Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
C++ Programing In Amharic Part I Yohannes Ezezew.pdf
16.5 MB
C++ ኘሮግራሚንግ በአማርኛ ክፍል አንድ (C++ Programing In Amharic Part I)

በጣም ገራሚ መጽሀፍ ነው በአቶ ዮሀንስ እዘዘው የተዘጋጄ ነው።

የገጽ ብዛት 346


📖🎖⚠️⚠️⚠️ሼር አርጉላቸው 👇👇

📌Join and share 👇👇👇


✦Join➬ @EthiopiaDigitalLibrary
✦Join➬ @EthiopiaDigitalLibrary
👍476🔥5👻2🕊1
በአማራ ክልል የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የስራና ስልጠና መምሪያ (ቴክኒክና ሙያ መምሪያ) የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር የዲጅታል መረጃ አያያዝ ስርአት (ሶፍትዌር) በማበልጸግ ወደ ስራ ማስገባትና ማስመረቅ ችለናል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አይተነው ታዴ መርቀው ወደ ስራ ማስገባት ችለዋል።

ይህ ሶፍትዌር በዞኑ ያሉትን ሁሉንም አንድ ማእከላትን፣ ኮሌጆችን፣ የከተማና የወረዳ የስራና ስልጠና ጽ/ቤቶችን እስከ ዞን ድረስ የሚያስተሳስር የዲጅታል ቴክኖሎጅ ነው።

ሶፍትዌሩ በአማራ ክልል ያሉትን እንዲሁም እንደ ሀገር የሚያስተሳስር እንዲሆን በማድረግ የተሰራ ስራ ነው።

ጊዜው የዲጅታል የቴክኖሎጂ ነው፡፡
ህልምዎን እውን የሚያደርጉ ሲስተሞችን, ድረ-ገጾችን (ዌብሳይቶችን) ለማሰራት  ይደውሉ። አሰራርዎን ዘመናዊ ያድርጉ!

🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
email: mct16plc@gmail.com
Facebook:- https://m.facebook.com/MuhammedComputerTechnology/
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@muhammedcomputertechnology
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
👍287👏1
ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ለሀገር እድገት በርካታ አስተዋጽኦዎች አሉት። እነዚህ ዋና ዋና አስተዋጽኦዎች እንደሚከተለው ይገኛሉ፦

1. ኢኮኖሚያዊ እድገት
- IT አዳዲስ የስራ እድሎችን ይፈጥራል፣ ለምሳሌ በሶፍትዌር ልማት፣ የውሂብ ትንተና፣ የሲበር ደህንነት፣ እና የመሳሰሉት።
- የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) እንዲጨምር ያስተዋፅኣል።
- የማህበራዊ ሚዲያ እና የኢ-ኮሜርስ ስራዎች በኩል ትልቅ የኢኮኖሚ እድገት ያስከትላል።

2. የትምህርት ማሻሻያ
- የኦንላይን ትምህርት እና የዲጂታል መሳሪያዎች በርካታ ሰዎች ትምህርት እንዲያገኙ ያስችላሉ።
- የማህበረሰብ ደረጃ የሆነ የትምህርት እድል ይፈጥራል።

3. የጤና አገልግሎት ማሻሻያ
- የኢ-ጤና (e-health) ስርዓቶች የጤና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ቀላል እና ውጤታማ እንዲሆን ያስችላሉ።
- የበሽታዎች አስተዳደር እና የተገኙ መረጃዎች ማከማቸት ቀላል ይሆናል።

4. የመንግስት አገልግሎቶች ማሻሻያ
- የኢ-መንግስት (e-government) ስርዓቶች የመንግስት አገልግሎቶችን የበለጠ ቀላል እና ተደራሽ ያደርጋሉ።
- የስርዓተ-ፆታ ማሻሻያ እና የስራ አፈጻጸም ማሻሻያ ያስከትላል።

5. የማህበረሰብ እድገት
- የመረጃ እና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ማህበረሰብን አንድ ላይ ያጠቃልላሉ።
- የማህበራዊ ሚዲያ እና የመረጃ ማሰራጫ መሳሪያዎች የማህበራዊ ለውጥ እንዲፈጠር ያስችላሉ።

6. የግብይት እና የንግድ ማሻሻያ
- የኢ-ኮሜርስ መሳሪያዎች ንግድን ቀላል እና ፈጣን ያደርጋሉ።
- ትናንሽ እና አማካይ ድርጅቶች (SMEs) በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላሉ።

7. የመረጃ ተደራሽነት
- የመረጃ ቴክኖሎጂዎች ሰዎች ከዓለም ዙሪያ ያለውን መረጃ በቀላሉ እንዲደርሱ ያስችላሉ።
- ይህ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ያፋጥናል።

