጡ፣ ስትወዱ ስጦታ እንሰጣለን በሚሉ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች ያጭበረብራሉ፡፡ እነዚህ አጭበርባሪዎች የተከታዮችን ግላዊ መረጃ ለመውሰድ መልካም አጋጣሚ ይሆንላቸዋል፡፡

እንዴት ከአጭበርባሪዎች ራሳችንን እንጠብቅ?

• ከማያውቁት ግለሰብ የሚደርስዎትን የማኅበራዊ ሚዲያ እንወዳጅ ጥያቄ አይቀበሉ፡፡
• የቅናሽ ማስታወቂያዎችን በጥርጣሬ ይመልከቱ፤
• በኦንላይን ብቻ ለተዋወቁት ግለሰብ ገንዘብ አይላኩ፡፡
• በማኅበራዊ ሚዲያ የግል መረጃዎን አይስጡ።
• የማስታወቂያ አስነጋሪዎችን ህጋዊነት ሳያረጋግጡ ምንም አይነት እርምጃ አይውሰዱ፡፡
• ከማህበራዊ ሚዲያ ጓደኛ የሚመጣን የእርዳታ ጥሪ በጥንቃቄ ይፈትሹ።
• ከማያውቁት አካል በሚደርስዎት አጭር የፅሁፍ መልእክት፣ ኢሜይል ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ መልእክት የሚያገኙትን ማስፈንጠሪያ (link) አይክፈቱ፡፡
• ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን ይከተሉ፡፡
👍80❤7🥰6👎1
የደሞዝ አሰራር እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? ክፍል -1
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
የደሞዝ አሰራር እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? ክፍል -2
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
👍22❤5
የእትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!!!
_______

1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡

2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡

3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
፪=በራሱ ፈቃድ
፫=በጤና ጉድለት
፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
፭=በሞት ናቸው፡፡

4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
፩= በእርጅና
፪=በህመም
፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡

5ኛ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::

6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
፫= የጡረታ መለያ ቁጥር
፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ
ናቸው፡፡

የደሞዝ አሰራር እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? ክፍል -1
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
የደሞዝ አሰራር እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? ክፍል -2
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
👍61❤16👏3🔥2🤔2😁1
🛑 ዳታ ማይኒንግ ምን ዓይነት ጥቅም አለው?

✅ ዳታ ማይኒንግ ብዙ መጠን ያለውን ዳታ በመመርመር እና በመተንተን በተለያዩ መስኮች ችግር ፈቺና ትርጉም አዘል መረጃዎችን ለይቶ ለማወቅ ትልቅ አበርክቶው አለው።

✅ በዘርፉ አሜሪካ፣ ቻይና፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና እስራዔል ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ እና ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ከሚሰሩ ሀገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

✅ ተመራማሪዎች የንግድ ተቋማት እንዲሁም መንግሥታት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔን እንዲያሳልፉ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው የሳይንስ ዳይሬክት ድረ-ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

✅ ዳታ ማይኒንግ እንደ ጤናና ትምህርት ባሉት መስኮች የሚያጠነጥኑ መረጃዎችን በተገቢ መልኩ በመረዳት ዜጋ ተኮር ስራዎች ላይ ለመስራት ዕድል ይፈጥራል፡፡ አገልግሎት ሰጪ እና በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትም የደንበኞችን ፍላጎት በማወቅ እርካታን ለማሳደግ እንዲችሉ ጉልህ ሚና አለው፡፡
#MCT
👍13❤1
✅ ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው?

✅ ይህን ቃል በተለያዩ አጋጣሚዎች ሳንሰማው አንቀርም በተለይ አሁን ላይ ይህ ቃል ለብዝዎቻችን እምዛም አዲስ አይደለም ፤ በተለያዩ ሚዲያ ነክ በሆኑ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ቢዝነሶች አገልግሎታቸውን ሲያስተዋውቁ ከዝርዝራቸው መካከል "ዲጂታል ማርኬቲንግ" የሚል እናገኛለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግ አሁን ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ውጤታማ የማርኬቲንግ ዘዴ ነው" ሲባል እንሰማለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ዘመናዊዉን የማርኬቲንግ ዘርፍ ሊቀላቀሉ እና ቢዝነስዎን ሊያሳድጉ ይገባል" የሚል መልዕክት ያዘሉ የማነቃቂያ ጽሁፎችም አጋጥመውን ይሆናል ... ለመሆኑ ይህ ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው? ከተለመደው የማርኬቲንግ ዘዴስ በምን ይለያል? እውነት ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ቢዝነስን ማሳደግ ይቻላል? በየትኛው ደረጃ ላይ ያሉ ቢዝነሶችስ ናቸው ዲጂታል ማርኬቲንግን መጠቀም የሚችሉት?

✅ እስቲ እነዚህን እና መሰል ከዲጂታል ማርኬቲንግ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በሚመልስ መልኩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ዙርያ አጭር ዳሰሳ እናድርግ።ዝግጁ ናችሁ? ተከተሉኝ፦

✅ በመጀመሪያ ደረጃ ዲጂታል ማርኬቲንግን በቀላሉ እንድንገነዘብ  ስለማርኬቲንግ (Marketing) ጥቅል የሆነ ግንዛቤ እንውሰድ። ማርኬቲንግ (marketing) ማለት   "በምርት እና አገልግሎቶች ላይ የገበያውን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል እሴትን (Value) የማጥናት  ፣ የመፍጠር እና ለተጠቃሚው የማቅረብ ሂደት ነው። " ከዚህ ገለጻ እንደምንረዳው ማርኬቲንግ "ሂደት" (process) ነው። ይህ ሂደት :-  ምርቱን  ወይም አገልግሎቱን ይገዛሉ ተብለው የሚታሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማጥናት እና መለየት ፣ ፍላጎታቸውን መረዳት  እና ችግራቸውን ማዳመጥ ፣ ፍላጎታችውን ሊያሟላ ፤ ችግራቸውንም ሊፈታ የሚችል እሴትን አጥንቶ በምርቱ ወይም አገልግሎቱ ላይ ማከል ፣ ከዚያም ማስተዋወቅ ፣  ቀጥሎም ለተጠቃሚዎች አመቺ በሆነ መልኩ ለሽያጭ ማቅረብ እና ከሽያጩም በኋላ ሸማቹ  ለምርቱ ወይም አገልግሎቱ ያለው ደንበኝነት ዘላቂ እንዲሆን መስራትን አቅፎ የያዘ ነው።

✅ ማርኬቲንግ ማለት በጥቅሉ ይህ ከሆነ፤ ዲጂታል ማርኬቲንግ፡ ዘመናዊ የሆነ አንድ የማርኬቲንግ አካል ሲሆን ፤ ይህም ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን( በዋናነት ኢንተርኔትን በመጠቀም) ደንበኞችን የማፈላለግ ፣ ምርት እና አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ እና ከደንበኞች ጋር ጥሩ ግንኙነትን በመፍጠር ደንበኝነታቸውን ዘላቂ የማድረግ  ሂደት ነው።ይህ  እንግዲህ በአጭሩ ስንገልጸው እንጂ ዲጂታል ማርኬቲንግ ሰፊ እና   የተለያዩ ዘርፎች ያሉት እራሱን የቻለ አንድ መስክ ነው።

✅ ማርኬቲንግ ለየትኛውም ቢዝነስ መሳካት ትልቅን ሚና ከሚጫወቱ መሳሪያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።ዲጂታል ማርኪቲንግ ሾል ላይ ከመዋሉ በፊት ፤  ደንበኞችን ማፈላለግ እና ምርት እና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ የመሰሉ የማርኬቲንግ ስራዎች እንደ ጋዜጣ እና መጽሔት ባሉ የህትመት ውጤቶች ፣ እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ የሚዲያ አውታሮች እንዲሁም በየመንገዱ በተተከሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ይሰራ ነበር።ዲጂታል ማርኬቲንግ ከመጣም በኋላ ቢሆን  እነዚህ የማስተዋወቂያ መንገዶች ዛሬም ድረስ ይሰራባቸዋል።