በአጠቃላይ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለሀገር እድገት ቁልፍ አስተዋጽኦ ያለው ነው። የቴክኖሎጂ እድገት በተለይም በልማት ላይ ያሉ ሀገራት እንደ ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጥ እንዲያመጡ ያስችላቸዋል።
👍5117
የአዘና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በዲጂታላይዜሽን ቴክኖሎጂ የወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት በዛሬው ዕለት ይፋ አደረገ።

አዘና ጥር 22/2017 ዓ.ም (አየሁ ጓ/ኮሙኒኬሽን)
በአዊ ብሔ/አስ/አየሁ ጓ/ወ/የአዘና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ መሬት መረጃ አያያዝና አስተዳደር ስረዓትን በማዘመን የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ በማድረግ ለተጠቃሚው/ለደንበኛው ማህበረሰብ የወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት በራሱ አቅም ሶፍት ዌር በማበልጸግ በቅርብ ጊዜ ማስመረቁ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ተቋሙ በዲጂታላይዜሽን ስረዓት አገልግሎት ለመስጠት አጠቃላይ ስራውን አጠናቆ የወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

የተቋሙ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ወንድም ምህረት የወረቀት አልባ አገልግሎትን ለመስጠት በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረጉ ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ ከአደጋ ስጋት ነፃ፣ ለአገልግሎቱ ፈጣን፣ የባለይዞታውን የፋይል ደህንነት የሚጠብቅ፣ ዋስትናው የተረጋገጠ፣ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ከተቋሙ በተሠጠው መለያ ኮድ መሠረት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከሐሜት የፀዳ አገልግሎት የሚያገኝበት መሆኑን አብራርተዋል።

ከተቋሙ አገልግሎት ተጠቃሚው ማህበረሰብ በያዘው መለያ ኮድ መሠረት ከዛሬው ቀን ጀምሮ የወረቀት አልባ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ይፋ ያደረጉት አቶ ወንድም ይህ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ እውን በመሆን በሲስተም የወረቀት አልባ አገልግሎት በመጀመሩ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን ብለዋል።

የአዘና ከተማ መሪ ማ/ቤት የወረቀት አልባ ሲስተም ይፋ ባደረገበት በዛሬው ዕለት በቦታው የተገኙት የወረዳው ከተማና መሠረተ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አየነው ዋሲሁን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ይህ ቴክኖሎጂ እውን እንዲሆን ከማሰብ ጀምሮ ለስኬት እስከሚደርስ የተሳተፉ ለሶፍት ዌሩ አበልፃጊና ባለቤቱ ለአቶ መሀመድ ያሲን፣ ለተቋሙ ስራአስኪያጅና መላ ሠራተኞች፣ ለከተማው ማህበረሰብና የድርሻውን ለተወጡ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የተቋሙ ሠራተኞችም የወረቀት አልባ አገልግሎት/ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ለደንበኞቻቸው ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልፀው ይህ ስራ በስኬት በመጠናቀቁ ደስታቸውን ገልጸዋል።
👍2612
#ፍላሽ_ዲስክ_እንዴት_በፓስዎርድ_ማሰር_ይቻላል?
በፍላሽ ዲስክ የተለያዪ ሚስጥራዊ ዳታዎች እንይዛለን! ከራሳችሁ ውጪ ሌላ ማንም ሰው እንዳያየው የምትፈልጉት ዳታ(ፋይል፣ቪድዮ፣ፎቶዎች ወዘተ) በፍላሽ ዲስክ ትይዛላችሁ።
ስለዚህ ሚስጥራዊ ዳታችሁን ከናንተ ውጪ ማንም ሰው እንዳያየው ወይም እንዳይጠቀምበት የግድ ፍላሽ ዲስኩን በፓስወርድ መቆለፍ ይኖርባችኋል።
እሺ windows 10 የምትጠቀሙ ሰዎች ፍላሽ ዲስካችሁን በፖስወርድ ለመቆለፍ የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል መቆለፍ ትችላላችሁ።
1-ፍላሽ ዲስኩን ኮምፒውተራችሁ ላይ ሰኩት እና"This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ አድርጉት
2- "This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ ስታደርጉት የሚመጣው ቦክስ ውስጥ ፍላሽ ዲስካችሁ ይመጣል
3- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አድርጉ
4- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አ.ስታደርጉ "Turn BitLocker on" የሚለውን ሴሌክት ማድረግ
5- ከዚያ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል፣ የማትረሱት ፓስወርድ አስገቡና "next" በሉት
6- ከዚያ "Encrypt entire drive" የሚለውን ሴሌክት በማድረግ "next" ማለት። በቃ አለቀ።ፍላሽ ዲስኩ በፓስውርድ ተቆለፈ።
ከዚህ በኋላ ያለ እናንት ሌላ ማንም ሰው ፍላሹን መጠቀም አይችልም።
ፍላሽ ዲስኩን መጠቀም ስትፈልጉ ኮምፒውተራችሁ ላይ ፍላሹን ደብል ክሊክ ስታደርጉ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል።ፓስወርድ በማስገባት መጠቀም ትችላላችሁ
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
👍61275