✅ ኢንተርኔት እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቅ ብቅ ማለታቸውን ተከትሎ ጥቅም ላይ እየዋለ የመጣው ዲጂታል ማርኬቲንግ በተለመዱት የማርኬቲግ ዘዴዎች ለመስራት አስቸጋሪ የነበሩ የማርኬቲንግ  ስራዎችን በቀላሉ እና እጅግ ውጤታማ በሆነ መልኩ በመፈጸም  በማርኬቲንግ ዘርፉ ላይ ከአሰራር ጀምሮ ትልቅን ለውጥ ፈጥሯል።

✅ ምንም እንኳን በኢንተርኔትን አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች ከዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ትልቁን ድራሻ ቢይዙም ፤  ያለ ኢንተርኔት የሚሰሩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ሾር የሚካተቱ የማርኬቲንግ ስራዎች አሉ።ለምሳሌ :- በሞባይል መተግበሪያዎች (mobile apps) እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክቶች (SMS) አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች በዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።ምክንያቱም ዲጂታል ማርኬቲንግ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው "አዳዳኢስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የሚሰራ የማርኬቲንግ ሾል ነው"።

✅ ዲጂታል ማርኬቲንግ "E-CRM"  ላይ የተመሰረተ የንግድ አካሄድ ላይ የሚያተኩር ሲሆን "E-CRM (Electronic Customer Relationship Management)" ቃል በቃል ሲተረጎም "ኤሌክትሮኒክ የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር" እንደማለት ሲሆን ፤ ይህም አንድ ቢዝነስ ወይም ድርጅት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የደንበኞቹን መረጃ የሚያሰባስብበት እንዲሁም ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እና መስተጋብር የሚያስተዳድርበት ስርዓት ነው።
#MCT
👍55❤9
Urban Land Information Management System Graduation የከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት የትግበራ የምረቃ ስነስርዓት MCT

https://youtu.be/Gda4E0o9u7M
https://youtu.be/Gda4E0o9u7M
https://youtu.be/Gda4E0o9u7M
👍15❤4
Myhammed Computer Technology MCT
እናመሰግናለን! 70,000+
MCT YouTube 7️⃣0️⃣0️⃣0️⃣0️⃣+ subscribers ደርሰናል
👇👇👇ሰብስክራይቭ ያድርጉ👇👇👇 https://www.youtube.com/c/MuhammedComputerTechnology
❤20👍11😁3
#Telegram ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለብን 10 ወሳኝ ነገሮች

✔ 1ኛ :- ያለንበትን #ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልክለትን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላኪያዋን ከፍተን location የሚለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::

✔ 2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን password ማዘጋጀት ይቻላል መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::

✔ 3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ብር እንዳይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የሚለዉን እንነካለን ከዛ
when using mobile data -OF-አድርጉት ::

✔4ኛ :- የላክነዉን message ከደረሰ በኃላ delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የላክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የሚለውን Also delete receive የሚለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::

5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት

✅6ኛ :- በተለይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከሚሰጠን የመልክ ምርጫ የፈለግነዉን እንመርጣለን ::

✔7ኛ :- ቴሌግራም ያሉ ጽሁፎች አልነበብ እያሎት ተቸግረዋል ማለት ፊደሎቹ አንሰዉ ለዓይን አልታይ ካለ ፊደሎቹን ትልቅh ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፈለግነዉን ያህል ትልቅ ማድረግ ይቻላል ::

✔8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የሚለውን ነክተን create new channel የሚለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፈለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::

✔9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ግሩፕ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የሚለውን እንነካለን ከዛ create new group የሚለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፈለግነዉን የግሩፕ ስም እናስገባለን ::

✔10ኛ :- እንዴት አድርገን profile photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የሚለውን በመንካት የፈለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ፡፡

https://t.me/MuhammedComputerTechnology
👍109❤23🙏11🤣11😁5👎2